ሰርኩላር ቁጥር 3 - Ethiopian Postal Service Cirulars.docx final...ሰርኩላር...
Transcript of ሰርኩላር ቁጥር 3 - Ethiopian Postal Service Cirulars.docx final...ሰርኩላር...
ሰርኩላር ቁጥር 3
የኮንጎ ሪፐብሊክ ፖስታ አስተዳደር ለህብረቱ አባል አገራት
የሚከተለውን ጉዳይ አሳውቋል፡ ፡
ወደ አገሪቷ በሚላኩ የአደራ ደብዳቤዎች ፣ ጥቅል መልዕክቶች እና
ኢ.ኤም.ኤስ መልዕክቶች ላይ በሙሉ የተቀባይ ደንበኛ ሞባይል ስክክ
ቁጥር እንዲኖር በማድረግ እንዲላኩ ይህም ተቀባይ ደንበኛን በአጭር
የፅሁፍ መልዕክተ እንደመጣለት ለማሳወቅ ፤ ወቅቱን የጠበቀ እደላን
ለማቀላጠፍ እንዲሁም ለማደል ሙከራ የሚሰጡ ማስታወቂያዎችን
ለመቀነ ስ እንደሚረዳ ገልፃDል፡ ፡
ሰርኩላር ቁጥር 5
የኢንዶኔዢያ ፖስታ አስተዳደር ለህብረቱ አባል አገራት የሚከተለውን
ጉዳይ ማሳወቅ ይፈልጋል፡ ፡ በጉምሩክ መፈተሽ የሚገባቸው መልዕክቶ
ሙሉ በሙሉ ካልተሞሉ ወይም በትክክል ካልተሞሉ የከስተም ዲክላሬሽን
ፎርሞች (CN22 ወይም CN23) ጋር እየደረሱት እንደሆነ
አሳውቋል፡ ፡ ይህም በጉምሩክ አገልግሎት ላይ ችግር እየፈጠረ
በመሆኑ መልዕክቶች እዚያው የሚዘገዩበትን ሁኔታ ፈጥሯል፡ ፡
ከዚህ ጋር በተያያዘም ፖስታ አስተዳደሩ በደብዳቤ አሰራር ህግ
አንቀፅ 152 መሠረት ወደ ኢንዶኔዢያ መልዕክቶች ሲላኩ ከዚህ
በታች የተዘረዘሩት መረጃዎች ተሟልተው እንዲላኩ ጠይቋል፡ -
- በ CN22 እና CN23 የሚሞሉ መረጃዎች በሙሉ በእንግሊዝኛ ፣
በፈረንሳይኛ ወይም በባሃሳ ቋንቋ መሞላት ይኖርበታል፤
- ስለሚላከው ዕቃ ዝርዝር እና ሙሉ ገለፃ የእያንዳንዱን መልዕክት
ዋጋ ጨምሮ መሰጠት ይኖርበታል
- የላኪ እና የተቀባይ የስልክ ቁጥር በCN23 ፎርም ላይ መሞላት
ይኖርበታል (ከተገኘ)
- ማኝኛውም አስፈላጊና ደጋፊ ዶክመንቶች (ኢንቮይስ ፣ የኢምፖርት
ወይም ኤክስፖርት ፍቃድ እና የመሳሰሉት) ተያይዘው መላክ
ይኖርበታል፡ ፡
ሰርኩላር ቁጥር 7
የዩክሬይን ፖስታ አስተዳደር ለህብረቱ አባል አገራት የሚከተለውን
ጉዳይ ያሳውቃል፡ ፡ የዩክሬይን መንግስት ለጊዜው Donetsk እና
Luhansk Oblasts በሚባሉ ክልሎች ላይ ሙሉ በሙሉ ሆነ
በከፊል ስልጣኑን ተግባራዊ ማድረግ የማይችልበት ሁኔታ ላይ ያለ
በመሆኑ ከ20 November 2014 ጀምሮ የዩክሬይን ፖስታ
አስተዳደር ከላይ በተጠቀሱት ክልሎች የሚታደሉ መልዕክቶችን
የማይቀበል መሆኑን አሳውቋል፡ ፡ ወቅታዊ የተደረገ የክልሎች ዝርዝር
እና የፖስታ ኮዶቻቸው ከዚህ በታች ባለው አድራሻ የሚገኝ መሆኑን
ገልፃ Dል፡ ፡ http://ukrposhta.ua/en/robota-
ukrposhti-v-doneckij-ta-luganskij-
oblastyax.
የዩክሬይን ፖስታ አስተዳደር የህብረቱ አባል አገራት ከላይ
ወደተጠቀሱት ክልሎች የሚተላለፉ አለምአቀፍ መልዕክቶችን
እንዳይልኩለት በትህትና እየጠየቀ ሆኖም ግን አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ
እነ ዚህን መልዕክቶች በፖስት ሪስታንቴ መላክ የሚችሉ ሲሆን
መልዕክቶቹ የሚከተሉትን መረጃዎች መያዝ እንደሚገባቸው አሳስቧል፡ ፡
- የተቀባይ ሙሉ ስም
- በዩክሬይን መንግስት ቁጥጥር ስር ያለ መልዕክቱ የሚታደልበት
አካባቢ መጠሪያ
- የወረዳው/አውራጃው (district) መጠሪያ
- የክልሉ (region) መጠሪያ
- የአዳይ ፖስታ ቤት መጠሪያ
- ፖስት ኮድ
- የአዳይ አገር መጠሪያ
- የተቀባይ ደንበኛ መደበኛ ወይም ተንቀሳቃሽ ስልክ ቁጥር
ለበለጠ መረጃ ዋናውን የእንግሊዝኛ ሰርኩላር ቁጥር 7 ይመልከቱ፡ ፡
ሰርኩላር ቁጥር 19
የዩራጓይ ፖስታ አስተዳደር ለህብረቱ አባል አገራት የሚከተለውን ጉዳይ
ያሳስባል፡ ፡ ወደ ዩራጓይ ለሚልኳቸው መልዕክቶች ከዚህ በታች በተገለፀው የዓለም
አቀፍ መልዕክት መስሪያ ማዕከል ኮዶች እንዲጠቀሙ አሳውቋል፡ ፡ ከዚህ በተጨማሪም
የዓለም አቀፍ ሂያጅ መልዕክት ማዘጋጃ ማዕከላት ኮዶችንም አሳውቀዋል፡ ፡
የመጪ መልዕክቶች ማዘጋጃ ማዕከል ኮዶች
ኮድ የመልዕክት ልውውጥ ቢሮ
መጠሪያ
የሚቀበለው የመልዕክት ዓይነ ት
UYMVDA MONTEVIDEO CPP
APERTURA
ደብዳቤ እና የታተሙ ፅሁፎች (የአየር
መልዕክቶች እና የሳል መልዕክቶች)
UYMVDE MONTEVIDEO UNIDAD
CONTENEDORES
ባዶ የመልዕክት ሸራዎች
UYMVDH MONTEVIDEO CP INT
EMS LC/AO
- አነ ስተኛ ጥቅሎች እና ጥቅሎች
- ኢ.ኤም.ኤስ
የመጪ መልዕክቶች ማዘጋጃ ማዕከል ኮዶች
ኮድ የመልዕክት ልውውጥ ቢሮ
መጠሪያ
የሚያዘጋጀው የመልዕክት ዓይነ ት
UYMVDB MONTEVIDEO CAMBIO
AEREO
ደብዳቤ ፣ የታተሙ ፅሁፎች ፣
አነ ስተኛ ጥቅሎች እና ጥቅሎች
(የአየር መልዕክቶች)
UYMVDD MONTEVIDEO
ENCAMINAMIENTO
AEREO
ደብዳቤ ፣ የታተሙ ፅሁፎች እና
አነ ስተኛ ጥቅሎች (የአየር
መልዕክቶች)
UYMVDE MONTEVIDEO UNIDAD
CONTENEDORES
- ባዶ የመልዕክት ሸራዎች
UYMVDH MONTEVIDEO CPINT
EMS LC/AO
- አነ ስተኛ ጥቅሎች እና ጥቅሎች
(የአየር መልዕክቶች)
- EMS
የዩራጓይ ፖስታ አስተዳደር የህብረት UYMVDF የሚባለውን መልዕክት ልውውጥ ቢሮውን
የዘጋ በመሆኑ መልዕክቶች ወደዚያ እንዳይላኩ አሳስቧል፡ ፡
ሰርኩላር ቁጥር 20
የሃንጋሪ ፖስታ አስተዳደር ከህብረቱ አባል አገራት በCN 15
ያልተደገፉ ወይም የተሟላ መረጃ ካልያዘ CN 15 ሌብል ጋር
ተመላሽ መልዕክቶች እየደረሱት መሆኑን አሳውቋል፡ ፡
በመሆኑም የሃንጋሪ ፖስታ በደብዳቤ አሰራር ሬጉሌሽን አንቀጽ RL
151.8 እና በጥቅል መልዕክት አሰራር ሬጉሌሽን አንቀጽ RC
144.5 መሠረት CN 15 በሚጠይቀው መልኩ መልዕክቱ ያልታደለበት
ምክንያት ተገልጾ እንዲላክለት ጠይቋል፡ ፡
ሰርኩላር ቁጥር 21
የሴኔጋል ፖስታ አስተዳደር ለህብረቱ አባል አገራት ከ5 ጃንዋሪ
2015 ጀምሮ አዲስ ፖስትኮድ ተግባራዊ ማድረጉን አሳውቋል፡ ፡
አዲሱ ፖስትኮድ ባለአምስት ዲጂት ሲሆን ይህም መልዕክቱ
የሚታደልበትን ፖስታ ቤት እና የፖስታ ማደያ ዞኖችን የሚገልጽ
ነው፡ ፡ የአድራሻ አፃፃፉም ከዚህ በታች በተቀመጠው ምሳሌ
መሰረትመሆን እንደሚገባው አሳስቧል፡ ፡
Ms Madeleine Tounde Mr Bouya KA
BP 1534 24 Avenue de
la gare
27000 Ziguinchor 10000
Dakar
SENEGAL SENEGAL
አባል አገራት ትክክለኛ የፖስት ኮድ ማግኘት የሚፈልጉ
ደንበኞቻቸውን በፖስታ አስተዳደሩ ድረ-ገፅ
(http://www.laposte.sn/laposte/trouver_co
depostal.php) ላይ የሚገኘውን የፖስት ኮድ ማፈላለጊያ
በመጠቀም ማግኘት የሚችሉ መሆኑንና ትክክለኛ አድራሻ መጠቀማቸውንም
እንዲያረጋግጡ እንዲደረግ ጠይቋል፡ ፡
ሰርኩላር ቁጥር 22
የሴኔጋል ፖስታ አስተዳደር ለህብቱ አባል አገራት ወደ ሴኔጋል
የሚላኩ መልዕክቶች አድራሻ ከዚህ በታች የተዘረዘሩ ቁልፍ
መረጃዎችን መያዝ እንደሚገባቸው ማሳወቅ ይፈልጋል፡ ፡
- የተቀባይ ሙሉ ስም እና አድራሻ
- የላኪ ሙሉ ስምና አድራሻ
- የተቀባይ መደበኛ ወይ የተንቀሳቃሽ ስልክ ቁጥር እና የኢ-ሜይል
አድራሻ (ከተገኘ)
- የአዳይ ፖስታ ቤት ፖስት ኮድ
ሰርኩላር ቁጥር 23
የቻይና ፖስታ አስተዳደር ለህብረቱ አባል አገራት እንስሳትና
እጽዋት እንዲሁም የእንስሳትና እፅዋት ተዋጽኦ/ውጤቶችን ወደ ቻይና
ማስገባት የማይቻል መሆኑን ገልፃDል፡ ፡
ከላይ የተገለጹት እቃዎችን የያዙ የአለም አቀፍ ደብዳቤዎች ፣
ጥቅሎች ወይም ኢ.ኤም.ኤስ መልዕክቶችን በክሎዝድም ሆነ በኦፕን
ትራንዚት በቻይና በኩል ማሳለፍ የማይቻል መሆኑን ጨምሮ
አስረድቷል፡ ፡
እንዳይተላለፉ የተከለከሉ መልዕክቶች ዝርዝር መረጃ በዋናው
የእንግሊዝኛ ሰርኩላር ላይ አባሪ ተደርጎ የተላከ መሆኑን
እንገልፃለን፡ ፡
ሰርኩላር ቁጥር 30
የሲንጋፖር ፖስታ አስተዳደር ለህብረቱ አባል አገራት ቫፖራይዘር
(ኤልክትሮኒክ ሲጋራዎች፣ ኤሌክትሮኒክ ፒፓዎች እና የመሳሰሉትን)
እንዲሁም የሺሻ ሞላሰስ የተፈለጉበት ምክንያት ግምት ውስጥ ሳይገባ
ወደ አገሪቱ ማስገባት የማይቻል መሆኑን ማሳወቅ ይፈልጋል፡ ፡
ቫፖራይዘሮች በላኪ ደንበኞች እንደ መጫዎቻ/አሻንጉሊት ፣
የኤሌክትሪክ ዕቃ ፣ የኤሌክትሪክ መለዋወጫ ወይም እንደ ዩ.ኤስ.ቢ
መሳሪያ ተደርገው የሚወሰዱ/የሚጠሩ በመሆኑ በፍተሻ ተገኝተው
ከሚያዙ ይልቅ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ እና እነ ዚህን
ዕቃዎች መላክ እንደማይቻል አስፈላጊውን መመሪያ እንዲሰጣDቸው
ፖስታ አስተዳደሩ አሳስቧል፡ ፡
ሰርኩላር ቁጥር 32
የአውስትሪያ ፖስታ አስተዳደር ለህብረቱ አባል አገራት የሚከተለውን
ጉዳይ ማሳወቅ ይፈልጋል፡ ፡
ከእንስሳት ህክምና እና ከፋይቶሳኒታሪ/ከእጽዋት ጤና ጋር ተያያዥ
የሆኑ መልእክቶችን ተቀብሎ የማያስተናግድ መሆኑን እና ወደ ላኪ
አገር ተመላሽ የሚያደርግ መሆኑን አሳውቋል፡ ፡
ለበለጠ መረጃ ዋናውን የእንግሊዝኛ ሰርኩላር ቁጥር 32
ይመልከቱ፡ ፡
ሰርኩላር ቁጥር 33
የቤላሩስ ፖስታ አስተዳደር ለህብረቱ አባል አገራት አለም አቀፍ
የአየር መልዕክቶች ማስተናገጃ አዲስ ኦፊስ ኦፎ ኤክስቼንጅ በኮድ
ስሙ MINSK AMU የተባለ መክፈቱን ይህም ከ1 December
2014 ጀምሮ ዋጋ ላላቸው የደብዳቤ መልዕክቶች አገልግሎት መስጠት
የጀመረ መሆኑን ማሳወቅ ይፈልጋል፡ ፡
በዚህም መሠረት አባል አገራት ወደ ቤላሩስ ዲስፓች ሲልኩ ከዚህ
ቀጥሎ የተዘረዘረውን የአለም አቀፍ መልዕክት ማስተናገጃ መጠሪያ
ኮድ እንዲጠቀሙ አሳስቧል፡ ፡
Office of
Exchange/ኦፊስ
ኦፍ ኤክስቼንጅ
IMPC ኮድ Mail category/የመልዕክት ዓይነት
MINSK EMS BYMSQA EMS
MINSK PCI BYMSQB መተማመኛ ኖቶች/ Verification notes
MINSK PI 2 BYMSQC ሁሉም የደብዳቤ መልዕክቶች (non-
priority)
MINSK PI 3 BYMSQD ጥቅል
MINSK PI 5 BYMSQE ባዶ ሸራዎች
MINSK PI 6 BYMSQF ከቻይና፣ ከሆንግ ኮንግ እና ከሲንጋፖር
ለሚላኩ ደብዳቤ መልዕክቶች (priority,
S.A.L.) ብቻ
MINSK PI 4 BYMSQI ከሩሲያ እና ካዛኪስታን ለሚላኩ ደብዳቤ
መልዕክቶች (priority, S.A.L., nonpriority)
ብቻ MINSK PI 7 BYMSQK ከሩሲያ እና ካዛኪስታን ለሚላኩ ጥቅል
መልዕክቶች (airmail, S.A.L., surface) ብቻ
MINSK AMU BYMSQL ለአየር መልዕክቶች
MINSK
AMUPI2
BYMSQG ለሁሉም የደብዳቤ መልዕክቶች (priority, S.A.L.)
ሰርኩላር ቁጥር 38
የታይላንድ ፖስታ አስተዳደር ለህብረቱ አባል አገራት የሚከተለውን
ጉዳይ አሳውቋል፡ ፡ የተወሰኑ የህብረቱ አባል አገራት የኢ.ኤም.ኤስ
ማደያ ዋጋ መጨመራቸውን ለማሳወቅ የዓለም አቀፉ ፖስታ ህብረት
ቢሮ ሰርኩላርን እንደመጀመሪያ ዘዴ አድርገው እየወሰዱ መሆኑን
ተረድቷል፡ ፡
የኢ.ኤም.ኤስ መልዕክት ማደያ ዋጋን ወይም የክፍያ ስርዓትን
ከማሻሻል ጋር በተያያዘ ከፖስታ አስተዳደሮች ጋር የሚኖር ጭቅጭቅን
ለማስቀረት የታይላንድ ፖስታ አስተዳደር በኢ.ኤም.ኤስ ማደያ ታሪፍ
ላይ ያለውን አቋም እንደሚከተለው ገልፃDል፡ ፡
የታይላንድ ፖስታ አስተዳደር የሚከተሉት ሁኔታዎች ካልተሟሉ የታሪፍ
ማሻሻያዎችን አይቀበልም፡
1. የኢ.ኤም.ኤስ ማደያ ታሪፍን ለማሻሻል የፈለገ ፖስታ
አስተዳደር አዲሱ ታሪፍ ተግባራዊ ለማድረግ ከሚታሰብበት
ጊዜ ቀደም ብሎ ለታይላንድ ፖስታ አስተዳደር ማሳወቅ
ይኖርበታል ይህም በሁኔታው ላይ ለመወያየት እና የሁለትዮሽ
ስምምነት ላይ ለመድረስ በቂ ጊዜ እንዲኖር ያደርጋል፡ ፡
2. በሁለቱ አካላት መካከል ስምምነት ላይ መደረስ ይኖርበታል
፤ የስምምነቱም በጽሁፍ የሰፈረ መሆን እና መጠናቀቅም
ይጠበቅበታል፡ ፡
ሰርኩላር ቁጥር 39
የዶሚኒካን ሪፐብሊክ ፖስታ አስተዳደር ለህብረቱ አባል አገራት ከ
March 2015 ጀምሮ በሁለትዮሽ ስምምነት መሠረት ወደ
Anguilla, Antigua እና Barbuda, Aruba,
Curaçao እና Sint Maarten, Barbados,
Bonaire, Dominica, Guadeloupe, Jamaica,
Martinique, Saint Christopher (St Kitts)
እና Nevis, Saint Croix, Saint Lucia, Saint
Thomas, እንዲሁም Trinidad እና Tobago የሚላኩ
መልዕክቶችን ተቀብሎ የሚያስተላልፍ/ትራንዚት የሚያደርግ መሆኑን
አሳውቋል፡ ፡
ለበለጠ መረጃ አባል አገራት ከዚህ ቀጥሎ ባለው አድራሻ፡
Ms Elizabeth Frías
ኢ-ሜይል ([email protected]
ስልክ ቁጥር : 809–534–5838, ኤክስቴንሽን ቁጥር 211
or 89–763– 0512
በማግኘት መጠየቅ የሚቻል መሆኑን አሳስቧል፡ ፡
ሰርኩላር ቁጥር 40
የቤላሩስ ፖስታ አስዳደር ለህብረቱ አባል አገራት የሚከተለውን
ጉዳይ ማሳወቅ ይፈልጋል፡ ፡
የጥቅል ፣ አነ ስተኛ ጥቅልና የኢ.ኤም.ኤስ መልዕክቶችን እደላ
ለማቀላጠፍ ፖስታ አስተዳደሮች ደንበኞች ከዚህ በታች የተዘረዘሩ
መረጃዎችን እንዲሞሉ እንዲጠይቁ አሳስቧል፡ ፡
- የተቀባይ ሙሉ ስም እና አድራሻ
- የተቀባይ ስልክ ቁጥር
- በጥቅል አሰራር ህግ አንቀጽ RC 151 እና በደብዳቤ አሰራር
ህግ አንቀጽ RL 156 መሠረት በCN 22 እና CN 23 ላይ
የሚጠየቁ መረጃዎችን በሙሉ በእንግሊዝኛ ወይም ፈረንሳይኛ ቋንቋ
እንዲሙሉ
- ስለሚላከው ዕቃ ይዞታ ሙሉ እና ዝርዝር መረጃ ከዕቃዎቹ ዋጋ
ጋር መሞላት እንደሚገባ አሳስቧል፡ ፡
ሰርኩላር ቁጥር 44
የካዛኪስታን መንግስት ለዓለም አቀፉ ፖስታ ህብረት አባል አገራት
የሚከተውን ጉዳይ ያሳውቃል፡ ፡
በቀን 22 December 2014 በሰርኩላር ቁጥር 221
እንደተገለፀው ካዛፖስት "Kazpost" የኢ.ኤም.ኤስ አገልግሎት
የሚሰጥ እና በዩፒዩ ኮንቬንሽን መሠረት የሚጠበቁ ግዴታዎችንም
የሚፈጽም መሆኑን አሳውቋል፡ ፡
ሰርኩላር ቁጥር 45
የሆንግ ኮንግ “ቻይና” ፖስታ አስተዳደር ይሰጠው የነ በረውን
የሂያጅና መጪ ፈጣን ደብዳቤ መልዕክት አገልግሎት ከ1 April
2015 ጀምሮ ያቋረጠ መሆኑን እያሳወቀ ከተጠቀሰው ጊዜ ጀምሮም
ሆነ በኋላ የሚደርሱትን ፈጣን የደብዳቤ መልዕክቶች እንደተራ
መልዕክት የሚያስተናግዳቸው መሆኑን ገልፃDል፡ ፡
ሰርኩላር ቁጥር 49
የፊንላንድ ፖስታ አስተዳደር ለዓለም አቀፉ ፖስታ ህብረት አባል
አገራት ከ1 ጃኑዋሪ 2015 ጀምሮ የስም ለውጥ ያደረገ ሲሆን
የስም ለውጡም ከ Itella Posti Oy ወደ Posti Ltd
መሆኑDን ገልፃል፡ ፡
የቢዝነ ስ መታወቂያ ቁጥሩ (0109357–9) ሲሆን ይጠቀምበት
የነ በሩት ስልክ ቁጥሮች እና የጎዳና አድራሻዎች አለመቀየራቸውን
የኢ-ሜይል አፃፃፍ ፎርማቱ
[email protected] እንዲሁም የድርጅቱ
ድረ-ገጽ www.posti.fi መሆኑን ከዚህ ጋር በተያያዘም የስም
ለውጡ ከድርጅቱ የመጠሪያ ስም በስተቀር የዓለም አቀፍ የሂሳብ
አካውንቶቹን የማይነ ካ መሆኑን አሳውቋል፡ ፡
ሰርኩላር ቁጥር 50
የሳውዲ አረቢያ ፖስታ አስተዳደር ለህብረቱ አባል አገራት ወደ
ሳውዲ አረቢያ በሚላኩ መልዕክቶች ውስጥ ሽቶ መላክ የተከለከለ
መሆኑን አያሳወቀ ሽቶ የያዙ መልዕክቶችን በምንም አይነት ሁኔታ
የማያድል በመሆኑ ለላኪ ደንበኛ ተመላሽ የሚያደርግ መሆኑን
አሳውቋል፡ ፡
ሰርኩላር ቁጥር 52
የቬትናም ፖስታ አስተዳደር ለዓለም አቀፉ ፖስታ ህብረት አባል
አገራት የሚከተለውን ጉዳይ ማሳወቅ ይፈልጋል፡ ፡
ወደ ቬትናም በተለይም ወደ ሆቺሚኒ የመልዕክት ልውውጥ ማዕከል
(IMPC code: VNSGNA) በሚላኩ መልዕክቶች ሌብል (CN 35
ወይም CP 84 እና CN 38 ዴሊቨሪ ቢሎች) ላይ የሚቀመጡ
የአውሮፕላን በረራ ቁጥር እና ሌሎች ከዲስፓች ጋር ተያያዥ የሆኑ
ዳታዎች መልዕክቱን በትክክል ጭኖ ከሚወጣው አውሮፕላን ጋር ተዛማጅ
መሆን እንዳለባቸው አሳውቋል፡ ፡
አግባብነት ያለው የመረጃ መጣጣም ከአየር መንገዱ ጋር ሊኖር
እንደሚገባ እያሳሰበ ይህ አስፈላጊ ሁኔታ ሳይሟላ ሲቀር አየር
መንገዱ መልዕክቱ ለምን በትክክለኛው አየርመንገድ እንዳልተላከ
እንዲያብራራ ይጠየቃል፡ ፡
በመሆኑን በዚህ ሳቢያ መልዕክቶች የሚዘገዩበት እድል የሚፈጠር
መሆኑን አሳስቧል፡ ፡
ሰርኩላር ቁጥር 56
የሳይፕረስ ፖስታ አገልግሎት ለህብረቱ አባል አገራት የሚከተለው
ጉዳይ ያሳውቃል፡ ፡
ፖስታ አስተዳደሩ ለሁሉም አይነ ት መልዕክቶች የሚጠቀመው ለአንድ
ጊዜ አገልግሎት የሚውሉ ሸራዎችን በመሆኑ አባል አገራት እነ ዚህን
ባዶ ሸራዎች ለሳይፕረስ እንዳይመልሱ አሳውቋል፡ ፡
ሆኖም ግን በጥሩ ሁኔታ ላይ ያሉ ሸራዎችን ለሳይፕረስ ለሚላኩ
ዲስፓቾች መጠቀም የሚችሉ መሆኑን አሳስቧል፡ ፡
ሰርኩላር ቁጥር 57
የፓፑዋ ኒው ጊኒ ፖስታ አስተዳደር ለህብረቱ አባል አገራት
የመልዕክት እደላን ለማቀላጠፍ እና ለትክክለኛው ደንበኛ ለማደል
እንዲረዳ ወደ ፓፑዋ ኒው ጊኒ በሚላክ በእያንዳንዱ መልዕክት ላይ
ከዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩ ቁልፍ መረጃዎች እንዲፃፉ ጠይቋል፡ ፡
- የተቀባይ ሙሉ ስም
- የፖስታ ሳጥን ቁጥር
- የገጠር ወይም ከተማ ስም
- ፖስትኮድ
- የአገር ስም
- የተቀባይ ስልክ ቁጥር እና ኢ-ሜይል አድራሻ /ከተገኘ/
ሰርኩላር ቁጥር 58
የሲውዘርላንድ ፖስታ አስተዳደር ለህብረቱ አባል አገራት
በሲውዘርላንድ በኩል በአዲኮቨርት ትራንዚት ስለሚላኩ መልዕክቶች
ስርዓት/ሂደት የሚከተለውን ጉዳይ ያሳውቃል፡ ፡
ደብዳቤ
በሰርኩላር ቁጥር 220/2014 እንዳሳወቀው በደብዳቤ አሰራር ህግ
አንቀጽ RL 176 መሠረት ወደ ሌይቸቴንስቴይን
/Liechtenstein/ ለሚላኩ መልዕክቶችን የኦፕን ትራንዚት
አገልግሎት የሚሰጥ መሆኑ ይታወቃል፡ ፡ በደብዳቤ አሰራር ህግ
አንቀጽ RL 211 መሠረት ለቆጠራ ወቅት ሲባል፤ በአዲኮቨርት
ትራንዚት ወደ Liechtenstein የሚላኩ መልዕክቶች በ CN
65 ቢል ተደግፈው መላክ ይኖርባቸዋል፡ ፡
የሲውዝ ፖስታ አስተዳደር ለህብረቱ አባል አገራት በ2015
ትራንዚት ኮምፔንዲም በምድብ 1 እና 2 ላይ በክፍል V ለተዘረዘሩ
መዳረሻ አገሮች የሚላኩ የትራንዚት አዲኮቨርት መልዕክቶችን
የሚቀበል መሆኑን አስታውሷል፡ ፡
ጥቅል
በኦፕን ትራንዚት ወደ Liechtenstein ለሚላኩ አነ ስተኛ
መጠን ጥቅል መልዕክቶችን አገልግሎት ይሰጣል፡ ፡ በጥቅል አሰራር
ህግ አንቀጽ RC 172.3 እና RC 176.2 መሠረት ጥቅሎች በ
CP 87 ቢል መካተት ይኖርባቸዋል፡ ፡
ኢ.ኤም.ኤስ
የስዊዝ ፖስታ አስተዳደር ወደ Liechtenstein የሚላኩ
ኢ.ኤም.ኤስ መልዕክቶችን ተቀብሎ መስራቱን የሚቀጥል ሲሆን እንደ
ከዚህቀደሙ ኢ.ኤም.ኤስ መልዕክቶች በኢ.ኤም.ኤስ ዲስፓች
ለሲውዘርላንድ መላክ ይኖርባቸዋል (በአዲኮቨርት ትራንዚት
አይላኩም)፡ ፡
ሰርኩላር ቁጥር 63
የኩራካኦ (CURAÇAO) ፖስታ አስተዳደር ለህብረቱ አባል አገራት
ከ1 February 2014 ጀምሮ ከ Nieuwe Post
Nederlandse Antillen N.V. ወደ Cpost
International N.V.የመጠሪያ ስም ለውጥ ያደረገ መሆኑን
አሳውቋል፡ ፡
የፖስታ አስተዳደሩ ስልክ ቁጥሮች እና የፖስታ አድራሻዎች
ያልተቀየሩ መሆናቸውን የኢ-ሜይል አድራሻ ግን ማለቂያው
@cpostint.com መሆኑን እንዲሁም የፖስታ አስተዳደሩ
ዌብሳይት አድራሻ www.cpostinternational.com
መሆኑን አሳውቋል፡ ፡
የድርጅቱን ሎጎ ከዋናው የእንግሊዝኛ ሰርኩላር ቁጥር 63 ላይ
ይመልከቱ፡ ፡
ሰርኩላር ቁጥር 73
የአፍጋኒስታን ፖስታ አስተዳደር የህብረቱ አባል አገራትን በደብዳቤ
አሰራር ህግ አንቀጽ RL 203.4 መሠረት በይዞታቸው ስር የሚገኙ
የድርጅቱ ንብረት የሆኑ ባዶ ሸራዎችን እንዲመልሱለት ጠይቋል፡ ፡
ሰርኩላር ቁጥር 74
የማዳጋስካር ፖስታ አስተዳደር ለህብረቱ አባል አገራት የሚከተለውን
ጉዳይ ማሳወቅ ይፈልጋል፡ ፡
ወደ ማዳጋስካር ተልከው የሚታደሉ መልዕክቶች እደላ ለማቀላጠፍ
እንዲረዳ ከዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩ የአድራሻ መረጃዎች አስፈላጊ
መሆናቸውን አሳስቧል፡ ፡
- የተቀባይ ሙሉ ስም እና አድራሻ
- የተቀባይ ደንበኛ ሞባይ እና መደበኛ ስልክ ቁጥር እንዲሁም
የኢ-ሜይል አድራሻ (ከተገኘ)
- የአዳይ ፖስታ ቤት ፖስት ኮድ
- የላኪ ሙሉ ስም እና አድራሻ
ሰርኩላር ቁጥር 76
የጅቡቲ ፖስታ አስተዳደር ለዓለም አቀፉ ፖስታ ህብረት አባል
አገራት ለደንበኞች SMS የመላክ አገልግሎት እና የመልዕክት
ትራኪንግ (Mail Tracking Service) አገልግሎት
መጀመሩን አሳውቋል፡ ፡
ከዚህ ጋር በተያያዘም የመልዕክት ጥራትን ፣ ብቃትን እና
የመልዕክት አሰራር ፍጥነ ት ከማሻሻል አንፃር የስልክ ቁጥር እና
የፖስታ ሳጥን ቁጥር ወደ ጅቡቲ በሚላኩ የአደራ መልዕክቶች ፣
ጥቅሎች እና የኢ.ኤም.ኤስ መልዕክቶች በሙሉ እንዲፃፍ ጠይቋል፡ ፡
ሰርኩላር ቁጥር 78
የኮሪያ ፖስታ አስተዳደር ለህብረቱ አባል አገራት የሚከተለውን
ጉዳይ ማሳወቅ ይፈልጋል፡ ፡
ከ1 August 2015 ጀምሮ በአሁኑ ወቅት እየተጠቀመበት ያለው
ባለ 6ዲጂት የፖስት ኮድ ስርዓት በባለ 5ዲጂት ስርዓት የሚለወጥ
መሆኑን ገልፃ Dል፡ ፡
አዲሱ ፖስት ኮድ ከነባሩ ፖስት ኮድ ጋር የማይመሳሰል በመሆኑ
ሁለቱንም ፖስት ኮዶች በአንድ ጊዜ መጠቀም የማይቻል በመሆኑ አባል
አገራት ከ1 August 2015 ጀምሮ የሚልኳቸው መልዕክቶች
አዲሱን የፖስት ኮድ አድራሻ መያዛቸውን እንዲያረጋግጡ አሳስቧል፡ ፡
ለበለጠ መረጃ ዋናውን የእንግሊዝኛ ሰርኩላር ይመልከቱ፡ ፡
ሰርኩላር ቁጥር 80
በፖስታል ኮንቬንሽን አንቀጽ 34 መሠረት የዓለም አቀፉ ፖስታ
ህብረት ኦፕሬሽን ካውንስል በ April 2015 የስብሰባ ፕሮግራሙ
የ2016 የቤዚክ ኤይር ኮንቬያንስ ታሪፍ 0.624 ሺህኛ SDR
ወይም 0.000624 SDR በኪሎግራም (ከአጠቃላይ
ክብደት/Gross weight) እና በኪሎሜትር እንዲሆን መወሰኑን
አስታውቋል፡ ፡
ይህም ታሪፍ ተለዋጭ ማሳሰቢያ እስኪሰጥ ድረስ ተግባራዊ እንደሚሆን
ጨምሮ አስታውቋል፡ ፡
ለበለጠ መረጃ ዋናውን የእንግሊዝኛ ሰርኩላር ቁጥር 80
ይመልከቱ፡ ፡
ሰርኩላር ቁጥር 84
የቤላሩስ ፖስታ አስተዳደር ለህብረቱ አባል አገራት
የደብዳቤመልዕክት ዲስፓች አዘገጃጀት ጋር በተያያ ሚከተለውን
አስተያየት መስጠት ይፈልጋል፡ ፡
ደክመንት የያዙ የደብዳቤ መልዕክቶች (LC) እና አነ ስተኛ ጥቅል
መልዕክትን የያዙ የደብዳቤ መልዕክቶች (AO) ለየብቻ ዲስፓች
ተዘጃቶላቸው ቢላኩ የመልዕክት ስራው እንዲቀላጠፍ የሚያደርግ
መሆኑንና ይህ አይነ ቱ የዲስፓች አዘገጃጀት ዕቃ ያልያዙ የደብዳቤ
መልዕክቶች በጉምሩክ ሳይፈተሸ በቀጥታ እንዲያልፉ የሚያደርግ
በመሆኑ በፍጥነት እንዲታደሉ እንደሚያደርግ ገልፃ Dል፡ ፡
ሰርኩላር ቁጥር 88
የስፔን ፖስታ አስተደዳደር ከህብረቱ አባል አገራት በጉምሩክ ተፈትሸው የሚያልፉ
መልዕክቶች ትክክል ካልሆነ ወይም ካልተሟላ የጉምሩክ ዲክላሬሽን ሌብል (CN22 ወይም
CN23) ጋር በተደጋጋሚ እየተላኩለት መሆኑንና ይህም ለጉምሩክ አሰራር አስቸጋሪ
ከመሆኑም ባሻገር የመልዕክት ስራው ላይ መዘግየትን እያስከተለ መሆኑን ለህብረቱ አባል
አገራት ማሳወቅ ይፈልጋል፡ ፡
በስፔይን የጉምሩክ አሰራር ህግ መሠረት የጉምሩክ ፍተሻ የሚፈልግ ዕቃ የያዙ ማንኛው
አይነ ት ዓለም አቀፍ መልዕክቶች (ጥቅል፣ አነ ስተኛ ጥቅል እና ኢ.ኤም.ኤስ) በCN22
ወይም CN23 የከስተም ዲክላሬሽን ተደግፈው መላክ ይኖርባቸዋል፡ ፡
ትክክለኛ ካልሆነ ወይም ካልተሟላ የጉምሩክ ዲክላሬሽን ሌብል ጋር የሚላኩ መልዕክቶች
በጉምሩክ ተቀባይነ ት የሌላቸው በመሆኑ ይህ ሁኔታ ሲያጋጥም ተቀባይ ፖስታ አስተዳደር
ያልተሟሉ መረጃዎችን እንዲያሟላ ፤ የተሳሳቱ መረጃዎችንም እንዲያስተካከል የሚደረግ
ሲሆን ይህም የመልዕክት ስራው እንዲጓተት የሚያደርግ በመሆኑ በመልዕክት ጥራት ላይ
ቀጥተኛ አሉታዊ ተፅእኖ ያሳድራል፡ ፡
በመሆኑም የስፔን ፖስታ አስተዳደር የህብረቱ አባል አገራት CN22 እና CN23
የከስተም ዲክላሬሽን ሌብሎች በትክክል መሞላታቸውን እያረጋገጡ ጠይቋል፡ ፡ በደብዳቤ
አሰራር ህግ አንቀጽ RL156 እና በጥቅል አሰራር ህግ አንቀጽ RC151 መሰረት
ከዚህ በታች የተዘረዙ መረጃዎች በጉምሩክ ዲክላሬሽን ሌብል ላይ መሙላታቸውን ማረጋገጥ
አስፈላጊ መሆኑን አሳስቧል፡ ፡
- ፎርሙ በእንግሊዝኛ ቋንቋ መሞላቱን
- የእቃው ይዘት ሙሉ ዝርዝር መረጃና የእያንዳንዱ እቃ ትክክለኛ ዋጋ
- ከተቻለ የላኪና የተቀባይ ደንበኞች ስልክ ቁጥሮች
- ማንኛውም አስፈላጊ ዶክመንቶች (ኢንቮይስ ፣ የላኪ እና አስመጪ ፍቃድ፣
የሳኒታሪ ሰርተፊኬት እና የመሳሰሉት) በላይኛው የመልዕክቱ አካል ላይ
መለጠፉን
ሰርኩላር ቁጥር 89
የአንጎላ ፖስታ አስተዳደር ከዚህ በታች የተጠቀሱ መረጃዎችን በሚላኩ
ጥቅሎች ላይ ማስፈር አስፈላጊ መሆኑን ለህብረቱ አባል አገራት ማሳወቅ
ይፈልጋል፡ ፡
- የላኪ እና የተቀባይ ሙሉ አድራሻ
- የእቃው ብዛት እና የእናዳንዱ ዕቃ ዋጋ እንዲሁም የኢንቮይሱ
አጠቃላይ የዋጋ ድምር
ከላይ የተገለፀው መረጃ ሳይካተት ሲቀር የጉምሩክ ፍተሻ ስራው የሚዘገይ
መሆኑን እና ለእቃው/ለመለልዕክቱ ግምታዊ ዋጋ የሚሰጥ መሆኑን
ገልፃ Dል፡ ፡
ሰርኩላር ቁጥር 91
የአዘርባጃን ፖስታ አስተዳደር ለህብረቱ አባል አገራት የሚከተለው
ጉዳይ ማሳወቅ ይፈልጋል፡ ፡
የመልዕክት እደላ ጥራትን እና የጉምሩክ ፍተሻ/ቁጥጥር ስራን
ለማቀላጠፍ አባል አገራትን ከዚህ በታች የተዘረዘሩ ጉዳዮችን
እንዲያሟሉ በትህትና ጠይቋል፡ ፡
- በCN 23 ከስተም ዲክላሬሽን ፎርም ላይ የተቀባይ ደንበኛ ሙሉ
ስም እና አድራሻ እንዲሁም ስልክ ቁጥር (ከተገኘ)
እንዲያሰፍሩ፡ ፡
- በዓለም አቀፉ ፖስታ አሰራር ህግ በተለይም በደብዳቤ አሰራር
ህግ አንቀጽ RL 156 እንዲሁም በጥቅል አሰራር ህግ አንቀጽ
RC 151 መሠረት የCN 23 እና CN 22 ከስተም ዲክላሬሽን
ፎርም ላይ የሚጠየቁ መረጃዎች በአግባቡ ተሞልተው እንዲላኩ፡ ፡
ሰርኩላር ቁጥር 94
የጃማይካ ፖስታ አስተዳደር ለህብረቱ አባል አገራት የሚከተለውን ጉዳይ
ጠይቋል፡ ፡
ወደ ጃማይጀካ ተልከው በሚታደሉ መልዕክቶች ላይ የተቀባይ ደንበኛ ቀጥታ
ወይም ሞባይል ስልክ ቁጥር (ከተገኘ) በማስፈር መላክ እንደሚገባ
እያሳሰበ ይህም የጃማይካ ፖስታ አስተዳደር የተቀበላቸውን መልዕክቶች
ለደንበኞች መልዕክት እንደመጣላቸው በአጭር ጽሁፍ መልዕክት (SMS)
በማሳወቅ መልዕክቶቹን ሳይዘገዩ ማደል እንደሚያስችለው እንዲሁም
የማኑዋል አድቫይሶችን ቁጥር ለመቀነ ስ እንደሚያግዘው ገልፃ Dል፡ ፡
ሰርኩላር ቁጥር 95
የካዛኪስታን ፖስታ አስተዳደር የህብረቱ አባል አገራት የሚከተለውን
ጉዳይ ጠይቋል፡ ፡
ወደ ካዛኪስታን ተልከው በሚታደሉ በሁሉም አደራ ደብዳቤዎች እና ጥቅል
መልዕክቶች ላይ የተቀባይ ሞባይል ስልክ ቁጥር (ከታወቀ) ላኪ ደንበኞች
አንዲያሰፍሩ እዲያደርጉ ፤ ይህም ተቀባይ ደንበኞችን በአጭር የጽሁፍ
መልዕክት (SMS) ፖስታ እንደመጣላቸው ለማሳወቅ የሚረዳና ወቅታዊ
የመልዕክት ዕደላ ስራን የሚያቀላጥፍ እንዲሁም የዕደላ ሙከራ
ማስታወሻዎችን (አድቫይሶችን) አስፈላጊነት ለመቀነ ስ የሚየስችለው
መሆኑን ጨምሮ ገልፃ Dል፡ ፡
ሰርኩላር ቁጥር 96
የኖርዌይ ፖስታ አስተዳደር ለህብረቱ አባል አገራት በኮፐንሃገን
አለማቀፍ የመልዕክት ማዕከል ይጠቀምበት በነበረው የ IMPC ኮድ (IMPC
code: DKCPHK) ላይ ለውጥ ያደረገ መሆኑን ማሳወቅ ይፈልጋል፡ ፡
ከ10 June 2015 ይህ IMPC ከደብዳቤ መልዕክት በተጨማሪ የጥቅል መልዕክቶችንም የሚያስተናግድ ይሆናል፡ ፡
የፖስታ ቤቱ IMPC ኮድ እና መጠሪያ ከዚህ ቀጥሎ በተዘረዘረው መሠረት የተለወጠ መሆኑን ያረጋግጡ፡ ፡
IMPC ኦፕሬተር ኮድ ፡ NOA
IMPC ኮድ: DKCPHZ
IMPC ባለ 12 ካራክተር ስም፡ CPH ETOE NOA
IMPC ባለ 32 ካራክተር ስም፡ COPENHAGEN Z ETOE NOA
ከዚህ ቀደም የነ በረው IMPC ኮድ እና ተያያዥ ስሞች በቀጣይ የማያገለግሉ መሆኑን አሳስቧል፡ ፡
ሰርኩላር ቁጥር 97
የታላቋ ብሪታንያ ፖስታ አስተዳደር ለህብረቱ አባል አገራት የCN 08 አቤቱታዎች እና
የዘገዩ/የጠፉ መልዕክቶች አቤቱታዎችን መላኪያ ትክክለኛ ዝርዝር አድራሻን ማስታወስ
ይፈልጋል፡ ፡
ለደብዳቤ መልዕክት አቤቱታዎች የህብረቱ አባል አገራት CN08 አቤቱታዎች እና ሌሎች
ተያያዥ አቤቱታዎቻቸውን በኢሜይል አድራሻ
[email protected] እንዲልኩ ይህም ተመራጭ የመገናኛ ዘዴ
መሆኑን አሳስቧል፡ ፡ አቤቱታዎቹን ኢ-ሜይል ለማድረግ የማያስችሉ አስቸጋሪ ሁኔታ ከተፈጠረ
ትክክለኛው የፖስታ አድራሻ እንደሚከተለው ይሆናል፡ ፡
Royal Mail International Team P.O.Box 740 STOKE ON TRENT ST1 5XZ GREAT BRITAIN
አቤቱታዎች በፖስታ በሚላኩበት ወቅት በአደራ የአየር መልዕክት መላክ እንደሚገባ እና ቀደም
ሲል የቀረቡ አቤቱታዎች ወይም ተመሳሳይ አቤቱታዎች (duplicate
inquires/CN08) መላክ እንደማይገባ ከተላኩ ግን የመልስ አሰጣጥ ስራው ላይ
መዘግየትን የሚፈጥር መሆኑን አሳስቧል፡ ፡
በተመሳሳይ ለጥቅል መልዕክት አቤቱታዎች IBISን (Internet Based Inquiry
System) መጠቀም የሚመረጥ ሰሆን ይህን ስርዓት ለመጠቀም የማያስችል አስቸጋሪ ሲሆን
CN08 ፎርሞች ከዚህ ቀጥሎ ባለው ኢ-ሜይል አድራሻ
[email protected] መላክ እንደሚቻል፡ ፡
ኢሜይል ለመጠቀም አስቸጋሪ ከሆነ ደግሞ በሚከተለው ፖስታ አድራሻ በአደራ የአየር መልዕክት
እንዲላኩለት ጠይቋል፡ ፡
Parcelforce Worldwide Enquiry Center Enquiries Manager 2 Denby Dale Road WAKEFIELD WF1 1AA GREAT BRITAIN
ሰርኩላር ቁጥር 100
የዚምባቡዌ ፖስታ አስተዳደር ሂያጅ ጥቅል ፤ ደብዳቤ እና ኢ.ኤም.ኤስ
መልዕክቶችላይ ላኪ ደንበኞች ከዚህ ቀጥሎ ያሉትን መረጃዎች ማሟላታቸውን
እንዲያረጋግጡ የህብረቱ አባል አገራት ጠይቋል፡ ፡
- የተቀባይ ሙሉ ስም እና አድራሻ
- የተቀባይ ሞባይል ስልክ ቁጥር እና ኢ-ሜይል አድራሻ (ከተገኘ)
- በCN 22 እና CN 23 ላይ የተጠየቁ መረጃዎች በሙሉ መሞላታቸውን
- ሙሉ እና ዝርዝር የመልዕክቱ ይዘት ከዕቃው ዋጋ ጋር
ከላይ የተገለፁት መረጃዎች ሲሟሉ የጉምሩክ ፍተሻ ስራን የሚያቀላጥፍ
መሆኑን አስረድቷል፡ ፡
ሰርኩላር ቁጥር 101
የፊንላንድ ፖስታ አስተዳደር በዓም አቀፉ ፖስታ ህብረት አባል አገራት
ይዞታ ስር ሊገኙ የሚችሉ የፖስታ አስተዳደሩ ንብረት የሆኑ ባዶ
ጀሸራዎችን እንደሚልስሉት ጠይቋል፡ ፡
ሰርኩላር ቁጥር 103
የዓለም አቀፉ ፖስታ ህብረት በ20015.1 ባደረገው የፖስታል ኦፕሬሽን
ካውንስል (POC) ስብሰባ በዓለም አቀፉ ፖስታ ህብረት ጀነ ራል
ሬጉሌሽን አንቀጽ 104.9.2 መሠረት በደብዳቤ እና ጥቅል ሬጉሌሽን
ላይ የቀረቡ የማሻሻያ ሃሳቦችን በመመርመር እንዲጸድቁ ያደርጓል፡ ፡
እነ ዚህም ማሻሻያዎች በዋናው የእንግሊዝኛ ሰርኩላር ላይ የቀረቡ ሲሆን
ተግባራዊ የሚሆንበትም ተገልፃ Dል፡ ፡
ሰርኩላር ቁጥር 104
የቬትናም ፖስታ አስተዳደር ለህብረቱ አባል አገራት የሚከተለውን ጉዳይ
ማሳወቅ ይፈልጋል፡ ፡
በሃኖዪ እና ሆቺሚንህ የሚገኙ ሁለት የመልዕክት ልውውጥ ቢሮዎቹን መጪ
መልዕክቶችን በመረከብ ወደ ተለያዩ የአገሪቱ ወደቦች እንዲያሰራጭ
የወሰነ መሆኑንና ግቡም ፈጣን የመልዕክት እደላን መፍጠር መሆኑን
ገልፃ Dል፡ ፡
በመሆኑም የቬትናም ፖስታ አስተዳደር በዋናው የእንግሊዝኛ ሰርኩላር
ቁጥር 104 አባሪ በተደረገው ሰንጠረዥ ላይ በተገለፀው ፖስትኮድ
መሠረት መልዕክቶችን በመዘርዘር ወደ ትክክለኛው የመልዕክት ልውውጥ ቢሮ
እንዲልኩለት ጠይቋል፡ ፡
ሰርኩላር ቁጥር 105
የሃንጋሪ ፖስታ አስተዳደር ቁጥራቸው ብዙ የሆነ በቂ አድራሻ የሌላቸው
አደራ እና ተራ የደብዳቤ መልዕክቶች እየደረሱት መሆኑን ለህብረቱ አባል
አገራት አሳውቋል፡ ፡ እነ ዚህ መልዕክቶች የቤት ወይም የጎዳና ቁጥር
የሌላቸው ሲሆን የተቀባይ ስልክ ቁጥር ፤ ከተማ እና ፖስት ኮድ ብቻ
የተፃፈባቸው መሆኑን ገልፃ Dል፡ ፡
የደንበኞችን አቤቱታ ለማስቀረት የሃንጋሪ ፖስታ አስተዳደር ላኪ ፖስታ
አስተዳደሮች በደብዳቤ አሰራር ህግ አንቀጽ RL 125.3.3 ላይ
የሰፈረውን ድንጋጌ እንዲያሟሉ ጠይቋል፡ ፡
ከላይ የተገለፀውን ድንጋጌ ባለመከተል የሚላኩ መልዕክቶችን የሃንጋሪ
ፖስታ አስተዳደር የማያድል መሆኑንና መልዕክቶቹንም ከ CN15 ሌብል
ጋር ለላኪ አገር ተመላሽ የሚያደርግ መሆኑን አሳውቋል፡ ፡
ሰርኩላር ቁጥር 106
የኮሎምቢያ ፖስታ አስተዳደር (Servicios Postales Nacional S.A 4–
72) የመልዕክት ፍሰትን ፣ የመልክት ለማዘጋጀት የሚወስደውን ጊዜ እና የዕደላ
ፍጥትን ለማሻሻል መልዕክት የሚልኩና የሚቀበሉ የመልዕክት ልውውጥ ቢሮዎችን ያዋቀረ
መሆኑን ለህብረቱ አባል አገራት አሳውቋል፡ ፡
ፖስታ አስተዳደሮችም ከዚህ በታች የተዘረዘሩ የዓለም አቀፍ መልዕክት ማዘጋጃ
ማዕከሎች/international mail processing centres (IMPCs)
ኮዶችን እንዲቀሙ ጠይቋል፡ ፡
IMPC
ኮድ
IMPC ስም የመልዕክት
ምድብ
የመልዕክት
ዓይነ ት
የመልዕክት
ፍሰት
የማዕከሉ
አገ/ት
COBAQA BARRANQUILLA Surface
non-
priority
and
surface
priority
ጥቅል፣
ደብዳቤ፣
ኢ.ኤም.ኤስ
እና ባዶ
ሸራዎች
መጪ መልዕክት ብቻ
መልዕክት ልውውጥና መልዕክት ክፍል
COBOGC BOGOTA C IMPORT EXCHANGE OFFICE
Air,
S.A.L.,
surface
non-
priority
and
surface
priority
ጥቅል፣
ደብዳቤ፣
ኢ.ኤም.ኤስ
እና ባዶ
ሸራዎች
መጪ መልዕክትና ትራንዚት መልዕክት
መልዕክት ልውውጥና መልዕክት ክፍል
COBOGG BOGOTA G EXPORT EXCHANGE
Air,
S.A.L.,
surface
ጥቅል፣
ደብዳቤ፣
ኢ.ኤም.ኤስ
ሂያጅ መልዕክትና ትራንዚት
መልዕክት ልውውጥና መልዕክት
OFFIC non-
priority
and
surface
priority
እና ባዶ
ሸራዎች
መልዕክት ክፍል
ሰርኩላር ቁጥር 107
የኢንዶኔዢያ ፖስታ አስተዳደር ለህብረቱ አባል አገራት እ.ኤ.አ 2009 በተላከው
ሰርኩላር ቁጥር 33 ላይ ያሳወቀውን ጉዳይ ማስታወስ ይፈልጋል፡ ፡
የኢንዶኔዢያ ፖስታ አስተዳደር ወደ Timor-Leste (Dem. Rep) ለሚላኩ
መልዕክቶች የትራንዚት አዲኮቨርት አገልግሎት የሚሰጥ መሆኑን ሆኖም ግን ከቲሞር
ሌስቴ ውጭ ወደ ሌላ አገር የሚላኩ መልዕክቶች ሲደርሱት እንደሚስሴንት መልዕክት
በመቁጠር ክፍያ የሚጠይቅ መሆኑን ገልፃ Dል፡ ፡
በደብዳቤ አሰራር ህግ አንቀጽ RL 211.1.5 መሠረት የኢንዶኔዢያ ፖስታ ለህብረቱ
አባል አገራት እንደየአገሩ ምድብ ከዚህ በታች በተገለፀው የሚሴንት ታሪፍ መሠረት
ክፍያ የሚጠየቁ መሆኑን አሳውቋል፡ ፡
የመዳረሻ አገር የማጓጓዣ ክፍያ ታሪፍ
ሃንድሊንግ ክፍያ
ተጨማሪ ክፍያ
አጠቃላይ የሚሴንት መልዕክት ክፍያ
ምድብ
አገራት በኪ.ግ (SDR)
በኪ.ግ (SDR)
በኪ.ግ (SDR
)
በኪ.ግ (SDR)
1 ደቡብ ምስራቅ ኤሲያ አባል አገራት
1.804 0.195 2 3.999
2 ኤሲያ-ፓሲፊክ 3.492 0.195 1 5.687
3 አፍሪካ 6.926 0.195 2 9.121
4 አውሮፓ 7.566 0.195 2 9.761
5 ሰሜንና ደቡብ አሜሪካ
10.185 0.195 2 12.385
ሰርኩላር ቁጥር 109
የሊብያ ፖስታ አስተዳደር ለህብረቱ አባል አገራት የሚከተለውን ጉዳይ
ማሳወቅ ይፈልጋል፡ ፤
በ3 August 2011 በተደረገው የአገሪቱ ትራንዚሽናል ካውንስል
አዋጅ ከዚህ በፊት Libyan Arab Jamahiriya ተብሎ ይጠራ
የነ በረው የአገሪቱ መጠሪያ ስም ወደ "Libya" የተቀየረ መሆኑን
እንዲሁም የአገሪቱ ብሔራዊ ሰንደቃላማም የተለወጠ መሆኑን አሳስቧል፡ ፡
ሰርኩላር ቁጥር 110
የዴንማርክ ፖስታ አስተዳደር ለህብረቱ አባል አገራት ወደ ዴንማርክ
የሚላኩ መጽሄቶች እና ጋዜጣዎች የያዙ የደብዳቤ መልዕክቶች በCN
22 የጉምሩክ ዲክላሬሽን ሊኖራቸው እንደሚገባ እንዲሁም
ከመሰራጨታቸው በፊት በጉምሩክ እንዲፈተሸ አዲስ የወጣው የአገሪቷ
ብሔራዊ ህገደንብ እንደሚያስገድድ ማሳወቅ ይፈልጋል፡ ፡
ይህ ህገደንብ ከ 1 July 2015 ጀምሮ ተግባራዊ እንደሆነ
ተገልፃ Dል፡ ፡
ሰርኩላር ቁጥር 114
የናይጄሪያ ፖስታ አስተዳደር ለህብረቱ አባል አገራት የፖስታ አስተዳደሩ
ንብረት የሆኑ በይዞታቸው ስር ሊገኙ የሚችሉ ባዶ የኢ.ኤም.ኤስ
ሸራዎችን በተቻለ ፍጥነ ት እንደሚልስሉት ጠይቋል፡ ፡
በደብዳቤ አሰራር ህግ አንቀጽ RL 203 መሠረት ፖስታ አስተዳደሮች
ወደ ናይጄሪያ የሚልኳቸውን የኢ.ኤም.ኤስ መልዕክት ዲፓቾች በናይጄሪያ
ፖስታ አስተዳደር ሰማያዊ ሸራዎች በመጠቀም መላክ የሚችሉ መሆኑን
አሳስቧል፡ ፡
በተጠቀሰው ጊዜ ሸራዎቹ የማይመለሱለት ከሆነ በደብዳቤ አሰራር ህግ
አንቀጽ RL 203 ተ.ቁ 9 እና 10 ላይ በተጠቀሰው መሠረት እነዚህን
ሸራዎች ለመተካት ያወጣውን ወጪ ለመሸፈን ፖስታ አስተዳደሩ ክፍያ
የሚጠይቅ መሆኑን አሳውቋል፡ ፡
ሰርኩላር ቁጥር 115
የዩናይት ስቴትስ ኦፍ አሜሪካ ፖስታ አስተዳደር ከአሜሪካ በስህተት
የተላኩ በዓለም አቀፉ ፖስታ ህብረት ኮንቬንሽን አደገኛ ዕቃዎች ተብለው
የተፈረጁ መልዕክቶች ሲደርሱ በተሻሻለው ከዚህ በታች በተገለጸው የኢ-
ሜይል አድራሻ ሪፖርት እንዲያደርጉለት ለህብረቱን አባል አገራት
አሳውቋል፡ ፡
ፖስታ አስተዳደሮች ከላይ የተጠቀሱት ዓይነ ት ጉዳዮች ሲያጋጥሙ
የመልዕክቶቹን CN 13 መረጃዎች (የላኪና የተቀባይ ስም ፣
የመልዕክቱን ሬጂስተር ቁጥር እንዲሁም የመልዕክቱን ይዘት ዝርዝር መረጃ
ጨምሮ) በኢሜይል አድራሻ [email protected] ሪፖርት
እንዲያደርጉለት ጠይቋል፡ ፡
ሰርኩላር ቁጥር 116
የዩናይት ስቴትስ ኦፍ አሜሪካ ፖስታ አስተዳደር የመጪ አደራ መልዕክቶች
አገልግሎት አሰጣጡ ገጽታ ላይ ለውጥ የሚያደርግ መሆኑን ለህብረቱ አባል
አገራት ማሳወቅ ይወዳል፡ ፡
ከ1 October 2015 ጀምሮ በዩፒዩ ሰፕሊሜንታሪ ሪመነሬሽን
ፕሮግራም ለሚሳተፉ አገሮች ብቻ የመጪ መልዕክቶች ትራኪንግ እና የእደላ
መረጃ በwww.usps.com እንዲታይ የሚደረግ ሲሆን ለሌሎች አገሮች
ግን መረጃው በፖስታ አስተዳደሩ ድረገጽ ላይ የማይታይ መሆኑን
ገልፃ Dል፡ ፡
ሰርኩላር ቁጥር 118
የራሺያ ፖስታ አስተዳደር ለህብረቱ አባል አገራት ከዚህ በታች
የተዘረዘሩ 5 የመልዕክት ልውውጥ ቢሮዎቹን የዘጋ መሆኑን ማሳወቅ
ይፈልጋል፡ ፡
- MOSKVA PCI–1 (RUMOWB);
- MOSKVA PCI–1 SURFACE (RUMOWH);
- MOSKVA PCI–4 (RUMOWI)
- MOSKVA MINSK AMB (RUMOWP)
- MOSKVA PCI–15 (RUMOWK)
ከ1 August 2015 ጀምሮ የደብዳቤ መልዕክቶች አዲስ ወደተከፈተው
የመልዕክት ልውውጥ ቢሮ በሚከተለው አድራሻ መላክ እንደሚኖርባቸው
ገልፃ Dል፡ ፡
MOSKVA PCI–21 (IMPC code: RUMOWS)
Marushkinskoye settlement
near Sharapovo village
MOSCOW
102975
ሰርኩላር ቁጥር 119
የአርሜኒያ ፖስታ አስተዳደር ለህብረቱ አባል አገራት የሚከተለውን ጉዳይ
ማሳወቅ ይፈልጋል፡ ፡ በጉምሩክ ሊፈተሹ የሚገባቸው ዕቃዎችን የያዙ
መልዕክቶች ካልተሟላ ወይም ትክክለኛ መረጃ ካልያዙ CN 22 እና CN
23 ከስተም ዲክላሬሽን ፎርሞች ጋር እየተላኩለት እንደሆነ ይህም
በጉምሩክ አሰራር ላይ ችግር ከመፍጠሩም ባሻገር የመልዕክት ስራው ላይም
መዘግየትን እየፈጠረ እንደሚገኝ ገልፃ Dል፡ ፡
በአርሜኒያ የጉምሩክ አሰራር ህግ መሠረት ማንኛውም በጉምሩክ ተፈትሾ
ማለፍ ያለበትን ዕቃ የያዘ ዓለም አቀፍ መልዕክት (ጥቅል፣ አነ ስተኛ
ጥቅል እና ኢ.ኤም.ኤስ) በCN 22 እና CN 23 ከስተም ዲክላሬሽን
መደገፍ ይኖርበታል፡ ፡
በዚህም መሠረት የአርሜኒያ ፖስታ አስተዳደር ላኪ ፖስታ አስተዳደሮችን
በደብዳቤ አሰራር ህግ አነ ቀጽ RL156 እንዲሁም በጥቅል አሰራር ህግ
አንቀጽ RC151 ላይ የተዘረዘሩትን ሁኔታዎች ሟሟላት እንደሚገባቸው
በተለይም ፡ -
- በCN22 አና CN23 ከስተም ዲክላሬሽን ላይ የሚጠየቁ መረጃዎች
በአንግሊዝኛ ፣ በፈረንሳይኛ ወይም በተቀባይ አገር ተቀባይነ ት ባለው
ቋንቋ መሞላት እንዳለበት
- የእቃው ይዘትና የእያንዳንዱ እቃ ዋጋ በተሟላ እና በትክክል መግለጽ
- የላኪ እና የተቀባይ ስልክ ቁጥር (ከተገኘ) በCN 23 ፎርም ላይ
ማስፈር
- ማንኛው አስፈላጊ የሆነ ጠቃሚ ዶክመንት(ኢንቮይሶች ፣
የላኪ/የአስመጪ ፈቃድ ፣ የጤና ሰርተፊኬት ወዘተ…) በመልዕክቱ
ውጫዊ አካል ላይ አያይዞ መላክ እንደነሚገባ አሳውቋል፡ ፡
ሰርኩላር ቁጥር 121
የኪርጂዝስታን ትራንስፖርት እና መገናኛ ሚኒስቴር ከKyrgyz
Pochtasy እና Kyrgyz Express Post በተጨማሪ ሦስተኛ
Trans Asia Express CJSC የተባለ አዲስ ፖስታ አስተዳደር
በዓለም አቀፍ የፖስታ ኮንቬንሽን መሠረት እንዲሰራ ፈቃድ የሰጠ መሆኑን
ለህብረቱ ዓባል አገራት አሳውቋል፡ ፡
Trans Asia Express CJSC በኪርጂዝስታን ውስጥ የመጪ እና
ሂያጅ ደብዳቤ እና ጥቅል አገልግሎት የሚሰጥ ሲሆን አድራሻውም
የሚከተለው ነው፡ ፡
15 Razzakov Street
720040 BISHKEK
KYRGYZSTAN
Tel: +996 312 986 612
+996 555 588 547
E-mail: [email protected]
ከዚህ ጋር በተያያዘ በTrans Asia Express CJSC የሚሰጡ
የስራ መረጃዎች በቅርቡ በደብዳቤ እና ጥቅል ኮፔንዲየሞች ላይ በህብረቱ
ድረገጽ አማካኝነ ት እንዲገኙ የሚደረግ መሆኑን አሳውቋል፡ ፡
ለበለጠ መረጃ ዋናውን የእንግሊዝኛ ሰርኩላር ቁጥር 121 ይመልከቱ፡ ፡
ሰርኩላር ቁጥር 122
የዲሞክራቲክ ፒፕልስ ሪፐብሊክ ኦፍ ኮሪያ ፖስታ አስተዳደር ለሪፐብሊክ
ኦፍ ኮሪያ መላክ ያለባቸው ዲፓቾች/መልዕክቶች በስህተት እየደረሱት
እንደሆነ ለህብረቱ አባል አገራት ማሳወቅ ይፈልጋል፡ ፡
ወደ ዲሞክራቲክ ፒፕልስ ሪፐብሊክ ኦፍ ኮሪያ የሚላኩ ዲስፓቾች
“PYONGYANG, IMPC code KPFNJA” የሚል ሌብል ሊኖራቸው
እንደሚገባ ገልፃ Dል፡ ፡
ክሎዝድ ዲፓቾችን መላክ ያልቻሉ ፖስታ አስተዳደሮች የቻይና ፖስታ
አስተዳደርን በማማከር ትራንዚት አዲኮቨርት አገልግሎት ማመቻቸት የሚችሉ
መሆኑን አሳስቧል፡ ፡
ሰርኩላር ቁጥር 124
የሃንጋሪ ፖስታ አስተዳደር ለህብረቱ አባል አገራት የድርጅቱ እንብረት
የሆኑ በይዞታቸው ስር የሚገኙ ባዶ ሸራዎችን እንዲመልሱለት ጠይቋል፡ ፡
ባዶ ሸራዎች ወደ NPKK 1005 የመልዕክት ልውውጥ ቢሮ (IMPC
code: HUBUDA) በተላኩበት ተመሳሳይ ሩት እንዲላኩ አሳስቧል፡ ፡
እነ ዚህ ሸራዎች ሳይመለሱ ከቀረ በደብዳቤ አሰራር ህግ አንቀጽ RL
203.9 እና 10 መሠረት የመተኪያ ዋጋ ክፍያ የሚጠይቅ መሆኑን
ገልፃ Dል፡ ፡
ሰርኩላር ቁጥር 125
የቬንዙኤላ (ቦሊቫሪያን ሪፐብሊክ) ለህብረቱ አባል አገራት ከዚህ በታች
ከተዘረዘሩ አገራት ጋር የአየር መልዕክት ግንኙነ ት የሌለው በመሆኑ
ተለዋጭ መሳሰቢያ እስኪሰጥ ድረስ ለእነ ዚህ አገሮች በብትንም ሆነ
ክሎዝድ ትራንዚት የሚላኩ መልዕክቶች የማይቀበል መሆኑን አሳውቋል፡ ፡
አፍጋኒስታን ፤ አርሜኒያ ፣ አዘርባጃን ፣ ቤላሩስ ፣ ኮንጎ(ሪፐብ)፣
ኮትዲቫር፣ ኤርትራ፣ ጊኒ፣ ኢራን፣ ኢራቅ፣ ኮሪያ(ሪፐብ)፣ ሊባኖስ፣
ላይቤሪያ፣ ሊቢያ፣ ማያንማር፣ ሴራሊዮን፣ ሶማሊያ፣ ደቡብ ሱዳን፣
ሱዳን፣ ሲሪያ፣ የመን እና ዚምባቡዌ፡ ፡
ሰርኩላር ቁጥር 127
የአየርላንድ ፖስታ አስተዳደር ለህብረቱ አባል አገራት የሚከተለውን
ጉዳይ ማሳወቅ ይፈልጋል፡ ፡ የአየርላነድ መንግስት በዓይነ ቱ የተለየ ባለ
7 ዲጂት ፖስትኮድ ተግባራዊ ያደረገ መሆኑን ከ15 July 2015
ጀምሮ አዲሱን ፖስትኮድ በሁሉም አድራሻ ላይ መጠቀም እንደሚገባ
ገልፃ Dል፡ ፡ ወደአየርላንድ የሚላኩ መልዕክቶች ከዚህ በታች በተቀመጠው
የአድራሻ አፃፃፍ ምሳሌ መሰረት መላክ አለባቸው፡ ፡
Eason
80 Abbey Street Middle
DUBLIN 1
DO1 P8N3
IRELAND ከአዲሱ ፖስትኮድ ጋር ተያያዥ የሆኑ ጥያቄዎች ሲኖሩ በሚከተለው አድራሻ
መጠየቅ ይቻላል፡ ፡
Karen Dwyer, Operations Director
Capital Business Support Service (Ireland) Limited
Block C
Maynooth Business Campus
Straffan Road
MAYNOOTH
CO KILDARE
W23 F854
IRELAND
Mobile: +353 87 949 2066
E-mail: [email protected]
Website: www.ericode.ie
ሰርኩላር ቁጥር 129
የፔሩ ፖስታ አስተዳደር ለህብረቱ አባል አገራት የሚከተለውን ጉዳይ
ማሳወቅ ይፈልጋል፡ ፡
የፔሩ ጉምሩክ ለፔሩ ፖስታ አስተዳደር ወደ ፔሩ የሚመጡ የፖስታ
መልዕክቶች በበቂ ሁኔታ ባልተሞላ ወይም ተቀባይነ ት ከሌለው ከስተም
ዲክላሬሽን ጋር እየደረሱት እንደሆነ ይህም የፍተሻ እና መልዕክቱን ወደ
የሚፈለግበት ቦታ የማከፋፈል/የመላክ ስራ ላይ የማጓተት ችግር እየፈጠረ
መሆኑን አሳውቋል፡ ፡
በዚህም መሠረት የፔሩ ፖስታ አስተዳደር ለህብረቱ አባል አገራት በጥቅል
መልዕክት አሰራር ህግ አንቀጽ RC 125 እና በደብዳቤ አሰራር ህግ
አንቀጽ RL 156 መሠረት በከስተም ዲክላሬሽን ፎርም CP 72 እና
CN 23 ተደግፈው የሚላኩ መልዕክቶች (ጥቅል ፣ ኢ.ኤም.ኤስ እና
ደብዳቤ) የሚፈለገውን ትክክለኛ እና የተሟላ የጉምሩክ መረጃ መያዝ
እንዳለባቸው አሳስቧል፡ ፡
ከዚህ በታች የተዘረዘሩ መረጃዎች በከስተም ዲክላሬሽን ፎርም ላይ
ሊሰፍሩ ይገባል፡ ፡
- የላኪ ስም እና አድራሻ
- የተቀባይ ሙሉ ስም እና አድራሻ (መደበኛ ወይም ተንቀሳቃሽ ስልክ
ቁጥር እና ኢሜይል)
- የመልዕክቱ ይዘት ዝርዝር መረጃ ፣ ብዛት ፣ ክብደት እና ዋጋ
(የገንዘብ መጠሪያ ይገለፃል)
በሚላኩ መልዕክቶች ላይ የሚደረገውን የጉምሩክ ፍተሻ ስራን ለማቀላጠፍ
እንዲረዳ ፖስታ አስተዳደሮች ደንበኞቻቸው የጉምሩክ ዲክላሬሽን ፎርሞችን
እንዴት በትክክል መሙላት እንዳለባቸው ማሳወቅ እና ማረጋገጥ
እንዳለባቸው አሳስቧል፡ ፡
ሰርኩላር ቁጥር 130
የኢኳዶር ፖስታ አስተዳደር ለህብረቱ አባል አገራት የሚከተለውን ጉዳይ
ማሳወቅ ይፈልጋል፡ ፡
በከስተም ቁጥጥር ስር የሚያልፉ ሁሉም መልዕክቶች (ጥቅል ፣ አነ ስተኛ
ጥቅል እና ኢ.ኤም.ኤስ) ግልጽ ባልሆነ ወይም ባልተሟላ ከስተም
ዲክላሬሽን ተደግፈው ሲደርሱ በመልዕክት ስራው ላይ መጓተትን የሚፈጥር
መሆኑን ገልፃ Dል፡ ፡
የከስተም ፍተሻ እና የመልዕክት እደላ ስራን ለማቀላጠፍ ላኪ ፖስታ
አስተዳደሮች ከዚህ በታች የተዘረዘሩ መረጃዎችን የያዘ CN22/CN23
የጉምሩክ ዲክላራሲዮን ፎርም እንዲልኩ ጠይቋል፡ ፡
- የተቀባይ ሙሉ አድራሻ (ሙሉ ስም ፣ ስልክ ቁጥር)
- የመልዕክቱ ይዘት በዝርዝር ለምሳል አንድ አሻንጉሊት ፣ ሁለት ጥንድ
ሱሪዎች ፣ አንድ ሸሚዘው (ለስጠጦታ ፣ ለናሙና ወይም ለሌላ ጉዳይ
የተላከ መሆኑ ይገለፃል)
ይህ መረጃ በትክክል ወይም በአግባቡ ካልቀረበ መልዕክቱ ወደ መጣበት
አገር ተመላሽ የሚደረግ መሆኑን በተጨማሪም የመልዕክቱ ይዘት ግልጽ
ካልሆነ ጉምሩክ ተቀባይ ደንበኛ ደጋፊ ዶክመንቶችን እንዲቀርብ ለመጠየቅ
አድራሻውን የሚፈልግ መሆኑን አሳውቋል፡ ፡
ለበለጠ መረጃ ዋናውን የእንግሊዝኛ ሰርኩላር ቁጥር 130 ይመልከቱ፡ ፡
ሰርኩላር ቁጥር 131
የፓራጓይ ፖስታ አስተዳር ለህብረቱ አባል አገራት የሚከተለውን ጉዳይ
ማሳወቅ ይፈልጋል፡ ፡ ወደ ፓራጓይ የሚላኩ መልዕክቶች በአሜሪካ
የአየርመንገድ እና ታምፓ በሚባል አየር መንገድ ተጭኖ መላኩን እንዲሁም
ከዲስፓቹ ጋር CN 38 መያያዙን እንዲያረጋግጡ ጠይቋል፡ ፡
ይህም የመልዕክት ስርጭት ስራን እንደሚያቀላጥፍ ፣ በዕደላ ላይ
የሚያጋጥሙ ችግሮችን እንደሚቀንስ እንዲሁም አጠቃላይ የመልዕክት ስራውን
እንዲሻሻል የሚያደርግና የደንበኞችንም እምነ ት የሚያጠነክር መሆኑን
ገልፃ Dል፡ ፡
ሰርኩላር ቁጥር 132
የቤልጂየም ፖስታ አስተዳደር በጉምሩክ የሚፈተሹ መልዕክቶች ትክክል
ባልሆነ እና ባልተሟላ የጉምሩክ ዲክላራሲዮን ጋር እየደረሱት መሆኑን
ለህብረቱ አባል አገራት አሳውቋል፡ ፡
ይህም ሁኔታ በፖስታ አስተዳደሩ ላይ ተጨማሪ ስራን እየፈጠረ በመሆኑም
መልዕክት ከመላክ እስከ ማደል ባለው የደንበኞች አገልግሎት ልምድ ላይ
አሉታዊ ተጽእኖ እያሳደረ መሆኑን ገልፃ Dል፡ ፡ በመሆኑም የቤልጂየም ፖስታ
አስተዳደር ላኪ ፖስታ አስተዳደሮች CN 22 እና CN 23 ፎርሞች
በትክክልና በተሟላ መልኩ መሞላታቸውን እንዲያረጋግጡ ጠይቋል፡ ፡
በተጨማሪም ፖስታ አስተዳደሩ የህብረቱ አባል አገራት በደብዳቤ አሰራር
ህግ አንቀጽ RL 156 እንዲሁም በጥቅል አሰራር ህግ አንቀጽ RC
151 ላይ የተዘረዘሩ ሁኔታዎች በተለይም ከዚህ በታች የተዘረዘሩት
መሟላታቸውን እንዲያረጋግጡ መክሯል፡ ፡
- በCN 22 እና CN 23 ፎርም ላይ የሚጠየቁ መረጃዎች
በእንግሊዝኛ፣ በፈረንሳይኛ ወይም በስፓኒሽ ቋንቋ መሞላት
እንዳለባቸው
- የመልዕክቱ ይዘት ከእያንዳንዱ እቃ ዋጋ ጋር በዝርዝር መገለጽ
ይኖርበታል
- ከተገኘ የተቀባይ ደንበኛ ስልክ ቁጥር በCN 23 ፎርም ላይ
ይሰፍራል
- ሁሉም አስፈላጊ ዶክመንቶች (ኢንቮይስ ፣ የላኪ ወይም የአስመጪነት
ፈቃድ ፣ የጽዳትና ጤና አጠባበቅ ሰርተፊኬት እና የመሳሰሉት)
ከመልዕክቱ ውጫዊ አካል ጋር ተያይዘው መላክ ይኖርባቸዋል፡ ፡
ሰርኩላር ቁጥር 133
የኢኳዶር ፖስታ አስተዳደር የአቤቱታ (CN 08) አያየዝ ስራን
ለማሻሻል እንዲያግዘው ለዚህ ስራ ብቻ የሚያገለግል የኢ-ሜይል አድራሻ
ያዘጋጀ መሆኑን ለህብረቱ አባል አገራት ማሳወቅ ይፈልጋል፡ ፡
በመሆኑም የኢኳዶር ፖስታ አስተዳደር በቻለ መጠን የደንበኞች አቤቱታዎች
ከዚህ በታች በተገለፀው አድራሻ እንዲላኩለት ጠይቋል፡ ፡
ሰርኩላር ቁጥር 134
የጣሊያን ፖስታ አስተዳደር ለህብረቱ አባል አገራት የሚከተለውን ጉዳይ
ማሳወቅ ይፈልጋል፡ ፡
በቅርብ ጊዜ በፖስታ ኢንደስትሪ ሬጉሌሽን ላይ በተደረገው ለውጥ መሠረት
ከ October 1, 2015 ጀምሮ በምረቱ እና በዓለም አቀፍ ፖስታ
አገልግሎት ስራው ላይ ማሻሻያ የሚያደርግ መሆኑን ገልDፃል፡ ፡
ከአገልግሎት አሰጣጥ ጋር በተያያዘ፡
-
ሰርኩላር ቁጥር 136
የቬይትናም ፖስታ አስተዳደር ለህብረቱ አባል አገራት የሚከተለውን ጉዳይ
ያሳውቃል፡ ፡
የአደራ ደብዳቤዎችን እና ጥቅል መልዕክቶችን የሚመለከቱ CN 08 እና
CN 48 ፎርሞች ከዚህ በታች ባለው አድራሻ መላክ እንዳለባቸው
ገልፃ Dል፡ ፡
1 Hanoi Customer Service
No. 75 Dinh Tien Hoang Str.
Hoan Kiem District
HANOI
VIET NAM
Tel: +84 4 39392469
Fax: +84 4 39362578
E-mail: [email protected]
2 Hochiminh-City Customer Service
No. 125 Hai Ba Trung Str.
Ben Nghe Ward District 1
HOCHIMINH-CITY
VIET NAM
Tel: +84 8 38271352 or 38237785
Fax: +84 8 38237784
E-mail: [email protected]
ሰርኩላር ቁጥር 139
የሆንዱራስ ፖስታ አስተዳደር ወደ አገሩ የሚላኩለት ዲስፓቾች በሙሉ ለ EGUCIGALPA መልዕክት ልውውጥ (MPC code:
HNTGUA) ብቻ መላክ እንዳለባቸው እየገለፀ የፑኤርቶ ኮርቴስ መልዕክት ልውውጥ የተዘጋ መሆኑን አያይዞ ለህብረቱ አባል አገራት አሳውቋል፡ ፡
ሰርኩላር ቁጥር 140
የኬኒያ ፖስታ አስተዳደር ለህብረቱ አባል አገራት የሚከተለውን ጉዳይ
አሳውቋል፡ ፡ በዩ.ፒ.ዩ ስታንዳርድ መሠረት መልዕክቶችን ለትክክለኛው
ደንበኛ መታደሉን ለማረጋገጥ ወደ ኬኒያ የሚላኩ ሁሉም ዓይነ ት
ደብዳቤዎች እና ጥቅል መልዕክቶች ከዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩ ቁልፍ
መረጃዎችን መያዝ እንዳለባቸው አሳስቧል፡ ፡
- የተቀባይ ሙሉ ስም እና አድራሻ ፤ የፖ.ሳ.ቁ ፣ የፖስታ ቤቱን
መጠሪያ ፣ ክ/ሃገር እና አገርን ጨምሮ
- የአዳይ ፖስታ ቤት ፓስል ኮድ
- የላኪ ሙሉ ስም እና አድራሻ
- የተቀባይ ደንበኛ የስል ቁጥር እና ኢ-ሜይል (ከተገኘ)፡ ፡ ይህም
የመልዕክት አደላ መረጃ አያያዝን የሚያሻሽል መሆኑን አሳውቋል፡ ፡
ሰርኩላር ቁጥር 143
የዩክሬይን ፖስታ አስተዳደር "Ukrposhta" በአባል አገራት ይዞታ
ስር ሊኖር የሚችል የድርጅቱ ንብረት የሆኑ ባዶ ሸራዎችን እንዲመለሱለት
ጠይቋል፡ ፡
እነ ዚህ ባዶ ሸራዎች ወደ KIEV P1–15 (IMPC code:
UAIEVK) የመልዕክት ልውውጥ ቢሮ እንዲለመሱለት ጠይቋል፡ ፡
እነ ዚህ ባዶ ሸራዎች ሳይመለሱ ቢቀሩ በደብዳቤ አሰራር ህግ አንቀጽ RL
203.9 እና 10 መሠረት ከሚመለከተው ፖስታ አስተዳደር የማካካሻ
ክፍያ የሚጠይቅ መሆኑን ገልፃ Dል፡ ፡
ሰርኩላር ቁጥር 144
የማሌዢያ ፖስታ አስተዳደር ለህብረቱ አባል አገራት የሚከተለውን ጉዳይ
አሳውቋል፡ ፡ በአገሪቱ የጉምሩክ ህግ መሰረት እያንዳንዱ የፖስታ
መልዕክት የተቀባዩን ሙሉ ስም፣ አድራሻ እና መሰል መረጃዎች መያዝ
ይኖርበታል፡ ፡
ካልተሟላ የአድራሻ መረጃ የሚደርሱ መልዕክቶች ለጉምሩክ ፍተሻ
የማይተላለፉ ወይ የማይታደሉ በመሆኑ ወደ ላኪ አገር እንዲመለሱ
የሚደረግ መሆኑን አሳውቋል፡ ፡
የፖስታ መልዕክቶች ከዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩ ቁልፍ መረጃዎችን መያዝ
እንዳለባቸው አሳስቧል፡ ፡
- የተቀባይ ሙሉ ስም ፤ ወይም የተቋም ሙሉ ስም
- የተቀባይ ሙሉ አድራሻ
- የተቀባይ ደንበኛ የስል ቁጥር እና ኢ-ሜይል (ከተገኘ)
- የመልዕክቱን ይዘት እና ዋጋ
በመሆኑም ፖስታ አስተዳደሮች CN 22 እና CN 23 ፎርሞች የተሟላ
መረጃ መያዛቸውን እንዲያረጋግጡ እንዲያደርጉ አሳስቧል፡ ፡ ለበለጠ መረጃ
ዋናውን የእንግሊዝኛ ሰርኩላር ቁጥር 144 ይመልከቱ፡ ፡
ሰርኩላር ቁጥር 145
የዓለም አቀፉ ፖስታ ህብረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩ አገራት
በኢ.ኤም.ኤስ መልዕክት የማደያ ክፍያ ላይ ለውጥ ያደረጉ መሆኑን እና
ይህም መሻሻያ ከ1 January 2016 ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚሆን
ማሳወቃቸውን ገልፃ Dል፡ ፡
አውስትሪያ ፣ ባህሬይን፣ ኮስታ ሪካ፣ ዴንማርክ፣ ጂቡቲ፣ ፈረንሳይ፣
ጋና ፣ ብሪታኒያ፣ ሆንግ ኮንግ (ቻይና) እና ኢንዶኔዢያ ሲሆን ዝርዝር
መረጃው በዋናው የእንግሊዝኛ ሰርኩላር ቁጥር 145 ላይ ይገኛል፡ ፡
ሰርኩላር ቁጥር 146
የአፍጋኒስታን ፖስታ አስተዳደር በዓለም አቀፉ ፖስታ ህብረት አባል
አገራት ይዞታ ስር ሊገኙ የሚችሉ የፖስታ አስተዳደሩ ንብረት የሆኑ ባዶ
ሸራዎችን እንደሚልስሉት ጠይቋል፡ ፡
ሰርኩላር ቁጥር 148
የብሪታኒያ ፖስታ አስተዳደር (ሮያል ሜይል) ለዓለም አቀፉ ፖስታ
ህብረት አባል አገራት ሮያል ሜይልን ለማነ ጋገር ለሚፈልጉ ደንበኞች
ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ስልክ ቁጥሮች ያዘጋጀ መሆኑን አሳውቋል፡ ፡
ለማንኛውም ዓይነት ጥያቄዎች ፣ እርዳታ እና ምክር ስ.ቁ +44 1752
387112.
የአድራሻ ለውጥ ላደረጉ እና ሮያል ሜይል መልዕክቶቻቸውን
እንዲያስተላልፍላቸው ለሚፈልጉ ደንበኞች ስ.ቁ +44 1782 668007
በሮያል ሜይል ኦንላይን ኦፕ ላይ ስለሚገኙ ምርቶችን በተመለከተ መረጃ
ለማግኘት ስ.ቁ +44 131 316 7483.
የሮያል ሜይል ፖስታ አስተዳደር ከላይ የተገለፁት ቁጥሮች የሚያገግሉት
ለደብዳቤ መልዕክቶች ብቻ መሆኑን አሳስቧል፡ ፡
ሰርኩላር ቁጥር 151
የኢንዶኔዢያ ፖስታ አስተዳደር ለህብረቱ አባል አገራት የሚከተለውን
ጉዳይ ማሳወቅ ይፈልጋል፡ ፡ የመልዕክት እደላ እና የጉምሩክ ፍተሸ ስራን
ለማቀላጠፍ ላኪ ፖስታ አስተዳደር ደንበኞቻቸው ከዚህ በታች የተዘረዘሩ
አስፈላጊውን የአድራሻ መረጃዎችን በመልዕክቶች ላይ ማስፈራቸውን
እንዲያረጋግጡ አሳስቧል፡ ፡
- የተቀባይ ደንበኛ ሙሉ ስም እና የተሟላ አድራሻ ፤ ፖስታ ኮድን
ጨምሮ
- የተቀባይ ደንበኛ ቀጥታ እና ሞባይል ስልክ ቁጥር እንዲሁም የኢ-
ሜይል አድራሻ ከተገኘ
- የላኪ ደንበኛ ሙሉ ስም እና አድራሻ
ሰርኩላር ቁጥር 152
የፓፑዋ ኒው ጊኒ ፖስታ አስተዳደር በዓለም አቀፉ ፖስታ ህብረት አባል
አገራት ይዞታ ስር ሊገኙ የሚችሉ የፖስታ አስተዳደሩ ንብረት የሆኑ ባዶ
ሸራዎችን እንደሚልስሉት ጠይቋል፡ ፡
ሰርኩላር ቁጥር 154
የአውስትራሊያ ፖስታ አስተዳደር የመልዕክት ስራውን ለማሻሻል እና
የአነ ስተኛ ጥቅል መልዕክቶች እደላ ትክክለኛነትን ለማረጋገጥ የመልዕክት
ልውውጥ ቢሮዎችን በአዲስ መልክ ያደረጃ መሆኑን ለህብረቱ አባል አገራት
ያሳውቋ ል፡ ፡
ከ15 September 2015 ጀምሮ ላኪ ፖስታ አስተዳደሮች በተቻለ
አቅም E-format letter class mail (AO category)
ወይም አነ ስተኛ ጥቅል መልዕክቶችን ከዚህ በታች በተቀመጠው ሠንጠረዥ
በተገለፀው አድራሻ መሠረት እንዲልኩ አሳስቧል፡ ፡
መድረሻ የመልዕክት ልውውጥ ቢሮ ኮድ
የመልዕክት ምድብ የፖስት ኮድ ኮድ (ከ እስከ)
ክልል/ግዛት
ሲድኒ AUSYDA Air LC/AO 0200–0299 New South
Wales (NSW)
and Australian
Capital Territory
(ACT)
AUSYDD
S.A.L. LC/AO
1000–1999
2000–2999
5000-5999
South Australia
(SA)
4000-4999 Queensland
(QLD) 9000-9999
0800-0899 Northern
Territory (NT) 0900-0999
ሜልቦርን
AUMELA
Air and S.A.L.
LC/AO
3000-3999
Victoria (VIC) 8000-8999
7000-7999 Tasmania (TAS)
ፔርት/Perth AUPERA Air LC/AO
6000-6999 Western
Australia (WA) AUPERD S.A.L. LC/AO
ለበለጠ መረጃ ዋናውን የእንግሊዝኛ ሰርኩላር ቁጥር 154 ይመልከቱ፡ ፡
ሰርኩላር ቁጥር 155
የሞሪሺየስ ፖስታ አስተዳደር ትክክለኛ የCN 08 አቤቱታ እና
የመልዕክት መዘግየት ወይም መጥፋት የሚመለከቱ ጥያቄዎች አላላክ ሁኔታን
ለዓለም አቀፉ ፖስታ ህብረት አስተዳደር እንደሚከተለው ማሳወቅ
ይፈልጋል፡ ፡
ፖስታ አስተዳደሮች በሚከተለው መረጃ መሰረት መስራት ይኖርባቸዋል፡ ፡
1. ለደብዳቤ መልዕክት አቤቱታዎች - CN 08 ፎርም በሚከተለው
አድራሻ ኢ-ሜይል ይደረግ
2. የጥቅል መልዕክቶች አቤቱታ በIBIS መላክ ይኖርበታል
3. የኢ.ኤም.ኤስ አቤቱታ በሚከተለው ኢ-ሜይል አድራሻ መላክ
ይኖርበታል