ERROR: The requested URL could not be retrieved ERROR The requested URL could not be retrieved While...

80
ገጽ 1 | እሑድ | ጥር 19 ቀን 2005 FREE PRESS FREE SPEECH FREE SPRIT | ነፃ ፕሬስ ነፃ ሐሳብ ነፃ መንፈስ የእሑድ እትም ጥር 19 ቀን 2005 ትኩስና ተጨማሪ መረጃዎችን በድረ ገጻችን ያገኛሉ www.ethiopianreporter.com ቅፅ 18 ቁጥር 23/1330 ጳጉሜን 6 ቀን 1987 ተመሠረተ ዋጋው ብር 10.00 2 ፎቶ በሪፖርተር/መስፍን ሰሎሞን በውድነህ ዘነበ በአዲስ አበባ ከተማ የመሬትና መሬት ነክ ቋሚ ንብረት ባለይዞታዎች ንብረታቸው በድጋሚ ተመዝግቦ አዲስ የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ሊሰጣቸው ነው:: የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር በመሬትና በመሬት ላይ የተገኘ ሀብት ዳግም ተመዝግቦ ለይዞታው ባለቤት አዲስ ደብተር መስጠት የሚያስችል ቅድመ ዝግጅት እየተጠናቀቀ መሆኑን ገልጿል:: በአዲስ አበባ የመሬት ይዞታ ድጋሚ ምዝገባ ሊካሄድ ነው የቦሌና የንፋስ ስልክ ባለይዞታዎች በቅድሚያ የይዞታ ማረጋገጫ ያገኛሉ ከግራ ወደ ቀኝ የመሬትና መሬት ነክ ቋሚ ንብረት ምዝገባ ኤጀንሲ ተጠባባቂ ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ከበደና የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስትር አቶ መኩርያ ኃይሌ ለጋዜጠኞችና ለመንግሥት የኮሙዩኒኬሽን ባለሙያዎች ማብራሪያ ሲሰጡ በዳዊት ታዬ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ሐበሻ አክሲዮን ማኅበርን ጨምሮ ለተለያዩ የግል ኩባንያዎች እሰጣለሁ ያለውን ብድር እንደማይሰጥ ማሳወቁ ተጠቆመ:: ባንኩ ለሐበሻ ሲሚንቶ ፋብሪካ 1.2 ቢሊዮን ብር ብድር ለመስጠት መስከረም 2003 ዓ.ም. የብድር ስምምነት ተፈራርሞ የነበረ ቢሆንም፣ አሁን ግን ይህንን ስምምነቱን የሚያጥፍ ሰርኩላል ማስተላለፉን የሪፖርተር ምንጮች ጠቁመዋል:: ልማት ባንክ ለሐበሻ ሲሚንቶና ለሌሎች ኩባንያዎች ፈቅዶ የነበረውን ብድር አጠፈ ወደ ክፍል 1 ገጽ 43 ዞሯል ወደ ክፍል 1 ገጽ 43 ዞሯል በዳዊት ታዬ በአዲስ አበባ ከተማ ለሚገነባው የቀላል ባቡር መስመር ማቋረጫ በተለያዩ አካባቢዎች መንገዶችንና አደባባዮችን እንዲገነቡለት መንግሥት ዓይኑን የቻይና ኩባንያዎች ላይ ጥሏል:: የአደባባዮችን ግንባታ ሊያከናውኑ ይችላሉ የተባሉ ኩባንያዎችን በመጋበዝ በድርድር ሥራውን ለመስጠት ከታሰበበት ጊዜ ወዲህ፣ መንገዱን በባለቤትነት የሚያሠራው የአዲስ አበባ አስተዳደር ከተለያዩ የቻይና ኩባንያዎች ጋር ለመነጋገር ዝግጅት እያደረገ መሆኑ ታውቋል:: አሁን ባለው የግንባታ ዋጋ ተመን ከምሥራቅ ወደ ምዕራብ ያለውን የባቡር መስመር ተከትለው የሚሠሩ የተሽከርካሪ መንገዶችና አደባባዮች አጠቃላይ ወጪ ከ2.6 ቢሊዮን ብር በላይ እንደሚገመት፣ የአዲስ አበባ መንገዶች ባለሥልጣን ዋና ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ፍቃዱ ኃይሌ የገለጹ ሲሆን፣ የቻይና ኩባንያዎች እንዲገነቡ ፍላጐት መኖሩን አስታውቀዋል:: የባቡር መስመሩን ለሚያቋርጡ መንገዶችና አደባባዮች ግንባታ የቻይና ኩባንያዎች እየተፈለጉ ነው 2.6 ቢሊዮን ብር ለሚፈጀው ለዚህ ፕሮጀክት ሲአርቢሲ አንዱ ዕጩ ሆኗል ወደ ክፍል 1 ገጽ 44 ዞሯል የስብሰባ ማዕከልነት ዕድልን ወደ ኢንቨስትመንት ማዕከልነት ዕድል እናሸጋግረው!

description

dsd

Transcript of ERROR: The requested URL could not be retrieved ERROR The requested URL could not be retrieved While...

Page 1: ERROR: The requested URL could not be retrieved ERROR The requested URL could not be retrieved While trying to process the request: TEXT HTTP/1.1 Host: Proxy-Connection: keep-alive

ገጽ 1 | እሑድ | ጥር 19 ቀን 2005

FREE PRESS FREE SPEECH FREE SPRIT | ነፃ ፕሬስ ነፃ ሐሳብ ነፃ መንፈስ

የእሑድ እትም

ጥር 19 ቀን 2005 ትኩስና ተጨማሪ መረጃዎችን በድረ ገጻችን ያገኛሉ www.ethiopianreporter.com

ቅፅ 18 ቁጥር 23/1330 ጳጉሜን 6 ቀን 1987 ተመሠረተ ዋጋው ብር 10.00

2

ፎቶ በ

ሪፖርተ

ር/መስፍ

ን ሰሎ

ሞን

በውድነህ ዘነበ

በአዲስ አበባ ከተማ የመሬትና መሬት ነክ ቋሚ ንብረት ባለይዞታዎች ንብረታቸው በድጋሚ ተመዝግቦ አዲስ የይዞታ ማረጋገጫ

ካርታ ሊሰጣቸው ነው::

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር በመሬትና በመሬት ላይ የተገኘ ሀብት ዳግም ተመዝግቦ ለይዞታው ባለቤት

አዲስ ደብተር መስጠት የሚያስችል ቅድመ ዝግጅት እየተጠናቀቀ መሆኑን ገልጿል::

በአዲስ አበባ የመሬት ይዞታ ድጋሚ ምዝገባ ሊካሄድ ነው

የቦሌና የንፋስ ስልክ ባለይዞታዎች በቅድሚያ የይዞታ ማረጋገጫ ያገኛሉ

ከግራ ወደ ቀኝ የመሬትና መሬት ነክ ቋሚ ንብረት ምዝገባ ኤጀንሲ ተጠባባቂ ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ከበደና የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስትር አቶ መኩርያ ኃይሌ ለጋዜጠኞችና ለመንግሥት የኮሙዩኒኬሽን ባለሙያዎች ማብራሪያ ሲሰጡ

በዳዊት ታዬ

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ሐበሻ አክሲዮን ማኅበርን ጨምሮ ለተለያዩ የግል ኩባንያዎች እሰጣለሁ ያለውን ብድር እንደማይሰጥ

ማሳወቁ ተጠቆመ::

ባንኩ ለሐበሻ ሲሚንቶ ፋብሪካ 1.2 ቢሊዮን ብር ብድር ለመስጠት መስከረም 2003 ዓ.ም. የብድር ስምምነት ተፈራርሞ

የነበረ ቢሆንም፣ አሁን ግን ይህንን ስምምነቱን የሚያጥፍ ሰርኩላል ማስተላለፉን የሪፖርተር ምንጮች ጠቁመዋል::

ልማት ባንክ ለሐበሻ ሲሚንቶና ለሌሎች ኩባንያዎች ፈቅዶ የነበረውን ብድር አጠፈ

ወደ ክፍል 1 ገጽ 43 ዞሯል

ወደ ክፍል 1 ገጽ 43 ዞሯል

በዳዊት ታዬ

በአዲስ አበባ ከተማ ለሚገነባው የቀላል ባቡር መስመር ማቋረጫ በተለያዩ አካባቢዎች መንገዶችንና አደባባዮችን እንዲገነቡለት መንግሥት ዓይኑን የቻይና ኩባንያዎች ላይ ጥሏል::

የአደባባዮችን ግንባታ ሊያከናውኑ ይችላሉ የተባሉ ኩባንያዎችን በመጋበዝ በድርድር ሥራውን ለመስጠት ከታሰበበት ጊዜ ወዲህ፣ መንገዱን በባለቤትነት የሚያሠራው የአዲስ አበባ አስተዳደር ከተለያዩ የቻይና ኩባንያዎች ጋር ለመነጋገር ዝግጅት እያደረገ መሆኑ ታውቋል::

አሁን ባለው የግንባታ ዋጋ ተመን ከምሥራቅ ወደ ምዕራብ ያለውን የባቡር መስመር ተከትለው የሚሠሩ የተሽከርካሪ መንገዶችና አደባባዮች አጠቃላይ ወጪ ከ2.6 ቢሊዮን ብር በላይ እንደሚገመት፣ የአዲስ አበባ መንገዶች ባለሥልጣን ዋና ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ፍቃዱ ኃይሌ የገለጹ ሲሆን፣ የቻይና ኩባንያዎች እንዲገነቡ ፍላጐት መኖሩን አስታውቀዋል::

የባቡር መስመሩን ለሚያቋርጡ መንገዶችና አደባባዮች ግንባታ የቻይና ኩባንያዎች እየተፈለጉ ነው

2.6 ቢሊዮን ብር ለሚፈጀው ለዚህ ፕሮጀክት ሲአርቢሲ

አንዱ ዕጩ ሆኗል

ወደ ክፍል 1 ገጽ 44 ዞሯል

የስብሰባ ማዕከልነት ዕድልን ወደ ኢንቨስትመንት ማዕከልነት ዕድል

እናሸጋግረው!

Page 2: ERROR: The requested URL could not be retrieved ERROR The requested URL could not be retrieved While trying to process the request: TEXT HTTP/1.1 Host: Proxy-Connection: keep-alive

ገጽ 2 | እሑድ ጥር 19 ቀን 2005

በጳጉሜን 6 1987 ተጀመረ በሳምንት ሁለት ጊዜ የሚታተም አድራሻ፡- ከቦሌ መድኃኒዓለም ወደ ብራስ ሆስፒታል በሚወስደው መንገድ ከቦሌ ኢንተርናሽናል ሆቴል አጠገብ ስልክ 0910-885206/ 011-661 61 79/85/87/011-8614339 ፋክስ: 011-661 61 89

አድራሻ፡- ቦሌ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 03 የቤት ቁጥር 2347 ፖስታ 7023 አ.አ ኢትዮጵያ

ማስታወቂያ ሽያጭና ስርጭት 0910 885206/ 011 6 61 61 79/ 85

[email protected] E-mail: [email protected]

Website: www.ethiopianreporter.com

ዋና ሥራ አስኪያጅ፡ አማረ አረጋዊማኔጂንግ ኤዲተር፡ መላኩ ደምሴዋና አዘጋጅ፡ ዘካሪያስ ስንታየሁየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 09/11/12 የቤት ቁ. 217

ከፍተኛ አዘጋጅ፡ ዳዊት ታዬ አዘጋጆች፡ ሔኖክ ያሬድ ጌታቸው ንጋቱ

ምሕረት ሞገስ ኃይሌ ሙሉ

ረዳት አዘጋጆች፡ ታደሰ ገ/ማርያም ምሕረት አስቻለው ታምሩ ጽጌ የማነ ናግሽ

ዋና ግራፊክ ዲዛይነር፡ ይበቃል ጌታሁንከፍተኛ ግራፊክ ዲዛይነር፡ ቴዎድሮስ ክብካብግራፊክ ዲዛይነሮች፡ ፀሐይ ታደሰ ፋሲካ ባልቻ እንዳለ ሰሎሞን ስሜነህ ሲሳይ ቢኒያም ግርማ ነፃነት ያዕቆብ ቤዛዬ ቴዎድሮስ

ዋና ፎቶ ግራፈር ናሆም ተሰፋዬፎቶ ግራፈሮች፡ ታምራት ጌታቸው መስፍን ሰሎሞን

ካርቱኒስት፡ ኤልያስ አረዳ

በሚዲያና ኮምዩኒኬሽንስ ሴንተር (ኤም.ሲ.ሲ) ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር

እየታተመ የሚወጣ ጋዜጣ

ከፍተኛ ሪፖርተሮች፡ ደረጀ ጠገናው ብርሃኑ ፈቃደ ውድነህ ዘነበ፣ ሰለሞን ጎሹሪፖርተር፡ ምዕራፍ ብርሃኔማርኬቲንግ ማናጀር፡ እንዳልካቸው ይማምሴልስ፡ ቤዛዊት ፀጋዬ' Hና Ó`T' w\¡ S<K<Ñ@�' IK=ና ከuደ፣ ብሩክ ቸርነትማስታወቂያ ፕሩፍሪደር፡መሳይ ሰይፉ፤ ኤፍሬም ገ/መስቀል፤ ዳዊት ወርቁኮምፒውተር ጽሑፍ፡ ብርቱካን አባተ፣ ሄለን ይታየው፣ ፍሬሕይወት ተሰማ፣ ማስታወቂያ ፅሁፍ እስከዳር ደጀኔ፣ መሠረት ወንድሙ፣ ራሔል ሻወልሕትመት ክትትል፡ ተስፋዬ መንገሻ፣ የየሱስወርቅ ማሞ፣ ገዛኸኝ ማንደፍሮዌብ ሳይት፡ ቤዛዊት ተስፋዬ፣ ቢኒያም ሐይሉ

ርእሰ አንቀጽ

እሑድ ጥር 19 ቀን 2005

ማስታ

ወቂያ

የስብሰባ ማዕከልነት ዕድልን ወደ ኢንቨስትመንት ማዕከልነት ዕድል

እናሸጋግረው! በ2005 ዓ.ም. ዓበይት ዓለም አቀፍና አኅጉር አቀፍ ስብሰባዎችና በዓሎች በኢትዮጵያ ይካሄዳሉ፣

ይከበራሉ:: የአፍሪካ ኅብረት አባል አገሮች የመሪዎች ስብሰባ፣ የአፍሪካ ኅብረት ሃምሳኛ ዓመት በዓል፣ የአጎአ (ከቀረጥና ከኮታ ነፃ ንግድ የሚጠቀሙ የአፍሪካ አገሮች ስብሰባ ከአሜሪካ ጋር)፣ የዓባይ ቀን በዓል ተጠቀሽ ናቸው:: ሦስቱም በአዲስ አበባ የሚከናወኑ ሲሆን፣ የዓባይ ተፋሰስ አገሮች የዓባይን ቀን በጋራ የሚያከብሩት ግን በባህር ዳር ነው::

እነዚህን በዓላትና ስብሰባዎች ለማሳያ ጠቃቀስን እንጂ፣ በኢትዮጵያ በርካታ ዓለም አቀፍና አኅጉር አቀፍ ስብሰባዎችና በዓሎች እንደሚካሄዱ ሁላችንም እናውቃለን:: በዚህ ጉዳይ ላይ ግን ሁላችንም በጋራ አንድ ጥያቄ እናንሳ:: ኢትዮጵያ ከእነዚህ በዓላትና ስብሰባዎች ዝግጅት ምን ትጠቀማለች?

ኢትዮጵያ ለስብሰባና ለበዓል ዝግጅት መመረጥዋ ሊያኮራን የሚገባ ነው:: ልናጠናክረውም ይገባል:: በዓላትና ስብሰባዎች በኢትዮጵያችን ሲካሄዱ በርካታ እንግዶች ስለሚመጡ ኢትዮጵያ ይበልጥ ትታወቃለች:: የውጭ ምንዛሪም ይመጣል:: በዓለምም አመኔታ እያገኘን እንሄዳለን:: ስለሆነም የስብሰባዎችና የበዓል ዝግጅቶች በኢትዮጵያ መካሄዳቸው ጠቃሚ ነው::

ጠቃሚ ነው ብለን ብቻ የምንተወው ሳይሆን ተጨማሪ በርካታ በዓላትና ስብሰባዎች በኢትዮጵያ እንዲካሄዱም ይበልጥ መጣር አለብን:: ዓለም አቀፍና አኅጉር አቀፍ የወጣቶች፣ የሴቶች፣ የስፖርተኞች፣ የአርቲስቶች፣ የቴክኖሎጂ ባለሙያዎች፣ የተመራማሪዎች፣ የሕክምና ባለሙያዎች፣ ወዘተ ስብሰባዎች በኢትዮጵያ እንዲሆኑ እንታገል:: ሌሎች አገሮችና መንግሥታትም አገራቸውን የስብሰባ፣ የበዓላትና የተለያዩ ጉዳዮች ማዕከል ለማድረግ እየታገሉ ናቸው:: በአንዳንድ ዘርፎችም እያሸነፉን ነው::

ኢትዮጵያ የአፍሪካ ኅብረት ማዕከል ስለሆነች የአፍሪካ ፓርላማ ኅብረት በደቡብ አፍሪካ እንዲሆን ተሟግታ ደቡብ አፍሪካ ወስዳለች:: የአፍሪካ ባንክ እኔ ዘንድ ይሁን ብላ ቱኒዚያ ወስዳለች:: በቅርቡም ታንዛኒያ የአፍሪካ የፀረ ሙስና ትግል ማዕከል እኔ ጋ ይሁን ብላ ወስዳለች:: ናይጄሪያም የአፍሪካ የወጣቶች ማዕከል እኔ ጋ ይሁን እያለች እየተሟገተች ነው፤ ልትወስደው ትችላለች:: ለምን እነሱ ዘንድ ሆነ አንልም አጋሮቻችን ናቸውና:: ነገር ግን ብዙ ትግል ካላደረግን ያለንንም ልንነጠቅ እንደምንችል በማወቅ አስቀድመን እንጠንቀቅ፣ እንታገል፣ ብቁና ንቁ እንሁን::

የበዓልና የስብሰባ ዝግጅት ማዕከልነታችንን ልናሳድገውና ልናጠናክረው የሚገባ ቢሆንም፣ ዋናው ራዕያችንና ፍላጎታችን ግን በዚህ ማቆም የለበትም:: ስትራቴጂያችን ይህን የበዓልና የስብሰባ ማዕከልነት ዕድል ተጠቅመን አገራችን ኢትዮጵያ የዓለምና የአኅጉሩ የኢንቨስትመንት ማዕከል ማድረግ ነው::

ኢትዮጵያ አገራችንን ከስብሰባ ማዕከልነት ወደ ኢንቨስትመንት ማዕከልነት እናሸጋግራት፣ እናሳድጋት:: የአፍሪካ ኅብረት ዓመታዊ ስብሰባ ሲካሄድና የአፍሪካ ኅብረት ሃምሳኛ ዓመት ሲከበር በዓሉን በተሳካ ሁኔታ ለማጠናከር ጥረት ከማድረጋችን ጎን ለጎን፣ የአፍሪካ ኢንቨስተሮች በኢትዮጵያ ኢንቨስት እንዲያደርጉ ከፍተኛ እንቅስቃሴ የምናደርግበትና የምናሳምንበት መድረክ ማድረግ አለብን::

አሜሪካ ከሰሃራ በታች የሚገኙ የአፍሪካ አገሮች ያለቀረጥና ያለኮታ ወደ አሜሪካ ኤክስፖርት እንዲያደርጉ ፈቅዳለች:: ይህ ድጋፍ አሁን ማቆም የነበረበት ቢሆንም እ.ኤ.አ. እስከ 2015 ድረስ አራዝማዋለች:: በርካታ አሜሪካዊያንና አፍሪካውያን የሚሳተፉበት ስብሰባ በአዲስ አበባችን በመጪው ክረምት ይካሄዳል:: ዓላማችን ግን ስብሰባውን ስለማዘጋጀትና ማሳካት ብቻ ሳይሆን፣ ከቀረጥ ነፃ የሆኑ ምርቶችን ለመላክ መረባረብ ብቻ ሳይሆን፣ አፍሪካውያንና አሜሪካዊያን ኢንቨስተሮች በኢትዮጵያ ኢንቨስት እንዲያደርጉ ለማሳመንና ለማሳካት የምንረባረብበት ሊሆን ይገባዋል::

የዓባይ ቀን በዓልም እንደዚሁ:: በዓሉን እናሳካ:: ግን የዓባይ አገሮች አጀንዳቸው በቂ የውኃ መጠቀም ብቻ ሳይሆን በጋራ የማደግና ንግድና ኢንቨስትመንት የማስፋፋት ስለሆነ ኑና ኢትዮጵያ ውስጥ ኢንቨስት አድርጉ፣ በጋራ እናልማ፣ በጋራ ድህነትን እናጥፋ እያልን ኢንቨስትመንት ማጠናከር አለብን:: የአፍሪካ ኅብረት (የአፍሪካ አንድነት ድርጅት) ሃምሳኛ ዓመት በኢትዮጵያ ስናከብር እስቲ በሃምሳ ዓመታት ውስጥ ምን ያህል የአፍሪካ ኢንቨስትመንት በኢትዮጵያ እንዳለ እንጠይቅ:: የለም ማለት ይቻላል:: ያለውም ሁለትና ሦስት ቢሆን ነው:: ያለፈው አልፏል:: አሁንም ኢትዮጵያ ይህንን በዓል ከስብሰባና ከበዓል ማዕከልነት ወደ ኢንቨስትመንት ማዕከልነት ማሸጋገሪያ ዕድል አድርጋ ትጠቀምበት::

የዳያስፖራ ኢትዮጵያውያን ስብሰባ ሲካሄድም እንደዚሁ ዳያስፖራ ኢትዮጵያውያን ከሚኖሩባቸውና ከሚሠሩባቸው አገሮች ኢንቨስተሮች ይዘው እንዲመጡ የምንመክርበት፣ የምናበረታታበትና ዕድልና አጋጣሚ የምንከፍትበት ስብሰባ መሆን አለበት:: እነሱ ራሳቸውም በአገራቸው ኢንቨስት እንዲያርጉ፣ በሚኖሩበት አገር የሚገኙ ባለሀብቶችም በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት እንዲያደርጉ የምንታገልበት መድረክ መሆን አለበት:: የስብሰባን መድረክ ወደ ኢንቨስትመንት መድረክ እንቀይረው::

ኢንቨስትመንት ስንል ግን ትክክለኛ፣ እውነተኛ፣ ሕጋዊና ልማታዊ ማለታችን ነው እንጂ፣ በኢንቨስተርነት ስም መጥቶ ኮንትሮባንድ የሚነግድ፣ ጥቁር ገበያ የሚያስፋፋ፣ ሕገወጥ ገንዘብ የሚያሸጋግርና ከኢትዮጵያ ባንክ እየተበደረና የኢትዮጵያን ሀብት እየተጠቀመ ሀብታም ነኝ የሚል በአገር የሚቀልድ ኢንቨስተመንት ማለታችን አይደለም::

ሀብቱን በኢትዮጵያ የሚያፈስ፣ ቴክኖሎጂ ወደ ኢትዮጵያ የሚያሸጋግር፣ የኢትዮጵያን ሕግና ሥርዓት የሚያከብር፣ ዘመናዊ ማኔጅመንት ይዞ የሚመጣና ሀብት ቀናሽ ሳይሆን ሀብት የሚጨምር ኢንቨስተር ብቻ ማለታችን ነው:: የውጭ ኢንቨስትመንት ስንል የውጭ ሀብት፣ ዕውቀትና ቴክኖሎጂ ማለታችን እንጂ የውጭ ቆዳና ቀለም ማለታችን አይደለም::

በአጠቃላይ ሲታይ ስብሰባዎችና በዓላት በኢትዮጵያ መዘጋጀታቸው እጅግ ጠቃሚ ነው:: ገንዘብ ያስገኛል፣ ቱሪዝም ያስፋፋል (ኮንፈረንስ ቱሪዝም)፣ የአገር ገጽታ ይቀይራል፣ ያሻሽላል ጠቃሚ ነው:: ነገር ግን ዘለቄታዊ ጥቅም የሚገኘው ከኢንቨስትመንት ነውና እነዚህን የስብሰባ አጋጣሚዎች ወደ ኢንቨስትመንት አጋጣሚዎች እንቀይራቸው:: አገራችን ውስጥ የሚካሄዱ ስብሰባዎችን ቀርቶ ውጭ አገር ለመሳተፍ የምንሄድባቸው ስብሰባዎችንም ኢንቨስተሮችን ለመሳብ እንጠቀምባቸው::

እንቅስቃሴያችን ግን በስትራቴጂ፣ በራዕይ፣ በዕቅድና በፖሊሲ የተደገፈ እንጂ ገጠመኝ መሆን የለበትም:: ይህንን በማድረግ የስብሰባ ማዕከልነት ዕድልን ወደ ኢንቨስትመንት ማዕከልነት ዕድል እናሸጋግረው::

Page 3: ERROR: The requested URL could not be retrieved ERROR The requested URL could not be retrieved While trying to process the request: TEXT HTTP/1.1 Host: Proxy-Connection: keep-alive

www.ethiopianreporter.com

ገጽ 3 | እሑድ | ጥር 19 ቀን 2005 ክፍል-1ማስታ

ወቂያ

ወደ ክፍል-1 ገጽ 5 ዞሯል

በዮሐንስ አንበርብር

ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞችን በማደራጀት በአገር አቀፍ ደረጃ ቀጣይነት ያለው ልማት ለማረጋገጥና የሥራ አጦችን ቁጥር ለመቀነስ በመንግሥት የተያዘው ዕቅድ፣ በኢንተርፕራይዞች የኪራይ ሰብሳቢነት አመለካከትና ተግባር ማነቆ እንደሆነበት የከተማና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ገለጸ:: የሚሰጣቸውን የመሬትና የብድር አቅርቦት እያመከኑ መሆኑንም የሚኒስቴሩ ሪፖርት ያስረዳል::

በዚህ ዘርፍ የተያዘውን ግብ የማስፈጸም ኃላፊነት የተሰጠው ሚኒስቴሩ በ2005 ዓ.ም. የስድስት ወራት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርቱ ላይ እንዳስቀመጠው፣ ኢንተርፕራይዞቹን የማቋቋምና የመደገፍ እንዲሁም የሥራ አጦችን ቁጥር የመቀነስ እንቅስቃሴው ከሞላ ጎደል በመልካም አፈጻጸም ላይ ይገኛል::

ይሁን እንጂ ኢንተርፕራይዞቹ የሚያገኙትን የብድርና የመሬት አቅርቦት እያመከኑ እንደሆነ ይህም ለዕቅዱ ተግባራዊነት ማነቆ እንደሆነ ይገልጻል:: ለአብነትም በስድስት ወራት ውስጥ 1.6 ቢሊዮን ብር ከኢንተርፕራይዞቹ መመለስ የሚገባው ቢሆንም መመለስ የቻሉት ግን ከግማሽ በታች 575 ሚሊዮን ብር ብቻ

እንደሆነ አስረድቷል::

ኢንተርፕራይዞቹ ካሉበት የጥቃቅንና አነስተኛ ደረጃ ለመሸጋገር የገንዘብ ቁጠባ ወሳኝ ጉዳይ ቢሆንም፣ በዚህ ረገድ የሚታይባቸውም ባህሪም ደካማ እንደሆነ ያስረዳል:: በግማሽ ዓመቱ በተያዘው ዕቅድ መሠረት 1.1 ቢሊዮን ብር መቆጠብ ሲገባቸው፣ የቆጠቡት ግን አሁንም ከግማሽ በታች 540.4 ሚሊዮን ብር እንደሆነ ሪፖርቱ ይገልጻል::

ሚኒስቴሩ ይህንን የኪራይ ሰብሳቢነት አስተሳሰብ ለመቅረፍ እያደረገ ካለው እንቅስቃሴ በተጨማሪ፣ ኢንተርፕራይዞችን የማደራጀትና የማቋቋም ተግባሩ ግን መቀጠል ተገቢ እንደሆነና ይህንንም እያደረገ እንደሆነ ያስረዳል::

በግማሽ ዓመቱ ውስጥም ወደ ሥራ ለሚገቡ 63,955 አዲስና ነባር አንቀሳቃሾች 1.6 ቢሊዮን ብር የብድር አገልግሎት ለማመቻቸት አቅዶ፣ 31,724 ለሚሆኑት የ1.02 ቢሊዮን ብር ብድር እንዳመቻቸ ሪፖርቱ ገልጿል::

የመሬት አቅርቦትን በተመለከተም በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ 1,382 ሔክታር ቦታና 2,138 ሼዶችን ለማዘጋጀት ታቅዶ 658.4 ሔክታር መሬትና 1,145 ሼዶች

ጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት የሚያገኙትን የመሬትና የብድር

አቅርቦት እያመከኑ መሆኑ ተጠቆመ

ከ1.6 ቢሊዮን ብር ውስጥ 575 ሚሊዮን ብር ብቻ መልሰዋል

በታምሩ ጽጌ

የቀድሞውን ፓትርያርክ አቡነ ጳውሎስን ሕልፈት ተከትሎ፣ ስድስተኛውን ፓትርያርክ ለመምረጥ ሰላማዊ የሽግግር ጊዜውን ለማደናቀፍ የሚገኙ ቡድኖችን፣ የመገናኛ ብዙኅንና ግለሰቦችን የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት አስጠነቀቀ::

የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባዔን በማሟላት የቤተ ክርስቲያኗ ቀኖና በሚያዘው መሠረት፣ ቤተ ክርስቲያኒቱን በመምራት በሕጉ መሠረት መንበሩን የሚጠብቁ አባት በመሰየም ቀጣይ ጉዞ ሰላማዊ ለማድረግ እየተሠራ ባለበት በአሀኑ ጊዜ፣ ከውስጥና ከውጭ ያሉ በጐ አመለካከት የሌላቸው ግለሰቦች አፍራሽ ተግባር እየፈጸሙ እንደሚገኙ ጽሕፈት ቤቱ አስታውቋል::

የስድስተኛውን ፓትርያርክ አሿሿም በሚመለከት ሕገ ደንብ ወጥቶ ምርጫውን ተግባራዊ ለማድረግ በእንቅስቃሴ ውስጥ መሆኑን የሚያውቁ አንዳንድ የመገናኛ ብዙኅን፣ ከውስጥ አፍራሽ ኃይሎች የሚቀበሉትን ፀረ ሰላምና ከእውነት የራቀ

አሉባልታ ከድረ ገጽ ያገኙ በማስመሰልና ‹‹ምንጮቻችን›› እያሉ በውጭና በአገር ውስጥ ያለውን ምዕመናን እያወናበዱ በሚገኙት ላይ፣ ቤተ ክህነት ክስ መመሥረቷን ጽሕፈት ቤቱ ገልጿል::

በአንድነትና በመደማመጥ መንፈስ እየሠራ የሚገኘውን ቅዱስ ሲኖዶስ፣ አሉባልታ በመንዛት ትርምስ እንዲፈጠር ለማድረግ የሚንቀሳቀሱት ቡድኖችም ሆኑ ግለሰቦች ከቃላት ያለፈ ተግባር መፈጸም የማይችሉ ቢሆንም፣ ዝም ብሎ መመልከቱ ድርጊታቸውን እንደመደገፍ ስለሚቆጠር፣ በቀጣይም በመገናኛ ብዙኅኑም ላይ ሆነ በግለሰቦቹ ላይ ዕርምጃ ለመውሰድ ቤተ ክህነት በዝግጅት ላይ መሆኗን፣ የቤተ ክርስቲያኗ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ እስክንድር ገብረ ክርስቶስ አስታውቀዋል::

ብፁአን ሊቃነ ጳጳሳት ወይም የሚመለከታቸው ኃላፊዎች ማብራሪያና መግለጫ ሳይሰጡ፣ ምስላቸውንና እነሱ እንደተናገሩ በማስመሰል በአንዳንድ ድረ

ቤተ ክህነት የፓትርያርክ ምርጫን ለማደናቀፍ የሚንቀሳቀሱትን

አስጠነቀቀችበአንዳንዶቹ ላይ ክስ መሥርታለች

አንዳንድ የመገናኛ ብዙኅን ከውስጥ አፍራሽ ኃይሎች የሚቀበሉትን ፀረ ሰላምና ከእውነት የራቀ አሉባልታ ከድረ ገጽ

ያገኙ በማስመሰልና ‹‹ምንጮቻችን›› እያሉ በውጭና በአገር ውስጥ ያለውን ምዕመናን እያወናበዱ በሚገኙት ላይ፣ ቤተ

ክህነት ክስ መመሥረቷን ጽሕፈት ቤቱ ገልጿል::

ወደ ክፍል-1 ገጽ 5 ዞሯል

Page 4: ERROR: The requested URL could not be retrieved ERROR The requested URL could not be retrieved While trying to process the request: TEXT HTTP/1.1 Host: Proxy-Connection: keep-alive

www.ethiopianreporter.com

ገጽ 4 | እሑድ ጥር 19 ቀን 2005ክፍል-1

ወደ ክፍል-1 ገጽ 43 ዞሯል

ወደ ክፍል-1 ገጽ 43 ዞሯል

በታምሩ ጽጌ

ዓባይ፣ አዋሽ፣ ተከዜና ሌሎች የቤት አውቶሞቢሎችን እየገጣጠመ ለገበያ ያቀርብ የነበረው ሆላንድ ካር ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ላይ፣ የፌዴሪል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት 5ኛ ፍትሐ ብሔር ችሎት የኪሳራ ውሳኔ ሰጠ::

ፍርድ ቤቱ የኪሳራ ውሳኔ የሰጠው የሆላንድ ካር ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ታደሰ ተሰማ ድርጅቱ መክሰሩን በመግለጽ፣ ከግለሰቦችም ሆነ ከባንክ የወሰደውን ገንዘብ መክፈል እንደማይችል ይፋ በማድረጉ ምክንያት በተመሠረተ የፍትሐ ብሔር ክስ ነው::

ፍርድ ቤቱ በውሳኔው እንዳብራራው፣ ውሳኔው በንግድ ሕግ ቁጥር 982 መሠረት ለጊዜው ተፈጻሚ ሊሆን ይገባል:: የድርጅቱን ኪሳራ የሚመረምሩ ዳኛና ንብረት ጠባቂ በፍርድ ቤቱ ዋና ሬጅስትራር በኩል ይሾማሉ:: በድርጅቱ ላይ የገንዘብ ጥያቄ ለሚያቀርቡም ኮሚቴ

እንዲቋቋም በማለት ትዕዛዝ ሰጥቷል::

ውሳኔው እንዲሰጥና ሆላንድ ካር ያለው ንብረት ታግዶና ተጠብቆ በሚሾመው ዳኛና ንብረት ጠባቂ ቁጥጥር እንዲደረግበት የተወሰነው ሲስተር አሻ ኮተቦ ደቅሲሶ የተባሉ ግለሰብ በ290 ሺሕ ብር ሊገዙ ለተስማሙት ተከዜ አውቶሞቢል ቅድሚያ 145 ሺሕ ብር ቢከፍሉም፣ ተሽከርካሪው ሳይረከቡ ድርጅቱ ከስሬያለሁ በማለቱ ምክንያት ጠበቃቸው አዳሙ ሽፈራው ክስ መሥርተዋል::

በርካታ ግለሰቦችና ድርጅቶች ቅድሚያ ከከፈሉ በኋላ ድርጅቱ መክሰሩን በማሳወቁ፣ ሁሉም በየግላቸው የድርጅቱ ንብረት እንዲታገድላቸው እየተሯሯጡ ባሉበት በአሁኑ ጊዜ፣ የድርጅቱ አካሄድ ትክክል አለመሆኑንና ለደንበኞቹ ተሽከርካሪዎቹን ማስረከብ አለመቻሉንና በ15 ቀናት ውስጥ የመክሰር ውሳኔ እንዲሰጥለት ለፍርድ ቤት ማመልከት ሲገባው፣ በግሉ ማድረጉን በመቃወም ‹‹የኪሳራ ውሳኔ ይሰጥልን›› ክስ በመቅረቡ ለሁሉም ጠያቂዎች ውሳኔው

ተላልፏል::

ለፍርድ ቤቱ ደንበኞች በድርጅቱ ላይ ያቀረቡት ጥያቄ ድርጅቱ መክሰሩን በሚዲያ ከገለጸ በኋላ ሲሆን፣ በተለይ ባንኮች ብድር ሲሰጡ በመያዣነት የያዙት ንብረት በቅድሚያ የመከፈል መብታቸው ቀሪ ሆኖ ዋስትና ካልወሰዱት ሌሎች ተበዳዮች ጋር እኩል ተሠልፈው እንዲያገኙ እንዲወሰንላቸው፣ የኪሳሪ መርማሪ ዳኛና ንብረት ጠባቂዎች እንዲሾሙላቸው ነበር:: ፍርድ ቤቱ ጥያቄውን ተቀብሎ ድርጅቱ እንዲቀርብ ጥሪ ቢያደርግም ሳይቀርብ በመቅረቱ በሌለበት እንዲታይ ብይን ከሰጠ በኋላ፣ በድርጅቱ ላይ የመክሰር ፍርድ ሊሰጥ ይገባል ወይስ አይገባም? የሚገባ ከሆነስ መርማሪ ዳኛና ንብረት ጠባቂ ሊሾም ይገባል ወይስ አይገባም? የሚለውን ጭብጥ ይዞ መመርመሩን ውሳኔው ያሳያል::

በድርጅቱ ላይ የመክሰር ፍርድ የመስጠት ሥልጣን የፍርድ ቤት መሆኑን ጠቅሶ፣ የመክሰር

በሆላንድ ካር ላይ ፍርድ ቤት የኪሳራ ውሳኔ ሰጠኪሳራ መርማሪ ዳኛና የተበዳዮች ኮሚቴ እንዲቋቋም ታዘዘ

ኢንጂነር ታደሰ ተሰማ

በታምሩ ጽጌ

የአዲስ አበባና የአካባቢያዊ ምርጫን በተመለከተ ለደጋፊዎቹ ለማስረዳት የግማሽ ቀን ስብሰባ ለማድረግ አስተዳደሩን ጠይቆ ከመከልከሉም በተጨማሪ፣ አመራሮቹ ለደኅንነታቸው እንደሚያሰጋቸውና የሕግ ከለላ እንዲደረግላቸው የኢትዮጵያ ራዕይ ፓርቲ (ኢራፓ) ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ደብዳቤ ጻፈ::

በፕሬዚዳንቱ አቶ ተሻለ ሰብሮ ተፈርሞ የወጣው መግለጫ እንደሚያስረዳው፣ ፓርቲው በ2005 ዓ.ም. የአካባቢና የከተሞች ምርጫ ቅድመ ዝግጅትን በሚመለከት የአዲስ አበባ አባላቱንና ደጋፊዎቹን፣ በአዋጅ ቁጥር 662/2002 መንፈስ ለማስረዳትና በቂ ግንዛቤ ለማስጨበጥ የግማሽ ቀን ስብሰባ የአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት የባህል መሰብሰቢያ አዳራሽ እንዲፈቀድለት ጠይቋል:: አስተዳደሩም አዳራሹ ነፃ መሆኑን ገልጾለታል::

በመጨረሻው ሰዓት ግን ለማስተናገድ የማይችል መሆኑን አስተዳደሩ በማስታወቁ፣ ስብሰባውን በኢራፓ ቢሮ ለማድረግ መገደዳቸውን ለጠቅላይ ሚኒስትሩ በጻፉት ደብዳቤ ገልጸዋል::

ፓርቲው በራሱ ቢሮ ስብሰባውን ከማድረጉ በፊት በሌሎች ቦታዎች አዳራሽ ለመከራየት ያደረገው ጥረት ‹‹ከስብሰባ ፈቃድ ሰጭ አካል ፈቃድ ይዛችሁ ኑ›› በመባሉ እንዳልተሳካላቸው አቶ ተሻለ ገልጸዋል:: የተለመደውን የቅብብሎሽ ታክቲክ በመጠቀም ለሕገ መንግሥታዊ የመድበለ ፓርቲ ሥርዓት ግንባታና ሰላማዊ የፖለቲካ አማራጭ ጤናማ እንቅስቃሴ እንዳይደረግ ማድረጋቸው አሳዛኝና አሳፋሪ መሆኑን ፕሬዚዳንቱ ተናግረዋል::

ኢራፓ ሰባት የአመራር አባላት የሚገኙበት

ኢራፓ የመሰብሰቢያ አዳራሽ መከልከሉንና ለደኅንነቱ መስጋቱን ለጠቅላይ ሚኒስትሩ አቤት አለ

ወደ ክፍል-1 ገጽ 43 ዞሯል

ወደ ክፍል-1 ገጽ 43 ዞሯል

አቶ ተሻለ ሰብሮ

አቶ ሬድዋን ሁሴን

በውድነህ ዘነበ

ራሳቸውን ያገለሉ ተቃዋሚ ፓርቲዎች በምርጫ ተሳተፉም አልተሳተፉ ኢሕአዴግ ትርፍም ኪሳራም እንደሌለውና ራሳቸውን ከምርጫ የሚያገሉትም የተደራጀ አጀንዳ የላቸውም ሲሉ፣ የኢሕአዴግ ምክር ቤት ኃላፊና የጠቅላይ ሚኒስትሩ የሕዝብ አደረጃጀትና የተሳትፎ አማካሪ ሚኒስትር አቶ ሬድዋን ሁሴን ገልጸዋል::

አቶ ሬድዋን ኢሕአዴግ በሚያዝያ 2005 ዓ.ም. በሚካሄደው የአካባቢና የማሟያ ምርጫ እያካሄደ ስላለው ዝግጅት መግለጫ በሰጡበት ወቅት፣ ራሳቸውን ከምርጫ በማግለልና ባለማግለል እየወላወሉ የሚገኙትን ፓርቲዎች ተችተዋል::

ቀደም ሲል ሰላሳ ሦስት ፓርቲዎች የጋራ አቋም በመያዝ ለመንግሥት 18 ጥያቄዎች አቅርበው፣ ጥያቄዎቹ የማይመለሱ ከሆኑ በምርጫው እንደማይወዳደሩ መግለጻቸው ይታወቃል::

ከእነዚህ ሰላሳ ሦስት ፓርቲዎች መካከል አምስት ፓርቲዎች አቋማቸውን

በመቀየር በምርጫው ለመሳተፍ ወስነው የምርጫ ምልክት ወስደዋል:: የተቀሩት 28 ፓርቲዎች የምርጫ ምልክትና ዕጩዎችን

ለማስመዝገብ ሦስት ቀን እየቀረው ሐሳባቸውን አልወጡም::

አቶ ሬድዋን እንደገለጹት፣ እነዚህ ፓርቲዎች ያቀረቧቸው ጥያቄዎች ቀደም ባሉት ምርጫዎች የተመለሱ፣ በሒደትም የሚመለሱና በፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ውስጥ ሊመለሱ የሚችሉ ናቸው:: ነገር ግን አቶ ሬድዋን እነዚህ 18 ጥያቄዎች ሽፋን እንጂ ትክክለኛ ምክንያት አይደሉም ይላሉ::

የምርጫ ዝግጅት እየተካሄደ ባለበት ወቅት የተወሰኑ ፓርቲዎች አንወዳደርም ማለታቸው በዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ሒደት ላይ የሚያመጣው ተፅዕኖ እንደሌለም አስታውቀዋል::

እንደሳቸው ገለጻ፣ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ለሕዝብ የሚያቀርቡት የተደራጀና በቂ ትንታኔ ያለው አጀንዳ የላቸውም:: ‹‹ከዚህ በተጨማሪም ፓርቲዎች ለወረዳና ለማሟያ ምርጫ የመሳተፍ ፍላጎት የላቸውም:: እነዚህ ተቃዋሚዎች የሚዋደቁት ፓርላማ ለመግባት ነው:: ሥራ ያለው ወረዳ ላይ በመሆኑ እሱን አይፈልጉትም፤›› ሲሉ

‹‹ራሳችንን ከምርጫ ልናገል ነው የሚሉ ተቃዋሚ ፓርቲዎች የተደራጀ አጀንዳ የላቸውም››

አቶ ሬድዋን ሁሴን

በውድነህ ዘነበ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ክልል ውስጥ አዲስ ለሚገነቡ ባለኮከብ ሆቴሎች ሊሰጥ ስለሚገባው የመሬት ደረጃ ረቂቅ መመርያ እየተዘጋጀ መሆኑን ምንጮች ገለጹ፡፡

ምንጮች እንደሚገልጹት፣ ባለአምስት ኮከብ ሆቴሎች ሊገነቡ የሚገባው በ50 ሺሕ ካሬ ሜትር መሬት፣ ባለአራት ኮከብ ሆቴሎች ሊገነቡ የሚገባው 20 ሺሕ ካሬ ሜትር መሬት ላይ መሆን እንዳለበት ረቂቁ ይገልጻል፡፡

ይህ ረቂቅ የተዘጋጀው በከተማው ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ሲሆን፣ መመርያው ገና በረቂቅ ደረጃ ላይ መሆኑን የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡ ቢሮው ይህንን ለማዘጋጀት የተነሳሳው በከተማው የሚገኙ ባለኮከብ ሆቴሎች ከተወሰኑት በስተቀር የተጣበበና በቂ ፓርኪንግ የሌላቸው በመሆኑ፣ በአገልግሎት አሰጣጥ በኩል ችግር በመፍጠሩ ነው ተብሏል፡፡

ነገር ግን በረቂቁ የሰፈረው ቦታ መጠነ ሰፊ ነው በማለት የከተማው የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ ምንጮች ይገልጻሉ፡፡ ምክንያቱም በወጡት በርካታ ሕጎች መሬት በድርድር አይሰጥም፡፡ በአሁኑ ወቅት በርካታ ቦታዎች እየቀረቡ ያሉት በጨረታ ሲሆን፣ ይህንን ያህል መሬት አዘጋጅቶ ለጨረታ ማቅረብ አስቸጋሪ ነው በሚል ነው ባለሙያዎቹ ረቂቁን በጥርጣሬ የሚያዩት፡፡

ካቢኔው ይህንን መመርያ የሚያፀድቀው ከሆነ የሚሰጠው መሬት በድርድር ሊቀርብ ይገባል፡፡ ይህ ሳይሆን መመርያው ቢፀድቅ ግን ከዚህ በኋላ በከተማው ውስጥ ሆቴል መገንባት የማይቻልበት ደረጃ ይደረሳል ሲሉ ሥጋታቸውን ይገልጻሉ፡፡

ለባለኮከብ ሆቴሎች የመሬት አሰጣጥ ደረጃ ረቂቅ መመርያ ተዘጋጀ

Page 5: ERROR: The requested URL could not be retrieved ERROR The requested URL could not be retrieved While trying to process the request: TEXT HTTP/1.1 Host: Proxy-Connection: keep-alive

www.ethiopianreporter.com

ገጽ 5 | እሑድ | ጥር 19 ቀን 2005 ክፍል-1

ከክፍል-1 ገጽ 3 የዞረ ከክፍል-1 ገጽ 3 የዞረ

ማስታ

ወቂያ

በውድነህ ዘነበ

ሕገወጥ የሆኑ ይዞታዎችን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለመፍታትና ከዚህ በኋላም ሕገወጥ የመሬት ወረራ እንዳይፈጠር የሚያስችሉ የሕግ ማዕቀፎች እየተዘጋጁ መሆኑ ተገለጸ:: ሕገወጥ የሆኑ ባለይዞታዎች ሕጋዊ የሚደረጉበት አሠራር ምርጫ ስለደረሰ የሚተገበር ሳይሆን፣ የከተማውን ችግር በዘላቂነት ለመፍታት ያለመ ነው ሲሉ የኢሕአዴግ ምክር ቤት ኃላፊ አቶ ሬድዋን ሁሴን አስታወቁ::

አቶ ሬድዋን ከትናንት በስቲያ በጽሕፈት ቤታቸው በሰጡት መግለጫ፣ ሕገወጦችን ሕጋዊ ማድረግ ኢሕአዴግ ከምርጫው ለመጠቀም አስቦ ነውን? የሚል ጥያቄ ቀርቦላቸው ነው ይህን ያሉት:: ‹‹ምርጫውንና ይህንን ተግባር የሚያገኛቸው ነገር የለም፤›› ብለዋል አቶ ሬድዋን::

ይህ የሕግ ማዕቀፍ እየተዘጋጀ ያለው በአገር አቀፍ ደረጃ ቢሆንም፣ በተለይ በአዲስ አበባ ከተማ ከ60 ሺሕ በላይ አባወራዎች መሬት በሕገወጥ መንገድ ገንብተው ይዞታ ይዘዋል:: እነዚህ ባለይዞታዎች ከ1960 ዓ.ም. ጀምሮ የነበሩ ሲሆን፣ የአዲስ አበባ አስተዳደር ችግሩን ለመፍታት ያወጣው ደንብ ተግባራዊ የሚደረገው ከ1988 ዓ.ም. እስከ 2003 ዓ.ም. ባሉት ላይ ነው::

እነዚህ ሕገወጦች ሕጋዊ የሚሆኑት በ1988 ዓ.ም.፣ በ1994 ዓ.ም.፣ በ1997 ዓ.ም. በተነሳ የአየር ፎቶግራፍ መሠረት ነው:: ይህ መረጃ ከወጣ በኋላ ኢሕአዴግ ምርጫው ስለደረሰ በመንግሥት በኩል የሚያካሂደው የምርጫ

ቅስቀሳ ነው በማለት የሚተቹ በርካቶች ናቸው::

ነገር ግን አቶ ሬድዋን ይህንን አይቀበሉትም:: አቶ ሬድዋን እንደገለጹት፣ የከተሞችን ችግር ለመፍታት ፓኬጅ ከተቀረፀ ሦስት ዓመት ሆኖታል:: የአፈጻጸሙ ሒደት እዚህ ጊዜ ላይ አደረሰው እንጂ ከምርጫው ጋር የሚያገናኘው ጉዳይ የለም ሲሉ አቶ ሬድዋን አስረድተዋል::

መንግሥት እነዚህን ሕገወጦች ሕጋዊ የሚያደርገው ግንባታው ከማስተር ፕላኑ ጋር ተጣጥሞ የሚቀጥል ከሆነና የተወሰነ ቅጣት ተጥሎባቸው ነው:: የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስትሩ አቶ መኩርያ ኃይሌ፣ በዚህ ሐሳብ ሙሉ በሙሉ በመስማማት ከዚህ በኋላ ሕገወጥነት እንዳይነግስ አሠራር ተዘርግቷል ይላሉ::

አቶ መኩርያ እንደሚሉት፣ በሕገወጥ መንገድ መሬት በወረራ የያዘው ሰው ብቻ ሳይሆን፣ ይህ ሕገወጥ ተግባር የተፈጸመበት አካባቢን የሚያስተዳድረው አመራርም ተጠያቂ ይሆናል:: ‹‹ጠበቅ ያለ ቅጣት ይጠብቃቸዋል፤›› ሲሉ አቶ መኩርያ አስታውቀዋል::

ነገር ግን ቀደም ሲል የተፈጠረውን ችግር ለመፍታት ከአባባቢ ልማት ፕላን ጋር እየተጣጣመ የሚተገበርበት አሠራር ተዘርግቷል ይላሉ አቶ መኩርያ::

ምንጮች እንደሚገልጹት፣ በሁሉም ከተሞች ከሦስት መቶ ሺሕ የማያንሱ ሕገወጥ ይዞታዎች ይገኛሉ:: እነዚህ ይዞታዎች ከአሥርት ዓመታት በላይ ዕድሜ ያስቆጠሩ በመሆኑ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ምላሽ ሰጥቶ ማለፍ ይበጃል የሚል ዕቅድ በመንግሥት መያዙ ተመልክቷል::

ሕገወጥ ባለይዞታዎችን ሕጋዊ ማድረግ ከምርጫው ጋር አያገናኘውም ተባለ

በታምሩ ጽጌ

የከንቲባ ኩማ አስተዳደር አዲስ አበባን መምራት ከጀመረ ጊዜ አንስቶ፣ የአዲስ አበባ ከተማን በዋና ሥራ አስኪያጅነት በመምራት ከአቶ መኩሪያ ኃይሌ ቀጥሎ ተሹመው የነበሩት አቶ ኃይሌ ፍስሐ፣ ከመሬት ንክኪ ጋር የማይገናኝ የሥራ ዘርፍ ዋና ሥራ አስኪያጅ ተደርገው መሾማቸው ተሰማ፡፡

ባለፉት ሁለት ሳምንታት ውስጥ የሹመት ደብዳቤ የደረሳቸው አቶ ፍስሐ፣ ከመሬት ውጭ ያሉ ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎቶችን ማለትም የውኃ፣ የእሳት፣ የቆሻሻ፣ የውበትና የመናፈሻ አገልግሎቶችን ጨምሮ በርካታ አገልግሎቶች የሚሰጥበት ዘርፍ ዋና ሥራ አስኪያጅ ተደርገው መሾማቸውን ምንጮች ተናግረዋል፡፡

ከመልካም አስተዳደር እጦት ጋር በተያያዘ በ2004 ዓ.ም. በተደረገ ግምገማ ከከተማው ዋና ሥራ አስኪያጅነታቸው ተነስተው፣ የመሬት ነክ ጉዳዮች ዘርፍ ምክትል ሥራ አስኪያጅ ሆነው ሲሠሩ መቆየታቸውን ምንጮቹ አክለዋል፡፡ አቶ ፍስሐ በወቅቱ በተደረገ ግምገማ እሳቸውን መገምገም በማይገባቸው አባል ተገምግመው ከዋና ሥራ አስኪያጅነታቸው ዝቅ በማድረግ እንዲሠሩ መደረጋቸው አግባብ እንዳልነበረ የገለጹት ምንጮቹ፣ አሁን የተመደቡበት የሥራ ዘርፍ ሁለተኛ ዲግሪያቸውን ከያዙበት የትምህርት ዘርፍ ጋር የሚገናኝ በመሆኑ ውጤታማ ሥራ ለመሥራት እንደሚያስችላቸው ግምታቸውን አስቀምጠዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ሥራ አስኪያጅ ከመሬት ንክኪ ነፃ የሆነ

ሹመት ተሰጣቸው

መዘጋጀታቸውን ይጠቁማል::

ለ260,876 አንቀሳቃሾች የ2.3 ቢሊዮን ብር የአገር ውስጥ የገበያ ትስስር ለመፍጠር ተይዞ የነበረው ዕቅድም 95,130 ለሚሆኑ አንቀሳቃሾች የ2.4 ቢሊዮን ብር የአገር ውስጥ ገበያ በመፍጠር መፈጸሙን ያስረዳል::

በተደረገው ጥረትም በግማሽ ዓመት ውስጥ ለ669,608 ሥራ አጦች የሥራ ዕድል መፈጠሩን የሚኒስቴሩ ሪፖርት ገልጿል::

ጥቃቅንና...ገጾችና የመገናኛ ብዙኅን እየተገለጸና እየተጻፈ መሆኑን የገለጹት ኃላፊው፣ ኃላፊነት በተሞላበት ሁኔታ በውጭም ሆነ በአገር ውስጥ ሕዝቡ ወደ ትርምስና አላስፈላጊ ሁኔታ ውስጥ እንዳይገባ የሚያደርጉትን አመስግነዋል:: ቤተ ክህነት ትክክለኛ መረጃ ለሕዝብ እንዲደርስ የምትፈልግና የምትደግፍ መሆኑን አክለው፣ ያልተባለን ተብሏል ብሎ ፎቶን በማስደገፍ ባገኙት ቦታ መለጠፍ የሚያስጠይቅ ከመሆኑም ባሻገር ተገቢ አለመሆኑንም አስረድተዋል::

ቤተ ክህነት...

Page 6: ERROR: The requested URL could not be retrieved ERROR The requested URL could not be retrieved While trying to process the request: TEXT HTTP/1.1 Host: Proxy-Connection: keep-alive

www.ethiopianreporter.com

ገጽ 6 | እሑድ ጥር 19 ቀን 2005ክፍል-1

ማስታ

ወቂያ

ማስታ

ወቂያ

ፖ ለ ቲ ካ

በየማነ ናግሽ

የምሥራቅ አፍሪካ በይነ መንግሥታት ድርጅት (ኢጋድ) በአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ስብሰባ ዋዜማ አስቸኳይ ስብሰባ በመጥራት፣ በክልሉ የፀጥታና የደኅንነት ሁኔታ ላይ መነጋገርና አንድ የጋራ አቋም ይዞ መግባት ያልተለመደ ክስተት አይደለም::

ባለፈው ዓመት በሸራተን አዲስ ላሊበላ አዳራሽ በተጠራው 22ኛው የመሪዎች አስቸኳይ ስብሰባ በወቅቱ መላ ሶማሊያን ለመቆጣጠር በመገስገስ ላይ የነበረው አልሸባብ የአካባቢው የፀጥታ ሥጋት ተደርጎ ነበር የታየው:: እሱን ለማስወገድ ደግሞ የመፍትሔ ሐሳብ ተይዞ ነበር ለአፍሪካ ኅብረት የቀረበው:: ሁለቱ ሱዳኖችን በተመለከተም እንዲሁ::

በወቅቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ሊቀመንበርነት የተመራው የኢጋድ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባ አስቸኳይ ብቻም አልነበረም:: አጣዳፊም ጭምር እንጂ:: ከ20 ዓመታት በላይ ደም ያፈሰሰው የደቡብ ሱዳን የመገንጠል ጥያቄ እልባት ያገኘው ሐምሌ 2003 ዓ.ም. ነበር:: ሆኖም ሱዳንን ለሁለት መክፈል ምክንያት በሆነው በወቅቱ በተካሄደው ሕዝበ ውሳኔ፣ የሁለቱ ሕዝቦች የዘመናት ቂምና ቁርሾ ያበቃል ተብሎ ተጠብቆ የነበረ ቢሆንም እንደተገመተው አልሆነም:: በአቢዬ የግዛት ይገባኛል ጥያቄና የነዳጅና የሀብት ክፍፍል በውዝፍ ያደሩ ጉዳዮች ስለነበሩ ሌላ አዲስ ጦርነት ለመቀስቀስ ዋና ምክንያት ሊሆኑ ችለዋል:: አጠቃላይ የአካባቢው ደህንነት ስጋት ተደርጎም ነበር የተፈራው::

ኢጋድም የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲፈረምና ሁለቱም ሱዳኖች በጠረጴዛ ዙርያ ችግራቸውን የሚፈቱበት ድርድር እንዲጀመር የሚል የመፍትሔ ሐሳብ ነበር ያቀረበው:: በሶማሊያ ጉዳይም ቢሆን ቀደም ሲል በኢትዮጵያ ወታደሮች የተበታተነው የእስላማዊ ፍርድ ቤቶች ኅብረት በአልሸባብ አማካይነት እንደገና እግር በመትከል ጉልበቱ እየጨመረና የሽግግር መንግሥቱን ህልውና የተፈታተነበት ወቅት ነበር::

እንደ የአካባቢው የሰላምና የፀጥታ ዋነኛ ተዋናይነቱ ሁለቱን ጉዳዮች አስመልክቶ

ኢጋድ እንደ መንገድ

በመወያየት የመፍትሔ ሐሳብ ኢጋድ በማቅረቡ፣ በኅብረቱ ተቀባይነት አግኝቶ ላለፈው አንድ ዓመት ተግባራዊ ተደርጓል::

በቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ (የወቅቱ የኢጋድ ሊቀመንበር) የተመራው የያኔው የኢጋድ የመሪዎች 20ኛ አስቸኳይ ስብሰባ አሚሶምና የኬንያ የፀጥታ ኃይሎች እያስመዘገቡት የነበረውን ድል በማድነቅ የኢትዮጵያን ወታደራዊም ሆነ

ፖለቲካዊ ድጋፍ የተጠየቀበት ወቅትም ነበር:: በሱዳንም በኩል ኢትዮጵያ በሁለቱ ሱዳኖች መካከል በተመድ ሥር ለሰፈረው ሰላም አስከባሪ ኃይል ወታደሮችና ቁሳቁስ ያዋጣች ሲሆን፣ የሁለቱም ሱዳኖች መሪዎች ወደ ውይይት እንዲመጡ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ በዓለም አቀፉ ማኅበረተሰብ ከፍተኛ ኃላፊነት ነበር የተሰጣቸው::

በድርጅቱ የሚኒስትሮች ምክር ቤትና የአገር

የሶማሊያ አዲሷ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፎውሲያ ዩሱፍና አቻቸው ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም በኢጋድ ስብሰባ ላይ

ፎቶ በ

ሪፖርተ

ር/ታምራት ጌ

ታቸው

Page 7: ERROR: The requested URL could not be retrieved ERROR The requested URL could not be retrieved While trying to process the request: TEXT HTTP/1.1 Host: Proxy-Connection: keep-alive

www.ethiopianreporter.com

ገጽ 7 | እሑድ | ጥር 19 ቀን 2005 ክፍል-1ማስታ

ወቂያ

ማስታ

ወቂያ

ፖ ለ ቲ ካመሪዎች ለተከታታይ ቀናት የተካሄደው የአምና ስብሰባ፣ በከፍተኛ ጭንቅና አሳሳቢነት የታጀበ ነበር:: የኢትዮጵያ መንግሥት በአካባቢው ሰላምና መረጋጋትን ለመፍጠር እንደ የጋራ መድረክ እየተጠቀመበት ያለው ኢጋድ፣ በወቅቱ የተቀመጡትን ግቦች በአመዛኙ ፈጽሟል ማለት ይቻላል:: ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ በወቅቱ እንደ የድርጅቱ ሊቀመንበር በሁለቱም አወዛጋቢ የፖለቲካ ጉዳዮች የሰላምና የድርድር መንገድ በመጠንሰስ፣ በሶማሊያም ታላቅ የማረጋጋት ስትራቴጂ በመቅረጽ ባለፈው አመት ተግባራዊ አድርገዋል::

አዲስ ሊቀመንበር - አዲስ ዜናዘንድሮም በተመሳሳይ ጊዜና ቦታ የተደረገው

46ኛው አስቸኳይ የኢጋድ ስብሰባ ዋነኛ አጀንዳ ሆነው የቀረቡት የሶማሊያና የሁለቱ ሱዳኖች የፖለቲከና የደህንነት ጉዳዮች ነበሩ:: በድርጅቱ የዚህ ዓመት ግምገማ መሠረት ከሞላ ጎደል ባለፈው ዓመት የታቀዱ ነገሮች መሳካታቸውን ማየት ነው:: ዘንድሮ የድርጅቱ አዳዲስ መሪዎችና አባል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች የተነጋገሩት በክልሉ ስላለው የደኅንነት ሥጋት ሳይሆን፣ ሥጋቱ የተወገደበትን አካሄድ እንዴት ዘላቂ ማድረግ ይቻላል የሚልና አንፃራዊ ሰላም በሰፈነበት ማግስት ነው::

ቀደም ሲል ኢትዮጵያ የኢጋድ መሪነቱን መያዟን ተከትሎ እንደ ድርጅቱ አሠራር፣ የአባል አገሮችን የመሪዎች ጉባዔ የሚመሩት ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ የነበሩ ሲሆን፣ የሚኒስትሮች ምክር ቤትን ደግሞ በወቅቱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የአሁኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ነበሩ:: የድርጅቱ መሪነት አሁንም በኢትዮጵያ እጅ እንዳለ በመሆኑ፣ የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ሕልፈትን ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው የተሾሙት አቶ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ የድርጅቱ ጉባዔ ሊቀመንበር ሆነዋል:: እንዲሁም ደግሞ አዲሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም የድርጅቱ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ሊቀመንበር ናቸው::

ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ሕይወታቸው በድንገት በማለፉ በአገርም ሆነ በአጠቃላይ በክልሉ የደኅንነት ክፍተት ይፈጠራል የሚል ሥጋት ተፈጥሮ የነበረ ቢሆንም፣ በኢጋድ አማካይነት

በአካባቢው ያከናወኑዋቸው የሰላምና የማረጋጋት ሥራዎች አሁንም ኢትዮጵያ የሰላም አምባሳደርና የክልሉ ልዕለ ኃያል ሆና እንድትታይ ያደረጋት ይመስላል::

በሶማሊያም ሆነ በሁለቱም ሱዳኖች በኩል የነበረውን የደኅንነት ችግር ለመቅረፍ በተደረገው የተሳካ ጥረት የኢትዮጵያና የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ስም አብሮ የሚነሳ ሆኗል::

ለዚህም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው ከተሾሙ ጊዜ የውጭ ዲፕሎማቶችን በማነጋገር የተጠመዱን ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ናቸው:: ዋናው አጅንዳውም ‹‹ኢትዮጵያ በአካባቢው ሰላም ለማስፈን ያደረገችው ጥረት ተጠናክሮ እንዲቀጥል እንፈልጋለን፣ እናግዛለንም፤›› በሚል ዙርያ ነው::

ለ20 ዓመታት ያህል መንግሥት አልባ በመሆን የሸብርተኝነት መናኸሪያ ሆና የምትታየው ሶማሊያ፣ ለመጀመርያ ጊዜ ከአክራሪው አልሸባብ ነፃ ወጥታ በነፃነት አዲስ ፕሬዚዳንት መምረጥ ችላለች:: ይህንኑ በማከናወን ላይ ያለው የሽግግር መንግሥት እዚህ ደረጃ የደረሰው በኢትዮጵያ ደጋፊነትና ጠባቂነት እንደሆነ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ይገነዘባል:: በሱዳንም በኩል በጠቅላይ ሚኒስትር መለስ የተጀመረው ሁለቱን ወንድም መሪዎች አቀራርቦ የማነጋገርና የማግባባት ሥራ በአዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ የቀጠለ ሲሆን፣ የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ሕይወት በድንገት ማለፉን ተከትሎ፣ ከጥቂት ወራት በኋላ ነበር ወሳኝ የተባለው ስምምነት በአዲስ አበባ ሊደረስ የቻለው:: አሁንም ከጥቂት ሳምንታት በፊት ስምምነቱ ተግባራዊ የሚሆንበት ድርድር እየቀጠለ ነው:: አንዳንድ አለመግባባቶች መከሰታቸው እየተናፈሰ ቢሆንም፣ በሁለቱ ሱዳኖች መካከል ያለው ሁኔታ ለክፋት እንደማይሰጥ ይነገራል::

ባለፈው ረቡዕ በሸራተን አዲስ የኢጋድ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባን ለመጀመርያ ጊዜ ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ሲመሩ፣ የድርጅቱ ዋና ፀሐፊ ኢንጂነር ማሕቡብ መአሊም በእንኳን ደህና መጡ ንግግራቸው ላይ፣ ‹‹የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው ከመሾምዎ በፊት በጤና ጥበቃ ያስመዘገቡትን ድል እናውቃለን:: አሁንም በእርስዎ አመራር ከፍተኛ ልምድ እንደምናገኝ እርግጠኛ ነኝ፤›› በሚል ነበር መሪነታቸውን እንዲረከቡ ግብዣ ያደረጉላቸው:: በሶማሊያና በሁለቱ ሱዳኖች ጉዳዮች የተቃኘን ስብሰባ የአጀንዳ አቅጣጫ አመላክተውም

መድረኩን ለዶ/ር ቴድሮስ አስረክበዋቸዋል::

የወቅቱ የኢጋድ ስብሰባ አጀንዳ በሶማሊያና በሱዳን ባለው ወቅታዊ ሁኔታ የሚያተኩር መሆኑን ከማብራራታቸው በፊት ግን ‹‹በሶማሊያ ያለው የፖለቲካና የደኅንነት መሻሻል›› ማሳያ ያሉት የሚስስ ምሜ ፈዊሰያ ዩሱፍ የሶማሊያ የመጀመርያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትርና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው መሾም ነበር:: ‹‹አሁን ሶማሊያ ወደ ዲሞክራሲ እያመራች ያለችው ከመጀመርያው የሴትና የወንድ እኩልነትን ሙሉ ዕውቅና በመስጠት ነው፤›› በማለት::

ሶማሊያን ወክለው የተገኙት ወይዘሮዋ፣ በአዲሱ የሶማሊያ ካቢኔ ትልቅ ሥልጣን የተሰጣቸው የመጀመርያ ሴት ሲሆኑ፣ አዲሱ የሶማሊያ ፓርላማ በዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ለመንቆለጳጰሱ አንዱ ምክንያት ሆኗል:: ዶ/ር ቴድሮስም ሁለቱንም የስብሰባው አጀንዳዎች ባብራሩበት የመክፈቻ ንግግራቸው፣ በዓለም በጦርነትና በመንግሥት አልባነት የምትታወቀው ሶማሊያ አዲስ ሕገ መንግሥት በማፅደቅዋ፣ አዲስ ፕሬዚዳንት በነፃነት በመምረጥዋና ሁሉንም አሳታፊ የሆነ ፓርላማ በማቋቋምዋ አሞካሽተዋል:: በኢጋድ በኩል ስለሶማሊያ እንዲህ ዓይነት የስኬት ወሬ ሲሰማ የመጀመርያ መሆኑ ነው::

ዶ/ር ቴድሮስ ቀጠል አድርገውም፣ በሁለቱም ሱዳኖች መካከል ስለተፈረመው ባለዘጠኝ ነጥቦች ስምምነትና መሪዎቹ ስምምነቱን ተግባራዊ ለማድረግ ስላላቸው ቁርጠኝነትና ዝግጅት ሳያስታውሱ አላለፉም::

ምን ቀረ?

ዶ/ር ቴድሮስ በዚሁ መክፈቻ ንግግራቸው ግን ስለስኬት ብቻ አልነበረም የተናገሩት:: በሁለቱም አካባቢዎች ስላሉት ያልተጠናቀቁ ጉዳዮችና ውዝፍ ችግሮችም አውስተዋል:: የሁለቱም አካባቢዎች የደኅንነት ጉዳይ የአጠቃላይ ክልሉ ሰላምና ደኅንነት የሚመለከት መሆኑን በመግለጽ:: በሶማሊያ በኩል የተወሰነው የአገሪቱ ክፍል አሁንም በአልሸባብ እጅ እንደሚገኝ፣ ያንን ሙሉ ለሙሉ ለማስለቀቅ ደግሞ የተጣመረ ክንድ እንደሚያስፈልግ፣ እንዲሁም ደግሞ የአልሸባብ መወገድ በራሱ ዘላቂ ሰላም የሚያመጣ አለመሆኑን ተናግረዋል:: በሶማሊያ የነበረው ቀውስ ትቶት ያለፈውን ሰቆቃና ድህነት ማስቆም እንደሚያስፈልግ፣ ተቋማትን መገንባት ለነገ ይደር የማይባል ሥራ መሆኑንም

አስምረውበታል::

በሁለቱም አካባቢዎች ላለፉት 20 ዓመታት የቆዩ አሰቃቂ ጦርነቶችና ደም መፋሰሶች ግን አንዱ ከሌላው ተነጥለው የሚታዩ እንዳልሆኑም ዶ/ር ቴድሮስ ገልጸዋል::

የአፍሪካ ኅብረት የሰላምና የፀጥታው ምክር ቤት ኮሚሽነር አምባሳደር ራማንቴ ላማምራ በበኩላቸው፣ ከኅብረቱ እይታ አንፃር ንግግር አድርገዋል:: ንግግራቸው በአብዛኛው በሶማሊያ ላይ ያተኮረ ሲሆን፣ የአልሸባብ መጥፋት አሁንም የመጨረሻ ግብ አለመሆኑንና ኢጋድ የሚወስናቸውን ማናቸውም የሰላምና የአስተዳደር ተግባራት ከዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ጋር አብሮ ለመሥራት የኅብረቱን ዝግጁነት አመላክተዋል::

የድርጅቱ ሚኒስትሮች ረዘም ላለ ጊዜ በዝግ ስብሰባቸው አንዳንድ ውሳኔዎች ያሳለፉ ሲሆን፣ በተለይ ግን ከአልሸባብ ነፃ በወጡ አካባቢዎች የተደረገው የተሳካ ወታደራዊ ዘመቻ በሚፈለገው የፖለቲካ ስትራቴጂ እየተሠራ አለመሆኑን፣ በአገሪቱ ሊቋቋም የታሰበውን ቀጣይነት ያለው መንግሥት የመመሥረት ፈተና የሚል ነው:: ይኼኛው ክፍተት አማፂዎችን እንዲያንሰራሩና አለመረጋጋትን ለመፍጠር ምክንያት እንዳይሆን በመስጋት፣ ባለፈው ዓመት የፀደቀው ትልቁ የማረጋጋት ስትራቴጂ (Grand Stabilization Strategy) በአገሪቱ መንግሥት ቅድሚያ እንዲሰጠውና መንግሥት ዝርዝር የማስፈጸሚያ ስትራቴጂ እንዲያዘጋጅም ድርጅቱ ጠይቋል::

ሁለቱም ሱዳኖች ለተፈረሙ ስምምነቶች በዚያው ልክ በአዎንታዊ መንፈስ ለተግባራዊነታቸው እንዲቆሙ ጥሪ አድርገዋል:: የተጀመረው ድርድር እንዲቀጥል፣ እያንዳንዳቸው ስምምነቶች ተግባራዊ የሚሆኑበት ቀነ ገደብ ጭምር እንዲኖርም ድርጅቱ ወስኗል::

ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ በአከባቢው ማተራመስ ስትራተጂ ይከተል የነበረው የኤርትራ መንግሥትን ከዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ለመነጠል የተጠቀሙትን ኢጋድን ነበር:: አሁን ደግሞ በአካባቢው በተለይ ደግሞ በሱዳንና በሶማሊያ የነበረውን የደኅንነት ሥጋት ለማስወገድ የኢትዮጵያ መንግሥት በኢጋድ በኩል የሠራው ሥራ እየተመሰገነበት ሲሆን፣ በዓለም አቀፉ ማኅበረሰብም ከፍተኛ ዕውቅና ያገኘበት ይመስላል::

Page 8: ERROR: The requested URL could not be retrieved ERROR The requested URL could not be retrieved While trying to process the request: TEXT HTTP/1.1 Host: Proxy-Connection: keep-alive

www.ethiopianreporter.com

ገጽ 8 | እሑድ ጥር 19 ቀን 2005ክፍል-1

ማስታወቂያ

Page 9: ERROR: The requested URL could not be retrieved ERROR The requested URL could not be retrieved While trying to process the request: TEXT HTTP/1.1 Host: Proxy-Connection: keep-alive

www.ethiopianreporter.com

ገጽ 9 | እሑድ | ጥር 19 ቀን 2005 ክፍል-1ማስታወቂያ

Page 10: ERROR: The requested URL could not be retrieved ERROR The requested URL could not be retrieved While trying to process the request: TEXT HTTP/1.1 Host: Proxy-Connection: keep-alive

www.ethiopianreporter.com

ገጽ 10 | እሑድ ጥር 19 ቀን 2005ክፍል-1

በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ በአስተማሪነት ያገለግላሉ:: የዶክትሬት ዲግሪያቸውንም እዚያው እየሠሩ ይገኛሉ:: በቀደሙት ጊዜያት የመልቲ ሞዳል ትራንስፖርት ሥርዓት ተግባራዊ ለማድረግ ሲታሰብ ጀምሮ እስከ ጅምር ሒደቱ ተሳትፎ አድርገዋል:: ሥርዓቱ አስተማማኝ ጥቅም እንዳለው ቁርጠኛ አቋም አላቸው:: አተገባበሩ ላይ የታዩ ችግሮችንም ይተቻሉ:: ችግሮቹን ካባባሱ ምክንያቶች አንዱ ደግሞ የንግዱ ማኅበረሰብ ጭምር ይሳተፍበታል ተብሎ ስምምነት የተደረገበት የጋራ ቴክኒካል ኮሚቴ በወቅቱ አለመቋቋሙ እንደሆነ ያምናሉ:: በመልቲ ሞዳል ልዩ ልዩ ጉዳዮች ዙርያ አቶ ለማ ጉዲሳን ብርሃኑ ፈቃደ አነጋግሯቸዋል::

ሪፖርተር፡- ከመልቲ ሞዳል ትራንስፖርት ሥርዓት ጋር የነበርዎ ግንኙነት ምን ይመስላል?

አቶ ለማ፡- ከሥርዓቱ ጋር የነበረኝ ግንኙነት በዋነኝነት የተጀመረው የቀድሞዎቹ የገቢዎች ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ ጉምሩክ ባለሥልጣንና የፌዴራል አገር ውስጥ ገቢ ባለሥልጣን አንድ ላይ ተዋህደው የአሁኑ የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን በተመሠረተበት በሐምሌ ወር 2003 ዓ.ም. የባለሥልጣኑ የጉምሩክ ሥነ ሥርዓት አፈጻጸም ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሆኜ ከተመደብኩበት ጊዜ አንስቶ ነው:: እንደአጋጣሚ ሆኖ በሞጆ የተገነባው ደረቅ ወደብም በዚያው ጊዜ አካባቢ ተጠናቆ ለአገልግሎት እየተዘጋጀ ስለነበር አገልግሎቱን ለማስተዋወቅ የትራንስፖርትና መገናኛ ሚኒስቴርና የደረቅ ወደብ አገልግሎት ድርጅት በአዳማ በመስከረም ወር 2001 ዓ.ም. ባካሄዱት አውደ ጥናት ላይ አንድ የመወያያ ጽሑፍ አቅርቤ ነበር:: በ1999 ዓ.ም. በኢትዮጵያና በጂቡቲ መንግሥታት መካከል የተፈረመው የመልቲ ሞዳል ትራንስፖርት ስምምነት የማስፈጸሚያ ስልቶች (Implementation Modalities) መካከል አንዱ የሆነው የኢትዮ-ጂቡቲ የጉምሩክ ትራንዚት ፕሮቶኮል ስምምነት በኅዳር 2001 ዓ.ም. ከተፈረመ በኋላ የኢትዮጵያ ወገን የቴክኒክ ኮሚቴ ሰብሳቢና የልኡካኑ መሪ ሆኜ ስሠራ ነበር:: በሞጆ ደረቅ ወደብና በሰመራ ደረቅ ወደብ ውስጥ ከደረቅ ወደብ ድርጅት ቀጥሎ ከሁሉም ተቋማት ቀድሞ የተደራጁትን የጉምሩክ ቢሮዎችና የአሠራር ሥርዓቶች በበላይነት አስተባብሬአለሁ:: በተጨማሪም የመልቲ ሞዳል ትራንስፖርት ሥርዓትና የደረቅ ወደብ አገልግሎት አተገባበርን በተመለከተ በማሪታይም ጉዳዮች ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አስተባባሪነት ተቋቁሞ በነበረው ብሔራዊ ግብረ ኃይል ውስጥም አባል ነበርኩ:: በመጨረሻም የምሥራቃዊና ደቡባዊ አፍሪካ አገሮች የጋራ ገበያ (ኮሜሳ) በተነደፈው የጋራ ገበያው የጉምሩክ

የትራንዚት ዋስትና (Regional Customs Transit Guarantee-RCTG) ለኢትዮ-ጂቡቱ የመልቲ ሞዳል ትራንስፖርት ሥርዓት ትግበራ ሊውል የሚችልበትን አግባብ በተመለከተ ከኮሜሳ ጽሕፈት ቤት ጋር በመቀናጀት ለጉምሩክ ሠራተኞችና የመልቲ ሞዳል ትራንስፖርት ሥርዓት ትግበራ ለሚመለከታቸው ባለድርሻ ወገኖች ሠራተኞች (ለኢትዮጵያ ንግድ መርከብ፣ ለባህር ትራንዚት፣ ለመድን ድርጅቶች፣ ለደረቅ ወደብና ለትራንዚት ድርጅቶች) በተዘጋጁ ሥልጠናዎች ላይ በአሠልጣኝነት ተሳትፌያለሁ::

ሪፖርተር፡- ከእነዚህ ልምዶችዎ በመነሳት የመልቲ ሞዳል ትራንስፖርት ሥርዓት መሠረታዊ ዓላማዎችና ጥቅሞቹ ምን ምን እንደሆኑ ቢገልጹልን?

አቶ ለማ፡- የመልቲ ሞዳል ትራንስፖርት ሥርዓት ማለት ሁለትና ከዚያ በላይ የሆኑ የማጓጓዣ ዜዴዎችን በመጠቀም ዕቃዎች ከመነሻቸው እስከ መድረሻቸው የሚጓጓዙበት ሥርዓት ነው:: ዓላማዎቹም ወጪዎችና ውጣውረዶች ሳይበዙ ዕቃዎችን በፍጥነትና በቀላሉ ማጓጓዝ ነው:: ከዚህ አንፃር ጥቅሞቹም ወጪ ቅነሳና ፍጥነት ናቸው::

ሪፖርተር፡- ከኢትዮጵያ አንፃር የመልቲ ሞዳል ትራንስፖርት ሥርዓትን መተግበር ወጪዎችን ለመቀነስና ለፍጥነት እንዴት ነው ሊያግዝ የሚችለው?

አቶ ለማ፡- የመልቲ ሞዳል ትራንስፖርት ሥርዓት ትግበራ ለኢትዮጵያ የሚያስገኛቸውን ጥቅሞች በዝርዝርና በግልጽ ልናውቅ የምንችለው አገሪቱ ለረጅም ጊዜ ስትጠቀምበት በነበረው የዩኒ ሞዳል ትራንስፖርት ሥርዓት ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን በደንብ ስንረዳ ነው:: እነዚህ ችግሮች አንደኛ እንደማጓጓዣና ክፍያ ያሉ የግዥ ሰነዶች በባንክ በኩል ሳይደርሱ ዕቃዎቹ ጂቡቲ ወደብ ይደርሳሉ:: በዩኒ ሞዳል አሠራር የአጓጓዡ ኃላፊነት ዕቃዎቹን ጂቡቲ ወደብ ማድረስ ብቻ ሲሆን፣ ዕቃዎቹን ከጂቡቲ ወደብ ወደ አገር ውስጥ ለማጓጓዝ የዕቃዎቹ ባለቤቶች ወደ ደንበኛ ባንኮቻቸው ቀርበው የሚፈለግባቸውን ክፍያ ከፈጸሙ በኋላ የዕቃ ባለቤትነታቸውን ማረጋገጥና ማረጋገጫውን ለጉምሩክ በማቅረብ ትራንዚት ማስፈቀድ ይኖርባቸዋል:: ሰነዶቹ ቀድመው በባንክ ካልደረሱ ይህን ማድረግ ስለማይቻል ዕቃዎቹ በወደብ ቆይተው ለከፍተኛ ወጪ ከመዳረጋቸውም በላይ በተጨማሪ ለተፈለጉለት ዓላማ በወቅቱ ስለማይደርሱ በዚህም ረገድ እንደገና ለሌላ ወጪ ይዳርጋሉ ማለት ነው:: ዕቃዎቹ በመልቲ ሞዳል ትራንስፖርት ሥርዓት ተጓጉዘው ከመጡ ግን መዳረሻቸው እስኪደርሱ ድረስ በመልቲ ሞዳል ኦፕሬተሩ ኃላፊነት ሥር ስለሚሆኑና የባንክ ክፍያም ሆነ የባለቤትነት ማረጋገጫ ሳይጠየቁ መዳረሻቸው ድረስ ሊጓጓዙ ስለሚችሉ በዩኒ ሞዳል

‹‹የመልቲ ሞዳል ሥርዓት ብቻውን የገቢና የወጪ ዕቃዎችን ችግሮች ይፈታል ተብሎ አይታሰብም››

አቶ ለማ ጉዲሳ፣ የመልቲ ሞዳል ከፍተኛ ባለሙያ

አሠራር ጊዜ ያለው ችግር አያጋጥማቸውም:: ሁለተኛ ለባንክና ለጉምሩክ የሚከፈል የገንዘብ እጥረት ሊያጋጥም ይችላል:: ሰነዶቹ ከዕቃዎቹ እኩል ወይም ቀድመው ቢደርሱም ለባንክ ብድር ክፍያ ወይም ለጉምሩክ ቀረጥና ታክስ የሚሆን የገንዘብ እጥረት ሲያጋጥማቸው አስመጪዎች ዕቃዎቻቸውን በወደብ አቆይተው ላላስፈላጊ ወጪ ሊዳረጉ ይችላሉ:: በመልቲ ሞዳል ትራንስፖርት ሥርዓት ከሆነ ግን ቢያንስ ዕቃዎቹ አገር ውስጥ እስኪደርሱ ድረስ ይህ ሥጋት አይኖርም:: የትራንዚት ማስፈቀጃ ሰነዶች ከኢትዮጵያ ወደ ጂቡቲ እስከሚላኩ ድረስ ጊዜ ይወስዳሉ::

በአሁኑ ወቅት ለረጅም ጊዜ በሥራ ላይ በቆየው የኢትዮ-ጂቡቲ የጉምሩክ ትራንዚት አሠራር መሠረት በዩኒ ሞዳል ትራንስፖርት ሥርዓት የሚመጡ ዕቃዎች ትራንዚት የሚፈቀደው አስመጪዎች ተገቢውን ፎርማሊቲ አሟልተውና ቀረጥና ታክስ ሲከፍሉ ወይም በቂ ዋስትና ሲያስይዙ ብቻ ነው:: አገር ውስጥ የሚሰጠው የትራንዚት ፈቃድ በጉምሩክ አስተላላፊው በኩል ለጂቡቲ አቻው በአየር ወይም በየብስ ተልኮ ጂቡቲ ጉምሩክ ካልደረሰ ዕቃው ከደቡቲ ወደብ ሊወጣ አይችልም:: በትራንስፖርት እጥረት ወይም በሌሎች ምክንያት የሰነድ መላላኩ ሒደት ከዘገየ አስመጪው ለተጨማሪ የወደብ ወጪ ይዳረጋል ማለት ነው:: በመልቲ ሞዳል ትራንስፖርት ሥርዓት ግን ከአገር ውስጥ ወደ ጂቡቲ የሚላክ ሰነድ ባለመኖሩ ይህ ችግር ይቀረፋል:: ሌሎቹ ችግሮች ዕቃዎቹ ወደብ መድረሳቸውን አለማወቅ፣ የትራንስፖርት እጥረት/የቅንጅት ማነስ፣ አንዳንድ አስመጪዎች በተለይም አንዳንድ የመንግሥት ተቋማት ዕቃዎቻቸውን ወደ አገር ለማስገባት ተገቢውን ትኩረት አለመስጠታቸው፣ በኢትዮጵያና በጂቡቲ ትራንዚተሮች መካከል አልፎ አልፎ የክፍያ ውዝግቦችና አለመግባባት፣ እንዲሁም ወደ አገር እንዳይገቡ የተገደቡ ዕቃዎች (ለምሳሌ በፍራንኮቫሉታ ሕጉ ምክንያት) ቶሎ ፈቃድ አለማግኘት ወይም ጭርሱኑ መከልከል በዩኒ ሞዳል ትራንስፖርት ሥርዓት ጊዜ የሚከሰቱና የመልቲ ሞዳል ትራንስፖርት ሥርዓቱ ትግበራ የሚያስቀራቸው ናቸው::

ሪፖርተር፡- ብዙዎቹ አስመጪዎችና የሥርዓቱ ተጠቃሚዎች ግን ሥርዓቱ የነበሩትን ችግሮች መቅረፍ ቀርቶ እንዲያውም አባብሶታል የሚል ወቀሳና ሮሮ እያቀረቡ ነው፤ ጥቅም ሳይሆን ጉዳቱ በዝቷል ከተባለ ከላይ ከዘረዘሩዋቸው ጥቅሞች ጋር አይቃረንም?

አቶ ለማ፡- ከላይ የዘረዘርኩዋቸው የመልቲ ሞዳል ትራንስፖርት ሥርዓት ጥቅሞች ንድፈ ሐሳባዊ ሳይሆን በተጨባጭ ተሞክሮዎች የተረጋገጡ ናቸው:: የመልቲ ሞዳል ትራንስፖርት ሥርዓት ትግበራ ለኢትዮጵያ ትራንዚት ዕቃዎች አስፈላጊነት ጥናት መካሄድ ከጀመረ ቢያንስ 15 ዓመት ይሆነዋል:: በህንድ፣ በኔፓል፣ በደቡብ አፍሪካና በመሳሰሉት ሥርዓቱ ተጠቃሚ አገሮች በመዘዋወር የተለያዩ ቡድኖች የተለያዩ ጥናቶችን አካሂደዋል:: ሁሉም እናቶችና ተሞክሮዎች ሥርዓቱ ለኢትዮጵያ ጠቃሚ እንደሆነ ደምድመዋል:: አንድም ጥናት አስፈላጊነቱንና ችግር ፈቺነቱን ሳይጠቁም አላለፈም:: ከዛሬ አራት ዓመት በፊት በፌዴራል የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን በኩል የመንግሥት ዕቃዎችን በጂቡቲ ወደብ መቆየት አስመልክቶ የተካሄደው ጥናት የመልቲ ሞዳል ትራንስፖርት ሥርዓትን ጠቀሜታ አመላክቷል:: የሥርዓቱን ጠቀሜታ የተረዱ በርካታ አስመጪዎችና የሥርዓቱ ተጠቃሚዎች ጭምር ሥርዓቱ በፍጥነት በአገራችን እንዲተገበር ሲወተውቱ እንደነበር አስታውሳለሁ:: ለዓለም አገሮች በተለይም ለወደብ አልባ አገሮች ጠቃሚነቱ የተረጋገጠ ሥርዓት ለኢትዮጵያ ብቻ የማይሠራበት ምክንያት ፈጽሞ አይታየኝም:: ደግሞም ትዝ የሚለኝ፣ በ2002 ዓ.ም. ሥርዓቱ በሞጆ ደረቅ ወደብ በመንግሥት ዕቃዎች ላይ በሙከራ ደረጃ ሲጀመር በአገሪቱ የዕቃዎች የጉምሩክ የትራንዚት ታሪክ ተመዝግቦ በማይታወቅ መልኩ ዕቃዎች ጂቡቲ ወደብ በደረሱ ከ10 ቀናት ባነሰ ጊዜ ውስጥ የትራንዚት ብቻ ሳይሆን የጉምሩክ ክሊራንስ ጭምር ተጠናቆባቸው፣ ባለቤቶቻቸው የተረከቡባቸው ሁኔታዎች ተመዝግበው ነበር:: የዕቃዎቹ ባለቤቶች የምስጋና ደብዳቤ ጭምር እስከመጻፍ ደርሰው ነበር:: ስለዚህ ሥርዓቱ እንደሥርዓት የሚነቀፍና እንዲያውም ችግሩን አባብሷል የሚያስብል አይመስለኝም:: ይልቁንም ሦስት ጥያቄዎች ቢነሱ በትራንዚት ዕቃዎች አገልግሎት

ፎቶ በ

ሪፖርተ

ር/ታምራት ጌ

ታቸው

Page 11: ERROR: The requested URL could not be retrieved ERROR The requested URL could not be retrieved While trying to process the request: TEXT HTTP/1.1 Host: Proxy-Connection: keep-alive

www.ethiopianreporter.com

ገጽ 11 | እሑድ | ጥር 19 ቀን 2005 ክፍል-1ማስታ

ወቂያ

አሰጣጥ ዙሪያ እየተስተዋሉ ስላሉት ችግሮችና መንስዔዎቻቸው ግንዛቤ ሊያስጨብጡ የሚችሉ ይመስለኛል:: እነሱም አንደኛ በመልቲ ሞዳል ትራንስፖርት ሥርዓት ትግበራ ብቻ ሁሉንም የትራንዚት ዕቃዎች ችግር መፍታት ይቻላል ወይ? ሁለተኛ የመልቲ ሞዳል ትራንስፖርት ሥርዓቱ በአግባቡና መተግበር በነበረበት መልኩ ተተግብሯል ወይ? ሦስተኛ የሥርዓቱስ ወሰን (Scope) በደንብ ታውቋል ወይ? የሚሉት ናቸው:: መቆየትና ለአላስፈላጊ ወጪዎች መዳረግ መንስዔዎችን ለይቶ መፍትሔዎችንም ለማፈላለግ ይረዳሉ ብዬ አስባለሁ::

የመጀመርያውን ጥያቄ በተመለከተ የኢትዮጵያ የትራንዚት ዕቃዎች ችግሮች የመልቲ ሞዳል ትራንስፖርት ሥርዓቱን በመተግበር ብቻ ሙሉ በሙሉ ይቀረፋሉ የሚል አስተያየት የለኝም:: የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በከፍተኛ ፍጥነት በማደግ ላይ ይገኛል:: ለኢኮኖሚው ማደግ ከፍተኛ ሚና የተጫወቱት ግብዓቶችና የካፒታል ዕቃዎች ደግሞ በአብዛኛው የሚመረቱት በአገር ውስጥ ሳይሆኑ በብዛት ከውጭ የሚገቡት ናቸው:: ኢኮኖሚው ሲያድግና የሕዝብ ቁጥር ሲጨምር ፍላጎት እንደሚጨምር የታወቀ ነው:: ፍላጎቱን የሚያሟሉ የልማትም ሆነ የፍጆታ ዕቃዎች በአገር ውስጥ እስካልተመረቱ ድረስ ከውጭ መግባታቸው አይቀሬ ነው::

ለምሳሌ በ1985 ዓ.ም. 600 ሚሊዮን ብር ወይም 290 ሚሊዮን ዶላር ያህል ብቻ ከጉምሩክ ቀረጥና ታክስ ተሰብስቦ የነበረ ሲሆን፣ በአሁኑ ጊዜ ግን ከ40 ቢሊዮን ብር ወይም ከሁለት ቢሊዮን ዶላር በላይ እንደሚደርስ ይገመታል:: ይህም በኢንቨስትመንትና በኤክስፖርት ማበረታቻነት የሚሰጠውን (ሳይሰበስብ የሚቀረውን) ሳይጨምር ማለት ነው:: ይህም ከሚሰበሰበው የሚያንስ አይሆንም:: ከዚህ አንፃር መጠየቅ ያለበት ፋሲሊቲዎቹ፣ ቴክኖሎጂዎቹ፣ ዕውቀቱና ቅድመ ዝግጅቶቹ በሙሉ በተመጣጣኝ መልኩ አድገዋል ወይ? የሚል ነው:: ማጓጓዣዎች፣ የጉምሩክ ማስተናገጃ ሥፍራዎች፣ የዕቃ መጫኛና ማውረጃ መሣሪያዎች፣ የመገናኛ ዘዴዎች፣ መጋዘኖች፣ ወደቦች ወዘተ. የተወሰነ ለውጥ ተደርጐባቸው ይሆናል:: በበቂ መጠንና ሁኔታ

አለመስፋፋታቸው ግን ይታወቃል:: የኢኮኖሚ ብሎም የውጭ ንግድ ዕድገቱ ስኬት ነው፤ አገልግሎት አሰጣጡም ከንግድ ዕድገቱ ጋር እኩል መራመድ ካልቻለ የስኬታችን ሰለባ ልንሆን እንችላለን:: ስኬቱ ተመልሶ ሥጋት ይሆናል:: ለዚህ አንድ ምሳሌ ላንሳ በቀድሞው የአዲስ አበባ ላጋር ጉምሩክ ውስጥ ያሉት መጋዘኖችና የጉምሩክ ማስተናገጃ ሥፍራዎች የተገነቡት በአፄ ምኒልክ ዘመነ መንግሥት ማለት፣ የኢትዮ-ጂቡቲ የባቡር መስመር በተዘረጋበት ጊዜ የነበረውን የውጭ ንግድ ለማስተናገድ ነበር:: ለአንድ ክፍለ ዘመን ያህል ምንም ትርጉም ያለው ለውጥ ሳይደረግበት ቆይቶ ገቢና ወጪ ዕቃዎችን ፈጽሞ ማስተናገድ በማያስችል ደረጃ ላይ ከደረሰ በኋላ ነው:: የአዲስ አበባ ላጋር ጉምሩክ በ1995 ዓ.ም. መጨረሻ ላይ አሁን ወደሚገኝበት ቃሊቲ (ኮሜት ግቢ) የተዛወረው:: በዚያን ጊዜ ማለትም በ1995 መጋዘኖቹ፣ ግቢው፣ ቢሮዎቹ፣ ሌሎች አገልግሎት መስጫ መሣርያዎችና ሥፍራዎች በተወሰነ መልኩም ቢሆን ይበቁ ነበር:: ከ10 ዓመት በኋላ ዛሬ ላይ ሆነን ስንመለከተው ግን በቂና ተመጣጣኝ እንዳልሆነና መጨናነቅ እንደሚታይበት ይገለጻል::

ሪፖርተር፡- ስለዚህ መልቲ ሞዳል ትራንስፖርትም በራሱ በቂ አይደለም ማለት ነው? ከጥቅሙ የበዙ ችግሮች ይታዩበታልና እዚህስ ላይ ምን ይላሉ?

አቶ ለማ፡- ይህ እንግዲህ የሚያሳየን የመልቲ ሞዳል ትራንስፖርት ሥርዓቱ እንደ ሥርዓት ጠቃሚ ቢሆንም፣ ብቻውን ሁሉንም የገቢና ወጪ ዕቃዎችን ችግሮች ይፈታል ተብሎ መታሰብ እንደሌለበት ነው:: የመልቲ ሞዳል ትራንስፖርት ሥርዓቱ አተገባበር ችግር የለበትም ወይ የሚለውን ሁለተኛውን ጥያቄ በተመለከተም አፈጻጸሙ ላይ አንዳንድ መሠረታዊ ችግሮች ይስተዋላሉ:: አሳታፊነቱ ላይ ውስንነት ይታይበታል:: የሥርዓቱ ተጠቃሚዎች ይሆናሉ የተባሉት አስመጪዎች፣ ላኪዎች፣ አጓጓዦች፣ ትራዚተሮችና ሌሎች ባለድርሻ ወገኖች በበቂ ሁኔታ እየተሳተፉበት አይመስለኝም:: ለዚህም ነው አንዳንዶቹ ለአገር ጥቅም ሲባል የተዘረጋ ሥርዓት ሳይሆን ሊጐዳቸው ታስቦ የመጣ አድርገው የሚመለከቱት:: በኢትዮጵያና በጂቡቲ

መንግሥታት መካከል በ1999 ዓ.ም. በተፈረመው የመልቲ ሞዳል ትራንስፖርት ሥርዓት ትግበራ ስምምነት መሠረት የስምምነቱን አፈጻጸም የሚከታተል የጋራ ቴክኒካል ኮሚቴ እንደሚቋቋምና በቴክኒክ ኮሚቴው ውስጥ የሁለቱ አገሮች የንግድ ምክር ቤቶች አባላት እንደሚሆኑ ተጠቁሞ ነበር:: ይህ የጋራ ኮሚቴ እስከ ቅርብ ጊዜ ደረስ አልተቋቋመም ነበር:: አሁን ተቋቁሞ እንደሆነ አላውቅም:: ኮሚቴው ተቋቁሞ የንግድ ምክር ቤቶቹ ቢሳተፉበት ኖሮ የንግድ ማኅበረሰቡ በእነሱ በኩል ስለሥርዓቱ እንዲያውቅና እንዲመክርበት ማድረግ ይቻል ነበር:: ኮሚቴው እንዲቋቋም በኢትዮጵያ (በማሪታይም ጉዳዮች ባለሥልጣን) በኩል ጥረት ተደርጐ እንደነበር አስታውሳለሁ፤ ነገር ግን እስካሁን ተቋቁሞ ሥራ የጀመረ አይመስለኝም:: የመልቲ ሞዳል ትራንስፖርት ሥርዓቱ በአንድ አገር ጥረት ብቻ ሳይሆን የትራንዚት አገሩንም (የጂቡቲውን) ተሳትፎ ይጠይቃል:: ከዚህ አንፃር ከሁለቱ አሮች ጉምሩኮች ውጭ ሌሎቹ ባለድርሻ አካላት የጠበቀና ወቅታዊ ግንኙነት እያደረጉ ያሉ አይመስለኝም:: የጋራ ቴክኒካል ኮሚቴው ቢቋቋም ኖሮ ይህንንም መከታተል ይቻል ነበር::

ሌላው በሁለቱ አገሮች የመልቲ ሞዳል ትራንስፖርት ሥርዓት የትግበራ ስምምነት መሠረት የሁለቱ አገሮች ጉምሩኮች አንድ ወጥ የትራንዚት ሰነድ (Single Administrative Document - SAD) እንደሚጠቀሙና ይህም ኮሜሳ የትራንዚት ሰነድ መሠረት እንደሚሆን ተቀምጧል:: የኮሜሳ የትራንዚት ሰነድ ደግሞ ለየጭነቱ የጉምሩክ ቀረጥና ታክስ እንደሚሠሩ ያመለክታል:: በየጭነቱ ቀረጥና ታክስ ማስላት ደግሞ ጊዜ ይወስዳል:: ምክንያቱም የታሪፍ ምደባና የዋጋ ትመና ሥራ ውስጥ ስለማያስገባ:: ጊዜ መውሰድ ብቻ ሳይሆን ታሪፍ ለመመደብና ዋጋ ለመተመን የሚያስችሉ ዝርዝር የዕቃ መግለጫና የዋጋ ሰነደች እንዲቀርቡ የግድ ይላል:: ይህ ከመልቲ ሞዳል ትራንስፖርት ሥርዓት የወጪ ቅነሳና የፍጥነት መርህ ጋር አይጣጣምም::

በተባበሩት መንግሥታት የመልቲ ሞዳል ወደ ክፍል-1 ገጽ 35 ዞሯል

Page 12: ERROR: The requested URL could not be retrieved ERROR The requested URL could not be retrieved While trying to process the request: TEXT HTTP/1.1 Host: Proxy-Connection: keep-alive

www.ethiopianreporter.com

ገጽ 12 | እሑድ ጥር 19 ቀን 2005ክፍል-1

በብርሃኑ ፈቃደ

በአዳማ ከተማ 50 ሺሕ ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ተንጣልሎ ቢዋይዲ በሚል ስያሜ F3 የተባሉ መኪኖችን መገጣጠም የጀመረው በጥረት ኢንተርናሽናል ኃላፊነቱ የተወሰነ ኩባንያ፣ ከዚሁ የቻይና መኪና አምራች ከሆነው ቢዋዲ ኩባንያ ጋር ያደረገውን ስምምነት ተከትሎ መኪኖቹን ለኢትዮጵያ ገበያ ማቅረብ መጀመሩን ይፋ አድርጓል::

ባለፈው ረቡዕ በአዳማ የሚገኘውንና ከ50 ሺሕ ካሬው ላይ በሰባት ሺሕ ላይ ያሳረፈው መገጣጠሚያ ፋብሪካውን ለጋዜጠኞች ያስጎበኘው በጥረት ኢንተርናሽናል፣ አሁን ባለው አቅሙ አራት መኪኖችን በቀን እየገጣጠመ ለገበያ የማቅረብ ሥራ መጀመሩን አስታውቋል:: የኩባንያው ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ካሳኑን አድማሱ እንዳስታወቁት፣ በቻይናና በዓለም ገበያዎች ከፍተኛ ሽያጭ ያስመዘገቡት ቢዋይዲ F3 መኪኖች በጥንካሬም በጥራትም የኢትዮጵያ ገበያን እንደሚመጥኑ በማመን ከኩባንያው ጋር ስምምነት እንዳደረጉና መገጣጠሙን እንደጀመሩ ገልጸዋል::

በዓመት ከሰባት ሺሕ ያላነሱ መኪኖችን የመገጣጠም አቅም ያለው ፋብሪካቸው፣ የሚገጣጥማቸው አዲሶቹ ተሽከርካሪዎች በቻይና በተለይ ለታክሲ ሥራ የሚያገለግሉ ጠንካሮች መሆናቸውን ይናገራሉ:: ምንም እንኳ በዓመት ሰባት ሺሕ ይገጣጥማል ቢባልም፣ አሁን በመነሻ አቅሙ 17 ሠራተኞችን ይዞ በቀን አራት መኪኖችን በመገጣጠም ላይ የሚገኘው በጥረት ቢዋይዲ፣ ለገበያ ያቀረባቸውን ተሽከርካሪዎች ወዲያውኑ ለተጠቃሚዎች የሚያስተላልፍበት አሠራር እንዳለው አስታውቋል:: ለሽያጭ የሚቀርቡት መኪኖች የታርጋና የቦሎ አቅርቦቶችን አሟልተው እንደሆነም ተገልጿል::

ክፍያ ፈጽመው ወዲያውኑ መውሰድ የሚቻሉት መኪኖች F3 በሚባለው ስያሜያቸው ጂአይ እንዲሁም ጂኤልአይ በሚሉ ሞዴሎች ለገበያ የወጡ ናቸው:: ጂአይ ሞዴል መኪኖች ዋጋቸው 419 ሺሕ ብር ሲሆን፣ ጂኤልአይ የተባሉት ደግሞ 439 ሺሕ ብር ያወጣሉ:: ሁለቱም 1.5 ሲሲ የፈረስ ጉልበት አላቸው::

በአንድ ሊትር ነዳጅ አሥራ ስድስት ኪሎ ሜትር እንደሚጋልቡም ታውቋል::

መኪኖችን ከመገጣጠም ባሻገር የሽያጭና የጥገና ማዕከላትን በአገሪቱ ዋና ዋና ከተሞች እንደሚከፍት ያስታወቀው ኩባንያው፣ ወደፊት የዱቤ ሽያጭ እንደሚጀምርም የሽያጭ ክፍል ኃላፊው አቶ ደሳለኝ ብርሃኑ ይፋ አድርገዋል::

የመገጣጠሚያ ፋብሪካው ሥራ አስኪያጅ አቶ ቢንያም ወርቅአለማየሁ፣ መኪኖቹ በአራት መስመሮች የመገጣጠም ሥራቸው እንደሚጠናቀቅ ገልጸው፣ በእያንዳንዱ ሒደትም የኢንስፔክሽን ሥራዎች የሚከናወኑ መሆናቸውን አስታውቀዋል:: ይህ መሆኑ ደግሞ መኪኖቹ የቴክኒክ ብቃት ደረጃቸውን ሙሉ ለሙሉ በማረጋገጥ አስተማማኝ እንዲሆኑ ለማስቻልና ለደንበኛውም እንከን የሌላቸውን መኪኖች ለማቅረብ ያስችላል ተብሎ ነው ብለዋል:: በመሬት ያላቸውን ከፍታ ጨምሮ በፍጥነት እየተንደረደሩ ባሉበት ቅጽበት ያለ ችግር መታጠፍ ይችላሉ የተባሉት እነዚህ መኪኖች፣ የሁለት ዓመት ዋስትና እንደሚሰጥባቸውም አቶ ካሳሁን አስታውቀዋል::

በቻይና መኪና ኢንዱስትሪና በሽያጭ ትልቅ ቦታ ካላቸው አንዱ የሆነው ቢዋይዲ በመላው ዓለም ካሉት ከ20 በላይ ፋብሪካዎች ውስጥ በግብፅና በሱዳን የሚገኙትን ቀጥሎ በኢትዮጵያ የከፈተው ሦስተኛው የአፍሪካ ፋብሪካው ሲሆን፣

ወደፊት የመኪና ክፍሎችን ከማስመጣትና ከመገጣጠም ባሻገር የመኪናው አካል ቅርፅ የሚያወጡ የ‹‹ሞልድ›› ማሽኖችንም ለማምጣት እንደሚታሰብ ተገልጿል::

እ.ኤ.አ. በ1995 የተቋቋመው ቢዋይዲ ከመኪና ቀድሞ የተሰማራበት ሥራ ባትሪዎችን ማምረቱ ላይ ሲሆን፣ በዚህም ኖኪያን ጨምሮ የተለያዩ ኩባንያዎች ደንበኞቹ ናቸው:: ወደ መኪናው ምርት ፊቱን ካዞረ በኋላም አሜሪካና አውሮፓን ጨምሮ በበርካታ አገሮች የሚነዱ አሥር ያህል ሞዴሎችን በማምረት ላይ ይገኛል::

ከቢዋይዲ ጋር የተጣመረው በጥረት ኢንተርናሽናል በበኩሉ የኮንስትራክሽን ዕቃዎችንና የተለያዩ ተሽከርካሪዎችን በማስመጣት ሥራ ላይ የቆየ ሲሆን፣ ከዚህ ቀደም Fo የተባሉ ባለአንድ ሲሲ መኪኖችን ከቢዋይዲ እያስመጣ መሸጡም ታውቋል::

በአሥር ሚሊዮን ብር መነሻ ካፒታል ሥራ የጀመረው በጥረት ኢንተርናሽናል በአሁኑ ጊዜ ከ40 ሚሊዮን ብር ያላነሰ የመንቀሳቀሻ ካፒታል እንዳለው አቶ ካሳሁን አስታውቀዋል:: መኪና በመገጣጠም ኢንዱስትሪ ውስጥ የመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽንን ጨምሮ የኢንዶውመንት ድርጅቶችና፣ የግል ኩባንያዎች እየተስፋፉ የመጡ ሲሆን፣ ከስሮ ከገበያ የወጣው ሆላንድ ካር እንዲሁም ሊፋን ሞተርስ በቀዳሚነት ወደ ገበያው እንደገቡ ይታወቃል::

ቢዋይዲ የተባለው የቻይና ኩባንያ የመኪና መገጣጠሚያ በመክፈት ኢንዱስትሪውን ተቀላቀለ

በዳዊት ታዬ

በአዲስ አበባ ከመርካቶ ቀጥሎ በየዕለቱ በሚሊዮን የሚገመት የገንዘብ ዝውውር ይደረግበታል ተብሎ የሚታመንበት አካባቢ ቢኖር የአፍሪካ ጐዳና ወይም የቦሌ መስመር ነው:: ካለፈው አንድ ዓመት ወዲህ ግን በዚህ መስመር የቢዝነስ እንቅስቃሴ እንደቀድሞው አይደለም:: ምክንያቱ ደግሞ ከመስቀል አደባባይ ቦሌ ቀለበት መንገድ ድረስ ያለው የ4.2 ኪሎ ሜትር የመንገድ ግንባታ መጀመር ነው:: ከማለዳ እስከ ምሽት ተሽከርካሪዎች የማያጡት የከተማዋ የቢዝነስ ስፍራ እንቅስቃሴ መደብዘዝ ከጀመረ ወዲህ ብዙዎች የቀድሞ ቢዝነሳቸውን እየሠሩ አይደለም:: የመንገድ ግንባታው በዚህ አካባቢ ባሉ ቢዝነሶች ላይ ካስከተለው ጉዳት ባለፈ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በከተማችን ለተፈጠረውም የትራፊክ መጨናነቅ ምክንያት ሆኗል::

ወትሮም ቢሆን ከፍተኛ የትራፊክ መጨናነቅ ካለባቸው የከተማው መንገዶች መካከል አንዱ ከቦሌ መስቀል አደባባይ ያለው መንገድ ነው:: በተመሳሳይ ከመስቀል አደባባይ ወደ ቃሊቲ የሚዘልቀው መንገድም በትራፊክ መጨናነቅ ከሚታይባቸው የከተማችን መንገዶች ውስጥ ይጠቀሳል:: እነዚህ መንገዶች ሁሌም የትራፊክ መጨናነቅ የሚታይባቸው የተለየ ምክንያት አለ::

የቦሌ መንገድ አገሪቱ ከሌላው ዓለም ጋር

የምትገናኝበት መግቢያና መውጪያ ሲሆን፣ የቃሊቲው መንገድ ደግሞ የአገሪቱ ገቢና ወጪ ምርቶች መግቢያ በር ሆኖ መገኘቱ ነው::

በተለይ ከአገር ውስጥም ሆነ ከመላው ዓለም በአውሮፕላን የሚገቡና የሚወጡ ዜጐች የቦሌ መንገድን ዘወትር መጠቀማቸው፣ መንገዱ 24 ሰዓት የትራፊክ ፍሰት እንዲኖረው አድርጓል::

ያሳለፍነው ዓመት የኢትዮጵያ አየር መንገድ መረጃ እንደሚጠቁመው፣ ከ3.5 ሚሊዮን በላይ መንገደኞችን አስተናግዷል:: የሌሎች አየር መንገዶችም በተመሳሳይ በርካታ መንገደኞችን ወደ አዲስ አበባ አስገብተዋል፤ ይዘውም በረዋል:: ሁሉም አየር መንገዶች ያመጧቸውና የሚወስዷቸው መንገደኞች ይህንን መንገድ

መጠቀማቸው የቦሌ መንገድን የትራፊክ ፍሰት ጫና ከፍተኛ እንዲሆን አድርጐታል::

የአዲስ አበባ መንገዶች ባለሥልጣን ዋና ሥራ አስኪያጅ ኢንጅነር ፍቃዱ ኃይሌም ይህንን እውነት ያረጋግጣሉ:: የቦሌ መስመር ከፍተኛ የሆነ ጭነት የነበረበት መሆኑ ለግንባታ መዘጋቱም የዚያኑ ያህል ጉዳት አምጥቷል::

በዚህ መንገድ ለአገልግሎት የበቁ ዘመናዊ ሕንፃዎች ከምድር ቤት እስከ መጨረሻው ሕንፃ ወለል ድረስ ያሉትን ቢሮዎች በሺዎች ለሚቆጠሩ የንግድ ተቋማት አገልግሎት በመዋላቸው፣ የቦሌ መንገድ የሚፈሱት ተሽከርካሪዎች ከወትሮው የበለጠ እንዲሆኑ አድርጓል::

በጌቱ ገለቴ፣ በደንበል፣ በፍሬንድሺፕ፣ በዲኤችገዳና በሌሎችም ሕንፃዎች የንግድ እንቅስቃሴያቸውን የሚያካሂዱ ድርጅቶች ተሽከርካሪዎች ብቻ ሳይሆን ወደእነዚህ ሕንፃዎች ያሉ አገልግሎቶችን ለማግኘት የሚመጡት ደንበኞች አብዛኛዎቹ ተሽከርካሪዎችን ይዘው የሚገለገሉ በመሆናቸው፣ መንገዱ የተጨናነቀ ትራፊክ እንዲኖረው አስተዋጽኦ አድርገዋል:: ይህም በዚህ መስመር ላይ በሺዎች የሚቆጠሩ የንግድ ተቋማት አሉ:: ትላልቅ ሆቴሎች አሉ፤ በተለይ በከፍተኛ ገንዘብ የሚንቀሳቀሱ ናቸው የሚባሉ:: የሁሉም ባንኮች ቅርንጫፎችም በዚሁ መንገድ ዳርቻ ይታያሉ::

በዚህ መንገድ ቀድሞ የሞቀ ገበያ ይታይባቸው

የንግድ እንቅስቃሴው ላይ ጫና እያሳደረ ያለው የመንገድ ግንባታ

ወደ ክፍል-1 ገጽ 29 ዞሯል

በአዳማ የሚገኘው መገጣጠሚያ ፋብሪካ

ቢዋይዲ F3

Page 13: ERROR: The requested URL could not be retrieved ERROR The requested URL could not be retrieved While trying to process the request: TEXT HTTP/1.1 Host: Proxy-Connection: keep-alive

www.ethiopianreporter.com

ገጽ 13 | እሑድ | ጥር 19 ቀን 2005 ክፍል-1ማስታ

ወቂያ

ማስታወቂያ

በናታን ዳዊት

የራሴ የሚሉት ቤት የሌላቸው በርካታ ወዳጆች አሉኝ:: ጐጆ የመቀለስ አቅም ያላቸውም ሆኑ የሌላቸው እኩል ቤት ተከራይተው ይኖራሉ:: ከእነዚህ ወዳጆቼ መካከል አንዱ ከሦስት ዓመት በፊት ትዳር ሲይዝ ጐጆ መውጫ ብሎ ባለአንድ መኝታ ቤት ኮንዶሚኒየም በአንድ ሺሕ ብር ተከራይቶ ነበር ኑሮ የጀመረው::

ይህ ወዳጄ አሁንም በዚሁ ኮንዶሚኒየም ቤት ውስጥ ይኖራል:: ለቤቱ የሚከፍለው ኪራይ ግን ከዛሬ ሦስት ዓመት በፊት እንደነበረው አይደለም:: ባላሰበውና ባልጠበቀው ጊዜ ሦስት ጊዜ ‹‹የዋጋ ማስተካከያ›› ተደርጐበታል:: በዚህ ‹‹የዋጋ ማስተካከያ›› መሠረት ዛሬ ለዚያው የኮንዶሚኒየም ቤት ሦስት ሺሕ ብር እየከፈለ ይገኛል:: በዚህ ሦስት ዓመት ጊዜ ውስጥ ወርሐዊ ገቢው ብዙም ፈቀቅ ያለ አይደለም:: ግን ክፈል የተባለውን እየከፈለ እየኖረ ነው::

እንዲህ ዓይነት አጋጣሚዎችን እያስተናገዱ ያሉ የአዲስ አባ ከተማ ነዋሪዎች ቁጥር ቀላል አይደለም:: ከሚቀጥለው ወር ጀምሮ የቤት ኪራይ ጨምሬያለሁ ለሚል አከራይ ‹‹ለምን?›› እና ‹‹እንዴት?›› ብሎ ሊፎክር የሚቃጣ ተከራይ፣ ምላሹን ያውቃልና የሆዴን በሆዴ ብሎ አንጀቱ እያረረ ፀጥ ይላል::

በአንድ ሺሕ ብር ኪራይ የገባበት ቤት በሦስት ዓመት ሦስት ሺሕ ብር እንዲከፍል የተገደደው ወዳጄ፣ ከደመወዙ እኩሌታ በላይ የሚሆነውን ለቤት ኪራይ እየገበረ በመኖሩ እጅግ ቢማረርም፣ አማራጭ ስለሌለው ምክንያት አልባውን ጭማሪ

በምኞት የተቀለሱ ጐጆዎች

ለመሆን የሚያስችሉ ሙከራዎችን አድርጓል::

አብዛኛው የአዲስ አበባ ነዋሪ ቤት ለምቦሳ የሚባልበትን ቀን ይናፍቃል:: ይህንን ምኞቱን ከዳር ለማድረስ ግን አልቻለም:: ተስፋ የተጣለበት የኮንዶሚኒየም ቤት ማግኘት መቻል በራሱ ዕድለኛ መሆንን እየጠየቀ ነው:: በሚሊዮን የሚቆጠሩ ነዋሪዎች ቤት ፈላጊ በሆኑበት ከተማ፣ ለእያንዳንዱ ቤት የሚቀልስበት ቦታ መስጠት የማይቻል መሆኑንም ሁሉም ይረዳል::

አሁን ባለንበት ደረጃ የከተማዋን የቤት ፈላጊዎች ፍላጐት ለማሟላት የጋራ መኖርያ ቤቶች ቀዳሚ ምርጫ ናቸው:: ሆኖም ይህንንም ለማግኘት በቂ ግንባታ የለም:: ሌላው ቀርቶ የዛሬ ስምንት ዓመት አካባቢ ኮንዶሚኒየም ቤት እንፈልጋለን ብለው ከተመዘገቡት ግማሽ ሚሊዮን ከሚጠጉ የከተማው ነዋሪዎች፣ ግማሽ ያህሉ እንኳን አላገኙም::

በዚህ ሁኔታ የቆየው የከተማው ነዋሪ 40/60 የሚል የቤት ልማት ፕሮጀክት መጣ ሲባል፣ ከዚህስ መጠቀም እችላለሁ ብሎ ተስፋ ያላደረገ ቤት አልባ አልነበረም:: ስለዚህ ፕሮጀክት ብዙ ብዙ ተብሎ መሀል ላይ ወሬው ጠፋ:: በዚህ ፕሮጀክት ተጠቃሚ ለመሆን ምዝገባ ከመጀመሩ በፊት መቆጠብ የጀመሩ ሁሉ ነበሩ:: ሆኖም ምዝገባው ከዛሬ ነገ ይጀመራል እየተባለ ዛሬ ደርሰናል:: ቆየት ብሎም 20/80 የሚባል አሠራር ሊጀመር ነው የሚል ወሬ ተናፈሰ:: ይህም ቢሆን ምን ደረጃ ላይ እንዳለ ለማወቅ አስቸጋሪ ሆነ:: በዚህ ጉዳይ የተብራራ ነገር ካለመኖሩም በላይ በጉዳዩ ላይ ተጨባጭ ነገር የሚሰጥም ጠፋ::

ልብ አንጠልጣይ ሆነው የከተማዋን ቤት ፈላጊ ተስፋ የሰጡ ፕሮጀክቶች ምን ደረጃ ላይ እንዳሉ ለማወቅ ባልተቻለበት ሁኔታ ላይ እያለን፣ አሁን ደግሞ በማኅበር ተደራጅቶ ቤት መገንባት የሚቻል መሆኑ ተደመጠ::

ባለፈው ዓመትና እያጋመስን በምንገኘው 2005 ዓ.ም. የሰማናቸው የመንግሥት ዕቅዶች አንዳቸውም መሬት ላይ ሳይውሉ አዲስ አሠራር

ሊመጣ ነው እየተባለ፣ ቤት ፈላጊው ሁሉ በምኞት ቤት እየቀለሰ በመንፈስ ባለቤት ሆኖ የአከራዮችን ኪስ እያደለበ ነው::

የከተማዋን የቤት ፍላጐት ለማሟላት የታሰቡት ሦስቱም ዓይነት ዘዴዎች መልካም ስለመሆናቸው አይካዱም:: ጥያቄ የሚነሳው ግን አፈጻጸሙ ምን ያህል ተግባራዊ ሆኗል የሚለው ጉዳይ ሲታይ ነው:: ከዛሬ ነገ ለውጥ ይመጣል እየተባለ ሲጠበቅ ከሥር ከሥር አከራዮች የሚቆልሉት የቤት ኪራይ ለብዙዎች ራስ ምታት እየሆነ መጥቷል:: በተለይ ለጭማሪው የሚሰጠው ምክንያት ግልጽ አይደለም:: አጨማመሩም ቢሆን እጅግ የሚገርም ሲሆን፣ የተከራዩን አቅም ለማገናዘብ እንኳ አይሞከርም::

መንግሥትም ቤት ለመገንባት ለሌሎች አማራጮች በር የማይከፍትና በራሱ ዕቅዶች መጓዝን ከመረጠ እንኳን፣ ዕቅዶቹን ቶሎ መሬት ላይ ለማዋል ብርታት ሊኖረው ይገባል:: ዕቅድ ብቻውን ግብ አይሆንም::

በዕቅድ ብቻ የሚባክኑ ጊዜዎችን ማሰብ ያስፈልጋል:: በተለይ በኮንስትራክሽን ግንባታ አንዲትም ቀን ብትሆን የሚያስከፍለው ዋጋ ይታወቃል:: ዛሬ 100 ሺሕ ብር ይጨርስ የነበረ ግንባታ ነገ በከፍተኛ ሁኔታ ይጨምራልና:: በዕቅድ ያሉ ሥራዎችን ማቆየቱን የሚፈጥረውን ጫና ጭምር ከግምት ማስገባት ያስፈልጋል::

ከዚህም በተጨማሪ መጠለያ መሠረታዊ ከሚባሉ የሰው ልጅ ፍላጐቶች አንዱ ስለሆነ ማንኛውም ዜጋ በአገሩ ቤት የማግኘት መብቱ የተጠበቀ መሆን ይገባዋል:: ዜጐች በመንግሥት ላይ ከሚያነሱት የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች መካከል አንዱ መጠለያ ያለማግኘታቸው ጉዳይ ሲሆን፣ ይህንን አንገብጋቢ ጥያቄ በአፋጣኝ መመለስ ለመንግሥትም እፎይታን ይፈጥራል:: መንግሥት ደግሞ ሁሉንም የዜጐች ችግር በራሱ መፍታት ስለማይችል፣ እንደዚህ ዓይነት የማኅበር ቤቶች ነዋሪዎች እንዲሠሩ ሁኔታውን ማመቻቸት ይጠበቅበታል::

መቀበል ግድ ሆኖበታል::

ነገር ግን የመጨረሻዋ ጭማሪ ከተደረገበት ጊዜ ወዲህ ቤት ለመሥራት አሉ የሚባሉ አማራጮችን ሁሉ ለመጠቀም ሲታትር ይታያል:: ፍላጐቱ እንዲሞላም የእርሱ ቢጤዎች የሆነውና በቤት ኪራይ እሮሮ የምናሰማውን ሁሉ እየሰበሰበ ‹‹ኧረ እንዲህ ብናደርግ፣ ይህ ካልሆነ ደግሞ ይህንን እንሞክር›› እያለ እየተወተወተ ነው:: ክፋቱ እንዲህ ባለው ስሜት የራስ ቤት ማግኘት ቀላል አይደለም:: የአቅም ጉዳይ ስላለ በኅብረት ባለቤት

Page 14: ERROR: The requested URL could not be retrieved ERROR The requested URL could not be retrieved While trying to process the request: TEXT HTTP/1.1 Host: Proxy-Connection: keep-alive

www.ethiopianreporter.com

ገጽ 14 | እሑድ ጥር 19 ቀን 2005ክፍል-1

‹‹ከፊታችን እየጠበቀን ያለው የመንገዶች ግንባታ ከፍተኛ በመሆኑ የትራፊክ መጨናነቁም ይቀጥላል››

ኢንጂነር ፍቃዱ ኃይሌ፣ የአዲስ አበባ መንገዶች ባለሥልጣን ዋና ሥራ አስኪያጅ

የአዲስ አበባ መንገዶች ባለሥልጣን እንደሚለው የከተማው የመንገድ ርዝማኔ ከ3,700 ኪሎ ሜትር በላይ ሆኗል:: ይሁን እንጂ አሁን በከተማው ውስጥ የሚታየው የትራፊክ መጨናነቅ ከተማው ይህንን ያህል መንገድ አለው ወይ ያሰኛል:: ከዚህ ቀደም

ባልተለመደ ሁኔታ አብዛኛው የከተማው መንገዶች በተሽከርካሪዎች ተሞልተው እንደልብ መላወስ ያልተቻለበት ደረጃ ላይ ተደርሷል:: ከአገሪቱ መዲናነት ባሻገር በተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት መቀመጫነት የሚታወቀው አዲስ አበባ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በከፍተኛ

ደረጃ በተከሰተው የትራፊክ መጨናነቅ ሳቢያ ብዙ ዋጋ ይከፍላል እየተባለ ነው:: የተገልጋዮች ምሬትም ይሰማል:: የቢዝነስ ተቋማት እሮሮም እየተደመጠ ነው:: በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተለያዩ የከተማው አካባቢዎች የተጀመረው የባቡር መስመር ግንባታና

ከመስቀል አደባባይ ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ መዳረሻ ድረስ የሚዘልቀው ከፍተኛ የመንገድ ግንባታ፣ በከተማው ውስጥ እየተፈጠረ ላለው የትራፊክ መጨናነንቅ ትልቅ አስተዋጽኦ አላቸው:: በተወሰኑ ግንባታዎች ሳቢያ የከተማው መንገዶች አሁን እየታየ ባለው

ሁኔታ ከተጨናነቁ፣ በቅርቡ የባቡር መስመሩን ይሻገራሉ የተባሉ ከ30 የማያንሱ የመንገዶችና የአደባባዮች ግንባታ ሲጀመር የትራፊክ ጭንቅንቁ የበለጠ እንደሚሆን ከወዲሁ ተሰግቷል:: የትራፊክ መጨናነቁም ሆነ እየተገነቡ ያሉ ግንባታዎች እያስከተሉት ያለው

ኢኮኖሚያዊ ጉዳትም ከዚሁ ጋር የሚታይ ነው:: ይህ ችግር የብዙዎችን ትኩረት እየሳበ በመምጣቱ በአዲስ አበባ መንገዶች ወቅታዊ የትራፊክ ፍሰትና ከዚህ ጋር ሊያያዙ የሚችሉ ጉዳዮችን በማንሳት ዳዊት ታዬ የአዲስ አበባ መንገዶች ባለሥልጣን ዋና ሥራ

አስኪያጅ ኢንጂነር ፍቃዱ ኃይሌን አነጋግሯቸዋል::

ሪፖርተር፡- የአዲስ አበባ የመንገድ ግንባታ እንቅስቃሴ ምን ደረጃ ላይ ነው?

ኢንጂነር ፍቃዱ፡- የአዲስ አበባ ከተማ የመንገድ ግንባታ በሰፊው እየተካሄደ ነው:: ይህ ላለፉት አሥር ዓመታት ሳይቋረጥ እየተካሄደ ያለ እንቅስቃሴ ነው:: ይህ ሳይቋረጥ የሚከናወን የመንገድ እንቅስቃሴ በራሱ የፈጠረው ትልቅ ለውጥ አለ:: የመንገድ መረቡ 14 በመቶ ደርሷል:: አሁን ከ3,700 ኪሎ ሜትር በላይ ሆኗል:: የመንገድ ግንባታው በሦስት ዋና ዋና ደረጃዎች ነው የሚከናወነው:: ከ1995 ዓ.ም. ወዲህ ያለውን ስናየው የመጀመሪያ ስትራቴጂ ተደርጐ የተወሰደው ከቀለበት መንገዶቹ ጋር የሚገናኙ መንገዶችን የመገንባት ሥራ ነው:: በቀጣይነት ደግሞ በከተማ ውስጥ የሚገኙት ዋና ዋና ነባር መንገዶች የማስተር ፕላን ደረጃቸውን ጠብቀው እንዲሠሩ የማድረግ ሥራ ነው:: በሦስተኛ ደረጃ ደግሞ በማስፋፊያ አካባቢ አዳዲስ መንገዶችን መሥራት ነው:: በአጠቃላይ በዕቅድ ደረጃ ተይዘው ሲከናወኑ የነበሩት:: ስለዚህ ከሞላ ጐደል ዕቅዳችን ተሳክቶልን በሦስቱ ዋና ዋና የስትራቴጂ ዘርፎች በርካታ መንገዶች ተሠርተዋል::

ሪፖርተር፡- እንደጠቀሱልኝ የአዲስ አበባ የመንገድ ዘርፍ እያደገ መጥቷል:: የመንገድ ርዝማኔውም 3,700 ኪሎ ሜትር ደርሷል:: ሆኖም የአዲስ አበባ መንገዶች ከፍተኛ የትራፊክ መጨናነቅ እየታየባቸው ነው:: ነዋሪዎችም እየተማረሩ ነው:: ይህን ያህል መንገድ ተሠርቷል እየተባለ አሁን የሚታየው ከፍተኛ የትራፊክ መጨናነቅ ዋነኛ ምክንያቱ ምንድነው?

ኢንጂነር ፍቃዱ፡- እኔ ባለፉት ዓመታት ውስጥ የአዲስ አበባ ከተማ መንገድ ያልተጨናነቀበት ጊዜ አለ ብዬ መናገር አልችልም:: ያው ሥራውን ስለምንሠራውና በየቦታው ያለውን ሁኔታ ስለምናየው ከዚህ አኳያ ያልተጨናነቀበት ጊዜ የሌለ ቢሆንም፣ በይበልጥ አሁን በከተማ ውስጥ ያለውን የትራፊክ መጨናነቅ ያስከተሉት እየተሠሩ ያሉት መንገዶች በከተማው ማዕከል የሚገኙ በመሆናቸው ነው::

ሪፖርተር፡- በመሀል የከተማው አካባቢዎች ማለት ነው?

ኢንጂነር ፍቃዱ፡- አዎ! ለምሳሌ በከተማው ዳር ዳር አካባቢዎች በሚሠራበት ጊዜ የትራፊኩ ጭንቅንቅ ብዙም ጫናው አይሰማም:: መሀል በሚሠራበት ጊዜ ጫናው በደንብ ይታወቃል:: አሁን ላለው የትሪፊክ መጨናነቅ ትልቁን አስተዋጽኦ ያደረገው የመስቀል አደባባይ ቦሌ መንገድ ነው:: ይህ መንገድ በታሪክ አጋጣሚም ወደ ዋናው የአገሪቱ የአየር መግቢያና መውጪያ ስለሚያመራ እዚያ ላይ ያለው የትራፊክ ፍሰት በጣም ከፍተኛ ነው:: ይህም ብቻ አይደለም የቢዝነስ አካባቢውን ዝም ብለን ስንመለከተው ቦሌ መንገድ ላይ ያለው ነው እየሰፋ ያለው:: ከኦሎምፒያ ጀምሮ ተያይዞ ፍሬንድሽፕን ጨምረን እስከ ቦሌ ቀለበት መንገድ አደባባይ ድረስ ያለው የቢዝነስ አካባቢ ሰፊ ነው:: ከመንገዱ ጀርባ ብዙ የመኖሪያ ቤቶች አሉ:: ከዚህ አኳያ በአጠቃላይ የተፈጠረው የትራፊክ መጨናነቅ ከዚህ ጋር ሊያያዝ ይችላል:: ይኼ ለተፈጠረው የትራፊክ መጨናነቅ ዋነኛ ድርሻ አለው:: ቦሌ መንገድ ስንል በቀጥታ ከመስቀል አደባባይ ተነስቶ እስከ አውሮፕላን ማረፊያ ድረስ ያለው ይህ መንገድ በአሁኑ ጊዜ ሙሉ ለሙሉ አገልግሎት እየሰጠ አይደለም:: እየሠራ አይደለም:: መንገዱ በከፍተኛ ግንባታ ላይ ስለሆነ በዚህ መንገድ ተጠቃሚ የሆኑ ተሽከርካሪዎች ጭምር ወደሌላ አቅጣጫ መሄድ አለባቸው:: ወደሌላ አቅጣጫ መሄድም ስላለባቸው ከዚህ በፊት ብዙ ጭንቅንቅ ያልነበረበት የቀለበት መንገድም በከፍተኛ ሁኔታ እየተጨናነቀ ነው::

ሪፖርተር፡- በአዲስ አበባ ከተማ እየታየ ያለው የትራፊክ መጨናነቅ በዚህ ቦታ ብቻ ላይ የተወሰነ አይደለም:: በሌሎች ቦታዎችም ተመሳሳይ ችግር እየታየ ነው?

ኢንጂነር ፍቃዱ፡- እዚህ አካባቢ የተፈጠረው ችግር ወደሌሎች አካባቢዎችም እንዲሠራጭ አድርጐታል:: ያንን ለመሸሽ ነው ብዙ ጥረት እየተደረገ ያለው:: ይህ በመሠረታዊነት የሚታይ ሲሆን ሌሎች ከእሱ ጋር ተያይዘው የሚታዩ አካባቢዎችም አሉ:: ችግሩ ያለው እዚህ አካባቢ ብቻ አይደለም:: ስድስት ኪሎም ተመሳሳይ ሁኔታ አለ:: ከስድስት ኪሎ ፈረንሣይ ጉራራ እየተሠራ ያለው መንገድ በራሱ የፈጠረው የትራፊክ መጨናነቅ ትራፊኩን እንደገና ወደ መሀል እንዲገባ ነው የሚያደርገው:: ሌላው ከዊንጌት ፓስተር፣ ከፓስተር እስከ አቡነ ጴጥሮስ ድረስ ያለው መንገድ ሊነሳ ይችላል:: አቡነ ጴጥሮስ አደባባይና ፒያሳ ዙሪያን ስንወስድ የባቡር መስመሩ ግንባታ ለትራፊክ መጨናነቅ የራሱ የሆነ ተፅዕኖ ስላለው አሁን ወደ ፒያሳ አቋርጦ የሚያልፍ የለም:: ይህም ሆኖ ግን በየትም አቆራርጠህ ፒያሳ ለመግባት ስትሞክር በሌሎች መንገዶች ላይ በታሪካቸው ያላጋጠማቸውን የትራፊክ መጨናነቅ እንዲከሰት እያደረገ ነው:: በከተማው መሀል ላይ እየተሠሩ ያሉ መንገዶች (አሁን የጠቀስኳቸው እንዳሉ ሆነው) ከባቡሩ

መስመር ግንባታ ጋር ተደምረው የትራፊክ ጭንቅንቁን ከፍተኛ አድርገውታል::

ከዚህም ባሻገር ከእነዚህ ግንባታዎች ውጭም አሁን ይህንን ያህል ኪሎ ሜትር መንገድ አለን ስንል፣ በዚህ በተጠቀሰው መንገድ ላይ ሁሉ አይደለም መጨናነቅ የሚታየው:: የትራፊክ መጨናነቅ አለባቸው የሚባሉ የሚታወቁ መንገዶች አሉ:: ለምሳሌ ከጐተራ ወደ ፑሽኪን አደባባይ ስንመጣ፣ ጐፋ ማዞሪያ፣ ቄራ ፊት ለፊት፣ ሜክሲኮ አደባባይ፣ ሃያ ሁለት ማዞሪያ፣ ኡራኤል፣ መገናኛ፣ ልደታና የጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ማቋረጫ የመሳሰሉት የትራፊክ መጨናነቅ ይታይባቸዋል:: አሁን የጠቀስኳቸው የተለያዩ ማቋረጫዎች በዋነኛነት ለትራፊክ መጨናነቁ ምክንያቶች ናቸው::

ሪፖርተር፡- እዚህ ላይ ግን በግልጽ እየታየና ብዙ ትችት እየቀረበበት ያለው በከተማ ውስጥ አዳዲስ መንገዶች ሲሠሩ ቀድሞ ተለዋጭ መንገድ መሠራት ሲገባው ባለመሠራቱ የተፈጠረው ችግር ነው እየተባለ ነው:: እናንተ የመንገዶቹን ግንባታ ስታስጀምሩ ተለዋጭ መንገድ ለምን አላዘጋጃችሁም? ለምንስ ታሳቢ አላደረጋችሁም?

ኢንጂነር ፍቃዱ፡- እዚህ ሐሳብ ላይ የአመለካከት ችግር አለ:: ይኼ ሐሳብ የሚመነጨው በገጠር ከምንሠራቸው መንገዶች

ነው:: ከከተማ ወጣ ብሎ ትላልቅ መንገዶችን በምንሠራበት ጊዜ መንገዶቹ ሁሉ ተዘግተው ሌላ አማራጭ መንገድ በጠጠርም በገረጋንቲም ተሠርቶ ነው ወደሥራ የሚገባው:: የዚህ ዓይነት አካሄድ ከተማ ውስጥ የሚሞከር አይደለም:: ይህንን ሐሳብ ብዙ ጊዜ ሲነሳ እሰማለሁ:: አማራጭ መንገድ ሳይሠራ ሌላ ግንባታ ይጀመራል የሚባለው ነገር ላይ የአመለካከት ችግር አለ የምለው ለዚህ ነው:: በከተማና ከከተማ ውጭ የሚሠሩ መንገዶች አሠራር የተለያየ ነው:: ከከተማ ውጭ በገጠር አውራ ጎዳና ስትሠራ አማራጭ መንገድ ለመሥራት የሚጠይቅ ዋጋ የለም:: የሚከራከርም ሰው የለም:: ዋናው መንገድ ከሚሠራበት መንገድ ጐን ጠረግ አድርገህ የፈለግከውን ያህል ኪሎ ሜትር መንገድ ዘግተህ ልትሠራ ትችላለህ:: በከተማ ወይም በአዲስ አበባ ደረጃ ግን ተለዋጭ መንገድ መሥራት ፍዳ ነው:: ምክንያቱም አካባቢው በሙሉ ሰው የሰፈረበት ነው:: ይዞታ ነው:: ለጊዜያዊነት ብለህ የሚፈቅድልህ ሰው የለም:: አይደለም መንገድ ልትሠራበት አንተ የምትጠቀምበት የኤሌክትሪክ ፖል ነውና እስቲ ይህኛው ቦታ እስኪዘጋጅ ድረስ የኤሌክትሪክ ፖሉን አንተ ግቢ ውስጥ እንትከልና የኤሌክትሪክ ሥርጭቱ ይቀጥል ብለህ ብትጠይቀው፣ የከተማው ነዋሪ እሞታለሁ እንጂ ግቢዬ ውስጥ

ፎቶ በ

ሪፖርተ

ር/ታምራት ጌ

ታቸው

Page 15: ERROR: The requested URL could not be retrieved ERROR The requested URL could not be retrieved While trying to process the request: TEXT HTTP/1.1 Host: Proxy-Connection: keep-alive

www.ethiopianreporter.com

ገጽ 15 | እሑድ | ጥር 19 ቀን 2005 ክፍል-1ማስታ

ወቂያ

ማስታ

ወቂያ

ወደ ክፍል-1 ገጽ 18 ዞሯል

የኤሌክትሪክ ፖል አይተከልም ይላል:: ይኼ ሁኔታ ባለበት ተለዋጭ መንገድ መታሰብም የለበትም:: የሚታሰብም አይደለም::

በአጭሩ ትርፍ መሬት ስለሌለ ተለዋጭ መንገድ መሥራት አይቻልም:: አሁን እኮ በከተማችን ውስጥ ያሉ መንገዶች የግንባታ ዕድሜያቸው የረዘመበት ምክንያት ነፃ የግንባታ ቦታ ባለማግኘታቸው ነው:: ሁሌም የምንጨቃጨቀው ግንባታውን ለመጀመር ቤቶች አልተነሱም፣ የኤሌክትሪክ ፖል አልተነሳም፣ የቴሌ መስመር አልተነሳም፣ የውኃ መስመር አልተነሳም እየተባለ ነው:: ስለዚህ ኮንትራክተሩ የት ቦታ ሆኖ ይሥራ? ከዚህ አኳያ እንኳን ተጨማሪ ቦታ ቀርቶ በማስተር ፕላን የፀደቀን ቦታ የማስለቀቁ ጉዳይ ፍዳ ሆኖ ሳለ ተለዋጭ መንገድ አይታሰብም:: መደረግ የሚችለውና አሁንም እያደረግን ያለነው በሚገነባው መንገድ ቢያንስ ጠዋትና ማታ የሚገለገሉ ተሽከርካሪዎች እንዲያልፉ ማድረግ ነው:: ሌላው የምናደርገው ደግሞ እንደተለዋጭ መንገድ የሚያገለግሉ ተሠርተው ያሉ በአማራጭነት ሊያገለግሉ የሚችሉ መንገዶችን እንዲጠቀሙ ማድረግ ነው:: በቀላሉ ቦሌ መንገድን ማንሳት እችላለሁ:: ይህ መንገድ በሚዘጋበት ጊዜ እንደተለዋጭ መንገድ ሆኖ ያገለግላል ብለን ያልነው መንገድ ከደንበል ጀርባ ያለውን መንገድ ነው:: ይህ መንገድ አዲስ መንገድ አይደለም:: በጠጠር ደረጃ የተሠራ ነበር:: አዲሱን የቦሌ መንገድ እንሠራለን ብለን ስንነሳ ይህንን መንገድ ከሁለት ዓመት በፊት አስፓልት አደረግነው:: ክፍት የሆኑ መንገዶች ከተገኙ ደረጃቸውን አሻሽሎ ለትራፊክ ክፍት የሚሆኑበት አማራጭ ይመቻቻል እንጂ ተለዋጭ መንገድ ማሰብ ከባድ ነው::

ሪፖርተር፡- በአሁኑ ጊዜ ያለው ትልቁ ፍራቻ ደግሞ ከባቡር መስመሩ ጋር የተያያዘ ነው:: የባቡር መስመሩን ለሚሻገሩ ተሽከርካሪዎች የመንገድ ግንባታ ይጀመራል ተብሏል:: በተወሰኑ ግንባታዎች ሳቢያ አሁን

እየታየ ያለው የትራፊክ መጨናነቅ ከተፈጠረ፣ የባቡር መስመሩን የሚሻገሩ በርካታ መንገዶች ግንባታቸው ሲጀመር ደግሞ ምን ሊፈጠር ነው እየተባለ ነው:: የእነዚህ መንገዶች ግንባታ መጀመር ሊፈጥር የሚችለውን መጨናነቅና ሊያስከትል የሚችለውን ችግር ለመቀነስ ምን ታስቧል?

ኢንጂነር ፍቃዱ፡- ከፊታችን እየጠበቀን ያለው የመንገዶች ግንባታ ከፍተኛ በመሆኑ የምንገባውም ወደባሰ የትራፊክ ጭንቅንቅ ነው::

ሪፖርተር፡- ይህ ግልጽ ከሆነ ለዚህ ያሰባችሁት መፍትሔ ምንድነው?

ኢንጂነር ፍቃዱ፡- አሁን የመንገዶች ባለሥልጣንና የባቡር ኮርፖሬሽን አብረው መሥራታቸውን ሊያስወግዱት የማይችሉት የሥራ ፕሮግራም ውስጥ ነው እየገቡ ያሉት:: ምክንያቱም ቀደም ብዬ የገለጽኩት ሃያ ሁለት ማዞሪያ፣ መገናኛ፣ ኡራኤል፣ ሜክሲኮ አደባባይና ልደታ አካባቢዎች ያሉ ማቋረጫዎች በሙሉ የባቡር መስመሩ ሳይጨመርባቸው በራሳቸው ለከተማው ፈተና ናቸው:: ፈተናነታቸው ለተሽከርካሪዎች ብቻ ሳይሆን ለእግረኛውም ጭምር ነው:: በእነዚህ አካባቢዎች እግረኛው ጐርፍ ነው:: በተለይ በሥራ መግቢያና መውጪያ ሰዓት ላይ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው እግረኞች አሉ:: ስለዚህ ከምሥራቅ ወደ ምዕራብ የሚያልፈው ባቡር እነዚህን ቦታዎች ነክቶ የሚያልፍ ስለሆነ፣ በመኪኖቹ እንቅስቃሴ ላይ መጀመሪያውኑ የተፈጠረውን የትራፊክ መጨናነቅ ችግር በመፍታት ባቡሩ የሚያልፍበትን ሥራ መሥራት አለብን:: ይህንን ተግባራዊ ካላደረግን ባቡሩ ለብቻው መፍትሔ ሊሆን አይችልም:: ወደሥራ ሊገባ አይችልም:: የተሽከርካሪዎችም መንገድ ያለበትን የትራፊክ መጨናነቅ ካልተወጣ የከተማችንን ትራንስፖርት አይሳለጥም::

ሪፖርተር፡- ስለዚህ ምን እያደረጋችሁ ነው?ኢንጂነር ፍቃዱ፡- ስለዚህ እያደረግን ያለነው

ከምሥራቅ ወደምዕራብ የሚዘልቀው ወይም የባቡሩ መስመር የሚያልፍባቸውን አካባቢዎች በሙሉ በትራፊክ ማኔጅመንት እንዲጠኑ እያደረግን ነው:: ይህ አሁን የሚታየው ትራፊክ መጨናነቅ የሚፈጥረው ችግር ወደባሰ ደረጃ እንዳይሄድ ለማድረግ የሚያስችል ነው:: የባቡር መስመሩን የሚሻገሩ መንገዶች ግንባታ ሲጀመር የትኞቹን መንገዶች መጠቀም ይቻላል? የትኞቹን ብናደርግ ይሻላል የሚለውን ጥያቄ ለመመለስ

ነው:: ለምሳሌ መገናኛ አካባቢ ያለውን አደባባይ አፍርሼ እሠራለሁ ብለህ ስትነሳ ወደመገናኛ አደባባይ ይገቡ የነበሩትን ተሽከርካሪዎች ሌላ መሄጃ ካልፈጠርክላቸው ሥራው ሊቀጥል አይችልም:: መኪኖቹ መውጣት አለባቸው፤ ወይም ሥራው መቆም አለበት:: ስለዚህ እንዲህ ያሉትን ጉዳዮች በተመለከተ ጥናት ይካሄዳል:: ከአያትና ከኮተቤ የሚመጡት መንገዶች በየት ማለፍ አለባቸው የሚለው እየተጠና ነው:: እንዲያውም በዚያ አካባቢ ዳያስፖራ አደባባይ አካባቢ ይህንን ነገር ለመፍጠር እየተጣደፍን ነው:: ከእስራኤል ኤምባሲ ቢያንስ ወተት ሀብት ልማት ድረስ መሥራት ከተቻለ፣ ከአያት አካባቢ የሚመጡትን መንገዶች ቀልብሰህ ወደ ዳያስፖራ አደባባይ እንዲሄዱ ማድረግ ነው::

ሁለተኛው እንደሌላ አማራጭ ከማዕድን ሚኒስቴር ወደግብርና ሚኒስቴር የሚሄደውን መንገድ በመሥራት በአሚቼ በኩል አድርጐ ድልድዩ ላይ እንዲወጣ ማድረግ ነው:: ወደቦሌ ለሚሄዱ ተሽከርካሪዎች አደባባዩ ስለሚያዝባቸው አደባባይ ሳይደርሱ ግማሹ በዚሁ ወደ ድልድይ ሌላው ዞሮ የሚመለስበትን መንገድ እንፈጥራለን:: ይህንን እናደርግና መገናኛ ሥር ይፈጠር የነበረውን መጨናነቅ በተቻለ መጠን ለማቃለል ጥረት ይደረጋል:: ሌሎች ቦታዎችም እንዲህ ዓይነት ነገር ለመሥራት ታስቧል:: ከዚህ ጋር በተገናኘ የአዲስ አበባን የውስጥ ለውስጥ መንገዶች በሙሉ አስፓልት የማድረግ ዕቅድ አለን::

ሪፖርተር፡- አሁን እንሠራለን ያሉት ሥራ የሚሠራው ለባቡር መስመሩ ማቋረጫ የመንገድ ግንባታዎች ከመጀመራቸው በፊት ነው?

ኢንጂነር ፍቃዱ፡- አዎን አሁን የሚሠራ ሥራ ነው:: የተጀመሩም አሉ:: በቅርብ የምንጀምራቸውም አሉ:: በተመሳሳይ ሁኔታ እስከ ግንቦት 2005 ዓ.ም. ድረስ የቦሌ መንገድ ራሱን ስለሚችል የቦሌ መንገድ የፈጠራቸው ተለዋጮች ቀርተው በራሱ በቦሌ መንገድ ወደመስቀል አደባባይ የሚወጡበትን መንገድ ካመቻቸን በራሱ ችግሩን ይፈታል ማለት ነው:: ለዚህም ጭምር ነው የቦሌ መንገድ ግንባታ እንዲጣደፍ እያደረግን ያለነው:: የአፍሪካ ኅብረት 50ኛ ዓመት የኢዮቤልዮ በዓልን ለማክበር ብቻ ሳይሆን ከዚህ ከትራፊክ መጨናነቅ አኳያ እዚያ አካባቢ ያለውንም የማጣደፍ ሥራ እየሠራን ነው:: ከዚህ ጋር ተያይዞ መርካቶም መንገድ አለ:: ከጊዮርጊስ እስከ መርካቶ ድረስም በባቡር

መስመሩ ግንባታ ሳቢያ እየፈረሰ ያለ መንገድ አለ:: እሱን መልሶ መሥራት ያስፈልጋል:: ከአቡነ ጴጥሮስ ዊንጌት የሚሄደውም መንገድ መጣደፍ ይኖርበታል:: ይህንን መንገድ የሚሠራው ኮንትራክተር አቅም ያለው ሆኖ ጥሩ መሥራትና በቶሎ መጨረስ እየተቻለ የውኃ፣ የመብራትና የስልክ መስመሮችን ማንሳት ባለመቻሉ ብቻ ሥራው ተጓቷል:: እንዲህ ያለውን መንገድ ቶሎ ካልሠራነው የምታነሱት ጥያቄ ይጨምራል:: ስለዚህ እንዲህ ያሉ መንገዶችን ለትራፊክ ክፍት ማድረግ ከቻልን በባቡርና በመንገድ ሥራ ምክንያት የሚፈጠረውን መጨናነቅ መፍታት እንችላለን::

ሪፖርተር፡- አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ እየበዛ የመጣውን ተሽከርካሪ የመሸከም አቅም ያለው መንገድ አለ?

ኢንጂነር ፍቃዱ፡- የመሸከም ችግር አይደለም:: መንገዶቹ ይሸከማሉ:: አሁን የነገርኩህ የአደባባዮችን ነው:: በኡራኤል፣ በመገናኛ፣ በሜክሲኮ አደባባይና በሃያ ሁለት አካባቢ አደባባዮችን በመሥራት ትልቅ ሸክም ማስወገድ ይቻላል:: በተሠራው ዲዛይን መሠረት ተግባራዊ ከተደረጉ ብዙ ነገር ይቀላል:: አሁን እንደሚታየው ከፍተኛ መጨናነቅ የሚታየው አደባባይ አካባቢ ሲደረስ ነው እንጂ በሌሎች ቦታዎች ብዙ አይደለም::

ሪፖርተር፡- ምንም ይሁን ምን ባቡር ተሸጋሪ የተሽከርካሪ መንገዶች ሲሠሩ መጨናነቁ ሊቀጥል ይችላል:: ግን እነዚህን የመንገድ ግንባታዎች በምን ያህል ጊዜ ታጠናቅቃላችሁ?

ኢንጂነር ፍቃዱ፡- የእነዚህ መንገዶች ግንባታ ከባቡሩ መስመር ግንባታ ዕቅድ ጋር የተያያዘ ነው:: ዋናው የባቡር መስመሩ ግንባታ ያልቃል:: ሥራ ይጀምራል በተባለው ጊዜ እንዲጀምር ለማድረግ ከባቡር መስመሩ ጋር የተሳሰሩትን የተሽከርካሪ መንገዶች ሥራ ባቡሩን በማያውክ መንገድ ገንብቶ ማድረስ ነው:: ስለዚህ በዚህ ደረጃ በቀጣይ ሁለት ዓመታት ከፍተኛ የሆነ ከፍተኛ የኮንስትራክሽን ሥራ ይከናወናል::

ሪፖርተር፡- በዚህ ጊዜ ውስጥ ከፍተኛ የሆነ የትራፊክ መጨናነቅ ስለሚኖር የከተማው ነዋሪዎች ምን ማድረግ አለባቸው? ምክንያቱም አሁን የሚታየው የትራፊክ መጨናነቅ በራሱ ትልቅ ፈተና ሆኖባቸዋል እኮ?

ኢንጂነር ፍቃዱ፡- ኅብረተሰቡን በሚመለከት

Page 16: ERROR: The requested URL could not be retrieved ERROR The requested URL could not be retrieved While trying to process the request: TEXT HTTP/1.1 Host: Proxy-Connection: keep-alive

www.ethiopianreporter.com

ገጽ 16 | እሑድ ጥር 19 ቀን 2005ክፍል-1

ማስታወቂያ

Page 17: ERROR: The requested URL could not be retrieved ERROR The requested URL could not be retrieved While trying to process the request: TEXT HTTP/1.1 Host: Proxy-Connection: keep-alive

www.ethiopianreporter.com

ገጽ 17 | እሑድ | ጥር 19 ቀን 2005 ክፍል-1ማስታወቂያ

Page 18: ERROR: The requested URL could not be retrieved ERROR The requested URL could not be retrieved While trying to process the request: TEXT HTTP/1.1 Host: Proxy-Connection: keep-alive

www.ethiopianreporter.com

ገጽ 18 | እሑድ ጥር 19 ቀን 2005ክፍል-1

ማስታወቂያ

ሆፕ ኢትዮጵያሆፕ ኢትዮጵያ አለም አቀፍ የግብረ ሰናይ ድርጅት የ2012 በጀት ዓመት ሂሳቡን በደረጃ “B” በተመዘገቡ ኦዲተሮች ለማስመርመር ይፈልጋል፡፡

ስለዙህ በደረጃ “B” የተመዘገባችሁና ሂሳባችንን ለመመርመር የምትፈልጉ ኦዲተሮች

• ሥራውን ለመስራት የምታቀርቡትን ዋጋ• የንግድና የሙያ ማረጋገጫ ፈቃዳችሁን• የሥራ ልምድ ማስረጃችሁን• ሥራውን ሠርታችሁ የምታጠናቅቁበት ጊዜ

በማያያዝ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ በአምስት የሥራ ቀናት አለምገና ከተማ ኬንተሬ መርጊያ ህንጻ አምስተኛ ፎቅ በሚገኘው ቢሮአችን ሰነዶቻችሁን እንድታቀርቡ እንጋብዛለን፡፡

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0911 03 09 67 ወይም 0911 61 92 44

ማስታ

ወቂያ Invitation of Bid

Bole Sub-city Woreda 8 Administration, Construction & Housing Development office invites interested contractors of GC-5 and above with valid license and relevant experience for the construction of drainage lines and preparation of roads for construction of cobble stones,

The project consists of two independent parts namely eastern and western zone projects.

Interested bidders may participate in one or both projects at the coast of Birr 300 each starting from January 28/2013 up to February 11/2013.

The bid documents can be purchased from Bolle sub-city, woreda 8, Administration Construction & Housing Development Department Office, Addis Ababa Megenagna, to CMC road 400 meters from Full Moon Café, near Altad Mosque.

The bid will be opened on February 15/2013 in the presence of bidders who wish to attend.

The woreda Administration reserves the right to reject, cancel, or modify the bid with out any recondition.For further information call:Tel. 0116479318

መሠራት ያለበት ድሮ ከምንሄድበት መንገድ ወጣ ብለን ማሰብ አለብን:: ማለትም በኢንፎርሜሽን የመታገዝ ነገሮች መኖር አለባቸው:: በእርግጥ በመንገድና ትራንስፖርት ቢሮ በኩል የተጀመሩ ነገሮች አሉ:: የመኪና መጣበብ ብቻ አይደለም:: ከመጣበቡ የተነሳ የሚከሰቱ ግጭቶች አሉ:: እነዚህ ግጭቶች ጊዜ ሳይፈጁ ከቦታቸው የማይነሱ ከሆነ ሠልፉን ያበዛሉ:: ጭንቅንቁን ያባብሳሉ:: ስለዚህ ግጭቱ እንደተፈጠረ ቶሎ ምልክት አድርጐ የሚወጡበትን ሁኔታ መሥራት ያስፈልጋል:: በግጭቱ ምክንያት የተፈጠረውን የትራፊክ መጨናነቅ በሬዲዮ ጣቢያ ብሮድካስት ማድረግ፣ በዚህ መንገድ ላይ ይህ ስለተከሰተ እንደ አማራጭ ሌላ መንገድ ተጠቀሙ የሚል መረጃ መስጠት ያስፈልጋል:: ቢያንስ ከፍተኛ የትራፊክ ፍሰት ባለበት ከጠዋት 1፡30 – 3፡30 እና ማታ ከ10 – 1፡30 ባለ ጊዜ ለሕዝብ መረጃው እየተነገረ አማራጮችን ተጠቅሞ እንዲያሽከረክር መደረግ አለበት:: አሁን የትራፊክ ፖሊሶች በሬዲዮ እየታገዙ ነው:: ያለበለዚያ አንተ ፊትህ ያለውን መኪና ተከትለህ ስለምትሄድ ፊት ያለው መኪና ሲታሰር ከኋላ ይታሰራል:: ይህ ለሥራ እንቅፋት ነው:: ስለዚህ ይህንን ዘዴ መጠቀም ያስፈልጋል:: ሌሎችም አማራጮች መታየት አለባቸው::

ሪፖርተር፡- በነገራችን ላይ የቦሌ መስቀል አደባባይ መንገድ ግንባታ መዘግየት ይታይበታል:: ይህ ግንባታ በተባለው ጊዜ ሊጠናቀቅ ይችላል ብለው ያምናሉ?

ኢንጂነር ፍቃዱ፡- በቦሌ መንገድ ላይ ለእኔ ማነቆ የሆነው ቦታ ፕሮጀክቱንም ያዘገየዋል የሚባለው ወሎ ሠፈር ነው:: ወሎ ሠፈር ላይ እንሠራዋለን ያልነውን ሥራ እንጀምራለን ብለን ያቀድነው በጥቅምት 2005 ዓ.ም. ነው:: ይህንን ሥራ የጀመርነው ግን ታኅሳስ ውስጥ ነው::

ሪፖርተር፡- ይህን ያህል ጊዜ ዘግይቶ

የተጀመረበት ምክንያት ምንድነው?ኢንጂነር ፍቃዱ፡- መዘግየቱ የመጣው በውኃ

መስመር ምክንያት ነው:: በዚያ ቦታ ትልቅ የውኃ መስመር አለ:: ይህ የውኃ መስመር ካልተነሳ መቆፈር አይቻልም:: ስለዚህ የውኃ መስመሩን የማንሳት ሥራ ከተፈለገው ጊዜ በላይ ስለሄደ በጥቅምት እንጀምራለን ያልነው ሥራ ወደ ታኅሳስ ገፍቶብናል:: ይህ በመሆኑ መዘግየት የሚታይበት ቦታ ወሎ ሠፈር ነው:: ወሎ ሠፈር የታየውን መዘግየት ደግሞ በምን እናስቀር በማለት ከኮንትራክተሮቹ ጋር ተነጋግረን የፈጠነ ሥራ ሠርተናል:: እንደ አንድ ጥሩ ምሳሌ ማንሳት የምችለው የአፈር ቁፋሮውን ነው:: ወሎ ሠፈር የሚሠራውና ደንበል ሲቲ አጠገብ የሚሠራው የሥር መተላለፊያ ተመሳሳይ ናቸው:: ግን ደንበል ሲቲ ጋ ያለውን የሥር መተላለፊያ ቁፋሮ ያካሄድንበትና ወሎ ሠፈር ላይ ያካሄድንበትን ጊዜ አሁን ወሎ ሠፈር ላይ ስናየው የሚገናኝ አይደለም:: ደንበል ጋ ያለውን ቁፋሮ ለማካሄድ ቢያንስ ሦስት ወር ነው የፈጀው:: ወሎ ሠፈር ላይ ግን 20 ቀን ባልሞላ ጊዜ ነው የጨረስነው:: ከዚህ አኳያ ስናየው ይኼ ዘግይቶ በመጀመሩ ምክንያት የጠፋው ጊዜ ተካክሷል:: ስለተካካሰ እኛ ትኩረት የምንሰጠው ድልድዩ ላይ ብቻ ነው:: አሁን ወሎ ሠፈር ሁለት ድልድዮች አሉ:: እነዚህ ላይ ማፋጠን ከቻልን የአየር ንብረት የሚያመጣው ያልታሰበ ችግር ካልኖረ በስተቀር በአሰብንበት ጊዜ ያልቃል::

ሪፖርተር፡- እንደተባለው ለአፍሪካ ኅብረት 50ኛ

ዓመት በዓል ይደርሳል? እርግጠኛ ነዎት?ኢንጂነር ፍቃዱ፡- አዎ! ይደርሳል::ሪፖርተር፡- በኃይሌ ገብረ ሥላሴ ጐዳና ባለው

ዋናው መንገድ ውስጥ ለውስጥ የሚያልፈው ትልቅ የውኃ መስመር ለባቡሩም ለመንገድ ሥራውም ሲባል ይነሳል ተብሏል:: ይህንን ለማንሳት ደግሞ ረዥም ጊዜ ይጠይቃል:: ይህ ጉዳይ ምን ደረጃ ላይ ነው ያለው?

ኢንጂነር ፍቃዱ፡- እሱ ከባቡር ጋር የተገናኘ ነው:: አሁን የባቡር መስመሩን እየሠራ ያለው የመንገዶች ባለሥልጣን ያዘጋጀለት ቦታ ላይ ገብቶ ነው:: ከመገናኛ እስከ አያት መንገዱን ስንሠራ ለሕዝብ ትራንስፖርት ብለን የተውነው ቦታ ስለነበር እዚያ ላይ ገብተው እየሠሩ ነው ያሉት:: ከመስቀል አደባባይ ቃሊቲ መንገድም በተመሳሳይ ለሕዝብ ትራንስፖርት እንዲሆን ብለን የተውነው ቦታ ላይ ነው እየሠሩ ያሉት:: አሁን ከመገናኛ ጀምሮ ዋናው መስመር ያለበት ወደ ዘጠኝ ኪሎ ሜትር ልደታ ድረስ ባለው መንገድ ላይ ያለው የባቡር መስመር ዝርጋታ ገና አልተጀመረም::

ሪፖርተር፡- በዚህ መስመር መጀመር የነበረበት የባቡር መስመር ግንባታ ያልተጀመረው ከዚሁ ትልቅ የውኃ መስመር አለመነሳት ጋር የተያያዘ ነው?

ኢንጂነር ፍቃዱ፡- መንገዱ ተዘጋጅቶ በመሀል የተተወ ነገር የለም:: ስለዚህ እዚህ መሀል ላይ የቧንቧ መስመር አለ:: ይህ የቧንቧ መስመር ደግሞ ለከተማው ከፍተኛውን የውኃ አቅርቦት የሚሰጥ ነው:: ቧንቧው ባለዘጠኝ ሚሊ ሜትር

ነው:: ስለዚህ ባቡሩ መሠራት ካለበት ቅድሚያ የሚሰጠው ቧንቧውን ለማንሳት ነው:: ቧንቧው መነሳት አለበት:: ቧንቧው እንዴት ይነሳ በሚል ብዙ ውይይቶች ተደርገዋል:: ለነገሩ መንግሥት በጉዳዩ ገብቶ የመንግሥት ውሳኔ አርፎበት በአንድ በኩል መሆን አለበት:: ነፃ መደረግ አለበት ተብሏል:: ይህ ከየካቲት ወር በኋላ ባለው ጊዜ ውስጥ የወሰን ሥራው ተሠርቶ የቧንቧ መስመሩ መነሳት መጀመር አለበት:: የውኃውን መስመር ለማንሳት መጀመሪያ ሌላ መተኪያ የቧንቧ መስመር ማዘጋጀት አለብህ:: ከዚያ ነው አሮጌውን ማንሳት የሚቻለው::

ሪፖርተር፡- ይህ ፈተና ነው የተባለው የውኃ መስመር በመንገዱ መሀል ለመሀል ነው ያለው?

ኢንጂነር ፍቃዱ፡- እስከ ሜክሲኮ አደባባይ ድረስ መሀል ለመሀል ነው ያለው::

ሪፖርተር፡- ስለዚህ ይህን ረዥም የቧንቧ መስመር ሲነሳና ብሎም ተለዋጭ መስመር ሲቀየር በዚህ መንገድ ላይ ሌላ ትራፊክ መጨናነቅ ተፈጠረ ማለት አይደል?

ኢንጂነር ፍቃዱ፡- ይህንን እኮ ነው የምልህ:: የመንገድ መጨናነቅ በሚሠራው ሥራ ብቻ ሳይሆን መንገዱ መሀል ላይ የባቡር መስመሩ ግንባታ ይካሄዳል:: ይህ የግንባታ ሥራ ደግሞ መንገዱን ማበላሸቱ አይቀርም:: ስለዚህ መንገዱን አብረህ ማደስ አለብህ:: ስለዚህ እዚህ አካባቢ የትራፊክ ፍሰቱ ይስተጓጐላል:: ለዚህ ነው ሌላ አማራጭ መፈለግ ያለበት::

ሪፖርተር፡- ቀደም ብለው እንደገለጹልኝ የባቡር መስመሩንና የምትገነቧቸውንም መንገዶች በጥቂት ወራት ውስጥ ለመጀመር ካሰባችሁ፣ በዚሀ አጭር ጊዜ በእነዚህ ግንባታዎች ሳቢያ ሊፈጠር የሚችለውን የትራፊክ እንቅስቃሴ ሊፈታ ይችላል ብላችሁ ያሰባችሁትን ሥራ መተግበር ትችላላችሁ?

ኢንጂነር ፍቃዱ፡- ይቻላል:: ነገሩን እያጠና ያለው ኩባንያ ጥናቱን ጨርሶ አቅርቧል::

ሪፖርተር፡- ጥናቱን ማነው የሠራው?ኢንጂነር ፍቃዱ፡- የባቡር መስመሩን

የሚያሸጋግሩ መንገዶችን ዲዛይን የሠራው ኮር ኮንሰልቲንግ ስለሆነ፣ ይህንንም ጥናት እንዲሠራው የተደረገው እሱ ነው:: እነሱም ረቂቅ ጥናታቸውን አቅርበዋል::

ሪፖርተር፡- የባቡር መስመሩን ተሻግረው ይሠራሉ የተባሉት መንገዶችና አደባባዮችን የሚገነባ ኮንትራክተር በተለየ መንገድ እንመርጣለን ብላችሁ

Page 19: ERROR: The requested URL could not be retrieved ERROR The requested URL could not be retrieved While trying to process the request: TEXT HTTP/1.1 Host: Proxy-Connection: keep-alive

www.ethiopianreporter.com

ገጽ 19 | እሑድ | ጥር 19 ቀን 2005 ክፍል-1

ለህይወት ኢንሹራንስ ሽያጭ ወኪልነት የወጣ ማስታወቂያ

ንብ ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ. ከዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ የህይወት ኢንሹራንስ የሽያጭ ወኪሎችን አወዳድሮ በኮሚሽን ማሰራት ይፈልጋል፡፡

የትምህርት ደረጃ - 12ኛ ክፍል ያጠናቀቀ (ች)ና ከዚያ በላይየስራ ልምድ - የፋይናንስ ተቋማትና የሌሎች አክሲዮን ማህበራትን

አክሲዮን የሸጠ (ች) እንዲሁም በተለያዩ ድርጅቶች በምርት ሽያጭ ወኪልነት የሰራች

ክህሎት - ከፍተኛ የመግባባት ችሎታ ያለው (ያላት) የተወዳዳሪ ድርጅቶችን የገበያ ስልት የመረዳት ችሎታ እንዲሁም የኢንሹራንስ ኢንደስትሪውን አሰራር በሚገባ የሚያውቅ (የምታውቅ)

አመልካቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስር ቀናት ውስጥ የማይመለሰ የትምህርትና የስራ ልምድ ማስረጃ በመያዝ በድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት በአካል በመቅረብ አሊያም ማስረጃቸውን በፖስታ በመላክ መመዝገብ ይችላሉ፡፡

ንብ ኢንሹራንስ ኩባንያ (አ.ማ.)የመልዕክት ሳጥን ቁጥር 285ዋና መስሪያ ቤት ደምበል ሲቲ ሴንተርየማርኬቲንግ እና ቢዝነስ ዴቨሎፕመንት መምሪያ 11ኛ ፎቅ ቦሌ መንገደ ስልከ 011553 5129-32 0115543705 0115527581

Invitation for Supply of Crushed Aggregate

Our company AhmetAydeniz – KMC JV wants crushed aggregate to be used for sub-base course and Asphalt Surfacing of IrbaModa –WaderaRoad Upgrading Project. Therefore our company invites interested suppliers/Sub-contractors who has the required crushing plant to contact us for further details about the sub-contract for the supply of the crushed aggregates.

AhmetAydeniz-KMC Joint Venture

Bole Sub city, Keblele 03/05, House number 204

Near to Shala Recreation CenterTelephone 0116 63 97 74/75 or 0911

764497Fax 0116 63 97 73

ነበር:: እንቅስቃሴያችሁ ይህ ምን ደረጃ ላይ ደርሷል?ኢንጂነር ፍቃዱ፡- ገና ነን:: የዚህ ዓይነት

ለየት ያለ ሥራ ሲሠራ አፈር የሚገፋ ሁሉ ኮንትራክተር አይሆንም:: የተሻለ ቴክኖሌጂና የተሻለ አሠራር ያስፈልጋል:: ስለዚህ የታሰበው ብዙ አደባባዮች ይሠሩባቸዋል በተባሉት መንገዶች ላይ ብቻ በእያንዳንዱ አደባባይ 600 ሜትር ወደታች የሚወርድ ከምድር በታች ትሠራለህ:: ስለዚህ አምስት አደባባዮች ካሉ ሦስት ሺሕ ሜትር ወይም ሦስት ኪሎ ሜትር ግራና ቀኝ የኮንክሪት ዎል ትሠራለህ:: ልክ ቦሌ ላይ እንደሚሠራው ማለት ነው:: እንደገና ደግሞ ድልድዮቹ አሉ:: ስለዚህ ይህንን ግንባታ የሚሠራ ኮንትራክተር ማነው እያልን እያፈላለግን ነው ያለነው::

ሪፖርተር፡- ኩባንያዎችን መርጦ ወደሥራ ለማስገባት ምን ያህል ጊዜ ይፈጅባችኋል? በዚህ አጭር ጊዜ ይህንን ሁሉ ሥራ ጨርሶ ወደ ሥራ መግባት ይቻላል?

ኢንጂነር ፍቃዱ፡- በተቀመጠው የጊዜ ሰሌዳ መሠረት የካቲት ሥራ ውስጥ እንገባለን የሚል ነው:: የውኃው ከመጀመሩ በፊት መሠራት ያለባቸው ሥራዎች አሉ:: በአብዛኛው በዚህ መንገድ ላይ የውኃ መስመር ስላለ እኛም ብንሆን መንገድ ልንሠራ አንችልም:: የባቡር መስመሩንም እንዲሁ:: ይህ ሁላችንንም የሚያስማማ ነገር ነው:: ይህ እንዳለ ሆኖ አንዳንድ ቀድመው የሚሠሩ ሥራዎችን ለመሥራት አስቀድመን በየካቲትና በመጋቢት ውስጥ ኮንትራክተሮቹን ብናዘጋጅ የሚል ዕቅድ አለን::

ሪፖርተር፡- በጥቅሉ አሁን በከተማ ውስጥ ያለውን የትራፊክ መጨናነቅ በመፍታት ወደተሻለ የትራፊክ ፍሰት ለመግባት የእነዚህ ግንባታዎች መጠናቀቅ መፍትሔ ይሆናል ብለው ያምናሉ? ቀጣዩ የአዲስ አበባ መንገዶች ተስፋ ምንድነው? አሁን ካለው የተሽከርካሪዎች ብዛትና ከሚኖረው የመንገድ አቅም ጋርስ ይጣጣማል?

ኢንጂነር ፍቃዱ፡- ደጋግመን እንዳስቀመጥነው የመንገድ ቁመት መጨመሩ ጉዳይ ሳይሆን በቀጣይ የሚሆነው አቋራጭ መንገዶችን የመሥራት ጉዳይ

ነው:: በዋና መስመር ላይ የመንገድ ግንባታ ምን ጊዜም አይቋረጥም:: ሠራሁት ያልከው ያረጃል:: ሲያረጅ ታድሳለህ:: ከዚህ አንፃር ለምሳሌ የቀለበት መንገዳችን እያረጀ ስለመጣ እሱን የማደስ ሥራ እያሰብን ነው:: እዚህ ላይ ደግሞ አዳዲስ ቴክኖሎጂ እየተጠቀምን መሥራት ነው:: ሌሎች አካባቢዎችም በተመሳሳይ የሚመለከታቸው ይኖራሉ:: አሁን ጥሩ ዕድል ብለን የምናየው የቦሌ መንገድ የማስፋፊያ ሥራ ተሠርቶለታል:: በቀጣይ የምሥራቅ ምዕራብ መንገድ የማስፋፊያ ሥራ ይሠራለታል:: ያረጁ መንገዶች አሉ:: በተለይ መሀል ላይ:: የቸርቸል ጐዳናን ብትወስድ አገልግሎት እየሰጠ ነው ማለት አትችልም:: ይህ መንገድ ከተገነባ ቆይቷል:: ብሔራዊ ቴአትር ሄደህ ስትመለከት በክረምት ወራት ጀልባ የምትፈልግበት አጋጣሚ ነው ያለው:: ገንዘብ እየተቀበሉ ሰው የሚያሻግሩም ታያለህ:: የውኃ ፍሳሹን የሚቀበሉት ቱቦዎች አሮጌና ትናንሽ ስለሆኑ ልክ በቦሌ መንገድ እንዳደረግነው መቀየር አለባቸው:: ይህ በየደረጃ የሚሠራ ነው:: ግን አሁን እንሠራለን ወደምንለው ዓይነት ከፍተኛ ኮንስትራክሽን ውስጥ የሚያስገባ አይደለም:: ቀለበት መንገዱም ባለበት ነው ዕደሳ የሚደረገው:: በሕንፃ መካከል የሚገኙትን መንገዶችን ደረጃ ታሳድጋለህ እንጂ መንገዶቹን አታፈርስም:: የዚህ ዓይነት ሥራዎች ይቀጥላሉ:: እነዚህን ዋና የሆኑ መሠረታዊ ነገሮች መሥራት ከተቻለ በቀጣይ ማቋረጫዎች ላይ ነው የትራፊክ ጭንቅንቅ የሚኖረው:: እሱን በተቻለ መጠን ከታችና ከላይ የሚሠሩ ነገሮችን እየፈጠሩ የማስተካከል ሥራዎች ይከናወናሉ:: እኔ በተለይ ከፍተኛ የትራፊክ መጨናነቅ አለ ብዬ የማምንባቸው ከመስቀል አደባባይ - ቦሌ፣ ከመስቀል አደባባይ - ቃሊቲ፣ ከአያት - መገናኛና ጦር ኃይሎች መንገድ ይገኙበታል::

ሪፖርተር፡- እዚህ ላይ ግን አሁን ላለው የትራፊክ መጨናነቅ በከፍተኛ ሁኔታ አገር ውስጥ የሚገቡ የተሽከርካሪዎች ቁጥር መብዛት ነው ይባላል:: በግልጽ እየታየ ያለውም የተሽከርካሪዎች ቁጥር መጨመር ነው:: በእርስዎ አስተያየት የተሽከርካሪዎች መብዛት ለትራፊክ መጨናነቁ ምክንያት አይሆንም? ይህንን የሚመጥንስ መንገድ አለ?

ኢንጂነር ፍቃዱ፡- የተሽከርካሪዎች መብዛት ጫናው ብዙ አይደለም:: እነዚህ ማቋረጫዎች ላይ ችግሩን መፍታት ከቻልን ብዙ ተፅዕኖ አይኖርም:: ከእነዚህ ዋና ዋና መንገዶች

ጋር የሚገናኙ የውስጥ ለውስጥ መንገዶችን የመሥራት ነገር ነው መቀጠል ያለበት::

ሪፖርተር፡- አሁን በከተማው ውስጥ እየተገነቡ ካሉ መንገዶች ጋር ተያይዞ የንግድ ሥራቸው የተጐዳባቸው ብዙ ናቸው:: በተለይ የመንገድ ግንባታዎቹ በተፈለገው ጊዜ ካልተጠናቀቁ ደግሞ ብዙ ጉዳት ይደርስባቸዋል:: በዚህ ምክንያት በሚደርሱ ተፅዕኖዎች ባለሥልጣኑ የሚያደርገው ነገር ይኖራል?

ኢንጂነር ፍቃዱ፡- እኛ ይሰማናል:: አልተጐዱም፣ ጉዳት የለም የሚል ነገር የለንም:: መንገዱ እየተሠራ ያለው በብዙ ሰዎች መስዋዕትነት ነው:: ይህንን በደንብ እናውቃለን:: ሌላው አካል ከእነርሱ ሥራ ጋር በተገናኘ የታስክ አስገቢው መሥርያ ቤት እንዴት ያየዋል የሚለው እንጂ፣ የእኛ አዘኔታ የሚጨምረው ነገር የለም:: ግን እነዚህ ሰዎች ቢዝነስ ላይ ባልነበሩበት ጊዜ የታክስ ክፍያው እንዴት ይሆናል የሚለው የመንግሥት ጉዳይ ነው እንጂ መጐዳታቸው በትክክል ይታያል:: ለዚህ ነው ለምሳሌ ቦሌ መንገድ ላይ ስንሠራ ፍሬንድሽፕ አካባቢ በማዶ ያለውን ጨርሰን ሆቴሎቹ ያሉበት አካባቢ ትራፊክ መግባት ጀምሯል:: እነሱን የማገናኘቱን ሥራ እየጨረስን ነው:: ግን መሀል ጌቱ ሕንፃ አካባቢ ያለው ግን ገና በመሆኑ በዚህ እናዝናለን:: ሌላ አማራጭ ስለሌለ ነው:: የከተማውን ዕድገት ማምጣት አለብን:: አገር መለወጥ አለብን:: ሌላ አማራጭ ከሌለ ምን ይደረጋል? ከዚህ አኳያ የተጎዱ እንዳሉ ይሰማናል:: ይህ ቀላል አይደለም:: ኅብረተሰቡ እየከፈለ ያለው መስዋዕትነት ከፍተኛ ነው:: ቦሌ መንገድ ላይ በታክሲ ይንቀሳቀስ የነበረው ሰው በእግሩ ነው የሚንቀሳቀሰው:: በግሌም ይሰማኛል:: ግን ዞሮ ነገ ከሚታየው ዕድገትና የተሻለ ዓለም ከማምጣት አኳያ ልትቀበለው የሚገባ ምሬት ነው:: አማራጭ የለም:: ይህ ልማት በከተማችን መሠረታዊ ለውጥ የሚያመጣ ነው:: ስለዚህ ኅብረተሰቡ አሁን በያዘው የትብብር መንፈስ እንዲቀጥል ነው የሚፈለገው:: ሌላው መነገር ያለበት ነገር መሥራት ብቻ ሳይሆን መጠበቅም ነው:: አሁን እየተከናወነ ላለው ነገር መሠራቱ ላይ ነው እንጂ ርብርብ ያለው መጠበቁ ላይ አይደለም:: የሚፈርሱ ነገሮች ይበዛሉ:: ይህ መቀጠል የለበትም:: ስለዚህ ሕዝብ የራሱን ንብረት መጠበቅ አለበት:: ይህ ከተጠበቀ መንገዶቹ ዕድሜያቸው ይረዝማል:: ሌሎች የተሻሉ መንገዶችንም ማምጣት እንችላለን:: ነገር ግን የሠራኸው መንገድ ካልተጠበቀ

እየተበላሸ ነው የሚሄደው:: እየተበላሸ ከሄደ ደግሞ ሌላ ነገር እሠራበታለሁ ያልከውን ገንዘብ የተበላሸውን እየጠገንክ ነው ጊዜ የምታጠፋው:: ሌላው ከአደጋ ጋር የተያያዘ ነው:: አደጋ ከራሳችን ጥንቃቄ ጋር የሚመጣ እንጂ ቁጣ አይደለም:: ስለዚህ እግረኛውም ከተጠነቀቀ፣ አሽከርካሪውም ከተጠነቀቀ፣ ምልክቶቹን በአግባቡ መጠቀም ከተቻለ፣ ማቋረጫዎቹንና ድልድዮችን በአግባቡ መሻገር ከተቻለ፣ የመንገዶች መሠራት ለሕይወት መጥፋት ምክንያት አይሆንም:: ሁሉም መንገዶች ሲሠሩ መታሰብ ያለባቸው ከአካል ጉዳተኞች ጋር የተያዙ ጉዳዮች ናቸው:: እነሱ በሚጠይቁት መሠረት ባለሥልጣኑ ይሠራል::

ሪፖርተር፡- በከተማው የትራፊክ መጨናነቅ ጋር ተያይዞ የሚታይ ሌላም ችግር አለ:: ከዋናው መንገድ ወደ መኖሪያ ቤቶች የሚገቡ የአስፓልት መንገዶች ለማቋረጫ መጠቀም አይቻልም:: ነዋሪዎቹ መንገዶቹን ዘግተዋል:: እነዚህን መንገዶች የመቆጣጠር ኃላፊነት ያለበት ማነው?

ኢንጂነር ፈቃዱ፡- በመሠረቱ በአዋጁ ላይ የተቀመጠው የመንገዶች ባለሥልጣን ኃላፊነት ነው:: አንዳንድ ቦታዎች ላይ የተሠሩትን መንገዶች ስንመለከታቸው መንግሥት ብቻ አይደለም የሚሠራው:: በተለይ የኮብልስቶን መንገዶች ሥራ ከተጀመረ ወዲህ ትልቅ የሕዝብ ንቅናቄ ተጀምሯል:: ሕዝብ ራሱ ማኅበር ፈጥሮ ነው ሥራውን እየሠራ ያለው:: ስለዚህ ሕዝብ ሁሉ ተሳትፎበት በሚሠራው ሥራ ላይ ባለቤትነቱ የሕዝብም ጭምር ነው:: እኛ አገር ሕግን ተከትለው ታዛዥ ሆነው የሚሠሩ አሽከርካሪዎች የተወሰኑ ናቸው:: በእነዚህ መንደሮች የተሠሩት የአስፓልት መንገዶች የተወሰነ ክብደት የመሸከም አቅም ያላቸው ናቸው:: ስለዚህ መሸከም ከሚችሉት በላይ ትልቅ ቦቴና ከሰል የጫነ ትልቅ መኪና በእነዚህ መንገዶች ላይ መንደር ውስጥ ካልገባሁ ይላል:: ምንም ምልክት ብታደርግ ጥሶ መሄድ ይታያል:: እነዚህ የግድ መገደብ ሊኖርባቸው ይችላል:: ይህንን ምልክት የሚያደርጉት እኛን አስፈቅደው ነው::

ሪፖርተር፡- ከዚህ ከምልክት ውጭ የፍጥነት መግቻ የሚያደርጉ አሉ::

ኢንጂነር ፈቃዱ፡- የፍጥነት መግቻው በጣም አስፈላጊ ነው:: ይህንንም ሲሠሩ ለእኛ ነግረው ነው:: ስለዚህ ከአደጋ አኳያም መደረግ ያለበት ነው::

Page 20: ERROR: The requested URL could not be retrieved ERROR The requested URL could not be retrieved While trying to process the request: TEXT HTTP/1.1 Host: Proxy-Connection: keep-alive

www.ethiopianreporter.com

ገጽ 20 | እሑድ ጥር 19 ቀን 2005ክፍል-1

ማስታወቂያ

I. Description of Requirement:1. ICAP- CU hereby seeks to pre-qualify a suitable vendor(s) with proven experience in supplying:

a) Medical Equipment and instruments,b) Medical Consumablesc) Laboratory Equipmentd) Laboratory Consumablese) Laboratory Reagentsf) Medical furnitureg) Office equipment and furniture

2. To be shortlisted, the vendor must:a) have a valid and renewed trading license and a Tax Clearance

Certificateb) be VAT- registeredc) be registered in the suppliers list issued by the Ministry of

Finance & Economic Development.d) have adequate number of skilled and experienced staff to

perform the said work.e) have adequate experience in undertaking similar works.f) prove capability of providing enough financial resources and

equipment to perform the works. 3. Eligible vendors, who meet all of the pre-qualification criteria in the EOI Response Form, may be invited to participate in the bid for the events organizing and facilitating services.

a. Only those vendors possessing substantial record of performance in similar works are encouraged to participate.

b. Those vendors wishing to participate in the bid must complete the EOI Response Form below. Only the vendors deemed to have adequate expertise, acceptable experience and sufficient size would be invited to participate in the bid.

4. The vendor must have a substantial structure and professional base in procurement. The EOI and capability will be assessed against evidence of skills and experience in providing services in large scale procurement; preferably in the health sector.5. The EOI should be sent along with a Capability Statement including a profile of the organization, covering relevant technical experience along with the financial turnover for the last 3 financial years.6. Price quotes are not required at this stage, and ICAP-CU merely seeks expression of interest to participate in the bid.7. A response to this Request for Expression of Interest does not automatically ensure that any vendor will be selected for Invitation to Bid. Responses are used to select vendors for bid, and will be carefully reviewed. 8. A shortlist of vendors will be compiled in accordance with the procedures set out in CU-ICAP Rules and Procedures. These short-listed vendors will be invited to the bid by a “Request for Proposal”. This bid envisages selection of more than one vendor to provide the above-mentioned services. II. Deadline for submission of EOI:Written EOIs must be marked “Expression of interest for supply of

Medical, Laboratory & Office Equipments, Furniture &Supplies” and delivered to the address below by 10:30 A.M on February 13, 2013.

Columbia University-ICAP Ethiopia

Kirkos Sub-city, Kebele: 05/06/07; Bld #: 021Tel: +251-11-467 44 75/80

P. O. Box 5566Addis Ababa

Ethiopia

III. Late/Incomplete EOI:Any EOI received after the deadline for submission of bids as prescribed or incomplete will be rejected.

Expression of Interest Response Form

Subject: Supply of Medical, Laboratory & Office Equipments, Furniture &Supplies.

As part of the pre-qualification process, interested vendors must provide ICAP-CU with the following information:

1. Name of the company:___________________________________2. Office Address: ______________________________________3. Telephone:_________________________4. Fax: ______________________________5. Email: ____________________________6. Contact Name: ________________________________Structure/capacity:7. Date of establishment of the Company:____________________8. Organizational set up (attach organogram)9. Number of years of experience the company has been working on

similar work: _______________________________________. Past experience10. List no more than ten organizations for which the Firm has provided

similar services within the past 5 years.____________________________________________________________________________________________________________________________________________________________

11. Provide the following information on the services provided for each organization listed above:a. Duration of serviceb. Itemize work performed for each clientc. Total budget d. Customer’s References: Names/ Company/ Title, Telephone

number/ fax number, email addresse. Average number of work force

Vendor’s financial capabilities:

12. Bank statement of the last three months.

13. Profit & Loss Statement and balance sheet for the years 2010, 2011,

and 2012.

International Centers for AIDS Care and Treatment Program-Columbia University

(ICAP-CU) in Ethiopia

Request for Expression of Interest (EOI)

Page 21: ERROR: The requested URL could not be retrieved ERROR The requested URL could not be retrieved While trying to process the request: TEXT HTTP/1.1 Host: Proxy-Connection: keep-alive

www.ethiopianreporter.com

ገጽ 21 | እሑድ | ጥር 19 ቀን 2005 ክፍል-1

Improving Quality of Primary Education Program (USAID/IQPEP) in Ethiopia

_________________________________________________________

በድጋሚ የወጣ ፍላጎት መግለጫ ማስታወቂያ

USAID/Improving Quality of Primary Education Program (USAID/IQPEP) የጭነት መኪናዎችን ተከራይቶ የትምህርት መገልገያ መሳሪያዎችን በሁሉም ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች ወደሚገኙ በፕሮግራሙ ለታቀፉ ትምህርት ቤቶች ማሰራጨት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ለፕሮግራሙ የትምህርት መሳሪያዎችን የማሰራጨት አገልግሎት ለመስጠት ፍላጎት ያላችሁ የጭነት መኪናዎችን አከራዬች ህጋዊና የታደሰ የንግድ ፈቃድ፤ የ VAT ምዝገባ ሰርተፊኬት፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር እና ሌሎች አስፈላጊ ተጨማሪ ማስረጃዎችን በማያያዝ ፍላጎታችሁን በደብዳቤ እንድትገልጹ እየጋበዝን የፍላጎት መግለጫ ደብዳቤው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሥራ ሰዓት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡00 እስከ ጥር 29 ቀን 2005 ድረስ ለUSAID/IQPEP ዋናው መስሪያ ቤት ቢሮ ቁጥር 316 መቅረብ ያለበት መሆኑን እንገልጻለን፡፡ለተጨማሪ መረጃ መስከረም አሰፋ፤ የእቃ ግዢ ኦፊሰርን በስልክ ቁጥር 011 1550874 /011 1111499 ማናገር ይቻላል፡፡

USAID/Improving Quality of Primary Education Program (USAID/IQPEP) in Ethiopia

አራት ኪሎ፣ ትምህርት ሚኒስተር፣ አዲሱ ህንጻ፣ 3ኛ ፎቅፖ.ሳ.ቁጥር 13157

አዲስ አበባ፣ ኢትዬጵያ

በኮንስትራክሽን ዘርፉ ለሴቶች ሠራኞች ልዩ

ትኩረት ያሻልሴቶችና የኮንስትራክሽን ሥራን በሚመለከት

አስተያየት ለመስጠት በማሰብ ይህን ደብዳቤ ላኩኝ:: እኔ አስተያየት ሰጪ በግል ሕንፃ ተቋራጭ ድርጅት ውስጥ በሲቪል መሐንዲስነት በማገልገል ላይ እገኛለሁ::

ሴቶችና የኮንስትራክሽን ሥራ ብዬ ለዚህ አስተያየት የተጠቀምኩት ከመሐንዲስና ከፎርማን በታች ያሉ ግንበኝነት፣ አናፂነት፣ ለሳኝነት ወዘተ. ተብለው የሚጠሩትን የኮንስትራክሽን የሥራ ዓይነቶችን ነው፤ ጉልበት ሥራን ጨምሮ::

ሴት የኮንስትራክሽን ሠራተኞችን ከላይ ከተዘረዘሩት ሙያዎች ጋር አስተሳስሬ ጠቃሚ አስተያየት እሰጣለሁ:: በኢትዮጵያ እነዚህን ከላይ የጠቀስኳቸውን ሙያዎች የሚያሰለጥን ማዕከል የለም:: በአገራችን ሙያዎቹ ለኮንስትራክሽን ዘርፉ መሠረታዊ ግብዓት ቢሆኑም፣ በ100 ሺሕ የሚቆጠሩ የሙያው ባለቤቶች (ሴቶችና ወንዶች) ከተራ የጉልበት ሥራ ጀምረው የባለሙያ ዕቃ አቀባይ በመሆን ዓመታትን በሚፈጅና መደበኛ ያልሆነ የሥራ ላይ ሥልጠና ያገኛሉ::

በአገራችን በሚሊዮን የሚቆጠሩ በኮንስትራክሽን ውስጥ የሚሠሩ ተራ የጉልበት ሠራተኞች አሉ:: በአሁኑ ወቅት የሴት ጉልበት ሠራተኞች ቁጥር በጣም ጨምሯል:: ግማሽ ያህሉ የተወሰነ ጥሪት በመቋጠር ወደ ትውልድ ቀያቸው በመመለስ ተምረው ሥራቸውን መቀየር ይፈልጋሉ:: ግማሾቹ ደግሞ ከጉልበት ሥራ ጋር ሲነጻጸር እጅግ አድካሚ ያልሆነውንና በገንዘብ ደረጃ ሲሰላ በአሁኑ ወቅት 70 እና 80 ብር በቀን የሚያስከፍለውን የልስን፣ የአናፂና የግንበኝነት ሙያ ለምደው ቤተሰብ መሥርተው በሒደት ለመሻሻል በማለም መኖር የሚፈልጉ ናቸው::

ከዚህ ጋር አያያዤ አንዳንድ ነጥቦችን ላንሳ:: ሴቶች በተለያየ ተፅዕኖ ምክንያት ሙያ የመልመድ ዕድላቸው እጅግ በጣም ጠባብ ነው:: በዚህ ምክንያት ከሙያ ሥራ ጋር ሲነጻጸር በጣም ጉልበት የሚያዝለውንና በዝቅተኛ ክፍያ የሚሠራውን ተራ የጉልበት ሥራ ለዓመታት ለመሥራት እንደሚገደዱ በ15 ዓመታት የመሐንዲስነት የሥራ ዘመኔ ለመታዘብ ችያለሁ:: ይህ የሚሆነው ተፈጥሮአቸውንና ልዩ ተሰጥዎአቸውን ባላገናዘበ ምደባና በባህላዊ ተፅዕኖ ምክንያት ነው::

ለዓመታት እንዳጠናሁትና በተግባርም ሞክሬ እንዳረጋገጥኩት፣ ወንዶች መንጠላጠልንና ሚስማርን

በኃይል በመዶሻ መቀጥቀጥ የሚፈልገውን የአናፂ ሥራ ቶሎ በመልመድ እንዲሁም ጊዜያዊ መወጣጫዎችን ወዘተ. በቀላሉ ይሠራሉ:: ሴቶች ደግሞ በብሎኬት ወይም በሸክላ የተሠራ ግንብን በአሸዋና በሲሚንቶ ቅይጥ የመለሰን፣ ጠርዝዎችን በትዕግሥት የማውጣት፣ ማለስለስን አጠቃሎ የያዘውን የልስን ሥራ በቀላሉ ሲካኑትና በተሻለ ጥራት እንደሚሠሩት በተግባር ሞክሬ አረጋግጫለሁ::

በ2004 የሥራ ዘመን የለሳኝ ረዳት አድርጌ የመደብኩዋቸው 20 ሴቶች፣ በ11 ወር ውስጥ ሙያውን ለምደው ለሳኝ በመሆን ከ25 ብር የቀን ደመወዝ ወደ 60 ብር ማደግ ችለዋል:: በዚህ ተፈጥሮንና ተሰጥኦን መሠረት ባደረገ የሥራ ክፍፍልና ምደባ በኮንስትራክሽን ዘርፉ በአንፃራዊነት ለሴቶች ጥሩ ገቢ የሚፈጥር የሥራ ዕድል በስፋት መፍጠር ይቻላል::

ጉልበታቸውንም ለዓመታት በትንሽ ገቢ ከመበዝበዝ መታደግ ይቻላል:: ይሄን ቀናና መልካም ተሞክሮ ትኩረት ላልሰጡት ምናልባትም ጉዳዬ ላላሉት በዘርፉ ውስጥ ላሉ በሙሉ አድርሱልኝ:: በሙያችሁ ለመሐንዲሱም፣ ለኮንትራክተሩም ወዘተ. በሴቶችና በኮንስትራክሽን ላይ የሚሠሩ ሚኒስትሮች ጭምር መልዕክቱን አድርሱልኝ::

የመንግሥት ፕሮጀክቶች ቤቶች ግንባታን ጨምሮ ተሞክሮውን በቀላሉ ወደተግባር መለወጥ ቢቻል፣ በዘርፉ የተሰማሩትን ሴቶች ሕይወት ማቅለል ይቻላል እላለሁ::

(ኢንጂነር ሰለሞን አበራ፣ ከአዲስ አበባ)

‹‹ሼክ መሐመድ ሁሴን አሊ አላሙዲን የገቡልን

ቃል ተጠብቋል››‹‹በዋንዛ በልዩ ልዩ ምክንያት ሠራተኞች እየተባረሩ

ነው፣ ቤተሰቦቻቸውም እየፈራረሱ ነው›› ተብሎ ይድረስ ለሪፖርተር አምድ ታኅሳስ 14 ቀን 2005 ዓ.ም. የወጣው ጽሑፍ የሌለ፣ ያልነበረና ከእውነት የራቀ ነው:: ሆኖ ተገኝቷል ቢባል እንኳን ከምንም በላይ በመሠረታዊ ሠራተኛ ማኅበር ተደራጅቶ አሁንም የአሠሪና ሠራተኛ ግንኙነት ጤናማ በሆነውና የድርጅቱንና የሠራተኞችን መብትና ግዴታዎችን በእኩል መንገድና በድልድይነት ለሚያገለግለው ማኅበር በቀረበ ነበር:: ዳሩ ግን በቴክኖሎጂ ግሩፕ ውስጥ ጠንካራ የማኔጅመነት ሥርዓት ከመኖሩም በላይ ለግልጽነትና ለተጠያቂነት ምቹ ሁኔታ በመፈጠሩ የአሠሪና ሠራተኛ ግንኙነታችን ጤናማ ነው::

በዋንዛ ፈርኒሺንግስ ኢንዱስትሪ ውስጥ ያለው የአሠሪና ሠራተኛ ሕግ በዘፈቀደ ውጣ ወይም ግባ የሚል ሥርዓት የለውም:: በአገር ደረጃም የድርጅቱና የማኅበሩ የጋራ ኅብረት ስምምነት አሻራዎች አይደለም:: ከዚሁ የሠራተኛ ማኅበርም ለግልና ለመንግሥት ድርጅቶች ምሳሌ በመሆን ልምድ እየተወሰደ ይገኛል:: በኢትዮጵያ ሠራተኛ ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን እንዲሁም በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ፌዴሬሽን ይኸው መልካም ተሞክሮ እየተወሰደ ለአዳዲስ ማኅበራት በቪዲዮ ሳይቀር ተቀርፆ እየተሠራጨ ያለ እውነታ ነው:: እኛ ከምናስረዳው በላይ ጠይቆ መረዳት ይቻላል::

የሜድሮክ ኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ሠራተኛ ተኮር ሥርዓቱን የወለደው የኩባንያዎች ፖሊሲ አንደኛው መገለጫና የተሻለ መብትና ጥቅም የሚያሰጥ መሆኑን ለባዶ ጩኸት ላሰሙት አያቁትም አንልም፤ ምክንያቱም እነሱ የበለጠ ያውቁታልና:: ‹‹ተባረርን፣ ቤተሰባችን እየፈረሰ ነው፣ ልጆቻችን ከትምህርት ቤት ቀሩ›› በማለት ለክቡር ሼክ መሐመድ ሁሴን አሊ አላሙዲ የቀረበው የይታደጉን ጥያቄ፣ አግባብ ያልሆነ ጩኸት መሆኑን የዋንዛ ፈርኒሺንግስ ኢንዱስትሪ መሠረታዊ ሠራተኛ ማኅበር ሥራ አስፈጻሚ አረጋግጧል:: በመሆኑም አንድም ሰው ከሥራው የተፈናቀለ ባለመኖሩ ይኸው እውነታ እንዲታወቅና በምላሽነትም እንዲገለጽልን እየጠየቅን፣ በቅርበትም በመምጣት ለማጣራት የሚቻል መሆኑን እናሳውቃለን:: ቅሬታው ሚዛናዊ እንዲሆን እንዲደረግልንና የኩባንያው ስምም ያላግባብ የተጠቀሰ በመሆኑ እጅግ ያሳዘነን መሆኑን እንገልጻለን::

(ከዋንዛ ፈርኒሺንግስ ኢንዱስትሪ መሠረታዊ ሠራተኛ ማኅበር)

የሥልጣን ጥማት ያቃዣል እንዴ?

ጥር 5 ቀን 2005 ዓ.ም. በሪፖርተር ይድረስ ለሪፖርተር አምድ ላይ ‹‹መተካካቱ ክትትል ያስፈልገዋል›› በሚል ርዕስ የቀድሞው የንብ ባንክ ፕሬዚዳንት ከሥራ መገለልና አዲስ ፕሬዚዳንት መሾም አስመልክቶ የተሰጠው አስተያየት፣ ከእውነት የራቀ በመሆኑ ዝም ለማለት ኅሊናዬ ስላልፈቀደልኝ የግል አስተያየቴን በአጭሩ አቀርባለሁ::

በመጀመሪያ ማንም ሰው በአንድ ድርጊት ላይ የተሰማውን ስሜት የሚገልጽበት መንገድ በመኖሩ ወይም በመገኘቱ ሁላችንም ለፈጠረን ፈጣሪ ምስጋና ይግባው:: ለፈቃድ ሰጪው፣ ለአሳታሚ ድርጅቱና ለአዘጋጆች ያለኝን ታላቅ አክብሮት እገልጻለሁ:: በተጨማሪም እጅግ ጠቃሚ ሊሆን የሚችል አስተያየትን ዝም ከማለት ይልቅ በተለያየ ሚዲያ ተጠቅመው ለአንባቢ ለሚያቀርቡ ሁሉ ታላቅ አክብሮት አለኝ::

በመቀጠልም ወደ ዋናው ፍሬ ሐሳብ ልግባና የቀድሞው የባንኩ ፕሬዚዳንት በተመለከተ በተሰጠው

አስተያየት ላይ ያለኝ አስተያየት የሚከተለው ነው::አንድ የሥራ ኃላፊ የሚወስነው ውሳኔና የሚሰጠው

አመራር ስህተት ሲኖርበት ወቀሳ ማቅረብ፣ መተቸት፣ አስተያየት መስጠትና ሁኔታዎች እንዲሻሻሉ ማድረግ እጅግ አስፈላጊና ጠቃሚ ነው:: አንድ የሥራ ኃላፊ ሥልጣን ላይ ሳለ ስህተት ሲሠራ በዝምታ ታልፎ ከሥልጣን ዞር ሲል ግን መሰል አስተያየት መስጠቱ ጠቀሜታው የጐላ አይመስለኝም:: በጊዜው ሐሳባችንን በግልጽ መስጠት እንኳን ባንችል ይህን በሚመስል ሚዲያ ለማስተላለፍ ብንሞክር ኖሮ ሁኔታዎች የበለጠ እንዲሻሻሉ የበኩላችንን አስተዋጽኦ እንደተወጣን ይቆጠር ነበር:: ፕሬዚዳንቱ በቆይታቸው ከመሰሎቻቸው ጋር ባንኩን የመሠረቱና አሁን ያለበት ደረጃ እንዲደርስ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረከቱ ክቡር ሰው ናቸው:: የባንኩን ዕድገት ለማየት አስተያየት ሰጪው ዋቢ ያደረጉት በጥልቀት ማየት በቂ ግንዛቤ ይሰጣል ብዬ እገምታለሁ::

አዲሱ ፕሬዚዳንትን በተመለከተ የተሰጠው አስተያየት ላይ ያለኝ አስተያየት ቀጥሎ አቀርባለሁ::

ፕሬዚዳንቱ ለረጅም ጊዜ ሲሠሩበት የነበረው ባንክ እንደ አስተያየት ሰጪው እርሻ ባንክ ሳይሆን በመንግሥት የተቋቋመና እጅግ በርካታ ዜጐችን ባለኢንዱስትሪ፣ ባለሰፋፊ እርሻ፣ ባለሆቴል ባለቤትና ውጤታማ ያደረገ የመንግሥት የልማት ባንክ ነው:: ከዚህ ባንክ የመጡ በባንክ ኢንዱስትሪው ውስጥ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊ ሆነው በመሥራት ላይ ያሉና በሙያቸው አንቱ የተሰኙ ሠራተኞች በርካቶች ናቸው:: ልማት ባንክ ሲሠራ የቆየ የሥራ ኃላፊ የንግድ ባንክ ሥራ መምራት አይችልም ማለት ከግንዛቤ ማጣት ወይም ማነስ ወይም አስተያየት ሰጪው እንዲሾም የፈለጉት ሰው ባለመሾሙ ከመቆጨት የመነጨ ነው ብዬ እገምታለሁ::

ፕሬዚዳንቱ ስለ ተማሩት ትምህርት ብዙ ማለት ቢቻልም የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን በኢኮኖሚክስ ሁለተኛ ዲግሪያቸውን ደግሞ በኢኮኖሚክስና ፖሊስ ማኔጅመንት ያገኙ መሆኑን ብቻ መግለጽ ይበቃል:: ካሉት የንግድ ባንኮች ውስጥ ሁለተኛ ዲግሪ እንኳ ሳይኖራቸው ለፕሬዚዳንትነት የበቁና ውጤታማ ሥራ በመሥራት ያሉ መኖራቸውን ለማስገንዘብ እወዳለሁ::

ሰው ዝንተ ዓለም የሚኖር ባለመሆኑ የመተካካት ነገር ወደድንም ጠላንም የምንቀበለው እውነታ ነው:: የመተካካቱ ነገር መቀበል ግድ ከሆነ የተተኪዎች የትምህርት፣ የሥራ ልምድና ችሎታ ደብቀን ወይም ሰውረን ሞራላቸውን እንዲነካ ማድረግ ከትክክለኛ ሰው የሚጠበቅ አይመስለኝም:: ለነገሩማ ተሿሚው ብልህና አስተዋይ ስለሆኑ በሀሰት ለሚቀርብ አሉባልታ ቦታ ይሰጡታል የሚል እምነት የለኝም::

እንደ እኔ ዕይታ እንዲህ ዓይነት ከእውነት የራቀ አስተያየት መስጠት ከቅን ልቦና የመነጨ ሳይሆን ከሥልጣን ጥማት የተነሳ ቅዠት ይመስለኛል::

(ከባንኩ ሠራተኞች አንዱ)

Page 22: ERROR: The requested URL could not be retrieved ERROR The requested URL could not be retrieved While trying to process the request: TEXT HTTP/1.1 Host: Proxy-Connection: keep-alive

www.ethiopianreporter.com

ገጽ 22 | እሑድ ጥር 19 ቀን 2005ክፍል-1

ማስታወቂያ

Call for Expressions of Interest: Afrobarometer National Survey

Date for submission: Wednesday 6th February 2013Your expression of interest must be delivered to: [email protected] and/or [email protected] This is a formal call for an Expression of Interest to conduct an Afrobarometer survey of a nationally representative sample of the adult population of Ethiopia during 2013. The purpose of the survey is to measure public attitudes and behaviour on political, economic and social issues in order to inform the public debate about democracy, governance and other policy and development issues.

This call is not a request for proposals and it does not present Afrobarometer’s requirements in full detail. Details will be provided to applicants who are approached to submit formal proposals following an assessment of the Expressions of Interest received.

BackgroundThe Afrobarometer is an independent, non-partisan research project that measures the social, political and economic atmosphere in Africa. The project conducts a comparative series of national public attitude surveys on democracy, markets, civil society and a host of related issues in thirty five (35) African countries. Round 1 survey was conducted in 12 countries (1999-2001); round 2 in 15 countries (2002-2003); and round 3 in 18 countries (2004-2005. Round 4 surveys were conducted in 20 countries (2008-2009) and round 5 surveys are on-going.

The Afrobarometer is dedicated to three main objectives: • To produce scientifically reliable data on public opinion in sub-Saharan

Africa• To build institutional capacity for survey research in Africa and• To broadly disseminate and apply survey results

The Afrobarometer project is run by the Afrobarometer Network, a consortium of independent survey research institutions based mainly in Africa. Four Core Partners (CPs) provide leadership to the Network on research design, fundraising, project management, publication, and the international dissemination of results. The CPs are:

• The Institute for Democracy in Southern Africa (Idasa) in South Africa• The Centre for Democracy and Development (CDD) in Ghana• Institute for Empirical Research in Political Economy (IREEP) in Benin• The Institute for Development Studies (IDS) at the University of Nairobi

in Kenya

The University of Cape Town and Michigan State University are support units within the network.

The network also includes National Partners (NPs) in each participating country. Based in the university, private or non-governmental sectors, these organisations are responsible for survey fieldwork and for the dissemination of survey results at the country level.

The results of the Afrobarometer surveys are fed directly into the policy process. We seek to reach diverse audiences; decision-makers in governments and parliaments, policy advocates and civic educators, journalists and researchers, and donor agencies and investors, as well as, all Africans who wish to become informed and active citizens.

Further information on the Afrobarometer, including publications and country reports can be found at www.afrobarometer.org

All potential service providers (national partners) should provide an up-to-date company/ organizational profile, including CVs of key personnel.

For Additional Information Contact:Mr. Abel Oyuke,Afrobarometer Manager,IDS, University of Nairobi,P.O. Box 30197—00100,Nairobi, Kenya.Phone: +254 722 816 242

+254 736 169 322E-mail: [email protected] [email protected]

www.afrobarometer.org

Federation of Ethiopia National Association of Person With Disabilities(FENAPD)

Invitation for bid for Developing Dynamic websiteNo. 001/2013FENAPD invites interested companies to develop a new dynamic website for our Organization. The Website should have English and Amharic, Public and administrative pages and fully support video and Audio.Requirements1. Who has experienced Dynamic website or web applications

development.2. Renewed Valid lenience and Tin Number3. The bid document and Terms of Requirements (TOR) you can

purchase with none refundable fee 100 birr from the FENAPD during office hours (Monday to Friday, Moring 8:30 - 12:30 and Afternoon 1:30 - 5:30) before Feb 6, 2013.

4. Bids must be accompanied by a bid security 2% CPO on bid Amount (not accepted cash or insurance).

5. The bidder document should sealed with wax and submit before Morning 12:30am on February 6, 2013.

6. Bid opening shall be held in the presence of bidders and/or there legal representatives who wish to attend, on at Morning 10:00am Feb 8, 2013

7. If FENAPD finds other alternatives, it has to right to reject partially or all bids.

8. Interested bidder may obtain further information: Tel: 0 11 1553003 / 0111 564458(morning) / 0911479143(mob)

Address:Semein hotel to Nigeria embassy in front of Ethio-Korea Veterans memorial park

በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

የሞሐ ለስላላሰ መጠጦች ኢንዱስትሪ አ.ማ. ንፋስ ስልክ ፔፕሲ ኮላ ፋብሪካ ልዩ ልዩ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን ባሉበት ሁኔታ በዝግ ጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም ተጫራቾች የጨረታውን ሠነድ በፋብሪካው የግዥና ክምችት መምሪያ ጽ/ቤት በመቅረብ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ) እየከፈሉ በመውሰድና ተሽከርካሪዎቹን በንፋስ ስልክ ፔፕሲ ኮላ ፋብሪካ ቅጥር ጊቢ ቀርቦ በመመልከት የሚገዙበትን ዋጋ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 (አሥር) ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ በፋብሪካው የግዥና ክምችት መምሪያ በማቅረብ መወዳደር ይችላሉ፡፡ጨረታው በ11 (አሥራ አንደኛው) የሥራ ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡

• አመልካቾች የጨረታ ዋስትና ብር 10000.00 (አሥር ሺ ብር) ከባንክ በተመሰከረለት ሲ.ፒ.ኦ ማስያዝ አለባቸው፣

• የመጫረቻ ዋጋ አንተርሶ ማቅረብ አይቻልም፣• የጨረታ አሸናፊ የመልካም ሥራ አፈጻጸም ዋስትና ማስከበሪያ

በመያዣነት የጠቅላላ ዋጋውን 10% በቅድሚያ ማስያዝ ይኖርበታል፣

• ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ በጨረታው አይገደድም፡፡

ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 0114-65-43-79 ግዥና ክምችት መምሪያ ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

Page 23: ERROR: The requested URL could not be retrieved ERROR The requested URL could not be retrieved While trying to process the request: TEXT HTTP/1.1 Host: Proxy-Connection: keep-alive

www.ethiopianreporter.com

ገጽ 23 | እሑድ | ጥር 19 ቀን 2005 ክፍል-1ማስታወቂያማስታወቂያ

PROCURNMENT NO. CPO/02/NCB/LIDETA/2005 E.C.

1. The Commercial Bank of Ethiopia has it is own budget to be used for the construction of Lideta branch office building project with three basements, ground ,mezzanine floor and eleven storey building . A 700 seat multi-purpose hall is also part of the project.

2. Commercial Bank of Ethiopia invites sealed bids from all registered Contractors of Category GC-I or BC-I and having,

- Trade license and construction work certificates valid and renewed for 2005 Ethiopian Calendar year

- VAT & Tax Registration Certificate

- Tax clearance certificate

3. Interested eligible bidders may purchase the bid document and obtain further information at the office of:

Commercial Bank of Ethiopia Construction Projects Office Ras Desta Damtew Road Near to office of Disaster prevention and preparedness (Adjacent to Ghandi Memorial Hospital), Room No. 093 Tel. 251-11 553 04 74/ 11 553 08 82 P.O. Box 255Starting from the date February 4 /2013.

4. Each prospective bidder proposing to bid for this project must be eligible fulfilling the requirements of the Particular Instruction of the Project.

5. A complete set of bidding documents may be purchased by any interested eligible bidder on the submission of a written application to the above address and payment of a non- refundable fee of Birr 2,000.00 (Two Thousands birr only). All bids must be accompanied by a bid security of Birr 100,000.00(Hundred Thousands birr only) The bid security shall be payable on demand to the employer, and must be an irrevocable letter of credit, or Bank Guarantee, or a Certified payment order (CPO) at the bidders option.

6. The Wax-sealed and signed bid for providing the necessary labor, material equipment and any other necessary requirements for the execution and completion of the works specified along with the bid security must be delivered to the;

Commercial Bank of Ethiopia Construction Project Office Ras Desta Damtew RoadNear to office of Disaster prevention and preparedness (Adjacent to Ghandi Memorial Hospital) Tel. 251-11 553 04 74/ 11 553 08 82P.O. Box 255

On or before March 5, 2013, 10:00 am No liability will be accepted for loss or late delivery.

Bids will be opened in the presence of bidders or bidder’s representative who chose to attend at the _address specified above on March 5, 2013, 10:30 am

7. The construction of the work shall be completed within 900 calendar days from commencement of works.

8. Bids should be submitted with ONE ORIGIANL AND THREE COPIES for technical and financial proposals and bid security, each in separate wax-sealed envelopes and all the three then be sealed in an outer envelope and submitted on the date and time specified above.

9. All bids must include 15% VAT (Value Added Tax) on the summery of price quotation.

10. Bidders are instructed to fill, sign and seal all the forms of the bid documents. Failure to fulfill this instruction may result in automatic rejection.

11. The Employer reserves the right to reject any or all bids, to waive informalities, to advertise for new bids or to proceed and do the work otherwise as may be for its best interest.

Commercial Bank of Ethiopia

INVITATION FOR BIDFOR CONSTRUCTION

WORKS(RE-ADVERTIZED)

INVITATION FOR EXPRESSION OF INTEREST FOR PRINTERS / CREATIVE GRAPHIC DESIGNERS IN ADDIS ABABA

TO REGISTER FOR REVIEW AND PRE-QUALIFICATION AS POTENTIAL PRINTERS / SERVICE PROVIDERS

TO UNICEF IN ETHIOPIA

CLOSING DATE: 7th FEBRUARY 2013, 1000 a.m.

The United Nations Children’s Fund (UNICEF), seeks to conduct a survey of the 1) Offset Lithography, 2) Screen Printing and 3) Graphic Design industry in Ethiopia to evaluate and update their internal database and registration systems with selected ‘pre-qualified’ suppliers who will be invited to submit Offers for print and graphic design contracts or will be eligible to participate in Long Term Arrangements (LTAs) and official tenders. To respond to this EOI, all interested vendors are invited to submit Letters in English expressing interest for registration and evaluation. Interested printers and graphic designers will be required to submit a detailed Questionnaire form for pre-qualification review. The Questionnaires for printing or graphic design can be obtained by directly contacting Ms. Yideneku Tilahun on [email protected]. All requests for questionnaires must be submitted with full details and contact numbers and addresses.

Questionnaires must be completed and submitted in both hard copy and soft copy or by e-mail copy as Ms Word and PDF files, no later than 7th February 2013 at 10.00 a.m. to Ms Yideneku Tilahun on [email protected]. All relevant supporting documentation must be attached to the hard copy of the questionnaire. Printers are encouraged to provide selected samples of printing.

It is recommended that printers submit the Questionnaire response format electronically via email or in a CD so that they will be eligible for further evaluation.

Well-established companies with excellent printing quality and graphic design skills and a minimum of 5 years experience with reputable clients, are encouraged to register as potential suppliers of printing and graphic design requirements.

Offset Lithography and Screen Printers will be assessed and qualified for registration on the following criteria;

- Completeness of valid documents submitted as required in the Questionnaire;

- Individual assessment of printer/supplier (Including Financial Status/review);

- Adequate printing/binding equipment;- Adequate printing premises;- Adequate packing, storage and warehouse facilities;- Proven ability to handle both small and large orders;- For Screen Printing; ability to produce high quality t-shirts, caps, banners.- Proven ability to produce high quality work; and work effectively under

pressure,- Capabilities to communicate fluently both in written and verbal English,- Established quality control mechanisms

A limited number of offset and screen printers will be short-listed for physical inspection and evaluation. Vendors with positive evaluations will be invited for participation in the Long Term Arrangement (LTA) Bid process. Other vendors, depending upon the desk assessment, will also be retained for inclusion in appropriate and relative tenders.

UNICEF fully reserves the right to accept or reject registration. Address: UNICEF Ethiopia, Supply Section, Room Nr. 118 (first floor) Attn. Ms. Yideneku Tilahun / Mr. Michael Dagne ([email protected]) / ([email protected]) PO Box 1169, Addis Ababa, Ethiopia Tel. +251-11-5184800 Ext. 4158 (Yideneku), Ext. 4160 (Michael Dagne)

Page 24: ERROR: The requested URL could not be retrieved ERROR The requested URL could not be retrieved While trying to process the request: TEXT HTTP/1.1 Host: Proxy-Connection: keep-alive

www.ethiopianreporter.com

ገጽ 24 | እሑድ ጥር 19 ቀን 2005ክፍል-1

ማስታወቂያ

Page 25: ERROR: The requested URL could not be retrieved ERROR The requested URL could not be retrieved While trying to process the request: TEXT HTTP/1.1 Host: Proxy-Connection: keep-alive

www.ethiopianreporter.com

ገጽ 25 | እሑድ | ጥር 19 ቀን 2005 ክፍል-1ማስታወቂያ

Page 26: ERROR: The requested URL could not be retrieved ERROR The requested URL could not be retrieved While trying to process the request: TEXT HTTP/1.1 Host: Proxy-Connection: keep-alive

www.ethiopianreporter.com

ገጽ 26 | እሑድ ጥር 19 ቀን 2005ክፍል-1

ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን

መታሰቢያ ድርጅት ለኢየሩሳሌም ጥር 25 ቀን 2005 ዓ.ም.

ቅዳሜ የመደበኛና አስቸኳይ የአባላት ጠቅላላ ጉባዔ ስብሰባ

ያካሄዳል፡፡

የጉባዔው አጀንዳዎች፡-

1. የድርጅቱ የ2005 ዓ.ም. ግማሽ ዓመት የሥራ አፈጻጸም

ሪፖርት ያቀርባል፣ ጉባዔው ተነጋግሮ ውሳኔ ይሰጣል፡፡

2. የድርጅቱን ፈቃድ የተመለከተ ሪፖርት ያቀርባል፣

ጉባዔው ተነጋግሮ ውሳኔ ይሰጣል፡፡

ከጉባዔው ፍፃሜ በኋላ የዘመኑን ጉዞ የተመለከተ መግለጫ

ይሰጣል፡፡

ስለዚህ የድርጅቱ አባላት የአባልነት ግዴታቸውን መወጣታቸውን

በማረጋገጥና የድርጅቱን መታወቂያ በመያዝ በዚሁ ቀን ከሰዓት

በኋላ በ8፡00 ሰዓት ቦሌ በሚገኘው የድርጅቱ አዳራሽ ተገኝተው

በጉባዔው እንዲሳተፉ በአክብሮት እናሳስባለን፡፡

የኢየሩሳሌም መታሰቢያ ድርጅት

የጠቅላላ ጉባዔ መደበኛና አስቸኳይ የስብሰባ ጥሪ

CALL FOR CONSULTANCYADHENO: INTEGRATED RURAL DEVELOPMENT ASSOCIATION

Job DescriptionBackgroundADHENO: Integrated Rural Development Association is a non-profit indigenous non-governmental organization established in 2002 and re-registered as and “Ethiopian Resident Charity Organization” in 2009 (Registration No. 0353). The primary purpose of ADHENO is to contribute towards alleviation of poverty and improving the living conditions of rural communities by improving the productive potential of the land resource base and building the capacity of the communities it works with. As part of its economic empowerment program, ADHENO has recently helped communities in its project site to establish a cooperative (Tegulet Bee product Development and Marketing Cooperative). The objective of the cooperative is to help its members produce more and better quality of honey which should sale at a competitive price. The strategy includes awarness creation, training on the management of hone bee, managing the cooperative and developing competitive market for the bee products.The cooperative wishes to scale-up its operation in Bassona Worana Worana Woreda. The objective of the present consultancy is to map beekeeping potential of three kebeles in Bassona Worana Woreda and selected kebeles of adjacent woredas as well as recommend actions to augment productivity as well as further develop market accessibility.Qualifications required

• At least a Master Degree in Apiculture• Experience in honey bee Management, assessment of production

potential and market linkage Application GuidelineThe consultant may collect the Terms of reference from ADHENO’s office off Haile G/Silassie Road, near Plaza Hotel (011 663 50 80 or 0911 169341) before February 5, 2013. Applicants are expected to submit in person their appreciation of the project as well as technical and financial proposal with copies of relevant credentials.

በሁነኛው ጓዴ

የኢትዮጵያን ፖለቲከኞች በተመለከተ በዚህ ጋዜጣ ላይ በርካታ ጽሑፎች እየተስተናገዱ ነው:: የጽሑፎቹ አማካይ ነጥብ የያኔዎቹንና የዛሬዎቹን ፖለቲከኞች እያካለለ ነው:: በተለይ ራሱን ‹‹ያ ትውልድ›› በማለት የሚጠራው ቡድን አባላትና የዚህ ዘመን ሰዎች በጸሐፊዎቻችን አተያይ እየተመዘኑ ነው:: ግማሽ ክፍለ ዘመን ያልሞላው የኢትዮጵያ የፖለቲካ ንቅናቄ ተዋንያን ሲመዘኑ አጠቃላዩን ድባብ ማሳየት ካልቻልን፣ ከላይ ነካ ነካ የሚደረገው ፖለቲካችን የደበዘዘው ምስሉ ጥርት ብሎ አይታይም:: በርካታ ስንክሳሮች የታጨቁበት የአገሪቱ ፖለቲካ ዛሬም እንቆቅልሽ ከሚሆንባቸው ዜጎች መካከል አንዱ ብሆንም፣ በጣም መሠረታዊ የሆኑ ችግሮቻችንን ግን ነቅሼ ማውጣት እችላለሁ::

በመጀመርያ ደረጃ አገሪቱ ከፊል ፊውዳልና ከፊል ካፒታሊስት አስተሳሰብ ባላቸው ልሂቃን ቅራኔ ውስጥ መዋዥቅ የጀመረችው፣ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ የመጀመርያውን የአገሪቱን ፓርላማ በመልካም ፈቃዳቸው መሥርተው፣ በአገሪቱ አጠቃላይ ጉዳይ ላይ መምከር ከተጀመረ ወዲህ ነው ቢባል ስህተት አይሆንም:: የፋሺስት ኢጣሊያ ጦር ተሸንፎ ንጉሡ በእንግሊዞች ረዳትነት ሥልጣናቸውን በሚያጠናክሩበት ወቅት አንዱ ትልቁ ሥራቸው አዲሱን ትውልድ በማስተማር የቀድሞውን ትውልድ መተካት ነበር:: በዚህም መሠረት በርካታ ኢትዮጵያውያን በአገር ውስጥና በውጭ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እየተማሩ የዘመኑን ዕውቀት እንዲገበዩ ጥረት ተደርጓል:: አገሪቱ ከዘመኑ ግስጋሴ ጋር እኩል እንድትራመድ በማሰብ በተደረገው ጥረት በርካታ ወጣቶች በተለያዩ አገሮች ዩኒቨርሲቲዎች እየተማሩ በመኳንንቱና በመሳፍንቱ የተያዘውን ቢሮክራሲ እንዲረከቡ መደረጉን የምንረሳው አይደለም:: የዘመነ መሳፍንትና የአዲሱ ትውልድ መቃቃር የተጀመረው ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ነበር::

አዲሱ ትውልድ አገሪቱ ለምን ወደኋላ እንደቀረች መጠየቅ ሲጀምር የተገለጸለት አንደኛውና ዋነኛው ምክንያት፣ ጥቂት

ተ ሟ ገ ትተስፋ መቁረጥ ከሞት የከፋ ነው

ፊውዳሎች የአገሪቱን መሬት በቁጥጥራቸው ሥር በማዋል ብዙኅኑን ሕዝብ አደህይተው መግዛታቸው ነው:: በተማከለው ንጉሣዊ አስተዳደር ዙርያ የተኮለኮሉ የዘመኑ ገዢዎች አገሪቱን የገዛ ርስታቸው በማድረግ ብዙኅኑን ሕዝብ ተጠቃሚ አለማድረጋቸው፣ የትምህርት፣ የጤናና የሌሎች ማኅበራዊ ዘርፎች ለሕዝቡ ተደራሽ አለመሆናቸው፣ ሰፊው ሕዝብ በገዛ አገሩ ባይተዋር መደረጉ፣ ወዘተ በአዲሱ ዘመን ትውልድና በቆየው መካከል ቅራኔ ተፈጠረ:: በጄኔራል መንግሥቱ ነዋይ የተመራው የከሸፈው መፈንቅለ መንግሥት የዚህ ውጤት ነበር:: ‹‹መሬት ላራሹ›› የሚባለው ታሪካዊ ጥያቄ የተነሳውም በዚህ ምክንያት ነበር:: በአገር ውስጥና በውጭ የተማሩ ኢትዮጵያውያንና ተማሪዎች በሥርዓቱ ላይ ማመፅ የጀመሩት ከዚህ በኋላ ነበር:: የየካቲት 1966 ታላቁ ሕዝባዊ አብዮት የተቆጣጠለውም በዚህ መነሻ ነበር:: ይህ እንግዲህ የዛሬ አርባ ዓመት አካባቢ የነበረው የኢትዮጵያ የፖለቲካ ጥንስስ ነው::

የየካቲት አብዮት ፈንድቶ የፊውዳሉ ሥርዓት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ተወግዶ አገሪቱ በለውጥ ማዕበል ስትገፋ፣ በአገሪቱ ታሪክ ለመጀመርያ ጊዜ ታላቅ ሕዝባዊ መነሳሳት ታየ:: ተማሪዎችን፣ ሠራተኞችን፣ አርሶ አደሮችን፣ ወታደሮችንና ሌሎች የኅብረተሰብ ክፍሎችን ያካተተው ይኼ ታሪካዊ ሕዝባዊ ንቅናቄ የለውጥ ፈላጊውን ሕዝብ ምኞትና ፍላጎት ፍንትው አድርጎ ያሳየ ነበር:: ይኼ ሕዝባዊ አብዮት ድንገት ሳይታሰብ መሣርያ በታጠቀው ጦር በመጠለፉ አብዮቱ ተቀለበሰ:: በዚህ ምክንያት አዲስ ፖለቲካዊ አሠላለፍ በመፈጠሩና የቅራኔ አፈታቱም ኃይል የተቀላቀለበት ስለነበር የለውጥ ፈላጊው ሕዝብ ልጆች ደም ፈሰሰ:: ከአፄው ሥርዓት በኋላ ሕዝባዊ መንግሥት ተመሥርቶ አገሪቱ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ትገነባለች ተብሎ ሲጠበቅ የኢትዮጵያ ወጣቶች ደም እንደጎርፍ ፈሰሰ:: ብዙኅኑ በየእስር ቤቱ ታጉረው ተሰቃዩ፣ የተቀሩት ተሰደዱ:: የባሰባቸው አምፀው ጫካ ገቡ:: ለአፍሪካ አርዓያ ይሆናል የተባለው አብዮት የአገሪቷን ልጆች በልቶ ተዳፈነ:: ለአገራቸው

ታላቅ መስዋዕትነት የከፈሉ ጀግኞችና አርበኞች ተፈጁ:: ለዲሞክራሲያዊ ሥርዓት የታገሉ የተማሩ ወጣቶች እንደወጡ ቀሩ:: አብዮቱ በምርጥ ወታደሮች ተቀምቶ ብዙኅኑ ሕዝብ ታፈነ:: ኢትዮጵያ የመርገምት አገር ሆነች:: የሚቀጥሉት 17 ዓመታት የእንባና የሞት መገለጫ ሆኑ::

ማለፉ አይቀርምና ለ17 ዓመታት በኢትዮጵያ ሕዝብ ጫንቃ ላይ የተሳፈረው የደርግ መንግሥት በተራው አይወድቁ አወዳደቅ ደረሰበት:: አገሪቱን አፍኖ የያዘው ደርግ የዜጎችን ሰብዓዊ መብት በመጣስ፣ ሐሳብን በነፃነት የመግለጽ መብት በመንፈግ፣ አገሪቱን በማደህየትና የእርስ በርስ ግጭት ውስጥ በመዝፈቅ፣ ለሕዝቡ መሠረታዊ ፍላጎቶች ደንታ ቢስ በመሆን፣ ወዘተ አገሪቱን አደቀቀ:: ከሕዝብ ፍላጎት በተቃራኒ ይጓዝ የነበረው ደርግ ብቻውን ሲቀር የሚመካበት ጦር ኃይልና የታጠቀው ዘመናዊ መሣርያ ሊያስጥለው አልቻለም:: በመጨረሻም ኤርትራን ከባህር በሮቿ ጋር ለሻዕቢያ አስረክቦ፣ የተዘፈዘፈበትን ሥልጣን ደግሞ ለኢሕአዴግ አሳልፎ ሰጠ:: እንደ ጎልያድ ይፈሩ የነበሩት መንግሥቱ ኃይለ ማርያም አገር ጥለው ሲሸሹ የማይደፈሩት ባለሥልጣናቶቻቸው ወደ እስር ቤት ተሸኙ:: ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ደርግ ታሪክ ሆነ:: ምንም እንኳን ኢሕአዴግ ዛሬም ራሱን ከደርግ ጋር ማነፃፀሩን ባይተወውም::

በድል አድራጊነት የአራት ኪሎ ቤተ መንግሥትን የተቆጣጠረው ኢሕአዴግ ሰላም፣ ዲሞክራሲና ሰብዓዊ መብትን ስለማክበር እየደሰኮረ አገሪቱን ጠቅልሎ ያዘ:: በሥልጣን ላይ ሃያ አንድ ዓመታት ያስቆጠረው ኢሕአዴግ ለተቃውሞ ፖለቲካ በሩን በመክፈት፣ ሐሳብን በነፃነት የመግለጽ መብትን በመቀበል፣ አዲስ ሕገ መንግሥት በማርቀቅ፣ ኢኮኖሚውን ከዕዝ ወደ ነፃ ገበያ በማሸጋገር፣ በመሠረተ ልማት አመርቂ ተግባሮችን በማከናወን፣ አራት ተከታታይ ምርጫዎችን በማካሄድ፣ ወዘተ ከደርግ መንግሥት የተሻለ መሆኑን ለማስመስከር ተንቀሳቅሷል:: ኢሕአዴግ ራሱን ብሶት የወለደው በማለት በበርካታ ሰማዕታቱ ተጋድሎ ለሥልጣን ቢበቃም፣ አሁን ድረስ መልስ ሊሰጥባቸው

Page 27: ERROR: The requested URL could not be retrieved ERROR The requested URL could not be retrieved While trying to process the request: TEXT HTTP/1.1 Host: Proxy-Connection: keep-alive

www.ethiopianreporter.com

ገጽ 27 | እሑድ | ጥር 19 ቀን 2005 ክፍል-1

ለሚመለከተው ሁሉየመ/ቤታችን የጤና ባለሙያ የሆኑት ሲስተር ኤለን ወልዱ ፈረደ

በጉልበታቸው መገጣጠሚያ ላይ በደረሰባቸው ከፍተኛ የጤና ችግር

ምክንያት ህክምናቸውን ሲከታተሉ የነበረው በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ

ሆስፒታል በቁጥር ጥቁ2/4/37829 በ15/10/2004 ዓ.ም የተጻፈ ማስረጃ

ተሰጥቷቸዋል ነገር ግን በውጭ አገር ለመታከም $ 50,000 /ሃምሳ ሺህ የአሜሪካን ዶላር/ በመጠየቃቸው ይህንን ለመሸፈን ግን አቅማቸው ስለማይፈቅድ የወገናቸውን እርዳታ በአምላክ ሰም ይማፀናሉ፡፡ ይህንን

ችግራቸውን ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት ድጋፍ ለማድረግ ፍቃደኛ የሆናችሁ

ወገኖች የሚከተለውን የቁጠባ ሂሳብ ቁጥር በመጠቀም የተቻላችሁን እርዳታ እንድታደርጉ እና ህይወታቸውን ከአደጋ እንድትታደጉ በፈጣሪ ስም ይማፀናሉ፡፡

ተ.ቁ. የቁጠባ ሂሳብ ያለበት ባንክ የሂሳብ ቁጥር

1 አዋሽ ኢንተርናሽናል ባንክ (ኦዳ ታወር) 01320035349600 ካዛንቺስ

2 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ (አንድነት ቅርንጫፍ) 1000024300815

ማስታወሻ፡-ጉዳዩን በተመለከተ ማነጋገር ለሚፈልግ ይህንን ስልክ ቁጥር መጠቀም ይችላል፡፡

0913 54 19 750910 51 12 80

ለሚደረግላቸው ትብብር ሁሉ ከልብ እናመሰግሃለንየአዲስ አበባ ጤና ቢሮ

Meseret Humanitarian Organization (MHO) is nonprofit local

charitable organization (NGO) that is legally registered under

Ethiopian law and registered under license no. 2455 in October 14,

2011 according to the new government guidelines. The main objectives

of the organization are to bring about changes in the live of orphan

and vulnerable children and destitute women.

MHO here by invites all interested competent registered and recognized

audit firms by Ethiopian Auditors General and other responsible

bodies to submit their proposal to audit books of accountant for the

year ended December 31,2012.

The bidder are required for attach renewed business license, VAT

registration certificate, TIN certificate technical and financial proposal

together with date of commencement and completion of task within

one sealed envelope submit in our office in person within 5 working

days from the first announcement date.

For more information please contact our office by telephone

no+251-118-50-36-33 +251-910-28-23-29 +251-930-07-86-79

ተ ሟ ገ ት

ያልቻሉ በርካታ ጥያቄዎች ይነሱበታል:: በሰብዓዊ መብት አከባበር ረገድ ያለው ስም በጣም የወረደ ነው:: አራት ጊዜያት ምርጫዎችን ቢያካሂድም ምርጫዎቹ ዓለም አቀፍ መስፈርትን ያሟሉ እንዳልሆኑ ራሱ ጋብዞ ባመጣቸው የምርጫ ታዛቢዎች ተነግሮታል::

በተለይ በ1997 ምርጫ ምክንያት በአገሪቱ የተፈጠረው ፖለቲካዊ መነሳሳት እንዲዳፈን በማድረጉና በርካታ ዜጎች በመገደላቸው ዛሬም ድረስ ጣት ይጠነቆልበታል:: በመልካም አስተዳደር ዕጦት ሕዝቡ አሁንም እየጮኸ ነው:: ሙስና የሥርዓቱ መገለጫ እስኪመስል ድረስ ቅጥ አጥቷል:: በበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማኅበራት አዋጅ ምክንያት የአገሪቱ ሲቪል ማኅበረሰብ ሽባ ተደርጓል:: በፕሬስ አዋጁ ምክንያት የአገሪቱ የፕሬስ ነፃነት የይስሙላ ሆኗል:: በፀረ ሽብርተኝነት ሕጉ ምክንያት የተቃዋሚ ፖለቲከኞችና የጋዜጠኞች እንቅስቃሴ ተገድቧል:: ከድጡ ወደ ማጡ የሆነው የአገሪቱ ፖለቲካ ሥነ ምኅዳር በኢሕአዴግ ቁጥጥር ሥር ሆኗል:: መንግሥትና ገዢውን ፓርቲ ለመለየት እስከሚያስቸግር ድረስ መንግሥታዊ ተቋማትና በመንግሥት ቁጥጥር ሥር ያለው ሚዲያ የኢሕአዴግ ንብረት ሆነዋል:: ብዙ ብዙ ማለት ይቻላል:: ኢሕአዴግ ለነፃነት ተጋድሎ ከፈልኩ ላለው መስዋዕትነት ግማሹን ያህል እንኳ ቢሠራ ኖሮ ካለፉት ሥርዓቶች ምን ያህል የተሻለ ይሆን እንደነበር ስናስብ እናዝናለን::

በደርግ አፈናና ግድያ ሞራሉ ተንኮታኩቶ ወድቆ የነበረው ሕዝብ ለረጅም ዓመታት ከፖለቲካ ተገልሎ ነበር:: ሌላው ቀርቶ በደርግ እስር ቤቶች ስቃይ የደረሰባቸው ዜጎች የፖለቲካ ጉዳይ ሲነሳ እንዴት ይደነብሩ እንደነበር የምናውቅ እናውቀዋለን:: ዛሬም ድረስ ከመደንበር ያልተላቀቁ በርካታ የስቃይ ሰለባዎች አሉ:: ይህ አንገቱን እንዲደፋ የተደረገ ሕዝብ ‹‹ፖለቲካና ኮረንቲን በሩቁ›› ይል የነበረው ምንም ዓይነት ዋስትና ስላልነበረው ነው:: ኢሕአዴግ ሥልጣን በያዘባቸው የመጀመርያ ዓመታት ስለሕዝቡ ነፃነት ቢደሰኩርም፣ ከእሱ ዓላማ በተቃራኒ የተመሠረቱ የፖለቲካ ፓርቲዎችን ዓይኑ እየቀላ ዝም ቢልም፣ የኋላ የኋላ ግን በነፍጠኝነትና በጠባብነት እየፈረጀ ቁም ስቅላቸውን ማሳየቱን ማን ይክዳል? እየተንገዳገዱም ቢሆን ለ97 ምርጫ የደረሱት

ፓርቲዎች በመጨረሻ ለመቀናጀትና የሕዝቡን ቀልብ ለመሳብ የቻሉት እኮ የኢሕአዴግ ፈሩን የሳተ ጭቆና በመብዛቱ ነበር::

መኢአድ፣ ኢዴፓና በኋላ የተፈጠሩት ቀስተ ደመናና ኢዲሊ ቅንጅት የሚባለውን ስብስብ መሥርተው ከኢሕአዴግ የተሻሉ መሆናቸውን ለሕዝብ ለማስረዳትና ተቀባይነት ለማግኘት የፈጁባቸው ከአምስት ያነሱ ወራት ብቻ እንደነበሩ ስናስብ፣ ኢሕአዴግ ምን ያህል በሕዝብ ዘንድ የተፈጠረበትን ጥላቻና ማግለል በቀላሉ እንገነዘባለን:: በተለያዩ መስኮች ከኢሕአዴግ የተሻለ አማራጭ ይዘው በመቅረብ ሕዝቡን ማንቀሳቀሳቸው በሕዝቡ ውስጥ ምን ያህል የለውጥ ፍላጎት እንደነበረ ግልጽ ነበር::

ምንም እንኳን ዕድለ ቢሱ ፖለቲካችን ከሰላም ይልቅ ለጠብ፣ ከዲሞክራሲ ይልቅ ለጉልበት፣ ከፍትሕ ይልቅ ለሕገወጥነት የቀረበ ቢሆንም፣ ያኔ በአጭር የተቀጨው የሕዝቡ መነሳሳትና የጋራ ፍላጎት ጊዜውን ጠብቆ መሳካቱ አይቀርም ብዬ አስባለሁ:: የቅንጅትን ስብስብ የመሠረቱት ግለሰብ ፖለቲከኞቻችን በፈጠሩት ውዥንብርና ኢሕአዴግ ባደረሰው ገደብ የለሽ የኃይል ጥቃት የሕዝቡ መነሳሳት ቢከሽፍም፣ ለዲሞክራሲ የሚከፈለው መስዋዕትነት ወደፊትም ይቀጥላል:: የኢትዮጵያ ሕዝብ በነፃነት መኖር ይፈልጋል ስንል አማራጮች ሊቀርቡለት የግድ ነው:: ሕዝብ የሥልጣን ምንጭ ነው ሲባል የመንግሥት ሥልጣን በትክክለኛ ምርጫ አማካይነት ሊያዝ ይገባዋል ማለት ነው::

ኢሕአዴግ 99.6 በመቶ የፓርላማ መቀመጫዎችን በሕዝባዊ ምርጫ ይዤአለሁ ሲል ቆም ብሎ ራሱን እንደገና ሊጠይቅ ይገባዋል:: ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት የሚኖረው በአማራጮች መካከል እንጂ ለአንድ ወገን ባደላ የጉልበት ምርጫ አይደለም:: ሁሌም እንደሚባለው በርካታ ብሔር ብሔረሰቦች፣ የተለያዩ ቋንቋዎች፣ ባህሎችና ልማዶች ባሉበት አገር ውስጥ አንድ ፓርቲ የአገሪቱን ፓርላማ ጠቅልሎ ያዘ ሲባል ምንም አሳማኝ ምክንያት አይኖርም:: ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት የሚመሠረተው በተለያዩ ፍላጎቶች መካከል በሚካሄድ ፍትሐዊ ውድድር በሚገኝ የሕዝብ ዳኝነት ብቻ ነው:: ከዚያ ውጭ ሌሎችን ከመድረኩ እየገፉ ለብቻ መሮጥ ለአገሪቷ ፋይዳ የለውም:: ኢሕአዴግ በሚገባ ማወቅ ያለበት ‹‹ብቻውን የበላ ብቻውን ይሞታል›› የሚለውን ዕድሜ ጠገብ ብሂል ብቻ ነው:: ሕዝብን ያገለለ

አካሄድ ማንንም የትም አላደረሰምና::በሌላ በኩል ደግሞ የኢትዮጵያ ተቃዋሚ

የፖለቲካ ድርጅቶች የተሻለ አማራጭ ይዘው ከመቅረባቸው በተጨማሪ ጠንካራና ፅኑ መሆን ይገባቸዋል:: እየታገሉ ያሉት ከኢሕአዴግ ጋር መሆኑን መገንዘብ አለባቸው:: ኢሕአዴግ በሁሉም መስክ የፈረጠመ በመሆኑ፣ የጫካም ሆነ የከተማ ትግል ስልትን በሚገባ የተካነበትና በማንኛውም ጊዜ የበላይነት ለመያዝ እንቅልፉን የማይተኛ ነው:: እንዲህ ዓይነቱን ድርጅት ፖለቲካን የትርፍ ጊዜ ሥራ ያደረጉ ጠበቆች፣ ነጋዴዎች፣ መምህራን፣ ጡረተኞች፣ ወዘተ የሚመሯቸው ፓርቲዎች ሊቋቋሙት አይችሉም:: ራሳቸውን ለሙሉ ጊዜ የፓርቲ ፖለቲካ ለሰጡ ወጣት ፖለቲከኞች አመራሩን አሳልፈው ካልሰጡ ዋጋ አይኖራቸውም:: ኢሕአዴግ ከስድስት ሚሊዮን በላይ አባላት ይዞ ስለ መተካካት ደረቱን ነፍቶ ሲያወራ በአዛውንቶች የሚመሩት የተቃዋሚ ፓርቲዎች የት እንደሚደርሱ ግራ ያጋባል:: ኢሕአዴግን በምርጫ ለማሸነፍ የሕዝቡን ቀልብ ማግኘት ያስፈልጋል ሲባል የኢሕአዴግን ድክመት ብቻ ለማጋለጥ መሯሯጥ የትም አያደርሳቸውም:: ብዙዎቹ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች ራሳቸውን ለፓርቲ ፖለቲካ ያዘጋጁ አይመስሉም::

የፖለቲካ ሥራቸው ለኑሮአቸው ከሚያደርጉት መሯሯጥ በኋላ የሚታሰብ ይመስላል:: ጉልህ በሆኑ የፖሊሲ አጀንዳዎች ላይ ኢሕአዴግን ለመተቸት ይረባረባሉ እንጂ አማራጭ ብለው የሚያቀርቡት የላቸውም:: የፋይናንስና የሎጂስቲክስ እጥረት ስላለባቸው ስብሰባ ለማካሄድ እንኳ አቅሙ የላቸውም:: የአገሪቷን ዙሪያ ገብ ችግሮች በባለሙያዎች አስጠንተው ለሕዝቡ የተሻለ አማራጭ ማቅረብ ይቅርና እዚህ ግቡ የሚባሉ አባላትና ደጋፊዎች የሉዋቸውም:: ኢሕአዴግ እግር እግራቸውን እየተከተለ ከሚያዳክማቸው በተጨማሪ እርስ በርሳቸው ተገናኝተው ቅራኔያቸውን በማጥበብ ጠንካራ ሆነው ለመውጣት ጥረት ሲያደርጉ አይታዩም:: ትግሉ መራራና እልህ አስጨራሽ መሆኑ እየታወቀ በትንሽ በትልቁ ተስፋ ሲቆርጡ ይታያሉ::

ተቃዋሚ ፓርቲዎች በመጀመርያ የጠራ ዓላማ ሊይዙ ይገባቸዋል:: ይህን ዓላማ በሚገባ አብጠርጥረው የራሳቸውን አይዲኦሎጂ ሕዝቡ ውስጥ የሚያሰርፁበትን መንገድ ካላፈላለጉ ችግራቸው ይቀጥላል:: የብዙዎቹ የፓርቲ

Page 28: ERROR: The requested URL could not be retrieved ERROR The requested URL could not be retrieved While trying to process the request: TEXT HTTP/1.1 Host: Proxy-Connection: keep-alive

www.ethiopianreporter.com

ገጽ 28 | እሑድ ጥር 19 ቀን 2005ክፍል-1

ማስታ

ወቂያ (xb!s!NÃ ÆNK ¼x.¥.¼)

BANK OF ABYSSINIA (S.C.)

ተ ሟ ገ ት

መሪዎች ችግር ራዕይ አልባ መሆን ነው:: ለምሳሌ በኢዴፓና በመኢአድ መካከል ይኼ ነው የሚባል የመስመር ልዩነት ሳይኖር በግለሰቦች መካከል በተፈጠረ ጠብ ብቻ ተለያይተው ይጓዛሉ:: ከዚያም አልፈው ተርፈው ይወነጃጀላሉ:: መድረክ የሚባለው ስብስብ ወደ ግንባር ተሸጋግሬያለሁ ቢልም የተለያዩ ፍላጎት ባላቸው አባል ድርጅቶች ምክንያት አንድ ቀን መፈረካከሱ አይቀርም:: ኅብረ ብሔርና ብሔር ተኮር ድርጅቶች መቼም ቢሆን የሚያስማማቸው የጋራ ዓላማ የላቸውምና::

ሌላው ቀርቶ በፌዴራሊዝም ፅንሰ ሐሳብና በመሬት ጉዳይ ላይ የሚግባቡ አይደሉም:: ከዚህ በላይ ደግሞ የፖለቲካ ድርጅቶቹ ከዓመታት በፊት የነበሩባቸውን ቁርሾዎች ይዘው በተለያዩ መድረኮች ሲላተሙ ይስተዋላሉ:: በቀላሉ ሊፈቱ የሚችሉ ቅራኔዎቻቸውን ማስታረቅ አቅቶአቸው በአገር ውስጥና በውጭ ደጋፊዎቻቸው ሳይቀር ጠባቸው ተካሮ ይታያል:: የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች የተጓዙበትን መንገድ አይተውና ከሚስተዋሉባቸው ፀረ ዲሞክራቲክ አካሄዳቸው ካልታቀቡ ለህልውናቸውም ያሰጋዋል:: በተለይ አንዳንዶቹ ሥልጣን ቢይዙ ምን ይዘው ይመጡ ይሆን ተብለው የሚያስፈሩ ናቸው:: አፍኖናል ብለው ከሚወቅሱት ኢሕአዴግ በላይ አፈና ሊያመጡ የሚችሉ የፓርቲ መሪዎች መኖራቸውን ስናስብ ብንፈራ አይፈረድብንም::

አሁን ያለንበት ሁኔታ ለትክክለኛ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ጥያቄ እንድናቀርብ ያስገድደናል:: በመጀመርያ ደረጃ የአንድ ፓርቲ የበላይነት ወይም አውራነት ለአገር ዕድገት አይበጅም:: በኢሕአዴግ የበላይነት የተያዘው የፖለቲካ ሥነ ምኅዳር ለሁሉም ወገኖች እኩል ሆኖ መዘጋጀት ይገባዋል:: ፍትሕ የሚኖረው፣ የሕግ የበላይነት የሚሰፍነው፣ ሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች የሚከበሩት፣ ሁሉም ዜጎች በእኩልነት የሚሳተፉት የሁሉም ወገኖች የተለያዩ አስተሳሰቦች እኩል ሲደመጡ ነው:: እኩልነት በሌለበት ዲሞክራሲ አይኖርም:: የኢትዮጵያ ዲሞክራሲ መሠረቱ መጣል ያለበት በዜጎች እኩል ተሳትፎ ብቻ ነው:: ሰላማዊና ሕጋዊ ዜጋ ያለምንም መሸማቀቅ በፖለቲካው ተሳትፎ እንዲኖረው መደረግ አለበት::

የዲሞክራሲ ግቡ ሥልጣንን የሕዝብ ማድረግ እንጂ አምባገነንነትን ማስፈን አይደለም:: በዚህ ዘመን ደግሞ ይህ ተግባራዊ ይሆን ዘንድ ወጣቱ ትውልድ የአገሪቱን የፖለቲካ ምህዋር መረከብ አለበት:: የደፈረሰው የአገሪቱ ፖለቲካ ጠርቶ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት እንዲያብብ ዜጎች ተሳትፎአቸው መጎልበት አለበት:: የኢትዮጵያ ፖለቲካ ከተተበተበበት የጥላቻና የመናናቅ አባዜ መላቀቅ ይኖርበታል:: በዲሞክራሲያዊ አስተምህሮ ላይ መሠረቱን ያልጣለ የፖለቲካ ፓርቲና ፖለቲከኛ ለዚህ ዘመን አይረቤ ናቸው:: በመሆኑም ሙሉ ጊዜያቸውን ለፖለቲካ ትግል የሰጡ ወጣት ዲሞክራት ተተኪዎች ዕድሉ ተሰጥቷቸው ለዘመናት ከተዘፈቅንበት አዙሪት ውስጥ መውጣት አለብን:: ካልደፈረሰ ስለማይጠራ ይኼንን አማራጭ መቀበል ይኖርብናል::

በአገራችን በመጪው ሚያዝያ ለአዲስ አበባና ለአካባቢዎች ምክር ቤቶች ምርጫ እንደሚካሄድ እየሰማን ነው:: ለእዚህ ምርጫ በመላ አገሪቱ ከ23 ሚሊዮን በላይ መራጮች መመዝገባቸውንም እንዲሁ:: ገዥው ፓርቲና አጋሮቹ ለዚህ ምርጫ ከፍተኛ ዝግጅት እያደረጉ ባሉበት በዚህ ወቅት በርካታ ተቃዋሚ ፓርቲዎች እንደማይሳተፉ እየተሰማ ነው:: በተለይ በአዲስ አበባ ከተማ ምርጫ ስለመኖሩም የማያውቁ ሰዎች መኖራቸው ወይም ቢያውቁም ደንታ የሌላቸው ሰዎች መብዛታቸውን ስንሰማ ልናዝን ይገባል:: ተቃዋሚዎች ያቀረቡዋቸው 18 ያህል ጥያቄዎቻቸው አዳማጭ በማጣታቸው ምክንያት ከምርጫ ውድድር ራሳቸውን እንደሚያገልሉ ወይም ሊሳተፉ እንደማይችሉ መግለጻቸው ለአገሪቱ መልካም ያልሆነ ዜና ነው:: ምርጫ የሕዝብ ድምፅ የመጨረሻው ውሳኔ የሚሰጥበት ዋነኛው የዲሞክራሲ ምህዋር መሆኑ ቀርቶ ለዲሞክራሲ የሚደረገው ትግል ሲደነቃቀፍ እንደ አገር ማዘን አለብን:: የፖለቲካ ምኅዳሩ ባልተስተካከለበት ሜዳ ላይ አንወዳደርም የሚሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች በርክተው ድምፃቸውን ሲያሰሙ መንግሥትም ሆነ ገዥው ፓርቲ ሊደነግጡ ይገባል:: የተቃዋሚዎቹን በምርጫ አለመሳተፍ እንደ መልካም አጋጣሚ የሚመለከቱ ሰዎች ካሉ ጤነኝነታቸው ያጠራጥራል::

ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎችም ለዋናው ምርጫ እንደ መንደርደርያ የሚያገለግለውን የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ምርጫ ለመወዳደር እልህ አስጨራሹን ትግል በአስተዋይነት

ሊወጡት ካልቻሉ ጉዳቱ የእነሱ ብቻ ሳይሆን የአገር ጭምር መሆኑን ሊረዱት የግድ ይላል:: በሰላማዊ የፖለቲካ ትግል ውስጥ የፈለገውን ያህል ጫና ቢፈጠር፣ የፈለገውን ያህል ያለመመቸት ቢኖር በተቻለ መጠን ለድርድርና ለውይይት በራቸውን ክፍት ማድረግ ይጠበቅባቸዋል:: ሰጥቶ መቀበል የሚባለውን መርህ መሠረት በማድረግ ጠንክረው በመልፋት ፍሬያማ ውጤት ለማግኘት መትጋት አለባቸው:: ሁሌም እንደሚባለውም በለስላሳ ምንጣፍና ሥጋጃ ላይ ተረማምዶ ትግል ማድረግ አይቻልም:: ምርጫ የፖለቲካ ሥልጣን መረከቢያ ዋነኛው መንገድ በመሆኑ በሰላማዊው የፖለቲካ ትግል ውስጥ ከፍተኛ የብልጠት ሥራ ያስፈልጋል:: በምርጫ መሳተፍ ሕገ መንግሥታዊ መብት ሆኖ መስፈሩ አይደለም ቁም ነገሩ:: ይህንን መብት እስከ ጥግ ድረስ ተጉዞ ተግባራዊ ለማድረግ የፓርቲዎቹ መሪዎችና አባላት ጥንካሬ ሊፈተን ይገባዋል:: አለበለዚያ የይስሙላ ያዝ ለቀቅ ዓይነት ጨዋታ የትም አያደርስም::

ኢሕአዴግ እንደ ገዥ ፓርቲነቱ ኃላፊነት አለበት:: መንግሥትን የሚመራና አገር የሚያስተዳድር ፓርቲ የሕግ የላይነት እንዲከበር ከማንም በላይ ይጠበቃል:: በአገሪቱ ውስጥ ፍትሐዊ የሆነ ሥርዓት መፈጠር አለበት:: የዲሞክራሲና የሰብዓዊ መብት ጥያቄዎች ሊመለሱ የግድ ይላል:: መልካም አስተዳደር በሌለበት አገርን ማስተዳደር ውጤቱ የከፋ ይሆናል:: ሰላማዊና ሕጋዊ የፖለቲካ ትግል ወዳልተፈለገ አቅጣጫ እንዳይገፋ ጥንቃቄ ማድረግ አለበት:: ሰላማዊ ትግሉ በተገፋ ቁጥር የሚከተለው አመፅና ብጥብጥ ነው:: በዚህ ምርጫ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ሳይኖሩ በምርጫው ለማሸነፍ መዘጋጀት ከንቱ ነው:: የተሟሟቀ ፉክክርና አማራጭ ባልቀረበበት ሕዝብን ለምርጫ ውጣ ማለት ቀልድ ነው የሚሆነው:: ተቃዋሚዎችም የፈለገው መገፋትና መንገላታት ይኑር ጥርሳቸውን ነክሰው ለዚህ ምርጫ ካልቀረቡ የአገሪቱ የዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ህልም መጨንገፉ አይቀርም:: ይህ ህልም እንዳይጨነግፍ ማንኛውም መስዋዕትነት ሊከፈል ይገባል:: የዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታው ህልም ቢጨናገፍ ማዘን የሚገባን ለአገራችን ነው:: ተስፋ መቁረጥ ከሞት የከፋ ነውና::

ተቁ መያዣ ሰጪው የተሽከርካሪው ዓይነት የሻንሲው ቁጥር የሞተር

ቁጥር የጨረታው መነሻ

ዋጋ በብር የምዝገባ ስዓት

የጨረታ ሰዓት

ጨረታው የሚካሄድበት ቀን

1 መስህን አህመድ ፎርድ ሬንጀር ደብል ገቢና የሠሌዳ ቁጥር

03-አአ-54621 MNCLSFE

408W746691

WLAT941911 800,000.00 3፡00-4፡00 4፡00-5፡30

የካቲት 5 ቀን 2005 ዓ.ም

ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ የሐራጅ ሽያጭ ማስተወቂያ

xb!s!Nà ÆNK ¼x.¥.¼ ls-W BDR bêST yÃzWN b\N-r¢$ የተገለፀውን ተሽከርካሪ bxêJ q_R 97¼1990 መሠረት ሜክሲኮ አደባባይ አካባቢ የፌዴራል ፖሊስ ዋና መሥሪያ ቤት አጠገብ በሚገኘው የባንኩ ኘሮጀክት ጽ/ቤት ግቢ ውስጥ በሚካሄደው GL{ =r¬ xwÄDé lm¹_ YfLULÝÝ tʼnÓC l=r¬ kmQrÆcW bðT y¸ktl#TN dNïC mgNzB YñRÆcêLÝÝ

• tʼnÓC ለመጫረት ሲቀርቡ y=r¬ mnš êUWN 1¼4 ¼xND x‰t¾¼ በአቢሲንያ ባንክ /አማ/ የተዘጋጀ ሲ.ፒ.ኦ. l=r¬

¥Skb¶Ã b¥SÃZ b=r¬W lmútF YC§l#ÝÝ

• በሚኪናው ሽያጭ ምክንያት ለመንስት ሊከፈሉ የሚገቡ ክፍያዎች የተጨማሪ እሴት ታክስ ገዥ ይከፍላል፡፡ • y=r¬W x¹Âð ùnfbTN -Q§§ êU b15 ¼x|‰ xMST¼ qÂT WS_ x-”lÖ mKfL YñRb¬LÝÝ bXnz!H

qÂT WS_ x-”lÖ µLkfl ÃSÃzW gNzB lÆNk# gb! YçÂLÝÝ b=r¬W lt¹nûT tʼnÓC ÃSÃz#T s!.pE.å.

YmlS§cêLÝÝ

• mÃÏ sÀW b/‰° qN bï¬W mgßT y¸Cl# s!çN½ úYgß# b!q„ /‰° bl@l#bT YµÿÄLÝÝ

• ÆNk# =r¬WN bkðLM çn bÑl# ym\rZ mBt$ yt-bq nWÝÝ

• ተሽከርካሪዎቹን አስቀድሞ ለማየት ባንኩ የጉብኝት ኘሮግራም ያዘጋጃል ፡፡ • lt=¥¶ mr© bSLK q$_R 0911 30 31 30 wYM 0115 54 67 37 bmdwL m-yQ YÒ§LÝÝ

Page 29: ERROR: The requested URL could not be retrieved ERROR The requested URL could not be retrieved While trying to process the request: TEXT HTTP/1.1 Host: Proxy-Connection: keep-alive

www.ethiopianreporter.com

ገጽ 29 | እሑድ | ጥር 19 ቀን 2005 ክፍል-1ማስታ

ወቂያ

ናይል ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ. የቢሮ ዕቃዎችን (Office Furniture) በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል፡፡

1. ተጫራቾች ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡

2. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 10,000 በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም ባንክ ጋራንቲ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

3. ተጫራቾች ስለጨረታው የሚገልጸውን ሠነድ የማይመለስ ብር 5ዐ /ሃምሣ/ በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት ናይል ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ. ዋናው መ/ቤት የሰው ኃይልና ንብረት አስተዳደር መምሪያ /3ኛ ፎቅ/ በመምጣት መግዛት ይችላሉ፡፡፡

4. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ እስከ የካቲት 01 ቀን 2ዐዐ5 ዓ.ም. 11፡ዐዐ ሠዓት ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

5. ጨረታው የካቲት 02 ቀን 2ዐዐ5 ዓ.ም. ከጠዋቱ በ3፡3ዐ ሠዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት በኩባንያው መሰብሰቢያ አዳራሽ /4ኛ ፎቅ/ ይከፈታል፡፡

6. አንዱ ተጫራች በሌላው ዋጋ ላይ ተንተርሶ መጫረት አይችልም፡፡

7. ኩባንያው ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ

ነው፡፡

አድራሻ ፣ ናይል ኢንሹራንስ አ.ማ. ዋናው መ/ቤት /ጎተራ/ የሰው ኃይልና ንብረት አስተዳደር መምሪያ /3ኛ ፎቅ/

የመ.ሣ.ቁ. 12836 የስልክ ቁጥር 0114-42 60 00

አዲስ አበባ

የ ጨ ረ ታ ማ ስ ታ ወ ቂ ያ ¾›=ƒÄåÁ ’`f‹ TIu`

¾*Ç=ƒ e^ Teq¨mÁ

¾›=ƒÄåÁ ’`f‹ TIu` ¾2012 u˃ ¯Sƒ H>dw

KTeS`S` /*Ç=ƒ KTeÅ[Ó/ eKT>ðMÓ Ÿ²=I uq‹

¾}²[²\ƒ” Seð`„‹ ¾UqTÙK< ¾*Ç=ƒ É`Ï„‹

S¨ÇÅ` ¾Uƒ‹K< SJ’<” à”ÑMíK”::

IÒ© õnÉ ÁL†¨<&

¾²S’<” Ów` ŸõK¨< u2004 ¯.U u˃ ¯Sƒ

ðndž¨<” ÁdÅc<&

¾*Ç=+”Ó um ¾Y^ MUÉ“ vKS<Á ‹ ÁL†¨<&

¾Ów` Ÿóà SKÁ lØ` ÁL†¨< }¨ÇÇ] ‹ &

K›ÑMÓKA~ ¾T>ÁeŸõK<ƒ” ªÒ à“ e^¨<” c`}¨<

¾T>Áe[¡u<uƒ” Ñ>²? ¾T>ÑMî W’É uTÁÁ´ ucU

uqgÑ ›?”yKAý ÃI Teq¨mÁ Ÿ¨×uƒ k” ËUa u

7 k“ƒ ¨<eØ uÒ²?× u}Ökc¨< ›É^h TSMŸƒ

¾T>‹K< SJ’<” à“d¨<nK”::

›É^h:-m`qe ¡õK Ÿ}T kuK? 02/03 ‚K? Ò^» òƒ

Kòƒ ¾yL¨`p I”í 5— öp u=a lØ` 31 & eM¡

lØ`:- 0114 655436 & þ.d.l 467 & ›Ç=e ›uv

ከነበሩ ሕንፃዎች መካከል አንዱ የሆነው ፍሬንድሽፕ ውስጥ በአልባሳት ንግድ ሥራ ላይ የተሰማሩ አንድ ነጋዴ እንደገለጹት፣ በዚህ መንገድ ግንባታ ሳቢያ ቀድሞ የነበረ ገቢያቸው ቀንሷል::

ላለፈው አንድ ዓመት ምንም ሠርቻለሁ አልልም የሚሉት እኚሁ ነጋዴ፣ የተገኘችውን በመለቃቀም የቤት ኪራይ እየከፈሉና የመንገድ ግንባታውን መጠናቀቅ እየተጠባበቁ መሆኑን ተናግረዋል:: በገቢያቸው መቀነስ በመደብራቸው በፈረቃ ሲሠሩ ከነበሩ ስድስት ሠራተኞች ሁለቱን መቀነሳቸውንም አስታውሰዋል::

በደንበል ሲቲ ሕንፃ በአንድ የውጭ ጫማ መሸጫ ውስጥ የምትሠራ ወጣትም፣ ተቀጥራ በምትሠራበት መደብር ውስጥ ቀድሞ የነበረውን ያህል እንቅስቃሴ እንደሌለ ትናገራለች:: ይህም ብቻ ሳይሆን በዚያ አካባቢ የትራንስፖርት እንቅስቃሴ ስለሌለ በየዕለቱ በእግር ብዙ እየተጓዘች ወደ ሕንፃው መምጣቷ እንዳሰለቻት ትገልጻለች:: አሁንም ይኸው እየቀጠለ በመሆኑ መቼ አልቆ እንደበፊቱ ሕንፃው አጠገብ ታክሲ የሚያወርዳትን ጊዜ እየናፈቀች ነው::

በሺሕ የሚቆጠሩ ተገልጋዮችን ያስተናግዱ የነበሩ የተለያዩ ባንኮች ቅርንጫፎች ደንበኞቻቸውን በአግባቡ ለማስተናገድ ሳይችሉ ቆይተዋል::

የባንክ ደንበኞች የቁጠባ ሒሳባቸውን ወደከፈቱበትና ቦሌ መስመር ወደሚገኙት ቅርንጫፎች መሄድ ባመቻላቸው፣ የባንክ ሒሳባቸውን ከቦሌ

መንገድ ውጪ ባሉ የባንኮቹ ቅርንጫፍ በመሄድ ለማንቀሳቀስ ተገድደዋል::

ደንበል ሲቲ ሴንተር ሥር የሚገኘው የኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ የቁጠባ ደብተር ከፍቶ የነበረ አንድ የባንኩ ደንበኛ እንደገለጸው፣ ከመኖሪያ ቤቴ ቅርብ በመሆኑ በደንበል ሲቲ ሴንተር ባለው ቅርንጫፍ ይጠቀም ነበር:: ‹‹የመንገዱ ሥራ ከተጀመረ በኋላ ግን ወደዚህ ቅርንጫፍ መሄዱ ከባድ ሆነ፤ መኪና ማስገቢያም የለም:: ደግነቱ የባንክ ሒሳቤን በየትኛውም ቅርንጫፍ ማንቀሳቀስ የሚያስችለኝ አሠራር ባንኩ ስለዘረጋ በዚሁ መንገድ እጠቀማለሁ:: ዕድሜ ለኮር ባንኪንግ፤›› ብሏል:: አንድ የባንክ ደንበኛ ሒሳቡን በየትኛውም የባንኩ ቅርንጫፍ ማንቀሳቀስ የሚያስችል አሠራር (የኮር ባንኪንግ) ባይኖር ኖሮ የዚህ መንገድ ግንባታ ብዙ ነገር ያበላሽ እንደነበርም አስታውሷል::

በዚህ ያለው የቢዝነስ እንቅስቃሴ መዳከሙን በተመለከተ ኢንጂነር ፍቃዱ በእንዲህ ዓይነቱ የኮንስትራክሽን ግንባታ የቢዝነስ መቀዛቀዝ ሊኖር ይችላል ብለው፣ ብዙዎችም መጐዳታቸውን ይናገራሉ:: አማራጭ የሌለው ጉዳይ ሆኖ እንጂ በዚያ አካባቢ በሚሠራው መንገድ ሳቢያ ብዙ የቢዝነስ ድርጅቶች በመጐዳታቸው ሐዘኔታ እንደሚሰማቸው ገልጸዋል:: ሆኖም አማራጭ የሌለው ጉዳይ ስለሆነ የግድ መንገዱን እስኪጠናቀቅ እስካሁን የታየው ትዕግሥት መቀጠል አለበት ይላሉ::

የቦሌ መንገድን ለሥራ መዝጋት ብዙ ዋጋ

እያስከፈለ መሆኑን ያልሸሸጉት ኢንጂነር ፍቃዱ፣ የዚህ መንገድ መዘጋት በከተማው በተለያዩ አካባቢዎች ከፍተኛ የትራፊክ መጨናነቅ መፍጠሩንም ይጠቁማሉ::

ሌላው ቀርቶ እንደልብ ጉዞ ይደረግበት የነበረው የቀለበት መንገድ እንዲጨናነቅ ምክንያት ሆኗል የሚሉት ኢንጂነር ፍቃዱ፣ ይህ ደግሞ ኢኮኖሚያዊ ጉዳት አለው ይላሉ:: ሆኖም ከተማ ለማልማት እየተከፈለ ያለ መስዋዕትነት ተደርጐ መታየት እንዳለበት ሳይጠቅሱ አላለፉም::

የቦሌ መንገድ ግንባታ በዚያ መስመር ያለውን ቢዝነስ ከማደብዘዝ ባለፈ በቦሌ መስመር ላይ ወደሚገኙ የመንግሥትም ሆነ የግል መሥሪያ ቤቶች ውስጥ የሚሠሩ ሠራተኞች ሲጉላሉ መመለከቱ የተለመደ ነው::

በዚህ መንገድ ግንባታ ታስቦ የነበረው የመንገዱን አንደኛ መስመር ጨርሶ ወደሌላኛው መስመር መግባት ቢሆንም፣ እንደታሰበው ብዙ የተሠራበት አይመስልም:: ይህም በመሆኑ በዚህ መስመር በተወሰነ ሁኔታ አንደኛው ክፍል ለትራፊክ ክፍት ቢሆንም፣ በአብዛኛው እንደተዘጋ በመሆኑ በዚያ መስመር ላይ የሚሠሩ ሠራተኞች ረዥም መንገድ በእግር ሄደው ወደሥራቸው እንዲገቡ አድርጓል::

በዚህ አካባቢ በርካታ ሠራተኞች ካላቸው መንግሥታዊ መሥርያ ቤቶች መካከል አንዱ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ጽሕፈት ቤት ነው:: በዚህ መሥሪያ ቤት የሚሠሩ ሠራተኞች ወትሮ ከመሥሪያ ቤታቸው ቅጥር ግቢ ይወስዳቸው የነበረው ሰርቪስ በመንገድ ግንባታ ሳቢያ ወደመሥርያ ቤቱ መሄድ ስለሚያዳግተው፣ ሠራተኞች የሰርቪስ አገልግሎት ለማግኘት መስቀል አደባባይ ድረስ በመሄድ እየተጠቀሙም ይገኛሉ::

በቦሌ መንገድ የሞቀ ገበያ ከነበራቸው ሬስቶራንቶች አንዱ የሆነው ኒውዮርክ ካፌና ሬስቶራንትም ሌላ ምሳሌ ይሆናል:: በአብዛኛው የከተማችን ወጣቶች ይስተናገዱበት የነበረው ይህ ሬስቶራንት ዛሬ የቀድሞውን ያህል ተገልጋይ የለውም::

በቦሌ መስመር ግንባታ የተፈጠረው መጨናነቅ የፈጠረው ተፅዕኖ በቅርብ ሊፈታ ይችላል የሚል እምነት ቢያሳድርም፣ በቅርቡ የሚጀመሩ አዳዲስ የመንገድ ግንባታዎች በሌላኛውና የከተማዋ ክፍል ተፅዕኖ ሊያሳድሩ ይችላሉ ተብሎ ተሰግቷል:: እነዚህም በአዲስ አበባ እየተገነባ ያለው የባቡር መስመርና ይህንኑ ተከትሎ የሚሠሩት የተሽከርካሪዎች ማሳለጫ ግንባታዎች ናቸው::

የከተማዋ ትልቁ የመንገድ ፕሮጀክት መሆኑ የሚነገረው ይህ ፕሮጀክት በአንድ የባቡር መስመር ላይ ብቻ ከ30 ያላነሱ ማቋረጫዎችና አደባባዮች የሚሠሩ ስለሆነ፣ ከአያት ጦር ኃይሎች ድረስ ያለውን የቢዝነስ እንቅስቃሴ ይስተጓጐላል የሚል ሥጋት አለ:: ኢንጂነር ፍቃዱም ይህንን ሥጋት ቢጋሩም፣ ተፅዕኖውን ለመቀነስ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል::

በባቡር መስመር ዝርጋታውና በቅርቡ ይጀመራሉ የተባሉ የባቡር መስመሩን ያሳልጣሉ የተባሉ የተሽከርካሪ መንገዶችና አደባባዮች፣ በከተማው የትራፊክ ፍሰት ላይ የሚፈጥሩትን ጫና በመገንዘብ አማራጭ መፍትሔዎች እየተፈለጉ ነው::

የባቡር ኢንጂነሪንግ ፕሮፌሰር ኤሊያስ ካሳ እንደገለጹት ደግሞ፣ እንዲህ ዓይነት ትላልቅ ግንባታዎች የትራፊክ መጨናነቅን ስለሚያስከትሉ የመንገዶቹም ሆኑ የባቡር መስመሮቹ የአገነባብ ፕሮግራም በጥንቃቄ መደረግ አለበት::

በምሳሌ ያስቀመጡትም ከምሥራቅ ወደ ምዕራብ በሚዘረጋው የባቡር መስመር ግንባታ በአንዴ ከማካሄድ ይልቅ በመጀመሪያ ከአያት መገናኛ ድረስ ያለውን ሥራ መሥራት፣ ከዚያ ጐን ለጐን ደግሞ የባቡር መስመሩንም የማሽነሪ ሥራዎችን አብሮ ሠርቶ ሙሉ ሥራውን አጠናቆ እንደገና ወደሌላው ክፍል መግባት ይጠቅማል ብለዋል::

‹‹የመጀመሪያው ክፍል ግንባታ ሙሉ ለሙሉ ሲጠናቀቅ፣ ቦታውን ለትሪፊክ ክፍት ማድረግ ይቻላል:: ያለበለዚያ እዚህም እዚያም ግንባታው ከተጀመረ የትራፊክ መጨናነቁን ሊያባብስ ይችላል፤›› የሚልም አስተያየት አላቸው::

ለባቡር መስመር ዝርጋታው አሁን እየተቆፈሩ ያሉት ቦታዎች የፈጠሩት መጨናነቅ የበለጠ መጨናነቅ የሚፈጠረው ዋናው የሐዲድ ዝርጋታ ሲካሄድ ነው:: በዚህ ምክንያት ሊዘጉ የሚችሉ መንገዶች ስለሚኖሩ ተሽከርካሪዎች በአማራጭ የሚጠቀሙበት መንገዶችን ማደስ ያስፈልጋልም ይላሉ::

ፕሮፌሰር ኤሊያስ አያይዘውም እንዲህ ያለው ትልቅ ፕሮጀክት ሲታሰብ የትራፊክ ማኔጅመንት ቀድሞ መታሰብ እንደነበረበት ያመላክታሉ:: ከዚህም በኋላ ቢሆን የባቡር ኮርፖሬሽኑም ሆነ የተሽከርካሪ መንገዶችን የሚያሠራው መሥርያ ቤት የትራፊክ መጨናነቁ ሊያስከትል የሚችለውን አጠቃላይ ኢኮኖሚያዊ ጉዳት ሊቀንስ የሚችለውን አሠራር በፍጥነት ተግባራዊ ማድረግ እንዳለበት ተናግረዋል::

የንግድ እንቅስቃሴው... ከክፍል-1 ገጽ 12 የዞረ

Page 30: ERROR: The requested URL could not be retrieved ERROR The requested URL could not be retrieved While trying to process the request: TEXT HTTP/1.1 Host: Proxy-Connection: keep-alive

www.ethiopianreporter.com

ገጽ 30 | እሑድ ጥር 19 ቀን 2005ክፍል-1

በአዲስ አበባ ከአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ በፊት በርካታ ስብሰባዎች ተካሂደዋል ፎቶ ታምራት ጌታቸው

ፎቶ ዜና

Page 31: ERROR: The requested URL could not be retrieved ERROR The requested URL could not be retrieved While trying to process the request: TEXT HTTP/1.1 Host: Proxy-Connection: keep-alive

www.ethiopianreporter.com

ገጽ 31 | እሑድ | ጥር 19 ቀን 2005 ክፍል-1

የአገር ውስጥ ዜና የዓለም ዜናተስፍሽ እና ገብርሽግብፃውያን በካይሮ ጎዳናዎች ላይ ከፖሊስ ጋር ተጋጩየቀድሞው ፕሬዚዳንት ሆስኒ ሙባረክ በሕዝባዊ

ተቃውሞ ከሥልጣን የወረዱበት ሁለተኛ ዓመት ሲዘከር፣ ግብፃውያን በካይሮ ጎዳናዎች ላይ ከፖሊስ ጋር ተጋጩ:: ባለፈው ዓርብ ፕሬዚዳንት መሐመድ ሙርሲን በሚቃወሙ ግብፃውያን ሠልፈኞችና በፖሊስ መካከል በተካሄደው ግጭት 29 ሰዎች ቀላልና ከባድ ጉዳት እንደደረሰባቸው የዘገበው ሲኤንኤን ነው:: የግብፅ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ካሊድ አል ካቲብ እንደገለጹት፣ 29 ግብፃውያን ቀላልና ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል:: ስድስት የፖሊስ አባላትም ጉዳት እንደደረሰባቸው በዘገባው ሰፍሮአል:: የግብፅ የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ባወጣው መግለጫ በታህሪር አደባባይ አካባቢ በፖሊስና በሠልፈኞቹ መካከል ግጭት ተካሂዷል:: ፖሊስ ሠልፈኞች ወደ አደባባዩ እንዳያመሩ መንገዱን መዝጋቱ ታውቋል:: የዛሬ ሁለት ዓመት እ.ኤ.አ. ጃንዋሪ 25 ቀን 2011 በታህሪር አደባባይ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ግብፃውያን ሆስኒ ሙባረክን ለመቃወም ወጥተው እሳቸውም ሥልጣናቸውን ማጣታቸው አይዘነጋም:: አዲሱ የግብፅ ፕሬዚዳንትም ደጋፊዎች ያሉዋቸውን ያህል ተቃውሞ እየገጠማቸው ነው::

ደቡብ አፍሪካ ውስጥ የጠፉ 15 ሺሕ አዞዎች እየተፈለጉ ነውየደቡብ አፍሪካ ፖሊስ የጠፉ 15 ሺሕ አዞዎችን

ለማፈላለግ አደን መጀመሩን አስታወቀ:: እንደ ዴይሊ ቢስት ዘገባ፣ ባለፈው ዓርብ ማፈላለጉን የተቀላቀለው የአገሪቱ ፖሊስ ከኤደኒ የእንስሳት ክልል የጠፉ አዞዎችን ለመታደግ ነው:: አዞዎቹ ከኤደኒ ማቆያ ሊጠፉ የቻሉት በአካባቢው በተከሰተ ኃይለኛ ማኅበል ምክንያት መሆኑ ታውቋል:: አዞዎቹ ምናልባት በውኃው ግፊት ተጠራርገው በአካባቢው የሚገኙ ወንዞች ውስጥ ገብተው ሊሆን እንደሚችል ዘገባው አስረድቷል:: የአዞ አርቢዎች፣ የአካባቢው ሰዎችና ፖሊስ እስካሁን ድረስ በሺሕ የሚቆጠሩ አዞዎችን የተለያዩ ቁሳቁሶችን በመጠቀም መያዛቸው ተገልጾ፣ በቦትስዋናና በዚምባቡዌ በኩል ያሉ የጎርፍ መተላለፊያዎች ለፍለጋው ክፍት ተደርገዋል ተብሏል:: በዚህም ምክንያት የዚምባቡዌ መንግሥት ዜጎች በውኃ አካላት ውስጥ እንዳይዋኙ ጥብቅ ማስጠንቀቂያ ማውጣቱ ተሰምቷል::

ሰሜን ኮሪያ የኑክሌር ሙከራ ካደረገች ዕርዳታ እንደምታቋርጥ

ቻይና አስጠነቀቀችየሰሜን ኮሪያ ብቸኛና ዋነኛ አጋር ተብላ

የምትታወቀው ቻይና አገሪቱ የኑክሌር ሙከራዋን ካላቆመች ዕርዳታዋን እንደምታቆም ማስጠንቀቋን የቻይና የመንግሥት ሚዲያ አስታወቀ:: ባለፈው ዓርብ የቻይና መንግሥት ባወጣው ግልጽ ማስጠንቀቂያ ሰሜን ኮሪያ የኑክሌር ሙከራ ከማድረግ እንድትቆጠብ ጠይቋል:: ቻይና ለሰሜን ኮሪያ ዋነኛዋ የኃይል አቅራቢና የንግድ ሸሪክ ስትሆን፣ በአገሪቱ ላይም ተፅዕኖ ለማድረግ የምትችል ብቸኛዋ አገር ናት:: ሰሜን ኮሪያ የኑክሌር ሙከራ ብታደርግ ቻይና ድጋፏን ከመስጠት እንደምትገታ የቻይና መንግሥት ማስታወቁን ዘገባው አመልክቷል:: ቻይና የተረጋጋ የኮሪያ ልሳነ ምድር መኖር እንዳለበት አስታውቃ፣ በአካባቢው ችግር መፈጠሩ የዓለም ፍፃሜ እንዳልሆነም ገልጻለች:: ሰሜን ኮሪያ ሰሞኑን አሜሪካን ዒላማ ያደረገ የኑክሌር ሙከራ አካሂዳለሁ ማለቷ በምዕራቡ ዓለም ቁጣን የቀሰቀሰ ሲሆን፣ ቻይና አጋሯ ከዚህ ድርጊት እንድትቆጠብ ማስጠንቀቅዋ የሁኔታውን አስጊነት ያሳያል እየተባለ ነው::

የፈረንሳይና የማሊ ወታደሮች አክራሪ አማፂያንን እያጠቁ ነው

በቅርቡ የማሊ ሰሜናዊ ክፍልን በመቆጣጠር በመላ አገሪቱ ላይ አደጋ ጋርጠው የነበሩትን አክራሪዎች የፈረንሳይና የማሊ ወታደሮች እያጠቁዋቸው መሆኑን ዘገባዎች አስረድተዋል:: በተለይ የፈረንሳይ ተዋጊ ጄቶች በአማፂያኑ ይዞታዎች ላይ ባካሄዱት ጥቃት ከፍተኛ ጉዳት ያደረሱ ሲሆን፣ በአክራሪዎቹ ላይ ጫና ፈጥረዋል:: ፈረንሳይ በማሊ 2,500 ወታደሮችን በማስፈር ከማሊ ሠራዊት ጎን ስትሰለፍ፣ የምዕራብ አፍሪካ አገሮች 3,300 ወታደሮችን በማሰማራት ላይ መሆናቸው ታውቋል:: በፈረንሳይና በማሊ ወታደሮች ጥቃት መፈናፈኛ ያጣ አንድ የአክራሪዎች አንጃ ለድርድር ዝግጁ መሆኑን ባለፈው ዓርብ አስታውቋል:: የፈረንሳይና የማሊ ወታደሮች በጋራ በሰነዘሩት ጥቃት ሆምቦሪ የምትባል ከተማ መቆጣጠራቸውን ዘገባዎች አስረድተዋል::

ባለፈው ሰኞ ምሽት በኢትዮጵያና በዛምቢያ ብሔራዊ ቡድኖች መካከል የተደረገውን ግጥሚያ በጊዜ ቤቴ ገብቼ ለመከታተል መንገድ ብጀምርም መንገዱ በመዘጋጋቱ ምክንያት ሊሳካልኝ አልቻለም:: የተለያዩ አማራጮችን ለመጠቀም ብሞክርም፣ ከቦሌ ድልድይ ወደ ሃያ ሁለት የሚሄደውን አቅጣጫ ባስብም ሊሳካልኝ አልቻለም:: ያለኝ አማራጭ አንዱ ሆቴል ወይም ሬስቶራንት ጎራ ማለት ነው:: በዚህ ምክንያት ለአላስፈላጊ ወጪ መዳረጌ እየቆጨኝ ብሔራዊ ቡድናችንን ማየት ደግሞ የግድ መሆኑን ከራሴ ጋር እየተነጋገርኩ በርካታ ሰዎች የታደሙበት ሆቴል ወስጥ ገባሁ:: ከ31 ዓመታት በኋላ ወደ ውድድር የተመለሰውን ብሔራዊ ቡድናችንን ጨዋታ ለማየት በርካቶች በጉጉት ውስጥ ሆነው ሲጠባበቁ ማየት አስደሳች ነበር::

እንደምንም ብዬ አንድ ጥግ ላይ መቀመጫ ከያዝኩ በኋላ ‹‹ምን ልታዘዝ?›› የሚል አንድ አስተናጋጅ ቀረበኝ:: ቀዝቀዝ ያለ ቢራ አዝዤ ከነቢሉ መጣልኝ:: እንደዘበት ዓይኔን ቢሉ ላይ ጣል ሳደርግ ለአንድ ቢራ 18 ብር ተጠይቄአለሁ:: በሆዴ እየበሸቅኩ የመጣልኝን ቢራ መቀማመስ ስጀምር በእጁ ደረሰኝ የያዘ ሰው ከቴሌቪዥን ተመልካቾች ላይ ገንዘብ ሲሰበስብ አየሁት:: ከተወሰኑ ደቂቃዎች በኋላ አጠገቤ መጥቶ ደረሰኙን ሲያቀብለኝ ዋጋው አሥር ብር ይላል:: ሌላ ጊዜ እንደ ጨዋታው ዓይነት በስፖርት ባሮች ከአምስት እስከ አሥር ብር እንከፍላለን:: እዚህ ደግሞ መጀመርያ የመጠጥ ትዕዛዝ ይቀበሉና ከዚያ የኳስ መመልከቻ ያስከፍላሉ:: አንጀቴ እያረረ አሥር ብዬ ከፍዬ የተጀመረውን ጨዋታ መከታተል ጀመርኩ:: የማታ ማታ በተገኘው የብሔራዊ ቡድናችን ውጠት ብደሰትም በስግብግቦች ምክንያት የሚፈጸመው ገፈፋ አበሳጭቶኝ ነበር:: ምን ያህል ሞራል የጠፋበት ጊዜ ላይ እንደደረስን ማሳያ ይመስለኛል::

ከጨዋታው መጠናቀቂያ በኋላ ታክሲ ብፈልግ ምንም የለም:: መንገዱ በብሔራዊ ቡድኑ ውጤት በተደሰቱ ወጣቶችና ጎልማሶች ተሞልቶ ስለነበር ያለው አማራጭ በእግር መጓዝ ነበር:: የተወሰነ መንገድ ተጉዤ ኤድና ሞል ማቲ ሲኒማ ስደርስ ጠጠር መጣያ እስኪጠፋ ድረስ በሰው ተሞልቷል:: እንደምንም ተሹለክልኬ የሃያ ሁለት አቅጣጫን ብይዝም ያለው አማራጭ በእግር መጓዝ ይመስላል:: በዚያ ላይ በሁለቱም አቅጣጫ በተሽከርካሪዎች ተጨናንቆ ስለነበር በእግሬ ረጅሙን መንገድ ተያያዝኩት:: እንደማያልቅ የለም በጣም ደክሞኝ ሠፈሬ ስደርስ እዚህም ሆታው ደርቷል:: ያለኝ አማራጭ በቀጥታ ወደ ቤት መግባት ነው::

የግቢዬን በር ከፍቼ ስገባ ባለቤቴና አንዲት የጎረቤት ሴት ቆመው ሲያወሩ ደረስኩ:: ሰዓቱ በመምሸቱ ምን ሆነው ነው በማለት ቀርቤ ስጠይቃቸው ልጆቹ የሉም ተባልኩ:: ቤት ውስጥ ቴለቪዥን እያለ እንዴት ደጅ ሄደው ያያሉ በማለት ሁለቱ ልጆቼ ዘንድ ስልክ ስደውል አያነሱትም:: ደጋግሜ ብሞክር አቃተኝ:: እስቲ ወጣ በማለት ልፈልጋቸው ብዬ ገና አጥሩን ከፍቼ ብቅ ስል ልጆቼ እየተጣደፉ ሲመጡ ተገጣጠምን:: ቆጣ ብዬ የት እንደነበሩ ስጠይቃቸው አንደኛው ልጄ፣ ‹‹አንተ ብትቀርብን ጓደኞቻችን ዘንድ ጨዋታውን ለማየት ሄድን፤›› በማለት ከእኛ ቤት በቅርብ ርቀት ያሉት የሠፈር ልጆች ቤት መሄዳቸውን ነገሩኝ:: ስልካቸውን ያልሰሙት እየሮጡ ሲመጡ እንደነበርም ገለጹልኝ::

ተያይዘን ቤት ከገባን በኋላ በብሔራዊ ቡድናችን ማራኪ አጨዋወትና በተገኘው ውጤት መደሰታቸውን በተየራ ተረኩልኝ:: ከበረኛው ያልተገባ ጥፋት እስከ አጥቂዎቹና አማካዮቹ እንዲሁም ተከላካዮች በሚገባ ተነተኑልኝ:: የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግን አብረን ስለምናይ ስለኳስ ትንተና በቂ የሆነ ግንዛቤ አላቸው:: ሁሌም ከጨዋታ በኋላ ስለ አጠቃላዩ እንቅስቃሴ የሚሰጡት አስተያየት ይገርመኛል:: ዓይናቸውን ቴሌቪዥኑ ላይ ጥለው የኮሜንታተሮችን ገለጻ በጆሮአቸው በንቃት ስለሚያዳምጡ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳበረከተላቸው አውቃለሁ:: ከጥናታቸው በኋላ የኢንተርኔት ዘገባዎችን ስለሚከታተሉ ከፍተኛ የማስረዳት ችሎታ አላቸው:: ይኼ እንግዲህ ከትምህርታቸው ቀጥሎ ባላቸው ትርፍ ጊዜ የሚከታተሉት በመሆኑ የተጎናጸፉት ክህሎት ነው::

በዚህ መሀል ትልቁ ልጄ በአንድ ነገር ማዘኑን ነገረኝ:: ‹‹ምን ይሆን?›› በማለት ጠየቅኩት:: በጣም ተናዶ ‹‹እንዴት የመንግሥት ቴሌቪዥን ከሌላ ጣቢያ የውድድሩን ሥርጭት ያለ ክፍያ ይሰርቃል?›› አለ:: ስላልገባኝ ‹‹ማነው እሱ?› አልኩት:: ‹‹የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ያለ ክፍያ ውድድሩን በማስተላለፉ ይከሰሳል እያሉ ኮሜንታተሮች ሲናገሩ ሰማሁ:: የቲቪው ስክሪን ላይ ደግሞ የተለጣጠፉ ነገሮች ይታዩ ነበር:: በሕዝብ ገንዘብ የሚተዳደር የቴሌቪዥን ጣቢያ ሌባ ተብሎ አንድ ቢሊዮን ሕዝብ በሚከታተለው የውድድር ሥርጭት ተሰድቦ አሰደበን እኮ?›› ሲለኝ ደነገጥኩ:: ‹‹አስፈላጊውን ክፍያ ከፍሎ ስፖንሰሮችን ማፈላለግ ሲገባው እንዲህ ዓይነት ቅሌት ውስጥ የከተተን ቲቪ እዚህ አገር በአስቸኳይ ለፍርድ ቀርቦ ካልተቀጣና መንግሥት የሕዝቡን ሞራል ካልጠበቀ አስተዛዛቢ ነው:: ይህ ዓይነቱ ድርጊት ከባህር ላይ ውንብድና ወይም ፓይሬሲ ተለይቶ አይታይም፤› ብሎ ትንሹ ልጄ በንዴት ሲንቦገቦግ በጣም አዘንኩ:: መንግሥት ይህን ጉድ እየሰማ ነው? ወይስ እንቅልፉን ተኝቷል? ቢያንስ ለታዳጊዎች መልካም አስተዳደግ ሲባል እንዲህ ዓይነቱ ነውር አደብ ይግዛ:: የሞራል መላሸቅ በዛ እኮ!? (መርዓዊ ተክለ ሃይማኖት፣ ከለም ሆቴል)

ገጠመኝ

የመጠባበቂያ እህል ክምችት 460 ሺሕ ሜትሪክ ቶን

መድረሱ ተነገረአገሪቱ ለአደጋ ጊዜ መጠባበቂያ ያላት የእህል

ክምችት 460 ሺሕ ሜትሪክ ቶን መድረሱን የመጠባበቂያ ምግብ ክምችት አስተዳደር አስታወቀ:: እንደ ኢዜአ ዘገባ፣ አሁን ባለው የመጠባበቂያ የእህል ክምችት ለስድስት ወራት ስድስት ሚሊዮን ሕዝብ መመገብ ይቻላል:: ባለፉት ስድስት ወራትም 50 ሺሕ ሜትሪክ ቶን ወደ መጠባበቂያ እህል መጋዘን መግባቱን ዘገባው አስረድቶ፣ አስተዳደሩ በሰባት ቅርንጫፎች ያሉትን 67 መጋዘኖች በማስፋፋትና ተጨማሪ 200 መጋዘኖችን በሦስት ዓመታት በመገንባት የእህል ክምችቱን ሦስት ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ለማድረስ በስፋት እየተንቀሳቀሰ መሆኑን አመልክቷል:: መጋዘኖቹ ሲጠናቀቁ የሚይዙት የእህል ክምችት 20 ሚሊዮን ሕዝብ ለአንድ ዓመት ያህል የመመገብ አቅም ይኖረዋል ተብሏል:: አስተዳደሩ ለአስቸኳይ ዕርዳታ፣ ለሴፍቲኔት፣ ለገበያ ዋጋ ማረጋጊያ ፕሮግራሞች 107 ሺሕ ሜትሪክ ቶን እህል ለግብርና ሚኒስቴር፣ ለእህል ንግድ ድርጅትና ለዓለም የምግብ ፕሮግራም በብድር መስጠቱ ተዘግቧል:: በብድር የሰጠውንም እህል እንዳስመለሰና በክምችት ላለው እህል ተገቢው ክትትል እየተደረገ መሆኑን፣ ክምችቱን አስተማማኝ ለማድረግ በዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅዱ መሠረት መንግሥት 13 ቢሊዮን ብር መመደቡን ዘገባው አውስቷል::

ሳምሰንግና ኤልጂ ፋብሪካዎቻቸውን ኢትዮጵያ ውስጥ ለማቋቋም ፍላጎት

ማሳየታቸው ተሰማየደቡብ ኮሪያ ትልልቆቹ ኩባንያዎች ሳምሰንግና

ኤልጂ ኤሌክትሮኒክስ ኢትዮጵያ ውስጥ ኢንቨስት ለማድረግ ፍላጎት እንዳላቸው የአገሪቱ አፈ ጉባዔ መግለጻቸውን የዘገበው ዋልታ ነው:: አፈ ጉባዔው ሚስተር ፓርክ ባዩንግ ሱግ እንዳሉት፣ ሁለቱ ትልልቅ ኩባንያዎች ኢትዮጵያ ውስጥ ለመሥራት ከፍተኛ ፍላጎት አላቸው:: የኢትዮጵያን መንግሥት ፈቃድና ተገቢ ድጋፍ ካገኙ የማምረቻ ኢንዱስትሪዎቻቸው ይዘው በቅርቡ እንደሚገቡ በዘገባው ተጠቅሷል:: ለዚህም የኢትዮጵያ መንግሥትን የቅርብ ድጋፍና ክትትል መጠየቃቸው ተዘግቧል:: ደቡብ ኮሪያ ኢትዮጵያ ውስጥ እየገነባችው ላለው የኢንዱስትሪ መንደር የተደረገውን ድጋፍ አመስግነው፣ አስፈላጊ ነገሮች ተሟልተው ተገቢውን አገልግሎት መስጠት እንዲችል የኮሪያ መንግሥት ጠንክሮ ይሠራል ማለታቸው ተመልክቷል::

መንግሥት በአልጄሪያ ጋዝ ፍለጋ በተሰማሩ ሠራተኞች ላይ የተፈጸመውን ጥቃት አወገዘባለፈው ሳምንት በአልጄሪያ በጋዝ ፍለጋ ሥራ

ላይ በተሰማሩ ሠራተኞች ላይ የተፈጸመውን ጥቃት መንግሥት አወገዘ:: ኢዜአ እንደዘገበው፣ መንግሥት ኢን አሜናስ በተባለው ሥፍራ የተፈጸመውን ጥቃት አጥብቆ ተቃውሟል:: በአደጋው ሕይወታቸውን ላጡና አካል ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች የተሰማውን ሐዘንም መግለጹን ዘገባው አስረድቷል:: ዓላማው ምንም ይሁን ምንም በማንኛውም መንገድ አኅጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ሰላምና ደኅንነትን የሚያደፈርስ የሽብር ተግባር ኢትዮጵያ እንደማትቀበል መንግሥት አስታውቋል:: የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ከውግዘት ባሻገር ድርጊቱን ለመግታት ከመቼውም ጊዜ በላይ እንዲተባበር ጥያቄ ያቀረበ ሲሆን፣ ኢትዮጵያ ከስትራቴጂያዊ አጋሯ አልጄሪያ ጋር ያላትን አንድነት ዳግም ታረጋግጣለች ብሏል:: ሽብርተኝነትን በአንድነትና በተጠናከረ መንገድ ለመታገል ጽኑ አቋም እንዳላት ዘገባው አስረድቷል::

ከ3.2 ቢሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ ስድስት መንገዶች

ሊገነቡ ነውየኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ከ3.2 ቢሊዮን

ብር በላይ የሚያወጡ የስድስት መንገዶችን ደረጃ ለማሳደግና ለመገንባት የሚያስችሉ ስምምነቶችን ከሦስት የአገር ውስጥና ከሁለት የውጭ ድርጅቶች ጋር ተፈራረመ:: እንደ ዋልታ ዘገባ፣ መንገዶቹ የሚገነቡት መንግሥት በቀረፀው የአራተኛው የመንገድ ዘርፍ ልማት መርሕ ግብር መሠረት ነው:: የሚገነቡት መንገዶችም ከአዘዞ - ጎርጎራ፣ የሐረር ተለዋጭ መንገድ፣ የያሎ - ኔጌሎ ኮንትራት አንድና ማዞሪያ - ዱራሜ - ዱርጊ - ኦሞ ወንዝ ድረስ ናቸው:: በተጨማሪም የዚሁ መንገድ ኮንትራት ሁለት ፈለገ ሰላም - አመያ - ጭዳ ድረስ ያሉት መንገዶች ይገኙበታል:: መንገዶቹ ቀደም ሲል በገጠር መንገድ ደረጃ የነበሩና ምንም መንገድ የሌለባቸው አዳዲስ መንገዶች መሆናቸው በዘገባው ተካቷል::

Page 32: ERROR: The requested URL could not be retrieved ERROR The requested URL could not be retrieved While trying to process the request: TEXT HTTP/1.1 Host: Proxy-Connection: keep-alive

www.ethiopianreporter.com

ገጽ 32 | እሑድ ጥር 19 ቀን 2005ክፍል-1 ማስታወቂያ

Page 33: ERROR: The requested URL could not be retrieved ERROR The requested URL could not be retrieved While trying to process the request: TEXT HTTP/1.1 Host: Proxy-Connection: keep-alive

www.ethiopianreporter.com

ገጽ 33 | እሑድ | ጥር 19 ቀን 2005 ክፍል-1ማስታወቂያ

Page 34: ERROR: The requested URL could not be retrieved ERROR The requested URL could not be retrieved While trying to process the request: TEXT HTTP/1.1 Host: Proxy-Connection: keep-alive

www.ethiopianreporter.com

ገጽ 34 | እሑድ ጥር 19 ቀን 2005ክፍል-1

ማስታ

ወቂያ

የኦዲት አገልግሎት ጨረታ ማስታወቂያ

ፕሮ-ፑር በመባል የሚታወቅ የኢትዮጵያ ነዋሪዎች በጎ አድራጎት ድርጅት የህፃናት፣ የእናቶችና የወጣቶች ኑሮ ለማሻሻል በመሥራት ላይ ይገኛል፡፡ ድርጅቱ ከጃንዋሪ 1 - ዲሴምበር 31/2012 ያለውን የገንዘብ እንቅስቃሴውን

1. የታደሰ የንግድ ፈቃድ እና የሞያ ማረጋገጫ ፍቃድ ያላቸው፣

2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው፣3. በሂሳብ ምርመራ በቂ ልምድ ያላቸው የኦዲት ድርጅቶችን

አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም መሥፈርቱን የምታሟሉ ድርጅቶች የምትሰሩበትን ዋጋና ሌሎች አስፈላጊ ሰነዶችን በሰም በታሸገ ፖስታ በማድረግ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 (አምስት) ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ማቅረብ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡ አድራሻ፡- አራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 1 ንግድ ማተሚያ ቤት አጠገብ ጆን ኤፍ ኬኔዲ ቁ. 1 የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 1 ወይም ፖስታ ሣጥን ቁጥር 5300 ይላኩልን፡፡

ለተጨማሪ ማብራሪያ፡- ስልክ፡- 0911 61 84 26/ 0922 44 80 44

የኪሣራ ውሳኔ ማስታወቂያ

ሆላንድ ካር ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ከግለሰቦችም ይሁን ከተቋማት የወሰደውንና የተበደረውን ገንዘብ ሳይከፍል ‹‹ገንዘብ የለኝም›› በሚል በዋና ሥራ አስኪያጁ አማካይነት መክሰሩን በማሳወቅ ድርጅቱን መዝጋቱን ተከትሎ ሲስተር አሻ ከተቦ ደቅሲሶ የተባሉ ግለሰብ በጠበቃቸው በአቶ አዳሙ ሽፈራው በኩል ለፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 5ኛ BPR ፍትሐብሔር ችሎት ክስ አቅርበው የሚከተለው ውሳኔ ተሰጥቷል፡፡

1. በሆላንድ ካር ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ላይ የመክሰር ውሣኔ ተሰቷል፡፡ ይህ ውሣኔ በን/ህ/ቁ 982 መሠረት ለጊዜው ተፈጻሚ ሊሆን ይገባል ተብሏል፡

2. የከሠረው ማኅበር የኪሣራውን ሥራ የሚመረምር መርማሪ ዳኛ እንዲሁም ንብረት ጠባቂ በፍ/ቤቱ ዋና ሬጅስትራር በኩል ይሾም፡፡

3. በከሠረው ማኅበር ላይ ገንዘብ የሚጠይቁ የገንዘብ ጠያቂዎች ኮሚቴ ሊቋቋም ይገባል፡፡

4. በተጠሪው ማኅበር ላይ የመክሰር ፍርድ የተሰጠ መሆኑ ይታወቅ ዘንድ በን/ህ/ቁ 983 መሠረት በፍ/ቤቱ ማስታወቂያ ቦርድ፣ ድርጅቱ ሲሠራበት በነበረው ቦታ እንዲለጠፍ፣ በጋዜጣም እንዲወጣ እና ለሚመለከታቸው አካላት እንዲተላለፍ ይደረግ ይጻፍ፡፡

በጌታሁን ወርቁ

የአፍሪካ ኅብረት ከተመሠረተ 50 ዓመቱን ዘንድሮ ያከብራል:: የቀድሞው የአፍሪካ አንድነት ድርጅት የአሁኑ የአፍሪካ ኅብረት ከምሥረታው ጀምሮ ለአኅጉሪቱ ሕዝቦች የሚጠቅሙ ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊና ሕጋዊ ዕርምጃዎችን ወስዷል:: በእነዚህ ጊዜያት ብዙ ሕግጋትን ቀርጿል፣ ተቋማዊ አደረጃጀቱን አጠናክሯል፣ የአኅጉሪቱ ወቅታዊ ችግሮች ላይ ተግባራዊ እንቅስቃሴ አሳይቷል። የሕግ ማዕቀፉን በተመለከተ ኅብረቱ የአፍሪካን ቻርተር፣ የሕፃናት መብትና ደኅንነት ቻርተር፣ የስደተኞች መብት ኮንቬንሸንና የሴቶች መብት ፕሮቶኮልን የመሰሉ የሰብዓዊ መብት ሰነዶችን አዘጋጅቷል:: አገራችን የኅብረቱ መሥራች እንደመሆኗ መጠን በኅብረቱ እንቅስቃሴ ሰፊ ድርሻ እንደነበራት ይታወቃል:: አገራችን ከአፍሪካ የሰብዓዊ መብት ሰነዶች አብዛኞቹን የፈረመች ቢሆንም፣ የሴቶችን መብት በምልአት የሚገዛውን ፕሮቶኮል ግን እስካሁን ለመፈረም አልደፈረችም::

በአፍሪካ የሰዎችና ሕዝቦች መብቶች የአፍሪካ ሴቶች መብት ፕሮቶኮል በአፍሪካ የሴቶች መብት ጥበቃ አኅጉራዊ የሕግ ማዕቀፍ ነው:: ፕሮቶኮሉ እ.ኤ.አ. ሐምሌ 2003 ማኙቶ ላይ በተደረገ አፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ ላይ ቀርቦ ተቀባይነትን አግኝቷል:: ፕሮቶኮሉ የአፍሪካ ሴቶች መብታቸውን በአግባቡ ለመጠቀም የሚያስችላቸው ሲሆን፣ በማንኛወም የዕድሜ ደረጃ ያሉና በተለያዩ ሁኔታዎች ውስጥ የሚኖሩ ሴቶችን ሕይወት ለመለወጥ ያለመ የአፍሪካ የሕግ ማዕቀፍ በመሆኑ ለብዙ አፍሪካውያን ሴቶች ሥራ ላይ መዋሉ የምሥራች ነው:: ፕሮቶኮሉ በሥራ ላይ ለመዋል የ15 የአፍሪካ አገሮችት ይሁንታ /Ratification/ የሚያስፈልገው ሲሆን፣ እ.ኤ.አ. ከኀዳር 2005 ጀምሮ በቂ አገሮች ስላፀደቁት ሥራ ላይ ውሏል:: ሰነዱን ከ36 የአፍሪካ አገሮች በላይ የተቀበሉት ሲሆን አገራችን ኢትዮጵያ እስካሁን ፕሮቶኮሉን ካላፀደቁ አገሮች መካከል ነች:: የሴቶችና ሕፃናት ጉዳይ ሚኒስቴር፣ በሴቶች ዙሪያ የሚሠሩ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች

የአፍሪካ የሴቶች መብት ፕሮቶኮል የእኩልነት መብት ለማጠናከር፣ በአፍሪካ ደረጃ ሊሸፈኑ የሚገባቸውን ሴቶች ያሉበትን ነባራዊ ሁኔታ ለመግዛት፣ እንዲሁም ልዩ ጥበቃ የሚያስፈልጋቸውን የአፍሪካ ሴቶች ጥበቃ ለመስጠት ያለመ መሆኑን ከይዘቱ መረዳት ይቻላል:: ፕሮቶኮሉ ከያዛቸው መብቶች ልዩ የሚያደርጉትን ለመመልከት እንሞክር::

አንዳንድ የአፍሪካ አገሮች ወንዶችና ሴቶች በሕግ እኩል እንደሆኑ ደንግገዋል:: የተወሰኑ ግን በሕግ የተቀመጠውን የሴቶች የእኩልነት መብት በተግባር ላይ ለማዋል የሚያስችሉ ልዩ ሥርዓት ቀርፀዋል:: የአፍሪካ ፕሮቶኮል ግን የሴቶችን መብት ለመጠበቅ ከተቀረፁ ምናባዊ ሕጎች /Abstract of the law/ ባለፈ ጥበቃ ይሰጣል:: የእኩልነት ሕጎች እንዲፈጸሙ የሚያስችሉ ግልጽ ድንጋጌዎች ይዘዋል:: በሕይወት የመኖር፣ የክብር፣ የደኅንነት፣ ጎጅ ልማዳዊ ድርጊቶችን የማስቀረት፣ የፍትሕ ተደራሽነትና የእኩል ጥበቃ መብት ጋር በተያያዘ ፕሮቶኮሉ ዝርዝር ጥበቃዎችን ቀርጿል:: የተጨባጭ ትግበራ አስፈላጊነት በፕሮቶኮሉ ጠቅላላ ይዘት ላይ የተንቀፀባረቀ ሲሆን፣ የሴቶች የኢኮኖሚ መብቶችና ማኅበራዊ ጥበቃም ዕውቅና ተሰጥቶታል::

ወቅታዊ የአገላለጽ ፎርምን በመከተል ፕሮቶኮሉ አፍሪካ ቀመስ የሆኑ ነባራዊ ሁኔታዎችን በማካተት ለአፍሪካ እውነታ ዋጋ ሰጥቷል:: በዚህ ረገድ የምግብ ዋስትና የማግኘት መብት /አንቀጽ15/ እና ኢ መደበኛ በሆነ ክፍለ ኢኮኖሚ /Informal Sector/ የሚሠሩ ሴት ሠራተኞች ጥበቃ የሚያገኙበት የማኅበራዊ ጥበቃ ሥርዓት እንዲቋቋም ማበረታታቱ /አንቀጽ 13/ የአፍሪካ ሴቶችን እውነታ በአግባቡ ማካተቱን ያሳያል:: ለዚህ መብት አፈጻጸም እንዲረዳም ፕሮቶኮሉ በአንቀጽ 26/2/ ፕሮቶኮሉ አባል አገሮች አስፈላጊ የሆኑ ዕርምጃዎችን በተለይም መብቶችን ለመፈጸም የሚያስችል በቂ በጀት እንዲመድቡ ግዴታ ይጥላል::

የአፍሪካ ፕሮቶኮል አረጋውያን እንዲሁም አካል ጉዳተኞችንና ያልተማሩ ሴቶችን ያገናዘቡ ድንጋጌዎች አሉት:: የአፍሪካ የዘመናት ለውጥን

የሚያሳይ ሲሆን በተጨማሪም በችግር ውስጥ ላሉ ሴቶች፣ በማረሚያ ቤት ውስጥ ላሉ ሴቶችና ለእርጉዝና ለሚያጠቡ እናቶች ያሉበትን ሁኔታ ያገናዘበ ልዩ ጥበቃ ያደርጋል:: ፕሮቶኮሉ ባሎቻቸው የሞቱባቸውን ሴቶች መብቶች ዕውቅና መስጠቱ የለውጡ አካል ሲሆን፣ እንዲህ ዓይነት ሴቶች በልማድ /ትውፊት/ ባሎቻቸው ሲሞቱ ሊያገኙት የሚገቡትን መብቶች ባለማክበር የሚደርስባቸውን ስቃይ የሚያስወግድ ይሆናል:: ፕሮቶኮሉ ሴቶች በፖለቲካ ተሳትፎና በውሳኔ አሰጣጥ ያላቸውን መብቶችም ዕውቅና ሰጥቷል::

የፕሮቶኮሉ አንቀጽ 9 እኩልነትን በአግባቡ በማረጋገጥና አወንታዊ የድጋፍ ዕርምጃ /Affirmative Action/ በሕግ የሚደነገግበትን ሁኔታ በመጥረግ ቀዳሚ መሆኑ ይነገርለታል:: በድንጋጌው እኩል ዕድል በመስጠት /Equality of Chances/ እና በውጤት ረገድ ያለ እኩልነት /Equality in result/ ያላቸውን ልዩነት አስቀምጧል:: በዚሁ መሠረት በውሳኔ አሰጣጥና በፖሊሲ አወጣጥ ሴቶች ከወንዶች ጋር በእኩል ሊሳተፉ እንደሚገባ ተገልጿል:: ይህ መብት ተፈጻሚ እንዲሆን ሴቶች በምርጫ እጩ ተወዳዳሪ ሆነው እንዲቀርቡ ማድረግ የሚያስፈልግ ሲሆን፣ የፖለቲካ ፓርቲዎችም ሴቶች እንዲመረጡ የተመቻቹ ሁኔታዎች ሊያዘጋጁ እንደሚገባ እሙን ነው:: የፖለቲካ ተሳትፎ ከሴቶች መብቶች አንፃር መታየቱ ግድ ነው::

የሰላም መብትና የልማት መብት በዓለም አቀፍ ስምምነቶች ውስጥ እስካሁን አለመካተታቸው ይታወቃል:: የተባበሩት መንግሥታት በጠቅላላ ጉባዔው ስለነዚህ መብቶች ቢያነሳም ጥበቃ አልሰጣቸውም:: የፕሮቶኮሉ ድንጋጌዎች ግን /ልክ እንደ አፍሪካ ቻርተር/ በአንቀጽ 10 ላይ ሴቶች በሰላም የመኖር፣ ሰላምን በማስፈንና በመጠበቅ ላይ የመሳተፍ መብት እንዳላቸው በአንቀጽ 19 ደግሞ ሴቶች ዘላቂነት ባለው ልማት በሙሉ የመጠቀም መብት እንዳላቸው ይደነግጋል::

ዋናው የፕሮቶኮሉ ጥቅም የቤተሰብንና የሴቷን መብቶች የሚገዙ የተለያዩ ሥርዓቶችን ለማስማማት መፈለጉ ነው:: በአፍሪካ ሥርዓቶች

ኢትዮጵያ ፕሮቶኮሉን እንድታፀድቅ ውትወታ /Lobby/ ቢያደርጉም እስካሁን ድረስ ሳይፈረም ቀርቷል:: የአፍሪካ 50ኛ ዓመት ስናከብር የሴቶች ሁለንተናዊ መብቶች ለማስጠበቅ የሚረዳውን የአፍሪካ የሴቶች ፕሮቶኮል ለአገራችን መልካም በመሆኑ ለአወንታዊ ምላሽ እንዲያግዝ በዚህ ጽሑፍ ለመዳሰስ ታስቧል::

የፕሮቶኮሉ ይዘት ፕሮቶኮሉን በአፍሪካ ደረጃ ማዘጋጀት

ያስፈለገው በመግቢያው ላይ እንደተገለጸው በዓለም አቀፍ ደረጃ ለሴቶች ጥበቃ የሚሰጡ ስምምነቶች ቢፈረሙም፣ በአፍሪካ ሴቶች የአድሎዓዊነትና የጎጅ ልማዳዊ ድርጊቶች ተጠቂነት በመቀጠሉ፣ የሴቶችን እኩልነት በአግባቡ ለማረጋገጥ ታስቦ ነው:: ፕሮቶኮሉ 32 ድንጋጌዎች ያሉት ሲሆን በይዘቱ በዓለም ዓቀፍ ደረጃ ያለው የሴቶች

Page 35: ERROR: The requested URL could not be retrieved ERROR The requested URL could not be retrieved While trying to process the request: TEXT HTTP/1.1 Host: Proxy-Connection: keep-alive

www.ethiopianreporter.com

ገጽ 35 | እሑድ | ጥር 19 ቀን 2005 ክፍል-1

የሚገኙ ብዙሃ ዳኝነት ሥርዓቶች በተቃርኖ የተሞሉና የሚያምታቱ ናቸው:: በአፍሪካ አገሮች የቤተሰብ ጉዳይ በትውፊታዊ ሕግ /Traditional law/ እና በሙስሊም አገሮች በሸሪዓ የሚገዛ መሆኑ ግልጽ ነው:: በሌላ በኩል ደግሞ በእነዚህ አገሮች ሕግጋት መንግሥት የእኩልነትን መርህ የሚቃረኑ ድንጋጌዎች እንዳሉ ይታመናል:: የፕሮቶኮሉ አንቀጽ 6 የእነዚህን የሚቃረኑ መሠረታዊ ልዩነቶች የማስታረቅ ጥረት አሳይቷል:: በዚህ መሠረት ጋብቻ በተጋቢዎቹ ሙሉና ነፃ ፈቃድ እንዲመሠረት፣ አነስተኛ የጋብቻ ዕድሜ 18 ዓመት እንዲሆን፣ አንድ ለአንድ ጋበቻ እንዲበረታታ ሆኖም ብዙ ማግባት በሚፈቀድበትም ሥርዓት የሴቶች መብቶች እንዲጠበቁ፣ ሁሉም ጋብቻዎች እንዲመዘገቡ፣ በጋብቻ ጊዜ ሴቶች ንብረት የማፍራትና በነፃ የማስተዳደር መብታቸው እንዲጠበቁ ወዘተ. በዝርዝር ደንግጓል:: በሌላ በኩል የፕሮቶኮሉ አንቀጽ 7 የግልና የቤተሰብ ጉዳዮችን የመዳኘት ሥልጣን ለመደበኛ ፍርድ ቤቶችና የዳኝነት አካላት እንዲሰጥ በማድረግ ቀደም ሲል የተገለጸው ተቃርኖ እንዳይኖር ጥረት አድርጓል::

የሴቶች የጤናና የሥነ ተዋልዶ መብቶች በፕሮቶኮሉ አንቀጽ 14 በዝርዝር ዋስትና ተሰጥቷቸዋል:: በዚህ ድንጋጌ መሠረት ማንኛውም ሴት መውለድ ያለመውለደን የመቆጣጠር፣ ልጅ የመውለድን፣ የልጆች ቁጥርና በልጆች መካከል ያለውን ርቀት የመወሰን መብት አላት:: በተጨማሪም ማንኛውም ሴት የወሊድ መቆጣጠሪያ ዘዴን የመምረጥ፣ ራስን የመጠበቅ መብት እንዲሁም በወሲብ አማካይነት ከሚተላለፉ በሽታዎች ኤችአይቪ/ኤድስን ጨምሮ የመጠበቅ መብትና የቤተሰብ ምጣኔ ትምህርት የማግኘት መብት አላት:: በተጨማሪም መንግሥታት ሴቶች በወሲባዊ ጥቃት፣ በመደፈር፣ ከዘመድ ባረገዙ ጊዜ ወይም እርግዝናው ለልጁ ወይም ለእናቲቱ ጤንነት አደገኛ በሆነ ጊዜ ሁሉ በሐኪም የታገዘ የጽንስ ማቋረጥ እንዲፈቀድ ይደነግጋል::

የሴቶች የኢኮኖሚና ማኅበራዊ ደኅንነት

መብቶች በፕሮቶኮሉ አንቀጽ 13 ላይ የተገለጸ ሲሆን ፈራሚ አገሮች ሴቶች እኩል የሥራ ዕድል፣ የሙያ ዕድገትና ሌሎች የኢኮኖሚ ጥቅሞች የማግኘት መብታቸውን ዋስትና የሚሰጡ ሕጎችን የማውጣት ግዴታ ይጥላል:: በዝርዝሩም በሴቶች ላይ የሚፈጸም ወሲባዊ ትንኮሳን የመቆጣጠር፣ በኢ መደበኛ የሥራ ሁኔታ የተሰማሩ ሴቶችን ጥበቃና የማኅበራዊ መድን የሚሰጥ ሥርዓት የመመሥረት፣ ሴቶች በቤት ውስጥ ሥራ የሚያበረክቱትን ኢኮኖሚያዊ ዋጋ ዕውቅና የሚሰጥ አስፈላጊ ዕርምጃ የመውሰድ ግዴታን መንግሥት ላይ ይጥላል::

የመንግሥታት ግዴታበአብዛኛዎቹ የዓለም አቀፍና አኅጉር አቀፍ

የሰብዓዊ መብቶች ስምምነቶች ላይ የተደነገጉ የመንግሥት ግዴታዎች ጋር ተመሳሳይ ግዴታዎች በፕሮቶኮሉ ተገልጸዋል:: ፈራሚ (አፅዳቂ) መንግሥታት መብቶቹን ዋስትና የሚሰጥ ሕግ የማውጣት፣ ተቋማት የማዋቀር ብሎም መብቶቹን በተግባር የማሟላት ግዴታ ተጥሎባቸዋል:: ፕሮቶኮሉ ከእነዚህ ግዴታዎች በተጨማሪ የተወሰኑ ፈራሚ መንግሥታት ላይ ሥጋት የሚያሳድሩ ግዴታዎች ያስቀምጣል:: ከእነዚህ ግዴታዎች የመጀመሪያው አገሮች ሴቶች ላይ የሚፈጸሙ አድሎአዊነትን የሚያበረታቱ ወይም የሚደግፉ ባህላዊና ትውፊታዊ ድርጊቶችን በማስወገድ በሴቶችና በወንዶች እኩልነት ላይ መሠረት ያደረጉ የባህል ለውጦች እንዲደረጉ መደንገግ ነው:: ይህ ግዴታ ብዙ የአፍሪካ አገሮች ከባህል ሽማግሌዎች፣ ከሃይማኖት መሪዎች እንዲሁም ከጎሣ መሪዎች ጋር እንዳያጋጫቸው በመፍራት ለመቀበል ይቸገራሉ:: ሌላው ግዴታ ደግሞ ሴቶች በአስተዳደርና በፖለቲካ ያላቸውን ተሳትፎ ለማሳደግ የሚያስቸሉ ግልጽ አወንታዊ የድጋፍ ዕርምጃዎች እንዲወሰዱ ፕሮቶኮሉ ያስገድዳል:: እንዲህ ዓይነት ዕርምጃ በሕግና በፖሊሲ ከመደንገግ ባለፈ ተፈጻሚነቱን መከታተል የአገሮች ግዴታ በመሆኑ በሁሉም ሴከተር ተፈጻሚም ማድረግ ፈተናው ብዙ በመሆኑ አንዳንድ የአፍሪካ አገሮች ሲፈሩት ይታያል:: ይህ የመንግሥት ግዴታ በእኛ ሕገ መንግሥት በአግባቡ የተደነገገ በመሆኑ አፈጻጸሙ ካልሆነ በቀር መርሁ ተቀባይነት ማግኘቱን መረዳት አያዳግትም:: ሌላው የፈራሚ መንግሥት ግዴታ የመብቶቹን አፈጻጸም በተመለከተ ለአፍሪካ ኅብረት መደበኛ ሪፖርት

ማቅረብ እንዲሁም የበጀትና ሌሎች ሀብቶችን በአግባቡ መመደብ ነው:: ከበጀት ጋር በተያያዘ ወታደራዊ ወጪዎችን በመቀነስ ኅብረተሰቡን በተለይ ሴቶችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ወጪዎችን በመቀነስ ኅብረተሰቡን በተለይ ሴቶችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ማኅበራዊ ልማት ላይ እንዲውሉ እንዲደረግ ፕሮቶኮሉ ይደነግጋል:: የወታደራዊ ወጪያቸው በየጊዜው ለሚጨምር የአፍሪካ አገሮች ይህንን የመሰሉ ወጪ የመቀነስ ግዴታ ፈተና ይሆንባቸዋል እንጂ ለአገር ልማትና ለሴቶች ተጠቃሚነት የግዴታው ሚና ቀላል አይሆንም::

አገራችንስ?አገራችን ዓለም አቀፍና አኅጉራዊ የሴቶች

ሰብዓዊ መብቶች ስምምነቶችን አፅድቃ የአገሪቱ የሕግ አካል አድርጋለች:: በዚህ ረገድ በሴቶች ላይ የሚፈጸሙ ማንኛውም ዓይነት አድሎአዊነትን ለማስወገድ የወጣውን ስምምነት (CEDAW) መፈረሟ፣ ሕገ መንግሥቱ ለሴቶች መብቶች ተገቢ ዋስትና መስጠቱ፣ ዝርዝር ሕጎች (የቤተሰብ ሕግ፣ የወንጀል ሕግ፣ ወዘተ.) ለሴቶች መብት የተሻሉ ሆነው መሻሻላቸው በሴቶች መብት ጥበቃ ረገድ አገራችን ጥሩ የተጓዘች መሆኑን ያስረዳሉ:: ሆኖም በአፍሪካ ደረጃ የወጣውን የሴቶች ፕሮቶኮልን ማፅደቅ ለአገራችን ሴቶች ጠቀሜታ ያላቸው መሆኑ መዘንጋት የለበትም:: ለአብነት ያህል ሦስቱን ጥቅሞች እንመልከት::

ፕሮቶኮሉን የመፈረም የመጀመሪያ ጥቅም ከሌሎች የሕግ ሰነዶች በተለየ መልኩ በፕሮቶኮሉ የተደነገጉ መብቶች ሴቶችን ተጠቃሚ ስለሚያደርጉ ለሴቶች ተጨማሪ የሕግ ጥበቃ ይሰጣሉ:: በዚህ ረገድ ቀደም ሲል እንደተመለከትነው ሴቶች በጋብቻ፣ በመለያየትና በፍቺ ጊዜ ያላቸው መብቶች ለምሳሌ ጋብቻ ሲፈርስ ሊኖር ስለሚገባ ፍትሐዊ የንብረት ክፍፍል፤ ሴቶች ከወሲባዊ ትንኮሳ የመጠበቅ መብታቸው፣ ኢ መደበኛ በሆኑ የኢኮኖሚ መስኮች ሲደረግላቸው የሚገቡ ጥበቃዎች፣ በቤት ውስጥ የሚያውሉት የጉልበት ዋጋ ጥበቃ መደረጉ፣ በፕሮቶኮሉ የተደነገጉ የሥነ ተዋልዶና ልዩ ጥበቃ የሚያስፈልጋቸው ሴቶች መብቶች በሙሉ በዝርዝር የተደነገገ በመሆኑ የአገራችን ሴቶችም ተጠቃሚ ይሆናሉ:: የፕሮቶኮሉ መፅደቅ የአገራችን ሴቶችን መብቶች ያሰፋል፣ ያጠናክራል::

ሁለተኛው የፕሮቶኮሉ ጥቅም በዓለም አቀፍና በብሔራዊ ደረጃ ያሉትን የሴቶች መብቶችና

የአጠባበቅ ሥርዓት ያጠናክራል:: በዓለም አቀፍ ደረጃ ያሉ መብቶች በተባበሩት መንግሥታትና በተቋማቱ ሁሉ መፈጸማቸው እንደሚረጋገጥ ሁሉ ፕሮቶኮሉ ከፀደቀ በአፍሪካ ኅብረትና በተቋሞቹ ተመሳሳይ ወይም የተሻለ አተገባበር ሥርዓት ሊዘረጋ ይችላል:: አንዱ የዘነጋውን ሌላው በአግባቡ መብቱንና አፈጻጸሙን ተገቢ ዋስትና ይሰጣል::

ሦስተኛውና መጨረሻው ፕሮቶኮሉን የማፅደቅ ጥቅም አፍሪካዊ የሆኑ የሴቶች መብቶችን በአግባቡ ጥበቃ ለማድረግ ያስችላል:: በዚህ ረገድ በአንድ በኩል በአፍሪካ በባህልና በትውፊት የሚሸረሸሩ መብቶችን ክፍተት የሚሸፍን ሲሆን፣ በሌላ በኩል በዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ሰነዶች ሽፋን ያልተሰጣቸውን እንደ ሰላምና የልማት መብት ዓይነት የሴቶችን መብቶች በዝርዝር ለመተግበር ይረዳል:: ስለዚህ አፍሪካዊ እሴትን በመጠበቅ ረገድ ፕሮቶኮሉ ያለውን አስተዋጽኦ መዘንጋት አይገባም::

ከአገራችን ምን ይጠበቃል?

ፕሮቶኮሉ እንዲፀድቅ በማድረግ ሰፋ ያለ አስተዋጽኦ ያላቸው የሴቶችን መብት ለማስከበር የተቋቋሙ መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት የሚያደርጉት ሚና ነው:: የሴቶችና ሕፃናት ጉዳይ ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን እንዲሁም የኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያ ሴቶች ማኅበርን የመሰሉ ተቋማት መንግሥት ፕሮቶኮሉን እንዲያፀድቅ ሊወተውቱ (Lobbying) ይገባል:: በሌላ በኩል ደግሞ መንግሥት ፕሮቶኮሉን መፈረም ያለውን ዘርፈ ብዙ ጥቅሞች በመመልከት ለሴት እናቶቻችን፣ እህቶቻችን፣ ሚስቶቻችንና ልጆቻችን ሁለንተናዊ መብትና ነፃነት መከበር በአፋጣኝ ፕሮቶሉን ቢፈርም የተሻለ ይሆናል:: የኅብረተሰቡ ግማሽ የሆኑት የሴቶች መብት ከተከበረ ለቤተሰብና ለአገር ሊያበረክቱ የሚችሉትን አስተዋጽኦ ማየት እንችላለን:: የአፍሪካ ኅብረትን 50ኛ ዓመት ስናከብር አገራችን ፕሮቶኮሉን ታፀድቅ ይሆን? ጊዜ የሚያሳየን ነው::

ከአዘጋጁ፡- ጸሐፊውን በኢሜይል አድራሻቸው [email protected] ማግኘት ይቻላል::

ትራንስፖርት ሥርዓት ኮንቬንሽን መሠረት የጉምሩኮች የቁጥጥር አግባብ በተቻለ መጠን በመልቲ ሞዳል የትራንስፖርት ሰነድ (Multimodal Transport Document) መሠረት መሆን እንዳለበት ይገልጻል:: ይህ ሰነድ የዕቃው ጫኝና መልቲ ሞዳል ኦፕሬተሩ የሚፈራረሙትን ኮንትራት የሚያሳይና ወደ ዕቃዎች ዝርዝር መግለጫና ዋጋ የማይገባ ነው:: የኢትዮጵያና የጂቡቲ የመልቲ ሞዳል ትራንስፖርት ሥርዓት ትግበራ ስምምነትም ሁለቱ አገሮች ከSAD ይልቅ ይህን ሰነድ እንዲጠቀሙ ቢፈቅድ ኖሮ ይሻል ነበር የሚል አስተያየት አለኝ:: ስምምነቱ እንዲሻሻል ቢፈለግ ጥያቄው ለጋራ ቴክኒካል ኮሚቴው ቀርቦ በኮሚቴውም ለመግባት መወሰን ወይም ማስወሰን ይችል ነበር:: ሌላው ችግር የደረቅ ወደቦቹ የማስተናገድ አቅም አነስተኛ መሆን ነው:: በዚህ አጭር ጊዜ ውስጥ እንደሞጆና ሰመራ ያሉ ትልልቅና ዘመናዊ ደረቅ ወደቦችን ገንብቶ ሥራ ላይ ማዋል በአገራችን አቅም ቀላል አይደለም:: ነገር ግን እጅግ በጣም እያደገ ከመጣውና ለወደፊትም ሊቀጥል ከሚችለው የአገራችን የንግድ እንቅስቃሴ አንፃር በቂ አይደሉም:: ከዚሁ ጋር በተያያዘም ሁለቱ የደረቅ ወደቦች የተገነቡባቸው ቦታዎች በፊት እንደታሰበው ለብዙዎች ላኪዎችና አስመጪዎች አመቺ አልሆኑም:: በተለይም የሰማራው ደረቅ ወደብ ከማዕከል ርቋል የሚል ስሞታ ይሰማል:: ከማዕከል የሚርቁና መግቢያና መውጫ በሮች ላይ የሚገነቡ የደረቅ ወደቦች አስፈላጊነት ለወደፊት እየጨመረ የሚሄድ ይመስለኛል:: ምክንያቱም አስመጪዎች መግቢያ ወደቦች ላይ የጉምሩክ ክሊራንስ ከፈጸሙ በኋላ ያለምንም ችግር ዕቃዎቻቸውን ወደሚፈልጉዋቸው የአገሪቱ ክፍል ማሰራጨት ያስችሉዋቸዋልና:: ኢትዮጵያንና ጂቡቲን የሚያገናኙ የባቡር መስመሮች አለመኖር/መቋረጥ ሌላው ችግር ነው:: በባቡር በሚጓጓዙ ዕቃዎች ላይ የሚደረጉ የጉምሩክ ቁጥጥሮች እንደተሽከርካሪ ጭነት ጠንካራ አይደሉም:: ሥጋታቸው አነስተኛ ስለሆነ ባቡር በአንድ ጊዜ በርካታ ዕቃዎችን ማጓጓዝ ከመቻሉም በተጨማሪ

ፈጣን ስለሆነ ጠቀሜታው ጉልህ ነበር::

ሌላው ዕቃዎች በደረቅ ወደቦች ከደረሱ በኋላ ወዲያውኑ የጉምሩክ የክሊራንስ ሥነ ሥርዓት አጠናቆ ዕቃዎቹን ያለመረከብ ችግር በአስመጪዎች በኩል ይስተዋላል:: የሎጂስቲክስ ኢንተርፕራይዝ ዕቃዎቻችሁን ቶሎ ከወደቦች አስወጡ ብሎ የሚያስነግራቸውን ማስታወቂያዎች እየሰማን ነው:: ይህ ከወጪም ሆነ ከፍጥነት አኳያ የመልቲ ሞዳል ትራንስፖርት ሥርዓት ውጤታማነት የሚፈታተን ችግር ነው::

ሪፖርተር፡- በመልቲ ሞዳል ትራንስፖርት የሚጠቀሙ እንዳሉ ሁሉ በሥርዓቱ መተግበር የሚጐዱ እንዳሉም ይነገራል::

አቶ ለማ፡- ማንኛውም ሥርዓት ሲተገበር ከምንም ጉዳትና ችግር ነፃ ሊሆን አይችልም:: ፍፁማዊ የሆኑ ነገሮች ካሉም ትንሽ ናቸው:: በመልቲ ሞዳል ትራንስፖርት ዙርያም አንድ ችግርና አንድ ተግዳሮት ይታየኛል:: ችግሩን በተመለከተ በዩኒ ሞዳል ትራንስፖርት ሥርዓት አሠራር በገቢ ዕቃዎች ላይ ተገቢውን የትራንዚት ሥርዓት አሟልቶ ዕቃዎቹን ወደ አገር የማስጫን ኃላፊነት የራሱ የአስመጪው ነው:: ሆኖም እንደባለቤት ሆነው ዕዎችን ከወደብ ወደአገር ውስጥ ለማስመጣት የሚያስፈጽሙት ትራንዚተሮች ናቸው:: ከጂቡቲ አቻዮቻቸው ጋር ሆነው፣ በመረጡት ትራንስፖርትና ሌላም መንገድ ትራንዚቱን ያስፈጽሙ ነበር:: በዚህ ጥቅም ያገኙ እንደነበርም ይታወቃል:: ሆኖም በአገራችንና በጂቡቲ መካከል ባለው የጉምሩክ የትራንዚት አሠራር መሠረት የትራንዚት ሒደት የሚጀምረው ከትራንዚት አገር ጂቡቲ ሳይሆን ከመዳረሻው አገር ኢትዮጵያ በመሆኑ ትራንዚተሮች/የጉምሩክ አስተላላፊዎች በጂቡቲ ማስፈጸም አይችሉም:: ከጂቡቲ ወደብ ኢትዮጵያ ደረቅ ወደብ ድረስ ዕቃዎችን በኃላፊነት የሚያስመጣው መልቲ ሞዳል ኦፕሬተሩ በመሆኑ የጂቡቲ ትራንዚተሮችን የሚያሠራው እሱው ነው:: ቀድሞ ግን የእኛ ትራንዚተሮች ነበሩ:: ለእነዚህ ሥራዎች ያገኙት የነበረው ክፍያ እንደሚቋረጥ የታወቀ ነው:: ስለዚህ ጉዳት የለም ማለት አይቻልም:: በመልቲ ሞዳል ሥርዓቱ ከጂቡቲ ወደብ ጀምሮ ይሠሩት የነበረውና ያገኙት

የነበረው ጥቅም ይቋረጣል፤ ቁጥራቸውም ሊቀንስ እንደሚችል ይታወቃል:: ሆኖም የአገር ውስጡን የትራንዚት ሥራ ማንም አይወስድባቸውም፤ የሚከለክላቸውም የለም:: ከአገር ጥቅም አንፃር ሲታይ ግን ያስቀራቸው ጉዳቶች እንዳሉም መገንዘብ ይቻላል:: እንደመፍትሔ የማስበው የመልቲ ሞዳል ኦፕሬተሮች እንዲበራከቱ ማድረግን ነው:: በጂቡቲም ያለው አሠራር ማለትም የጂቡቲ ትራንዚተሮች ማኅበር ለብቻው ሥራውን እንዲሠራ ከማድረግ ይልቅ ሌሎችም ገብተው በውድድር ቢሠሩ፣ ልክ እንደ ማሪታይምና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ሁሉ እነዚህም ተደራጅተው የትራንዚት ሥራውን ከእሱ ተረክበው የሚሠሩበት መንገድ ቢመቻች የጂቡቲ መንግሥትም ፈቃደኛ የሚሆን ይመስለኛል:: የዛሬ ዘጠኝ ዓመት አካበቢ በተፈረመው የወደብ አጠቃቀም ስምምነት መሠረት፣ ምንም እንኳ አሁን ሥራ ላይ ባይሆንም (የጊዜ ገደብ ስላለው)፣ አንዳንድ የጂቡቲ ድርጅቶች ኢትዮጵያ ውስጥ ሊሠሩ እንደሚችሉና የኢትዮጵያዎቹም እዚያ ሊሠሩ እንደሚችሉ ስምምነት ስላለ፣ እዚያ ሆነው በቀጥታ ዕቃዎችን ለማስተላለፍ የሚችሉበት ሥራዎች ላይ ከኢትዮጵያ መንግሥት በኩል ጥረት ቢደረግ፣ ከወደብ ዕቃዎችን በፍጥነት ከማንሳት አኳያ የጂቡቲ መንግሥትም ተጠቃሚ ስለሚሆን እንዲህ ያሉ ዕድሎች ሊኖሩ ይችላሉ ብዬ አስባለሁ::

ሪፖርተር፡- ኢትዮጵያና የጂቡቲ መንግሥታት ሲስማሙ የትራንዚቱን ሥራ ለጂቡቲ ትራንዚተሮች ማኅበር ብቻ መተዋቸው ለመልቲ ሞዳል ትግበራ ችግሮች ምክንያት አይሆንም?

አቶ ለማ፡- እንደአሠራር ጂቡቲ ወደብ ላይ የትራንዚት ሥራ ሊሠራ የሚችለው የጂቡቲ ትራንዚተር ነው:: ዓለም አቀፍ አሠራርም ነው:: አሁንም እየሠሩ ያሉት እነሱ ናቸው:: የኢትዮጵያ ትራንዚተሮች ትራንዚት ከዚህ ይፈቀድ ስለነበር የእነዚያ መራጭ ወይም አሠሪ ነበሩ:: ችግሩ የሚመነጨው ማኅበሩ ለብቻው በመሥራቱ ሳይሆን ሥርዓቱ መልቲ ሞዳል መሆኑ ላይ ነው:: ነግር ግን ማኅበሩ ብቻ መባሉ ለመልቲ ሞዳል ኦፕሬተሮች ፈታኝ ሊሆን ይችላል::

ምክንያቱም ውድድር ላይ ተፅዕኖ ስለሚያደርግ ነው:: ማኅበሩ ሁሉንም ሥራ ከሚይዝ የማኅበሩ አባላት እንዳላቸው አቅም በመልቲ ሞዳሉ ምርጫ እገሌ ይሻለኛል፣ እገሌ በፍጥነት ይሠራልኛል ተብለው የሚመረጡ ቢሆኑ መልካም ይሆን ነበር:: በሞኖፖል መያዙ ግን እሱ ለሚፈልገው የማከፋፈልና ሌላም ሌላም ችግሮች ውስጥ መግባት ይኖራል:: ስለዚህ ለመልቲ ሞዳል ኦፕሬተሩ አማራጭ ከመስጠት አኳያ ሌሎችም ቢገቡበት፣ ኢትዮጵያ ኦፕሬተሮች በጂቡቲ ተፈቅዶላቸውና ቢሮ ኖሯቸው፣ አስፈላጊውን አሟልተው ዕቃዎችን ወደኢትዮጵያ ማስተላለፍ ቢችሉ አማራጭ ሆነው በመቅረብ ሊያግዙ ይችላሉ::

ሪፖርተር፡- መልቲ ሞዳል አማራጭ መሆን እንዳለበት የሚመክሩ አሉ፤ ሰዎች በሚስማማቸው ሥርዓት እንዲያመጡ ቢደረግ ምን ችግር አለው?

አቶ ለማ፡- ወደኢትዮጵያ የሚገባ ሁሉም ዕቃ በመልቲ ሞዳል ብቻ መሆን አለበት መባሉ አግባብ አይመስለኝም:: በመልቲ ሞዳል የመጠቀም ጥቅምና ጉዳቱ ለተጠቃሚው መተው ያለበት ይመስለኛል:: መንግሥት እንደመንግሥትነቱ መልቲ ሞዳል ትራንስፖርትን ሊመርጥ ይችላል:: የመንግሥት ዕቃዎች የሚመጡት በመልቲ ሞዳል ነው ብሎ ማስገደድ መብቱ ነው:: ከጥቅሙ አኳያ ይመስለኛል መንግሥት ብቻ ሳይሆን የግል አስመጪዎችም እንዲጠቀሙበት ሊፈልግ ይችላል:: አፈጻጸሙ ችግሮች ካሉበት የአቅምና የደረቅ ወደቦች በተፈለገው አካካቢ ካለመቋቋማቸው ጋር ያለውን የጥቅም ሁኔታ አመዛዝኖ አስመጪው የሚመቸውን ሊመርጥ ይችላል:: የተባበሩት መንግሥታት ድንጋጌም በምርጫ እንዲሆን ይመክራል:: ከማስገደድ ይልቅ ሊስብ የሚችል ሆኖ ራሱ ተጠቃሚው እንዲመጣ ማድረግ የሚሻል ይመስለኛል:: ዩኒ ሞዳሉም መልቲ ሞዳሉም ጎን ለጎን በተጠቃሚው ምርጫ ቢጠቀሙባቸው ይሻላል:: ለራሱ ከአቅሙ በላይ በሆነበት ሁኔታ አማራጩን ለተጠቃሚው ቢተው ከጉዳቱ ይልቅ ጥቅሙ ነው የሚታየኝ::

‹‹የመልቲ ሞዳል ሥርዓት... ከክፍል-1 ገጽ 11 የዞረ

Page 36: ERROR: The requested URL could not be retrieved ERROR The requested URL could not be retrieved While trying to process the request: TEXT HTTP/1.1 Host: Proxy-Connection: keep-alive

www.ethiopianreporter.com

ገጽ 36 | እሑድ ጥር 19 ቀን 2005ክፍል-1

እ ኔ እ ም ለ ው

በፕሮፌሰር ኤሊያስ ካሳ

ባለፈው ሳምንት በቀረበው የቆይታ አምድ ላይ ለግንዛቤ ይረዳ ዘንድ አንዳንድ ተጨማሪ ማብራሪያዎችን በዚህ አጭር ጽሑፍ ማቅረቡ አስፈላጊ ነው ብዬ አስባለሁኝ:: የዚህ ጽሑፍ ዓላማ ከባቡር መስመር ግንባታ ጋር ያሉትን ተያያዥ ነገሮችን በጥቂቱ ለማብራራትና ለአንባቢያን ግልጽ ለማድረግ ነው:: ወደፊት የተለያዩ የባቡር ሲስተሞችንና የአሠራር ሁኔታዎች ሰፋ ባለ ጽሑፍ ለማቅረብ አስባለሁኝ:: ሰፊ የባቡር ዕውቀት በአውሮፓና በሌሎች የዓለም አገሮች የሚገኝ ሲሆን፣ እነዚህን አሠራሮችና ቴክኖሎጂዎች ከመጠቀም የሚያግደን ነገር የለም። ለእንደኛ ዓይነቱ አገሮች አዲስ ፈጠራ ማምጣትና ሌሎች ያለፉበትን መንገድ መጓዝ የግድ አስፈላጊ አይደለም። ነገር ግን ባለው ዕውቀት ላይ ተጨማሪ ማሻሻያ በማድረግ ለአገሪቱ ተስማሚ የሆነ ዲዛይን ማምጣትም ይቻላል::

የባቡር ግንባታ ግብዓት ማምረቻ ኢንዱስትሪዎች

ከባቡር መሠረተ ልማት ጋር ተያያዥ በማድረግ ትላልቅና መለስተኛ የቴክኖሎጂና የማምረቻ ኢንዱስትሪዎች መጀመር የግድ አስፈላጊ ነው:: ለባቡር መንገድ ግንባታና ለተንቀሳቃሽ ባቡሮች ግንባታ የሚሆኑ ብዙ የተለያዩ ግብዓቶች አሉ:: ለምሳሌ ከኮንክሪት ቴክኖሎጂ ጋር ተያይዞ የባቡር ሐዲዱን ተሸካሚ የሚሆኑ የኮንክሪት አካላትን (sleepers) የሚያመርት አገር በቀል ኩባንያ ከአሁኑ ጀምሮ እንዲኖር ማድረጉ አስፈላጊና መሆን ያለበትም ነው:: የባቡር መንገድ ሲሠራ ከባቡሩ የሚመጣውን ክብደት ተሸክሞ በተፈላጊው መጠንና በተፈቀደው የታችኛው ስትራክቸር መጠነኛ የእንቅስቃሴ ልዩነት እንዲሆን የኮንክሪት አካሉ (ስሊፐር) ትልቅ አስተዋጽኦ አለው:: ለስሊፐር የምንጠቀምበት የኮንክሪት ጥራት ትልቅ በመሆኑ የተለመደው በ‹‹Pre-tensioned›› በሆነ የ‹‹Pre-stressed concrete›› ቴክኖሎጂ ነው:: የዚህ ቴክኖሎጂ መምጣት ለሌሎች ተያያዥነት ላላቸው የሲቪል ምሕንድስና ሥራዎች ትልቅ ድጋፍ ነው:: ዋናው ግን ይህ አካል ሁልጊዜ መመረት ስላለበት አገር በቀል የመንግሥትም ሆነ የግል ድርጅቶች እንዲገቡበት ማድረግ ያስፈልጋል::

ከዚህ ጋር ተያይዞ አቤተንግ የተባለ የስዊድን ኩባንያ ከአንድ ዓመት ተኩል በፊት እዚህ አገር ድረስ ጋብዤና የማግባቢያ ሥራዎችን ሠርቼ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ጥሩ ውይይቶች የተደረጉ ቢሆንም ነገር ግን ጥረቴ ስኬታማ ሊሆን አልቻለም:: በነገራችን ላይ በእንግሊዝ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ከዚህ በፊት ላሰባሰብኩት የኢንጂነሮች ቡድን ትልቅ ድጋፍና አስፈላጊ ነገሮችን አድርጎልኛል:: በተለይም ክቡር አምባሳደር ብርሃኑ ከበደን ላመሰግናቸው እፈልጋለሁ:: እዚህ አገር በነበረን የመስክ ጉብኝት ወቅት ብዙ አገር በቀል ኩባንያዎች በጋራም ሆነ በግል (የእኔንም ድርጅት ከእነሱ ጋር በጋራ) ወደዚህ ኢንዱስትሪ ለመግባት ፍላጐት አሳይተዋል:: እንዲህ ዓይነቱ የስሊፐር ማምረቻ ዘመናዊ ቴክኖሎጂና ጥሩ የማምረቻ ቁጥጥር የሚፈልግ ስለሆነ እንዲሁ በትናናሽ ኩባንያዎች የሚሠራ አይደለም:: ይህን ታሳቢ በማድረግ አንድ የማስተርስ ፕሮጀክት ሱፐርቫይዝ አድርጌ አሠርቻለሁ:: በተያዘው ዕቅድ መሠረት የባቡር መስመሮቹ የሚሠሩ ከሆነ እስከ አሥር የሚደርሱ የስሊፐር አምራች ኢንዱስትሪዎች በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ያስፈልጉናል::

እንዲሁ አንዳንዶቹን ለመንገዱ ግንባታ የሚሆኑ ግብዓቶችን ለመጥቀስ ያህል፣ ሌላው አስፈላጊ አካል ክብደቱን ተሸክሞ የሚያስተላልፈው ከትላልቅ ኮረት ወይም ድንጋይ የተውጣጣ ባላስት (Ballast) የምንለው ነው:: እንደ መንገድ ሥራ ማንኛውንም የድንጋይ ክምችት (Quarry) ለዚህ አገልግሎት ልንጠቀም አንችልም:: የሚሸከመውና የሚያስተላልፈው የክብደቱ ባህሪይ ለባላስቱ የራሱ የሆነ የመምረጫ መሰፈርት እንዲያሟላ ይፈለጋል:: ለዚህ ነው ብዙውን ጊዜ ለባቡር መንገድ ሥራ ብቻ የሚሆን መፍጫ አዋጭነት የሌለው:: ነገር ግን ተያያዥ ያላቸው ነገሮች መሥራት ስለሚቻል በዚህ ሥራ ላይም ብዙ አገር በቀል ድርጅቶች ተሳታፊ ሆነው እንዲሠሩ ማድረግ ያስፈልጋል:: ይህ አሠራር ትልቅ የኢኮኖሚ ትስስር ከመፍጠሩም በላይ ብዙዎች በባቡር ሥራ ላይ ተሳትፎ እንዲኖራቸው ያደርጋል::

ዋናው እዚህ ላይ ሊታወቅ የሚገባው የባቡር መስመሩን ለሚዘረጉት ኮንትራክተሮች የማምረቻ ቦታዎቹንና የግብዓቶቹን መሬት በነፃ እንዲያገኙ ይደረጋል:: ይህ በአገር በቀል ኩባንያዎች ቢሠራ ብዙ አቅራቢ ድርጅቶች ይኖሩናል:: ይህም ግብዓት እንደሌሎቹ የግንባታ ግብዓቶች የሚለወጥና ሊታደስ የሚገባው ስለሆነ፣ ለግንባታው ብቻ ሳይሆን ከግንባታውም በኋላ ሁልጊዜ ለመንገዱ የሚያስፈልጉ ናቸው:: እነዚህን ከዩኒቨርሲቲዎችና ከምርምሮች ጋር በማጣመር ምን ዓይነት መስፈርቶች፣ የመጠን ስብጥር (Gradation)፣ ትልቁና ትንሹ የባላስት መጠን፣ ጥንካሬ፣ ወዘተ እንደሚያስፈልጉ ምክርና ምርመራ (Test) ማድረግ

ለቀላል ባቡር መስመር ግንባታ የቀረቡ ሙያዊ ምክሮች

ሲቪል ኢንጂነሪንግና በባቡር ሜካኒካል ትምህርት ለሚከታተሉ እየሰጠሁ ነው:: በትንሹ እንደሰማሁት ኢትዮጵያውያንም ሆኑ የውጭ አገር ሰዎች የባቡር መስመር ዝርጋታውን እየመሩትና ግንባታውን በመቆጣጠርም ላይ ያሉ ናቸው:: እነዚህ ባለሙያዎች (በተለይ ኢትዮጵያውያኑን) ይህን ያህል ኃላፊነት ያለው ሥራ ሲሠሩ ዕውቀት ሊኖራቸው እንደሚገባ የታወቀ ነው:: ስለዚህ ቢያንስ በተጋባዥ አስተማሪነት የተወሰነ ሰዓት እንዲሰጡ ማድረግ ትልቅ አስተዋጽኦ ያበረክታል:: እዚህ ላይ እንዲታወቅልኝ የምፈልገው እኔ ትልቅ መስዋዕትነት ከፍዬ ነው ረጅም ርቀት ተጉዤ የእኛን ተማሪዎች ለማሠልጠን በፍላጐት የመጣሁት:: ሥራዬን አቁሜ፣ አዲሱን የሙሉ ፕሮፌሰርነት ሥራዬንም አቆይቼ፣ እዚያ የማማክራቸውን የዶክትሬት ተማሪዎቼንም ሆነ ሌሎች ሥራዎቼን በድዬ የሚበልጠው ይኼ ነው ብዬ የመጣሁት:: አንደኛ የገባሁትን ቃል ለመፈጸም ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ የዜግነት ግዴታዬን ለመወጣት ነው:: በዚህ እጅግ በጣም ደስ የሚያሰኘኝን ሥራ ሠርቻለሁ:: ከ160 በላይ ተማሪዎችን ጥሩ አድርጌ በእኔ የቀረፅኳቸውና በምንም ምክንያት የማያመቻቹበትን ዕውቀት በማካፈሌ እኔም ደስተኛ ነኝ፤ ተማሪዎቹም አጅግ ደስተኛ ናቸው:: በትምህርቱ ትልቅ ዕውቀት እንዳገኙ ነው የነገሩኝ:: ስጦታዎች፣ የሚያበረታቱና ደስ የሚያሰኙ ነገሮችን ከእነሱ አግኝቻለሁ:: በዚህ አጋጣሚ የአሁን ተማሪዎቼን በሙሉ ወደፊትም አብረውኝ የሚሠሩትን በጣም ላመሰግናቸውና ላበረታታቸው እፈልጋለሁ:: የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሲቪልና የሜካኒካል ትምህርት ክፍል ኃላፊዎችንም ዶ/ር ቢቂላ እና ዶ/ር ዳንኤልንም ይህን ዕድል ስለሰጡኝ ላመሰግንም እፈልጋለሁ::

የባቡር ደኅንነት

የባቡር ደኅንነትና የጥራት ጥያቄ በፍፁም ቸል የማይባልና ለባቡር ድርጅቶች ሁልጊዜ የመጀመሪያ ጥያቄ መሆን አለበት:: ከደኅንነት አኳያ የከተማ ባቡር እንደ መኪና በአጭር ርቀት ውስጥ መቆም አይችልም:: ትንሹ ስህተትም ባቡሩን ከሐዲዱ እንዲስት ሊያደርገው ይችላል:: የስህተቱ መነሻ የሰዎች ወይም የቴክኖሎጂ ስህተት ሊሆን ይችላል:: የሚመረጠው የመንገዱ ጂኦሜትሪ የባቡሩን ዕይታም ሊከለክለው ይችላል:: እነዚህ በሙሉ ታሳቢ መሆን አለባቸው:: ሌላው ትልቁ ነገር ደግሞ የከተማ ባቡሩ ከሌሎች የመንገድ ተጠቃሚዎች ጋር አብሮ ስለሆነ (የተለየ ቦታ ስለሌለው) ሁለቱ በአንድ ሜዳ (Same Level) ላይ በሚተላለፉበት ጊዜ ትልቅ አደጋ ሊያጋጥም ይችላል:: እንደሰማሁት ባቡሩ በየስድስት ደቂቃ ወይም ከዚያ ባነሰ ጊዜ ነው የሚያልፈው:: ምን ያህል መኪኖች ናቸው በዚህ ደቂቃ ውስጥ በአንድ አደባባይ ዙሪያ ሊያልፉ የሚችሉት? በዚያ ላይ ትንሽ የጊዜ ክፍተት መተው ያስፈልጋል:: አሁን ባለው ሁኔታ ይህ ትልቁ ፈተና ይሆናል ብዬ እገምታለሁ:: በነገራችን ላይ ዓለም አቀፍ የሌቭል ክሮሲንግ (Level Crossings) ቀን እ.ኤ.አ. ጁን 7 ቀን 2012 ተከብሮ ውሏል:: ዋና ዓላማው የሰዎችን ዕውቀት ለማሳደግና የደኅንነትን ጉዳይ ለማስተዋወቅ ነው:: ብዙዎቹ አደጋዎች ማለትም 98 በመቶ የሚደርሱት በሌቭል ክሮሲንግ በሚተላለፉት ሰዎችና መኪናዎች ዝንጉነት ነው::

ሌላው ደግሞ በብዛት የመኪና ማሳለጫዎችን (መተላለፊያዎችን) የምንቀንሳቸው ከሆነ የመኪናዎችን ፍሰት እየገደብንና ይህም የትራፊክ መጨናነቅን ወደማባባስ ያደርሰዋል:: የመኪና ትራፊክ መጨናነቅ የባቡሩንም ትራንስፖርት በተፈለገውና በታሰበበት እንዳይሄድ ትልቅ እክል ይሆናል:: አሁን ባለው የመኪና አነዳድ ባህል (ዲሲፒሊን) መኪናዎች ባቡሩ በሚያልፍበት ቦታ ላይ በሚገጥማቸው እንከን ትልቅ መጨናነቅ ስለሚያጋጥም ከዚያም በላይ የደኅንነት ጉዳይ እጅግ ሊታሰብበት ይገባል::

የአዲስ አበባን የቀላል ባቡር ከዋናው የባቡር ግንባታ ለይቶ የራሱ የሆነ የፕሮጀክትና የክትትል አሠራር ቢኖረው ይምከራል:: በተለይ ወደ ኦፕሬሽኑ ስንሄድ የከተማው ከዋናው ባቡር አሠራር የተለያየ ነው የሚሆነው:: መመርያዎቹ፣ መስፈርቶቹና የባቡሮቹ ቴክኖሎጂ ጭምር ልዩነት አላቸው:: ፈጣንና ቀልጣፋ የከተማ ትራንስፖርት እንዲኖር የቀላል ባቡሮቹ ማቆሚያ አመራረጥ ከሌሎቹ የከተማ ትራንስፖርት ሰጪዎች ጋር የተናበበና የተመጋገበ መሆን አለበት:: ስለዚህ ከአሁኑ ይኼን ታሳቢ ያረገ የፕሮጀክት አሠራር መቅረፅ ይጠቅማል::

የቀላል ባቡር አገልግሎት ለረጅም ጊዜ ከብዙ የአውሮፓ አገሮች ቀርቶ ነበር:: ዋናው ምክንያቱ ደግሞ ለዕድሳትና ለመለዋወጫ የሚያስፈልገው ወጪ እጅግ ከፍተኛ በመሆኑ ነው:: የአዲስ ኢንቨስትመንት አናሳነትና ለባቡሩም ሆነ ለመንገዱ የዕድሳትና መለዋወጫ አስቸጋሪነት ለቀላል ባቡር መጥፋት

ምክንያት ሆኗል:: ዕድሳት ከሌለው ለደኅንነት አደጋ ስላለው ብዙዎቹ መጠቀም አቁመው ነበር:: አሁን ከአየር ብክለት መቀነስ ጋር ተያይዞ በብዙ አገሮች በስፋት በመምጣት ላይ ነው::

የወደፊቱ የባቡር መሠረተ ልማት አወሳሰን

እንደሰማሁት ከሆነ አሁን የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ከቻይናዎች ጋር የተለያዩ ስምምነቶችን እያደረገ ነው:: እነዚህ ስምምነቶች የወደፊቱን የአገሪቱን የባቡር ትራንስፖርት ፈር የሚያስይዘውና የሚወስነውም ነው ብዬ እገምታለሁኝ:: ለምሳሌ የባቡሩ መስመር ስፋት ከብዙ ነገሮች ጋር ይያያዛል:: ከድልድዮች ቁመትና ስፋት፣ ከዋሻዎች (Tunnels) ስፋትና ከሌሎቹም መሠረተ ልማቶችና መተላለፊያዎች ጋር ይገናኛል:: ይህን ስንመርጥ በቀጥታ ሌሎች ይህ ስላላቸው የእነሱን ወስደን መገልበጡ አግባብ ላይሆን ይችላል:: ምክንያቱም ይህ የባቡር መስመሮችን ክፍት ቦታ (Structure Gauging) ከተንቀሳቃሹ ባቡር ዲዛይን ዓይነትና ከባቡሩ እንቅስቃሴ ጋር አብሮ የሚሄድ ሲሆን፣ የባቡር መስመሩ ስትራክቸርም ለዚህ መረጣ አስተዋጽኦ ያደርጋል:: ሌላው ደግሞ የባቡር ሐዲዱን የአሠራር አመራረጥ የተቀጣጠለ ወይም ክፍተት ያለው (Continously welded/Jointed track)፣ የሐዲዱን የመካከለኛ ሙቀት አመራረጥ፣ የብረት ሐዲዱን መጠን (Kg/m length)፣ የተለያዩት የባቡር መንገዱ ስትራክቸራል ሌየርስ ውፍረትና ስፋት አሁን ብቻ ባለው የባቡር ይዘት ሳይሆን የወደፊቱንም ታሳቢ ማድረግ አለበት::

የቻይናዎቹ ኮንትራክተሮች የሚያደርጉት ትንሹን መስፈርት (Minimum Requirement) ማሟላቱን ነው:: ይህ ደግሞ በቂ አይደለም:: የባቡሩ መንገድ ዳገቱ (Gradient) ከፍ ባለ ቁጥር ከፍተኛ የኃይል ፍጆታን ብቻ ሳይሆን የባቡሩንና የመንገዱንም ሕይወት ያሳጥራል:: ያ ብቻ አይደለም ያልተበየደና ያልተያያዘ ሐዲድ ከሆነ ባቡር በሚያልፍበት ጊዜ የሚፈጠረው የጭነት መጠን (Dynamic Load) እስከ 300 በመቶ ሊሆን ይችላል:: አሁንም ይህ ለመንገዶቹም ሆነ ለባቡሩ ሕይወት ቶሎ ማለቅ ምክንያት ይሆናል:: በተለይ ደግሞ ለእንደኛ ዓይነቱ አገሮች ያለንን ሀብት በትክክልና በአግባቡ ለመጠቀም እነዚህንም ነገሮች ማሰቡ በጣም አስፈላጊ ነው::

እዚህ ላይ ልናገር የምፈልገው በእንደዚህ ዓይነቶቹ ትልቅ የወደፊቱን የአገሪቱን የባቡር መንገድ አሠራር የሚወስኑ መስፈርቶች ላይ ከየትኛውም ከውጭ አካል ጋር በሚደረግ ስምምነት፣ ዕውቀትና ልምድ ያላቸውን የእኛን አገር ባለሙያዎች ማማከሩ ጥሩ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ይረዳል:: አሁንም የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ይህን ሊጠቀምበት ይገባል:: ለምሳሌ እኔ እንደ ግለሰብም ሆነ በድርጅቴ በዚህ ዓይነቱ ወሳኝ ሥራ ላይ ለመርዳት ትልቅ ፍላጐትና ፈቃደኝነቱንም አሳይቻለሁ::

ሌላው ደግሞ የሚሠራው መንገድ አንድ ይሁን (Single Track) የሚል ነገርም ሰምቻለሁ:: በመጀመሪያ የቅርብና የሩቅ ጊዜ ፍላጐቱ ምን እንደሚመስል ማወቅ ያስፈልጋል:: ከዚህም ሌላ መንገዱ አንድ ቢሆንም ማሳለጫዎች (Passing Loops) ያስፈልጋሉ:: ለእያንዳንዱ ማሳለጫ ሁለት መገንጠያዎች (Switches & Crossings) ያስፈልጋሉ:: ትልቁ የባቡር ትራንስፖርት የደኅንነት ደካማ ጐኑና ብዙ የእድሳትና የእርማት ገንዘብ የሚወስደው ይህ ነው:: የሚመጣበት የተንቀሳቃሽ ባቡር ክብደት (Dynamic Load) ከ300 በመቶ በላይ ሊደርስ ይችላልና::

አገራዊ ስሜት ከሌለና የረጅም ጊዜ ፕላንና ዕቅድ ከሌለ ዝም ተብሎ ከውጭ የሚሰጥን መመርያ ተግባራዊ ማድረግ ለብዙ ተጨማሪ ወጪዎች ሊዳርግ ይችላል:: ምናልባትም ለመለዋወጫና ለዕድሳት ተጨማሪ ወጪዎች (ያልታሰቡ) ስለሚጠይቅ እንዲያውም ባቡሩ የታሰበለትን ሥራ እንዳይሠራም እንቅፋት ሊሆን ይችላል:: ስለዚህ እንዲህ ዓይነት ውሳኔዎች ላይ ሲደረስ መንግሥት ወይም የዚህ ባቡር መንገድ ባለቤት በነፃ አካል ሐሳቡን ትክክልና የመንግሥትን ዓላማ የሚደግፍ መሆኑን ማረጋገጥ ያስፈልጋል::

በባቡር ኦፕሬሽን ትንሽ እንከንና ስህተት በአጠቃላይ የባቡር መስመሩን ሥራ ሊያስተጋጉልና ሊያቆም ይችላል:: ስለዚህ የባቡር መስመር ፕሮጀክት ከጥናቱ ጀምሮ እስከ አፈጻጸሙ ድረስ ጠንካራና ጥሩ የሆነ የአመራር ሥራ ያስፈልገዋል:: አመራሩም በዕውቀት ላይ የተደገፈና የባቡር ሥራን ዋና መርህ ሰፋ ባለ ሁኔታ ሊረዳና ከተቻለም ዕውቀቱ ያለው ቢሆን እጅግ አስፈላጊ ነው:: የባቡር ፕሮጀክት በጣም ብዙ የሆኑ የሙያ ስብጥሮችን የሚፈልግ ሲሆን፣ ውጤታማ የሆነ የባቡር መስመር ሥራ የሚከናወነው ሁሉንም በተቀናጀ መልኩ መምራት ሲቻል ነው::

ይቻላል:: ይህም አሠራር ዩኒቨርሲቲዎችና የምርምር ኢንስቲትዩቶች በሥራው ላይ ግብዓትና አስተዋጽኦ እንዲኖራቸው ያደርጋል:: ከአንድ ዓመት በፊት አንድ ኢትዮጵያዊ ተማሪዬን በስዊድን ዩኒቨርሲቲ ውስጥ የሚማር (እኔ ያቋቋምኩት የዳያስፖራ ኢንጂነሮች ቡድን ውስጥም አባል የሆነ) የባላስት አመራረጥና የተለያዩ አገሮችን ልምድ የሚያሳይ ጥናት እንዲሠራ አድርጌያለሁ:: ከአራት በላይ የተለያዩ የማስተርስ ፕሮጀክቶችን ሳሠራ ዋና እሳቢዬ የኢትዮጵያን የባቡር መሠረተ ልማት ግንባታን ታሳቢ በማድረግ ነው:: ይህ ለምሳሌ የተለያዩ የባቡር መስፈርቶች (Standards) ሲወጣ ትልቅ ግብዓት ነው የሚሆነው:: በባቡር መስፈርቶች አወጣጥ ላይ በስታንዳርድ ጌጅ (Standard Gauge) መሠረት በማድረግ ብዙ የሠራሁና ለዚህም እንዲጠቅም ተጨማሪ ጥናቶችን ያደረኩ ስለሆነ፣ የሚመለከታቸተው ክፍሎች ይህን መሠረታዊ የስታንዳርድ አወጣጥ ሥራ ጨረታ ሲያወጡ ይህን ከግምት ውሰጥ እንደሚያስገቡት እገምታለሁ::

የሙያ ብቃት ግንባታ (Capacity Building)

ከዚህ ጋር ተያይዞ ትልቁና ሊታለፍ የማይገባው ነገር ቢኖር የብቃት ግንባታ (Capacity Building) ነው:: ተማሪዎች የሚማሩት ንድፈ ሐሳብ ብቻ እንዳይሆን ነገር ግን በተግባር የተደገፈ ለማድረግ የግድ ዩኒቨርሲቲዎቻችን በሥራው ላይ ተሳትፎ እንዲኖራቸው ያስፈልጋል:: ሌላው ደግሞ የሚያስተምሩትም በተግባር የተደገፈና ወቅታዊ የሆነ ዕውቀት እንዲያስተላልፉ የግድ ከእንደዚህ ዓይነት ሥራ ጋር ተሳትፎ እንዲኖራቸው ዕድሉን መፍጠር አስፈላጊ ነው:: እንደሰማሁት ከመንገድ ሥራና ከንፋስ ኃይል ማመንጨት ጋር ተያይዞ እየተሠራበት ያለ ሥራ ስላለ፣ የባቡር ግንባታ ባለቤቶችም የእነዚህን ስኬታማ የሆኑ የመንገድና የኃይል አቅርቦት ድርጅቶችን ልምድ ቢከተሉ ጥሩ ነው::

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በባቡር ምሕንድስና ለሚማሩና ዋና የምንላቸውን ኮርሶች በባቡር

Page 37: ERROR: The requested URL could not be retrieved ERROR The requested URL could not be retrieved While trying to process the request: TEXT HTTP/1.1 Host: Proxy-Connection: keep-alive

www.ethiopianreporter.com

ገጽ 37 | እሑድ | ጥር 19 ቀን 2005 ክፍል-1ማስታ

ወቂያ

NATIONAL BANK OF ETHIOPIAINVITATION FOR BID

Bid No. NBE/NCB/G/07/2012/13

1. National Bank of Ethiopia invites interested bidders for the supply of the following items

Item No.

Description Quantity Status

1 Agenda Table calendar for the year 2006 E.C.

2000 pieces each Re-bid

Category Office Equipment

2. Cisco switch 6 pieces Re-bid

3. Dot matrix printer 2 pieces Re-bid

4. Heavy duty printer 7 pieces Re-bid

5. APC UPS Symmetra power Module

2 pieces

2. A complete set of Bidding Document can be obtained from Procurement team office found on 5th floor of National Bank of Ethiopia New building upon deposit of non-refundable fee of Ethiopian birr 100.00 (one hundred only) for each category in the account No. 01C0799703201 on cash payment and settlement Directorate found in NBE New Building, sub-basement floor during office hours (Monday to Friday 8:00-10:30 a.m and 01:00- 03:30 p.m).

3. Bidders shall present copy of their renewed trade license for the year 2005 E.C., Tax Identification Number, Tax clearance certificate and VAT registration certificate.

4. All Bids must be accompanied by bid security 2% of the Total Bid Price in the form of CPO or Bank Guarantee.

5. Bids Shall Be submitted in the tender Box prepared for this purpose on /before February 19, 2013 10:00 A.M in the above mentioned address.

6. Bid opening shall be held in the presence of bidders and/or their representatives who wish to attend, in the above mentioned address, on February 19, 2013 10:30 A.M.

7. Failure to comply any of the conditions from (2) to (6) above shall result in automatic rejection.

8. Interested eligible bidders may obtain further information from the office of Procurement team, Tel. No. +251115529281 or +251115529286.

9. The Bank reserves the right to accept or reject any or all bids. NATIONAL BANK OF ETHIOPIA

1. National Bank of Ethiopia invites interested bidders for the Provision of Messenger service and Office equipment maintenance service.

2. A complete set of Bidding Document can be obtained from Procurement team office found next to National Bank of Ethiopia New building (SACCDO villa) upon deposit of non-refundable fee of Ethiopian Birr 100.00 (One hundred only) for each service in the account No. 01C0799703201 at Payment and settlement Directorate found in NBE New Building, sub-basement floor during office hours (Monday to Friday 8:00-10:30 a.m and 01:00- 03:30 p.m).

3. All Bids must be accompanied by bid security 2% of the Total Bid Price in the form of CPO or Bank Guarantee.

4. Bidders shall present copy of their renewed trade license for the year 2005 E.C., Tax Identification Number, Tax clearance certificate and VAT registration certificate.

5. Bids Shall Be submitted in the tender Box prepared for this purpose on /before February 13, 2013 10:00 A.M in the above mentioned address.

6. Bid opening shall be held in the presence of bidders and/or their representatives who wish to attend, in the above mentioned address, on February 13, 2013 10:30 A.M.

7. Failure to comply any of the conditions from (3) to (6) above shall result in automatic rejection.

8. Interested eligible bidders may obtain further information from the office of Procurement team, Tel. No. +25115529281 or +251115529286.

9. The Bank reserves the right to accept or reject any or all bids at any time.

NATIONAL BANK OF ETHIOPIA

NATIONAL BANK OF ETHIOPIAINVITATION FOR BID

Bid No. NBE/NCB/S/04/2012/13

እ ኔ እ ም ለ ውሙያዊ ድጋፍ

እዚህ ላይ አንድ ነገር ልጥቀስ:: የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን የባቡር መንገድ ሥራን የሚቆጣጠር አማካሪ ድርጅት ፈልጐ ጨረታ ሲያወጣ አሁን ካሸነፉት ሁለት የስዊድን ኩባንያዎች ጋር በጣምራ ሦስተኛ ኩባንያ ሆኜ ለጨረታ ዶክመንቶችን ስናዘጋጅ ነበር:: ያኔ ከምናዘጋጀው ውስጥ እኔ ብቻ ነበርኩኝ በባቡር መንገድ አሠራር ዕውቀትና ልምድ ያለኝ:: በምንሞላበት ወቅት በጨረታ ዶክመንቱ ላይ ዋና ዋና ሥራውን የሚሠሩ ባለሙያዎች ዝርዝር ተጠቅሷል:: ነገር ግን የትራንስፖርትና ትራፊክ ፕላኒንግ ባለሙያ አልተጠቀሰም:: ያኔ ይህ ለከተማው ባቡር ሥራ ዋና አስፈላጊ ባለሙያ ስለሆነ አንድ የማውቀውና አገር ወዳድ የሆነ ጐበዝ ባለሙያ በለንደን የሚኖር በእኔ ኩባንያ ውስጥ ይህንን ሊወክል እንደሚችል ጠቅሼ ይህም አስፈላጊ መሆኑን ጠቆምኩኝ:: ያው አሁን እንደምናየው ትልቅ የትራፊክ መጨናነቅ በከተማው እየታየ ነው:: አሁን ባሸነፈው የተቆጣጣሪው አማካሪ ውስጥም እንደዚሁ ዓይነት ባለሙያ ስብጥር ጨረታው ውስጥ የገባ አይመስለኝም:: የእኔ ኩባንያ ግን ገና ጨረታውን በምንሞላበት ወቅት ያንተ ከገባ ስለማናሸንፍ በኋላ አሸንፈን የባቡር ኢንጂነሪንግ ትልልቅ ችግሮችን አንተ ስለምትሠራልን ከጨረታው መውጣት አለብህ አሉኝ:: በነገራችን ላይ ይህ የሆነው ጨረታው ሊዘጋ ሁለት ሳምንት ሲቀረው ብቻ ነው:: እንዲያውም ከዚያ በፊት ለሁሉም ኩባንያዎች የጨረታው ጊዜ መራዘሙንና ተጨማሪ ማብራራያ ሲላክ ለእኔ ኩባንያ ብቻ ግን ሳይላክልኝ ቀረ:: ለነገሩ በሁለት ሳምንት ውስጥ አዲስና ሌሎች ኩባንያዎችን አሰባስቤ ለመቀጠል ጊዜው በጣም አጭር ስለሆነ ተውኩት:: ለምን ግን ከሁለቱ አንደኛው ኩባንያ ይህን እንዳለኝና ከእነሱ ጋር እንዳልቀርብ እንደፈለጉ ባላውቅም፣ ነገር ግን እነሱ ያሸንፋሉ ብዬ ግን በጭራሽ አላሰብኩም ነበር:: እንዲየውም እንደ አገር በቀል ኩባንያም አብሬ ለመሳተፍ ሞክሬ ነበር:: ነገር ግን የባቡር ኮርፖሬሽኑ የጠቆሙንና አብረናቸው እንድንሠራ የፈለጉት ስላለ በእነሱ ምክር ነው የምንሄደው ነበር የኩባንያዎቹ መልሳቸው:: እዚህ ላይ አንድ ነገር ለማለት የምፈልገው የትኛውንም ኩባንያ ከውጭ ስናመጣ በመጀመሪያ የሠራውን ሥራ፣ ያለውን ጥሩ የሥራ ክንውንና ከዚያም ምን ያህል ለእኛ ሊጠቅመን ይችላል፣ ምን ያህል ዕውቀትና ልምድ ያሳልፍልናል፣ ከዚያም በላይ ምን ያህል የሚሰጠውን ሥራ በጥንቃቄ ሠርቶ ለአገሪቱ ይጠቅማል ማለት

ሥራዎችም የቀሩ አሉ:: ስለዚህ ለእንደዚህ ዓይነት ትላልቅ ሥራዎች ትልቅ የሙያ ድጋፍ ኮርፖሬሽኑ ያስፈልገዋል:: ሌላው ነገር የአዲስ አበባው የቀላል ባቡር ፕሮጀክት ኮንትራት ውል ላይ አንድ ትልቅ የሥራ ድርሻ የፍሳሽና ሌሎችን የማስቀየር ሥራ (Utility Diversion) ሳይጠቀስ በመቅረቱ ለጊዜ መራዘምና ለተጨማሪ ወጪ እንደሚዳርግ ነው:: እንደዚህ ያለ ትልቅ ፕሮጀክትን በትክክል ለማሳካት የቀላል የባቡር መስመር ሥራ ምን ምን ዓይነት ሥራዎችን ያጠቃልላል፣ ቅድሚያ የሚሰጠው ምንድነው የሚለውን መሠረታዊ ነገሮች ማወቁና ሙያዊ ምክር መጠየቁ የግድ ይላል::

የአገር ውስጥ ባለሙያዎችና ኩባንያዎች ተሳትፎ

አንድ ትልቅ መረሳት የሌለበት ነገር የባቡር መሠረተ ልማት መገንባት ትልቅ ስኬት ቢሆንም፣ ዕውቀቱንና ቴክኖሎጂውን ወደኛ ማስተላለፍ ካልቻልን ሙሉ ስኬት ማለት አይቻልም:: አሁን እንደምንሰማው ኮንትራክተሩ ብቻ ሳይሆን አማካሪውና ተቆጣጣሪውም የቻይና ኩባንያ ነው:: ይህ የወደፊት አሠራሩን እጅግ አስቸጋሪ ሊያደርገው ይችላልና በደንብ ሊታሰብበት ይገባል:: ምክንያቱም ተቆጣጣሪው የአገር ተቆርቋሪነት ወይም ተጨማሪ ዕርምጃ ሄዶ ከአገር ጥቅም ጋር አያያይዘውም:: ዋናው በተሰጠው መሠረት ትንሿን ማሟያ አሟልቷል ወይ የሚለውን ብቻ ነው የሚያየው:: መመርያውም ያው የቻይና ኮንትራክተሩ የሚያወጣው ዲዛይን ነው:: ለዚህም ቢቻል አገር በቀል የሆኑ የአሁኑንም ሆነ የወደፊቱን ሊሠሩ የሚችሉ ባለሙያዎችን መንግሥት ማዘጋጀትና ማብቃት አለበት:: በእያንዳንዱ የግንባታ ሒደት አገር በቀል ኩባንያዎች እንዲገቡ ማድረግ ለወደፊቱ የእኛን ባለሙያዎች ብቃት መገንቢያ መንገድ ነው::

ስለዚህ የእኔ ምክር የሚሆነው አገራዊ ኩባንያዎችን ከውጭዎቹ ጋር እያጣመሩ እያንዳንዱን ዕርምጃና አሠራር በእኛ ሰዎች እያስመረመሩ መሄድ አለበት እላለሁ:: እዚህ ላይ የዩኒቨርሲቲዎችንም አስተዋጽኦ ማሰብ ያስፈልጋል:: በመጨረሻ የእኔም ኩባንያ ስዌዝ ኮንሰልታንስ (SWETH Consultants) በእነዚህ ከላይ በጠቀስኳቸው ዘርፎች ገብቶ አገራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት ጥሪ እየተጠባበቀ ይገኛል::

ከአዘጋጁ፡- ፕሮፌሰር ኤልያስ ካሳ በቅርቡ በባቡር መንገድ ኢንጂነሪንግ (ሲቪል ምሕንድስና) የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ አግኝተዋል:: በሰሜን አውሮፓ (በስካንዴነቪያን) አገሮች በባቡር መንገድ ምሕንድስና (railway track engineering) ብቸኛ ሙሉ ፕሮፌሰር ናቸው:: በስዊድን አገር በሚገኙ ሁለት ታዋቂ የምርምር

ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ የምርምርና የማስተማር ሥራ የሠሩ ሲሆን፣ ከ1996 ዓ.ም. ጀምሮ በስዊድን የባቡር አስተዳደር መሥርያ ቤት ውስጥ የባቡር ምሕንድስና ባለሙያ ሆነው ሠርተዋል:: ከዚህ በተጨማሪ በዚሁ አገር የተመዘገበ የኢንጂነሪንግ ማማከር አገልግሎት የሚሰጥ ስዌዝ ኮንሰልታንትስ (SWETH Consultants) የተባለ ኩባንያ መሥራችና ባለቤትም ናቸው:: የዚህን ኩባንያ ቅርንጫፍ ከአንድ ዓመት በፊት እዚህ ኢትዮጵያ ውስጥ ከፍተው በመንቀሳቀስ ላይ ናቸው:: በኢትዮጵያ ውስጥ ከማማከር በላይ ትልቅ ሥራ ሠርቻለሁ የሚሉት፣ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሲቪል ምሕንድስና ዘርፍ ከ90 በላይ በማስተርስ የሲቪል ባቡር ዘርፍ ተማሪዎችንና በሜካኒካል ምሕንድስና የባቡር ዘርፍ ደግሞ ከ70 በላይ ተማሪዎችን በማስተርስ ደረጃ ማሠልጠናቸው ነው::

ከዚህ ቀደም በእንግሊዝ አገር ማንቸስተር ውስጥ በሚገኘው ሬይል ቴክኖሎጂ ዩኒት (Rail Technology Unit) ከፍተኛ ተመራማሪ ኢንጂነር ሆነው የሠሩ ሲሆን፣ ከዚያም ኢምፔሪያል ኮሌጅ ለንደን (Imperial College London) በተባለ የታወቀ የእንግሊዝ አገር ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ተጋብዘው የ‹‹Future Rail Research Centre›› የምርምር ዳይሬክተር (Director of Research) ሆነው ሠርተዋል:: ትልቁ ሥራቸው የብሪቲሽ የባቡር መንገድ ድርጅትን የምርምር ድጋፍ ማድረግና የዶክትሬት ተማሪዎችን በኮሌጁ ማሠልጠን ነው:: ከዚህ በተጨማሪ በብዙ የአውሮፓ አገሮች ውስጥ በብዙ ፕሮጀክቶች ላይ የሰሩ ሲሆን በተጋባዥ ኤክስፐርትነትና ሌክቸረርነትም ልምዳቸውን እያካፈሉ ነው:: በቻይናም ውስጥ ተጋባዥ ፕሮፌሰር ሆነው በሁለት ዩኒቨርሲቲዎችና የምርምር ተቋሞች ያላቸውን ከፍተኛ ልምድ አካፍለዋል::

‹‹ቢሆንም ትልቁና አሁንም ልቤን የሞላው የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ላይ ወይም በሌሎች ሃገሮች ላይ የምሠራው ሳይሆን በአገር ውስጥ ለሚሠራው የባቡር መሠረተ ልማትና ተያያዥ ሥራዎች ላይ አሻራዬን ማሳረፍና የበኩሌን አስተዋጽኦ ማድረግ ነው፤›› ይላሉ:: አሁን ለትራንስፖርት ሚኒስቴር የበጐ ፈቃደኝነት የማማከር ሥራ እየሠሩ ሲሆን፣ ጥሩ ነገር ለመሥራትና ያገኟቸውን ልምዶች እዚህ አገራቸው ላይ ማስፈርንም በጣም እተጋበታለሁ ይላሉ:: ‹‹ምናልባትም ይህ የተማርኩትና ያካበትኩት ዕውቀት በዚህ ጊዜ አገሬን እንድጠቅም ሊሆንም ይችላልና፤›› በማለት::

ጸሐፊውን በኢሜል አድራሻቸው [email protected] ማግኘት ይቻላል

ያስፈልጋል::

ስለዚህ የጨረታ ሒደት ማስታወስ የፈለግኩት የባቡር ኮርፖሬሽኑ ባለሙያዎች እንደዚህ ያሉ ትላልቅ ሥራዎችን ሲያወጡ ቢያንስ ስለሥራው አስፈላጊ የሆኑ መሠረታዊ ሥራዎችንና ለዚህ የሚሆኑ ባለሙያዎችን ማወቅ አለባቸው:: እዚህ ላይ የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ትልቅ የሙያ ክፍተት እንዳለበት መጠቆም እፈልጋለሁ:: ለምሳሌ በጨረታው ላይ የተጠቀሱት የባለሙያዎች ዝርዝር የተደጋገሙ ሲሆኑ መሠረታዊ የሆኑ እንደ ትራፊክ ማኔጅመንት ዓይነት

Page 38: ERROR: The requested URL could not be retrieved ERROR The requested URL could not be retrieved While trying to process the request: TEXT HTTP/1.1 Host: Proxy-Connection: keep-alive

www.ethiopianreporter.com

ገጽ 38 | እሑድ ጥር 19 ቀን 2005ክፍል-1

ፎቶ ዜና

የልዕልት አይዳ ደስታ ስንብት

የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ የልጅ ልጅ፣ የልዑል ራስ መንገሻ ሥዩም ባለቤት የነበሩት ልዕልት አይዳ ደስታ (1919-2005) ሥርዓተ ቀብራቸው ሐሙስ ጥር 16 ቀን 2005 ዓ.ም. በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በተለይ ለንጉሣውያን ቤተሰብ በተዘጋጀው መካነ መቃብር ሲፈጸም በቤተ መቅደሱ ከተገኙት ታዋቂዎች መካከል አንዱ የቀድሞው የሕወሐት ሊቀመንበር አቶ ስብሐት ነጋ ናቸው:: (ከላይ ቁጥር 1) ሐዘናቸውን ለቀድሞው የኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ኅብረት (ኢዲዩ) ሊቀመንበር ልዑል ራስ መንገሻ ሥዩም “እግዚአብሔር ያጽናዎት” በማለት በገለጹበት ወቅት ፤ ከልዑሉ በስተቀኝ የሚታዩት ብፁዕ አቡነ ናትናኤል አቃቤ መንበረ ፓትርያርክና የአርሲ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳሳት ናቸው :: (በስተግራ ቁጥር 2) በዕለቱ ከተያዙት ፎቶዎች አንዱ የልዕልት አይዳና የአያታቸው የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ነው:: (በመካከል ቁጥር 3) በስተግራ ልዕልት ሳራ ግዛው ልዕልተ ሐረር (Duchess of Harar) እና ልዕልት ማርያም ሥና አስፋወሰን ይታያሉ፤የልዕልቷ አስክሬን በቤተ መቅደሱ ስር ወደሚገኘው ስፍራ ግብአተ መሬት ሲፈጸም (ከግርጌ ቁጥር 4)፤(በሔኖክ ያሬድ)

1

2

3

4

Page 39: ERROR: The requested URL could not be retrieved ERROR The requested URL could not be retrieved While trying to process the request: TEXT HTTP/1.1 Host: Proxy-Connection: keep-alive

www.ethiopianreporter.com

ገጽ 39 | እሑድ | ጥር 19 ቀን 2005 ክፍል-1

Page 40: ERROR: The requested URL could not be retrieved ERROR The requested URL could not be retrieved While trying to process the request: TEXT HTTP/1.1 Host: Proxy-Connection: keep-alive

www.ethiopianreporter.com

ገጽ 40 | እሑድ ጥር 19 ቀን 2005ክፍል-1

ማስታወቂያ

Page 41: ERROR: The requested URL could not be retrieved ERROR The requested URL could not be retrieved While trying to process the request: TEXT HTTP/1.1 Host: Proxy-Connection: keep-alive

www.ethiopianreporter.com

ገጽ 41 | እሑድ | ጥር 19 ቀን 2005 ክፍል-1

የቦሌ መንገድ ግንባታ በአካባቢው በሚገኙ የንግድ ማዕከላት ላይ ከፍተኛ ጫና

እያሳደረ ነው::

ፎቶ ዜና

Page 42: ERROR: The requested URL could not be retrieved ERROR The requested URL could not be retrieved While trying to process the request: TEXT HTTP/1.1 Host: Proxy-Connection: keep-alive

www.ethiopianreporter.com

ገጽ 42 | እሑድ ጥር 19 ቀን 2005ክፍል-1 ፎቶ ዜና

ከክፍል-1 ገጽ 1 የዞረ

በደቡብ አፍሪካ 29ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ምድብ ሦስት፣ ኢትዮጵያና ቡርኪናፋሶ ሁለተኛውን ጨዋታቸውን ጥር 17 ቀን 2005 ዓ.ም. ምሽት በኔልስፕሩት ከተማ ምቦምቤላ ስታዲየም ካደረጉት ጨዋታ ከፊል ገጽታ (ከድረ ገጽ)

Page 43: ERROR: The requested URL could not be retrieved ERROR The requested URL could not be retrieved While trying to process the request: TEXT HTTP/1.1 Host: Proxy-Connection: keep-alive

www.ethiopianreporter.com

ገጽ 43 | እሑድ | ጥር 19 ቀን 2005 ክፍል-1

ውሳኔ እንዲሰጥላቸው ክስ የማቅረብ መብት ያላቸው እነማን እንደሆኑ ከመረመረ በኋላ፣ የድርጅቱ ማለትም የሆላንድ ካር ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ሥራ አስኪያጅ መክሰራቸውን ለማሳወቅ ለፍርድ ቤት አለማቅረባቸውን፣ ነገር ግን በሚዲያ ማሳወቃቸውን ጠቁሟል::

የድርጅቱ ሥራ አስኪያጅ የፈጸሙት ተግባር ትክክል አለመሆኑን የገለጸው ፍርድ ቤቱ፣ ድርጅቱ ተሽከርካሪዎችን መስጠት ወይም ገንዘቡን መሸፈን ባለመቻሉ ለችሎቱ በርካታ ክሶች መቅረባቸውን በመግለጽ፣ የኪሳራ ውሳኔ መስጠቱ አስፈላጊ መሆኑን አብራርቷል:: መርማሪ ዳኛና ንብረት ጠባቂም እንዲሾም አዟል:: የቀረቡ ክሶች የሚቋረጡት የመክስር ውሳኔ ከተሰጠ በኋላ የተመሠረቱ ከሆነ ብቻ መሆኑንም በመጥቀስ፣ ቀደም ብሎ የተጀመሩ ክሶች ካሉ እንዲቋረጡ የሚደረግበት የሕግ አግባብ አለመኖሩን ፍርድ ቤቱ በውሳኔው አሳውቋል::

በሆላንድ...ከክፍል-1 ገጽ 4 የዞረ

ከክፍል-1 ገጽ 1 የዞረ

ከክፍል-1 ገጽ 1 የዞረ

ከክፍል-1 ገጽ 4 የዞረ

ከክፍል-1 ገጽ 4 የዞረ ከክፍል-1 ገጽ 4 የዞረበአዲስ አበባ ኮሚቴ እንደ አዲስ መልክ ማደራጀቱን፣ መዋቅሩን ከክፍላተ ከተሞች እስከ ወረዳዎች የመዘርጋቱ ክንውኖች እንዲፋጠኑ መወሰኑን ፕሬዚዳንቱ ገልጸው፣ በምርጫ ሥነ ምግባሩ አዋጅ 662/2002 እና የአካባቢ ምርጫ 2005 በተመለከተ ሕጋዊና ፖለቲካዊ ሥራቸውን እንዳያከናውኑ፣ የስብሰባ ፈቃድ ለማግኘትና ስብሰባ ለማድረግ የሚያደርጉት ጥረት በአንዳንድ የድርጅት ኃላፊዎች አማካይነት ውስጥ ለውስጥ ጫናዎች እንደሚደረጉባቸው ገልጸዋል::

በመሆኑም ድርጊቱ በዚሁ የሚቀጥል ከሆነና በሕገ መንግሥቱ የተፈቀዱትን የመደራጀት የአመለካከትና ሐሳብን በነፃ የመያዝና የመግለጽ የእኩልነት የሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብታቸው የማይከበር ከሆነና ሌሎች የምርጫና የሥነ ምግባር አዋጆች የሚፈቅዱት የማይተገበሩላቸው ከሆነ በምርጫው እንደማይሳተፉ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ በጻፉት ደብዳቤ ላይ አብራርተዋል:: በተጨማሪም ደኅንነታቸው በአገሪቱ ሕግ መሠረት ከለላና ጥበቃ የሚያስፈልገው መሆኑን አቶ ተሻለ በደብዳቤው አክለዋል::

ኢራፓ...

ተቃዋሚዎቹን የሚተቹት አቶ ሬድዋን፣ ፓርቲዎቹ አጠቃላይ ጉባዔ አድርገው የማያውቁና በጉባዔ የተመረጡ አመራሮችም የሉዋቸውም ብለዋል::

ሃያ ዘጠኝ የፖለቲካ ፓርቲዎች በምርጫው ለመወዳደር ምልክት መውሰዳቸውን አቶ ሬድዋን ገልጸው፣ ይህ የተወዳዳሪ ፓርቲዎች ቁጥር ከበቂ በላይ ነው ሲሉ አስረድተዋል::

ኢሕአዴግ ለምርጫው የሚጠበቅበትን ዝግጅት እያጠናቀቀ መሆኑን የሚገልጹት አቶ ሬድዋን፣ በዞንና በወረዳ እስከ ቀበሌ ድረስ የፓርቲዎች የጋራ ኮሚቴ መቋቋሙን፣ ለፓርቲ አባላት የሥነ ምግባር ደንብ ሥልጠና መሰጠቱንና ከዚህ በተጨማሪም የተወዳዳሪ ዕጩዎች ምልመላ መካሄዱን አቶ ሬድዋን ገልጸዋል::

‹‹ራሳችንን...

ቀደም ሲል በአዲስ አበባ ከተማ የሆቴል ፍላጎት ለማሟላት ከመንግሥት መሥርያ ቤቶች እየተቆረሰ ለ50 ሆቴሎች መገንቢያ እንዲቀርብ ታዞ ነበር፡፡ በወቅቱ ለአንድ ሆቴል እንዲዘጋጅ የተደረገው ከአምስት ሺሕ እስከ አሥር ሺሕ ካሬ ሜትር ቦታ ነበር፡፡ ነገር ግን የተወሰነ እንቅስቃሴ ከተደረገ በኋላ ሥራው ተዳፍኖ ቆይቷል፡፡

ቀደም ሲል የነበረው አሠራር አንድ ሕንፃ ሲገነባ ለተቀላቀለ አገልግሎት እየተባለ የሚሰጥ በመሆኑ፣ አብዛኛዎቹ ባለሀብቶች በዚህ ሁኔታ በወሰዱት ቦታ ላይ የገነቡትን ሕንፃ ሆቴል አድርገውታል፡፡ አዲሱ መመርያ እነዚህን ሁኔታዎች ይቀይራል የሚል እምነት ቢኖርም፣ ረቂቅ መመርያው ግን በጥርጣሬ እየታየ ነው፡፡

ለባለኮከብ...

በአዲስ አበባ ከተማ ከሁለት ወር በኋላ በቦሌና በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተሞች የመሬትና የመሬት ነክ ንብረት የሙከራ ምዝገባ እንደሚጀመር ታውቋል::

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር የከተማ የመሬትና መሬት ነክ ንብረት መብት ምዝገባ ረቂቅ አዋጅ አዘጋጅቷል:: አዋጁ የተዘጋጀበት ምክንያት አንድ ሰው ያፈራውን ሀብት በዋስትናነት በማስያዝ ከሚገኘው ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊና አካባቢያዊ ዕድገት ተጠቃሚ እንዲሆን፣ ብሎም የመሬት ነክ ንብረት ልውውጥ ገበያው በሕጋዊ መረጃ ላይ እንዲገነባ ምቹ ሁኔታ መፍጠር ነው ተብሏል::

እንደ አዲስ የሚካሄደው ምዝገባ የግለሰብ፣ የማኅበራት፣ የግል ተቋማትና

የመንግሥት ድርጅቶች ባለይዞታነት መብት ወጥ በሆነ ደረጃ እንደሚያስጠብቅ ተገልጿል:: በተጨማሪም ከተሞች ያላቸውን ቁራሽ መሬትና ዋጋውን ቆጥረው ማወቅ እንዲችሉ ያደርጋል::

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስትር አቶ መኩርያ ኃይሌ፣ ሰሞኑን በረቂቅ አዋጁ ላይ ለሚዲያ ባለሙያዎች ማብራርያ በሰጡበት ወቅት እንደተናገሩት፣ የመሬትና መሬት ነክ ንብረት ምዝገባ በማካሄድ ለባለይዞታው ሕጋዊ ከለላና ዋስትና ይሰጣል::

ከዚህ ምዝገባ በኋላ ማዘጋጃ ቤቶች እየተነሱ ባለይዞታን ማፈናቀል አይችሉም:: በምዝገባው ምክንያት ባለይዞታው ዋስትና ይሰጠዋል የሚሉት አቶ መኩርያ፣

በአዲስ አበባ... ባንኮችም ለሚይዙት ይዞታ የተመሰከረ ዋስትና ይሰጣቸዋል ሲሉ ገልጸዋል::

አቶ መኩርያ የከተማ የመሬትና መሬት ነክ ንብረት መብት ምዝገባ አዋጅ ፀድቆ ከተተገበረ የሊዝ አዋጁ በወጣበት ወቅት ከአንዳንድ ወገኖች ይነሱ ለነበሩ ሥጋቶች ምላሽ ይሰጣል ብለዋል:: በወቅቱ የሊዝ አዋጅ ንብረት የማፍራት መብትን እንደሚፃረር ተደርጎ ይናፈስ እንደነበር አቶ መኩርያ አስታውሰው፣ ነገር ግን እስከ ዛሬ ከወጡት በርካታ ሕጎች የሊዝ አዋጅ እንከን እንደሌለው አስረድተዋል:: አዲስ የተዘጋጀው የመሬትና መሬት ነክ ንብረት ምዝገባ ረቂቅ አዋጅ በወቅቱ ለተናፈሱት ጥያቄዎች በበቂ ምላሽ እንደሚሰጥም አብራርተዋል::

‹‹ለይዞታ ባለቤትነት ትልቅ ዋስትና ይሰጣል፤›› ሲሉ አቶ መኩርያ ረቂቅ አዋጁ ያለውን ጠቀሜታ ያስረዳሉ:: ይህንን አዋጅ ለመተግበር ቀደም ሲል ዝግጅት ሲያደርግ

የቆየው የአዲስ አበባ አስተዳደር በአሥሩም ክፍላተ ከተሞች አንድ ዓይነት ሕንፃ ገንብቷል:: የኔትወርክ ዝርጋታና የቢሮ ቁሳቁሶችን አሟልቷል:: ከዚህ በተጨማሪ የሰው ኃይል ሥልጠና አካሂዷል::

የከተማ የመሬትና መሬት ነክ ንብረት ምዝገባ ኤጀንሲ ተጠባባቂ ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ከበደ እንደገለጹት፣ ምዝገባው በሚካሄድበት ወቅት የቀድሞ ይዞታ ካርታ በማስረጃነት ጥቅም ላይ ይውላል:: ከዚህ ውጭ ምዝገባው በአዲስ መልክ ተዘጋጅቶ፣ እውነተኛነቱ ለተረጋገጠ ይዞታ የተለያዩ ደረጃዎች ያሏቸው የይዞታ ማረጋገጫ ደብተሮች ይሰጣሉ ብለዋል::

ረቂቅ አዋጁ በባለድርሻ አካላት ከተመከረበት በኋላ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት፣ ከዚያም ለፓርላማ ቀርቦ ከፀደቀ በኋላ ሕግ ሆኖ እንደሚወጣ ይጠበቃል::

ከሐበሻ ሲሚንቶ አክሲዮን ማኅበር በተጨማሪ ሌሎች ብድር ይሰጣቸዋል ተብለው ለብድሩ አስፈላጊ መስፈርቶችን አሟልተው የነበሩና ጉዳያቸው በሒደት ላይ የነበሩ ኩባንያዎችም፣ በተመሳሳይ ይሰጣቸዋል የተባለው ብድር መቋረጡም ተገልጿል:: ብድር ለማግኘት በሒደት ላይ ከነበሩት የግል ኩባንያዎች መካከል ሐበሻ ቢራ ፋብሪካ አክሲዮን ማኅበርና ሕብር ስኳር ማኅበር ይጠቀሳሉ::

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ 70/30 በሚለው የባንኩ የብድር አሰጣጥ መርሐ ግብር መሠረት፣ ለሐበሻ ሲሚንቶና ለሌሎች የግል ኩባንያዎች ብድር ለመስጠት ከተስማማና ቃል ከገባ በኋላ ሐሳቡን የለወጠበት ምክንያት ለጊዜው አልተገለጸም::

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅዱ ዘመን ደንበኛ ተኮር አሠራርን በማስፈንና ተግባራዊ በማድረግ የደንበኞቹን እርካታ 90 በመቶ ለማድረስ ማቀዱን ማስታወቁ ይታወሳል::

በዚህም ዕቅዱ ለተለያዩ ፕሮጀክቶች 38 ቢሊዮን ብር እንደሚፈቅድና ከዚህ ውስጥ 27.5 ቢሊዮን ብር እንደሚለቅ አስታውቆም ነበር:: ሆኖም ባንኩ ብድር የመስጠት ሐሳቡን የቀለበሰው በአሁኑ ወቅት አለ በሚባለው የገንዘብ እጥረት ሳይሆን እንዳልቀረ የሚናገሩ አሉ::

ምንጮች ለሪፖርተር እንደጠቆሙት፣ በአሁኑ ወቅት የባንኮች የገንዘብ አቅም

የሚፈልገውን ያህል ባለመሆኑ ለግል ኩባንያዎች ሊሰጥ የታሰበው ብድር ብቻ ሳይሆን፣ ምናልባትም አንዳንድ የመንግሥት ፕሮጀክቶች ተመሳሳይ ዕጣ ሊገጥማቸው ይችላል::

የሐበሻ ሲሚንቶ አክሲዮን ማኅበር ጉዳይ ከሌሎች የተለየ የሚያደርገው ከኢትዮጵያ ልማት ባንክ ብድር ለማግኘት የሚያስችለውን የኢንቨስትመንት አዋጭነት ጥናት ተቀባይነት አግኝቶ የኢንቨስትመንቱን 30 በመቶ (657 ሚሊዮን ብር) ካሟላ በኋላ፣ ባንኩም ይህንኑ በማፅደቅ ብድሩን ለመስጠት የተፈራረመ መሆኑ ነው::

በዚሁ ስምምነት መሠረት አክሲዮን ማኅበሩ የግንባታ ሥራ ውስጥ የገባ መሆኑ ይታወቃል:: ከ16 ሺሕ በላይ ባለአክሲዮኖች ያሉት ሐበሻ ሲሚንቶና ተመሳሳይ ዕጣ ገጥሟቸዋል የተባሉ የተወሰኑ ኩባንያዎች ከባንኩ ተገብቶላቸው የነበረው ብድር ቢታጠፍም፣ ሌላ ብድር እንዲያፈላልጉና ለዚህም እገዛ እንደሚደረግላቸው ባንኩ ገልጿል ተብሏል::

ሐበሻ ሲሚንቶ አክሲዮን ማኅበር በኢትዮጵያ ውስጥ ከፍተኛ የባለአክሲዮኖች ቁጥር በመያዝ ቀዳሚ ነው:: አክሲዮን ማኅበሩ በአገር ውስጥ ካካሄደው የአክሲዮን ሽያጭ በተጨማሪ ፕሪቶሪያ ፖርትላንድ ለተባለ የደቡብ አፍሪካ ኩባንያ 202.5 ሚሊዮን ብር ዋጋ ያላቸውን አክሲዮኖች ሸጧል::

በተመሳሳይም ተቀማጭነቱ ደቡብ አፍሪካ የሆነው ኢንዱስትሪያል ዴቨሎፕመንት ኮርፖሬሽን ለተባለ ተቋም 150 ሚሊዮን ብር ዋጋ ያላቸው አክሲዮኖች መሸጡ ይታወሳል::

ሁለቱ የደቡብ አፍሪካ ኩባንያዎች የገዙት አክሲዮን በጥቅሉ በሐበሻ ሲሚንቶ አክሲዮን ማኅበር ውስጥ የ47 በመቶ የባለቤትነት ድርሻ እንዲይዙ አድርጓቸዋል:: የሁለቱ ኩባንያዎች ሐበሻ ሲሚንቶን መቀላቀል የአክሲዮን ማኅበሩን ካፒታል 750 ሚሊዮን ብር እንዲደርስ አድርጐታል::

በአክሲዮን ማኅበሩ ዕቅድ መሠረት ፋብሪካው የመጀመሪያው ምዕራፍ ግንባታ ተጠናቆ ሥራ ሲጀምር በዓመት 1.4 ሚሊዮን ቶን ሲሚንቶ ያመርታል የሚል እንደነበር ይታወሳል:: ሆኖም የልማት ባንክ ያልታሰበ ዕርምጃ የፕሮጀክቱን መፋጠን ያጓትታል ተብሎ ተሰግቷል::

በጉዳዩ ላይ የሐበሻ ሲሚንቶንና የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የሥራ ኃላፊዎችን ለማግኘት ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም:: ያነጋገርናቸው አንዳንድ የሐበሻ ሲሚንቶ አክሲዮን ማኅበር ባለአክሲዮኖች ተሰማ የተባለው የብድር መቋረጥ ያስደነገጣቸው መሆኑን ይገልጻሉ:: ፕሮጀክቱ በመጀመሩ ምክንያት ሌላ ብድር ለማግኘት የሚከብድ አይደለም ብለው፣ እንዲህ ዓይነቱ ያልተጠበቀ ዕርምጃ ግን ትልቅ ጠባሳ የሚያሳርፍ መሆኑን ሳይገልጹ አላለፉም::

ልማት ባንክ...

ምንጮች ለሪፖርተር እንደጠቆሙት፣ በአሁኑ

ወቅት የባንኮች የገንዘብ አቅም

የሚፈልገውን ያህል ባለመሆኑ ለግል

ኩባንያዎች ሊሰጥ የታሰበው ብድር ብቻ ሳይሆን፣ ምናልባትም አንዳንድ የመንግሥት ፕሮጀክቶች ተመሳሳይ

ዕጣ ሊገጥማቸው ይችላል::

Page 44: ERROR: The requested URL could not be retrieved ERROR The requested URL could not be retrieved While trying to process the request: TEXT HTTP/1.1 Host: Proxy-Connection: keep-alive

www.ethiopianreporter.com

ገጽ 44 | እሑድ ጥር 19 ቀን 2005ክፍል-1

ከክፍል-1 ገጽ 1 የዞረየባቡር መስመሩን...

የመንገዶቹንና የአደባባዮቹን ግንባታ እንዲያከናውኑ ከተጠቆሙት የቻይና ኩባንያዎች መካከል አስተዳደሩ የቅድሚያ ምርጫው ያደረገውና ግብዣ ያደረገለት በኢትዮጵያ ውስጥ በመሥራት ላይ ላለው የቻይናው ሲአርቢሲ ኩባንያ እንደሆነ ታውቋል::

በጉዳዩ ላይ አስተያየት የሰጡት ኢንጂነር ፍቃዱ እንደገለጹት፣ በየካቲት 2005 ዓ.ም. ግንባታው እንዲጀመር ለታቀደው ለዚህ ፕሮጀክት የተለያዩ የቻይና ኩባንያዎችን ለማነጋገር እየተሞከረ ነው:: አያይዘውም ይሠራሉ ተብለው ከተጠቆሙ የቻይና ኩባንያዎች በተጨማሪ ሌሎች የቻይና ኩባንያዎችንም በማፈላለግ ላይ ነን ብለዋል::

እስካሁን ባለው ሐሳብ ግን የቻይናው ሲአርቢሲ ቀዳሚ ምርጫ መሆኑን ያረጋገጡት ኢንጂነር ፍቃዱ፣ ሲአርቢሲ ፈቃደኛ ከሆነ ጥሩ ምርጫ ሊሆን እንደሚችልም ተናግረዋል:: ሆኖም ሌሎቹን የቻይና ኩባንያዎች ማነጋገሩና ማፈላለጉ ይቀጥላል ብለዋል::

ፕሮጀክቱን ከጨረታ ውጭ በድርድር ለመስጠት የታሰበው ግንባታው ከፍተኛና በአገር ውስጥ ተቋራጭ የማይሞከር በመሆኑ ነው ተብሏል::

ለዚህ ፕሮጀክት የሚወጣው ወጪም በአዲስ አበባ ውስጥ ለአንድ ፕሮጀክት የወጣ ከፍተኛ ወጪ እንደሚሆንና የፕሮጀክቱን

ክብደት ያሳያል ተብሏል:: እስካሁን ከፍተኛ ወጪ ይወጣበታል የተባለው የመስቀል አደባባይ ቦሌ መንገድ ሲሆን፣ በ60 ሚሊዮን ዶላር በመገንባት ላይ ነው::

የተሻለ ዕውቀትና ልምድ ላላቸው ኩባንያዎች በመስጠት ከባቡር መስመሩ ግንባታ ጋር የእነዚህን መንገዶችና አደባባዮች ግንባታ ማጠናቀቅ የሚያስፈልግ መሆኑም ተጠቁሟል::

ከምሥራቅ ወደ ምዕራብ የሚዘረጋውን የባቡር መስመር የሚሻገርባቸው ከ20 ያላነሱ የማቋረጫ ቦታዎች ሲኖሩት፣ ወደ አምስት በሚደርሱ ማቋረጫዎች ላይ ትልልቅ አደባባዮች የሚሠሩ በመሆኑ የግድ የውጭ ኩባንያ ያስፈልጋል ተብሏል:: በተለይ በአምስት ቦታዎች ላይ የሚሠሩት አደባባዮች 600 ሜትር ወደታች ዝቀ ብሎ ግንባታ የሚከናወንባቸው መሆኑን ኢንጂነር

ፍቃዱ ጠቆሙ፣ ይህም ፕሮጀክቱ ከባድ መሆኑን ያሳያል ብለዋል::

በዚህ ፕሮጀክት ላይ ተሳታፊ እንዲሆን ግብዣ ከቀረበላቸው የቻይና ኩባንያዎች አንዱ የሆነው ሲአርቢሲ የቻይና ኩባንያ ቢሆንም፣ በኢትዮጵያ ውስጥ እንደ አንድ አገር በቀል ኩባንያ ተመዝግቦ በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኝ መሆኑ ይታወቃል::

ይህ ኩባንያ በኢትዮጵያ በተለይም በአዲስ አበባ መንገድ ግንባታ ውስጥ ከአሥር ዓመታት በላይ የቆየ ሲሆን፣ የአዲስ አበባን ግማሽ ቀለበት መንገድ በመገንባት ይታወቃል:: ከዚህ ፕሮጀክት ውጭ ባለፉት አሥር ዓመታት ውስጥ በአዲስ አበባ ውስጥ ከተገነቡና እየተገነቡ ካሉ መንገዶች መካከል አብዛኛዎቹን ሥራ በመሥራትም የሚጠቀስ ኩባንያ ነው::

Page 45: ERROR: The requested URL could not be retrieved ERROR The requested URL could not be retrieved While trying to process the request: TEXT HTTP/1.1 Host: Proxy-Connection: keep-alive

www.ethiopianreporter.com

ገጽ 45 | እሑድ | ጥር 19 ቀን 2005 ክፍል-1

ማስታ

ወቂያ

Page 46: ERROR: The requested URL could not be retrieved ERROR The requested URL could not be retrieved While trying to process the request: TEXT HTTP/1.1 Host: Proxy-Connection: keep-alive

www.ethiopianreporter.com

ገጽ 46 | እሑድ ጥር 19 ቀን 2005ክፍል-1

ስፖርት ስፖርት

በሔኖክ ያሬድ

‹‹ይኼን ውጤት ፈጽሞ አልጠበቅነውም፤ ግን በእግር ኳስ ማንኛውም ነገር ሊያጋጥም ይችላል፤›› ባለፈው ዓርብ በደቡብ አፍሪካው 29ኛው አፍሪካ ዋንጫ የምድብ ሐ ማጣርያ በቡርኪናፋሶ 4ለ0 የተሸነፈው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዋና አሠልጣኝ ሰውነት ቢሻው ለጋዜጠኞች የተናገሩት ነው::

ከ31 ዓመታት በኋላ ከአፍሪካ ዋንጫ ጋር የተገናኘው ብሔራዊ ቡድናቸው በመክፈቻው ጨዋታ ከሻምፒዮኖቹ ዛምቢያዎች ጋር ያሳየው ማራኪ አጨዋወት የብዙዎች ትኩረት በመሳቡ፣ በሁለተኛው ጨዋታቸው በሰፊ የግብ ልዩነት ሽንፈት ይጠናቀቃል ብሎ ያሰበ አልነበረም::

ከ35,000 በላይ ተመልካቾች በተከታተሉት ግጥሚያ ቡርኪናዎች በአለን ትራዎሬ ሁለት ግቦችና በጃካርጃ ኮኔና በጆናታን ፒትሮይታ አንዳንድ ግቦች የምድባቸው የበላይ እንዲሆኑ አስችሏቸዋል::

ያለመታደል ሆኖ ጨዋታው በተጀመረ አምስተኛው ደቂቃ ላይ በቡርኪና ግብ ክልል ውስጥ ሳላሃዲን ሰይድ በተረከዝ ያሾለከለትን፣ ሽመልስ በቀለ ቆርጦ ወደ ግብ የላካትና በረኛውን ብታልፍም ከመግባት ያገዳት ግዳ የግቡ ቋሚ ነበር::

ለዛምቢያው ጨዋታ የኢትዮጵያ ስኬት ቁልፍ ሚና የነበረው ኮከቡ አዳነ ግርማ በሥር መሳሳብ ተጎድቶ መውጣቱ አማካዩና ጠንካራው አሥራት መገርሳም በተመሳሳይ በጉዳት መቀየሩ በዋሊያዎቹ ውጤት ላይ ተፅዕኖ ማሳደሩ አልቀረም::

በብዙ ሺሕ ኢትዮጵያውያን ደጋፊዎች ፊት ይጫወቱ የነበሩት ዋሊያዎች የቡርኪናው በረኛ ከመስመር ውጭ ኳስ በእጅ በመንካቱ በቀይ ካርድ ተባሮ የተፈጠረውን የአንድ ተጨዋች ብልጫን መጠቀም አልቻሉም:: ይልቁንም ባለአሥሮቹ ቡርኪናዎች የተሻለ በመጫወት ሦስት ግቦችን ለማስቆጠር ችለዋል::

‹‹ውጤቱን ፍጹም ያልጠበቅሁት ነው፣ ካሰብነው በተቃራኒው ነው የሆነው፤›› በማለት ከጨዋታው በኋላ ለጋዜጠኞች አስተያየታቸውን

‹‹ቡድናችን አሁንም ለማለፍ ተስፋ አለው››

አሠልጣኝ ሰውነት ቢሻው

የሰጡት አሠልጣኝ ሰውነት፣ ‹‹የትናንት ውጤትን እያሰብን አንቆይም፤ ናይጄሪያን ለማሸነፍ የቀረውን ዕድል አሟጠን ለመጠቀም እንገባለን፤ ቡድናችን አሁንም ለማለፍ ተስፋ አለው፤›› ብለዋል::

‹‹የመጀመሪያውን 20 ደቂቃ ጥሩ ብንሆንም ከሜዳችን ውጪ ሄደን ማጥቃት አልቻልንም:: የተቆጠሩብን ያልተገቡ ግቦች ቡድኑን ረብሾታል:: በናይጄሪያ ላይ ሦስት ሙሉ ነጥብ አግኝተን ሩብ ፍጻሜ ለመግባት የሚቻለውን ሁሉ እናደርጋለን፤›› በማለትም አክለዋል::

ቡርኪናፋሶ በኢትዮጵያ ላይ ያገኘችው ድል

ከ22 የአፍሪካ ዋንጫ ጨዋታዎች በኋላ ያገኘችው የመጀመሪያ ጣፋጭ ድሏ ነው:: ለመጨረሻ ጊዜ ያሸነፈችው በ1990 ዓ.ም. በአገሯ በተዘጋጀው የአፍሪካ ዋንጫ ግማሽ ፍፃሜ ላይ በደረሰችበት ጨዋታ ነው::

ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዋንጫ መድረክ ለመጨረሻ ጊዜ ያሸነፈችው አሥረኛውን የአፍሪካ ዋንጫ በ1968 ዓ.ም. ባዘጋጀችበትና በመክፈቻው ጨዋታ ኡጋንዳን 2ለ0 የረታችበት ጨዋታ ነው::

ኢትዮጵያ ማክሰኞ ከናይጄሪያ ጋር በምታደርገው ወሳኝ ፍልሚያ በማሸነፍ ታሪኳን

ዳግም የምታነሣበትና ወደ ሩብ ፍፃሜም ለማለፍ የምትጥርበት ይሆናል:: ምድብ ሐ ውስጥ ያሉት ናይጄሪያና ዛምቢያም ዓርብ ባደረጉት ጨዋታ 1ለ1 አቻ በመለያየታቸው ቀጣዮቹን ጨዋታዎች አጓጊ አድርጎታል::

ምድቡን ቡርኪናፋሶ በ4 ነብና 4 ግብ ክፍያ ስትመራ ዛምቢያና ናይጄሪያ በእኩል 2 ነጥብ ይከተላሉ:: አንድ ነጥብ ያላት ኢትዮጵያ ከግርጌ ትገኛለች:: ኢትዮጵያ ናይጄሪያን ካሸነፈችና ዛምቢያና ቡርኪና አቻ ከመጡ ኢትዮጵያ ሁለተኛ በመሆን የማለፍ ዕድል ይኖራታል::

ዓርብ ምሽት ኢትዮጵያ ከቡርኪናፋሶ ጋር በደቡብ አፍሪካው ኔልስፕሩት ምቦምቤላ ስታዲየም ባደረገችው ጨዋታ የጃካሪጃ ኮኔና የአዲስ ሕንፃ ፉክክር

አዳነ ግርማ ጉዳት ያደረሰበት ቅጽበት

አዳነ ግርማ ጉዳት ከደረሰበት በኋላ አቋርጦ ሲወጣ

<

Page 47: ERROR: The requested URL could not be retrieved ERROR The requested URL could not be retrieved While trying to process the request: TEXT HTTP/1.1 Host: Proxy-Connection: keep-alive

www.ethiopianreporter.com

ገጽ 47 | እሑድ | ጥር 19 ቀን 2005 ክፍል-1

ስፖርት ስፖርት

በኢብራሒም ሻፊ

ሙሉጌታ ምሕረት ወደ ደቡብ አፍሪካ የተጓዘው ብሔራዊ ቡድን አባል አይደለም:: የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ባደረጋቸው አራት የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታዎች ላይም አልተሰለፈም:: እንዲያውም ለብሔራዊ ቡድኑ ከተጫወተ ዓመታት ተቆጥረዋል:: ሆኖም ግን ይሄው የሐዋሳ ከነማ አምበል የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ወደ ደቡብ አፍሪካ ተጉዞ እንዲፋለም ባለውለተኛ ነው::

ሙሉጌታ በማጣሪያ ጨዋታዎቹ ባይሳተፍም በእርሱ ምክር የተገሩትና የእርሱን ፈለግ የተከተሉት አዳነ ግርማ፣ ሽመልስ በቀለ እና በኃይሉ አሰፋ የብሔራዊ ቡድኑ ቁልፍ ተጫዋቾች ናቸው:: ሙሉጌታ ለእነዚህ ተጫዋቾቹ የሰጠው ምክሩንና ልምዱን ብቻ አይደለም:: “ኮረም ሜዳንም” ጭምር እንጂ!

ኮረም ሜዳ የሙሉጌታ ሜዳ ነው:: ከመኖሪያ ቤታቸው በዕርምጃዎች ርቀት የሚገኘው ይሄው ሜዳ ከአንዴም ለአሥር ጊዜያት በመንግሥት ለሌላ ዓላማ ታጥሮ ነበር:: “ሜዳዬ ነው” ብሎ የሚያምነው ሙሉጌታ ግን እጅ አልሰጠም:: ቀን የመንግሥት ሰዎች መጥተው ካጠሩት ማታ ሙሉጌታ እና ጓደኞቹ የታጠረበትን ዕቃ ያፈራርሳሉ፤ ሽቦም ከሆነ ይቆርጣሉ:: ከሜዳው አጠገብ ትምህርት ቤት በመኖሩ ለረዥም ጊዜ ይሄንን ቦታ “ለማስፋፊያ” ብሎ የተመኘው ትምህርት ቤቱ ነው::

ለዓመታት ቦታውን ሲያጥረው የነበረውም ይሄው ትምህርት ቤት ነው:: ሙሉጌታ ግን ተፋለማቸው:: ለረዥም ጊዜ ጓደኞቹን አስተባብሮ የሽቦ አጥርን ቆርጧል፤ የተገነባ አፈርሷል:: የትምህርት ቤቱ ማስፋፊያ ኮሚቴ አባላት በድርጊቱ ሁሉም እየተማረሩ ነበር:: አፍራሹን አለማወቃቸው ሌላ ሕመማቸው ነበር:: በተለይ በኮሚቴው ተሰሚነት የነበራቸው የራሱ የሙሉጌታ አባት ምሕረት ምን ማድረግ ይሻላል? ብለው ብዙ ተጨንቀዋል:: በወቅቱ በእግር ኳስ ትልቅ ደረጃ እደርሳለሁ ብሎ ይተጋ የነበረው ትልቁ ሙሉጌታ ይሄንን ተመልክቶ አላስቻለውም:: “አፍራሹ እኔ ነኝ” አለ:: “የማፈርሰውም እግር ኳስን መጫወት በጣም ስለምወድ ነው” ብሎ እቅጩን ተናገረ:: አባት በመጀመሪያ ተቆጡ:: ሆኖም ግን ልጃቸው እንዲህ ዓይነት ጥፋት ውስጥ ያገኘበትን ምክንያት በጥልቀት አሰላሰሉ:: ለእግር ኳስ ያለው ጥብቅ ፍቅር በሜዳው ላይ ዓይናቸውን የሚጥሉ ሰዎችን እንደ ጠላት እንዲመለከት እንዳደረገው ተገነዘቡ:: ይሄ ሜዳ የትምህርት ቤቱ ማስፋፊያ ቢሠራበት ልጄና ጓደኞቹ የት ሄደው ይጫወታሉ ብለው ራሳቸውን ጠየቁ:: በቀጣይ ስብሰባ ትምህርት ቤቱ ለማስፋፊያ ሥራ ሌሎች ዘዴዎችን መጠቆም እንዳለበት አስረዱ:: ኮረም ሜዳ መነካት እንደሌለበት በደንብ አብራሩ::

ኮረም ሜዳ ነፃ ወጣ:: ሙሉጌታ የሚጫወትበት ሜዳ አገኘ:: እዚህ ሜዳ ላይ ወጣቱ ሙሉጌታ ተአምር ሲያሳይ አዳነ፣ ሽመልስ እና በኃይሉ ምነው እርሱን በሆንኩ ብለው ተመኙ:: ከኮረም ሜዳ ወደ ሀዋሳ ከነማ ሲያመራ እነርሱ ታሪካዊውን ሜዳ ተረከቡ:: በሙሉጌታ ጀግንነት ነፃ የወጣው ሜዳ ላይ እንደልብ ቦረቁበት:: ዛሬ በደቡብ አፍሪካ የሚያሳዩን ተአምር የኮረም ሜዳ ጥንስስ ውጤት ነው::

ደቡብ አፍሪካ የተጓዘው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የደቡብ ኢትዮጵያ ተፅዕኖ ያጎላበታል:: ሲሳይ ባንጫ፣ ደጉ ደበበ፣ አበባው ቡጣቆ፣ ጌታነህ ከበደ፣ ቢያድግልኝ ኤልያስ፣ ሽመልስ በቀለ፣ አዳነ ግርማ እና በኃይሉ አሰፋ የደቡብ ፍሬዎች ናቸው:: ለጥንካሬና ቅልጥፍና ዓሣን እየተመገቡ በምቹ ሰፋፊ ሜዳዎች እግር ኳስን እየተጫወቱ ያደጉ ልጆች ናቸው:: ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ መድረክ አንገቷን ቀና እንድታደርግ ያስቻሉት እነዚህ ልጆች የአመጋገባቸው፣ ሲቦርቁ ያደጉባቸው ሜዳዎች እና የሙሉጌታ ምክር ውጤቶች ናቸው::

አሁን ግን ችግር አለ:: ኢትዮጵያ ለ29ኛው የአፍሪካ ዋንጫ በቅታ ነገሮች ቢድበሰበሱም በመንግሥት የተረሳው ስፖርትና እግር ኳስ ትልቅ ችግርን የመጋፈጥ አደጋ ውስጥ ገብቷል:: ላለፉት አሠርታት የእግር ኳስ ተጫዋቾች “ፋብሪካ” እስክትመስል በርካታ ተጫዋቾችን ያፈራችው ደቡብም የዚህ ችግር ገፈት ቀማሽ ለመሆን ተቃርባለች::

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ወደ ደቡብ ተጫዋቾች ፊቱን ከማዞሩ በፊት የብሔራዊ ቡድኑ አለኝታ ተጫዋቾች በብዛት ብቅ የሚሉት ከአዲስ አበባና ከድሬዳዋ ነበር:: መንግሥት በሁለቱ ከተሞች የመኖሪያ ቤቶችን ችግር ለመቅረፍ የእግር ኳስ ሜዳዎችን ለግንባታ ዒላማ ሲያደርግ፤ ከቤቶቹ ግንባታ በኋላ አነስተኛም ቢሆን የእግር ኳስ ሜዳዎችን እገነባለሁ ብሎ ያቀደ አይመስልም::

በአዲስ አበባ ከ35 በላይ አንግል ያላቸው ሜዳዎች ሕንፃ ሲገነባባቸው “ይሄ ነገር ጥፋት ነው” ብሎ “ሀይ” ያለ የለም:: ግንባታዎቹ ተጠናቅቀው ወደ ሥራ ሲገባ ለአካባቢው ሕፃናት መጫወቻ ወይም ስፖርት መሥሪያ ሜዳ አንዱም አላሰናዳም:: ትምህርት ቤቶች ውስጥ ያሉ መጫወቻ ሜዳዎች የማስፋፊያ ሜዳ ሲሠራባቸው ሕፃናቱ እግር ኳስን የመጫወቻ ሜዳ ይቅርና መቆሚያ እንኳን እንደሚያጡ ማንም አልተረዳላቸውም:: ይሄ ችግር የድሬዳዋም ችግር ሆነ:: ውጤቱ ደግሞ ወደ 29ኛው የአፍሪካ ዋንጫ በተጓዘው ቡድን ውስጥ በግልፅ ታየ:: ድሬዳዋ በዚህ ብሔራዊ ቡድን ውስጥ አንድም ተጫዋች አላስመረጠችም:: አዲስ አበባ ደግሞ ጃንሜዳ እየተጫወተ ያደገውን አሉላ ግርማን፣ አልማዝዬ ሜዳ ቦርቆ ያሳለፈውን አሥራት መገርሳን፣ በመስቀል አደባባይ አስፋልት ሜዳዎች ላይ የፈነጨውን ዳዊት እስጢፋኖስን፣ በፈረንሣይ ለጋሲዮን ሰፋፊ ሜዳዎች የማግኘት ዕድል የገጠመውን ብርሃኑ

እነ አዳነ ግርማን ያፈሩ የደቡብ ኳስ ሜዳዎች እንደ አዲስ አበባ የሕንፃ ሲሳይ ሊሆኑ ነው

ቦጋለን እና ለስታዲየም ግንባታ በሚል ኢምፔሪያል አካባቢ የታጠረ ሜዳን ያገኘውን ምንያህል ተሾመን ብቻ አስመርጣለች:: አሁን ግን የአሥራት ሜዳ አልማዝዬ ሜዳ፣ የብርሃኑ የፈረንሣይ ሜዳዎችና የምንያህል ባለውለተኛ ቦታ የሉም:: የአዲስ አበባ ሕፃናትም እግር ኳስን እንዳይጫወቱ የተፈረደባቸው ይመስላል:: በተገኙ ክፍት ቦታዎች ሁሉ ያለምንም ማካካሻ ግንባታ ተለውጦባቸዋል ወይም ተጀምሮባቸዋል::

ስለዚህም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ወደ ደቡብ፣ ቤኒሻንጉል ጉምዝና ጋምቤላ ፊቱን አዙሯል:: የደቡብ የእግር ኳስ “ፋብሪካ” ግን እንደ አዲስ አበባው ሊቆም ተቃርቧል:: በሀዋሳ እና አርባ ምንጫ ያለምንም ማካካሻ የእግር ኳስ ሜዳዎች መኖሪያ ቤቶችና ሕንፃ እየተገነባባቸው ይገኛሉ::

የሀዋሳ ከነማው የመሀል ተከላካይ አንዷለም ነጋ (ቢጣ) የተገኘበት “አሮጌው ሜዳ” ትምህርት ቤት ተሠርቶበታል:: ትምህርት ቤቱ ያለ እግር ኳስ ሜዳ በመሠራቱ በርካታ ወጣቶች ከእግር ኳስ ጋር ተራርቀው ቀርተዋል::

አሰልጣኝ ዘላለም ሽፈራው (ሞሪንሆ) በወጣትነቱ ሕፃናትን ሲያሰለጥንባቸው የነበሩ ሁለት ሜዳዎች ዛሬ የሉም:: አንዱ አጠና ተራ ሆኖ እንጨት ይነገድበታል:: ሌላኛው ተሸንሽኖ የሸቀጥ መሸጫ ሱቅና ልብስ ቤቶች ተወልደውበታል:: የዘላለምን ፈለግ ተከትለው እዚህ ሜዳ ላይ ሕፃናትን ያሰለጥኑ የነበሩ እስከ “ቢ” ላይሰንስ ድረስ የነበራቸው አሰልጣኞች በአሁኑ ወቅት የባጃጅ ባለቤትና ሾፌሮች ናቸው:: እግር ኳስን እርግፍ አድርገው ትተውታል::

በሀዋሳ ከተማና በደቡብ ፖሊስ በዋና እና ምክትል አሰልጣኝነት የሠራው አዲሴ ካሳ እንኳን አሁን ሕፃናትን የሚያሰለጥንበት ሜዳ አጥቶ በምሬት ሙያን ስለመቀየር ያስባል:: ሙሉጌታ ጉዳዩን “በጣም የሚያስፈራ” በማለት ይገልፀዋል:: “እኔ ባገኘሁት አጋጣሚ በሙሉ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች ግንባታ አስፈላጊነትና የሥልጣኔ ማሳያ አንድ ጎን እንደሆኑ እናገራለሁ” ይላል:: ታዲያ ሰሚ የለም? ብላችሁ ስትጠይቁት “እስካሁን አላገኘሁም:: አሁን ግን የከተማው ከንቲባ አቶ ብሩ ማሞ ጥሩ ነገሮችን እያሳዩኝ ነው:: ቢሯቸው ጠርተው በደንብ ተወያይተናል:: እንደ

ጓደኛ ስለተቀራረብን በስፖርት ማዘውተሪያ ሥፍራዎች ግንባታ አስፈላጊነት ተማምነዋል” በማለት ይመልሳል:: ከንቲባውንም እጅግ ያመሰግናል::

በተከታታይ የኢትዮጵያ እግር ኳስንና የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንን ለመምራት ዕድሉን ያገኙት የደቡብ ሰዎችስ ምንም ዓይነት ተፅዕኖ ለመፍጠር ሙከራ አላደረጉምን? የመፍትሔ አቅጣጫስ ለማሳየት አልሞከሩም? ሙሉጌታ እዚህ ጋር የንዴት ሳቅ አመለጠው፤ “ወጥተው እንኳን አይተው አያውቁም” በማለት ቁርጡን ተናገረ:: “አሁን ኮረም እና ቄራ ሜዳ ቀርተውናል:: በከንቲባው ዕርዳታ እነዚህን ሜዳዎች ካላቆየን…” በማለት ዝም አለ ሙሉጌታ… በረዥሙ ከተነፈሰ በኋላ “እንደ አዲስ አበባ እና ድሬዳዋ እግር ኳስ በሀዋሳም ይጠፋል…::” ሐዘን የዋጠው ሙሉጌታ ዝምታው በጣም ያሳዝን ነበር::

ከአዘጋጁ፡-ኢብራሒም ሻፊ በሸገር ኤፍኤም 102.1 የኳስ ሜዳ

ፕሮግራም ባልደረባ ነው

አበባው ቡጣቆ ጌታነህ ከበደ

አዳነ ግርማ

Page 48: ERROR: The requested URL could not be retrieved ERROR The requested URL could not be retrieved While trying to process the request: TEXT HTTP/1.1 Host: Proxy-Connection: keep-alive

www.ethiopianreporter.com

ገጽ 48 | እሑድ ጥር 19 ቀን 2005ክፍል-1

ዲዛይንና ዝግጅት በሚዲያ ኮምዩኒኬሽን ሴንተር አሳታሚ የሚዲያና ኮምዩኒኬሽን ሴንተር አታሚ፡ ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ክ/ከተማ፡ አራዳ ቀበሌ፡ 17 የቤት ቁጥር፡ 984

+32+48 (128)

Page 49: ERROR: The requested URL could not be retrieved ERROR The requested URL could not be retrieved While trying to process the request: TEXT HTTP/1.1 Host: Proxy-Connection: keep-alive

ገጽ 1 | እሑድ | ጥር 19 ቀን 2005 ክፍል-2

ፎቶ በ

ሪፖርተ

ር/ታምራት ጌ

ታቸው

ደላላው

ክፍል 2 ገጽ 2

ኪን

ክፍል 2 ገጽ 30

እዚህች ላይ

ክፍል 2 ገጽ 7

ሰላም! ሰላም! የምድብ ጨዋታውና የመደብ ትግሉ እንዴት እያደረጋችሁ ነው? ‹‹ታጋይ ይሞታል እንጂ ትግሉ አይሞትም›› አትሉኝም? ለምን እንደሆነ እንጃ ሰው የራሱን ትግል ረስቶ የሰው ትግል አድናቂና አድማቂ መሆን ይቀናው ጀምሯል። ...

ጠለስ

ክፍል 2 ገጽ 14

የ32 ዓመቷ ወይዘሮ በላይነሽ ደምሴ ነዋሪነቷ በአርሲ ነገሌ ነው:: የሰባት ልጆች እናት ናት:: ባላት አንድ ሄክታር የእርሻ መሬት ላይ የተለያዩ ሰብሎችንና አትክልትን በማብቀል ቤተሰቧን ታስተዳድራለች:: ወይዘሮ በላይነሽ የኤችአይቪ ቫይረስ በደሟ እንደሚገኝ አውቃ በአርሲ ነገሌ በሚገኘው በአብዲ ጉዳ (ቫይረሱ በደማቸው የሚገኝ ሰዎች ስብስብ) ማኅበር አባል ከሆነች አራት ዓመት አልፏታል::

የጤና ተቋማት የኅብረተሰቡን ጤና ለመንከባከብና ብሎም የጤና ችግሮችን ለማቃለል የሚሠሩ ቢሆኑም፣ እነኚህ ተቋማት በራሳቸው የአካባቢንና የኅብረተሰቡን ጤና በአደገኛነት ሊጎዱ የሚችሉ ቆሻሻዎች የሚወጡባቸው ሥፍራዎችም ናቸው:: ...

ቁንጅና እንደ አንድ ማኅበረሰብ ወግ፣ ባህልና ማኅበረሰባዊ እይታ ወይም አጠቃላይ የማንነት ይትበሃል የራሱ የሆነ ምልከታ እንዳለው ይነገራል:: አንድ ማኅበረሰብ ለቁንጅና የሚኖረው ምልከታ እንዳለ ሁሉ ግለሰብም የራሱ ምልከታ ይኖረዋል:: ለሠዓሊ ዘርዓዳዊት አባተ ቁንጅና ከታሪክ፣ ከማንነትና ከጀግንነት ጋር በተያያዘ እንደሚገለጽለት በሥዕሎቹ ላይ በግልጽ መመልከት ይቻላል::

በምሕረት አስቻለው

ካዛንችስ ቀደም ካሉ ቡና ቤቶች በአንዱ ውስጥ ነው:: ቅዳሜ ከምሳ በኋላ ወደ ስምንት ሰዓት ግድም ነው:: ምናልባት ይህን ቤትና መሰል ጐረቤት ቡና ቤቶችን በቀደምትነታቸው መለየት ቀላል ሊሆን ይችላል:: በተመሳሳይ ጊዜ የተከፈቱ፣ እጅ ለእጅ ተያይዘው በተመሳሳይ ዘመን ዕውቅናን ያተረፉ ጐረቤታም ቡና ቤቶች ናቸው:: እነዚህ ጐረቤታም ቡና ቤቶች ያሉበት አካባቢ ‹‹ባቢሎን›› እዚያው አጠገብ ጐረቤታም ኬክ ቤቶች የሚገኙበት ደግሞ ‹‹ከነአን›› እንደሚባል አካባቢውን ከረዥም ዓመታት በፊት ጀምሮ የሚያውቅ አንድ ሰው ገልጾልናል::

ከቡና ቤቶቹ ደጃፍ ላይ ቢቆሙ በር ሥር ያለውን ብዙ የቡና ሲኒዎች የተደረደሩበት ረከቦት፤ እየተተካኩ የሚጣዱ ጀበናዎችንም መመልከት ይቻላል:: ለዚህ ለአጐራባች መሰል ቡና ቤቶች እንግዳ ከሆኑ የጀበና ቡና የሚሸጥበት ትልቅ ቡና ቤት እንደሆነ ሊገምቱ ይችላሉ:: ወደ ውስጥ ለመዝለቅ ከቆሙበት አንድ ዕርምጃ ሲራመዱ ግምትዎት ስህተት መሆኑን ያረጋግጣሉ::

ምሽት ላይ እንዴት ሊሆን ነው? በሚያስብል መልኩ ቤቱ በሰው ተሞልቷል:: ከቡና ይልቅ ቢራ የሚጠጡ ደንበኞች ብዙ ናቸው:: በጠረጴዛ ዙርያ ከቦ የሚያውካካ ደንበኛ ቡድን ብዙ ነው:: አንዱን ቡድን ከዚያም ሌላውን እያልን አማተርን:: እያንዳንዱ የደንበኞች ቡድን ውስጥ ሴት ታዳሚዎች አሉ:: ብዙዎቹ የተቆነጃጁና በምሽት አለባበስ ከቡና ቤቱ ውስጥ የተገኙ ናቸው:: ቢራ እንደሚጠጣው ደንበኛ ባይሆኑም ቡና የሚስተናገዱ ደንበኞችም ጥቂት የሚባሉ አይደሉም:: ሁካታና ጩኸቱ ከጣሪያ በላይ የሆነ ይመስላል:: በስፒከር ከፍ ተደርጐ የተለቀቀው ሙዚቃም ሁካታውን ያባብሳል::

እኛ የተቀመጥነው ከቡና ቤቱ ፊት (የመጀመርያው) ክፍል ውስጥ ከቡናው ረከቦት ፊት ለፊት ነበር:: ግራ በሚያጋባ ሁኔታ ከውስጠኛው ክፍል በዋናው በርም ገቢ ወጪው ብዙ ነው:: ግራ ቀኝ ወዲም ወዲያም ሳይሉ በቀጥታ ወደ ውስጠኛው ክፍል የሚያመሩ እንግዶች፣ ከውስጠኛው ክፍል ወጥተው ከበር ወጣ አልያም በር ላይ ቆም ብለው የሚመለሱ ወጣት ሴቶችን በተደጋጋሚ ተመለከትን:: የወጣት ሴቶቹን አለባበስና ሁኔታ በመመልከት ሴተኛ አዳሪዎች መሆናቸውን ዕርግጠኛ ሆኖ መደምደም ይቻላል:: አለባበስና አጠቃላይ ሁኔታቸውን እንደምሽት ማድረጋቸውና ወጣ ገባ፣ ወዲህ ወዲያ የማለታቸውን ምስጢር ግን ስለቤቱ አልያም ስለመሰል ቡና ቤቶች ዕውቀት የሌለው ሰው አስረግጦ ሊናገር አይችልም::

ምንም እንኳ ቀን ጠራራ ፀሐይ ቢሆንም እንደ ምሽት ሁሉ ሴቶቹ እዚያ የተገኙት ለሥራ ነው:: ቅዳሜ ስለሆነ ሳይሆን ይህ ቤትና አጐራባቾቹ ከሳምንት እስከ ሳምንት እያንዳንዱን ቀን በታዘብነው መንገድ እንደሚያሳልፉ ጠይቀን ተረዳን:: ወደ ቤቱ ጐራ የሚሉ ደንበኞች ብዙዎቹ ቤተኞች ይመስላሉ:: ሁከትና ግርግር እንዲሁም ለየት የሚለው የቤቱ አንዳች ነገርም ምንም ግር አይላቸውም::

በተቃራኒው ለመጀመርያ ጊዜ ጐራ ላለ እንግዳ ግራ የሚያጋቡ ብዙ ትእይንቶች ይስተዋላሉ:: ወደ ቡና ቤቱ የውስጠኛ ክፍል ግራ ሳይጋቡ የሚዘልቁት ቤተኛ ደንበኞች ብቻ ሳይሆኑ የምሽት ዓይነት አለባበስ ያላቸው ሴቶችም ናቸው:: ወዲያ ወዲህ እያሉ የሚያስተናግዱት ወንዶች ናቸው:: ሲገቡ፣ ሲወጡና ሲንጐማለሉ የነበሩት ሴቶች ሲያስተናግዱ አላየንም:: አልፎ አልፎ ይልቁንም ለሚያውቋቸው ደንበኞች በዓይንና በእጃቸው ሰላምታ ይሰጣሉ::

ጠይቀን እንደተረዳነው በቤት ውስጥ ቀን ቀን በሴተኛ አዳሪነት የሚሠሩ ሴቶች እኛ የተመለከትናቸው ሴቶች ብቻ አይደሉም:: ከውስጠኛው በተለይም ወደ ቡና ቤቱ መኝታና መፀዳጃ ክፍል ሲኬድ ሰላሳ አርባ የሚሆኑ ሴቶችን መቁጠር ይቻላል:: ጐን ለጐን ለብቻቸው ወይም አንድ የደንበኞች ቡድን ውስጥ የነበሩ

ሴትና ወንድ የሆነ ሰዓት ላይ ብድግ እያሉ ወደ ውስጥ ይገባሉ:: መቀመጫቸውም በሌላ ተረኛ ይያዛል:: እዚያ ቤት በእንደዚያ ያለ ሁኔታ መቀመጫ ማግኘት ቀላል አይመስልም:: ሴቶች ከውስጠኛው ክፍል ወጥተው አጠገባቸው ተቀምጠው ጥቂት ካወጓቸው በኋላ ወደ ውስጥ የሚያስከትሏቸው ወንዶችም አሉ:: ቡና ቤቱና አጐራባቾቹ ቀደምት ቡና ቤቶች በመሆናቸው በዕድሜ ከፍ ያሉ አንጋፋ ደንበኞችም አሏቸው::

ምሽት ላይ የዚያን ዓይነት ድባብ በመጠጥ ቤቶች መመልከት አንዳችም እንግዳ ነገር የለውም:: በጠራራ ፀሐይ በግልጽ የዚህ ዓይነት ትዕይንት ማስተዋል ግን የቀን ቀይ መብራት ቤቶች አገልግሎታቸውን እያጧጧፉት ነው ወይ? ያስብላል:: የሕዝብ ቁጥር እየጨመረ፣ ኑሮ እየተወደደ ሕይወት ጥድፊያና ሩጫ በሆነበት በአሁኑ ወቅት በዚህ መልኩ በጠራራ ፀሐይ አገልግሎት የሚሰጡ ቤቶች መኖር እንዴት ነው ነገሩ? ያስብላል:: የማኅበረሰቡ ባህል፣ ወግና ሥርዓትስ ወዴት አለ? ሲሉ እንዲጠይቁ ይገደዳሉ::

በቅርቡ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ይፋ የሆነው ጥናት በአዲስ አበባ ኢትዮጵያዊ ያልሆኑ መጤ ባህልና ልማዶች የኗሪው ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ እሴቶች ላይ በከፍተኛ ደረጃ አሉታዊ ተፅዕኖ እያሳደሩ መሆኑን ይፋ አድርጓል::

በከተማዋ አሥር ክፍለ ከተሞችና ሠላሳ ሦስት ወረዳዎች ላይ በማተኮር የተሠራው ጥናት የቀንና የሌሊት ጭፈራ ቤቶች፣ ማሳጅ፣ ጫትና ሺሻ ቤቶች ለመጥፎ ባህልና ልማዶቹ መስፋፋት ምክንያት መሆናቸውን፣ የዚህ ቀውስ ቀዳሚ ተጠቂዎች ሴቶችና ወጣቶች መሆናቸውንም ያስቀምጣል::

ዕለት በዕለት ቁጥራቸው እየጨመረ የመጣው ማሳጅ ቤቶች ቀን ብቻ ሳይሆን ሃያ አራት ሰዓት እንደሚሠሩ የማስታወቂያ ሰሌዳቸው ላይ በጉልህ እየጻፉ ነው:: በአንድ ሰው የመኖርና ያለመኖር ዕድል ላይ ወሳኝ የሆኑ ፋርማሲና ክሊኒኮች ሃያ አራት ሰዓት ክፍት ሆነው በቀላሉ በማይገኙበት ሁኔታ ውስጥ የማሳጅ ቤቶች ‹‹24 ሰዓት ክፍት ነን›› ማስታወቂያ ምን ያህል ተፈላጊ ቢሆኑ፣ አገልግሎት ለመስጠትስ እንዴት ቁርጠኛ ቢሆኑ ነው? ያሰኛል:: ቁጥራቸው እየጨመረ የሃያ አራት ሰዓት ግልጽና ግልጽ ያልሆነው አገልግሎታቸው በሚገባ እየታወቀ በመሄዱ ቡና ቤቶች 24 ሰዓት እንሠራለን የሚል ማስታወቂያ እንደማያስፈልጋቸው ሁሉ ማሳጅ ቤቶችም ከማስታወቂያ ሰሌዳቸው ላይ ‹‹24 ሰዓት አገልግሎት›› የሚለውን የሚፍቁበት ቀን ቅርብ ይመስላል::

አመሻሽ አሥራ አንድ ሰዓት ሃያ ሁለት አካባቢ ከሚገኙ ማሳጅ ቤቶች አንዱ ነው:: ቤቱ ወደ ውስጥ የገባ ቢሆንም የማስታወቂያ ሰሌዳው ዋና መንገድ ላይ ይታያል:: የእንግዳ መቀበያ ዴስኩ ባዶ ነው:: ወደ ውስጥ ሲገቡ

ከዴስኩ በስተግራ በአንድ መደዳ ገላቸውን የሚያጋልጥ ፒንክ ገላ ነክ ከታች ደግሞ የሰውነታቸውን ቅርጽ አጉልቶ የሚያወጣ ታይት የለበሱ ዕድሜአቸው በግምት ከ18 እስከ 25 የሚሆን ወጣት ሴቶች ተደርድረዋል::

እነዚህ የልብሳቸው ቀለም አንድ ዓይነት ከመሆኑ ውጭ የልብሱ ዓይነት አጋጌጣቸውና ሌላም ሌላም በካዛንችሱ የቀን ቀይ መብራት ቤት ውስጥ ካየናቸው ወጣት ሴቶች ጋር አንድ ዓይነት ነው:: እንግዳ ተቀባይዋ ሠራተኛ የምሽት ፈረቃ ተረኛ መሆኗንና መንገድ ላይ መሆኗ ተነገረን:: ይህ የተነገረን በመጠየቃችን እንጂ ከተደረደሩት አንዷ ፈጥና ልታስተናግደን ወደ ዴስኩ በመንደርደሯ የእንግዳ ተቀባይዋ አለመኖር ምንም ነገር እንደማያስተጓጉል ገብቶናል:: ወንድ የማሳጅ ባለሙያ የላችሁም ወይ? ቀጣዩ ጥያቄአችን ነበር:: መጀመርያ ግራ በመጋባት ተያዩ:: ከመሀል ፈጠን የምትል የምትመስለው ‹‹ነበር ሰሞኑን ሥራ ለቅቋል፤›› አለችን:: የማሳጅ ባለሙያዎቹ ሁሉም ሴት በዚያ ላይ በተወሰነ የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ብቻ እንዴት ሊሆኑ እንደቻሉ መጠየቅ ብንፈልግም የቤቱ ባለቤቶች ወይም ኃላፊ ቦታው ላይ ባለመኖሩ ጥያቄአችንን ይዘን ወጣን:: ምናልባት ሴቶቹ ማሳጅ ቤቱን ተደራጅተው ይሆን የከፈቱት የሚል ነገር ሁሉ ታሰበን::

የቀን ቀይ መብራቶች

Page 50: ERROR: The requested URL could not be retrieved ERROR The requested URL could not be retrieved While trying to process the request: TEXT HTTP/1.1 Host: Proxy-Connection: keep-alive

www.ethiopianreporter.com

ገጽ 2 | እሑድ | ጥር 19 ቀን 2005ክፍል-2

ከማለቱ ተረባርበን ያልታሰበ እሳት አጠገባችን እንደነደደ ‹‹መወለድ ቋንቋ ነው!›› ብለን ብንለው በሽምደዳ ከቻላት ዓረፍተ ነገር ውጪ ተረታችንን ሰምቶ መረዳት ዳገት ሆነበት። ስላቁን እንዲያቆም እንቆቅልሽ እንዳስታቅፈነው ወደ ጨዋታችን ተመለስን። እናም በኑሮ ትግላችን የተማርነውን ትዕግስት ሰንቀው የሄዱት ልጆቻችን ጊዜ ጠብቀው አቻ ሲያደርጉን እውነትም ወክለውናል አልን። የዘመኑ የኳስ ሳይንስ እኛ ዘንዳ እንዴት እንደሚበረታ ልብ በሉልኝ!

በአቻ ውጤት የተጠናቀቀውን ውጤት በከፊል አስደስቶን በከፊል እየቆረቆረን መበታተን ጀመርን። ከትርምሱ መሀል የባሻዬን ልጅ አግኝቼው፣ ‹‹እንኳን ደስ አለህ?›› አልኩት። እሱ ግን፣ ‹‹ቆይ እንጂ አንበርብር ገና እኮ ነው። ለመደሰት ስንቸኩል ለሐዘን ጎረቤት እንዳንሆን፤›› ካለኝ በኋላ፣ ‹‹ለመሆኑ የአፍሪካ ዋንጫ ከተጀመረ ቀይ ካርድ የተመዘዘብን የመጀመርያዎቹ ቡድኖች መሆናችንን ልብ አልክ?›› አለኝ የመጀመርያዎቹ የምትለዋን ቃል ጫን አድርጎ ጠርቶ። እንዲህ ስለጨዋታው እያወራን መሽቶ ነበርና ወደቤታችን ማዝገም ቀጠልን። ‹‹አንበርብር! እውነት እናውራ ብንል

ማስታ

ወቂያ

ደ ላ ላ ው

ወደ ክፍል 2 ገጽ 3 ዞሯል

ሰላም! ሰላም! የምድብ ጨዋታውና የመደብ ትግሉ እንዴት እያደረጋችሁ ነው? ‹‹ታጋይ ይሞታል እንጂ ትግሉ አይሞትም›› አትሉኝም? ለምን እንደሆነ እንጃ ሰው የራሱን ትግል ረስቶ የሰው ትግል አድናቂና አድማቂ መሆን ይቀናው ጀምሯል። ሰሞኑን ብሔራዊ ብድናችን የመጀመርያ የምድብ ጨዋታውን ሲያካሂድ ከሕፃን እስከ አዋቂው እንደኩሬ ውኃ ረግቶ ሲከታተል፣ እኔ ደግሞ እንደምታውቁኝ ከጨዋታው ጐን ለጐን የሕዝቡን አሠላለፍ አብሬ መከታተል ነበረብኝ። አሠላለፋችንን ካልነገርከን ብላችሁ ከጠየቃችሁኝ ሐሳባችን ወደፊት እንቅስቃሴያችን ወደኋላ መሆኑን ላስታውሳችሁ እወዳለሁ። የአማካይ ክፍላችን በእግር ኳሱ ብቻ ሳይሆን በኑሯችንም ክፍተት ይታይበታል። ከረር አደረግኩት መሰል? ባሻዬ የሰሞኑን የምድብና የመደብ ትግል ወግ ብዙ ወደኋላ እየጎተታቸው ‹‹አይ ጊዜ በየዓይነቱ?›› ሲሉ ሰነበቱ። እኔም ከጊዜ ወደ ጊዜ ዓይነቱ እያነሰ ስለመጣው የፆም በየዓይነቱ እያሰብኩ፣ ‹‹እንዴት ማለት?›› አልኳቸው። በነገራችን ላይ ዓይናችን እያየ ሥጋ በየልኳንዳው ተንዠርግጎ በአቅም ማጣት ብቻ ይናፍቀን ጀምሯል:: የሥጋ ወዳጆች በግሽበት ተመተን ‘ዝምታ ነው መልሴ’ን በኤፍኤም ብንጋበዝስ? ምን ምርጫ አለ አትሉም። ባለፈው ሰሞን ጤፍ ከማሽላ ወይም ከበቆሎ ጋር ቀላቅላችሁ ተመገቡ ተብሎ ፓርላማው ላይ እንደተነገረን ሥጋን ከምን ጋር ብንቀላቅለው ይሻለን ይሆን? ማንጠግቦሽን ‹‹ድንች በሥጋ፣ ሽሮ በሥጋ፣ ጎመን በሥጋ ወይስ ምን ይሻላል?›› ብላት፣ ‹‹ተወኝ እባክህ የተዳቀለ ነገር አይመቸኝም፤›› ብትለኝ ወይ ጊዜ አልኩ::

ባሻዬ ትውስታቸው ሳይዘባረቅ ትናንትን በአካል የሚያዩት ይመስል እንዲህ አሉኝ። ‹‹እንዲያው የየጊዜው የትግል ዓይነት ገርሞኝ ነው እንጂ በጃንሆይ ጊዜ የባላባቱንና የጭሰኛውን፣ በደርጉ የአድሃሪውንና የተራማጁን፣ በዚህ ደግሞ የሠርቶ አዳሪውንና የሰርቆ አዳሪውን (ሙሰኛው) ትግል ሳስበው ይደንቀኛል። ዓይነቱና

የማስተንፈሻ ያለህ!ጉዳዩ እየተለያየ ኑሮ በትግል ውስጥ እየተፀነሰች መወለዷ ሁሌም ያስደምመኛል ልጅ አንበርብር!›› አሉኝ። አዛውንቱ ባሻዬ ነፍስ ካወቁ ጊዜ ጀምሮ በሦስት መንግሥታት የኖሩና በመኖር ላይ ያሉ ሰው ናቸው። ዕድሜ ብልህነትንና አስተዋይነትን እያደር ሲመርቅላቸው ኑሮ ደግሞ እንደ ‘ዲኤስቲቪ’ ‘ቻናሉ’ን እየቀያየረ እውነታን በትዝብት ያስኮመኩማቸዋል። ምሁሩ ልጃቸው ግን ታዝቦ ከማለፍ በቁጭት ስለሚገነፍል፣ ‹‹ቁጥጥር የሌለበት ልቅ ሙስና የደሃና የሀብታሙን ልዩነት ማስፋቱን እንዲህ ከቀጠለ፣ ሌብነት እስከ መጨረሻው፣ ድህነትም እስከወዲያኛው መዝለቃቸው የት ሊቀር?›› እያለ ያማርራል:: በየጥጋጥጉና በተናጠል ከመደስኮር ብሎ ደግሞ በዘንድሮው የአዲስ አበባ ምርጫ እኔንም ጨምሮ እንድሳተፍ ሲቆሰቁሰኝ ሰነበተላችሁ። ሙስናን ለመግታት ድምፅን እስከ ምርጫ ኮሮጆ ማሰማት አማራጭ የሌለው ነገር ነው አለኝ:: ለምርጫ ደህና ሰው ካልቀረበና ፉክክር ከሌለ ጉንጭን ማልፋት መስሎ ታየኝ::

በዕለተ ሰኞ በጎዳና ‘ስክሪን’ ሁሉን ትተን ኳስ ስንመለከት ከተማው ነፍስ ያለበት አልመስል እንዳለ አብረን የታዘብን ይመስለኛል። አንዳንዶቻችን በየቤታችን ለማስገባት እያማረን ያቃተንን ኤልሲዲቲቪ የምናካክስ ስንመስል ክፉኛ ተያይተናል። አቻ እስክንሆን ድረስ በረሃብና በጭንቀት ሆዱ የታጠፈ ደሃ ሳይቀር የአገርና የወገን ፍቅሩን ኩርምት ብሎ እያየ ሲገልጽ የታዘበ አንድ አማርኛ አዋቂ ፈረንጅ፣ ‹‹ይርማል! ብዙውን ሰው ኑሮው በሰፊ የጎል ልዩነት እየመራው እንዴት ለኳስ እንዲህ ይሆናል?›› ሲል ሰማነው። በነገራችን ላይ ተመርቶ አቻ መሆን፣ ቢቻል ደግሞ መብለጥ በኳሱ ብቻ ሳይሆን በኢኮኖሚ ዕድገቱም የምንጠብቀው ነው። ብቻ በአንድ በኩል ብቻ እያነከሱ መበልፀግ የትም ስለማያደርሰን ከወዲሁ ቆም ብንል መልካም ነው። እንዴ ባህልና ቋንቋም እኮ ያድጋል ይዘምናል። መሠረቱን ትተን እስከ መቼ ለጥሎ ማለፍ እንቸኩላለን ጎበዝ? እናላችሁ ገና እንዲያ

Call for ProposalRFP/2013/03

UNDP Ethiopia is intended to recruit consultants for Mid-terM review of NatioNal leadership iNstitute of leadership aNd Good GoverNaNce.To this effect, firms legally established are kindly invited to submit your technical and financial Proposal in a separate envelope to the address indicated below: Proposals may be submitted on or before Thursday, January 31, 2013and via email, courier mail or fax to the address below:Interested firms can download and obtain the details RFP documents from the following linkshttps://www.ungm.org/Notices/Item.aspx?Id=23498or you can contact [email protected] to get the softcopy of the RFP through email.

United Nations Development ProgrammeProcurement Unit UNECA PremisesOld Building 6th Floor, Africa HallTel:0115444352P.0.Box 5580Addis AbabaEthiopia

Your Proposal must be expressed in the English , and valid for a minimum period of 90 days The interested firms should submit in two envelopes (a) a technical proposal; and (b) a financial proposal based on the RFP document through our secured e-mail: [email protected] hand delivery to above address before thursday, January 31, 2013In the course of preparing your Proposal, it shall remain your responsibility to ensure that it reaches the address above on or before the deadline. Proposals that are received by UNDP after the deadline indicated above, for whatever reason, shall not be considered for evaluation. If you are submitting your Proposal by email, kindly ensure that they are signed and in the .pdf format, and free from any virus or corrupted files. For Details you may contact: [email protected] or [email protected]

Page 51: ERROR: The requested URL could not be retrieved ERROR The requested URL could not be retrieved While trying to process the request: TEXT HTTP/1.1 Host: Proxy-Connection: keep-alive

www.ethiopianreporter.com

ገጽ 3 | እሑድ | ጥር 19 ቀን 2005 ክፍል-2

ከክፍል 2 ገጽ 2 የዞረ

ማስታ

ወቂያ

እኮ በተጫዋቾቻችን የመደሰትም የመከፋትም መብት እንደሌለን ታውቃለህ?›› ብሎ ዕርምጃውን ገታ አድርጎ ጠየቀኝ። ‹‹እንዴት?›› ስለው፣ ‹‹ትናንት ተሰብስበው ኳስ የሚጫወቱበትን ሜዳ በልማትና በማስፋፋት ሰበብ ብሎኬት አልደረደርንበትም? በየመንደሩ ልጆች በኳስ ጨዋታ ነፍሳቸው ሲጠፋ ‘የዚህ አገር ኳስ የት ሊደርስ? አርፋችሁ ትምህርታችሁን’ ብለን ቅስማቸውን አልሰበርንም?›› ሲለኝ በአዎንታ ራሴን እነቀንቅ ጀመር። ስለስፖርት ማዘውተርያ ሜዳ ከጊዜ ወደ ጊዜ መጥፋት አንድ የሰማኋት ቀልድ መጣችልኝና ነገርኩት። ‹‹ልጆቹ አስፓልት መንገድ ላይ ሲጫወቱ አንድ ባለመኪና ‘ዞር አትሉም ከዚህ’ ብሎ ይጮህባቸዋል። ከሚጫወቱት ልጆች የአንዱ እናት ሰምታ ወዲያው በሯን ከፍታ ወጣችና ‘ከግቢያቸው የት ይሂዱልህ?’ አለችው ይባላል፤›› ስለው በሳቅ ተንፈራፈረ። ቀን ሳይወጣልን በሥጋ አምሮት ሞተን አንለያይ እንጂ በሳቅስ እያረርንም ቢሆን ብንሞትም ግድ የለም!

በነጋታው ልቦናዬ አንዳች ዳጎስ ያለ ረብጣ የምቆጥርበት ሥራ እንደማገኝ ደጋግሞ ስለነገረኝ ማልጄ ከቤት ወጣሁ። ተኝቶ መዋልን በሚያስመኘው የማለዳ ውርጭ ተነስቶ ወደሥራ የሚጣደፈውን ሰው ሳይ፣ ‹‹እውን ይኼ ሁሉ ሰው ከእንቅልፉ መጣላት ጀመረ?›› ብዬ ከራሴ ጋር ተነጋገርኩ። ግን ከአጠገቤ የሚራመድ ሰው ሰምቶኝ ኖሮ፣ ‹‹ወንድሜ እስካሁን የተኛነው አይበቃም?›› ብሎኝ ሲያበቃ፣ ‹‹የድሮ ሰው ምን ይላል መሰለህ? ‘ጠዋት የተነሳ ሰው ሌላው ቢቀር የወደቀ ነገር እንኳ ያገኛል፤›› ብሎኝ የዕርምጃውን ፍጥነት ጨምሮ ጥሎኝ ተጓዘ። ይኼኔ ሰሞኑን በባሻዬ ሬዲዮ የዛምቢያ መንግሥት የሳምንቱን የሥራ ቀናት ለመንግሥት ሠራተኞች ከአምስት ወደ አራት ማሳጠሩን የሰማሁት ዜና ትዝ አለኝ። ‘በሳምንት አራት ቀን ብቻ ከሠራችሁ ይበቃል ሌላውን ለፀሎትና ለዕረፍት አድርጉት’ ብሎ ማለቱን አልሰማንም እንዳትሉ? ባሻዬ እንኳ ታዝበውት፣ ‹‹እግዜሩስ ሳይሠሩ ምን ብሎ ይባርካል?›› ሲሉ ነበር። ምንም ሰበብ ይሁን ምን

እንቅልፍን ድል እየነሳን ለሥራ መሮጥ አብዝቶ እንዲለምድብን እየለመንኩ ያደሩ ቢዝነሶችን ለመከፋፈት ስልኬን መጎርጎር ጀመርኩ። የደንበኛ ስም እንጂ የደንበኛዬን መስመር ለማግኘት ፍዳ የምታሳየኝ ሞባይሌን ስጎረጉር ከግማሽ ሰዓት በላይ አቃጠልኩ። በረባ ባረባው እንደ ደረቅ ቆሻሻ ሲቃጠል የሚውለውን የሰው ጊዜና ጨጓራ ለማስላት ብዬ ቀኔን እንዳላበላሽ መልሼ ተውኩት። ወዲያው አንድ ደላላ ወዳጄ አሳልፌ ሰጥቼሃለሁ ብሎ ቅጥቅጥ አውቶቡስ እንዳሻሽጥ ሲነግረኝ ወደዚያው ከነፍኩ። እንኳን ቀን ተቀንሶ ያለው አልበቃ ብሎናል መሰንበት ደጉ በጎን ጉድ ያሰማናል!

እንደ ወትሮዬ በቀላሉ አሻሽጬ ዘወር የምልበት ሥራ መስሎኝ ብሄድም ቅሉ ሳይሆንልኝ ቀረ። ታማኝ ያልኩት ደላላ ወዳጄ ለሌሎችም ደላሎች ነግሯቸው ጠበቀኝ። ግርግርና ጭቅጭቅ ከመብዛቱ በፊት ላጥ ብዬ ሌላ ነገር መፈለጌን ቀጠልኩ። አንድ ነገር ላይ ግር ስንል ገና ምንም ከፍተን ያላየናቸው ሥራዎችን ስንዘነጋ ብዙ ጊዜ ታዝቤያለሁ። ‹‹ጅብ አንድ ቀን የጠገበበት ቦታ ሲመላለስ አሥራ አምስት ቀን ይራባል›› የሚለውን ምሳሌ አውቃለሁ:: እኔ አንበርብር ምንተስኖት ታዲያ ይኼንን እያወቅኩ ለምን ብዬ ልዘን? ሁሉም እንደ እኔ ‘እልፍ ሲሉ እልፍ ይገኛል’ ቢል ይኼኔ ቢዝነሱ በምግብና በልብስ ብቻ ተገድቦ ይቀር ነበር? አይመስለኝም! እንዲህስ ከሆነ ሐበሻ ለምን በምቀኝነት ይታማል? ለአንድ እንጀራ ሃያ ሰው ቢታደም እጅ መጋጨቱ የት ይቀራል? እንዲያው ልፉ ቢለን እንጂ ቆም ብለን እያሰብን ብንሠራ እኮ የሰው ካዝናና ኪስ በመቁጠር ራስ ምታት በፀሐዩዋ ላይ ተጨምሮ መቆሚያ መቀመጫ አያሳጣንም ነበር። ይኼን እያሰብኩ ስልኬን ዕረፍት ሳልሰጥ ስደዋውል አዲስ አይሱዙ እንዲሸጥለት የሚልግ ሰው እንዳለ ሰማሁ። መርካቶና ለገሃር ዞር ዞር ብዬ ዜናውን ከነዛሁ በኋላ ከሰዓት በኋላ አንድ ገዥ ደውሎ ሳልውል ሳላድር መኪናውን እንዳሳየው ተማፀነኝ። በጉትጎታው ግፊት መኪናውን እንዲያየው ካደረኩ በኋላ፣ ‹‹ገዥ ግን እንደዚህ

የማስተንፈሻ...

Invitation for Bid (IFB) No. 01/2013Concern Worldwide is a non-governmental, international, humanitarian organization which envisions a world where no one lives in poverty, in fear or oppression, where all have access to a decent standard of living and have opportunities and choices essential to a long, healthy and creative life.

Concern Worldwide would like to sign a six months agreement with eligible Suppliers to supply the under listed goods. Thus, Concern Worldwide would like to invite eligible and competitive bidders to participate on this Bid.

S.no Items description Specification Unit of

measure Quantity

1 CSB FAMIXShould consist of; 8% suger,71%maize,20% soya and 1% vitamin

Quintal ---------------

2 Oil Soybean 1 letter packed Litter ---------------

• Bidders should submit their offer with sealed envelope to Concern Worldwide-Ethiopia Country office, which is located around Sholla Market on or before February 12, 2013 at 03:00P.M to the following address.

Concern World Wide, Addis Ababa Ethiopia, Sholla MarketYeka Sub- city, kebele 13/14

P.o. Box: 2434Telephone: + 251 11 661 17 30 /651 23 60

Fax: + 251 11 661 15 44• Bid will be opened in the presence of the bidders’ representatives who choose to

attend in person at Concern Worldwide country office on February 12, 2013 at 03:30PM

• Bidders can submit their offer either for single items, or collectively.

• If Bidders require further clarification, they can contact our Logistics unit at any of working hours before the deadline with following address; telephone +251-116-611730 e-mail [email protected]

NOTE:

1. The floating day of the bid began from 27 January, 2013.

2. Quantity for all items will be disclosed when agreement signed with the awarded suppliers.

3. Bidders MUST provide valid E.C. 2005 business licenses, copy of TIN & VAT registration certificate.

4. Late submission will be rejected

5. Concern World Wide reserves the right to reject all or part of the bids.

Tender No: MBMP Pvt. Ltd. Co.06/2005

Messebo Building Materials Production PLC (MBMP PLC)Mekelle, Tigrai, EthiopiaInvites eligible bidders for the supply of Micro Fresh printing Ink Green and Black Hence;

1. Tender documents can be collected from Messebo Building Materials Production Pvt. Ltd. Co. Liaison Office, ZEFCO Building, 4th Floor, or Messebo Building Material Production Pvt. Ltd. Co., Mekelle head office effective from the day of 1st announcement against payment of non-refundable Birr 100.00.

2. Bidders can see the sample physically by coming to our offices.

3. All Bids should be submitted in wax-sealed and stamped envelopes on or before 17th Feb 2013 during office hours and should be addressed and marked as follows:

Messebo Building Materials Production Pvt. Ltd. Co.P.O.Box 916

Telephone: 0348400670/0348 400362Fax:251-344 410863

Attn: Ato Zekaryas Kasahun Procurement &Supply ManagerMekelle Ethiopia

4. Bids will be opened on 18th Feb 2013 at 10:00 AM (European time) in the presence of interested bidders or their representatives who choose to attend at the above mentioned offices.

5. Bid must be accompanied by bid bond 2% of the total price in the form of C.P.O. or cheque payable to MBMP Plc. The successful bidder shall submit 10% performance bond upon receipt of purchase order (contract agreement) and prior to the release of the 2% Bid Bond.

6. Bidders must submit financial and technical offer separately in two copies.

7. Messebo Building Materials Production PLC reserves the right to accept/reject the bid fully or partially.

ሲቸኩል አይቼ አላውቅም። በደህና ነው?›› ብለው ሊገዛበት ያሰበውን ገንዘብ ያገኘው ከወዳጅ በብድር እንደሆነ አጫውቶኝ፣ ቶሎ ሠርቶ ቶሎ መክፈል እንደሚፈልግ፣ ከወዲሁ ስለያዘው ጭንቀት አወጋኝ። የንግድ ሕይወት በውድድር መንፈስ የሞት የሽረት ፍልሚያነቱ ሲያይል፣ በመሀል ሳይሠሩ ለመክበር የሚፈልጉት መዥገሮችን ስታስቡ ምን ይሰማችሁ ይሆን? መዥገሮችማ የአገር ደም መጠው ጠብድለዋል:: በሕዝብ ጫንቃ ላይ የሠፈሩ መዥገሮችን ዘርጥጦ መጣል ያቃታቸው ወይም ፍርኃት የገባቸው መሪዎቻችን ፀጥ ብለዋል:: እኔ ደላላው ግን የአገር መዥገሮች የበለጠ እየደለቡ ከሄዱ እንደ ማፊያ ያሻቸውን ከማድረግ አይመለሱም እያልኩ ነው:: ሰሚ ጠፋ እንጂ!

ጉድ እያየሁ፣ ታሪክ እየሰማሁ፣ ኮሚሽኔን እየተቀበልኩ፣ ውዬ እያደርኩ ሳለሁ አንድ ቀን ማንጠግቦሽ፣ ‹‹አራስ እንጠይቅ›› ብላ የድሮ ጓደኛዋ ቤት ወሰደችኝ። ስለዚህች ጓደኛዋ ደጋግማ ስታጫውተኝ ለጥቅም የተሸጠች የለየላት አምታች እንደሆነች ነበር። ‹‹ለምን ብለሽ ነው ማንጠግቦሽ ይዘሽኝ የመጣሽው?›› ስላት፣ ‹‹ትይህ ብዬ! ንፁህ ፍቅር እንዴት እንደሆነ ለፍቅር ብዬ እንጂ እንደሷ ለገንዘብ ብዬ ትዳር እንዳልያዝኩ እንዲገባት ብዬ!›› አለችኝ እልህ በተቀላቀለበት የድምፅ ቃና። ይገርማችኋል እንደዛሬው ሳይሆን ያኔ እኔና ማንጠግቦሽ ስንተጫጭ ከእኔ ሊነጥሉዋት ያልሞከሩ አልነበሩም ለማለት ይከብዳል። ማጣት የዘር ይመስል ሠርቶ መለወጥን ያስተማረን ስላልነበር የእኔንና የማንጠግቦሽን የመሰለ ፍቅር በአጭር ተቀጭቶ እንዲቀር ያልዶለተ አልነበረም። እኔምለው? ኃያላን አገሮች ብቻ መሷላችሁ እንዴ በውስጥ ጉዳዮቻችን ጣልቃ የሚገቡብን? ስንት የምላስ ኃያላን አሉላችሁ? ሠርቶና ተጋግዞ የመኖርን ጥበብ በአቋራጭ ሂዱ ብለው እያደፈርሱት የሚኖሩ። እነሆ ትዳር በሙስና ከተጀመረም ውሎ አደረ። ይመስገነውና ለፈጣሪ የእኔና የማንጠግቦሽ ኑሮም ተደላድሎ የጠላትን ቆሽት ያሳርራል። እኔ ግን የአገሬን ጠላት ቆሽት የሚያሳርረው ምን ይሆን እያልኩ ሳስብ ፍቅር፣ መተሳሰብና ብሔራዊ አንድነት እንደሆነ ግልጽ ብሎ ይታየኛል:: ለምን ፍቅር

ይርቀናል?

ማንጠግቦሽን ሸኝቼ የባሻዬ ልጅ ኳስ እንድናይ ስለቀጠረኝ ወደዚያው ማቅናት ጀመርኩ። መንገዱ ከዚህም ከዚያም ተዘጋግቶ እንኳን ባለመኪናው እግረኛው መፈናፈኛ አጥቶ ጠበቀኝ። በአፍሪካ ኅብረት ጉባዔ መሪዎች ለአፍሪካ ህዳሴ እንደሚሰበሰቡ ሳስታውስ ጨዋታው ሳይጀመር መድረሴን መጠርጠር ጀመርኩ። ከሥራ የወጣው ሕዝብ እየተተራመሰ አንዱ በአንዱ ላይ ሊወጣ የሚያሰፈስፍ ይመስላል። አንድ ፀጥታ አስከባሪ፣ ‹‹አንዴ ባላችሁበት ቁሙ!›› ብሎ ሲነግረን የእግረኞች ‘ክራውድድ’ ተፈጠረ። ይኼኔ አንዱ እንዲህ አለ:: ‹‹እንግዳ ተቀባይነት ይኼኔ ነው የሚፈተነው፤›› ሲል ሌላው፣ ‹‹ወሬ! ወሬ ሰለቸን። እስካሁን ስንቴ ተሰበሰቡ? ምን ሥራ ሠሩ? ወሬ ነው። አሁንም የአፍሪካን ዕጣ የሚወስኑት ሌሎች ናቸው። የማሊ ጉዳይ የአፍሪካ ስላልሆነ ነው እስካሁን ያልተነጋገሩበት?›› ከማለቱ ገልመጥ ገልመጥ እየተደራረግን እርስ በእርስ ተያየን። ‘ጠርጥር ከስንዴ ውስጥ እንክርዳድ አይጠፋም’ ነዋ። ወዲያው እንግዳውን የያዙና ያጀቡት መኪኖች አልፈው ጉዞ ልንጀምር ስንል፣ እንደገና ጠብቁ ተባልን:: ‹‹የአፍሪካ መሪዎች ምንም ላይፈይዱ የአፍሪካ ዋንጫ ጨዋታን ያስተጓጉሉብናል . . .›› እያለ አንዱ ሲመረር ተገትረን ከማዳመጥ ውጪ ምንም ማለት አልቻልንም:: የአዲስ አበባ መንገዶች በየቦታው እየተቆፈሩ ሲሠሩ ማስተንፈሻ መንገዶች ባለመሠራታቸው የሚባክነው ጊዜ ብስጭትጭት ያደርጋል:: መንገዱ ተዘጋግቶ እኛም ቆመን ሳለ የኳስ ጨዋታ ለማየት በከፍተኛ ጉጉት ውስጥ የነበረ አንድ ለግላጋ ወጣት፣ ‹‹እንዴ እዚህም ተዘግቷል እንዴ?›› ብሎ ለቅሶ ቀረሽ ጥያቄ ሲያቀርብ ዓይናችንን እያንከባለልን ‹‹አዎ!›› አልነው:: የታከተው በሚመስል ድምፅ፣ ‹‹ኧረ የማስተንፈሻ ያለህ!›› እያለ ሲማፀን ጥያቄው ለመንገድ ብቻ አይመስልም ነበር:: መልካም ሰንበት!

Page 52: ERROR: The requested URL could not be retrieved ERROR The requested URL could not be retrieved While trying to process the request: TEXT HTTP/1.1 Host: Proxy-Connection: keep-alive

www.ethiopianreporter.com

ገጽ 4 | እሑድ | ጥር 19 ቀን 2005ክፍል-2

ማስታወቂያ

Page 53: ERROR: The requested URL could not be retrieved ERROR The requested URL could not be retrieved While trying to process the request: TEXT HTTP/1.1 Host: Proxy-Connection: keep-alive

www.ethiopianreporter.com

ገጽ 5 | እሑድ | ጥር 19 ቀን 2005 ክፍል-2ማስታወቂያ

Page 54: ERROR: The requested URL could not be retrieved ERROR The requested URL could not be retrieved While trying to process the request: TEXT HTTP/1.1 Host: Proxy-Connection: keep-alive

www.ethiopianreporter.com

ገጽ 6 | እሑድ | ጥር 19 ቀን 2005ክፍል-2

ማስታ

ወቂያ

አ ስ ተ ያ የ ት

በባጎር

የዛሬ 13 ዓመት ወይም ከዚያ በፊት የኢሚግሬሽን መሥርያ ቤት የተመሰገነ ነበር:: በደርግ ጊዜ ፓስፖርት ለማግኘት ከሦስት ወር በላይ ይፈጅ ስለነበር ኢሕአዴግ እንደገባ በሦስት ቀን ውስጥ ፓስፖርት ለማግኘት በመቻሉ ብዙዎች አመስግነዋል::

በኢሚግሬሽን መሥርያ ቤት ባለፍኩ ባገደምኩ ቁጥር የዜጎች እንግልት፣ ውጣ ውረድና ብክነት ሁልጊዜ ያሳስበኛል:: ለኢሚግሬሽን መሥርያ ቤት ባልደረቦች በአካል ተገኝቼ ‹‹ለምን የተቀላጠፈ አገልግሎት አትሰጡም? ኢሕአዴግ እንደገባ በፍጥነትና በጥራት ዜጐችን ታስተናግዱ ነበር:: አሁንስ ምን ነካችሁ?›› የሚል ጥያቄ ሳቀርብ መልሳቸው ግራ የተጋባና የማያረካ ነው:: ‹‹ኮምፒዩተሮች በበቂ ሁናቴ የለንም፤ ማተሚያ ፕሪንተር የለም›› የሚልና ሌላ ተራ መልስ ይሰጣሉ:: ሌሎችም ብዙ መልሶች ሊሰጡ ይችላሉ:: ዋናው ጉዳይ ግን ከዚህ በፊት የተቀላጠፈ አገልግሎት ይሰጥ የነበረ መሥርያ ቤት አገልግሎቱን የበለጠ ቀልጣፋ፣ የበለጠ ዘመናዊ፣ የበለጠ ተመስጋኝ ማድረግ ሲገባው ‹‹ታጥቦ ጭቃ›› መሆኑ በጣም የሚያሳዝን ነው::

አስታውሳለሁ የደርግ መንግሥት በኢሕአዴግ እንደተተካ ቦታውን ሙሉ ለሙሉ የተቆጣጠሩት የኢሕአዴግ ታጋዮች ነበሩ:: አሁንም ያሉት እነሱ ናቸው:: ያኔ በከፍተኛ ፍላጎት፣ ዲሲፕሊንና ቅልጥፍና ያገለግሉ የነበሩት ታጋዮች አሁን ተቀልብሰው ከደርግ የባሰ አገልግሎት መስጠታቸው ምን ይባላል?

ኢሕአዴግ ‹‹ያገኘነው ድል እንዳይቀለበስ እንታገላለን›› ይላል:: እንደውም አንድ ቱባ የኢሕአዴግ ባለሥልጣን ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ እንደሞቱ ‹‹ድላችን ከአለት የፀና በመሆኑ አይቀለበስም›› የሚል ንግግር አድርገዋል:: ይኸው ኢሚግሬሽን ቀልብሶታል::

ፓስፖርት የማግኘት መብት መሠረታዊ የዜግነት ግልጋሎት ነው:: መንግሥት/ኢሕአዴግ ይህንን መሠረታዊ የዜግነት ግልጋሎት በቅልጥፍና መስጠት ያልቻለው ለምንድን ነው?

ኢሕአዴግ ከ20 ዓመታት በላይ በሥልጣን በቆየባቸው ጊዜያት አግኝቻቸዋለሁ ያላቸው የፖለቲካና የኢኮኖሚ ድሎች ልክ እንደኢሚግሬሽን መሥርያ ቤት የማይቀለበሱበት ምን መተማመኛ አለ?

ኢሕአዴግ ዜጐች ቀና ብለው እንዲሄዱ ከውርደት እንዲላቀቁ እሠራለሁ ይላል:: ነገር ግን ዜጐች በየቀኑ በየሰዓቱ (አሁን ይህንን ስታነቡ ጭምር) በራሱ በኢሕአዴግ እየተዋረዱ ነው:: እህቶቻችን ያልፍልናል ብለው ከመላው ኢትዮጵያ አዲስ አበባ እየመጡ መሠረታዊ የዜግነት መገለጫ የሆነውን ፓስፖርት ለማግኘት በሚገጥማቸው እንግልት ላባቸውንና ሥጋቸውን ጨርሰው ያጠራቀሟትን ጥቂት ጥሪት ለአልጋ፣ ለትራንስፖርት፣ ለምግብ፣ ለሕክምና ወዘተ በማውጣት ሀብታቸውን ጊዜያቸውን አሟጠው ይበልጥ የሌላ ጥገኛ እንዲሆኑ ተዳርገዋል::

በማያውቁት ትልቅ ከተማ ውስጥ ራሳቸውን አግኝተው ለመደፈር፣ ለእንግልትና ለሁከት ተዳርገዋል:: ዓረብ አገር ሄደን ሠርተን ያልፍልናል የሚሉት ዜጐች በኢሚግሬሽን መሥርያ ቤት ራዕይ ማጣት፣ የሥራ ቅልጥፍና ጉድለትና አዳዲስ አሠራር ካለማየት እነሆ ከሕይወታቸው ከሦስት ወር እስከ ስድስት ወር ተነጥቀዋል:: ድህነትን ታሪክ አደርጋለሁ የሚለው ኢሕአዴግ ድህነትን በኢሚግሬሽን መሥርያ ቤት በኩል እያራዘመ ይገኛል::

አንድ ፓስፖርት ለማግኘት ዜጐች ከሦስት ወር እስከ ስድስት ወር የሚጠብቁት ለምንድን ነው?ምናልባት አንዳንድ ሰዎች ‹‹የፓስፖርት ፈላጊዎች ከተጠበቀው በላይ በመብዛታቸው ነው፤›› ሊሉ ይችላሉ:: ሌሎች ደግሞ፣ ‹‹ኢሕአዴግ በነፃ የመንቀሳቀስ መብት በመስጠቱ ነው›› በማለት አጉል ለመመፃደቅ የሚመኙ አሉ::

ነገር ግን መሥርያ ቤቱ ጊዜያዊ ሠራተኞችን በብዛት በመቅጠር፣ ያሉትን በማበረታታት፣ አስፈላጊ የኮምፒዩተር፣ የማተሚያ ፕሪንተርና ሌሎች ነገሮችን በመግዛት አዲስና ፈጣን አሠራሮችን በመዘርጋት ወንጀለኞች ፓስፖርት እንዳያገኙ ዘመናዊ ዘዴዎችን በመጠቀም፣ በሙያው ለረጅም ጊዜ ያገለገሉ ሠራተኞች በቁጥጥርና በክትትል ሙያ ላይ እንዲሰማሩ በማድረግና በሌሎችም አዳዲስ ዘመናዊ መንገዶች ይህ የተበላሸና አሳፋሪ አሠራር መቀየር አለበት::

ከዚህ በፊት በሦስት ቀንና ከዛ በላይ ፓስፖርት ይሰጥ የነበረ መሥርያ ቤት ከሦስት ወር እስከ ስድስት ወር ፓስፖርት

ለመስጠት ሲዘገይ አንድ መሠረታዊ ችግር እንዳለ መንግሥት/ኢሕአዴግ ሊገነዘብ ይችላል::

የመሥርያ ቤቱ የበላይ ኃላፊዎች ከዚህ በላይ አቅም የለንም የምንችለውን እያደረግን ነው የሚሉ ከሆነ ሌሎች ቦታውን ሊረከቡ ይችላሉ:: የልደትና የጋብቻ ሰነድ የሚያዘጋጀው ሌላው የኢሕአዴግ/መንግሥት መሥርያ ቤት በቅልጥፍናና በዘመናዊ አሠራሩ የተመሰገነ ነው:: ስለዚህ ልምዱንና ችሎታውን ለኢሚግሬሽን መሥርያ ቤት ሊያካፍል ይችላል:: አለበለዚያም ኢሕአዴግ የኢሚግሬሽን መሥርያ ቤትን በግብረ ኃይል፣ በዘመቻ አለበለዚያም በጥምር መምራት ይኖርበታል::

እነዚህ የተሻለ ሕይወት ፈልገው ለጋና ጣፋጭ ሕይወታቸውን ለመገበር ወደ ዓረብ አገር የሚሄዱ ወጣት ዜጐቻችን ዓረብ አገር ተዋርደው ሲኖሩ እዚህም ሌላ ውርደት ሊደርስባቸው አይገባም:: ብዙዎቹ ፊደል ያልቆጠሩ ጮርቃዎች በመሆናቸው ብሶታቸውን ባይገልጹም ማንም ሰው የነዚህን ልጃገረዶች ሰቆቃ ይረዳል:: ከዚህ በተጨማሪም እነዚህ ልጃገረዶች ደም ተፍተው፣ ተዋርደውና ማቀው ያገኙትን ዶላርና ድርሀም ወደ አገር ቤት ሲልኩ አገሪቷ ከሐዋላ ተጠቃሚ ነች:: ከሁሉም በላይ ዜጐች ናቸው:: መንግሥት ዜጐቹን እንዴት ነው የሚያየው? መንግሥት ለዜጐቹ ያለው ስሜትና ተቆርቋሪነት የሚታየው ከዚህ ጀምሮ ነው:: ችግሩን ከሥሩ ለማድረቅ ሥራ መፍጠሩና ዜጐች ለስደት የሚዳርጋቸውን ጉዳይ አጣርቶ መፍትሔ መስጠቱ እንዳለ ሆኖ ዜጐች ለፈለጉት ጉዳይ ከአገር ሲወጡ ቢያንስ በቀላሉ ፓስፖርት እንዲያገኙ ማድረግ መሠረታዊው የመንግሥት ኃላፊነት ነው::

የኢሚግሬሽን መሥርያ ቤት ኃላፊዎች ሌሎች ከኛ ያነሱ መንግሥታት ዜጐቻቸውን እንዴት እንደሚንከባከቡ ሳያዩ የቀሩ አይመስለኝም:: ያለበለዚያ እስኪ ሌሎች ፓስፖርት ለዜጐቻቸው እንዴት እንደሚሰጡ ይመልከቱ::

የኢሚግሬሽን መሥርያ ቤት በየቀኑ እየባሰበትና ከድጡ ወደ ማጡ ከመሆኑ ባሻገር ለሙስና የተጋለጠና ዜጐችን ለሰቆቃ፣ ለእንግልትና ለብክነት የዳረገ ሆኗል:: ኢሕአዴግ የኢሚግሬሽን መሥርያ ቤት ባለሥልጣናትን ያፈራቸዋል ልበል? ወይንስ እያየ እንዳላየ የሆነው ለምንድን ነው? በዚህ ዓይነት የኢሕአዴግ ሥራዎች በሙሉ እንደ ኢሚግሬሽን መሥርያ ቤት እንደማይቀለበሱ ምን ማስረጃና መተማመኛ?

መንግሥትን ታጥቦ ጭቃ ያደረገው የኢሚግሬሽን መሥርያ ቤት

Page 55: ERROR: The requested URL could not be retrieved ERROR The requested URL could not be retrieved While trying to process the request: TEXT HTTP/1.1 Host: Proxy-Connection: keep-alive

www.ethiopianreporter.com

ገጽ 7 | እሑድ | ጥር 19 ቀን 2005 ክፍል-2ማስታ

ወቂያ

እ ዚ ህ ች ላ ይ

የጤና ተቋማት የኅብረተሰቡን ጤና ለመንከባከብና ብሎም የጤና ችግሮችን ለማቃለል የሚሠሩ ቢሆኑም፣ እነኚህ ተቋማት በራሳቸው የአካባቢንና የኅብረተሰቡን ጤና በአደገኛነት ሊጎዱ የሚችሉ ቆሻሻዎች የሚወጡባቸው ሥፍራዎችም ናቸው:: በሕክምና ሒደት ውስጥ የሚወጡ (የሚመረቱ) ቆሻሻዎች በማንኛውም ሒደት ውስጥ ከሚወጡት (ከሚመረቱት) ቆሻሻዎች ይልቅ እጅግ አደገኛ የሆኑና ለተለያዩ በሽታዎችና ጉዳቶች የሚያጋልጡ በመሆናቸው ተገቢው ጥንቃቄና ትኩረት ተሰጥቷቸው ሊወገዱ ይገባል:: እንደኛ አገር ላሉ ታዳጊ አገሮች ደግሞ ያለው የሀብት ውስንነት ከነዚህ ተቋማት የሚወጣውን አደገኛ ቆሻሻ ለማስወገድ ተገቢውን ትኩረትና ቅድሚያ እንዳይሰጣቸው እንቅፋት ሆኗል:: ስለሆነም በእነዚህ ቀሻሻዎች የሚከሰተውን አደጋ ለመቀነስና እንዲሁም አደጋ ከደረሰብን በኋላም መወሰድ ያለባቸውን ጥንቃቄዎችና ዕርምጃዎች እንደሚከተለው እንመለከታለን::

በጤና ተቋማት ከሚወጡ (ከሚመረቱት) ቆሻሻዎች መካከል ከ75 በመቶ እስከ 90 በመቶ የሚሆኑት ጉዳት የለሽ ወይም አጠቃላይ የሚባሉት ቆሻሻዎች ናቸው:: የቀሩት 10 በመቶ እስከ 25 በመቶ የሚሆኑት ደግሞ አደገኛና (hazardous waste) ለተለያዩ በሽታዎችና ጉዳቶች ሊያጋልጡ የሚችሉ በመሆናቸው የአወጋገድ ሥርዓታቸው ጥንቃቄ የተሞላበትና በአግባቡ መሆን አለበት:: እነኚህ አደገኛ ቆሻሻዎች እንደየምንጫቸውና ጉዳታቸው በአጠቃላይ በዘጠኝ (9) ይከፈላሉ::

በሽታ አምጪ (Infectious waste) - በውስጣቸው በሽታ አምጪ ተህዋስያን ሊይዙ እንደሚችሉ የሚገመቱ ቆሻሻዎች በመሆናቸው ለተለያዩ ተላላፊ በሽታዎች የሚያጋልጡ ናቸው:: ለምሳሌ የላቦራቶሪ ቅሬቶች፣ ከተለዩ ክፍሎች (isolated room) የሚወጡ ቆሻሻዎች፣ የበሽተኛን ሰውነት ማፅጃ ጥጦች፣ ከበሽተኛ ጋራ ንክኪ ያላቸው የሕክምና መሣርያዎች፣ የበሽተኞች ዓይነምድር . . .

የሰውነት ቅሪቶች (Pathological waste) - ከሰው ሰውነት የሚወጡና ደም ነክ ቆሻሻዎች በመሆናቸው ለተለያዩ በደም ለሚተላለፉ በሽታዎች እንደ

የጤና ተቋማት ቆሻሻዎችና አወጋገዳቸው

ኤችአይቪና የጉበት በሽታዎች የሚያጋልጡ ናቸው:: ለምሳሌ የሰውነት ክፍል ቁራጭ፣ ደምና ሌሎችም ከሰውነት የሚወጡ ፈሳሾች . . .

ስለታማ (Sharps) - ስለታም መሣርያዎች ሰውነትን በመውጋት፣ በመቁረጥ ወይም በመቧጨርና በመቧጠጥ በሽታ የሚያስተላልፉ ናቸው:: ለምሳሌ መርፌ፣ ግሉኮስ መስጫ፣ ምላጮች፣ ቢላዎች . . .

የመድኃኒት ነክ ቆሻሻዎች (Pharmaceutical waste) - መድኃኒትና የመድኃኒት ቅሬቶችን የያዙ ቆሻሻዎች ናቸው:: ለምሳሌ የመጠቀሚያ ጊዜያቸው ያለፈ መድኃኒቶች፣ የተበላሹ መድኃኒቶች፣ ክትባቶች፣ መድኃኒቶች የሚታሸጉበት ብልቃጦች፣ ጠርሙሶች . . .

ዘረመል ላይ ችግር የሚያመጡ ቆሻሻዎች (Genotoxic waste) - የሰው ዘረመል ላይ የመርዛማነት ባህሪይ ያላቸው በመሆናቸው እጅግ አደገኛ የሆነ ጉዳትን የሚያስከትሉ ናቸው:: ለምሳሌ የካንሰር መድኃኒቶችና በነዚህ መድኃኒቶች የታከመ ሰው ትውከት፣ ተቅማጥ፣ ዓይነምድር . . .

ኬሚካል ቆሻሻዎች (Chemical waste) - የኬሚካል ንጥረ ነገር የያዙ ቆሻሻዎች ናቸው:: ለምሳሌ የላቦራቶሪ ምርመራ መሥርያ ኬሚካሎች የመጠቀሚያ ጊዜያቸው ያለፈ ኬሚካሎች (እንደ በረኪና) የተለያዩ ሶልቨንቶች፣ የነፍሳት ማጥፊያ ኬሚካሎች. . .

ብረት ነክ ቆሻሻዎች (Wastes with high content of heavy metals) - ከባድ ብረቶች በውስጣቸው የያዙ ቆሻሻዎች ናቸው:: ለምሳሌ ያረጁ ባትሪዎች የተሰበሩ የሙቀት መለኪያዎችና የደም ግፊት መለኪያዎች . . .

የታመቀ አየር መያዣ ቆሻሻዎች (Pressured containers) - በኃይለኛ ግፊት የታመቁ (የተሞሉ) ኮንቴነሮች:: ለምሳሌ የጋዝ ስሊንደር፣ የማደንዘዣ ስሊንደር . . .

ጨረር አፍላቂ ቆሻሻዎች (Radioactive waste) - ጨረራ ምንጭ ያላቸው ቆሻሻዎች ናቸው::

ለምሳሌ ጥቅም ላይ ያልዋሉ የራድዮቴራፒ ፈሳሾችና ማሸጊያዎቻቸው የተበከሉ መስታዎቶች . . .

በአጠቃላይ እነዚህ አደገኛ ቆሻሻዎች በሰውና አካባቢ ላይ ጉዳት የሚያደርሱት በሚከተሉት ምክንያቶች ነው::

በውስጣቸው በሽታ አምጪ ተህዋስ ስለሚይዙዘረመል ላይ የመርዛማነት ባህሪይ ስላላቸውበውስጣቸው አደገኛ መርዞችን፣ ኬሚካሎችንና

መድኃኒቶችን ስለሚይዙአደገኛ ጨረራ አፍላቂ ስለሆኑናስለታም መሣርያዎች ስለሆኑ ነው::በነዚህ አደገኛ ቆሻሻዎች ይበልጥ ለጉዳት ተጋላጭ

የሆኑት የኅብረተሰብ ክፍሎች በጤና ተቋማት ውስጥ የሚሠሩ የጤና ባለሙያዎች፣ የድጋፍ ሠራተኞች፣ የጥገናና የፅዳት ሠራተኞች፣ እንዲሁም በዚያው የሚገለገሉ በሽተኞችና ደንበኞች፣ ጠያቂዎችና አስታማሚዎች ናቸው::

በጤና ላይ የሚያደርሱት ጠንቅም ለተለያዩ ተላላፊ በሽታዎችና ለተለያዩ የካንሰር በሽታዎች ማጋለጣቸው ነው:: በሌላ በኩልም የአካል ጉዳት ያደርሳሉ፣ ዘረመል ላይ ችግር ያስከትላሉ፣ የአካባቢ ንፅህናን ያጎድፋሉ፣ ለከባድ ራስ ምታት ያጋልጣሉ፣ ለመተንፈሻ አካላት ጉዳቶችና በሽታዎች ያጋልጣሉ::

አግባባዊ አወጋገድና የሚያስፈልጉ ጥንቃቄዎችአደገኛ ቆሻሻዎች አግባብ ባለው መልኩ የማይወገዱ

ከሆነ ለምሳሌ ሜዳ ላይ መጣልና ያለአግባብ ለተጠቀሱት ጉዳቶችና በሽታዎች ያጋልጣሉ:: ስለዚህ አግባባዊ የሆነ የአወጋገድ ሥርዓት ያስፈልጋቸዋል:: አግባባዊ (ትክክለኛ) የጤና ተቋማት የቆሻሻ አወጋገድ ማለት እነዚህ ቆሻሻዎች የባለሙያውን እንዲሁም የኅብረተሰቡን ጤናና የአካባቢን ንጽህና እንዳይጎዱ የማድረግ ሒደት ነው:: ይህም ሒደት አራት ዋና ዋና ተግባራት አሉት፤ ቆሻሻን ከምንጩ መቀነስ (የቆሻሻን ምርት መቀነስ)፣ ቆሻሻዎችን በየዘርፋቸው መለየት፣

በጥንቃቄ ማጓጓዝና በአግባቡ ማከምና ማስወገድ ናቸው::

በተጨማሪም የጤና ባለሙያዎችና የፅዳት ሠራተኞችን ከብክለት ለመከላከል የሚከተሉትን ጥንቃቄዎች መውሰድ ያስፈልጋል::

ተገቢውን ሥልጠና መስጠት - ስለ አደገኛ ቆሻሻዎች በደንብ እንዲያውቁና እንዲረዱ፣ የሰውነት መከላከያ መሣርያዎችን በአግባቡ እንዲጠቀሙና ድንገተኛ አደጋ በሚደርስባቸው ወቅት መውሰድ ያለባቸውን ዕርምጃዎች እንዲያውቁ ለማድረግ፤

የሰውነት መከላከያ መሣርያዎችን በበቂ ሁኔታ ማቅረብ - የሚከተሉትን የመከላከያ መሣርያዎች መጠቀም እራስን ከብክለት ለመከላከል ይረዳል:: እንዳስፈላጊነታቸው ኮፍያ፣ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ፣ የዓይን መነፅር፣ ሙሉ የሰውነት መከላከያ ልብስ ማጥለቅ፤ ሽርጥ/ጋወን፣ የእግር ጫማ (ረጅም ቦቲ)፣ ጠንካራ የእጅ ጓንት ማድረግ ግን ግዴታ ነው::

የሥራ ላይ ደህንነት ፕሮግራም መተግበር - ለምሳሌ ክትባት እንደ ቲታነስ የመከላከያ መድኃኒት አቅርቦት (ከተጋለጡ በኋላ) . . .

ለአደጋ ከተጋለጡ በኋላ መወሰድ ያለባቸው ዕርምጃዎችም ቀጥለው የተመለከቱት ናቸው::

የመጀመርያ ዕርዳታ፣ ለሚመለከተው አካል ወዲያውኑ ሪፖርት ማድረግ፣ ከተቻለ ጉዳቱን ያደረሰውን ዕቃ ለተጨማሪ ምርመራ ማስቀመጥ፣ ተጨማሪ የሕክምና ዕርዳታ መጠየቅ፣ አስፈላጊ ከሆነ የደም ምርመራ ማካሄድ፣ ጉዳቱን (አደጋውን) መመዝገብ፣ አደጋውን ማጥናትና መለየት እንዲሁም የመከላከያ ዕርምጃዎችን መውሰድ ለወደፊት ተመሳሳይ ችግር እንዳይከሰት ያደርጋል::

(የኢትዮጵያ የምግብ፣ የመድኃኒትና የጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለሥልጣን)

ከአዘጋጁ፡- ባለሥልጣኑን በኢሜይል አድራሻው [email protected] ማግኘት ይቻላል::

Page 56: ERROR: The requested URL could not be retrieved ERROR The requested URL could not be retrieved While trying to process the request: TEXT HTTP/1.1 Host: Proxy-Connection: keep-alive

www.ethiopianreporter.com

ገጽ 8 | እሑድ | ጥር 19 ቀን 2005ክፍል-2

ማስታወቂያ

Page 57: ERROR: The requested URL could not be retrieved ERROR The requested URL could not be retrieved While trying to process the request: TEXT HTTP/1.1 Host: Proxy-Connection: keep-alive

www.ethiopianreporter.com

ገጽ 9 | እሑድ | ጥር 19 ቀን 2005 ክፍል-2ማስታወቂያ

Page 58: ERROR: The requested URL could not be retrieved ERROR The requested URL could not be retrieved While trying to process the request: TEXT HTTP/1.1 Host: Proxy-Connection: keep-alive

www.ethiopianreporter.com

ገጽ 10 | እሑድ | ጥር 19 ቀን 2005ክፍል-2

Ethiopian Catholic ChurchSocial Development Coordinating Office of Meki

Invitation for Bids (IFB)IFB No- ECC-SDCOM/03/2013

TO; ALL AUDITORS OF CATEGORY GRADE 1 WITH RENEWED LICENSE VALID FOR THE YEAR 2005 E.C.

ECC-SDCOM (Ethiopian Catholic Church Social Development Coordinating Office of Meki) is a faith based organization working in 3 Zones of Oromia Region, Arsi, West Arsi and part of East Shoa. The coordinating office is located at Meki, 130km south to Addis Ababa. In the year 2012, ECC-SDCOM has implemented 15 development projects with a total budget volume of Birr 57,173,316.08 with an average 10% administration expenses and 90% direct project expenses. According to the agreement we have with respective government offices, ECC-SDCOM would like to conduct an “Organizational Audit” by the external legal audit firm. Accordingly, ECC-SDCOM invites eligible auditors with grade 1 license to submit their price quotation for conducting an organizational audit.

Bidding process will be conducted through National Competitive bidding (NCB) procedures specified in FDRE procurement guidelines. It is open to all domestic audit firms having valid and renewal license for the fiscal year (2005 E.C)Price quotation must be delivered with sealed and stamped envelope to Ethiopian Catholic Church Social Development Coordinating Office of Meki compound, Office Room No, 6, Telephone No. + 251-22-118-0798, or +251-22-118-0193 P.O. Box 43 on or before February 6, 2013 at 12:00 am and will be opened on the same date February 6, 2013 at 2:30 pm in the presence of the bidders or their authorized representatives. Ethiopian Catholic Church Social Development Coordinating Office of Meki reserves the right to accept or reject any or all bids

Ethiopian Catholic Church Social Development Coordinating Office of MekiTelephone No + 251-22-118-07-98, or +251-22-118-0193

P.O. Box 43Meki, Ethiopia

የሚሸጡ ቤቶች ዝርዝር1. ለቡ አካባቢ ኢንዱስትሪ መንደር ቦታው 5000 ካሬ ስቶሩ 1500 ካሬ ሜትር ላይ ያረፈ ያለው

2. የቡና መሬት ሚዛን ተፈሪ ውስጥ 991 ሄክታር መሬት እና በ540 ሄክታር ላይ ተተከለ የ1፣

የ2፣ እና የ3 ዓመት እድሜ ቡና ያለው ማስፋፊያ 1000 ሄክታር መሬት ጋር

3. ጂ+3 ቦታው 250 ካሬ የሆነ አሚቼ አካባቢ

4. ሮፓክ ቪላ ቤት ያለው ቦታው 500 ካሬ የሆነ

5. ቦሌ ሆምስ ግቢ ጂ+1 አዲስ ቤት ያለው ቦታው 500 ካሬ ሜትር የሆነ

6. ሃይሌ ገ/ስላሴ መንገድ ከለም ሆቴል ከፍ ብሎ መንገድ ዳር ቦታው 450 ካሬ የሆነ

በመከራየት ላይ ያሉ ሱቆች ያሉት

7. ገላን ስቶር 500 ካሬ ላይ የዋለ ፊኒሺንግ የቀረው ቦታው 3000 ካሬ የሆነ በጥሩ ዋጋ

8. ቀበና ከእንግሊዝ ኤምባሲ አልፎ መንገድ ዳር ጂ+1 ፎቅ ቦታው ከ650 ካሬ

9. ዱከም ቦታው 5000 ካሬ 1000 ካሬ ላይ የዋለ መጋዘን ያለው ለፋብሪካ የሚሆን መብራት

የገባለት

10. ገላን አካባቢ የካርቶንና የሶፍት ወረቀት ፋብሪካ በመስራት ላይ ያለ ቦታው 10000 ካሬ ስፋት

1200 ካሬ ሜት መጋዘንና ጂ+2 ቢሮ በተጨማሪ 300 ካሬ ስቶር ያለው በሽያጭ ወይም

በጋራ ለመስራት የተመቻቸ

11. ሰበታ የከብት ርቢ በመስራት ላይ የሚገኝ ከሃያ በላይ ላሞች ያሉት

ማሳሰቢያ፡- ከእነዚህ ሌላ በተለያዩ አካባቢዎች የሚሸጡ ሆቴል፤ እንግዳ ማረፊያ (ገስት ሀውስ) አሉን

በሚፈልጉት አካባቢ የሚሸጡ መኖሪያ ቤቶች መንገድ ዳር ለፎቅ የሚሆኑ ቦታዎች ስላሉን

የሚከራይም ሆነ የሚሸጥ ቤት ካሎት ይደውሉ፣

አድራሻ፣ ስልክ፡- 0911 21 12 67 ወይም 0911 22 08 22

ኢ-ሜይል፣ [email protected] or [email protected]

ማስታወቂያ

Page 59: ERROR: The requested URL could not be retrieved ERROR The requested URL could not be retrieved While trying to process the request: TEXT HTTP/1.1 Host: Proxy-Connection: keep-alive

www.ethiopianreporter.com

ገጽ 11 | እሑድ | ጥር 19 ቀን 2005 ክፍል-2ማስታወቂያ

የስብሰባ ጥሪሐበሻ ሲሚንቶ አክሲዮን ማህበር

የሐበሻ ሲሚንቶ አክሲዮን ማህበር በንግድ ህጉ አንቀጽ 391 (1)፣392፣418፣419 እና 423 መሰረት እንዲሁም በማህበሩ መተዳደሪያ ደንብ አንቀጽ 9 እና 10 መሰረት ባለአክሲዮኖች 3ኛ መደበኛ እና 2ኛ ድንገተኛ ጠቅላላ ጉባኤ ቀደም ሲል ሊካሄድ የነበረበት ቀን ከፍተኛ ባለአክሲዮኖች ቀኑ እንዲቀየርላቸው ባቀረቡት ጥያቄ መሰረት እሁድ ጥር 19 ቀን 2005 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ጀምሮ አዲስ አበባ እስታዲየም በትንሿ አትሌቲክስ ሜዳ ይካሄዳል፡፡

በመሆኑም ባለአክሲዮኖች በተጠቀሰው ቦታ እንዲገኙ ተጋብዘዋል፡፡

የባለአክሲዮኖች 3ኛ መደበኛ እና 2ኛ ድንገተኛ ጠቅላላ ጉባኤ አጀንዳዎች

1ኛ) የመደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ አጀንዳዎች

1. ረቂቅ አጀንዳ ማጽደቅ

2. የዳሬክተሮች ሪፖርት መስማት

3. የውጭ ኦዲተሮች ሪፖርት መስማት

4. በቀረቡት ሁለት ሪፖርቶች ላይ ተወያይቶ መወሰን

5. የዳሬክተሮች ቦርድ አባላትን መምረጥ

6. የውጭ ኦዲተሮችን መምረጥ እና አባላቸውን መወሰን

7. የጉባኤውን ቃለጉባዔ ማፅደቅ

2ኛ) የድንገተኛ ጠቅላላ ጉባኤ አጀንዳ

1. አጀንዳ ማጽደቅ

2. በመተዳደሪያ ደንቡን እና የመመስረቻ ጽሑፉን ስለማሻሻል

3. የጉባኤውን ቃለጉባኤ ማጽደቅ

ማሳሰቢያ

በስብሰባው ላይ መገኘት የማይችሉ ባለአክሲዮኖች፤ - በንግድ ህጉ አንቀጽ 402 መሰረት ጉባኤው ከሚካሄድበት 3

የስራ ቀናት በፊት ወሎ ሰፈር አምባሰል ህንጻ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 108 በሚገኘው የዋና መስሪያ ቤቱ ጽ/ቤት በመገኘት የውክልና መስጫ ቅጽ በመሙላት ተወካዮች እንዲገኙ ማድረግ የሚቻል መሆኑን እንገልጻለን፡፡ ወይም

- ስልጣን በተሰጠው አካል የተረጋገጠ የውክልና ስልጣን የተሰጣቸው ተወካዮች በስብሰባው ላይ ባለአክሲዮኖችን ወክለው ለመገኘት እንደሚችሉ እናሳውቃለን፡፡

ባለአክሲዮኖች የከፈሉበትን ደረሰኝ፣ መታወቂያ ወይም የባለአክሲዮንነት ሰርተፍኬት ይዘው እንዲገኙ እናሳስባለን፡፡

ሐበሻ ሲሚንቶ አክሲዮን ማህበር የዳሬክተሮች ቦርድ

Invitation to Bid External AuditAfar Pastoralist Development Forum (APDF) is an indigenous, secular, non-profit, regional consortium of charities/CSOs operating in Afar Region, APDF wishes to invite interested audit firms to participate in auditing of the organization for the year ending December 31, 2012.The Audit shall be conducted at APDF office located at Afar Regional State Logya City. APDF location will be advised in detail for winning bidders.

The Audit Firm must meet the following requirements: 1. Registered by the Office of General Auditor of Ethiopia 2. Renewed business license 3. Having a TIN Number 4. Experience evidence in auditing of CSO’s

International audit firms who fulfill the above requirements can submit the bid in a sealed envelope to the address indicated below within ten days of this announcement.

Pastoralist Forum Ethiopia P.O.Box 364 Code 1250Addis Ababa, Ethiopia Tel: +251 (011) 552 45 82Fax: +251 (011) 552 45 82

የሉሲ ኢንሹራንስ አ.ማ. ባለአክሲዮኖች 2ኛ ድንገተኛ ጠቅላላ ጉባኤ የስብሰባ ጥሪ

የሉሲ ኢንሹራንስ አ.ማ የባለአክሲዮኖች 2ኛ ድንገተኛ ጠቅላላ ጉባዔ ቅዳሜ የካቲት 2 ቀን 2005 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ጀምሮ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጠመንጃ ያዥ ቅርንጫፍ አጠገብ ሙጂብ ሕንፃ ላይ በሚገኘው ዋና መ/ቤታችን ውስጥ ይካሄዳል:: ስለሆነም የኢንሹራንሱ ባለአክሲዮኖች ወይንም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በጉባዔው ላይ

እንዲገኙ የኢንሹራንሱ የዳይሬክተሮች ቦርድ ጥሪ ያቀርበል፡፡

የድንገተኛ ጉባዔው አጀንዳዎች• የጉባዔውን አጀንዳ ማፅደቅ፣

• በ1ኛ ድንገተኛ ጠቅላላ ጉባዔ ላይ በተላለፈው ውሳኔ መሠረት ውሳኔ የሚሹ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ማፅደቅ፣

• የጉባዔውን ቃለ-ጉባዔ ማፅደቅ

ማሳሰቢያ፣

በጉባዔው ላይ መገኘት የማይችሉ ባለአክሲዮኖች ጉባዔው ከሚካሄድበት ሦስት የሥራ ቀናት በፊት በዋናው መ/ቤታችን ውስጥ በመገኘት የውክልና ፎርም/ቅፅ በመሙላት ወይንም ውል ለማዋዋል ስልጣን በተሰጠው አካል ፊት የተሰጠ በስብሰባው ላይ ለመገኘትና ድምጽ ለመስጠት የሚያስችል የውክልና ሰነድ ዋናውንና አንድ ቅጅ በጉባዔው ዕለት

በማቅረብ በጉባዔው መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

የሉሲ ኢንሹራንስ አ.ማ. የዳይሬክተሮች ቦርድ

Page 60: ERROR: The requested URL could not be retrieved ERROR The requested URL could not be retrieved While trying to process the request: TEXT HTTP/1.1 Host: Proxy-Connection: keep-alive

www.ethiopianreporter.com

ገጽ 12 | እሑድ | ጥር 19 ቀን 2005ክፍል-2

ማስታወቂያ

ዲኬቲ ኢትዮጵያ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ሲሆን በተለያዩ የመገናኛ ብዙኃን ዘርፎች ህብረተሰቡ በቤተሠብ ምጣኔ ፣ በኤች አይ ቪ ኤድስ መከላከል ፣ በህጻናት ጤና ላይ ግንዛቤውን እንዲያሳድግ እያደረገ ይገኛል ፡፡ ይህን ፅሁፍ ለአንባቢያን ሲያቀርብም ከፍተኛ ደስታ ይሰማዋል ፡፡

ችሎትፈጣሪ ከግራና ከቀኝ በመላዕክቱ ታጅቦ ከተቀመጠበት ችሎት ፊት ለፊት የአንድ ሰውዬ ነፍስ እየጮኸች ‹‹ጌታ ሆይ ፍረድባቸው! ..እነዚህን ዓለማውያን ቅጣቸው! አንተ ንፁህ አድርገህ ከፈጠርከኝ ወዲያ አበላሹኝ ! ለኤች አይ ቪ ሰጡኝ ! በነሱ ጦስ እኔ በሃጢያት ጐደፍኩ! እባክህ አምላኬ ስለወንጀላቸው በይንባቸው !›› ትላለች፡፡ ተክሳሾቹ ጆሮዎች፣አይኖች፣አፍንጫ፣ከንፈሮች፣እጆች፣ እግሮችና ሃፍረተ ስጋ ድንግጥ እንዳሉ ከፍርድ ሸንጐው ቆመዋል ፡፡ ፈጣሪ የነፍስን አቤቱታ ከሰማ በኋላ ‹‹ ነፍስ ስለምትለው ምን ምላሽ አላችሁ ? ›› ሲል የመጀመሪያውን ጥያቄ ለጆሮዎች አቀረበ ፡፡ጆሮዎች መልስ ከመስጠታቸው በፊት በጭንቅላት ውስጥ ለውስጥ በሚገናኙበት የስልክ መስመራቸው በሹክሹክታ እንዲህ ተባባሉ ፡፡ ‹‹ ስማ....›› ‹‹ሰማሁ›› ‹‹እኛ ሴንሴሸን፣ ህይወት ትረስት፣ ሜምበርስ ኦንሊ ስለሚሏቸው ኮንዶሞች የሰማን ቢሆንም ሽምጥጥ አድርገን መካድ አለብን ፡፡ አለበለዚያ በኛ ይፈረዳል ›› ተባባሉና ችሎቱ የነሱን ምላሽ እየጠበቀ ስለነበር በጆሮኛ ‹‹ ክቡር ፍርድ ቤት እኛ ተስረቅራቂና ያሬዳዊ ቅላፄ ያለው እንደ ሞዛርትና ቬትሆቨን ዜማ የሚማርክ የሴት ልጅ ድምፅ ሰምተን ከመመሰጥ በቀር ምንም ያጠፋነው ነገር የለም ፡፡ እንደጠረጠርነው ግን ለነፍስ ክስ ተጠያቂዎቹ አይኖች ሳይሆኑ አይቀሩም አሉ ፡፡ ዓይኖች በድንጋጤ ፈጠጡ ፡፡ አይቻልም እንጂ ጆሮዎችን ፊት ለፊት ማየት ቢችሉ ሃይለኛና እሳታማ ጨረር ለቅቀው ቢያቃጥሏቸው በወደዱ ነበር ፡፡ ከብስጭታቸው በረድ ሲሉ በአፍንጫ አንገት በኩል አድርገው በሹክሹክታ እንዲህ ተባባሉ ፡፡‹‹ ወንድሜ … አቤት ! እኛ ኮምባይንድ እንክብል የሚሉትን በየወሩ የሚወሰድ የወሊድ መከላከያ ኪኒን ፣ አይ ዩ ሲዲ ብለው የሚጠሩትን ከ10 እስከ 12 ዓመት የሚያገለግል ሉፕ ዩኬር ያሉትን ለ5 ዓመት ወሊድ ለመቆጣጠር የሚጠቀሙበትን እንዲሁም ኢንፕላንት ያሉትን የወሊድ መከላከያ ሁሉ ብናይም በዚህ ችሎቱ ላይ መካድ አለብን ፡፡ በየመንገዱ የተፃፉትም የተሳሉትም የኮንዶም ማስታወቂያዎች የስነ-ተዋልዶ በራሪ ወረቀቶች አላየንም እንበል ፡፡ አለበለዚያ ዘብጥያ መውረዳችን አይቀርም ፡፡ ›› ተባባሉ ፡፡ ጌታ የችሎቱ ዳኛ ፡፡ ‹‹ እህስ ዓይኖች ምን ትላላችሁ ›› ሲላቸው እንዲህ መለሱ፤ ‹‹ የተከበረው ታላቁ ፍርድ ቤት እኛ በጣም የምታምር፣ፀጉሯ ሃር የመሰለ ውብ፣ ጡቶቿ ጉችጉች ያሉ ፣ የኮራ ዳሌ ያላት ፣ ሴት ተመልክተን ከመዋለል በስተቀር ምንም አላጠፋንም ፡፡ ይልቅዬ

ይሄ ከመሃላችን ተነስቶ ቁልቁል የተጋደመው አፍንጫ አንዳች ጥፋት ሳይሰራ አይቀርምና እሱ ይጠየቅ ›› አሉ ፡፡ አፍንጫ ተበሳጨ በዓይኖች ክስ አዘነ… በአፍንጫ ልቡም ‹‹ እንዲህ ካሉ ምቀኛ ጐረቤቶች ይሰውረን ›› አለ ፡፡ ንዴት እየሰነፈጠውም ‹‹ የተከበረው ፍርድ ቤት እኔ ማራኪ የሴት ገላ ጠረን ፣ ምርጥ መዓዛ ያለው ሽቶ ፣ ደስታን የሚሰጡ የፀጉር ላይ ቅባቶችና ሻምፑዎች ከማሽተትና ከመደሰት በስተቀር ምን ስህተት ሰራሁ ? ነገር ግን ለነፍስ ክስ ዋና ተጠያቂ ከበታቼ የተነባበሩት ከንፈሮች ሊሆኑ ይችላሉ ! ….›› ከማለቱ ከንፈሮች ተርገበገቡ ! ተጋጩ ! አይቻልም እንጂ ቢሆን ኖሮ ከላያቸው ሆኖ የሚያሳብቅባቸውን አፍንጫ አውርደው እወለሉ ላይ ቢፈጠፍጡት ደስታቸው ልዩ ይሆን ነበር፡፡ ‹‹ እህስ ከንፈሮች መልስ አላችሁ ? ›› ፈጣሪ ዳኛ ጠየቀ ፡፡እነርሱም እየተላተሙና እየተላቀቁ ‹‹ ታላቁ ፍርድ ቤት ሆይ እኛ ከእኛው አምሳያ ጋር ከመሳሳም ባለፈ ይሄ ነው የሚባል የሚያስወቅሰን የሚያስከስሰን ጉዳይ የለም›› ከማለታቸው አፍንጫ እየተነፋነፈ ‹‹ እንዴ እንዴ ክቡር ፍርድ ቤት ትዝ አለኝ ፡፡ ከንፈሮች ከንፈሮችን ከመሳም ባለፈ የሰራነው ስህተት የለም ቢሉም ሌላም ጥፋት አለባቸው ›› አለ ፡፡ ዳኛው ፈጣሪም ‹‹ ሌላ የምትለውን የከንፈሮች ጥፋት ተናገር ›› አለው ፡፡አፍንጫ እየተጣደፈ ‹‹ ከንፈሮች ወንጀለኛ ደብቀዋል የተባባሪያቸው የምላስ ምሸግ ሆነዋል ... ክቡር ፍርድ ቤት ምላስ በከንፈሮች በኩል ብቅ እያለች የቆጥ የባጡን እየቀባጠረች ብዙ ሴቶችን አታለለች ፡፡ ኮንደም ምን ያደርጋል የምን ወሊድ መከላከያ ኪኒን ነው በማለት የስንቶቹን ዓላማና ራዕይ አስታለች የስንቷን ገላ ልሳለች አንደእኛ ችሎቱ ፊት ያልቆመችውን ምላስ አሁንም ቢሆን ከንፈሮች ተገልጠው ሊያጋልጧት ይገባል ›› ሲል ተናገረ ፡፡ ይሄኔ ምንም መጥሪያ ሳይላክላት ከንፈሮችም ‹‹ ምላስን ደብቃችኋል ወይ ? ›› ተብለው የእምነት ክህደት ቃላቸውን ሳይጠየቁ ምላስ ከንፈሮችን ጥሳ ወጣችና ወዳጋለጣት አፍንጫ እጥፍ ብላ በሾለ ጫፏ ልትወጋው እየጣረች ‹‹ አንተ ትንፋሻም ምኑንም ምናምኑንም እያሸተትክ ስታስልሰኝ የኖርከው ፡፡ አንተ እያለህ በኔ ላይ ሁለት አፎችህን ትከፍታለህ ›› በማለት ተንጣጣችበትና ‹‹ ክቡር ፍርድ ቤት አፍንጫ እንዳለው ምላሳዊ ተግባርን ማከናወን እምኑ ላይ ነው ወንጀሉ ? ደግሞም አፍ ውስጥ ሆኜ አፍንጫ ሲናገር እንደሰማሁት ከንፈሮች እየተከፈቱ ባያስወጡኝ ኖሮ ከቤተሰቦቼ ከጥርሶች ጋር በፍቅር እኖር አልነበርን ?

ለነፍስ ክስ ተጠያቂ ሊያደርገኝ የፈለገው አፍንጫስ የት አባቱ ያውቀኝ ነበር ›› አለችና ሹል ጫፏ የላይኛውንና የታችኛውን ከንፈር ነካ ነካ በማድረግ ‹‹ እነዚህ ናቸው ጦሶኞቹ ›› ብላ ወደ አፍ ውስጥ ምልስ አለች፡፡ ከንፈሮች የጥርስ ስልጣን ተሰጥቷቸው ቢሆን ኖሮ ምላስን ቅርጥፍጥፍ አድርገው ቢያኝኳት ደስታቸውን አይችሉትም ነበር ፡፡‹‹ አንቺ ከሃዲ ቀዥቃዣ በሹል ጫፍሽ እየጣስሸን የምትወጪው በኛ ፍቃድ ነበርን ? ቆይ ከእንግዲህ መውጫሽን ታገኛታለሽ ፡፡ ›› በማለት ተናግረው ሲያበቁ የላይኛውና የታችኛው ከንፈር ጥቂት ተመካከሩና ‹‹ ይልቅስ ነፍስ ለደረሰባት በደል ተጠያቂ ማድረግ የሚገባት እጆችን ነው ….›› ከማለታቸው የችሎት አዳራሹ በጭብጨባ ቀለጠ ፡፡ አጫብጫቢዎቹ እጆች በንዴት እስኪቀሉ ድረስ ተላተሙ ተላተሙና ችሎቱ ዳኛ ፈጣሪ ጠረጴዛውን በመዶሻው ‹‹ ስነ ስርዓት›› እያለ ሲመታ ሁለቱም እጆች ተጣብቀው ፀጥ አሉ፡፡ በዚያው በተገናኙበት ፍጥነትም ዝግ ባለ ድምፅ መወጋገዝ መወቃቀስ ያዙ ፡፡ ቀኝ እጅ ግራን እንዲህ አለው ‹‹ አንተ ግን አገልግሎት ያልጨረሰ ኮንደም ከሃፍረተ ስጋ ላይ አውልቀህ ወርውረህ የለ … ›› ግራም በተራው ቀኝን እንዲህ አለው ፡፡ ‹‹ አንተስ ብትሆን የሆነ የወሊድ መከላከያ ኪኒን እንደ አልባሌ እቃ ወዲያ አሸቀንጥረህ የለ ፡፡ የማስተማሪያ ፖስተር አልቀደድክም ? አንተስ ስለኤች አይ ቪ የሚመክር በራሪ ወረቀት አልወረወርክም ›› ከተባባሉ በኋላ ‹‹ በል .... በል አሁን እኛ ብንጨቃጨቅ ዋጋ የለውም ስህተታችንን ዋጥ፣ በችሎቱ ብንጠየቅም ሽምጥጥ ካድ ማድረግ ነው ያለብን ‹ እጅ ቢያብር … › የተባለውን ተረት አልሰማህም …. ሰምቼአለሁ ›› ተባባሉና የእነሱን መልስ ወደሚጠብቀው ችሎት ዞረው ወደላይ ተዘርግተውና ጣቶቻቸውን አንጨፍረው ‹‹ እጅግ በጣም የተከበረው ፍርድ ቤት ዋና ችሎት ! እኛ ለስላሳ የሴት ገላና ፀጉር ከመደባበስ ፣ ጉችጉች ያሉ ጡቶችን ከማሻሸት ውጪ ከንፈሮች ቢያሳብቡብንም ተጠያቂ የምንሆንበት አንዳች ጉዳይ የለም .. ይልቅስ መጠርጠር ካልቀረ እግሮችን ነው ›› ሲሉ እነሱም ጭምር ባላወቁት ሁኔታ ከችሎቱ ሲርቁ ተሰማቸው ፡፡ እግሮች የተሸከሙትን ሁሉ ይዘው ወደ ችሎት አዳራሹ መውጪያ ሲሮጡ ከመላዕክት አንዱ ከበራፉ የነበረው አስቆማቸውና ወደ ችሎቱ መለሳቸው ፡፡ ባጋጣሚው በእግሮች ተሳፍረን ከአዳራሹ ወጣን ከተጠያቂነት አመለጥን! ብለው የነበሩት ጆሮዎች፣አይኖች፣አፍንጫ፣ ከንፈሮች ምላስ

፣ እጆች፣ ራሳቸው እግሮችም የማምለጥ ጥረቱ ባለመሳካቱ ኩምሽሽ አሉ ፡፡ እግሮች በነፍስ ክስ ተጠያቂ ባሏቸው እጆችና ከበር በመለሳቸው መልአክ እያዘኑ ‹‹ የተከበረው ፍርድ ቤት ›› ከማለታቸው ሌሎቹ ሳቅ እፍን አደረጋቸው ፡፡ ችሎት ደፍረው ከፈረጠጡና ተይዘው ከተመለሱ ወዲያ ‹‹ ክቡር ፍርድ ቤት እኛ ወደ አልቤርጐዎች ከመራመድ በቀር ለነፍስ ክስ ተጠያቂ አይደለንም … ንፁህ ሆኜ ተፈጥሬ በሃጢያት ረከስኩ ለምትለው ነፍስ ክስ ከማንም ከምንም በላይ በመካከላችን የሚኖረው ሀፍረተ ስጋ መወንጀል አለበት ፡፡ እሱ ራሱ ነው ስህተተኛው ›› ብለው ዝም ሲሉ ሃፍረተ ስጋ በድንጋጤ ኩምሽሽ ካለ ወዲያ ፀፀት ቢጤ ገባው ፡፡ ሴንሼሸን ፣ ህይወት ትረስት ፣ ኮፊ … እየተባለ በአይነት በአይነቱ በዲኬቲ ኢትዮጵያ የቀረበ ኮንደም ሲመጣልኝ መች ተጠቅሜ አውቃለሁ ፡፡ ራቁቴን ግንኙነት ከማደርግ ‹ እምቢዮ ያለ ኮንደም አልሰራም › ብዬ ቅዝቅዝ ብል ኖሮ ይሄ ሁሉ ጦስ አይመጣም ነበር ›› ብሎ ለራሱ ብቻ በሚሰማ ድምፅ ተናገረና ችሎቱ ፊት ግን ይሄን ባወራ ተቆርጦ ወዲያ ይጣል ተብሎ ይበየንብኛል ሲል ሰጋ ፡፡ እናም ‹‹ በጣም የተከበረው ፍርድ ቤት እኔ ምን አጠፋሁ ከተቃራኒዬ ጋር ግንኙነት ከመፈፀም ወዲያ ምን በደል ተገኘብኝ ›› ብሎ አንገቱን ደፋ ፡፡ በችሎቱ የከሳሽም የተከሳሾችም ቃል ተሰምቶ አበቃ ፡፡ የሁሉም ጉዳይ በጥሞና ተሰምቷል ፡፡ አሁን የሚጠበቀው የፈጣሪ የፍርድ ውሳኔ ሆነና አዳራሹ በፍርሃት፣ በሚያስፈራ ዝምታና በሚያሳቅቅ ስጋት ተዋጠ ፡፡ ችሎቱ ውሳኔ አስተላለፈ ፡፡ የፈጣሪ ቃል እንዲህ ተሰማ ፡፡ ‹‹ ጆሮዎች ለተስረቅራቂ ድምፆች ፣ ዓይኖች ለማራኪ ውበቶች ፣ አፍንጫ ለመዓዛ ዓይነቶች፣ ከንፈር ለከንፈሮች ፣ ምላስ የተገኘን ሁሉ ለመላስና እንዳሻሽ ለመቀባጠር ፣ እጆች ለለስላሳ ገላዎች ፣ እግሮች ለአልጋ ቤቶች ፣ ሀፍረተ ስጋም ለሀፍረተ ስጋዎች ሁሉ ባትማረኩ! መወሰን መታቀብ ብታወቁ እስከ ንስሃ ዘመናችሁ በመጠቀም እድሜያችሁን ብታስረዝሙ በነፍስ ክስ ከችሎቴ ባልቆማችሁ ነበር ፡፡ የሁላችሁም ስህተት ህብር ፈጥሮ ነፍስን አጐድፏታል ፡፡ ስለሆነም ሞት በሁላችሁም ፈርጃለሁ ! ›› ሲል ሁሉም አገልግሎታቸውን አቆሙ ፡፡ ከሳሿ ነፍስ በውስጡ የነበረችው የተከሳሽ ስጋ ባለቤት የሆነው ሰውዬ ሞተ ፡፡ በችሎቱ ሌላ ተጨማሪ ትዕዛዝ ተሰማ ፡፡ ‹‹ ዛሬ በፍርድ ቤቱ ያልተገኙት ፣ ስለወሊድ መከላከያ ፣ ስለቤተሰብ ምጣኔ አገልግሎት ሲነገር ሰምተው እንዳልሰማ አይተው እንዳላየ የሆኑት ፣ ዛሬ ከተፈረደባቸው ጋር የተመሳሰለ ወንጀል የሰሩትና እየሰሩም ያሉት ፣ ፈጥነው ያልታረሙት ፣ በሌሉበት ሞት ተፈርዶባቸዋል ፡፡ ›› መዶሻው ጠረጴዛውን መታ ፡፡

…… ተፈፀመ ……

የጨረታ ማስታወቂያ

የኢትየጵያ አረጋውያን እና ጡረተኞች ብሔራዊ

ማህበር ጽ/ቤት ሐምሌ 1/2003 እስከ ሰኔ

30/2004 ያለውን ሂሣብ በአንድ በውጭ ኦዲተር

ለማስመርመር፡-

• የሙያ ማስረጃ ያለው

• ሕጋዊ ፈቃድ ያለው

• የግብር ከፋይ መለያ ያለው

• የዘመኑ የታደሰ ፈቃድ ያለው

• ደረጃው ‘B’ የሆነ

ሂሣቡን ኦዲት በሚያደርገበት ዋጋ በሰም በታሸገ

ኤንቬሎፕ እስከ 24/06/2005 ዓ.ም. እንዲቀርብ

ሆኖ፣ ጨረታው የሚከፈተው በ27/06/2005

በ3፡30 ሰዓት መሆኑን እናስታውቃለን፡፡

INVITATION TO BID No. LITB-2013-9105275

For Long-Term AgreementUNICEF Ethiopia Office wishes to enter into a Long-Term Agreement to procure various types of Office Furniture.

Interested and eligible bidders are invited to collect the complete tender document at the address below starting from 29/01/2013. Formal offers return dates are indicated on the bid documents for each of the above listed items.

UNICEF reserves the right to accept or reject any part or the entire bid.

For further information and queries, please contact TegestZeleke

UNICEF ETHIOPIA,Kasanchisnext to Intercontinental Hotel, adjacent to German

House (GTZ)(New building, Supply Section 1st floor, Room No. 108)

P.O.BOX 1169TEL: 011 518 41 61 , 011518 40 00,

ADDIS ABABA, Ethiopia

Page 61: ERROR: The requested URL could not be retrieved ERROR The requested URL could not be retrieved While trying to process the request: TEXT HTTP/1.1 Host: Proxy-Connection: keep-alive

www.ethiopianreporter.com

ገጽ 13 | እሑድ | ጥር 19 ቀን 2005 ክፍል-2ማስታወቂያማስታወቂያ

Call for ProposalRFP/2013/02

UNDP Ethiopia is intended to recruit consultants for MID-TERM REVIEW CONFLICT PREVENTION .To this effect, firms legally established are kindly invited to submit your technical and financial Proposal in a separate envelope to the address indicated below: Proposals may be submitted on or before Thursday, January 31, 2013and via email, courier mail or fax to the address below:Interested firms can download and obtain the details RFP document from the following linkshttps://www.ungm.org/Notices/Item.aspx?Id=23497or you can contact [email protected] to get the softcopy of the RFP through email.

United Nations Development ProgrammeProcurement Unit UNECA PremisesOld Building 6th Floor, Africa HallTel:0115444352P.0.Box 5580Addis AbabaEthiopia

Your Proposal must be expressed in the English , and valid for a minimum period of 90 days

The interested firms should submit in two envelopes (a) a technical proposal; and (b) a financial proposal based on the RFP document through our secured e-mail: [email protected] hand delivery to above address before Thursday, January 31, 2013In the course of preparing your Proposal, it shall remain your responsibility to ensure that it reaches the address above on or before the deadline. Proposals that are received by UNDP after the deadline indicated above, for whatever reason, shall not be considered for evaluation. If you are submitting your Proposal by email, kindly ensure that they are signed and in the .pdf format, and free from any virus or corrupted files.

For Details you may contact: [email protected] or [email protected]

ማስታወቂያ በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፖሊስ ኮሚሽን የደሴ ከተማ

አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ የ2ኛ/መም ፖሊስ ጣቢያ በቁጥር

ህአወ-16/18/2005 በቀን 16/12/2004 ዓ.ም በፃፈው ደብዳቤ

በደሴ ከተማ ቀበሌ 06 ልዩ ስሙ መናኽሪያ ኮንዶሚኒየም ቤት

ፊት ለፊት አካባቢ አራስ ልጅ ጥላ መጥፋቷን ገልጾ ጽፏል፡

፡ ስለዚህ የሕፃኑ ወላጆች ነን ወይም ወላጆቹን እናሳውቃለን

የሚል ካለ ከታች በተገለፀው አድራሻ በአካል በመቅረብ

እንድታሳውቁን በትህትና እንጠይቃለን፡፡

አድራሻ፡- የተከፈተ አይን ሁለንተናዊ አገልግሎት ደሴ ከተማ

ቀበሌ 08 ልዩ ስሙ መናፈሻ አካባቢ

ስልክ ቁጥር 0920 85 64 94

ጥር 15 ቀን 2005 ዓ.ም

በኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን የቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ

ጽ/ቤት በቁጥር የቢሾ/2-8/446/05 በቀን 26/05/2005 ዓ.ም

በተፃፈ ደብዳቤ ዕድሜው በግምት 10 ቀን የሆነውን ወንድ

ሕፃን በቀን 28/02/2004 ዓ.ም 5፡30 ሰዓት ሲሆን በቢሾፍቱ

ከተማ ቀበሌ 10 የቦታው ልዩ ስም ከታ ተብሎ በሚጠራው

ቦታ ወንድሟ ሃምሣ አለቃ አለሙ ጉታ በመኖሪያ ቤት ውስጥ

ወ/ሮ ልኬ ጉታ የተባለች የሕፃን ኢፋ ቢሾፍቱ ወላጅ እናት

ጥላ የጠፋች መሆኑን ፖሊስ ገልጿል፡፡ ስለዚህ የሕፃኑን ወላጅ

እናት እናውቃለን የሚል ካለ ከታች በተገለጸው አድራሻ በአካል

በመቅረብ እንድታሳውቁን በትህትና እንጠይቃለን፡፡

አድራሻ፡- ኪንግደም ቪዥን ኢንተርናሽናል ልዩ ስሙ ቶሚ

ኢንተርናሽናል ሆቴል አቅራቢያ ቢሾፍቱ

ስልክ 0911 95 91 71

ጥር 15 ቀን 2005 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን የቦሌ ክፍለ

ከተማ ፖሊስ መምሪያ 02 በቁጥር 2073/03/05 በቀን

08/01/2005 ዓ.ም በፃፈው ደብዳቤ በተቋሙ ሕፃን አማኑኤል

ተብሎ ስም የወጣለት ፆታ ወንድ ዕድሜ 10 ቀን የሆነው በቦሌ

ክፍለ ከተማ ወረዳ 13 ልዩ ቦታው የፖይለት አሶሴሽን ቦሌ

ሆምስ ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ 03፡15 ሰዓት በ29/12/2004

ዓ.ም ካፒቴን እንድሪስ ጀምበሬ ተሰማ በተባለ የተገኘ መሆኑን

ፖሊስ ገልጿል፡፡ ስለዚህ የሕፃኑ ወላጆች ነን ወይም ወላጆቹን

እናውቃለን የሚል ካለ ከታች በተገለፀው አድራሻ በአካል

በመቅረብ እንድታሳውቁን በትህትና እንጠይቃለን፡፡

አድራሻ፡- ክበበፀሐይ የሕፃናት ማሳደጊያ በተለምዶ አፍንጮ

በር አካባቢ አዲስ አበባ

ስልክ ቁጥር 011 4 16 99 45

Page 62: ERROR: The requested URL could not be retrieved ERROR The requested URL could not be retrieved While trying to process the request: TEXT HTTP/1.1 Host: Proxy-Connection: keep-alive

www.ethiopianreporter.com

ገጽ 14 | እሑድ | ጥር 19 ቀን 2005ክፍል-2

ጠ ለ ስ

በምዕራፍ ብርሃኔ

የ32 ዓመቷ ወይዘሮ በላይነሽ ደምሴ ነዋሪነቷ በአርሲ ነገሌ ነው:: የሰባት ልጆች እናት ናት:: ባላት አንድ ሄክታር የእርሻ መሬት ላይ የተለያዩ ሰብሎችንና አትክልትን በማብቀል ቤተሰቧን ታስተዳድራለች:: ወይዘሮ በላይነሽ የኤችአይቪ ቫይረስ በደሟ እንደሚገኝ አውቃ በአርሲ ነገሌ በሚገኘው በአብዲ ጉዳ (ቫይረሱ በደማቸው

የሚገኝ ሰዎች ስብስብ) ማኅበር አባል ከሆነች አራት ዓመት አልፏታል::

እርሻዋን አርሳ ከምትሰበስበው እህል ላይ የዓመት ቀለቧን ከሰፈረች በኋላ የቀረውን ሸጣ ልጆቿን ለማስተዳደር በቂ ስለማይሆንላት

ልጆቿን የሚረዱላትን ድርጅቶች በመፈለግም ኑሮዋን ገፍታለች:: አሁን ላይ ግን የተሻለ ገቢን ለማግኘት ያስችለኛል ብላ በጓጓችበት የአምስት ቀን የንብ ዕርባታ የአሰልጣኞች ሥልጠና ላይ ተሳትፋለች:: ሕይወቷን ከነልጆቿ የሚቀይርላት አጋጣሚ እንደሆነም ትናገራለች::

ከ200 በላይ ከሆኑት የማኅበሩ አባላት መካከል 50ዎቹ ሴት በመሆናቸው፣ ቤተሰቦቻቸውን ብቻቸውን ስለሚያስተዳድሩ እንዲሁም ምንም

ዓይነት ተጨማሪ የገቢ ምንጭ የሌላቸው በሚለው መስፈርት ተመዝነው የሥልጠናው ተካፋይ ለመሆን ችለዋል::

ወይዘሮ በላይነሽም ከአብዲ ጉዳ ከተመረጡ 50 ሠልጣኞች መካከል የንብ ዕርባታን

የአሠልጣኞች ሥልጠና ከወሰዱ ተጠቃሚዎች አንዷ ናት::

የቫይረሱ በደማቸው መገኘት ወይም ከቤተሰቦቻቸው አባላት መካከል ከቫይረሱ ጋር የሚኖሩ መኖር ከመሥራትና የተሻለ ኑሮ ከመኖር እንደማያግዳቸው የሚናገሩት እነዚህ ሠልጣኞች፣ ጥሩ ገቢን ያስገኛል የተባለለትን ይህንን ሥራ መሥራት እስከሚጀምሩ ድረስ እንደጓጉ ተናግረዋል::

የኤችአይቪ ቫይረስ በደማቸው የሚገኝ ግለሰቦችን ኑሮ ለማሻሻልና ልጆቻቸው ትምህርት ቤት እንዲሄዱ የምግብ፣ የአልባሳት፣ የትምህርት ቤት ወጪዎቻቸውን ለመሸፈን ከግለሰብ አንስቶ እስከ ዓለም አቀፍ ተቋማት ድረስ ይረባረባሉ:: አብዛኛዎቹ ከቫይረሱ ጋር የሚኖሩ ግለሰቦችም ከመመጽወት ይልቅ ሠርተው መኖርን ይመርጣሉ:: ይህንን ስሜት የሚጋሩ የተለያዩ ተቋማት ከቫይረሱ ጋር የሚኖሩ ግለሰቦችን የተለያዩ የሙያና የቴከኒክ ሥልጠናዎች ሰጥተው በመሣርያ ወይም በገንዘብ በመደገፍ ያቋቁሟቸዋል::

በዩኤስአይዲ፤ በፔፕፋር የገንዘብ ዕርዳታ የሚንቀሳቀሰው የዘላቂ ቱሪዝም ጥምረት (Ethiopian Sustainable Tourism Alliance) አንዱ ነው:: ተቋሙ በኤችአይቪ ቫይረስ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ የተጠቁ 72 ግለሰቦችን የዘመናዊ ንብ ዕርባታ ሥልጠናን ለተከታታይ አምስት ቀናት ሰጥቶ ከሁለት ሳምንት በፊት አስመርቋል:: እነዚህ ግለሰቦች የተውጣጡት በመካከለኛው ስምጥ ሸለቆ ከሚገኙት ከአርሲ ኔጌሌ፣ ከምሥራቅ ላንጋኖና ከሌጲስ ነው:: ከእነዚህ ሠልጣኞች ውስጥ 34ቱ የአሠልጣኞች አሠልጣኝ በመሆናቸው ጠለቅ ያለ ሥልጠና ለአምስት ቀናት ሲወስዱ የተቀሩት ደግሞ የሦስት ቀናት ሥልጠናን ወስደዋል::

የንብ ዕርባታው ፕሮጀክት ያማከለባቸው የመካከለኛው ስምጥ ሸለቆ አካባቢዎች ለንብ ዕርባታ ተመራጭ በመሆናቸው በዘርፉ ከዚህ ቀደም ተሰማርተው የነበሩና ያልነበሩን 250

ሰዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ነው:: በመሆኑም የአምስት ቀን የአሠልጣኞች ሥልጠናን የወሰዱት ግለሰቦች፣ ወደየመጡበት ሲመለሱ ተጠቃሚ የሚሆኑትን ግለሰቦች ካሠለጠኑ በኋላ አሠልጣኙ ተቋም ለንብ ዕርባታ አስፈላጊ የሆኑ መሳሪያዎችን በተናጠልና በቡድን ይሰጣቸዋል:: እነርሱም በባህላዊው የንብ ዕርባታ መንገድ ከአንድ ቀፎ በዓመት በአማካይ ከ5-7 ኪሎ ይሰበሰቡ የነበረውን የማር ምርት በዘመናዊው ቀፎ በአማካይ ከዘጠኝ ኪሎ በላይ ማር ማምረት እንደሚችሉ የፕሮግራሙ አስተባባሪ አቶ ዳንኤል አደመ ተናግረዋል::

በዘመናዊ የንብ ዕርባታ የሥልጠና መርሐ ግብር የተካተቱትና እነርሱም የሚያሠለጥኗቸው አጠቃላይ 250 ግለሰቦች፣ በኅብረት ሥራ ማኅበር ተደራጅተው በሚሰጣቸው በግልና በጋራ መሳሪያዎች በመታገዝ ብዙ ጉልበት፣ ገንዘብ፣ ጊዜና ቦታ የሚጠይቀውን የንብ ዕርባታን በማከናወን በኪሎ እስከ 70 ብር በመሸጥ በማር ገበያው ተሳታፊ መሆን ያስችላቸዋል::

በዘርፉ የሚሰማሩት ሊሠሩ የሚችሉበት ቦታ ከሌላቸው ቦታ እንዲያገኙ እንደሚመቻች አቶ ዳንኤል ተናግረዋል:: በተጨማሪም ግለሰቦቹ በዓመት የሚያመርቱትን ማር እንዲያከፋፍሉ የገበያ ትስስር ይመቻችላቸዋል::

የዘላቂ ቱሪዝም ጥምረት በዘመናዊ የንብ ዕርባታ እንዲሳተፉ ከመረጣቸው 250 ግለሰቦች ውስጥ 25 በመቶ የሚሆኑት ሴቶች ናቸው::

የዘላቂ ቱሪዝም ጥምረት ሥራ አጦችን፣ ሴቶችን፣ ወጣቶችንና በተፈጥሮ ሀብት ላይ ጫና ይፈጥራሉ ለሚባሉት የማኅበረሰብ አባላት አማራጭ የሥራ ዕድሎችን ይፈጥራል:: ተቋሙ በመካከለኛው ስምጥ ሸለቆ የሚገኙ ቦታዎች ላይ የአካባቢ ጥበቃ፣ ኢኮ ቱሪዝም፣ ዕደ ጥበባትና ዘመናዊ የንብ ዕርባታ ላይ ተጠቃሚዎችን የማሳተፍ ሥራዎችን የሚሠራም ነው::

የጓጉለት የሥራ አማራጭ

ማስታ

ወቂያ

Tender No: MBMP Pvt. Ltd. Co.06/2005Messebo Building Materials Production PLC (MBMP PLC)

Mekelle, Tigrai, Ethiopia

Invites eligible bidders for the supply of Micro Fresh printing Ink Green and Black Hence;

1. Tender documents can be collected from Messebo Building Materials Production Pvt. Ltd. Co. Liaison Office, ZEFCO Building, 4th Floor, or Messebo Building Material Production Pvt. Ltd. Co., Mekelle head office effective from the day of 1st announcement against payment of non-refundable Birr 100.00.

2. Bidders can see the sample physically by coming to our offices.3. All Bids should be submitted in wax-sealed and stamped envelopes on

or before 17th Feb 2013 during office hours and should be addressed and marked as follows:

Messebo Building Materials Production Pvt. Ltd. Co.

P.O.Box 916

Telephone: 0348400670/0348 400362

Fax:251-344 410863

Attn: Ato Zekaryas Kasahun Procurement &Supply Manager

Mekelle Ethiopia

4. Bids will be opened on 18th Feb 2013 at 10:00 AM (European time) in the presence of interested bidders or their representatives who choose to attend at the above mentioned offices.

5. Bid must be accompanied by bid bond 2% of the total price in the form of C.P.O. or cheque payable to MBMP Plc. The successful bidder shall submit 10% performance bond upon receipt of purchase order (contract agreement) and prior to the release of the 2% Bid Bond.

6. Bidders must submit financial and technical offer separately in two copies. 7. Messebo Building Materials Production PLC reserves the right to accept/

reject the bid fully or partially.

የጨረታ ማስታወቂያ አዋሽ ኢንተርናሽናል ባንክ

እና አዋሽ ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ

የመንትያ ሕንፃዎችን መስታወት ውስጡንና ውጭውን ለማጽዳት የወጣ ጨረታ ማስታወቂያ

ቫት ተመዝጋቢ ሆኖ የዘመኑን ግብር የከፈለ

የሚያጸዳው የመስታወቱ ሥፋት (4545.63)2 ሜትር

ተጫራቹ ተመሳሳይ ሕንፃ ላይ የተሟላ የሥራ ልምድ ያለው ሆኖ ቢያንስ ቢያንስ ከ5 ዓመት በላይ የሥራ ልምድ ያለው

የተሟላ የጽዳት መሳሪያና ልምድ ያለው ባለሙያ ያለው

ስለ ሥራቸው ልምድ በደብዳቤ ለመግለጽና የሥራ ቦታውን ለማስጐብኘት የሚችል

ከየካቲት 15 ቀን እስከ መጋቢት 15 ቀን ሠርቶ የሚያስረክብ

ከላይ ለተጠቀሱት ሥራዎችን ለመሥራት ፈቃደኛ የሆነ ተጫራች የመስታወት ማጽጃ መሳሪያ /Dull pulley/ ስለአለን በራሱ ሠራተኛ (Operator) እየተጠቀመ ለመሥራት የመሳሪያውን ዋጋ በመቀነስ የሚሠራበትን ዋጋ

እንዲያስገባ እንጠይቃለን፡፡

ድርጅቱ

በባህላዊው የንብ ዕርባታ መንገድ ከአንድ ቀፎ በዓመት በአማካይ ከ5-7 ኪሎ ይሰበሰቡ የነበረውን የማር ምርት በዘመናዊው ቀፎ በአማካይ ከዘጠኝ ኪሎ በላይ ማር ማምረት ይቻላል

Page 63: ERROR: The requested URL could not be retrieved ERROR The requested URL could not be retrieved While trying to process the request: TEXT HTTP/1.1 Host: Proxy-Connection: keep-alive

www.ethiopianreporter.com

ገጽ 15 | እሑድ | ጥር 19 ቀን 2005 ክፍል-2

Invitation to bid for Modification works of SRH Referral Clinic(Re-advertised)

Background:

The Family Guidance Association of Ethiopia (FGAE) is an autonomous, non-profit, non-partisan and non-discriminatory indigenous non-government charitable organization. Since its establishment FGAE has been working to promote Sexual Reproductive Health and Family Planning services.

FGAE would like to undertake modification works inside its newly acquired Head Office building in Addis Ababa. Therefore the Family Guidance Association of Ethiopia (FGAE) invites contractors of GC/BC 5 and above to participate in the bid to select a contractor for the works.

Preparation of Proposals:

Bidders are expected to submit separate technical and financial proposals. In preparing the proposal, bidders are expected to examine all terms and instructions included in the documents. Failure to provide all the requested information shall be at your own risk and may result in rejection of your proposal. Bidders must present evidence of similar work carried out by their respective companies.

Interested eligible bidders may purchase the bidding documents from the Family Guidance Association of Ethiopia Head Office Kirkos subcity, Woreda 9 (Nine) house number 1218, office number 303 upon a payment of Birr 100 (one hundred) within 15 days from the announcement of the bid in the Addis Fortune and Amharic Reporter news papers. Dates will be counted from the announcement of the bid on either of the news papers which comes first. Interested eligible bidders must present:

1. Renewed trade license;2. VAT registration certificate;3. Renewed construction license to purchase the bid

documents.

Sealed bids must be submitted with separate technical and financial proposals with one original and one copy. The envelopes containing the proposals should be clearly marked as original or copy.Bid proposal shall be accompanied by a bid security of 2% of the bid amount in the form of CPO or bank guarantee.

Bids will be opened in the presence of bidders who choose to attend at the Family Guidance Association of Ethiopia Head Office Hall in Addis Ababa on the 15th day after this announcement at 10:00 am.

The Family Guidance Association of Ethiopia reserves the right to accept or reject any or all bids.

The Family Guidance Association of Ethiopia P.O.Box 5716Email: [email protected] Tel.: +251-114672300Fax: +251114671084Website: www.fgaeet.org Addis AbabaEthiopia

Dan Church Aid (DCA) is a Danish international NGO, providing development and humanitarian assistance to poor and disadvantaged people across the world. DCA has been operational in Ethiopia since 2004 and has been working with faith based and secular partners in three program thematic areas: Livelihood Security, HIV/AIDS, and Gender and Capacity Building, in the remote rural areas of East Amhara and Southern Oromia.

Dan Church Aid Ethiopia is seeking to engage a consulting firm/team with professionals of sound background and experience to carryout terminal evaluation for Emergency WASH Support to Sudanese Refugees Projects in Benshanguel Gumuz Region, Ethiopia The objectives of the evaluation is to undertake an independent assessment, provide findings on the efficiency, effectiveness, impact, relevance/appropriateness, sustainability, coherence and coordination, and accountability of the WASH refugee support project, and make practical recommendations.Minimum profile of the consultancy team/firm for undertaking the terminal evaluation study

The consultant/team/ undertaking the terminal evaluation should have the following minimum competencies, qualification and experience:

Consultant/Evaluator ProfileAn external consultant shall lead/undertake the evaluation. The consultant/s profile should include:

• Proven evaluation skills such as indicator analysis, sampling, participatory evaluation methodology, appreciative enquiry methods, focus group interviews, etc.

• Extensive field experience in the evaluating humanitarian projects

• Extensive practical knowledge of WASH interventions in an emergency context, particularly in refugee settings.

• Relevant post graduate qualification.

• Extensive understanding/knowledge of and experience with various guidelines and standards relevant to refugee WASH interventions (SPHERE, UNHCR guidelines, HAP, etc)

• Excellent understanding of DG ECHO guidelines and requirements

• Excellent report writing skills (may be required to produce examples of previous work/s)

• Excellent communication and facilitation skills and experience

• Ability to manage the available time and resources and to work under tight schedule

• The Consultancy team composition should not be more than two

• Firm’s experience in evaluating Emergency WASH refugee Project should be presented in a summary form

• A clear and detailed budget breakdown should be attached to the financial proposal

The consultant/firm shall submit copy of certificate of registration, valid business license for the Ethiopian FY 2005 or 2004 and VAT or TOT registration. Freelance consultants with appropriate TIN registration and who fully meet the above requirements may submit proposals. DCA will deduct all appropriate taxes and pay to the relevant government authority in case of engaging a freelance consultants.

Detailed information on the consultancy work can be obtained in the Terms of References (ToR) for conducting terminal evaluation for the Emergency WASH support to Sudanese refugee Project available at DCA Ethiopia Country Office.

The Terms of Reference /TOR/ can be collected during working hours from 25th to 31st January, 2013 from the Administrator, DCA Ethiopia Office, located at the Ethio-China Friendship Avenue, Welo Sefer, Norwegian Church Aid Compound, House No. 174, Kirkos Sub-City, Addis Ababa; Telephone 0115-514047 The deadline for the submission of technical as well as financial proposals would be 2nd February, 2013. The consultants are also required to submit their detailed work plan together with their proposals. DCA Ethiopia reserves the right to cancel part of or the entire consultancy work.

ማስታወቂያ

Page 64: ERROR: The requested URL could not be retrieved ERROR The requested URL could not be retrieved While trying to process the request: TEXT HTTP/1.1 Host: Proxy-Connection: keep-alive

www.ethiopianreporter.com

ገጽ 16 | እሑድ | ጥር 19 ቀን 2005ክፍል-2

ማስታወቂያ

Page 65: ERROR: The requested URL could not be retrieved ERROR The requested URL could not be retrieved While trying to process the request: TEXT HTTP/1.1 Host: Proxy-Connection: keep-alive

www.ethiopianreporter.com

ገጽ 17 | እሑድ | ጥር 19 ቀን 2005 ክፍል-2ማስታወቂያ

Page 66: ERROR: The requested URL could not be retrieved ERROR The requested URL could not be retrieved While trying to process the request: TEXT HTTP/1.1 Host: Proxy-Connection: keep-alive

www.ethiopianreporter.com

ገጽ 18 | እሑድ | ጥር 19 ቀን 2005ክፍል-2

ከ ታ ሪ ክ ጥ ግ

በተሾመ ብርሃኑ ከማል

«መውለድ አል-ነቢ» ወይም «መውሊድ አን-ነቢ» በአጭሩ «መውሊድ» የነቢዩ ሙሐመድ የልደት ቀን ነው:: ቱርካውያን ደግሞ «መውሊዲ ሸሪፍ» ይሉታል:: ትርጉሙም «የተቀደሰው ልደት» እንደማለት ነው:: ፋርሳውያንም «ሚላድ ፓየምባረ ኢክራም» ሲሉ ይጠሩታል:: የታላቁ/የቅዱሱ ነቢይ ልደት እንደማለት ነው:: አልጀሪያውያን በበኩላቸው ‹‹መውሊደ ነቢ ሻሪፍ›› ሲሉት የቅዱሱ ነቢይ ልደት ቀን ማለታቸው ነው:: ከዚህም ሌላ ‹‹የውም አነቢ›› ማለትም የነቢዩ ቀን ብለው የሚጠሩትና በየቋንቋቸው የሚጠሩት አሉ:: ዞሮ ዞሮ የነቢዩ ሙሐመድ የልደት ቀን ማለት ነው:: ሱኒዎች ይህን በዓል በወርሃ ረቢዓል አወል 12ኛው ቀን ሲያከብሩት ሺዓዎች ደግሞ በወርሃ ረቢዓል አወል 17ኛው ቀን ከኢማም ጃዕፈር አል-ሳዲቅ ልደት ጋር አብረው ያከብሩታል:: መውሊድ በወርሃ ረቢዓል አወል ይውላል:: የዓረብኛው የቀን አቆጣጠር በጨረቃ የመሬት ዑደትን መሠረት ያደረገ ስለሆነ ከኢትዮጵያም ሆነ ከአውሮፓውያን አቆጣጠር ጋር ይለያያል:: ለምሳሌ በ2000 ወርሃ መጋቢት፣ አምና በወርሃ ጥር 27 ቀን ሲከበር ዘንድሮ ደግሞ ደግሞ ጥር 16 ቀን ውሏል:: መውሊድ ከሳዑዲ ዓረቢያ በስተቀር በሁሉም የሙስሊም አገሮች ብሔራዊ ክብረ በዓል ነው::

አንዳንድ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት የነቢዩ ሙሐመድ የልደት ቀን መከበር የተጀመረው በመካ ውስጥ በስምንተኛው ክፍለ ዘመን ነው ሲሉ ሌሎች መረጃዎች ደግሞ ከ11ኛው ክፍለ ዘመን አንስቶ በግብፅ መከበር እንደተጀመረ ያወሳሉ:: በፋርስ ውስጥ በ12ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ እንደሆነም የሚገልጡ አሉ:: ከዚያም ቀጥሎ በሶሪያ ተቀባይነትን አገኘ:: ከሶሪያም በኋላ ቀስበቀስ ሁሉም አገሮች ተቀበሉት::

ይሁንና በ18ኛው ክፍለ ዘመን ብቅ ያሉት ሳዑዲ ዓረቢያዊው ሙሐመድ ኢብን ዓብደልዋሐብ እንዲከለከል አደረጉ:: ቁርዓኑን ብቻ እንከተላለን የሚሉት ሰለፎችም ከእምነቱ ጋር የሚጻረር ተግባር መሆኑን አመልክተው እንዳይከበር አወገዙ:: የሳቸው ተከታዮችም ከኢስላም አስተምህሮት ጋር የሚቃረን መሆኑን በሚመለከት ለማሳመን በርካታ የመከራከሪያ ሐሳብ አንስተዋል:: እነዚህ ኢስላማዊ ዘርፎች የነቢዩ ሙሐመድን ልደት ላለማክበር ትልቁ ምክንያታቸው በቁርዓኑ ውስጥ «ልደታቸውን አክብሩላቸው» የሚል ትዕዛዝ አለመኖሩ ሲሆን በእነሱ አመለካከት በልደት ምክንያት የሚታየው ፈንጠዝያ እራሱ በመጨረሻይቱ ቀን ተጠያቂ ሊያደርግ ይችላል:: እነዚህ ቡድኖች መጨነቅ ያለብን ወደ ፍርድ ቀን ይዘነው ለምንሄደው እንጅ ለምድራዊ ፈንጠዝያ መሆን አይኖርበትም:: «የልደት ቀን ማክበር» ከምዕራባውያን ጋር የተያያዘ መሆኑን ይገልጡና «ልደትኮ፣ ዕድሜያችን እየጨመረ ሳይሆን እየቀነሰ የሚሄድበት ነው:: ይህ ከሆነ ዕድሜያችን እያጠረ በመሄዱ ለምን እናከብረዋለን» የሚልም አመለካከትም አላቸው:: ከዚህም በተጨማሪ «ያላቸው ሲንበሸበሹ የሌላቸው የበታችነት እንዲሰማቸው የሚያደርግ ስለሆነ ሊበረታታ የሚገባው አይደለም፤» በማለት ይኮንኑታል:: ጉዳዩ ወደ ክርክር መድረክ በሚቀርብበት ጊዜም አንዳንድ የቁርዓንና የሐዲስ አንቀጾች በቀጥታና በገደምዳሜ እየተጠቀሱ የሸሪዓው ድጋፍ እንደሌለው ለማስረዳት ይሞክራሉ:: እነዚህም ክፍሎች ከሚጠቅሱት ውስጥ በግንባር ቀደምነት «ነቢዩ ሙሐመድ በሕይወት ዘመናቸው አላከበሩትምና እኛም አናከብርም» የሚለው የሚጠቀስ ሲሆን «የኢስላምን መንገድ ትታችሁ የኦሪትና የወንጌል አማኞች በሚሄዱበት መንገድ አትሂዱ» የሚለውን ይጠቅሳሉ:: ከዚያም በተጨማሪ መውሊድን ማክበር የማጋራት አቅጣጫን የተከተለ እንደሆነ ያስረዳሉ:: በእነዚህ ቡድኖች አመለካከት ሰዎች ወደ ተለያዩ መስጂዶች ወይም አድባራት ሄደው በተለይም የታወቁ ሙስሊም አባቶችን ስም እየጠሩ እንዲያማልዷቸው፣ ከህመማቸው እንዲፈውሷቸው፣ ሀብት እንዲሰጧቸው፣ ጠላቶቻቸውን እንዲያተፉላቸው፣ ወዳጆቻቸውን እንዲባርኩላቸው የሚፈጽሙት ተግባር ኢስላማዊ አይደለም::

ሁለቱ ኢስላማዊ ቤተ አስተምህሮቶች የመውሊድን በዓል የሚቃወሙት ቢሆንም «የነቢዩ መሐመድን በዓል እናንተ በምትሉት መንገድ ሳይሆን ለነብያችን ካለን ፍቅርና አክብሮት ተነስተን በጸሎት፣ በማወደስ፣ ስለሳቸው መሠረታዊ ጉዳዮችን በማውሳት፣ ድሆችና ችግረኞችን በመርዳት እንጅ በፈንጠዝያ አይደለም:: ከፈጣሪ በስተቀርም የሚያጠፋም ሆነ የሚያለማ ኃይል እንደሌለ እናምናለን:: የሃይማኖቱ አባቶችም ሆኑ አድባራቱም ከፈጣሪ በላይ ወይም እኩል ወይም ከዚያም ባነሰ የፈጣሪን ስልጣን የማይጋሩ ነገር ግን ፈጣሪያቸውንና ነቢያቸውን በከፍተኛ ደረጃ የሚያከብሩ ብቻ መሆናቸውን ያምናሉ፤» የሚሉት ደግሞ በሚገባ ያከብሩታል:: «ምነው እናንተ በሱረቱል አልአሕዛብ (33፡56) እናንተ ያመናችሁ ሆይ፣ በእርሱ ላይ የአክብሮት እዝነትን አውርዱ:: የማክበርንም ሰለምታ ሰላም በሉ:: ብሎ የለም ወይ? እኛኮ በተወለዱበት ቀን የማክበር ሰላምታን ስናቀርብ እንጅ ሌላ የማጋራት ነገር አንፈጽምም:: እንዲያውም የፈጣሪ አሐድነት በቁርዓን የተወረደልን በእሳቸው ስለሆነ የሳቸው መወለድ ለሙስሊሙ ታላቅ ደስታ ነው፤» በማለት መልስ ይሰጣሉ::

በእርግጥም በአገራችንም ሆነ በመላው ዓለም የነቢዩ መሐመድ የልደት ቀን የሚከበረው ስለነቢዩ መሐመድ ታሪክ በግጥምና በዝርው እንዲሁም በዜማና ያለዜማ በለሆሰሳ ነው:: ኢማም ሙጠዋሊ ሻዓራዊ የተባሉት የሃይማኖት አባትም «መዒደት አል-ፊቕ` አል-ኢስላሚያ በተሰኘው መጽሐፋቸው «ሕይወት ያላቸው ሁሉ በነቢዩ

የነቢዩ ሙሐመድ የልደት ቀንሀገሮችም በዕለቱ ሙስሊሞች ሃይማኖታዊ በዓላቸውን እንዲያከብሩ ሁኔታዎችን ያመቻቻሉ:: በፓኪስታን ብሔራዊ ሰንደቃላማ በከተሞች ጎዳኖች እንዲውለበለብ ሲደረግ በዋና ከተማዋ በኢስላማባድ 31 ጊዜም መድፍ ሲኮስ፣ በሌሎች ግዛቶች ደግሞ 21 ጊዜ ይተኮሳል:: በኢትዮጵያም በአዲስ አበባ መድፍ እንደሚተኮስ ልብ ይሏል::

የመውሊድ በዓል አከባበር ከሳዑዲ ዓረቢያ በሚመነጭ አስተምህሮት ተጽእኖ ያለበት ቢመስልም በዓለም የታወቁ እንደ ሙፍቲ ዓሊ ጎማ (የአልአዝሃር ዩኒቨርሲቲ ዕውቅ ሊቅ)፣ የሙስሊም ወንድማማችነት ንቅናቄ መሪ የሆኑት ዩሱፍ አልቃርዳዊ፣ የቆጵሮሱ ታላቁ ሙፍቲ ሙሐመድ ዓለዊ አል-ማሊኪ፣ የየመኑ ነዛም አል- ሐቃኒ ሐቢብ ዓሊ አል-ጂፋሪ፣ እንዲሁም ሌሎች የየመን፣ የቦሲኒያ፣ የሕንድ ሙፍቲዎች የነቢዩን መውሊድ ማክበር አስፈላጊነት በሥራዎቻቸው ገልጠዋል::

የመውሊድ በዓል አከባበር በኢትዮጵያበኢትዮጵያ የመውሊድ በዓል አከባበር ከአካባቢው

የሙስሊም አገሮች በተለይም ከሱዳን፣ ከግብፅ፣ ከሱማሊያና ከጅቡቲ ጋር በአብዛኛው ይመሳሰላል::

የዚህ ጽሑፍ አዘጋጅ በኢትዮጵያ የነቢዩ ሙሐመድ ልደት ቀን ከሚከበርባቸው ስፍራዎች መካከል በትግራይ ነጋሺና በሆጂራ ፎቂሳ (ራያ)፣ ሰሜን ወሎ ዳና፣ በደቡብ ወሎ በጃማ ንጉሥ፣ በባሌ በድሬ ሸኽ ኹሼን በሚከበርበት ጊዜ ከስፍራው ተገኝቶ የመመልከት ዕድል ገጥሞታል:: በሁሉም ስፍራዎች ሙስሊሞች ከአገሪቱ አራት ማዕዘናት ከአንድ ሳምንት በፊት ጀምሮ ይመጣሉ:: በመስጊዶችና በመስጊዶች ዙሪያም ይሰፍራሉ:: በዕለቱም በጎች፣ ፍየሎች፣ ሰንጋዎችና ግመሎች ሊታረዱ ይችላሉ:: በዚህ ዕለት በዓሉን ለማክበር የሚመጡ እንግዶች እንዳይቸገሩ ውሃ፣ እንጨት ይዘጋጃል:: ከየአቅጣጫው የሚመጡት እንግዶችም ችግሩን አስቀድመው ስለሚገነዘቡ ከሚያቋርጡት ወንዝ ውሃ፣ ከደን ደግሞ ደረቅ እንጨት ይዘው ሊመጡ ይችላሉ:: በዕለቱ የሚመቱ ድቤዎች በፀሐይ ብርሃን ሲመቱ ይሰነብቱና ከብረት እንደተሠራ ብረት ወይም የብረት ድምፅ ያለው በሃ ድንጋይ «ኪው፣ ኪው» የሚል ድምፅ እንዲያመጡ ይደረጋል:: የታወቁ የሃይማኖት አባቶች ከተከታዮቻቸው ጋር በመስጊዱ ወይም በመስጊዱ ዙርያ ይቀመጣሉ:: ምርጥ ጫት እስከሚያምር ዛላው መታደል ይጀመራል:: ፈጣሪንና ነቢዩ ሙሐመድን የሚያወድሱ ዜማዎች መውረድ ይጀምራሉ:: በዚህ ጊዜ ከዚች ዝባዝንኬ የበዛባት ዓለም ቀስ በቀስ በመንፈስ የሚወጡ ሰዎች አድናቆታቸውን በከፍተኛ ድምፅ ማሰማት ይጀመራል:: ስለፈጣሪያቸው ፍቅር፣ ስለነቢዩ ፍቅር ሲወዘወዙ ለብ ያለ ነፋስ የሚጓዝበት የጤፍ ብርት ይመስላሉ:: በአምስቱ የሰላት ሠዓዎችና በምግብ ሰዓት ካልሆነ ዕረፍት የለም:: የደወል ድምፅ ያለው ድቤዎች በቅርቡ ያለውን ሰው ልብ በደስታ ሲማርኩ በሩቁ ያለን ደግሞ «ና ወዲህ» በማለት ይጣራሉ:: ቦታው ሁሉ ፍቅር በፍቅር ይሆናል:: ቀኑና ሌሊቱን በጸሎትና በምህላ፣ ቁርዓን በመቅራትና ሐዲሶችን በማንበብ ያሰለፉት ምዕመናን በዕለቱ ወዳለፉ የሃይማኖት አባቶችና ሌሎችም ሙስሊሞች መቃብሮች በመሄድ ፈጣሪ ነፍሳቸውን በገነት እንድታስቀምጥ ጸሎት አድርገው ይመለሳሉ:: ረፋድ ላይ የነቢዩ መሐመድ ልደት ማክበር የተፈለገበት ምክንያት ገለጻ ይደረግና አገሪቱና ሕዝቧ በፍቅርና በሰላም እንዲኖሩ በመጸለይና በመመረቅ ይለያያሉ:: በእግሩም፣ በአጋሰስም፣ በመኪናም የመጣው ምዕመን በተመኘው ስፍራ ጸሎት አድርሶ በመመለሱ መንፈሱ በደስታ ይሞላል::

የነቢዩ መውሊድ ከሱፊዝም ጋር ስለመያያዙቀደም ባለው የመውሊድ አከባባር ኢትዮጵያውያን

ሙስሊሞች ወደ አንዱ መስጊድ ሄደው እንደሚያከብሩ ተገልጿል:: በመሠረቱ እንዲህ ያለው ሰላማዊ እንቅስቃሴ በአገራችን እጅግ ቀላል ይሁን እንጂ በሌሎቹ አገሮች የሚናፈቅ ነው:: ይህ ሰላማዊ እንቅስቃሴ ግን የራሱ የሆነ ታሪካዊ ምክንያት አለው:: ስለሆነም ይህንን አኩሪ ታሪካችን ከሌሎች ሃይማኖቶች ጋር ተስማምተንና ተግባብተን እንድንኖር ያደረገ ስለሆነ በኅብረተሰቡ ዘንድ መታወቅ ሲኖርበት ሙስሊሙን ብቻ ሳይሆን ክርስቲያኑና ሃይማኖት የሌለውን ጭምር በመርዳት የሚታወቁት ሱፊ አባቶቻችን በዚች አገር ላይ ሰላምና መቻቻል እንዲሰፍን አስችለዋልና እነርሱንም ለማወደስና ለማሞገስም በግድ ሱፊ መሆን እንደማያስፈልግ ጸሐፊው ያምናል:: ስለዚህ እኒያ ኢትዮጵያውያን የሃይማኖት አባቶች ምን አደረጉ? እንደምንስ በአገር ውስጥና በአጎራባች አገሮች የመቻቻል፣ አብሮ የመኖርና የፍቅር መንገዶች ሆኑ? ብለን እንጠይቅ:: አንድ በአንድም እንደሚከተለው እንመልከት::

በመሠረቱ፣ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ከጥንት ጀምሮ ከጂቡቲ፣ ከሱማሊያ፣ ከሱዳን፣ ከግብፅ፣ ከየመንና ከሳዑዲ ዓረቢያ ሙስሊሞች ጋር መልካም ግንኙነት ሲኖራቸው በተለይም ወደ ግብፅና ሱዳን ሄደው የእስልምና ትምህርት የሚማሩ ኢትዮጵያውያን በርካታ ናቸው:: ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ከአጎራባች ሙስሊም አገሮች የሚጋሯቸው ኢስላማዊ እሴቶች በስምምነትና በመተሳሰብ እንዲኖሩ ያደረጓቸው ሲሆን በተለይም ተመሳሳይ የሱፊ ስርዓት በመቀበላቸው አንደኛው ተማሪ ወደ ሌላው ሄዶ ትምህርት እንዲቀስም አስችሎታል::

በአገር ውስጥም ቢሆን የአንዱ ክልል ሙስሊም ተማሪ (ደረሳ) ወደሌላው ክልል ሸኽ ሔዶ መማር የተለመደ ሲሆን በሱማሌ ውስጥ የቃዲሪያ፣ የአሕመዲያ-ኢድሪስያ፣ የሳሊሕያ፣ የራፊዒያ፣ ጦሪቃ የነበረ ከመሆኑም በላይ ወደነ ሸኽ አብዱራሕማን አል-ዘይላዊ፣ የሸኽ

ኢብራሂም ሐሰን ጀብሮ ከሐረርጌ፣ ከባሌ፣ ከዓፋር ሄደው ይማሩ እንደነበረ ሁሉ ከሱማሌም ወደ ሐረር መጥተው ይማሩ ነበር:: ከነዚህም መካከል የአሕመዲያ-ኢድሪስያ ጦሪቃ የተመሠረተው በአህመድ ኢብን ኢድሪስ ሲሆን ይህም ከ1760-1837 እንደዘለቀ ይታወቃል:: የአሕመድያ ኢድሪስያን ጦሪቃ የማይከተሉት የሳሊሐን ጦሪቃ በ1887 አካባቢ የመሠረቱ ሲሆን ይህም ጠሪቃ በተለይ በኦጋዴን ተስፋፍቶ እንደነበር ይታወቃል:: የታወቁት የሱማሌ ሸኽ ዓዌስ ሙሐመድ ባራዊ (1909 አረፉ.)፣ የሳሊሕያና የአሕመዲያ-ኢድሪስያ ጠሪቃ በሸበሌና በጁባ ወንዞች አካባቢ ጀምዓት ፈጥረው እንደነበርም ይታወቃል:: ሸኽ ዓብዱራሕማን ዓብዱላህ (ሞቃዲሹ) የኡጋዴን በተለይም የሙስታሂል፣ የፈርፌር፣ የጎዴ ደረሶች እየሄዱ ትምህርት ይቀስሙባቸው ነበር::

በምሥራቅ ኢትዮጵያ በተለይም በሱማሊያ አካባቢ የነበረውን ትሥሥር ለመጥቀስ ያህል እንጅ በወሎ የነበረው የሸኾች መደድም (የሸኾች መንደር-ሰፈር) ቢሆን ከአገሪቱ አራት ማዕዘናት ከአጎራባች አገሮች የሚመጡትን ደረሶች ጭምር እየተቀበለ ያስተናግድ ነበር:: ይኸው ከ18ኛው እስከ 20ኛው ክፍለ ዘመን በወሎ ተንሰራፍቶ የነበረው መደድ እስከ ሰሜናዊ የአገሪቱ ግዛት የተንሰራፋ አገልግሎት ይሰጥ ነበር:: ዛሬ በወሎ ያሉት ዶሪሆች ከጭቃም ይሠሩ ከአጣና ታዛም ይሁኑ ጎጆ ች የእነዚያ ታላላቅ ሸኾች መኖሪያ ች ነበሩ::

የሱፊ ወንድማማችነት ሥርዓት በሀገራችን በኢማም አሕመድ ኢብራሂም ጊዜ በሰፊው የገባ ቢሆንም ከዚያ በፊት የሰይድ አብዱልቃድር ጀላኒ ተከታዮች በሐረር፣ በወሎ፣ በትግራይ፣ በኤርትራ፣ በጎንደር፣ በጎጃም፣ በኦሮሚያ በብዛት ይገኛሉ:: ስለሱፊያ የሚያውቅ ብቻ ሳይሆን ስለከራማቸው የሚያውቅ እንደሚበዛ ግን ጥርጥር የለውም:: በአገራችን የውጭ ወራሪ ብዙም ስላልበረ የተለያዩ ጠሪቃዎ ች (የሱፊ ሥርዓቶች) በተለያዩ ጊዜያት ቢገቡም እንኳ የቱ በምን ጊዜና ምክንያት እንደገባ ማወቅ ሰፊ ጥናት ይጠይቃል:: ዳሩ ግን ከጥንታውያኑ የኢትዮጵያ ግዛቶችና ከአሁኖቹ ከአጎራባች አገሮች ጋር በማገናዘብ ከሱዳን፣ ከሱማሊያ፣ ከጅቡቲ፣ ከኤርትራ በኩል ምን ጠሪቃ እንደገባ በጥቅሉ ማየት ይቻላል::

የኢትዮጵያ ሱፊ የእስልምና ሃይማኖት አባቶች አሰተሳሰብና እምነት ከሌሎች አገሮች ጋር ተመሳሳይ ነው:: እነሱም ከሁሉ አስቀድሞ መሠረታዊ የእስልምና እምነትን የተቀበሉ ሲሆን ከልጅነታቸው ጀምሮ ቁርዓኑና ሐዲሱን ጠንቅቀው ማወቅ ይጠበቅባቸዋል:: ብዙ ዎቹም ሐፊዞች (ቁርዓኑን በቃላቸው የያዙ) እንደነበሩ ይነገራል:: ከዚህም በተጨማሪ አራቱንም ማለትም የሐነፊ፣ የማሊኪ፣ የሻፊዒና የሐንበሊ መዝሀቦች ልዩነታቸውንና አንድነታቸውን ለይተው ማወቅ ይኖርባቸዋል:: እነዚህን መሠረታዊ ዕውቀቶች ከጨበጡ በኋላ ያሉትን የጦሪቃ ስሞችና ዓይነቶች ማወቅ ይኖርባቸዋል:: ሱፊ አባቶች ስለ ጠሪቃ መሪ ዎች ሲጠየቁ ትክክለኛ መልሶችን መስጠት ይኖርባቸዋል::

ከዚህም በተጨማሪ ጠሪቃውን ለመቀበል የሚያስችሉ ደረጃ ዎችን ማጥናት አለባቸው:: ይህ ሁሉ ከሆነ በኋላ በዚክር፣ በተፈኩር፣ በኻልዋ፣ በሸኾች እርዳታ ጦሪቃውን ይቀበላሉ::

ይህም ሆኖ ደግሞ የኢትዮጵያ ሙስሊም የሃይማኖት አባቶች ታሪኹ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ በግለሰቦች እጅ ታምቆ ቆይቷል:: ግለሰቦችም በቃል፣ በእጅ ጽሑፍ፣ በእንጉርጎሮና በመንዙማቸው ከትውልድ ትውልድ ሲያስተላልፉት ቆይተዋል:: የነዚህ ታላላቅ ሰ ዎች ታሪክ በህትመት ጽሑፍ፣ በድምፅና በፊልም መቀረፅ የተጀመረው ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ነው:: ከነዚህም ሥራ ዎች ውስጥ 1) የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ታሪክን በካሌት ያስቀረፁት ሸህ መሐመድ ወሌ፣ 2) የአውሊያ ችንና ሙሻኢኮችን የሚያወድሱት ሸህ ሙሐመድ አወልና አብዱል ወሃብ ሸህ በድሪዲን:: 3) አራት ዓይኖቹ በሚል ርእስ ስለ አውሊያ ች መጽሐፍ ያሳተሙት አቶ ተስፋዬ ብርሃኑ፣ 4) በወለኔ ሸህ ዑመር ሸህ በሺር የተጻፈ የኢትዮጵያ ቀደምትና ታላላቅ ዑለማ ች ታሪክ (ጥሮነ) ጥቂቶቹ ናቸው:: 5) የሸኽ ሁሴን ጅብሪልን ትንቢት ያሳተሙት አቶ ቦጋለ ተፈሪ 6) ከነዚህም ሌላ በእንግሊዘኛ፣ በፈረንሳይኛ፣ በጀርመንኛ፣ በዓረብኛ ወዘተ. የተጻፉትና በግለሰቦች እጅ የሚገኙ ትልልቅ መጻሕፍትም አሉ:: ከነዚህ ሁሉ መረጃዎ ች ውስጥ ለታሪክ ቀረቤታ ያለው ሸህ ሙሐመድ ወሌ በቴፕ ያስቀረፁት ትንታኔና በወለኔ ሸህ ዑመር ሸህ በሺር የተጻፈ ‹‹የኢትዮጵያ ቀደምትና ታላላቅ ዑለማ ች ታሪክ (ጥሮነ)›› እጅግ ጠቃሚ መረጃዎ ች ሲሆኑ ሸኽ ሙሐመድ አወል መንዙማዎ ችና እንጉርጉሮችም ለምርምር በር የሚከፍቱ ናቸው::

«በአገራችን የነቢዩ መሐመድ መውሊድ መከበር ከጀመረ ከአንድ መቶ ዓመት በፊት ነው» የሚሉ ቢኖሩም ይኸው በዓል በተወሰኑ ስፍራዎች ተወስኖ ይኖር እንደነበር ይታወቃል:: በዓሉ የመንግሥትን ይሁንታ አግኝቶ በብሔራዊ ደረጃ መከበር ከተጀመረ ደግሞ 38 ዓመታትን አስቆጥሯል:: ይህ በዓል ከያዘው መንፈሳዊ ፋይዳ በተጨማሪ የሕዝብን በዚያ አጋጣሚ ስለሀገሩ እንዲያውቅ፣ በዝቅተኛ ደረጃ የሚነግዱትን የሚረዳ፣ እርስ በርስ የሚያስተዋውቅና በአጭሩም ለማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማት አስተዋጽኦ የሚያበረክት በመሆኑ ሕዝቡና መንግሥት ልዩ ትኩረት ሊሰጡት የሚገባ የሕዝብ በዓል ነው::

ከአዘጋጁ፡- ጸሐፊውን በኢሜይል አድራሻቸው [email protected] ማግኘት ይቻላል::

ሙሐመድ መወለድ ደስተኛ ከሆኑ፣ በሳቸው መወለድ መላእክቱ ሁሉ ደስተኞች ከሆኑ እኛን በሳቸው ልደት እንዳንደሰት የሚከለክለን ነገር ምንድነው?» በማለት ለምን ማክበር እንደሚገባ ያብራራሉ:: እኒህ የሃይማኖት አባት «ምንም እንኳን ነቢዩ በረቢዓል አወል 12ኛ ቀን በመወለዳቸው አብዛኛው ሕዝብ ያንን ዕለት ከቤቱ ልዩ ልዩ ጣፋጭ ነገሮችን አዘጋጅቶ ቢያከብረው፣ አደባባይ ወይም መስጊድ ወይም ወደ አድባር ሄዶ በግጥምና በዜማ እያወደሰ ቢውልም በየወሩ፣ በየሳምንቱና በየቀኑ ማክበር የሚከለክለው የለም፤» በማለት የነቢዩ ሙሐመድ ልደት መከበር ያለበትን አሥር የማረጋገጫ አንቀጾችን በመጥቀስ ያስረዳሉ::

ሌሎች ሊቃውንት ደግሞ «የነቢዩ የልደት ቀን ማክበርን የሚቃወሙ ሰዎች በቁርዓንና በሐዲስ የሌለን ተግባር መፈጸም እንደነውር መሆኑን በማስረዳት እንዳይከበር የሚከለክሉ ሰዎች በእርግጥም በቁርዓንና በሐዲሳቸው ያልተጠቀሱትን ማድረግ የሚወገዝ ከሆነ በነሱ በኩል ብዙ ነገሮች ተደርገው የለም ወይ? ቁርዓኖችን ማብራራት፣ መተርጎም፣ በራስ መንገድ መግለጽ፣ በየቋንቋው ማስተማር ሁሉ ከነቢዩ በኋላ የተከናወኑ አይደሉምን? ከነዚህስ ሌላ ብዙ ነገሮች አልተከናወኑምን? እነዚህ የነቢዩን ልደት የሚቃወሙ ክፍሎች ቁርዓኑንና ሐዲሱን ለማስተግበር ብዙ የወጡ ነገሮችን አልፈጸሙምን? ስለዚህ እነሱ እኛን እንደነውር ፈጻሚ እራሳቸውን እንደትክክል ሊቆጥሩ አይችሉም፤» በማለት ያስረዳሉ::

ከነዚህ ሌላ «አንዱ ነውር ስለፈጸመ ሌላው መፈጸም አለበት፣ ወይም ነውርን በነውር ይቃወም የሚል የለም:: ነገር ግን የነቢዩ ሙሐመድን የልደት ቀን መከበር የሚቃወሙት ክፍሎች ይህንን ሐሳብ ያነሱት የሙስሊሙን ቤተሰብ ለመከፋፈል፣ አንድነት እንዳይኖረው ለማድረግና በመካከሉ ሰላም እንዳይኖር የሚፈልጉ ክፍሎች የፈጠሩት ነው፤» በማለት የራሳቸውን አመላካከት ያብራራሉ::

በዚህ ረገድ በሀገራችን አንድ ጫት ቃሚና የማይቅም ያደረጉት ውይይት ዓይነተኛ ምሳሌ ይመስላል:: ይኸውም ከዕለታት አንድ ቀን አንድ ጫት የማይቅሙ ሰለፊ ሸኽና ሌላ የሚቅሙ ሱፊ ሸኽ ይገናኙና ሱፊው የጫት ግብዣ ያቀርቡላቸዋል:: ሰለፊውም «ይህማ ነቢያችን ያልቃሙት ስለሆነ ክልክል ነው» በማለት ያስረዳሉ:: በሌላ ጊዜ ሱፊው በተራቸው ወደ ሰለፊው ቤት ሲሄዱ የቆጮ ምግብ ይቀርብላቸዋል:: ሱፊውም «ይህንማ አልበላም» የሚል መልስ ይሰጣሉ:: ጋባዡ ሰለፊም በድንጋጤ «ለምን?» ተብለው ይጠይቃሉ:: ሱፊው ሸኽም «ይህንማ መች ነቢዩ በሉት» የሚል መልስ ሰጡ:: ስለዚህን ነቢዩ ያላደረጉት ሁሉ ነውር ሊሆን እንደማይችል በቀላል ምሳሌ ገለጡ ይባላል::

የኚህ ሰው አገላለጥ ቀደም ሲል ለማስታወስ እንደተሞከረው ሁሉ «በቁርዓንና በሐዲስ ውስጥ የነቢዩን ልደት ማክበር የሚከለክል እስከ ሌለ፣ እሳቸውም ከሳቸው በፊት ይከበሩ የነበሩትን ከመልካም ታሪክና እምነት ጋር የተያያዙትን በዓላት ይከብሩ ስለነበረ፣ መከበር እንዳለባቸውም ያስተምሩ ስለነበር ከሳቸው ሕልፈት በኋላ ልደታቸውን ስለነቢይነታቸው፣ ስለደግነታቸው፣ ስለውዴታቸው፣ ስለክብራቸው እያወደስኩ ባሳልፈው ምን ችግር አለበት?» የሚል ይመስላል:: እነዚህ ክፍሎች ከሚያቀርቧቸው ምሳሌዎች መካከልም አይሁዶች ያከብሩት የነበረው የዓሹራ በዓል ይገኝበታል:: ከዚህም በተጨማሪ «የነቢዩን ልደት የሚቃወሙት ሊቃውንት ኢስላማዊ መንግሥታቸው የነፃነት ቀን፣ የሰላም ቀን፣ የሰንደቃላማ ቀን ወዘተ ሲያከብር አብረው የሚደልቁት የጽድቅ መንገድ ስለሆነ ነው?» በማለት ጥያቄ ለበስ አስተያየታቸውን ይሰነዝራሉ::

ያም ሆነ ይህ፣ የነቢዩ ሙሐመድን በዓል ኢስላማዊ መንግሥት ያልሆኑ አገሮች ጭምር ለዜጎቻቸው የሕሊና ነፃነት መከበር ሲሉ ብሔራዊ በዓል እንዲሆን በዓዋጅ ያጸደቁት ሲሆን ከነዚህም ኢትዮጵያ፣ ኬንያ፣ ታንዛንያ፣ ሕንድን እንደምሳሌ መጥቀስ ይቻላል:: እንደታላቋ ብሪታንያ፣ ሩሲያ፣ ካናዳ፣ አውስትራሊያ የመሳሰሉት

Page 67: ERROR: The requested URL could not be retrieved ERROR The requested URL could not be retrieved While trying to process the request: TEXT HTTP/1.1 Host: Proxy-Connection: keep-alive

www.ethiopianreporter.com

ገጽ 19 | እሑድ | ጥር 19 ቀን 2005 ክፍል-2ማስታ

ወቂያ

ሥ ነ ፍ ጥ ረ ት

ዋልያ በኢትዮጵያ ብቻ እዚህም በሰሜን ተራራዎች ብቻ የሚገኝ አጥቢ ነው:: የበግና የፍየል ነገድ (Caprini) አባል ነው:: ይህ ነገድ ካሉት ከ17 እስከ 19 ግድም የዱር ብቸኛ ዝርያዎች ውስጥ፣ በአፍሪካ የሚገኙት ሦስት ብቻ ናቸው:: የሰሃራው ባርባሪ በግ፣ የኑቢያ አይቤክስ እና የሰሜን ኢትዮጵያው ዋልያ:: አንዳንድ አጥኚዎች ዋልያንና የኑቢያ አይቤክስን፣ ሁለቱንም በአንድ ብቸኛ ዝርያ ውስጥ ያጠቃልሏቸዋል:: እናም እያንዳንዳቸውን Capra ibex waie እና Capra ibex nubiana ብለው ንዑስ ብቸኛ ዝርያ አድርገው ይቆጥሯቸዋል:: ሆኖም ዋልያ ከኑቢያው አይቤክስ የሚለይባቸው ሁኔታዎች አካላዊም ሆኑ ባሕርያዊ፣ ቁርጥ ያለ ብቸኛ ዝርያ ለመሆኑ በቂ ምክንያቶች አሉ:: ከነዚህ ውስጥ በማንኛውም ወራት ለመራባት መቻሉና በመጠን መብለጡ፣ ቀንዱ ከኑቢያው ወፍራም ሆኖ አጠር ማለቱ፣ የጢሙ አጠር ማለትና የቆዳው ቀለም ጠቆር ያለ ቡኒ መሆኑ በማስረጃነት ይጠቀሳሉ:: በተጨማሪም የኑቢያው አይቤክስ በቆላ መኖሩና ዋልያ ረጠብ ባለ የኢትዮጵያ ደጋ መኖሩ፣ በምግብ ምርጫም ጭምር እንደማይመሳሰሉ ያሳያል::

የዋልያ ሴቶችና ወንዶች ልዩነት የማያሻማ ነው:: ወንዶቹ ወደ 125 ኪሎ ግራም ገደማ ሲመዝኑ፣ ሴቶቹ የሚመዝኑት ወደ 80 ኪሎ ግራም ነው:: ከፊል ክብ የመሰለው ቀንድ ሴቶቹም ወንዶቹም ቢኖራቸውም የወንዶቹ ቀንድ ሳይሆን በውፍረቱም:: በቀንዶቹ ላይ ያሉት ጉጦችና አበጥ አበጥ ያለ የዕድሜ ክቦች፣ የያንዳንዱ ዋልያ መለያ ናቸው:: ዋልያዎች በቅልጥሞቻቸው ላይ ጥቁርና ነጭ ምልክቶች ሲኖራቸው ከስራቸው ደብዛዛ ነጭ ናቸው::

ወንዶቹ ጠቆር ያለ ቡኒ ቀለም ሲኖራቸው፣ የሴቶቹ ፈካ ያለ ቡኒ ነው:: በተረፈ የወንዶቹ ዕድሜ እየገፋ ሲሄድ ደረታቸው ይጠቁራል:: ሲምም ያበቅላሉ:: ጅራታቸው አጠር ብሎ ጫፉ ጎፈሬ ነው::

ማኅበራዊ አደረጃጀታቸው፣ ክልልተኛ፣ ማኅበራዊነትም ብቸኝነትም የሚታይበት ነው:: ከወንዶቹ ይልቅ ሴቶቹ የበለጠ ብቸኛ ናቸው:: ተመሳሳይ ዕድሜ ያላቸው ወንዶች ትናንሽ ቡድኖችን ይመሠርታሉ:: ሆኖም የስሪያ ጊዜ ሲሆን ቡድኑ

ዋልያ (Walia Ibex) Capra walie

ይፈርስና ለየብቻቸው ይሄዳሉ:: በማንኛውም ጊዜ መራባት የሚችሉ ቢሆንም፣ ከመጋቢት እስከ ግንቦት ያለውን ጊዜ የስሪያ ወቅት ማለት ይቻላል:: ሴቶቹ በወለዱ ጊዜ የእናቶች ቡድን ይሠራሉ:: የዚህ ምክንያቱ የሎስን የመሰሉ ትላልቅ ወፎች ልጆቻቸውን እንዳይወስዱባቸው ለመከላከል ነው የሚሉ አሉ::

ብዙዎቹ ግልገሎች የሚወልዱት ከዋነኛው ወንድ ነው:: ዋነኛው ወንድ ተደራራቢ የሆኑትን የተለያዩ ሴቶች ክልሎች እንደግሉ አድርጎ፣ ከሁሉ ሴቶች ጋር ግንኙነት ያደርጋል::

ዋልያዋ ከ150 እስከ 165 ቀኖች ከፈጀ እርግዝና በኋላ አንድ ግልገል፣ አንዳንዴ ደግሞ መንታ ግልገሎች ትገላገላለች:: ግልገሎቹ በተወለዱ በአንድ ዓመታቸው ለአካለ መጠን ይደርሳሉ:: ዕድገታቸው ግን ለብዙ ጊዜ ይቀጥላል:: እንዲያውም በመጠን ከፍ ያለው በዕድሜውም የበለጠው ነው ማለት ይቻላል:: አንድ ዋልያ በአማካይ 12 ዓመት ሊኖር ይችላል:: በስሪያ ጊዜ በወንዶቹ መካከል ግጭት ይኖራል ትልልቆቹ ያሸንፋሉ::

በሴቶቹ ቡድን ከ2 እስከ 12 ዋልያዎች ይገኙበታል:: ትላልቆቹ ወንዶች በስሪያ ጊዜ ካልሆነ ብቸኛ ናቸው:: ቀን የሚያርፉት በዋሻዎችና በጥሻዎች ውስጥ ነው:: ሆኖም ግልገሎቹ በስያትም ቢሆን ሲጫወቱ ማየት ይቻላል:: የወጣት ወንዶች ቡድንም አለ::

ዋልያ ሁሉን ዓይነት ዕፅዋት የሚመገብ ዕፀ በል ነው:: ብዙ የምግብ ጊዜውን የሚያጠፋው ጥቅጥቅ ባለ ቁጥቋጦ ውስጥ ቅጠል ሲቀነጥብ ነው:: ዋልያ ብዙ ጊዜውን የሚኖረው ተደብቆ ነው:: ሲንቀሳቀስም ሆነ ሲበላ የሚታየው እጅግ በማለዳና ሲመሻሽ ነው:: በእኩለ ቀን ገደማ ጥቅጥቅ ካለ ቁጥቋጦ ውስጥ ተደብቆ ይውላል::

ዋልያ የሚገኝበት የሰሜን ተራራዎች፣ የኢትዮጵያ ከፍተኛው ሥፍራ፣ ራስ ደጀን፣ የሚገኝበት አካባቢ ነው:: የራስ ደጀን አናቱ 4,650 ሜትር ከባሕር ወለል በላይ ነው:: ይህ ሥፍራ ከፍተኛ ተራራዎች ያሉበት ቢሆንም ሸለቆዎቹ እጅግ ዝቅ ያሉ ናቸው:: ከአንዳንድ ከፍተኛ ሥፍራዎች ቁልቁል ሲታዩ ተራራዎቹ በከፊል የተሰበሩ መሆናቸውን በግልጽ መረዳት ይቻላል:: ከሌላ ዘዋሬ ካልሆነ የምድርን የማይመስል ስሜትን ይሰጣል:: በዚህ ምድረ ፅፋዊ ሁኔታ፣ ዋልያዎች በአብዛኛው የሚኖሩት ከ2,500 ሜትር በላይ፣ ከ4,000 ሜትር በታች በሆኑ አካባቢዎች ነው:: በቀድሞ ዘመን መላው የሰሜን ተራራዎች ለዋልያ አገሩ የነበሩ ቢሆንም፣ አሁን

የቀሩት ዋልያዎች የሚኖሩት በዚሁ ከፍታ ውስጥ የተራራዎቹን ግድግዳ የመሰለ ዳገት ይዘው ነው:: የዚህ ዳገት ርዝመቱ 30 ኪሎ ሜትር ያህል ይሆናል:: ይኸንን አቀበት የሸፈኑት የተለያዩ ዕፅዋት፣ የዋልያ ምግብና መሸሸጊያው ናቸው:: የቀድሞው ሳይሆን አሁን ያሉበት ሥፍራ፣ አሁን ካሉት ጥቂት መቶዎች የበለጠ ቁጥር ሊያኖር እንደሚችል ይታወቃል:: የዓለም አቀፍ የተፈጥሮ ጥበቃ ማኅበር (IUCN) እንደሚገልጸው፣ የዋልያ ዘር ለመውደም በቋም ያለ ነው:: በሕይወት ካሉት ዋልያዎች አብዛኛዎቹ የሚገኙት በሰሜን ተራራዎች ብሔራዊ ፓርክ ነው:: የተፈጥሮ ጠላታቸው ለትልልቆቹ ጅብ ሲሆን፣ ለግልገሎቹ ደግሞ ቀበሮና የሎስ ናቸው:: የፈጇቸው ግን ሰዎች ናቸው:: በሰው ከመገደላቸው ሌላ የተፈጥሮ መኖርያ ሥፍራቸውን በብዛት በሰው መነጠቃቸው፣ የቁጥራቸው መመናመን ዋና ምክንያት ተደርጎ ይወሰዳል::

ሰሎሞን ይርጋ (ዶ/ር) ‹‹አጥቢዎች›› (2000)

Page 68: ERROR: The requested URL could not be retrieved ERROR The requested URL could not be retrieved While trying to process the request: TEXT HTTP/1.1 Host: Proxy-Connection: keep-alive

www.ethiopianreporter.com

ገጽ 20 | እሑድ | ጥር 19 ቀን 2005ክፍል-2

“በተያዘለት የጊዜ ገደብ ይጠናቀቃል” ይህን ያሉት የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ኢኒጂነር ፍቃዱ ኃይሌ ናቸው:: የቦሌ መንገድ መዘጋት በከተማዋ ውስጥ መጨናነቅ ስለመፈጠሩ በሪፖርተር ለቀረበላቸው የሰጡት ምላሽ ነው:: ከቦሌ ወደ ሜክሲኮ ለመሄድ በአትላስ ማቋረጥ፣ አትላስ ሲሞላ በዘሪሁን ሕንፃ ወደ ዑራኤል፣ ይህ ካልተቻለ በዘሪሁን ሕንፃ በሲግናል ካዛንቺስ፣ እነዚህ ሁሉ ሞልተው ደግሞ ካልሰለቸዎት ሌላ አማራጭ በሲግናል ቤልኤር አራት ኪሎ ሜክሲኮ መጓዝ ያስፈልጋል:: እንግዲህ ከተማው በቦሌ መንገድ መዘጋት ሳቢያ እንዴት እንደተወጠረ መገንዘብ ይቻላል ፎቶ ታምራት ጌታቸው

ፎ ቶ ዜ ና

Page 69: ERROR: The requested URL could not be retrieved ERROR The requested URL could not be retrieved While trying to process the request: TEXT HTTP/1.1 Host: Proxy-Connection: keep-alive

www.ethiopianreporter.com

ገጽ 21 | እሑድ | ጥር 19 ቀን 2005 ክፍል-2ማስታወቂያ

Invitation for Bid (IFB) No. 02/2013Concern Worldwide is a non-governmental, international, humanitarian organization which envisions a world where no one lives in poverty, in fear or oppression, where all have access to a decent standard of living and have opportunities and choices essential to a long, healthy and creative life. In order to implement our development and emergency relief operations in different part of the country specifically; Amhara, Tigray, Oromia and SNNPR regions, Concern Worldwide is seeking for competent and reliable Car Rental service provider Companies which fulfills our transport needs.

Required vehicles type and model:

S/no

Vehicles Type Model Engine

type Year of manufactured

Place of operation

1Toyota L/Cruiser Station Wagon

HZJ-80/81 1HZ 1992 and aboveAcross the country

2Toyota L/Cruiser Station Wagon

HZJ-105 1HZ 2000 and aboveAcross the country

3Toyota L/Cruiser Hard -Top (Long base)

HZJ-75 1HZ 1996 and aboveAcross the country

4Toyota L/Cruiser Hard -Top (Long base)

HZJ-78 1HZ 2000 and aboveAcross the country

5Toyota L/Cruiser Single Pick-Up

HZJ79 1HZ 2002 and aboveAcross the country

6Toyota HI-LUX Double cabin Pick-up

LAN25L 5L 2002 and aboveAcross the country

7 Toyota Corolla NZ120L 2NZ 2003 and aboveAddis Ababa

8 Toyota Min-Bus 13 Seat 5L 2000 and above Addis Ababa

9Toyota Min-Bus Costar 25 seat

1HZ 2002 and above

Addis Ababa and with in 150km radios from AA

Other requirement and documents that need to be submitted with the offer are:- • Renewed trade license, TAX identification certificate and VAT registration

certificate.• Summery table for the vehicles owned by the company with their model • Fuel cost will be covered by Concern on reimbursement basis i.e. the company

should present its vehicles with full tank before departed and Concern will return the vehicle with full tank.

• Recommendation letters from at least five similar organizations• Vehicle plate should be code 3-xxxxx • Copy of vehicle’s registration certificate must be presented at the time of

deployment • Vehicles must be insured and a copy of renewed Insurance certificate should be

presented whenever the vehicle is available for the trip. Note: 1. The floating day of the bid began from 27 January, 2013

2. Bidders can submit their offer either for single items, or collectively

3. Bidders should submit their offer with sealed envelope to Concern Worldwide-Ethiopia Country office, which is located around Sholla Market on or before February 12, 2013 at 10:00A.M to the following address.

Concern WorldwideYeka Sub City, Woreda 08

House No- 260, Sholla Market P.o. Box 2434

Tel. 00-251-11-661-173 or 651-2360Addis Ababa, Ethiopia

4. Bid will be opened in the presence of the bidders’ representatives who choose to attend in person at Concern Worldwide- Country office on February 12, 2013 at 10:30 AM

5. Rental fee must be on daily bases without fuel

6. Bidder must list the required vehicles only

7. If Bidders require further clarification, bidders can contact our Logistics unit at any of working hours before the deadline with following address; telephone +251-116-611730 e-mail [email protected]

8. Late submission will be rejected

9. Concern World Wide reserves the right to reject all or part of the bids.

The Organization:SNV is a non-profit, international development organization, established in the Netherlands in 1965, being present on the ground in developing countries for over 40 years, and now operate in 36 countries in Africa, Asia, Latin America and the Balkans. SNV aims at alleviating poverty by enabling those on the lowest incomes to be part of social and economic networks and so increase their income and employment opportunities. More than half of SNV’s work focuses on economic and private sector development. Alongside this, SNV focuses on three sectors – Agriculture, Water, Sanitation & Hygiene, and Renewable Energy. By focusing on three key roles, in combination with our local presence, SNV aims to boost the effectiveness, scale and sustainability of its work in three roles i.e. Advisory services - through which SNV create solutions with local impact; Knowledge networking - which expands knowledge bases for sustainable poverty reduction; and Evidence-based advocacy - which improves the enabling environment.Background of the assignment:SNV Ethiopia is implementing a 4-year program in two regions, namely Amhara and Oromia Region. The program intends to increase the output marketing of selected cooperative unions and support42,000 farming households increasing their income. SNV, with its recognized leadership in value chain development and technical expertise in private sector development in Ethiopia provides technical assistance on value chain development and build the capacity of unions to improve the business services to their members. For the monitoring and evaluation of this new project a baseline needs to be conducted.2. Assignment/responsibilities• Support in the design of a Baseline Study in accordance to outcome and impact indicators

• Conduct Baseline study for new SNV project

• Train, coach and monitor all enumerators

• Conduct survey with farmers and cooperative leaders as well as open-ended in-depth interview with probing questions

• Keep an accurate database of farmers included in baseline (both treatment and control group) for future follow-up surveys

• Mitigate for measurement errors as to ensure reliability of the data

• Analyse both qualitative and quantitative data

• Perform advanced statistical analysis on data using SPSS

All reports and data collected will remain SNV’s intellectual property and used and shared at their discretion and should be labeled as such.8. CONSULTANT SPECIFICATIONRequirements:Competency and qualification requirements:

The following are the required competencies and qualification requirements of the consultants with:• Master’s degree with an academic level of working and thinking• Experience in both quantitative and qualitative data collection• Experience with Randomised Control Group Trials • Experience in statistical data analysis• Good access and knowledge of secondary data sources (e.g. CSA) to complement survey data• Accurate mathematical skills and logical thinking• Advanced excel and SPSS skills • Sound understanding of economics and marketing of agricultural commodities• Strong intercultural and communication skills• Ability to produce brief and to-the-point analysis reports supported by accurate data and figures• Availability of team of motivated, skilled and trained surveyors• Willingness to go beyond the assignment on given and provide long term servicesDesirableo Knowledge of Agriculture and Rural Development Sector in Ethiopia and o Knowledge on Cooperative development sector, o Excellent communication and writing skills11. Submission: All interested candidates will submit the following documents as part of their proposal prepared in accordance to the TOR and submit to SNV Ethiopia Office located in Kirkos Sub City, Kebele 13/14, House No. 108, P.O. Box 40675; Addis Ababa, during working hours within 5 working days from the date of this announcement. 1. Technical proposal - the technical proposal should reflect how the consultant will undertake all of the tasks in the TOR, and demonstrate clearly how information on the different selection criteria will be presented. 2. Financial budget (with explanation of line items) 3. AppendicesSuccinct CVs of (up to five) key personnel proposed for the consultancy work stating:• General profile of consultants who will be conducting the field-work• Capability statement• Reference sample of related past work. if any All submission of interest should be sent in hard copy and electronic format to Human Resources Office, SNV Ethiopia, P.O. B ox 40675; Addis Ababa; E-mail: [email protected] or [email protected]; Tel: 0114 654386; Fax: 0114 65 43 88 The bid document shall be submitted in a sealed bid in English language as described in the term of reference (TOR).

Call for Consultancy Services(Baseline Survey)

Page 70: ERROR: The requested URL could not be retrieved ERROR The requested URL could not be retrieved While trying to process the request: TEXT HTTP/1.1 Host: Proxy-Connection: keep-alive

www.ethiopianreporter.com

ገጽ 22 | እሑድ | ጥር 19 ቀን 2005ክፍል-2

በምሕረት አስቻለው

ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የሙያ ማኅበራት ቁጥር እየጨመረ በተወሰነ መልኩ የአባላት ቁጥርም እንደዚያው እያደገ መምጣቱ አያከራክርም:: ሁለት ሦስት ከዚያም በላይ አሠርት አስቆጥረው ሥርዓቶችን መሻገር የቻሉ ኢትዮጵያዊ የሙያ ማኅበራትም አሉ:: የሙያ ማኅበራቱ ጥንካሬ፣ ተፅዕኖ ፈጣሪነት ካስቆጠሩት ዕድሜ አንጻር ሲታይ የሚለውን በተመለከተ የተለያዩ አስተያየቶች ይሰነዝራሉ::

በሌላ በኩል በተመሳሳይ የሙያ ዘርፎች ላይ ሁለት ምን አልባትም ከዚያ በላይ የሙያ ማኅበራት መኖራቸው ሲስተዋል የተለያዩ ጥያቄዎች እንዲነሱ የግድ ይላል:: አሠርት ያስቆጠሩና ዘመናትን የተሻገሩ የሙያ ማኅበራት አወቃቀርና አደረጃጀት የዘርፉን ወጣት ባለሙያ ለማቀፍ ምን ያህል ብቁ ነው? የሚሉና ሌሎችም መሰል ጥያቄዎች ከሙያ ማኅበራት ጋር በተያያዘ የሚነሱ ጥያቄዎች ናቸው::

እ.ኤ.አ. በ1991 የተቋቋመው የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ባለሙያዎች ማኅበር በአሁኑ ወቅት 3,500 የሚሆኑ አባላት አሉት:: ምንም እንኳ የአቅም ውስንነት ቢኖርም ለአባላትም ለአገሪቱንም እየሠራ መሆኑን የማኅበሩ ጥናት አድራጊ ዶ/ር አሰፋ አድማሴ ይናገራሉ::

ማኅበሩ በርካታ ወጣት አባላት እንዳሉት እነዚህን አባላት አሳታፊ የሆኑ ፕሮጀክቶችም ተግባራዊ የሆኑበት አግባብ መኖሩን ለሚናገሩት ዶ/ር አሰፋ ማኅበሩ በተለያዩ ጊዜያት የተለያዩ የአገሪቱ የኢኮኖሚ ፖሊሲዎችን እንዲሁም ውሳኔዎችን በሚመለከት የሚጠበቅበትን ባለማድረግ ይልቁንም ዝምታን በመምረጥ እንደሚወቀስ በመግለጽ ጥያቄ አንስተን ነበር::

ፖሊሲዎች ላይ ተፅዕኖ ማሳደር ከመነሻውም የማኅበሩ ዓላማ አይደለም:: ይልቁንም ለአገሪቱ ኢኮኖሚ የሚበጁ ፖሊሲዎች ይወጡ ዘንድ ጥናት አድርጐ ስለሁኔታዎች አዎንታዊና አሉታዊ ጐን መረጃ በማቅረብ ፖሊሲ አውጪዎች መረጃን መሠረት ያደረገ ውሳኔ እንዲሰጡ ማድረግ መሆኑን ዶ/ር አሰፋ ያስረዳሉ:: በየዓመቱ ማኅበሩ በሚያወጣቸው የሕትመት ውጤቶችም ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮችን በሚመለከት ሰፊ ግንዛቤ እንደሚያስጨብጡም ያስገነዝባሉ::

‹‹ችግሩ መገናኛ ብዙኀን በተለይም የግል ሚዲያው የመንግሥትን ፖሊሲዎች ሙያዊ መሠረት በሌለው

ማ ህ በ ራ ዊ

መልኩ እንድንተች፤ እነሱ ማለት የሚፈልጉትን እንድንል ይፈልጋሉ:: በሌላ በኩል ያለው ደግሞ መንግሥት ተመሳሳይ ፖሊሲዎችን እንድንደግፍ ይፈልጋል፤›› በማለት ይህን የሁለት በኩል ጉተታ ማኅበሩ እንደ አንድ ተግዳሮት እንደሚያየው ይናገራሉ:: አሳቸው እንደሚሉት ምንም እንኳ የመንግሥትን አጠቃላይ አቋም የሚደግፍ አልያም የሚቃወሙ አባላት ቢኖሩም አቋማቸው የግል በመሆኑ ማኅበሩ መሠረታዊ ሚዛን የሚያደርገው ሙያውን ነው:: በዚህ መሠረትም የማኅበሩን ዓላማ የሚደግፍ፣ መመዘኛ መስፈርቶችን የሚያሟላ ማንኛውም ሰው አባል መሆን ይችላል:: ‹‹ማኅበሩ እንዲሠራ እንዲያበረክት የሚፈለገውም ነገር በጣም ሰፊ ነው:: በሌላ በኩል አቅሙ ውስን ነው:: ቢሆንም ግን ማኅበሩ ለወጣት የኢኮኖሚ ባለሙያዎች ቦታ አለው፤›› ይላሉ::

ከተመሠረተ 53 ዓመታትን ያስቆጠረው የኢትዮጵያ ደራስያን ማኅበር በጥሩ ሁኔታ ቢንቀሳቀስም የዕድሜውን ያህል አለመሥራቱን የማኅበሩ ፕሬዚዳንት አቶ ጌታቸው በለጠ ይናገራሉ:: የራሱ ቋሚ ቢሮ መኖር፣ የሥራ አስፈጻሚዎች ጽናት፣ የ ሕትመትና የሥርጭት ተዘዋዋሪ የባንክ ሒሳብ በመክፈት የአባላት ሥራዎች ለሕትመት የሚበቁበትን መንገድ ማመቻቸት እንደ ስኬት ከሚቆጠሩ ነገሮች ቀዳሚዎቹ ናቸው:: ማኅበሩ የራሱን ሕንፃ ለመገንባት በመንቀሳቀስ ላይም ይገኛል::

‹‹ማኅበሩ የሚገባውን የዕድሜውን ያህል ሮጧል ለማለት አልደፍርም:: ቀለማት፣ እነሆና ብሌንን የመሳሰሉ የማኅበሩን ልሳናት በዘላቂነት ማስቀጠልም አልተቻለም፤›› የሚሉት አቶ ጌታቸው ጐን ለጐን የሴት ደራስያን ማኅበር መመሥረት መልካም መሆኑን ይናገራሉ:: አባል ለመሆን ወጣት ደራስያን ወደ ማኅበሩ በየጊዜው እንደሚሄዱ፤ በአማካይ በወር ከ10 እስከ 15 አዳዲስ አባላት ማኅበሩን እንደሚቀላቀሉ፤ ነገር ግን ማኅበሩ በወጣት የማኅበሩ አባላት ዕርምጃ ልክ መራመድ አለመቻሉን ይገልጻሉ::

‹‹ያገባናል በምንለው አገራዊ ጉዳይ ላይ መሳተፍ ይኖርብናል:: በእርግጥ አሁንም በተለያዩ ብሔራዊ ኮሚቴዎች ውስጥ እንሳተፋለን፤›› ብለዋል::

ወይዘሪት ማጂ ኃይለ ማርያም ሶሻል ወርከር ስትሆን የኢትዮጵያ ሶሻል ወርከሮች፣ ሶሾሎጂስቶችና አንትሮፖሎጂስቶች ማኅበር ቦርድ አባልም ነች:: የቦርድ አባል በመሆን እያገለገለች ካለችው ማኅበር በመነሳት በሙያ ማኅበራት በኩል አባላት ወደ ሙያ ማኅበራት የመሔድና የመቀላቀላቸው መነሻ አሳብ ስህተት እንዳለው ታዝባለች:: የዚህ ወይም የዚያ ሙያ ማኅበር አባል ብሆን እኔ ምን እጠቀማለሁ? እንጂ የማኅበራቱ አባል በመሆን በሙያዬ ምን ማበርከት እችላለሁ? የሚለው ነገር አለመቅደም፣ የአባላት በጐ ፈቃደኝነት አለመኖር በተለያዩ የሙያ ማኅበራት ውስጥ ችግር እንደሆነ ይሰማታል::

‹‹የአንድ ሙያ ማኅበር አባል ለመሆን ሲታሰብ ማኅበሩ ምን ያደርግልኛል? አባል ብሆን ምን ዓይነት ጥቅም አገኛለሁ ነው የሚባለው:: እኔ ላበረክት የምችለው ምንድን ነው የሚባል ነገር የለም፤›› የምትለው ወይዘሪት ማጂ የዚህ ፖይነቱ ጥቅም ብቻ የመፈለግ አካሔድ የበጐ ፈቃደኝነትን ስሜት እንደሚያጠፋ፤ አባላት እንዲሁም የሙያ ማኅበራት ተቀጣሪ ሠራተኞችንም ጭመር ወደ አልተፈለገ አቅጣጫ እንደሚወስድ ትናገራለች:: እነዚህ ሰዎች ለማኅበራቸው የመጡ ፕሮጀክት ሥራዎችን የግላቸው በማድረግ እስከመጠቀም ገፍተው ሊሔዱ እንደሚችሉ ያረጋገጠችባቸውን አጋጣሚዎች በማሳያነት ገልጻልናለች::

የሴት ሠዓልያንና ደራስያን ማኅበር ፕሬዚዳንት የሆነችው አርቲስት ስናፍቅሽ ዘለቀም በተለያዩ የሙያ ማኅበራት አባላት በኩል ማኅበሩ ምን ያደርግልኛል? በምን መልኩ ጥቅም አገኛለሁ የሚለው ነገር አስቸጋሪ እንደሆነ የእነሱ ማኅበርም ከዚህ ውጭ አለመሆኑን ትናገራለች::

‹‹የእኛ ማኅበር ሦስት ሙያዎችን ያቀፈ ነው::

ይህ አንድነት መታየት ያለበት እንደ ጥንካሬ ቢሆንም ብዙ ሥራዎች የሚመጡት በዚህ መልክ በመሆኑ እኛ ለብቻችን ብንሆን ይሻለናል የሚል ነገር ተነስቶ ሁሉ ያውቃል:: ይህ ጥቅምን ብቻ ከማሰብ የሚመጣ ይመስለኛል:: የምናዘጋጃቸው የሕትመት ውጤቶችን ለአባላት የሚሸጡት ከመደበኛ ዋጋ ዝቅ ተደርጐ ነው:: ነገር ግን የሕትመት ውጤቶች ሽያጭ ከአባላት የሚገኘው የአባልነት ክፍያም በጣም ትንሽ ነው:: አባላት በየዓመቱ አባልነታቸውን እንዲያድሱ የግድ መወትወት ያስፈልጋል:: ማኅበሩ ምንም አላደረገልንም ወይም እንዲህ ሳይሆን እንደዚያ ብሎ የሚወቅስ ግን ብዙ ነው፤›› የምትለው ወይዘሪት ማጂ ናት::

የአንጋፋና የወጣት አባላትን ግንኙነት በሚመለከት በእነሱ ማኅበር ያስተዋለችው የታየ ነገር ባይኖርም በሙያ ማኅበራት አንጋፎች ረዥም ጊዜ ኃላፊ ወይም አመራር ሆነው ሲቆዩ ወጣቱ አባል ነገሮችን ሰንጥቆ ወደ ላይ ማለፍ የሚሞክርበት ሁኔታ ሊኖር እንደሚችል ይሰማታል:: ወጣት አባላቱ በዚህ ካልተሳካላቸው የሚፈልጉት ዓይነት መዋቅር ያለው፣ በሚፈልጉት መልኩ የሚንቀሳቀስና ውጤታማ ሊሆን የሚችል የተመሳሳይ ሙያ ተመሳሳይ ማኅበር እስከ መመሥረት ሊሔዱ ይችላሉ::

በተለያዩ ስትራቴጂካዊ ምክንያቶች ባለፈው የፈረንጆች ዓመት የተቋቋመው የጐንደር ዩኒቨርሲቲ ሴት መምህራን ማኅበር ባለው የማኅበሩ የሥርዓተ ጾታ አደረጃጀት ውስጥ መንቀሳቀስ ሲገባቸው ሌላ ማኅበር በማቋቋማቸው በኢትዮጵያ መምህራን ማኅበር መወቀሳቸውን ከሴት መምህራኑ ማኅበር መረጃ አግኝተናል:: አንድነት ጥንካሬ ቢሆንም የቀደመውና ትልቁ ማኅበር በሚፈልጉት መልኩ ሊያሠራቸው የሚችል አደረጃጀትና እንቅስቃሴ ከሌለው የዩኒቨርሲቲው ሴት መምህራን ማኅበርን ማቋቋም ምንም ክፋት እንደሌለውም ማኅበሩ ለሪፖርተር ገልጿል::

የሙያ ማኅበራት መሠረት አገልግሎት ወይስ የአባላት ጥቅም?

Page 71: ERROR: The requested URL could not be retrieved ERROR The requested URL could not be retrieved While trying to process the request: TEXT HTTP/1.1 Host: Proxy-Connection: keep-alive

www.ethiopianreporter.com

ገጽ 23 | እሑድ | ጥር 19 ቀን 2005 ክፍል-2

በታደሰ ገብረማርያም

የኢትዮጵያ ስኳር ሕመም ማኅበር በዋና ዋና ከተሞችና አካባቢዎች ለሚገኙ፣ ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች ለሆኑና የስኳር ሕመም ለደረሰባቸው ሁለት ሺሕ ሕፃናት ነፃ የሕክምና አገልግሎት፣ እንዲሁም በመላ አገሪቱ ለሚገኙ ጠቅላላ ሐኪሞች በስኳር ሕመም ዙሪያ ትኩረት ያደረገ የአቅም ግንባታ ሥልጠና በመስጠት ላይ ነው::

ዶክተር አህመድ ረጃ የማኅበሩ ፕሬዚዳንት እንዳብራሩት ነፃ የሕክምና አገልግሎት የሚያገኙትም በአዲስ አበባ፣ በድሬዳዋ፣ በጅማ፣ በሐዋሳ፣ በባህርዳር፣ በመቀሌና በጎንደር ከተሞችና አካባቢዎች የሚገኙ የስኳር ሕሙማን ሕፃናት ናቸው::

ለጠቅላላ ሐኪሞቹ ሥልጠናውን የሚሰጡት ደግሞ በስኳር ሕመም በቂ ዕውቀትና ችሎታ ያላቸው አሥር ሐኪሞች ሲሆኑ አንድ ሐኪም 20 ጠቅላላ ሐኪሞችን እንዲያሰለጥን እየተደረገ ነው::

ለሕፃናቱ ከሚሰጠው የሕክምና አገልግሎት መካከልም ኢንሱሊን፣ የኢንሱሊን መውሰጃ መርፌ (ስሪንጅ)፣ ግሎኮሜተር፣ ስትሪፕ፣ ሂሞግሎቢን ኢ.ዋን.ሲ ምርመራና በስኳር ሕመም ላይ ያተኮረ ግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት መሆኑን አስረድተዋል::

ሂሞግሎቢን ኢ.ዋን.ሲ ምርመራ የሦስት ወራት አማካይ የስኳር ውጤትን የሚገልጽ ወይም ያለፈው የሦስት ወራት ስኳር እንዴት እንደነበር የሚናገርና በየትኛውም የመንግሥት ጤና ድርጅቶች የማይገኝ ውድ ምርመራ መሆኑን ገልጸዋል::

የስኳር ሕመም ሕክምና ውጤታማ ከሚሆንባቸው ወይም ከሚሻሻልባቸው መንገዶች መካከል አንደኛውና ግንባር ቀደሙ ዘዴ በደም ውስጥ ያለውን የስኳር መጠን/ደረጃ በጥሩ ሁኔታ መቆጣጠር ሲቻል ነው::

ማኅበሩ ለሕፃናቱ ነፃ የሕክምና አገልግሎት የሚሰጠው “ቼንጂንግ ዳያቤቲክስ ኢን ችልድረን” የሚል ፕሮጀክት በመቅረጽ ሲሆን፣ ለጠቅላላ ሐኪሞች የአቅም ግንባታ ሥልጠና የሚሰጠው ደግሞ “ቦዲ ዶክተር ኢኒሼቲቭ” የሚል ፕሮግራም በማውጣት ነው:: ለፕሮጀክቱና ለፕሮግራሙ ተግባራዊነት ዋና መሥሪያ ቤቱ ዴንማርክ የሚገኘውና “ኖቫ ኖርዲስክ” የተሰኘ የመድኃኒት አምራች ኩባንያ አስፈላጊውን ፈንድ በመስጠት እንደሚተባበር ተናግረዋል::

ከተጠቀሰው ፕሮጀክት ሌላ በዘጠኝ ክልሎችና በሁለት የከተሞች አስተዳደር በተመረጡ ሆስፒታሎች ለሚገኙ የሕክምና ባሙያዎች በዓመት አራት ጊዜ በስኳር ሕመም ዙሪያ ትኩረት ያደረገ ሥልጠና እንደሚሰጣቸው ዶክተር አህመድ ተናግረዋል::

ሚስተር ጂስፒር ሂላንድ የኖቫ ኖርዲስክ ከፍተኛ ምክትል ፕሬዚዳንት ‹‹በፕሮጀክቱ መሠረት ኢትዮጵያን ጨምሮ በመላው ዓለም የሚገኙና የስኳር ሕመም ያደረባቸውን 10 ሺሕ ሕፃናት ነፃ የሕክምና አገልግሎት እያገኙ ናቸው:: ይህንን አኀዝ ወደ 15 ሺሕ ከፍ ለማድረግ እየሠራን ነው፤” ብለዋል::

እንደ ከፍተኛ ምክትል ፕሬዚዳንቱ አነጋገር ከሆነ፣ ኢንሱሊን ከመገኘቱ ከ1914 ዓ.ም. በፊት የስኳር ሕመም ፈውስ ያልተገኘለት ከመሆኑ ባሻገር ሕክምና የሌለውና ትኩረት የጎደለው ነበር:: ዛሬ ላይ ፈውስ ባይገኝለትም በጣም ጥሩ እንክብካቤና አያያዝ እንዳለው በእርግጠኝነት

ማ ህ በ ራ ዊ

የበሬ ችምችም (ደረቅ) ወጥ (ለ8 ሰው)

አስፈላጊ ጥሬ ዕቃዎች• 1 ኪሎ ግራም የታላቅ ወይም

የሽንጥ ሥጋ• 4 መካከለኛ ጭልፋ (600 ኪሎ

ግራም) የደቀቀ ቀይ ሽንኩርት• 3 የሾርባ ማንኪያ ርጥብ ቅመም• 2 የሾርባ ማንኪያ ጥቁር ቅመም• 1 የሾርባ ማንኪያ መከለሻ• ግማሽ የሻይ ማንኪያ ምጥን

ሽንኩርት• 4 የሾርባ ማንኪያ ቅቤ• 6 የሾርባ ማንኪያ (100 ሚሊ

ሊትር) በጠጅ ወይም በውኃ የተበጠበጠ ርጥብ ቅመም

• 6 የሾርባ ማንኪያ (100 ሚሊ ሊትር) ዘይት

• 3 የሾርባ ማንኪያ አዋዜ• 1 የሻይ ማንኪያ ጨው

አዘገጃጀት1. ቀይ ሽንኩርቱን በውኃ ብቻ

ማብሰል፤2. ምጥን ሽንኩርት መጨመርና

ማቁላላት፤3. ዘይት መጨመር፤4. አዋዜውንና ጥቁር ቅመሙን

ጨምሮ በደንብ እንዲንተከተክ መተው፤

5. ሥጋውን አገንፍሎ ደቀቅ አድርጐ መክተፍና ውኃው መጠጥ ሲል መጨመር፤

6. ውኃው ደረቅ ሲል ትንሽ ሙቅ ውኃ ጠብ እያደረጉ ማሸት፤

7. በወፍራሙ እያንተከተኩ ማብሰልና ጨው መጨመር፤

8. ርጥብ ቅመምና ቅቤ ጨምሮ በወፍራሙ ማንተክተክ፤

9. በጠጅ ወይም በውኃ የተበጠበጠ ርጥብ ቅመምና መከለሻውን አስተካክሎ ወፍራም መረቅ እንዲኖረው በማድረግ አንሰክስኮ ማውጣት፡፡

አስ ሼፍ) የባህላዊ ምግቦች አዘገጃጀት፣ 2003)

የስኳር ሕሙማን ሕፃናት ነፃ ሕክምና እየተሰጣቸው ነው

መናገር ይቻላልም:: በአሁኑ ጊዜ በመላው ዓለም 303 ሚሊዮን የሚሆኑ

የስኳር ሕሙማን እንዳሉ፣ 20 ዓመት በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የሕሙማኑ ቁጥር 560 ሚሊዮን እንደሚያሻቅብ ወይም ከ10 አዋቂዎች መካከል አንዱ የስኳር ሕመምተኛ ሊሆን እንደሚችል ይገመታል:: ከዚህም ሌላ በየዓመቱ 10 ሚሊዮን ሰዎች በስኳር ሕመም ሳቢያ ለሕልፈተ ሕይወት ይዳረጋሉ::

ኢትዮጵያ በአፍሪካ ውስጥ በሕዝብ ብዛት ሁለተኛ አገር ብትሆንም የስኳር ሕሙማን ቁጥር 1.3 ሚሊዮን ወይም 3.3 በመቶ ነው ተብሎ እንደሚገመት ሆኖም ሁኔታው አሳሳቢ እየሆነ ቢመጣም የሕሙማኑ ብዛት ከሌሎች አገሮች ጋር ሲወዳደር ይህን ያህል አስደንጋጭ እንዳልሆነም ተናግረዋል::

ሚስተር ማድስ ቦ ላርሰን የኩባንያው ምክትል ፕሬዚዳንት ኩባንያው በኢንሱሊንና በሕክምና እጦት የተነሳ ማንም ቤተሰብና ሕፃን በስኳር ሕመም ሳቢያ መሞት የለባቸውም የሚል አቋም እንዳለው፣ ለዚህም እውን መሆን የስኳር ሕመምን ለማዳን የሚያስችል መድኃኒት ለማግኘት ለሚካሄደው ምርምር ኩባንያው በየዓመቱ ሁለት ቢሊዮን ዶላር እንደሚያወጣ አስረድተዋል::

ኢትዮጵያ ውስጥ ለስኳር ሕሙማን የሚደረግላቸውን ሕክምናና እንክብካቤ በይበልጥ ለማጠናከር ኩባንያቸው ከኢትዮጵያ የስኳር ሕመም ማኅበር ጋር አብሮ የመሥራት ፍላጎት እንዳለውም አስታውቀዋል::

ዶክተር አህመድ ረጃ፣ ሚስተር ጂስፒር ሂላንድ፣ ሚስተር ማድስ ቦ ላርሰን በመግለጫው ወቅት

በጋዜጣው ሪፖርተር

በማሊ ከዓመት በፊት በተቀሰቀሰው የአክራሪዎች ውጊያ ሳቢያ 147 ሺሕ ማሊያውያን ቀያቸውን ለቀው ለመሰደድ ተገደዋል:: በቅርቡ የማሊን መንግሥት ከአክራሪዎቹ ውጊያ ለመታደግ በፈረንሳይ መንግሥት የተጀመረው ወታደራዊ ጣልቃ ገብነት ደግሞ ስደተኞቹን በዕርዳታ ለመድረስ የሚደረገውን ጥረት አስቸጋሪ አድርጐታል:: ስደተኞቹም ለከፋ ችግር እየተጋለጡ ነው::

ኦክስፋም ጂቢ ባለፈው ሳምንት በማሊ ያለውን ቀውስ አስመልክቶ ባሳተመው ሪፖርት፤ በማሊ በተከሰተው ቀውስ ምክንያት በችግር ውስጥ የነበሩ በአሥር ሺዎች የሚቆጠሩ ማሊያውያን ወደከፋ ችግር እየገቡ ነው ሲል አስጠንቅቋል::

የዕርዳታ ድርጅቶች የሁሉንም ስደተኞች መሠረታዊ ፍላጐት ለማሟላት በትግል ውስጥ ቢሆኑም፤ ማሊያውያን እየተጋፈጡት ያለው መከራ የሚያሳስብ እንደሆነም

ሪፖርቱ ያሳያል:: አምና በማሊ የተከሰተውን ግጭት ሽሽት አገራቸውን

ጥለው የተሰደዱ ማሊያውያን በቡርኪና ፋሶ፣ በሞሪታኒያና በኒጀር ይገኛሉ:: የማሊያውያኑ በእነዚህ አገሮች መጠለል ደግሞ በተቀባይ አገሮቹ ላይ ችግር እያስከተለ ነው:: በሰሜናዊ ማሊ የሚገኙ የታጠቁ አማፅያን ወደጐረቤት አገሮች በመግባት የማሊ ስደተኞችን ለውትድርና ይመለምላሉ፤ ያስጠጉ አገሮችም በደኅንነት ስጋት ውስጥ ከተዋል:: በስደት ከሚገኙት ውጪም በሺዎች የሚቆጠሩ ማሊያውያን ከሚኖሩበት ስፍራ ተፈናቅለዋል:: ካለፈው ዓመት ወዲህ ብቻ 220 ሺሕ ነዋሪዎች ከመኖሪያቸው የተፈናቀሉ ሲሆን በማሊ ሰሜናዊ ክፍል ታግተው ስለሚገኙ ነዋሪዎች ደግሞ በቂ መረጃ የለም::

በስደት ላይ ያሉትንም ሆነ ከመኖሪያቸው የተፈናቀሉትን ማሊያውያን ለመታደግ፤ የዕርዳታ

ድርጅቶች የተቻላቸውን እየሠሩ ነው:: ሆኖም ጦርነቱ እየተባባሰ በመምጣቱ የዕርዳታ ድርጅቶች አካሄዳቸውን ካልቀየሩ ቁጥሩ እየጨመረ የመጣውን ስደተኛ ለመታደግ ያቅታቸዋል፤ እንደሪፖርቱ::

በአዲስ አበባ እየተካሔደ ባለው 20ኛው የአፍሪካ ኅብረት ጉባኤ በማሊና በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጐ ያለውን ቀውስ የሚያመላክት የፎቶ ዓውደ ርዕይ ጥር 15 ቀን 2005 ዓ.ም. የተከፈተ ሲሆን ኦክስፋም በማሊ ቀውስ ላይ ያጠናቀረውን ሪፖርትም ይፋ አድርጓል::

ጥር 19 እና 20 ቀን 2005 ዓ.ም. የሚሰበሰቡት የአፍሪካ ኅብረት አባል አገሮች መሪዎችም፤ በአህጉሪቷ በሚታዩ ቀውሶች በተለይም በማሊ፣ በኮንጐ፣ በደቡብ ሱዳንና በሶማሊያ ላይ ትኩረት ሰጥተው የመፍትሔ አሳብ ያስቀምጣሉ ተብሎ ይጠበቃል::

ከ140 ሺሕ በላይ የማሊ ስደተኞች ለከፋ ችግር እየተጋለጡ ነው

የማሊና ኮንጎ ቀውስ የሚያሳይ የፎቶ ዐውደ ርዕይ በአዲስ አበባ ተከፈተ

Page 72: ERROR: The requested URL could not be retrieved ERROR The requested URL could not be retrieved While trying to process the request: TEXT HTTP/1.1 Host: Proxy-Connection: keep-alive

www.ethiopianreporter.com

ገጽ 24 | እሑድ | ጥር 19 ቀን 2005ክፍል-2

ማስታወቂያ

Page 73: ERROR: The requested URL could not be retrieved ERROR The requested URL could not be retrieved While trying to process the request: TEXT HTTP/1.1 Host: Proxy-Connection: keep-alive

www.ethiopianreporter.com

ገጽ 25 | እሑድ | ጥር 19 ቀን 2005 ክፍል-2ማስታወቂያ

Page 74: ERROR: The requested URL could not be retrieved ERROR The requested URL could not be retrieved While trying to process the request: TEXT HTTP/1.1 Host: Proxy-Connection: keep-alive

www.ethiopianreporter.com

ገጽ 26 | እሑድ | ጥር 19 ቀን 2005ክፍል-2

ባ ህ ል

የያዓ መሠራ መስጊድ በቤኒሻንጉል ክልል ከሚገኙ ጥንታዊና ታሪካዊ ከሆኑ መስጊዶች መካከል አንዱ ሲሆን ብዙዎች በተለያዩ አጋጣሚዎች ወደ ስፍራው ተጉዘው የሚገረሙበትና መንፈሳቸው የሚረካበት የአምልኮ ቦታ ወደዚህ ስፍራ የተጓዝነው በእስልምና እምነት ተከታዮች ካሏቸው ሦስት ዓበይት በዓላት መካከል አንዱ የሆነውን የአረፋ (ኢድ አል አድሃ) ለማክበር ነው:: የአረፋ በዓል እስላማዊ ቅዱስ ቀን አረፋ በዓመተ ሒጅራ መሠረት በሐሳበ ጨረቃ በ12ኛው ወር ዙልሂጃ 10ኛ ቀን ላይ ይውላል::

ኢድ አልአድሃ የመስዋዕት በዓል ተብሎ ይከበራል:: ይሔም ነቢዩ ኢብራሂም ልጃቸውን እስማኤል ለመስዋዕት ሲያዘጋጁ በምትኩ በግ መስዋዕት የቀረበበት መሆኑ የሚያመለክት መሆኑን ድርሳናት ያመለክታሉ::

በሌላ ታሪክም አረፋ አደምና ሐዋ ከጀነት ወጥተው ለረዥም ጊዜ ተለያይተው ከሰነበቱ በኋላ በአራፋት ተራራ (ደብረ አራፋት) በመገናኘታቸው ‹‹ወአረፍተኒ ወአረፍቱ›› (አወቅሺኝ፣ አወቅኩህ) በመባባል ዳግመኛ መገናኘታቸው የሚታሰብበት ዕለት መሆኑንም ለማወቅ ችለናል::

እንዲህ የአረፋ በዓልን ለማክበር ያዓ መሠራ ከሚባል ስፍራ ከቤኒሻንጉል ክልል ዋና ከተማ ከሆነችው አሶሳን ማዕከል አድርጎ ለተንቀሳቀሰ ተጓዥ ከከተማዋ በስተደቡብ ምዕራብ አቅጣጫ 96 ኪሎ ሜትር ርቀት የሚገኝ ከማኦ ኮሞ ልዩ ወረዳ ከቶጎ በስተሰሜን ምዕራብ በ30 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ከሚገኝ ሥፍራ ነው:: ወደ ባምባሲ ከተማ የሚወስደው ጠጠር መንገድ 20 ኪሎ ሜትር ያህል ከተጓዙ በኋላ ጥቂት ኪሎ ሜትሮችን በጥርጊያ ጎዳና በመጓዝ ወደ መስጊዱ ቅጥር ግቢ መድረስ ይቻላል::

‹‹ያዓ›› ማለት መሰብሰብን አንድ መሆንን ያመለክታል:: በመስጊዱ ግቢ ውስጥ ሰፊ የእርሻ ልማት ሥራዎች ይከናወናሉ:: በዚህ ግቢ ውስጥ የተተከሉት አፀዶች መንፈስን ያድሳሉ:: ከእነዚህ ውስጥ ፅድ፣ ብርቱካን፣ ሎሚ የተለያዩ ፍራፍሬዎችና የማንጎ ዛፍ በብዛት ይገኛል:: ግቢው በጣም ውብና ማራኪ በተለይም ለአካባቢው ማኅበረሰብ ምቹ የፀሎትና የመኖሪያ ቦታ እንዲሆን ተደርጓል::

የዛፎቹ ጥላ ለእንግዶች ማረፊያም ሆነ ለሰላት መስገጃነት ሰፊ አገልግሎት ይሰጣል:: በየዛፉ ሥር በቡድን በቡድን የተቀመጡት ምእመናን እንደየ ባህላቸውና ወጋቸው፣ ተሰባስበው እርድ የሚፈጽሙበት ቅርጫ እየተካፈሉ ጽድቅ (ርዝቅ) የሚያደርጉበት ነው:: ሁሉም ሰው በቡድን በቡድን ሆኖ ይጨዋወታል:: ያለውን ይካፈላል ቡናውን ይጠጣል ይመራረቃል ፀሎቱንም ያደርሳል::

የያዓ መሠራ መስጊድ በ1942 ዓ.ም. እንደተመሠረተ ይነገራል:: ይህንን መስጊድ የመሠረቱት የናይጄሪያ ተወላጅ

ታሪካዊው ያዓ መሠራ መስጊድ

የሆኑት ሼህ አልፈትህ አህመድ ዑመር የተባሉ ታላቅ የሙስሊም ሀይማኖት መሪ አባት ናቸው:: ሼህ አልፈትህ አህመድ ሃይማኖታዊ ትምህርታቸውን በናይጄሪያ ተከታትለው ከጨረሱ በኋላ መቀመጫቸውን ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት በያዓ ሰመራ አካባቢ በማድረግ መስጊድ የቆረቆሩ ናቸው:: በያዓ መሠራና አጎራባች አካባቢዎች ለበርካታ የአካባቢ ተማሪዎች ቁርዓን በማስተማር ሺሂዎችንና ኡለማዎችን አፍርተዋል:: እሳቸው በዚህ ቦታ ብቻ ሳይሆን በተለያየ የኢትዮጵያ ቦታ እየዞሩ የእስልምና ትምህርትንና

ልማትን ሲያስተምሩ የነበሩ የሃይማኖት አባት እንደነበሩም ይነገራል::

የእሳቸው መካነ መቃብር በዚሁ ስፍራ ስለሚገኝ በአረፋ በዓል እሳቸውን እያሰበ ለሳቸውም ለራሱም ዱዓ (ፀሎት) አድርጎ የሚገባበት ነው::

የቤንሻንጉል ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ የሆኑት አቶ ኢስሐቅ አብዱልቃድር እንደገለጹት በየዓመቱ በዚህ በየዓ መሠራ የአረፋ በዓልን ለማክበር ከ20 ሺሕ በላይ ሰዎች ይመጣሉ:: በዚህም በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ የእምነቱ ተከታዮችና ጎብኚዎች የአረፋን በዓል ለማክበር ከአዲስ አበባ፣ አማራ፣ ከኦሮሚያ ክልል፣ አጎራባች ወረዳዎች እና እንዲሁም ከውጭ ሀገር ጭምር በመምጣት በበዓሉ ላይ ይታደማሉ:: ያዓ መሠራ በየዓመቱ ከሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች በእግር ወይም በመኪና ብዙ ቀናትን ተጉዘው ከሁለትና አንድ ሣምንት ቀደም ብለው ይሰባሰባሉ::

ከጎንደር የበዓሉ ታዳሚ የነበሩት ሼህ ሁሴን ዳውድ አሁን አካባቢውን ለመጎብኘት የተፈጠረውን ምቹ ሁኔታ ሲገልጹ ‹‹ወደዚህ አካባቢ ቢያንስ አምስት ጊዜ ተመላልሻለሁ:: ከዚያም በፊት ስለዚህ ታሪካዊ ቦታ ከአባቴና ከአያቶቼ በቂ መረጃ ነበረኝ:: በፊት መንገድ አልነበረም፣ በእግርም በበቅሎ በብዙ ስቃይና መከራ እየደረሰባቸው የጤና ችግር ተቋቁመው ፀሎት አድርገው እሳቸውን የሚዘይሩበት ሁኔታ ነበር:: ያ ሁሉ ልፋትና ድካሣ ተወግዶ አልሐምዲሊላሂ ረቢል ዓለሚን በመንግሥት ትልቅ ድጋፍ 1 ወር ይፈጅ የነበረው መንገድ ባንድ ቀን መሆኑ ትልቅ ዕድል ነው::›› ብለዋል::

ወደዚህ መስጊድ ለጉብኝት የሚመጣ ሁሉ ከመስጊዱ የሃይማኖት አባቶች መልካም የእንግዳ አቀባበል ባህል ጋር ተዳምሮ በቀላሉ የተለያዩ አገልግሎቶችን ማግኘት ይችላል::

በመስጊዱ ግቢ ውስጥ ረጅም ዕድሜ ያላቸው የሼህ አልፈትህ መኖሪያ በ1942 ዓ.ም. የተሠራች ጎጆ እና 20 ሜትር ቁመት ያለው መካነ መቃብራቸው በክብር ይገኛሉ:: ጥንታዊ ቁርዓን፣ ታሪካዊ ደብዳቤዎች የብራና ቅዱስ ቁርዓን መጻሕፍትና የመሳሰሉት በመስጊዱ ውስጥ ይገኛሉ:: ከመስጊዱ ግቢ ወጥተው የአካባቢው ባህላዊ ምግብ፣ ዕጣንና የመሳሰሉት የሚገኙበት ትንንሽ ገበያዎች ያገኛሉ:: በጣም ደስ የሚለው ገበያውን እንዳለፉ እንግዶችን የሚያዝናኑ የማኦ የባህል ቡድን አባላት መገኘታቸው ነው:: በየዓመቱ እነሱን ብሎ አገር አቋርጦ በጥዑም ዜማቸው መንፈሱን አድሶ የሚሄድ በርካታ ቱሪስት ያለ መሆኑንም ለማወቅ ችለናል::

ባህልና ቱሪዝም መጽሔት - ቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ

የያዓ መሠራ መስጊድ

ማስታ

ወቂያ

Page 75: ERROR: The requested URL could not be retrieved ERROR The requested URL could not be retrieved While trying to process the request: TEXT HTTP/1.1 Host: Proxy-Connection: keep-alive

www.ethiopianreporter.com

ገጽ 27 | እሑድ | ጥር 19 ቀን 2005 ክፍል-2

አሰናጅ፡- ሔኖክ ያሬድ፣ ምሕረት ሞገስ ዝ ን ቅ

ከ በ ር

እሱማ እኔም ነበረኝአንድ ደጃዝማችና አንድ ቀኛዝማች ከሌሎች ሹማምንቶች ጋር በመሆን ድግስ ላይ ይበላሉ፣ ይጠጣሉ:: በመካከሉ

ቀኛዝማቹ ውኃ ሽንታቸውን ለመክፈል ፈልገው አሽከራቸውን መክፈያ እንዲያመጣላቸው ያዙታል::አሽከሩም በታዘዘው መሠረት መክፈያውን ይዞ ከተፍ አለ:: ይሁንና ቀኛዝማች ሽንተቸውን ለመሽናት ቢፈልጉም

ፈሳቸው አብሮ መጣሁ መጣሁ እያለ አላሸና አላቸው:: ከዚያ አምልጦኝ ሰው ፊት ከምዋረድ ብቆይ ይሻላል በሚል፡-‹‹በል አንሳ›› ብለው መክፈያውን ወደዛ ገፋ ከማድረጋቸው አጠገባቸው የነበሩ ጓደኛቸው (ደጃዝማቹ)፡-‹‹አንተ እምቢ ካልህ እኔ ልሞክር›› አሉና ሽንታቸውን መሽናተ ሲጀምሩ አምልጦአቸው አንድ ሁለቴ ቷ…ቷ

አደረጉ:: በዚህን ጊዜ ከሚያመልጠኝ ይቅርብኝ ብለው የተቀመጡት ቀኛዘማች፡-‹‹አዬ ደጃዝማች ሌላ ታመጣለህ ብዬ ነው እንጂ እሱማ እኔም ነበረኝ›› አሉ ይባላል::

ካሕሣይ ገ/እግዚአብሔር፣ ‹‹ኅብረ-ብዕር›› (1998)

አገርም ጐረቤትም እየረዳኝበአንድ አካባቢ አንድ በስተእርጅና ዘመናቸው

ቆንጆ ወጣት ሴት ያገቡ አዛውንት እየሸመገሉ ሔዱና ዕድሜያቸው 105 ሞላ:: በአንጻሩ ሚስት እየቆነጀች፣ እያማረባት መጣ፤ አዛውንቱ ዕድሜያቸው እየገፋ ቢመጣም ሚስት ግን ልጅ መውለድዋን አላቆመችም::

የአካባቢው ሰው ግን ሚስት ጐረቤትዋ ከሆነ አንድ ጐረምሳ ጋር ሥውር ወዳጅነት መፍጠርዋን

ከመጠርጠር አልፎ ሁኔታውን በግልጽ ያውቅ ነበር:: አንድ ቀን ከአካባቢው ነዋሪዎች አንዱ አዛውንቱ ዘንድ ሔዶ፡-

‹‹አባት ለመሆኑ ይህን ያህል ዕድሜ ከሆነዎት በኋላ እንዴት ነው የሚወልዱት?›› አላቸው፤ ሽማግሌው የሰውየው ጥያቄ ከምን ጋር የተያያዘ እንደሆነ ገብቷቸው ኖሮ፡-

‹‹መቼም አገርም ጐረቤትም እየረዳኝ›› ብለው መለሱለት አሉ::ካሕሣይ ገ/እግዚአብሔር፣ ‹ኅብረ-ብዕር›› (1998)

300 እንስሳት በግለሰብ ቤትነዋሪነቱ በአሜሪካ አሃዩ ነው:: 300 የሚደርሱ ወፎች፣

ጥንችሎች፣ ዶሮዎችና ሌሎች እንስሳቶችን በቤቱ ሲያከማች ከርሟል:: ሮይተርስ እንደዘገበው ያለፈው ሳምንት እንስሳቱን በቤቱ ለሚሰበስበው ሰው ጥሩ አልነበረም:: ስለእንስሳት እውቀት ያለውና ለሚጠየቀው ሁሉ ተባባሪና ቀና የነበረው ግለሰብ የሚወዳቸው እንስሳቱን ለእንስሳት ተንከባካቢ እንዲያስረክብ ግድ ሆኖበታል:: ግለሰቡ የእንስሳትን መብት በመጣስ ወይም ከሌሎች ነጥሎ በማስቀመጥ ክስ ይመሰረትበት አይመሰረትበት ባይታወቅም ሁለት ውሾችና ጥቂት ድመቶች በቤቱ ማስቀረት እንዲችል ተፈቅዶለታል::

ኩላሊት በልመናየ28 ዓመት አሜሪካዊ ነው:: ከውልደት ጀምሮ

በዘር የሚተላለፍ የኩላሊት በሽታ አለበት:: ላለፉት 18 ወራት በቀን ለአራት ሰዓት ያህል በሳምንት ለሦስት ቀናት የዲያሉሲስ ወይም የኩላሊት እጥበት ሕክምና ሲወስድ ቆይቷል:: ዩፒአይ እንደዘገበው ወጣቱ ኩላሊቱን ለማስቀየር ገንዘብ ከመጠየቅ ይልቅ በየእግረኛ መንገዱ የሚተላለፈውን ሕዝብ ሲጠይቅ የነበረው ኩላሊት እንዲሰጡት ነበር::

ኤሪ ማርቲዝ የተባለው የኩላሊት ለማኝ ‹‹ይህን ያደረኩት ቤተሰቦቼ ሁሉ ለእኔ ኩላሊት መለገስ ስለማይችሉ ነው:: የገንዘብ ችግር የለብኝም:: ሙሉ ሕክምናዬን የሚሸፍነው ኢንሹራንስ ነው:: ኩላሊት ለሚሰጡኝም የሕክምና ወጪ ይሸፈንላቸዋል:: ኩላሊት እፈልጋለሁ፤›› ማለቱን ዘገባው ያሳያል::

ደባ ራሱን ስለት ድጉሱንከጥንት ጀምሮ በቃል ሲነገር የሚኖረውን የአባቶቻችንን

ተረት ብንመለከተው ብዙ የሚጠቅም ምክር እናገኝበታለን:: በአርእስቱ እንደተነገረው ክፉ ሥራ መሥራት ጉዳቱ

ለሠሪው ነው:: ንብ ሌላውን አጠቃሁ ስትል በመርዟ ትነድፋለች:: እሷም ይህን ክፋተ ከሠራች በኋላ አንድ ደቂቃ ሳትቆይ ትሞታለች:: የእሳት ራትም እንዲሁ መብራቱን ለማጥፋት ስትሞክር ተቃጥላ ራሷ ትጠፋለች:: ትንኝ ሰው ዓይን ለማወክ ትገባና ሕይወቷን አጥታ ተጎትታ ትወጣለች:: እንክርዳድን የዘራ እንክርዳድን ያመርታል ክፉ የሠራም ሰው በክፋቱ ይጠፋል:: በሰው የሚድነው በምነቱና በቅንነቱ ብቻ ነው:: አያሌው ተሰማ ዘብሔረ ጎጃም የካቲት 20 ቀን 1935 ዓ.ም.

ማስታወቂያ አምቦ ለጠበልና ነፋስ ለመለወጥ የምታስቡ፤

ክቡራኖችነፃነት ክብሬ በሚባለው ሆቴላችን እንግዶችን

በትሕትናና በፍቅር እንቀበላለን፤ አምቦ ከመውረዳችሁም በፊት አዲስ አበባ ፍልውሀ ግቢ ባለው ቡና ቤታችን አሽከር ልካችሁ የክፍል ቤቶችን ማዕረግ ልታስጠይቁ ትችላላችሁ::

አዘጋጅዎች:: ካብትህ ይመር አደራ ገብረ መስቀል ዋስ ይሁን

አዲስ ዘመን ታኅሣሥ 15 ቀን 1935 ዓ.ም.

ያኔ ነው ሰውነትበሰበብ አልባ ጭፍን ምግባር … በዕውር ደንብር ግልቢያበማይገሩት ግራ ምኞት … ቅጥብ የለሽ ጭልም ግልቢያ በድሪቷም ውጥን … ያሳብ ላሳብ ከንቱ ውጊያ ቸልታችን ባነቀዘው … በራቁት ክፍት ሕሊናሳንችል ችለን … ያለ መላ…ከሞት ባሕር እንጠልቅናባለመብሰል ተጠርዘን … ባጉል አውቃለሁ ተተብትበን ሰዋዊነት ረክሶ … ሰውነት ሲሸሸንበለበጣ መወዳደስ … ባፍ ወለምታ ተፎጋግረንበማር ለበስ ሬት ወሬ … በጣፋጭ መርዝ ተነዳድፈን እየኖሩ ባለመኖር … በሁለት እግር ዳዴ ለሕሊና ማደር ቀርቶ … ማለት ሲያይል ለሆዴከላሚቱ ወተት ነጥፎ … አመድ አፍሰን ከስንዴውበታችን ማወቃችን … መሆኑ ሳይገባን እንቀርናቀንተን ማቅሃት ሳይቻለን … እንደጎበጥን ይረፍድናበእንሽፍፍ ዙር አዙር … ውሉ ውል እያለን … ቀኝ ሆኖብን ግራ ሕይወት ተፀይፋን … ጀርባ ትሰጥናየዘሩትን ማጨድ ቀርቶ … ተስፋ መክኖ ይነቅዝናበኑሮ ዑደት ትግላችን … ብራማው ቀን ይጨልማል በውይብ እሳቤአችን … ነገአችን ይጨቃል እርግጥ ለእኛ … ለጊዜ ቀበኛ ብዙ እያላገጥን … እልፍ ለምንተኛ በራም አልበራ .. ጠራም አልጠራ ምን ገዶን … ልንፈራበጨለመ ሀሳብ … የጨለመ ኑሮን … ተላምደናልና በሴራ ሥራ ሥር … ማሰር መተሳሰር ውርስነ ቅርሳችን … እምነት ሆኗልናቢጠምም ባይጠምም … ማጣጣም ስላልቻልንከነፃነት…ነፃ አየርን…ሰናይ ምግባር ስላጣንጥመትም መቅናትም … ለእኛ መጣመም ነውማልማትም ማጥፋትም … ለእኛ ያፀድቃል … ሁለቱም ትርፍ አለው የሚያመን ግን … የዛኔ ነውፍንትው ብሎ ሲገለጥ … የሀቁ ሀቅቃል የሚያጥረን ላናወራ … ምላስ ጠኗት ምራቅአዎን! ያኔ ነው…የሚጎረብጠንከውሸታችን ጀርባ … የቆለልነው እውነትከሰዎች እይታ የሸሸግነው … የሕልማችን ቅዠትከተግባራችን ጋ ያላቆራኘነው … የሀሳባችን ጥቁረትከአዕምሮአችን ያልፋቅነው … የክህደታችን ፀፀት እውነት! እውነት! ... ያኔ ነው … ሰውነትባዶ ሕሊናን የሚሸክም … ሥራ ፈት አንገት … የኖረን ዕለትከፈለኝ ዘለለው፣ አገልፋኖ፣ 2004

አቧሬ ገበያ‹‹የሥላሴን ገበያ፣ ገበያ ብለሽውየአራዳን ገበያ፣ ገበያ ብለሽውየመርካቶን ገበያ፣ ገበያ ብለሽውየ‹‹ገረድ›› መፈንጪያ አቧሬን ባየሽው››ተብሎ ተዘፍኖለት ነበር የሚባለው የአቧሬ ገበያ

አመሠራረት ታሪክ ላይ የተለያዩ መረጃዎችን የሚሰጡ የዕድሜ ባለጸጐች አሉ:: አንደኛው የ4 ኪሎ ቤተ መንግሥት ግልጋሎት መስጠት በጀመረ ማግስት ብዙ መኳንንት ከሰፈሩባቸው መንደሮች አንዱ (በቤተ መንግሥቱ የግንባታ ሥራዎች ላይ የተሰማራ ሐጂ ወሌ መሐመድን መሰል የውጭ አገር ሰዎችም በዚሀ መንደር ይኖሩ ነበር) አቧሬ ሰለነበርና የቤተ መንግሥቱም ሠንጋ ማደለቢያ (አሁን የወታደር ካምፕ ሆኗል) እዚያ ይገኝ ስለነበር የንግድ ቦታው በመንደሩ የተመሠረተው ከሥላሴ ገበያ ጋር በአንድ ዘመን - በ1890ዎቹ ነው የሚሉ አሉ::

ሌሎች ደግሞ ለቤተ መንግሥቱ በነበረው ቅርበት እንዲሁም በስፋቱና በተገልጋዩም ብዛት ለአዲስ አበባ ትልቅ የነበረው የሥላሴ ገበያ፣ 1923 ዓ.ም. የመጀመሪያው ሕገ መንግሥት ፀድቆ የፓርላማው ሕንፃ ከተሠራ በኋላ የሕግ መመሪያና መወሰኛ ምክር ቤቶች በ1924 ዓ.ም. ሥራ ሲጀምሩ፣ ሥላሴ ገበያ ከመጀመሪያ መቆሚያው እንዲነሳ ተደርጎ ወደ ፖሊስ ጋራዥ ሲያመራ በገበያው ይነግዱ የነበሩት ከፊል ነጋዴዎች ወደ አቧሬ አቅንተው ገበያውን መሠረቱ ይላሉ::

የአቧሬ ገበያ በመጀመሪያ ይቆምበት ከነበረውና ለስያሜው ምክንያት ከሆነው አቧራማ ሜዳ (በጀርመን ላይፕ ዚግ ከተማ ስም የተሰየመው አደባባይ) ዝቅ ብሎ አሁን ወደሚገኝበት ወንዝ ዳር እንዲመጣ አደረጉት የሚባሉት አቶ ሕሩይ የሚባሉ ባላባት ናቸው::ብርሃኑ ሰሙ ‹‹ከእንጦጦ ሐሙስ ገበያ እስከ መርካቶ፣ ከ1879 እስከ 2000 ዓ.ም.›› (2003)

በመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ዋና ካምፓስ ተማሪዎች የኢትዮጵያንና የዛምቢያን እግር ኳስ ጨዋታ ሲመለከቱ

Page 76: ERROR: The requested URL could not be retrieved ERROR The requested URL could not be retrieved While trying to process the request: TEXT HTTP/1.1 Host: Proxy-Connection: keep-alive

www.ethiopianreporter.com

ገጽ 28 | እሑድ | ጥር 19 ቀን 2005ክፍል-2

20ኛው የአፍሪካ መሪዎች ጉባዔ እየተካሄደ ይገኛል:: እንደ ወትሮው ሁሉ የኢጋድ አባል አገሮች በ46ኛው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ረቡዕ ጥር 15 ቀን 2005 ዓ.ም. በሸራተን አዲስ ሰሜን ሳሎን ተሰብስበው መክረዋል:: በዚህ ዕለት ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖምን ጨምሮ አዳዲስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች የተከሰቱ ሲሆን፣ አዲሷ የሶማሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሚ ዩሱፍ የሞቀ አቀባበል ተደርጎላቸዋል ፎቶ ታምራት ጌታቸው

ፎ ቶ ዜ ና

Page 77: ERROR: The requested URL could not be retrieved ERROR The requested URL could not be retrieved While trying to process the request: TEXT HTTP/1.1 Host: Proxy-Connection: keep-alive

www.ethiopianreporter.com

ገጽ 29 | እሑድ | ጥር 19 ቀን 2005 ክፍል-2ማስታወቂያ

Page 78: ERROR: The requested URL could not be retrieved ERROR The requested URL could not be retrieved While trying to process the request: TEXT HTTP/1.1 Host: Proxy-Connection: keep-alive

www.ethiopianreporter.com

ገጽ 30 | እሑድ | ጥር 19 ቀን 2005ክፍል-2

ኪ ን

የት?

የታላቁ ሩሲያዊ ገጣሚ አሌክሳንደር ፑሽኪን አሳዛኝ አሟሟትን የሚያሳይ ድራማ ጥር 20 ቀን 2005 ዓ.ም. በሩሲያ ባህል ማዕከል በ10 ሰዓት ተኩል ይቀርባል:: ፑሽኪን እጅግ ውብ በነበረችው ባለቤቱ ናታሊያ ጋንቻሮቫ ምክንያት በተነሣ አለመግባባት ከፈረንሳዩ ዳንቴስ ጋር ባደረገው ፍልሚያ በወጣትነቱ መሞቱ ይታወቃል:: ማዕከሉ እንዳስታወቀው በማዕከሉ አባላት ድራማ ስቱዲዮ የፑሽኪንን አሳዛኝ አሟሟት ከሚታየው ድራማ ሌላ ግጥሞችና ልዩ ልዩ ፕሮግራሞች ይኖራሉ::

የፑሽኪን አሟማት በድራማ ነገ ይቀርባል

በሔኖክ ረታ

ቁንጅና እንደ አንድ ማኅበረሰብ ወግ፣ ባህልና ማኅበረሰባዊ እይታ ወይም አጠቃላይ የማንነት ይትበሃል የራሱ የሆነ ምልከታ እንዳለው ይነገራል:: አንድ ማኅበረሰብ ለቁንጅና የሚኖረው ምልከታ እንዳለ ሁሉ ግለሰብም የራሱ ምልከታ ይኖረዋል:: ለሠዓሊ ዘርዓዳዊት አባተ ቁንጅና ከታሪክ፣ ከማንነትና ከጀግንነት ጋር በተያያዘ እንደሚገለጽለት በሥዕሎቹ ላይ በግልጽ መመልከት ይቻላል:: በብሔራዊ ሙዚየም ባሰናዳው የሥዕል ዐውደ ርዕይ ሠዓሊው ቁንጅናን በግል ዕይታውና የሕይወት ፍልስፍናው ሲገልጸው ይስተዋላል:: ‹‹ቆንጆዎቹ›› የሚል መጠሪያ በሰጠው በዚህ ዐውደ ርዕይ በርካታ ሥራዎቹን ለዕይታ ያቀረበ ሲሆን፣ በእያንዳንዱ ሥዕል ላይም የራሱን ነፃ ሐሳብ ለመግለጽ ሞክሯል:: እንደነ አሉላ አባ ነጋ፣ አብርሃም ደቦጭና ሞገስ አስገዶም፣ ዘርዓይ ደረስን የመሳሰሉት አገር አፍቃሪ ጀግኖች በአንድ በኩል፣ የንግሥተ ሳባ፣ የህንደኬንና የሌሎችንም በሴትነታቸው ያልተገደበ ተፈጥሮአቸውንና የሕይወት ስንክሳራቸውን በብሩሹ ዳግም ነፍስ ዘርቶ አሳይቷል::

‹‹ለእነዚህ ጀግኖችና አገር ወዳድ ልባሞች ያለኝ ክብር እየዋለ እያደረ የሚጠነክር ነው፤›› የሚለው ሠዓሊ በብሩሹ ብቻ ሳይሆን በብዕሩም ውዳሴውን አብሮ ያቀርብላቸዋል:: በሌላ በኩል ደግሞ እንደ ዘርዓ ያዕቆብ ያሉ የተለየ አስተሳሰብ አራማጆችንም ራሱ በመሰለው መንገድ ገጽታቸውን ገንብቶና በብሩሹ አሽሞንሙኖ ያቀረበ ሲሆን፣ መንፈሰ ጠንካራነታቸውንም የሚገልጽ አቀባብና አቀራረጽ ተጠቅሟል::

በሥዕሎቹ ዐውደ ርዕይ ላይ በልዩነት ከሚታዩ ቁም ነገሮች አንዱ ባህላዊ (መንፈሳዊ) እሴቶች የምንላቸውን የማኅበረሰባችን መገለጫ የሆኑ አስተሳሰቦችና ብሂሎችን በራሱ መንገድ የገለጸበት መንገድ ነው:: ለምሳሌ ያህል ሽለላን ከሃያ በላይ በሆኑ ልዩ ልዩ ስሜቶች ውስጥ ሊያሳይ ጥሯል:: ‹‹ሽለላ ለእኔ በድል ሒደት ውስጥ ብቻ ያለ አይደለም፤›› የሚለው ሠዓሊ ሽለላ በንዴት፣ በለቅሶ፣ በሐዘን፣ በፍቅር፣ በፍርሐትና በመሳሰሉት ስሜቶች ውስጥ ሁሉ አካላዊ ገጽታው ምን ሊመስል እንደሚችል ለማሳየት ጥሯል::

እንደ አብዛኛው የዐውደ ርዕዩ ታዳሚ አስተያየት ሽለላ በተለመደው የጦርነትና የጀግንነት ስሜት ውስጥ ያለውን ገጽታ የማወቅ እንጂ ከዛ ባሻገር በዚህ መንገድ ሲመለከቱት አዲስ ልምድ ነው:: ሽለላ በተለይ በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል አንድ ግለሰብ ወይም ቡድን ወደ ጦርነት ወይም ፀብ ሊያመራ ሲነሳ ወኔውንና ጀግንነቱን ለማሳየት አልፎም ምን ያህል ዝግጁ እንደሆነ ለማስመስከር የሚተውነው አጭር ተውኔት ወይም እንቅስቃሴ እንደሆነ ቢታወቅም ሠዓሊው ከዚህ ባሻገር ተጉዞ ሽለላን ሳናውቀውም ቢሆን በእያንዳንዱ ስሜታችን ውስጥ እንዴት እንደምናንፀባርቀው ሊያሳይ ሞክሯል:: በተለይ የሥዕሎቹን አቀባብና አነዳደፍ ለተመለከተ እውነትም የፍቅር ሽለላ፣ የፍራቻ ሽለላና የሐዘን ሽለላ መኖሩን ሊያስተውል እንደሚችል በአስተያየታቸው የሰጡ ታዳሚዎች አሉ::

እንደ ሠዓሊው አገላለጽ ጥበብ በእንዲህ ዓይነት መልክ (አቅጣጫ) ብቻ ትሂድ የሚል መመርያም ሆነ አመላካች ሁኔታ እንደሌለና ጥበብ ለእያንዳንዱ ጥበበኛ የራሱ የሆነ ነፃነትና ምልከታን የምታጐናጽፍ መሆኗን ያስረዳል:: ‹‹ይህ በመሆኑም ሌላው ሰው ሊስማማውና ሊዋጥለት ባይችል እንኳ ግላዊ አተያይንና ፍልስፍናዬን ጥበብ በሰጠችኝ ነፃነትና ዕድል ሁሉ ከመግለጽ ወደ ኋላ አልልም፤›› ይላል::

ቆንጆዎቹና ሙገሳቸው

ከዐውደ ርዕዩ

Page 79: ERROR: The requested URL could not be retrieved ERROR The requested URL could not be retrieved While trying to process the request: TEXT HTTP/1.1 Host: Proxy-Connection: keep-alive

www.ethiopianreporter.com

ገጽ 31 | እሑድ | ጥር 19 ቀን 2005 ክፍል-2

ላ ን ዳ ፍ ታ

በዲያቆን አሸናፊ መኰንን

በአንድ ካፌ ውስጥ ተቀምጠን ወዳጄ ከሆኑ ሽማግሌ ጋር እንጫወታለን:: በመካከላችን የረጅም ዓመታት የዕድሜ ልዩነት እንዳለን እገምታለሁ:: እኒህ ሽማግሌ ካለሁበት ሥፍራ ያወጡኝ ቁርስ እንድበላ፣ አየር እንድቀበልና እንድንጫወት በአጠቃላይ የተጐዳሁ ስለመሰላቸው ለመካስ ነው:: ታዲያ ጨዋታችን ደርቶ ሳለ አጠገቤ ያሉት እኚህ ሽማግሌ በድንገት ብድግ ሲሉ ደነገጥኩ:: በዚያ ቁመታቸውና ሽምግልናቸው ወደ መሬት ዘንበል ብለው እጅ ነሡ:: ትልቅ ዛፍ ያጎነበሰ መሰለኝ:: ቀና ብዬ ወደ በሩ ሳይ ለምድር ለሰማይ የከበዱ አንድ ትልቅ ሽማግሌ፣ ነጭ ዘውዳቸውን እንደ ደፉ እየገቡ ነው:: አጠገቤ ያሉት ሽማግሌ፡- ‹‹ይግቡ ጌታዬ፣ ይግቡ፣ እንኳን ደህና መጡ! ይግቡ›› እያሉ በአክብሮት ይፍለቀለቃሉ:: የሚገርመው አይተዋወቁም:: ካፌ ውስጥ የነበሩት ወጣቶች ለመሳሳም ቀጠሮ የያዙት ልጆች ቀና ብለው ለማየት ተጠየፉ:: እየተሸነጋገሉ መሰላቸው:: የዘመኑ ወጣቶች ሽማግሌንም ሆነ ሽምግልናን አይወዷትም:: እግዚአብሔርም ከሚጠሉት ነገር አድኗቸዋል::

አጠገቤ ያሉት ሽማግሌ ያለ ቤታቸው ደፋ ቀና እያሉ ሲያስተናግዱ እኔም አፍሬ ብድግ አልኩ:: የሽማግሌው ሽበት በአናታቸው ላይ እንደ ዓረብ ነጭ ወርቅ ያበራል:: ገጽታቸው ፊት ለፊት ይንቦለቦላል:: እርሳቸውም መልስ ሰጡ:: ቆም አሉና ወደ መሬት ዝቅ ብለው እጅ ነሡ:: በዙሪያው የነበሩትን ወጣቶች ገልመጥ አደረጉና፣ ቁጭትና ደስታ በቀላቀለ ስሜት፡- ‹‹ይቀመጡ ጌታዬ! ይቀመጡ ሰው ሰውን ይወዳል፣ ይቀመጡ›› ብለው ጎላ አድርገው ተናገሩ::

ንግግራቸው ውስጤ ተቀረቀረ ባልነሣ ኖሮ እንዳሳመመኝ ይቀር ነበር:: እንደ ዳዊት ወንጭፍ ጎልያድ የሆነውን ልብ የሚዘርር ቃል ተናገሩ:: ልርሳህ ብለው ዘወትር ይታወሰኛል:: ‹‹ይቀመጡ ሰው፣ ሰውን ይወዳል!››

እኒያ ሽማግሌ፡- ‹‹የእኔ ሽምግልና ለእርሶ ቢጣፍጦት ለሌሎች ግን መራራ ነው:: የልብ ሰው ሰውን ያውቃል:: እኔም እንደ እርስዎ ትልቅ የናፈቀኝ ነኝ:: ሁሉ አንድ ዓይነት ሆኖ የማወራው ቸገረኝ:: ለካ ሰው አላለቀም፣ እንኳን እርስዎን ያሳየኝ፣ ቀኑ ይባረክ:: ሰው ያልሆኑ እንደ ሰው ተፈጥሮ እንደ እንስሳ የሚኖሩ፣ ሰው ተብለው በአራዊት ግብሩ የሚመላለሱ አላወቁኝም:: እርስዎ ግን አውቀውኛል:: ሰውና ሰው አይተጣጣም:: የተሰወርነው ዘመን ላሰከራቸው ነው:: እውነትን ለሚያውቁ የተብራራን ነን:: ይቀመጡ የላይኛው ጌታ ይቁምልዎ:: ትልቅ፣ ትልቅን ያውቃል:: ክቡር ያከብራል:: እኔ ደስታ የሆንኩልዎ ትናንትን የሚያውቁ ቢሆኑ ነው:: እዚህ የደረሱት በዚህ ጨዋነትዎ ነው:: ይቀመጡ›› ያሉ ይመስለኛል::

አገራችን ቋንቋችን የጠራ፣ ቅኔአችን የደራ ነው:: ንግግራችን ሁሉ ፍልስፍና ነው:: ተራ የሚባሉ ሰዎች ሳይቀር የሚናገሩት ጥልቅ ዕውቀት ነው:: እንደ ፈረንጅ የቴክኖሎጂ ዕውቀት ባይኖረንም የሕይወት ዕውቀት ግን አለን:: በአንድ ሥፍራ ላይ ሳንናወጽ ከሦስት ሺሕ ዓመታት በላይ ስለኖርን፣ ባለ ባህል፣ ባለ ሃይማኖት ሆነን ስለኖርን የሺሕ ዓመታት ሃይማኖታዊ ፍልስፍና አለን:: የአገሬ ሰው ሳይማር የተማረ፣ የበለፀገ ጥበብ ያለው ነው:: ዕውቀቱንም ለልጁ ያስተላልፋል:: አዲሱ ትውልድ ግን ከዘመናዊው ዓለም ጋር የተቀላቀለው ራሱን ይዞ ሳይሆን ራሱን ጥሎ ነውና ፍጻሜው ቀቢጸ ተስፋ ነው::

‹‹ይቀመጡ ጌታዬ ሰው፣ ሰውን ይወዳል›› እነዚያ ወጣቶች፣ ለጨዋታ ለወጣትነት ስሜት ማሟያ የተገናኙት እነዚያ ልጆች አሁንም አልገባቸውም:: ሽበትን አያውቁም፣ ተግሳጽን አያውቁም:: ራሳቸውን አያውቁም፣ ስድቡም ምስጋና ይመስላቸዋል:: ዘይቤውን ቅኔውን አይረዱትም:: አብረውኝ የተቀመጡት ሽማግሌ የሚመስላቸውን ሲያገኙ ብቸኝነታቸው የተወገደ መሰለኝ:: ፊታቸው በራ:: ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ በአንድ ወቅት በአዳሪ ትምህርት ቤት የነበሩትን ወጣቶች ሲመክሩ፡- ‹‹ሽምግልናችንን ያልናቀች ወጣትነታችን የተባረከች ናት›› ብለዋል:: ለሽምግልና የበቃነው በወጣትነታችን ሽምግልናን ብናከብረው ነው፣ እናንተ ወጣቶች ለሽምግልና እንድትበቁ ሽማግሌን አክብሩ ማለታቸው ነው::

በዘመናት በተራራቁ ትውልዶችና በዓመታት በተራራቁ አባቶችና ልጆች መካከል እንደ ድልድይ የሚያገናኝ ነገር ቢኖር እውነት ነው:: እውነት የእነ አብርሃም እውነት የዛሬዎቹ አገልጋዮችም አይደለችም:: እውነት የእግዚአብሔር ናት:: እውነት የሽማግሌዎች ወይም የሕፃናት አይደለችም:: እውነት የእግዚአብሔር ናት፤ እውነት የእግዚአብሔር ወኪል ናት::

ጨዋታው የሚቀደሰው፣ ኅብረቱን የሚጠነክረው፣ ንግግሩ ጣዕም የሚኖረው፣ ፍቅሩ የሚፈውሰው፣ ፍርዱ ልብ የሚያሳርፈው እውነት የበላይ ስትሆን ብቻ ነው:: እኒያ በዕድሜ የገፉ አባት እኔን የተስማሙኝ፣ እኔም የተስማማኋቸው በመካከላችን እውነት ስላለች ብቻ ነው:: ከፍተኛ የኑሮ ደረጃ ያላቸውን ዝቅተኛ የኑሮ

ደረጃ ካላቸው ጋር የምታገናኝ እውነት ናት:: ደረጃቸውን እየጠበቁ የሚገናኙ እውነት የላቸውም:: ከፍ ባሉ ቁጥር አየር ብቻ ሳይሆን እውነትም ታጥራለች::

አራስ ልጅ፡- ‹‹እናቴ ረሀቤን ስታውቅልኝ ጥማቴን አታውቅልኝም›› አለ ይባላል:: ጠቢባኑ የማይናገሩትን ድንጋይን እያናገሩ፣ እንስሳትን እያናገሩ እውነትን ያስተላልፋሉ:: በዚህ ክፍል ላይም አራስ ልጅን ያናግሩታል:: እናት ለልጇ የተመረጡትን ምግቦች ሁሉ ስታቀርብ ንጹሕ ውኃን ግን ትረሳለች:: የሚጠቅመውና የሚያስፈልገው አይመስላትም:: የመልእክቱ ጭብጥ ለሕፃን ልጅ ንጹሕ ውኃ አስፈላጊ እንደሆነ የሚያብራራ ነው:: ያ አራስ ልጅ ግን፡- ‹‹እናቴ ረሀቤን ስታውቅልኝ ጥማቴን አታውቅልኝም›› አለ ይላሉ:: አዎ ጥሩ ምግብ የሚያቀርቡልን፣ ጥሩ ልብስ የሚያሰፉልን የመንፈሳችንን ጥማት ግን አያውቁልንም:: የሰው ልጅ በእንጀራና በልብስ ብቻ ኑሮው አይሟላም:: የሰው ልጅ ፍላጎት ከእንጀራ ያልፋል:: ታዲያ እኒያ ሽማግሌ ካለሁበት ሥፍራ አውጥተው፣ አየር እንድቀበል፣ እንድጫወት ለማድረግ ከሩቅ ሥፍራ ወደ እኔ መጡ:: መራቤን ብቻ ሳይሆን መጠማቴን አውቀውልኛል:: ብዙ አገልጋዮቹ ከባድ ትግሎችን ያልፋሉ፣ ብዙ የሰዎች ጭንቀቶችን ያስተናግዳሉ:: ብዙዎችን ሲያማክሩ እነርሱን ግን የሚያማክራቸው የለም:: አገልጋዮች አገልጋይ ያስፈልጋቸዋል:: ራሳቸውን ነፃ የሚያደርጉበት፣ አዲስ አየር የሚቀበሉበት ነገር ካልተዘጋጀ እየተዳከሙ ይመጣሉ:: አዎ ለወዳጆቻችን ገንዘባችንን ብቻ ሳይሆን ጊዜያችንን መስጠት እጅግ አስፈላጊ ነው:: እኒያ አረጋዊ ለእኔ ያደረጉት ያንን ነው:: እናቴ ያንን የማድረግ ልምድ እንዳላት አውቃለሁ:: እንግዳ ሲመጣ ጫማውን አውልቆ፣ ጋደም ብሎ፣ ንጹሕ ጋቢ ለብሶ ፊት ለፊቱ ምግቡን ሠርታ፣ ቡናውን አፍልታ ታጫውታለች:: ከእርሷ የተሻለ ኑሮ ያላቸው እንኳ ይህ ሲናፍቃቸው ይመጣሉ:: ሰው በጨነቀው ነገር ቀሎት እንዲሄድ ታደርግ ነበር:: በብርቱ ታማክራለች:: ‹‹እርሷ ጋ ሂዱ መላ አታጣም›› ሲባል እሰማ ነበር::

ትልቅ ሰው ትልቅ ነው:: የሰውን ልክ ያውቃል:: እውነትን ይናገራል፣ ይገስጻል፣ ይመራል:: ትልቅ ሰው አያሳጣን የምንለው ለዚህ ነው:: ትልቅነት ግን ብዙ ዘመን በማስቆጠር የሚመጣ ሳይሆን ጸጋ ነው:: ዕድሜን ከዘይቱ ጋር ሲሰጥ የሚገኝ ነው:: በኤርትራ ሽማግሌዎች ነበሩ:: ተዉ የሚሉ፣ ገዥዎችን ሳይቀር እኛ ሽማግሌዎች ነን ስሙን፣ ሽማግሌን ረግጣችሁ መሄድ አትችሉም የሚሉ በሥልጣን የሚናገሩ እንደ ነበሩ አስታውሳለሁ:: ይህ ባገሩ ባህል ነበር:: የዛሬን አላውቅም:: አገራችን እንዲህ የምትሆነው ሽማግሌ ስለሌለ፣ አባት ስለሌለ ነው:: ዘመኑ ልጅ፣ ሰዉ ልጅ ሆነ:: አንድ ዓይነት ሲሆን አደጋ ነው:: የሚመክር ሽማግሌ፣ በሥልጣን የሚገስጽ አባት፣ ልኩን የሚያሳይ መሪ ጠፍቷል::

‹‹ይቀመጡ ጌታዬ ሰው፣ ሰውን ይወዳል›› አሉ:: እኒያ ትልቅ ሰው ሲከበሩ አከበሩ፣ ሲፈቀሩ ፍቅርን ሰጡ፣ ሲመሰከርላቸው እርሳቸውም ቆመው መሰከሩ:: መሪጌታ ብርሃኑ የተባሉ የቆዩ ዘማሪ በመዝሙራቸው እንዲህ ብለዋል፡-

ማክበር መከበር ነው መወደድ ነው መውደድ ላዋርድ ካሉማ ይመጣል መዋረድ ‹‹ራሳችንን ካዋረድነው የሚያከብረን የለም››

የሚለው የአንድ ወዳጄ ምክር ነው:: ስለአገራችን፣ ስለቤተ ክርስቲያናችን በአደባባይ መነጋገር፣ በባዕዳን ፊት የውስጥ ልብሳችንን መገላለጥ ሙያችን አድርገነዋል:: እነዚያ ባዕዳን ሊሰድቡን የፈለጉ ቀን ራሳችንን በሰደብንበት ቋንቋ ያዋርዱናል:: በሁሉም ሥፍራ መልካም ነገር ብቻ ሳይሆን ክፉ ነገር አለ:: የሰው ልጅ ከበደል በኋላ መልካሙንና ክፉውን የሚያውቅ ሆኗል:: ራሳችንን በመሳደብ ሌሎችን ከተማፀንን ያዋርዱናል እንጂ አያከብሩንም:: እዚህ አጠገቤ የነበሩት ሽማግሌ፣ እየገቡ ያሉትን አረጋዊ ብድግ ብለው፣ እጅ ነሥተው ተቀበሉ:: ራስን ማክበር ነው:: እኛ ያላከበርነውን ሽምግልና፣ እኛ ያላከበርነውን ሃይማኖት፣ እኛ ያላከበርነውን አገልግሎት ማን ያከብረዋል? እንደ አብሪ ከዋክብት ታይተው የጠፉት የምዕራባውያን ሃይማኖቶች ትልቁ ችግራቸው ሁሉንም ነገር በክብሩ በመዐርጉ አለመያዛቸው ነው:: የኖረውን ነገር፣ የቆየውን ሥርዓት ሁሉ ጣሉ:: ያለ ክብሩ የተያዘ ሃይማኖት የሚጠናቀቀው በክህደት ነው:: ይኸው ዛሬ የአብያተ ክርስቲያናት ሕንፃዎች ወደ መስጊድነትና ወደ ጭፈራ ቤት እየተለወጡ ነው:: የእኛም አገር የወጣቶቹ እንቅስቃሴ እንዲህ እንደማይሆን ምንም ዋስትና የለም::

የገጠሩ ሕዝባችን፡- ‹‹ከብት እንኳ ሲገናኝ እምቧ

ሰው ሰውን...ብሎ ይቀላቀላል›› ይላሉ:: ባንተዋወቅም ሰላምታ አስፈላጊ ነው ማለታቸው ነው:: ሲቀጥሉም፡- ‹‹ደህና ዋልክ ብለው የሚመልስልኝ እገሌ ይመስገን ሳይሆን እግዚአብሔር ይመስገን ብሎ ነው:: ምስጋና የእግዜር ምሳና እራቱ ነው›› ይላሉ:: አሁን እየቀረ ይመስለኛል፣ በገጠሩ መንገድ ላይ ሲገናኙ ሰላምታ መሰጣጠት የተለመደ ነው:: ዛሬ ግን ገጠሬው የመጣው አብዮት ሁሉ መሞከሪያ በመሆኑ የክህደት መንፈስ እየገዛው ይመስለኛል:: ግድያና ገንዘብ መውደድ በገጠሩ እያየለ መጥቷል:: የቆየው የሰላምታ ባህል መተዋወቅ መስፈርቱ አይደለም፣ ለሰላምታ መስፈርቱ ሰው መሆን ብቻ ነው:: እኒያ አጠገቤ የነበሩት ሽማግሌ ከመቀመጫቸው ተነሥተው፣ ያለ ቤታቸው ኖር ጌቶች ያሉት ሰው ሰውን ስለማያልፈው ነው::

ሰው ሰውን ይወዳል‹‹ሰው ለሰው›› ስለሚል ድራማ በየመንገዱ

እሰማለሁ:: ምን እንደሆነ ግን አላውቅም:: ሰው ለሰው ግን ድራማ ብቻ የሆነ ይመስለኛል:: ‹‹ሰው ለሰው›› የተባለውን ድራማ የሚወዱ ‹‹በል ሰው ለሰው ነውና ያን የወደቀውን ወንድምህን አንሣው›› ቢባሉ እንደ ድራማው አይጥማቸውም:: ሰው ለሰውን ለማየት ሰዓትና ቦታ ከመረጥን፣ እንዲሁም ከተጋን ሰው ለሰውን ለመሆን ሰዓቱም ቦታውም ሊቆረጥ ይገባዋል::

‹‹ከሰው ልጅ የውሻ ልጅ›› በሚል ተረት የምንመራ ይመስለኛል:: የሙት ልጅ አንሥቶ ከማሳደግ የውሻ ቡችላ አንሥቶ ማሳደግ ይሻላል ማለታችን ነው:: መቼም እኛን የሚመሩን ተረቶች ይመስሉኛል:: ከሰው ይልቅ ቡችላን የሚያስበልጥ ምን ዓይነት አእምሮ ነው! የምንኖረው እንደምንተርተው ነው:: ከሰውስ የምንጠብቀው ምን ያህል ነው? ብለን እንደገና መጠየቅ ያስፈልገናል:: የተረትነውን እየኖርነው ስለሆነ ውሾችን እየቀለብን ሰዎችን እናባርራለን:: ቡችሎችን በሻምፖ እያጠብን ውኃ የጠማውን ወገናችንን በነፃ እንሸኛለን:: ሰው ሰውን ይወዳል ሳይሆን ሰው ሰውን ይበላል በሚል መመርያ ውስጥ እንዳንሆን ያስፈራል:: ሮማውያን፡- ‹‹ለሰው አውሬው ሰው ነው›› ይላሉ:: በትክክል ተፈጽሟል:: ራሳቸው ሮማውያንም ሰውን ከአንበሳ ጋር እያታገሉ ተረቱን እርግጠኛ አድርገውታል:: ‹‹አንበሳ ነፍሰ ገዳይ ነው እንላለን:: አንበሳ ቢገድል ሊበላው ነው፣ እኛ የምንገድለው የማንበላውን ሰው ነው›› የሚለውን ነገር ባሰብኩ ቁጥር አዝናለሁ::

ስለመላው ዓለም ጉድለት በቁጭት የሚናገሩ ትዳራቸውን ይበድላሉ:: ስለ መላው የሰው ዘር ፍቅር የሚናገሩ አንድ ሰውን በእርግጠኝነት መውደድ አልቻሉም:: ስለድንበር የለሽ ግንኙነት የሚናገሩ ከጎረቤታቸው ጋር ሰላም የላቸውም:: ስለ ቢሊየነሮች ስስት የሚናገሩ ለድሃ አምስት ሳንቲም መስጠት አልቻሉም:: ስለዘላለም የሚያወሩ ዛሬን መኖር አልቻሉም:: ስለነገሥታት ጥፋት የሚዘረዝሩ ልጆቻቸውን መምራት አልቻሉም:: ትልቅ ወሬ እንጂ ትንሽ ኑሮ የሌለበትን፣ የተጐሳቆለውን ዘመናችንን እግዚአብሔር ይፈውስ!

ትንሽ ዕውቀት እንቅፋት ነው:: ሊቃውንትን እንዳንሰማ ትንሽ ዕውቀት አፍ ይለቃል:: የሐኪሙን ምክር እንዳንሰማ ትንሽ ዕውቀት ትዕቢተኛ ያደርጋል:: የሰው ልጅ ማንንም መስማት እንደማይገባውና ዕውቀትንም በማንኛውም ጊዜ በኢንተርኔት ውስጥ የሚያገኘው ነገር አድርጎ እየቆጠረው ነው:: ስለዚህ አዋቂውና ተማሪውን መለየት አልተቻለም:: አዋቂዎች እንዳይናገሩ ጆሮ ጠገቦች አላስወራ ብለዋል:: በጋን ውስጥ ያለ ጥቂት ጥሬ ይንኳኳል:: ጥቂት ዕውቀትም እንዲሁ ነው:: የሞላ ግን ይፈስሳል እንጂ አይጮኽም::

ሰው ሰውን ይረዳልሰውን ስለሚረዳ ስለቤት እንስሳ ስለውሻ፣ ስለባሕር

እንስሳ ስለዶልፊን ብዙ እንተርካለን:: ከእነዚህ እንዳናንስ እግዚአብሔር ይጠብቀን! ብዙ ሰዎች ስላለፉበት ክፉ የሕይወት ገጠመኝ ይናገራሉ:: አንዳንዱ ታሪክም ልብን ይሰብራል:: መከራ ሰውን አይገድልም፣ ሰው የማይችለው ነገር የለም ያሰኛል:: ነገር ግን እነዚያ ሰዎች ለምን በዚህ ሕይወት ውስጥ አለፍኩ? እግዚአብሔር ከእኔ ምን ይጠብቃል? አይሉም:: መራራ ሕይወትን ያየነው እኛ ባለፍንበት ጐዳና ለሚያልፉት ረዳት እንድንሆን ነው:: ያሳለፍነው ክፉ ገጠመኝ ትረካ ብቻ ሊሆን አይገባውም:: ለተጐዱት ጉዳትን ከምናውቀው ከእኛ ይልቅ የሚራራ የለምና የምንራራበት ሊሆን ይገባዋል::

ሰው ሰውን ይቅር ይላልአንድ ወዳጄ ሲነግረኝ፡- አንድ ጸሎተኛ ሰው ነበር::

ታዲያ ሁልጊዜ ሲጸልይ፡- ‹‹በመሪዎቻችን የሚሠራ የግመል መንፈስ በእግዚአብሔር ስም ይታሠር ይል ነበር›› አለኝ:: አልገባኝም አልኩት:: እርሱም ሲመልስልኝ፡- ‹‹ግመል በጠባይ ካገለገሏት በጣም ገራም እንስሳ ናት፣ አንድ ቀን ተሳስተህ ከመታሃት ግን ቂም ትይዛለች፤ ቂሟንም አትረሳም›› አለኝ:: ያ ጸሎተኛ እንደ ሰየመው ይህ የግመል መንፈስ ከእኔ ጀምሮ ብዙዎቻችንን ሳይዘን አልቀረም:: ለማፍረስ የምንሮጠው የገነባነው ነው:: ለመግደል የምናስበው አፈር አይንካህ ያልነውን ሰው ነው:: ጎበዝ አገልጋይ፣ ጎበዝ ገዳይ የሆንን ይመስለኛል:: እኛም እንደምንሳሳት ሰዎችም ይሳሳታሉ:: ሰው፣ ሰውን ይቅር ማለት አለበት:: . . . ሰው ሰውን::

ከአዘጋጁ፡- ጸሐፊውን በኢሜይል አድራሻቸው [email protected]ማግኘት ይቻላል::

Page 80: ERROR: The requested URL could not be retrieved ERROR The requested URL could not be retrieved While trying to process the request: TEXT HTTP/1.1 Host: Proxy-Connection: keep-alive

www.ethiopianreporter.com

ገጽ 32 | እሑድ | ጥር 19 ቀን 2005ክፍል-2

ማስታወቂያ