ለ አእምሮ መጽሔት ቅጽ 1 ቁጥር 2 - LeAimero Vol 1 No 2

61

description

ለ አእምሮ መጽሔት ቅጽ 1 ቁጥር 1 ግንቦት 2005 - Le'Aimero-Vol.1 No.1 May 2013(1)

Transcript of ለ አእምሮ መጽሔት ቅጽ 1 ቁጥር 2 - LeAimero Vol 1 No 2

Page 1: ለ አእምሮ መጽሔት ቅጽ 1 ቁጥር 2 - LeAimero Vol 1 No 2

7/16/2019 1 2 - LeAimero Vol 1 No 2

http://slidepdf.com/reader/full/-1-2-leaimero-vol-1-no-2 1/61

Page 2: ለ አእምሮ መጽሔት ቅጽ 1 ቁጥር 2 - LeAimero Vol 1 No 2

7/16/2019 1 2 - LeAimero Vol 1 No 2

http://slidepdf.com/reader/full/-1-2-leaimero-vol-1-no-2 2/61

ለለለለ አእምሮአእምሮአእምሮአእምሮ – መጽሔትመጽሔትመጽሔትመጽሔት -አዲሱአዲሱአዲሱአዲሱ እትምእትምእትምእትም የግንቦትየግንቦትየግንቦትየግንቦት ወርወርወርወር

2005/ May 2013…ቅጽቅጽቅጽቅጽ 1፣፣፣፣ ቁጥርቁጥርቁጥርቁጥር 2

Posted on May 17, 2013

ለለለለ አእምሮአእምሮአእምሮአእምሮ – Le'Aimero © መንፈሳዊ ሐሳብ የአእምሮ ምግብ ነው !

ለ አእምሮ – Le'Aimero © | መንፈሳዊ ሐሳብ የአእምሮ ምግብ ነው !

ለ አእምሮ – Le'Aimero © | መንፈሳዊ ሐሳብ የአእምሮ ምግብ ነው !1

Page 3: ለ አእምሮ መጽሔት ቅጽ 1 ቁጥር 2 - LeAimero Vol 1 No 2

7/16/2019 1 2 - LeAimero Vol 1 No 2

http://slidepdf.com/reader/full/-1-2-leaimero-vol-1-no-2 3/61

አዳዳስ ጽሁፎ ና ሰነዶ■ ለ አእምሮ – መጽሔት -አዲሱ እትም የግንቦት ወር 2005/ May 2013…ቅጽ 1፣ ቁጥር 2

■ የትላንት ለዛሬው፤ የዛሬው ለትላንት ? እስከመቼ ?

■ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት የኢትዮጵያ ባህልና ሥልጣኔ አነሳሱና አመጣጡ- ክፍል ሁለት

■ የኢትዮጵያና ኤርትራ ሕብረት – የውይይት ሃሳብና ግንዛቤ

■ ተዋጊ ሮቦታ / Robot

■ በሥልጣን መባለግ! ለምሳሌ በቱርክ አገር

■ የባንክ ዘረፋ በ21ኛው ክፍለ-ዘመን!

■ “በኢንቨስትመንት ስም የሚፈጸም የመሬት ነጠቃ፤ በኢትዮጵያ” ጥናት

■ እኛም አለን ሙዚቀኛ፣ ልብን የሚያቃና / ዶክተር አሸናፊ ከበደ

■ ILLICIT FINANCIAL FLOWS FROM AFRICA

■ ለ አእምሮ የግንቦት ዕትም /05-2013-Vol-1-No-1

© ለ አእምሮ 2005 / © LE’AIMERO COPYRIGHT 2013

Posted in ሌሎችሌሎችሌሎችሌሎች / others, ማህበራዊናማህበራዊናማህበራዊናማህበራዊና ፖለቲካፖለቲካፖለቲካፖለቲካ /Social & political, ባህላዊናባህላዊናባህላዊናባህላዊና ማህበራዊማህበራዊማህበራዊማህበራዊ /Cultural & social,

Cover-pages-headlines | Tagged Cover-page-Headlines , Culture, Ethiopia | Leave a reply

የትላንትየትላንትየትላንትየትላንት ለዛሬው፤ለዛሬው፤ለዛሬው፤ለዛሬው፤ የዛሬውየዛሬውየዛሬውየዛሬው ለትላንትለትላንትለትላንትለትላንት ? እስከመቼእስከመቼእስከመቼእስከመቼ ?

Posted on May 16, 2013

ርዕሰርዕሰርዕሰርዕሰ አንቀጽአንቀጽአንቀጽአንቀጽ

የትላንትየትላንትየትላንትየትላንት ለዛሬው፤ለዛሬው፤ለዛሬው፤ለዛሬው፤ የዛሬውየዛሬውየዛሬውየዛሬው ለትላንትለትላንትለትላንትለትላንት ?

ጊዜ ይቀያየራል። የትላንትየትላንትየትላንትየትላንት ለዛሬው፤ለዛሬው፤ለዛሬው፤ለዛሬው፤ የዛሬውየዛሬውየዛሬውየዛሬው ለትላንትለትላንትለትላንትለትላንት፣ እኛ ጋ ብቻ

እስከመቼ ተደበላልቆ ይቆይ ይሆን? ዱሮ፣ በጠራራ ጸሓይ ፣ የባንክ ካዝና

በሽጉጥ አስፈራርተው የሚዘርፉ ወንበዴዎች እንኳን፣ አሁን ሌላ ዘመን

ውስጥ ስለገባን ፣ ከጊዜው ጋር ተራምደው፣ የዝርፊያ ስልታቸውን

ቀይረዋል።

በፈረስ የሚመጡት፣ ካው ቦዮች፣ መኪና ይዘዋል። አሁን ደግሞ

መኪናውንም ትተው፣ እዚህ መጽሔት ላይ እንደምታነቡት፣ በ21ኛው ክፍለ

ዘመን፣ በባንክ ኤሌክትሮኒክ ካርድ፣ በቀላሉ ገንዘቡን ፣ ግድግዳው ላይ

ከተለጠፈ የባንክ ካዝና፣ የፈለጉትን ያህል ብር ማስተፋት፣ ችለውበታል።

ዱሮ ዘማች ወታደሮችን አስታጥቀው፣ ድንበር አቋርጠው፣ በጦርነት፣

ለ አእምሮ – Le'Aimero © | መንፈሳዊ ሐሳብ የአእምሮ ምግብ ነው !

ለ አእምሮ – Le'Aimero © | መንፈሳዊ ሐሳብ የአእምሮ ምግብ ነው !2

Page 4: ለ አእምሮ መጽሔት ቅጽ 1 ቁጥር 2 - LeAimero Vol 1 No 2

7/16/2019 1 2 - LeAimero Vol 1 No 2

http://slidepdf.com/reader/full/-1-2-leaimero-vol-1-no-2 4/61

ሌላውን አገር መውረር የሚችሉ ኃያል መንግሥታት፣ አሁንም፣ ወረድ

ብላችሁ እንደምታነቡት፣ በታጠቀ ሮቦተር፣ ልጆቻቸው ሳይሞቱ፣ ሳይቆስሉ፣

ዘመናዊ ውጊያ ለማካሄድ ችሎታ እንዳላቸው አስመስክረዋል።

እንደዚሁ የ 18 ተኛው ሆነ የ19ኛው ክፍለ ዘመን አይዶኦሎጂም፣ እሱቀርቶ፣ የ20ኛው ክፍለ ዘመን ርዕዮተ ዓለምም እንደማይሰራ ብዙዎቹ

ተረድተው፣ የፖለቲካ መስመራቸውን በጊዜው ቀይረዋል።

እኛም በ21ኛው ክፍለ-ዘመን፣ እባካችሁን የአረጀ የፈጀውን ቲዎሪአችሁን

እዚያው የመጣበት፣ ጣሉና ለአገራችሁ ለኢትዮጵያ፣ በዚህ መጽሔታችን ፣

እንደገና ልብ ገዝታችሁ አስቡ እንላለን።

መልካም ንባብ

————————-

Name (required)

ለ አእምሮ / Le'Aimero

Email (required)

[email protected]

Website

http://laimero.com

Message

Submit »

© ለ አእምሮ 2005 / © Le’Aimero Copyright 2013

ለ አእምሮ – Le'Aimero © | መንፈሳዊ ሐሳብ የአእምሮ ምግብ ነው !

ለ አእምሮ – Le'Aimero © | መንፈሳዊ ሐሳብ የአእምሮ ምግብ ነው !3

Page 5: ለ አእምሮ መጽሔት ቅጽ 1 ቁጥር 2 - LeAimero Vol 1 No 2

7/16/2019 1 2 - LeAimero Vol 1 No 2

http://slidepdf.com/reader/full/-1-2-leaimero-vol-1-no-2 5/61

Posted in ማህበራዊናማህበራዊናማህበራዊናማህበራዊና ፖለቲካፖለቲካፖለቲካፖለቲካ /Social & political, ርዕስርዕስርዕስርዕስ አነቀጽአነቀጽአነቀጽአነቀጽ / Editorial, ሳይንስናሳይንስናሳይንስናሳይንስና ቴክኖሎጂቴክኖሎጂቴክኖሎጂቴክኖሎጂ/Science &

Technology, ታሪክናታሪክናታሪክናታሪክና ባህልባህልባህልባህል | Leave a reply

ኢትዮጵያናኢትዮጵያናኢትዮጵያናኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነትኢትዮጵያዊነትኢትዮጵያዊነትኢትዮጵያዊነት የኢትዮጵያየኢትዮጵያየኢትዮጵያየኢትዮጵያ ባህልናባህልናባህልናባህልና ሥልጣኔሥልጣኔሥልጣኔሥልጣኔ

አነሳሱናአነሳሱናአነሳሱናአነሳሱና አመጣጡአመጣጡአመጣጡአመጣጡ- ክፍልክፍልክፍልክፍል ሁለትሁለትሁለትሁለትPosted on May 16, 2013

ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት

የኢትዮጵያ ባህልና ሥልጣኔ አነሳሱና አመጣጡ

….. እኛ ማን ነን?

የኢትዮጵያ ባህልና ሥልጣኔ አነሳሱና አመጣጡ (PDF)

(ካለፈው የቀጠለ /ክፍል አንድ)

ክፍል ሁለት

በአዋጅ የክርስትና ሃይማኖት የአገሪቱ የኢትዮጵያ ዋና መመሪያ ሃይማኖት

ሁኖ ለአራት መቶ አመታት፣ በተከታታይ በአገለገለበት በክርስቲያኑ ንጉሥ፣

በአሸማ ዘመን፣ የመጀመሪያው የነብዩ መሐመድ ተከታዮች፣ነፍሳቸውን

ለማዳን ፣ በነብዩ ምክር ኢትዮጵያ ድረስ መጥተው፣ ስደትና ጠለላን፣እንክብካቤም ጭምር ጠይቀው ፣ የመጀመሩያውን የሞስሊሞች መንደር፣

ኢትዮጵያ ውስጥ ይቆረቁራሉ። ቁጥራቸው ትንሽ ነበር።

የመጀመሪያው የኢትዮጵያ፣ የክርስትና ሃይማኖት ተከታዮች ደግሞ፣

መንደራቸውን ኢትዮጵያ ውስጥ የዘረጉት፣ የቆረቆሩት ማለት እንችላለን፣

በመጀመሪያው ክፍለ ዘመን፣ ብዙም ሳይቆይ በቀጥታ ከክርስቶስ ልደት

በሁዋላ ነው።

ለ አእምሮ – Le'Aimero © | መንፈሳዊ ሐሳብ የአእምሮ ምግብ ነው !

ለ አእምሮ – Le'Aimero © | መንፈሳዊ ሐሳብ የአእምሮ ምግብ ነው !4

Page 6: ለ አእምሮ መጽሔት ቅጽ 1 ቁጥር 2 - LeAimero Vol 1 No 2

7/16/2019 1 2 - LeAimero Vol 1 No 2

http://slidepdf.com/reader/full/-1-2-leaimero-vol-1-no-2 6/61

የክርስትና ሃይማኖት፣ ወደ ኢትዮጵያ ዘልቆ የገባው በሁለት መንገድ ነው።

እምነቱን አምጥቶ ያስተዋወቀው፣ መጽሐፍ ቅዱስ ላይ እንደሰፈረውና

አሁንም ድረስ ማንበብ እንደሚቻለው፣ የንግሥቲቱ የእቴጌ ካንዳኬ የግምጃ 

ቤት ኃላፊ የነበረው፣ እየሩሳሌም ላይ በዲዯቆኑ በፊሊፖስ ከተጠመቀ ወዲህነው። ይህ ሰው፣ ሠረገላ ውስጥ ተቀምጦ፣ የነቢዩ ኢሳያስ መጽሐፉ ላይ

እንደሰፈረው፣ ትንቢት ሲያነብ፣ መልአኩ ወርዶ ፊሊፖስን እንዲያነጋግረው

ያዘዋል።…..እሱም ጃንደረባው የክርስቶስን ቃል ተቀብሎ እዚያው ተጠምቆ

ክሪስተያን ይሆናል። „…የአመነ የተጠመቀ፣ የእግዚአብሔርን ቃል

የተቀበለ“፣ ይህ እራሱ፣ እንደዚህ ዓይነቱ፣ እርምጃ ምን አይነት ሕብረትና

አንድነት፣ ከዚያም አልፎ መተሣሰርን በሰው ልጆች ዘንድ፣ በእነሱ መካከል

እንደሚያመጣ፣ መገመቱ ከባድ አይደለም ።

ይህ ሃይማኖት፣ ኢትዮጵያ ደርሶ፣ ከቤተ መንግሥት ወጥቶ፣ በየመንደሩ

ተስፋፍቶ፣ አገሪቱን ሁሉ አዳርሶ በመጨረሻው የሕዝቡ እና የንጉሠ

ነገሥቱ ፣ በሰላም የአገሪቱም፣ ልዩ መለያ ሃይማኖት ሁኖ የወጣው፣ በንጉሥ

ኢዛና ዘመን መንግሥት፣ በ330 ዓመተ ምህረት ላይ ነው። በዚህምየምዕራቡን ዓለም –ሌሎቹማ ትላንትና ነው ተጠምቀው ክርሰቲያን የሆኑት

– በተለይ የሮምን መንግሥት ቀድመን እኛ የክርስትና ሃይማኖት ተቀብለን፣

የዓለም የፖለቲካ መድረክ ላይ ብቻችንን ብቅ ብለናል።

ሮም የክርስትናን ሃይማኖት የተቀበለቸው፣ የሕዝቡዋም ሃይማኖት

ያደረገቺው፣ አርፍዳ፣ በ391 ዓመተ ምህረት ላይ ነው።

ይህ ሁኔታ ደግሞ፣ አውሮፓያኖች መጽሐፍ ቅዱስን ይዘው ሌሎቹን

የአፍሪካና የእሲያን ወንድሞቻችንን „አጥመቀው“፣…አታለው፣ አገራቸውን

ወረው ባሪያ ሲያደርጉ፣ እኛን ለመያዝ፣ የምናውቀውን የክርስቲያና

ትምህርት፣ መልሶ ለማስተማር፣ ፈጽሞ ሰሚ ጆሮ ኢጥዮጵያ ውስጥ አጡ።

እንዲያውም ፈልገው አላገኙም። ሰውም ሰብስበው ለመያዝ አልቻሉም።ጥርስ ግን፣ አንዳዶቹ ነክሰውብን፣ ኢትዮጵያን ለመያዝ በጦር ታጅበው

መጥተዋል።

ለ አእምሮ – Le'Aimero © | መንፈሳዊ ሐሳብ የአእምሮ ምግብ ነው !

ለ አእምሮ – Le'Aimero © | መንፈሳዊ ሐሳብ የአእምሮ ምግብ ነው !5

Page 7: ለ አእምሮ መጽሔት ቅጽ 1 ቁጥር 2 - LeAimero Vol 1 No 2

7/16/2019 1 2 - LeAimero Vol 1 No 2

http://slidepdf.com/reader/full/-1-2-leaimero-vol-1-no-2 7/61

ግን ኢትዮጵያ በመጀመሪያው ክፍለ ዘመን ከክርስትና ሃይማኖት ጋር

ተዋወቀች እንላለን እነጂ፣ እራሱ ክርስቶስ ከእናቱ ከቅድስት ማሪያምና

ከዮሴፍ ጋር ተሰዶ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ከርሞ ፣ እንደሄደም ቤተ-

ክርስቲያናችን፣ ኮርታ በደንብ፣ ታስተምራለች።

ይህን አሁን እናንሳ እንጂ፣ ኢትዮጵያ ከአንዱ ኃያል አምላክ ከእግዚአብሔር

ጋር የተዋወቀችው፣ አንድ ሺህ ከክርስቶስ ልደት በፊት ነው። እሱም

በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ እንደተጻፈውና ኢትዮጵያም ከተቆረቆረችበት፣

ከተመሰረተችበት አፈ-ታሪክ፣ እሱም ላይ በትክክል እንደሰፈረው፣

(አይዞአችሁ!… ሁሉም ሕዝብና ሁሉም መንግሥታት የእራሱ የሆነ አፈታሪክ አለው፣ …. ሮምን የቆረቆሩት ሁለቱ ወንድማማቾች፣ ሮሚዎስንና

ሮሙለስን፣ አንዲት ተኩላ ናት ይባላል ጡዋት ማታ ጡትዋን ሰጥታ

አጥብታ ያሰደገቻቸው፤ ይህንንም ጣለያኖች ኮርተው ይተርካሉ፣…

የሌሎቹንም የአመጣጥ ታሪክ ጊዜ ከአላችሁ፣ አገላብጣችሁ ተመልከቱ…)

በንግሥት ሳባ ዘመን፣ በንጉሥ ሰለሞን ጊዜ ነው።

በዕውቀቱ ተደንቃ ይላል መጽሐፉ፣ በጥበቡ ችሎታ ተገርማ ይላል፣ ይኸው

ማንም የማይደርስበት የኢትዮጵያ ሚቶሎጂ፣ በሥነስርዓቱ የሰፈረበት „

ክብረ ነገሥት“ የሚባለው፣ መጽሐፋችን፣ ያቺ ወጣት ንግሥት፣ ብድግ ብላ

ወደ እየሩሳሌም ወረደች ይለናል።።

ንግሥት ሳባ ወደ ኢየሩሳሌም ወርዳ እዚያ ሰንብታ ስትመለስ፣ ዕውቀት ና

ጥበብ ብቻ ሳይሆን ወንድ ልጅም ጸንሳ ትመለሳለች። ስሙንም ምንልክ

ቀዳማዊ ትለዋለች። ምንልክ አድጎ አባቱን ሰለሞንን ለማየት፣ በሃያ አመቱ

ወደ ኢየሩሳሌም ይወርዳል። ከዚያ ይዞልን የመጣው — ይህ ነው ወሳኙ

ቦታ–ኢትዮጵያ አገራችንን ከሌሎች ሕዝቦች ታሪክ ሁሉ፣ እንደገና ፍጽም

ልዩ የሚያደርጋት፣ አድርጎአትም እስከ አሁን ጊዜ ድረስ ያቆያትን ( ይህን

ከአውቀንበት ደግሞ፣ እንደ ዓይን ብሌናችን ከጠበቅነው፣ እስከ ዘለዓለሙም

ለ አእምሮ – Le'Aimero © | መንፈሳዊ ሐሳብ የአእምሮ ምግብ ነው !

ለ አእምሮ – Le'Aimero © | መንፈሳዊ ሐሳብ የአእምሮ ምግብ ነው !6

Page 8: ለ አእምሮ መጽሔት ቅጽ 1 ቁጥር 2 - LeAimero Vol 1 No 2

7/16/2019 1 2 - LeAimero Vol 1 No 2

http://slidepdf.com/reader/full/-1-2-leaimero-vol-1-no-2 8/61

ድረስ፣ ልዩ አድርጎ የሚያቆያትን) የትም የማይገኝ ምርጥ ሐብት፣ ይህ ወጣት

ምንሊክ ከኢየሩሳሌም ይዞልን ተመልሶአል።

ዛሬ ዋናው ታቦቱ፣ ምንልክ ያኔ ይዞት የመጣው የሙሴ ጽላቱ፣ አክሱም

ጽዮን ተቀምጦ ከ50 ሺህ የሚበልጡ የተባረኩ ቅጂ ታቦቶች፣ ደግሞ

በኢትዮጵያ ምድር፣… በኤርትራም በሁሉም ቦታ በአገራችንን ሜዳና

ሸንተረር (ዕብዶች እየተሳለቁ የሚሉትን ጨርሶ አትስሙ) ተተክለው፣

ተበትነው ይገኛሉ። እንደሸረሪት ድር፣ እንደ አጥር እንደ ማግና ድር፣ አንድ

ላይ ሰብስቦ እኛን ያኖረን።

ኢትዮጵያ ብቻ ናት በንግሥት ሳባና በቀዳማዊ ምንልክ ጊዜ አገራችን ከገባው

ከአይሁድ ሃይማኖት በቀጥታ፣ መጽሐፉ ላይ እንደሰፈረው፣ ወደ ክርስትና

ሃይማኖት የተሸጋገረቺው።

ከአራት መቶ የክርስትና ሃይማኖት ዘመን በሁዋላ ነው፣ እንግዲህ፣ ነቢዩ

መሐመድ „እኔ እስከምጠራችሁ ድረስ ወደ ኢትዮጵያው ርህሩህ ንጉሥ ሂዱ፣

እሱ እናንተን ተቀብሎ እምነታችሁና አስተሳሰባችሁ ሳይረብሸው፣

ያስተናግዳችሁዋል፣ ይጠብቃችሁዋልም፣“ ብሎ ወደ ኢትዮጵያ ያኔ

ሚስቱንና ልጁን፣ ከእነሱም ጋር ወጣት ተከታዮቹን የላካቸው።

ተቻችሎና ተከባብሮ ፣ ተደማምጦና ተነጋግሮ አብሮ መኖርን፣ ለየት፥ያለ

አመለካከትና ለየት፥ያለ እምነትን ማንም ሰው፣ እንደ መብቱ እንደፈለገው

መከተልና ማምለክን አንደሚችል፣ ከኢትዮጵያው ንጉስ … ከእሱ፣ስደተኞችን ተቀብሎ ከማስተናገድ እርምጃ፣እኛ ዛሬ መመልከት እንችላለን።

እንደዚህ ዓይነቱን አብሮ የመኖር ጥበብ ንጉሡ ከየት አመጣው? እንደዚህ

ዓይነቱን የአስተዳደር ብልሃትና ዘዴ ማን አስተማረው?

እንደዚህ ዓይነቱ የአስተዳደር ጥበብና ዕውቀት፣ የግድ ከውጭ መምጣት

የለበትም። የሚያስቡ የሰው ልጆች ከተንቀሰቃሽ ሕይወት ከዚያም፣

ለ አእምሮ – Le'Aimero © | መንፈሳዊ ሐሳብ የአእምሮ ምግብ ነው !

ለ አእምሮ – Le'Aimero © | መንፈሳዊ ሐሳብ የአእምሮ ምግብ ነው !7

Page 9: ለ አእምሮ መጽሔት ቅጽ 1 ቁጥር 2 - LeAimero Vol 1 No 2

7/16/2019 1 2 - LeAimero Vol 1 No 2

http://slidepdf.com/reader/full/-1-2-leaimero-vol-1-no-2 9/61

ከሚያገኙት ተመክሮና ልምምዶች እራሳቸው፣ በቂ ትምህርት ቤቶች፣ እነሱ፣

ስለሆኑ፣ ብዙ ዕውቀቶችን አባቶቻችን እንደሰበስቡ መገመት ይቻላል።

ግን በአባቶቻቸው ሥራ የማይተማመኑትን ጠርጣሪዎች ለማረጋጋት፣

ከሁለት ቦታ፣ ይህ ዕውቀት ከውጭም መጥቶአል ብሎም መናገር ይቻላል።

አንደኛው ፣ ጽላቱ ላይ ፣ እኛ ዝቅ ብለን የምንሰግድለት ታቦቱ ላይ፣

እንደተጻፈው፣ „ ….አትግደል፣ አትስረቅ፣…እናትና አባትህን

አክብር…“ይላል። ይህን ቃል፣ ይህን ሕግ፣ ሕግ- አክባሪዉ (የዛሬውን ካድሬድርጊት ለጊዜው እንርሳ) የኢትዮጵያ ሕዝብና ነገሥታት፣ ያከብራሉ፣

የፈጣሪያቸውም ትዕዛዝ ስለሆነ ይከተላሉ።። በማክበራቸውም፣ ለየት ያለ

ሐሳብና እምነት የሚከተለውን፣ እንግዳም ቢሆን ጥሩ አድርገው፣

ያስተናግዳሉ።

ሁለተኛው ፣ አማኙ የኢትዮጵያ ሕዝብና የኢትዮጵያ ነገሥታቶች፣

ተቀብለውት የሚተዳደሩበት፣ እንደ መመሪያቸውም አድርገውም ለረጅም

አመታት የሚመሩበት ነገር አለ። እሱም፣ ረፈድ ያለው፣ የጥንታዊው

ቤተክርሰቲያን አስተማሪ ፣ አጉስቲኖስ ስለ መልካም አስተዳደር ከማስተማሩ

በፊትና ፣ ይህን የሚቀጥለውን ቃል ከመናገሩ በፊትም ፣ የአስተዳደር ሰዎች

በኢትዮጵያ የተቀበሉትም ትምህርት አለ። አሱም፣ በአጭሩ ንጉሥ ሰለሞን

የአባቱን ዙፋን ወርሶ ቅባ ቅዱሱን ከመቀባቱ በፊት እግዚአብሔርን ለምኖት፣ያገኘውም፣ እንደተጻፈው፣ ጸጋ ነው።

የአጉስቲኖስ ቃልና ትምህርትን እናስቀድመው። „….የአንድ ሕዝብና

መንግሥት፣ የሁሉም መተዳደሪያ ደንብ የሆነውን ሕግ፣ አንድ ሰው፣ ወይም

አንድ ቡድን ያንን ሕገ-መንግሥት ሸሮ፣ የእራሱን፣ ለእራሱ ብቻ የቀደደውን

ሕግ ተክሎ፣ የነበረውን ሥርዓቱን እንዳለ አጥፍቶ፣ የእራሱን አዲስ ሕገ ወጥ

ለ አእምሮ – Le'Aimero © | መንፈሳዊ ሐሳብ የአእምሮ ምግብ ነው !

ለ አእምሮ – Le'Aimero © | መንፈሳዊ ሐሳብ የአእምሮ ምግብ ነው !8

Page 10: ለ አእምሮ መጽሔት ቅጽ 1 ቁጥር 2 - LeAimero Vol 1 No 2

7/16/2019 1 2 - LeAimero Vol 1 No 2

http://slidepdf.com/reader/full/-1-2-leaimero-vol-1-no-2 10/61

አዋጅ በአገሪቱ ላይ ከአወጀ፣ ይህ መንግሥት፣ ከዘራፊ ሽፍቶች፣ ሥርዓት

ከሌላቸው ወረበሌች፣ ከጨረባ ተዝካር ምንም የምለየው ነገር የለም…“

ያለው አነጋገር ፣ አገራችን ኢትዮጵያም፣ እንደዚህ ዓይነቱ፣ አስተሳሰብ ሰርጎ

እንደገባም መገመት ይቻላል። እንዴት?

አንደኛው መንገድ በግሪክ አስተማሪዎች- ቀደም ተብሎ እንደተጠቀሰው-

ወደ ኢትዮጵያ መግባትና እና ግሪክ አገር ወርደው፣ ፍልስፍና ታሪክ፣

ሒሳብና የሕንጻ ሥራ፣… በተማሩ ተምረውም በተመለሱ፣ ኢትዮጵያኖች

በኩል ነው።

ሁለተኛው ከአይሁድ ሃይማኖት ትምህርት ጋር ወደ አገራችን የገባው የዳዊት

መዝሙር፣ የነብያት ጽሑፍ፣ ኦሪት ዘፍጥረት፣ እንበለው፣ እነዚህ ሁሉ ቀላል

ነገሮች አይደሉም። መልካም ሥነ-ምግባር፣ ኤቲክና ቀና አመለካከት

የሚመነጩት አፍልስፍና ትምህርት ብቻ ሳይሆን፣ ከሃይማኖት ትምህርትም

ነው።

ንጉስ ሰለሞን፣ የቀዳመዊ ምንልክ አባት፣ ቅባ ቅዱሱን ተቀብቶ ዘውዱን

ከመድፋቱ በፊት፣ መጽሐፈ ነገሥት ቀዳማዊ ምዕራፍ ፫ ላይ እንደምናነበው

–ይህ የሚከተለው አረፍተ ነገር ቀላል አይደለም– እግዚአብሔር በሕልሙ

ተገልጦለት“…ምን ዓይነት ነገር መርቄ እነድሰጥህ ትገልጋለህ?“ ሲለው

ወጣቱ ሰለሞን ከፈጣሪው ከአምላኩ የተመኘው፣

ትምህርት፣ ትልቅ ትምህርት፣ ፖለቲከኛ ለመሆን ለሚፈልግ አንድ ሰው ፣

ወይም ደግሞ ነኝ ብሎ ለቆመ ሰው፣ ግሩም ትምህርት የሚሰጥ ስለሆነ፣

እንዳለ መልሼ እዚህ ላይ አነሳለሁ። እጠቅሳለሁ።

ሰለሞን፣… ሐብትን፣ ዝናን፣ ረጅም እድሜን፣ ጠላቶቹን የሚያጠፋበት

ጠንካራ ክንድና ጠንካራ ጦር እግዚአብሔር፣ እንዲሰጠው አልተመኘም።

ይልቅስ: የጠየቀው ይህን ነው። እንደዚህ አለው:-

ለ አእምሮ – Le'Aimero © | መንፈሳዊ ሐሳብ የአእምሮ ምግብ ነው !

ለ አእምሮ – Le'Aimero © | መንፈሳዊ ሐሳብ የአእምሮ ምግብ ነው !9

Page 11: ለ አእምሮ መጽሔት ቅጽ 1 ቁጥር 2 - LeAimero Vol 1 No 2

7/16/2019 1 2 - LeAimero Vol 1 No 2

http://slidepdf.com/reader/full/-1-2-leaimero-vol-1-no-2 11/61

„….አቤቱ አምላኬ ሆይ ፣ እኔን ባሪያህን በአባቴ በዳዊት ፋንታ

አንግሠኽኛል። እኔም መውጫዬንና መግብያን የማላውቅ ታናሽ ብላቴና ነኝ።

ባሪያህም ያለው አንተ በመረጥኸው ሕዝብህ፣ ስለ ብዛቱም ይቆጠር ዘንድ

በማይቻል በታላቅ ሕዝብ መካከል ነው። ስለዚህም ሰምቶ በሕዝብህ ላይመፍረድ ይችል ዘንድ መልካሙንና ክፉውንም ይለይ ዘንድ ለባሪያህ

አስተዋይ ልቡና ስጠው። አለዚያማ በዚህ በታላቅ ሕዝብ ላይ ይፈርድ ዘንድ

ማን ይችላል?“

መጽሐፉ በዚህ ጥሩ ምሳሌ ኃላፊነት ተቀብለው አንድን ሕዝብ፣ አንድን የቆየ

ጥንታዊ አገር ለመምራት ለሚፈልጉ ፖለቲከኞች ለማስተማር የፈለገው፣የአንድ ፖለቲከኛ ፣ ዋና ዓላማ በሥልጣን ባልጎ የግል ሐብትን ማካባት፣

ዝናና እን ሹመትን ማዳበር፣ ተንኮልና ጥላአቻን በሰው ልጆች ዘንድ

መዝራትን ….ሳይሆን፣ ክፉና ደግን ለይቶ፣ ሕዝብና አገር አደጋ ላይ

እንዳይወድቅ፣ ፍትህንና ፍርድን አምጥቶ፣ ሰላምን ማስፈንና ማሽጸዳደር

እንደሆነ፣ እላይ ከጸጸረከ ታሪክ እንመለከታለን።

አንድ ሺህ አመት ከንጉሥ ሰለሞን ዘመን በሁዋላ ደግሞ፣ ወደ አገራችን

የመጣው የክርስትና ሃይማኖት ደግሞ፣ ስለ ፍቅር፣ ስለወንድማማችነት፣

ስለአንድነት፣ ስለሰላም፣ ስለ ነጻ ሰውና ስለነጻነት፣ እነዚህ ሁሉ ምን

እነደሆኑ፣ በሰፊው ያስተምራል። ከዚያም አልፎ፣ ጠላትህን ሳይቀር ውደደው

ይላል። ከዚያም ትምህርት ኢትዮጵያ ብዙ ወስዳለች።

ሕግና ሥርዓት፣ ሰብአዊ መብት የማይከበርበት፣ ነጻነት የሌለበት፣ ሃይማኖት

የጠፋበት ቦታ፣ ምን ዓይነት አሰቃቂ ወንጄሎች በሰው ልጆች ላይ

እንደተፈጸሙ፣ እሩቅ መሄድ አያስፈልግም፤ የ20 ኛውን ክፍለ-ዘመን

ወንጀልን፣ መለስ ብሎ በተለያይ አገሮች መመልከት በቂ ነው።

በግሪክ ፍልስፍና፣ በአይሁድ ሃይማኖት፣ በክርስትና ትምህርት አገራችን

ኢትዮጵያ እነዘህን ሶስቱን፣ የተለያዩ ግን ደግሞ የተወራረሱ፣ አመለካከቶች

ጨፍልቃ በአእምሮ ደረጃ የእራሱዋ አድርጋ ትመራ ነበር። በሁዋላ

ለ አእምሮ – Le'Aimero © | መንፈሳዊ ሐሳብ የአእምሮ ምግብ ነው !

ለ አእምሮ – Le'Aimero © | መንፈሳዊ ሐሳብ የአእምሮ ምግብ ነው !10

Page 12: ለ አእምሮ መጽሔት ቅጽ 1 ቁጥር 2 - LeAimero Vol 1 No 2

7/16/2019 1 2 - LeAimero Vol 1 No 2

http://slidepdf.com/reader/full/-1-2-leaimero-vol-1-no-2 12/61

እንዳየነው የእስልምና ሃይማኖት ቀስ እያለ እየተስፋፋ ከአገሪቱ ሁኔታ ጋር

እራሱን ያስተዋውቃል።

ይህም ሃይማኖት ልክ እንደ ክርስትናውና እንደ አይሁዱ ሃይማኖት፣

ኢትዮጵያ ሲደርስ ከአርብ አገሮች የተለየ – ኢትዮጵያዊ መልክ ያለው

አካሄዱን ይዞአል። አለባበሳቸውን ማየት ይበቃል። አመጋገባቸውን፣ እራሱ

መጠጣቸውን፣ ከዚያም አልፎ ትዳራቸውን፣ ልጆች አሰተዳደጋቸውን…

እነዚህን ሁሉ ከግምት ውስጥ አስገብቶ ከአረቦቹ ጋር ማነጻጸር ያስፈልጋል።

ልክ በኢትዮጵያ ክርስቲያንና በአውሮፓ ወይም በአፍሪካ ክርስቲያኖች

መካከል ልዩነት እንዳለ ሁሉ፣ በአረብ አገር እስላሞችና በኢትዮጵያ

ሞስሊሞች መካከል ትልቅ ልዪነት በሁለቱ መካከል አለ። በነገራችን ላይ

በኢትዮጵያ አይሁዶችና በሌላው ዓለም በሚገኙ አይሁዶች መካከል

እንደዚሁ ትልቅ ልዩነት እናያለን። ከአንድ ምንጭ የተቀዱ፣ ከአንድ ቦታ

የፈለቁ ባህልና ሥልጣኔ፣ ሌላ አካባቢ ሲደርሱ፣ ከቦታ ቦታ ይለያያሉ፣

የሚባለውም ለዚህ ነው።

እነዚህ ሦስቱም አራቱም ሃይማኖቶችና እምነቶች (አራተኛው የግሪኮች

ፍልስፍና ነው፣ የፋርሱ፣ ዛራሁስተስ፣ ኢትዮጵያ ገብቶ ነበር የሚሉ

ጸሐፊዎች አሉ) ምንም እነኳን በክርስቲያን ሃይማኖት ሥር ተቻችለውና

ተከባብረው ጎን ለጎን ቢኖሩም፣ ሁለት ጊዜ በተለያዩ ዘመናት እነዚህሃይማኖቶች፣ እኔ እሻላለሁ፣ እኔ እበልጣለሁ ብለው ጦርነት ከፍተው፣

ተናንቀው ሕዝቡን አፋጅተዋል። ጥንታዊ ቅርሶችን አውድመዋል።

የእስልምና ሃይማኖት ኢትዮጵያ ገብቶ ቀስ እያለ ሰባት መቶ አመት ከተስፋፋ

በሁዋላ በመካከለኛው ክፍለ-ዘመን ኢማም አሕመድ ኢብራሂም፣ ግራኝ

መሐመድ ወይም አሕመድ ግራኝ ፣ በእሱ መሪነት በቱርኮች ድጋፍና መሣሪያ

ለ አእምሮ – Le'Aimero © | መንፈሳዊ ሐሳብ የአእምሮ ምግብ ነው !

ለ አእምሮ – Le'Aimero © | መንፈሳዊ ሐሳብ የአእምሮ ምግብ ነው !11

Page 13: ለ አእምሮ መጽሔት ቅጽ 1 ቁጥር 2 - LeAimero Vol 1 No 2

7/16/2019 1 2 - LeAimero Vol 1 No 2

http://slidepdf.com/reader/full/-1-2-leaimero-vol-1-no-2 13/61

ብርታት፣ በሠይፍና በእሳት አገሪቱን ወደ እስላም ሃይማኖት ቀይሮ „የሻሪያን

ሕግ በሱዳን በሱማሌና በኢትዮጵያ“ ይህ ሰው፣ ለመዘርጋት ተነስቶ ነበር።

ልክ የአይሁድ ሃይማኖትን በኢትዮጵያ መልሶ ለማቋቋም፣ በአሥረኛው ክፍለ

ዘመን አካባቢ ተነስታ፣ በደረሰችበት ቦታ ሁሉ ገዳሞችንና ቤተክርስተያንን ፣

መጽሐፍት ቤቶችንና ትላልቅ ቤተ መንግሥቶችን፣ ጥንታዊ ከተማዎችንንና

መንደሮችን፣ እሳት ለኩሳ እንዳቀጠለችው „ዮዲት ጉዲት“፣ ግራኝ፣ የነብዩ

መሐመድን ቃል ጥሶ፣ ድፍን ኢትዮጵያን እስላም ለማድረግ፣ በደረሰበት ቦታ

ሁሉ እሳት እየለቀቀ፣ እንደገና ፈልገን የማናገኛቸውን ታሪካዊ ቅርሶች፣

እነዚህ ሁለት ጦረኞች፣ እኩል አጥፍተዋል። እንኳን እነሱ የእነ መንግሥቱኃይለማሪያምም ካድሬዎች አዲስ አበባ ላይ መጽሐፍቶችን – አሁን

ከአልተረሳ አቃጥለዋል።

ግን ያ ሁሉ ሁኖ፣ ሁለቱም ሶስቱም ሃይማኖቶች፣ ከዚያ በሁዋላ፣ ለአለፉት

አምስት መቶ አመታት ተቻችለው አብረው ኖረዋል።

እስከአሁን ድረስ መለስ ብዬ የኢትዮጵያን ባህልና ሥልጣኔ ወሳኝ ሁነው

በአገሪቱ ላይ፣ እስከ 20ኛው ክፍለ – ዘመን አጋማሽ ድረስ፣ ኮሚኒዝም

የሚባለው ፍልስፍና እና ትምህርት፣ ይህን የወጣቱ ትውልድ ሃይማኖት

ልንለው እንችላልን፣ አገራንችን ገብቶ፣ ከመስፋፋቱ በፊት፣ ማህተማቸውንና

አሻራቸውን በኢትዮጵያ ጥለው የሄዱ(!) ምሶሶዎች

ብዬ የአነሳሁአቸው፣ አበይት ነገሮች፣ ሁለት ናቸው።

አንደኛው ፣ ለማስታውስ ከሶስት ሺህ አመት በላይ በተከታታይ የአንድነት

ምልክት ሁኖ የቆየው ዘውድና፤

ሁለተኛው፣ እንደዚሁ ከሶስት ሺህ አመት በላይ በኢትዮጵያ ሥር ሰዶ

ባህላችንን የወሰነው፣ የአንድ አሃዱ አምላክ፣ ሃይማኖት ነው። ይህ ሃይማኖት

የሞራል ኮዶችን፣የኤቲክ መስመሮችን፣ ጥሎልን ሄዶአል።

ለ አእምሮ – Le'Aimero © | መንፈሳዊ ሐሳብ የአእምሮ ምግብ ነው !

ለ አእምሮ – Le'Aimero © | መንፈሳዊ ሐሳብ የአእምሮ ምግብ ነው !12

Page 14: ለ አእምሮ መጽሔት ቅጽ 1 ቁጥር 2 - LeAimero Vol 1 No 2

7/16/2019 1 2 - LeAimero Vol 1 No 2

http://slidepdf.com/reader/full/-1-2-leaimero-vol-1-no-2 14/61

በዚህ አቀራረቤ ከአድማጮቼ ወይም ከአንባቢዎቼ ከመሰናበቴ በፊት፣

ሦሰተኛውን ፣ የኢትዮጵያ፣ ባህልና ሥልጣኔ እንደዚሁ ለረጅም ሺህ

አመታቶች ያጀበውን ተጨማሪ ምሶሶ እንዳይረሳ፣ እንደዚሁ አሁን አነሳለሁ።

እሱም፣ ለእናት አገራችን ለኢትዮጵያ ያለን፣ እስከ ሞት መስዋዕትንት

የሚያደርሰውን ፍቅር ነው። ይህም ፍቅር ተበጥሶ እንዳይጠፋ፣ በተከታዩም

እንዳይረሳ፣ በሥነ – ሥርዓቱ እንድ ልጅ ሲወለድ፣ በተወለደ በአርባ ቀኑ

የሚወሰደውን፣ እርምጃ ነው።

ከወላጅ እናቱ ጋር የሚያስተሳስረውን እትብታቡን፣ ከተወለደ በሁዋላከእናት አገሩ መሬት ጋር መተሳሰሩን የሚያረጋግጠው፣ ቃል-ኪዳን ነው።

ይህም፣ በመጨረሻ እትብታቡ የተቀበረበት ቦታ ሰውዬው/ሴትዮዋ መቀበር

አለበት የሚለው ውሳኔ ነው። የልጅ እትብታብ፣ የተወለደበት ቦታ

ይቀበራል። ለምን?

ያ ማለት፣ እትብታብህ የተቀበረበት፣….አገርህን ፣ ድንበርህን፣ ግቢህን፣

መሬትህን፣ ዘመድና ቤተሰብህን፣ ደብርና ገዳምህን፣ ቅዱስ የጸሎት

ቤትህንም፣ እርሻህንና ከብትህን፣ ዱርና ገደሉን ጫካውንና ሜዳውን፣ ባሪያ

አድርጎ ሊሸጥ ከሚመጣ ጠላት ፣ በጦርና በጋሻህ፣ በክንድህና በጭንቅላትህ፣

በደምህ ፣ በሕይወት እስከ አለህ ድረስ፣ ጠብቀው ማለት ነው።

እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ በውጭ አገር በስደት ሆነ በሥራ፣ ትዳር መሥርተው

ልጆች ወልደው የሚኖሩ ቤተሰቦች፣ የልጆቻቸውን እትብታብ፣ ኢትዮጵያ

ድረስ አምጥተው እንደ አባቶቻቸው ይቀብሩ እንደነበር አውቃለሁ። አሁን

ማነው የሚጨነቅላት?

ሦስተኛው አገሪቱን አንድ አድርጎ የያዘው ምሶሶ „…መገንጠል፣

ከኢትዮጵያ፣ ግዛትና መንግሥት መገንጠል …“ የሚባለው ፈለጥ ሳይስፋፋ፣

ከዚያ በፊት፣ „ የአገር-ፍቅር“ የሚባለው፣ ትምህርት ደማችን ውስጥ ገብቶ

ለ አእምሮ – Le'Aimero © | መንፈሳዊ ሐሳብ የአእምሮ ምግብ ነው !

ለ አእምሮ – Le'Aimero © | መንፈሳዊ ሐሳብ የአእምሮ ምግብ ነው !13

Page 15: ለ አእምሮ መጽሔት ቅጽ 1 ቁጥር 2 - LeAimero Vol 1 No 2

7/16/2019 1 2 - LeAimero Vol 1 No 2

http://slidepdf.com/reader/full/-1-2-leaimero-vol-1-no-2 15/61

ነበር። ዛሬ ግን በብዙዎቹ፣ ዘንድ ይህ ነገር መቀለጃ ሁኖአል። ለምን? ምን

ሆነን?… ምንስ ነክቶን?

ወረድ ብዬ እግረ መንገዴን፣ እናንትን ሳላሰለች የማነሳላችሁ ሌሎቹ ሁለቱ

ነጥቦች ደግሞ፣ በኢትዮጵያ መንፈስና በኢትዮጵያ ነፍስ፣ በአእምሮ

ጥንካሬአችን ላይ ወሳኝ ቦታ ይዘው እዚህ በአደረሱን ጉዳዮች ላይ ነው።

ለመሆኑ ምንድናቸው እነሱ?

አንደኛው ፣ ማንም ኢትዮጵያዊ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ኮርቶ፣- አሁን እሱም

እንደ ሌሎቹ ጉዳዮች ተረስቶአል- ፣ እራሱን በእራሱ ዓይን የሚያይበት፣

መነጽር ፣… ወይም መስተዋት ነው።

ፈጣሪ አምላክ እኛ ልጆቹን (ነብዩ ኢሳያስ እንዳለው) የእሱ ምርጥ ልጆች

አደርጎ መርጦ መውሰዱ ሲሆን፣ ከዚሁ ጋር አከታትዬ ማንሳት የምፈልገው፣

ወይም ለጊዜው የመጨረሻው እኛን ኢትዮጵያኖችን፣ አንድ አድርጎ ሰብሰቦ

እንደ ችቦ የያዘው፣ ሁለተኛው ነጥብ ደግሞ፣ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ –

እሱም ተረስቶአል መሰለኝ- „ እኔ ጥቁር ነኝ፣ ነገር ግን ውብ ነኝ…“

የሚለው፣ ትልቅ ዓረፍተ ነገር ነው። በኋላም ጥቁር አሜሪካኖችም ዘረኝነት

ላይ ትግል በ60 ዎቹ ዘመን ሲያውጁ፣ ይህን ተቀብለው „I am black &

Proud“ ይሉ እንደነበር አስታውሳለሁ!

ይህ ዓረፍተ ነገር፣ እንደዚህ ዓይነቱ አመለካከት፣ ለኢትዮጵያና

ለኢትዮጵያኖች ይህ ነው የማይባል አንዳች መንፈስ ሰጥቶ እስከ ዛሬ ድረስአቆይቶናል።

ልጅ ሁኜ የተማርኩትን እንደገና ላንሳው:-

„….እኔ ጥቁር ነኝ፣ ነገር ግን ውብ ነኝ…“ ይላል።

„እንደ ቄዳር ድንኳኖች እንደ ሰሎሞንም መጋረጃዎች።

…እኔ የዱር ጽጌረዳ ፣ የቄለም የሱፍ አበባ ነኝ…“ቀጥሎ ይላል።

ለ አእምሮ – Le'Aimero © | መንፈሳዊ ሐሳብ የአእምሮ ምግብ ነው !

ለ አእምሮ – Le'Aimero © | መንፈሳዊ ሐሳብ የአእምሮ ምግብ ነው !14

Page 16: ለ አእምሮ መጽሔት ቅጽ 1 ቁጥር 2 - LeAimero Vol 1 No 2

7/16/2019 1 2 - LeAimero Vol 1 No 2

http://slidepdf.com/reader/full/-1-2-leaimero-vol-1-no-2 16/61

„በእሾህ መካከል እንዳለ የሱፍ አበባ…“ ብሎም ይዘልቃል።

(መሓልየ መሓልይ ዘሰሎሞን ተመልከት)

እዚይው ላይ ቀደም ሲል „….እናንተ የእየሩሳሌም ቆነጃጂት ሆይ፣“ – ብሎይጀምራል።

በመካከሉም „…ጸሓይ መልኬን አክስሎታልና ጥቁር ስለሆንኩ አትዩኝ…“

ብሎም ይጠይቃል።

በቀጥታ ደግሞ፣ ለመድገም፣ ተመልሶ „…እኔ ጥቁር ነኝ ነገር ግን ውብ ነኝ፣

… የዱር ጽጌረዳ የቄለም የሱፍ አበባ ….

በእሾህ መካከል እንዳለ የሱፍ አበባ…“ እያለ ኮርቶ ይጣራል።

ይህ አባት ለልጁ የጻፈለት ይሆን? ወይስ ልጅ ከአባቱ ጥበብ ሰብስቦ

ለኢትዮጵያ የተናገረው፣ቃል?

እንግዲህ ይህ ከሦሰት ሺህ አመት በላይ የኢትዮጵያኖችን ፣ አመለካከት እስከ

ቅርብ ጊዜ ድረስ ማንንም ሳይፈሩ፣ ጠብቆ ያቆየውና የጠረበው፣ እምነትና

ትምህርት፣ ይህቺን አገር ከሌሎቹ አገሮችና መንግሥታት በታች እራሳቸውን

ዝቅ አድርገው እንዲያዩ፣ ምን ጊዜም አላደረጋቸውም። እንዲያውም፣

ጠንካራ የመንፈስ ብርታት ሰጥቶአቸው፣ እስከ 20ኛው ክፍለ-ዘመን

መጨረሻ ድረስ አቆይቶአቸዋል።

አሁንስ፣ ወዳጆቼ እንዴት አድርጋችሁ ነው እረሳችሁን የምታዩት? ….እስቲ

እራሳችሁን ጠይቁ ? መልሱ ደግሞ በእጃችሁ ነው።

ሳላንዛዛው ሐሳቤን ዛሬ በአንድ ግንዛቤ ሸብ ላድርገው።

ለ አእምሮ – Le'Aimero © | መንፈሳዊ ሐሳብ የአእምሮ ምግብ ነው !

ለ አእምሮ – Le'Aimero © | መንፈሳዊ ሐሳብ የአእምሮ ምግብ ነው !15

Page 17: ለ አእምሮ መጽሔት ቅጽ 1 ቁጥር 2 - LeAimero Vol 1 No 2

7/16/2019 1 2 - LeAimero Vol 1 No 2

http://slidepdf.com/reader/full/-1-2-leaimero-vol-1-no-2 17/61

ብዙ መንገዶች በታሪካችን ፣ሌሎቹ ሲወድቁና ሲነሱ፣ እኛ ኢትዮጵያኖች፣

ብቻችንን ተጉዘናል። አንድ ትልቅ ቁም ነገር ላይ፣ ግን ሳንደርስ የጀመርነውን

መልካም መንገድ እራሳችን ባልሆነ ትምህርትና ፍልስፍና ሳናውቅበት

ቀጭተነው፣ ይኸው ዛሬ ተበታትነን፣ የአውሬ፣… የተኩላ፣… የጅቦች ራትለመሆን በጨለማ ዓለም ውስጥ፣ መውጫና መግብያው በማይታወቀው

ጫካ ውስጥ፣ ሁላችንም ወድቀን ፣ ተዘርተን፣ እንገኛለን።

ለአገራችን ነጻነት፣…. የባዕድ ሰው ጥገኛ አሽከር፣ ….ባርነትን፣ ጨርሶ

የማንወድ፣ኢትዮጵያኖች፣ አገር አቋርጠው ሊይዙን የመጡትን ጠላቶች ሁሉ

የፈለገውን ያህል መስዋዕትንተ ከፍለን፣ የአገራችንን ፣ የባነዲራችንን ነጻነት

ጠብቀን እስከ ዛሬ ድረስ (ይህ የእኛ ሳይሆን የአባቶቻችን ሥራ ነው)

ቆይተናል።

ግን የዚያኑ ያህል፣ እኛ የዛሬው ትውልድ (አባቶቻችንን ብቻ መክሰስ

እንወዳለን፣ እንጂ ) ከጨለማ ወደ ብርሃን፣ „ከባርነት“ ወደ ሙሉ ነጻነት፣

ሰበአዊ ክብሩና መብቱ የማንም ሰው፣ ትልቅ ይሁን ትንሽ፣ በማንም

( ኮሚኒስት ይሁን ነጻ- አውጪ፣ ሽፍታ ይሁን፣ ተገንጣይ፣ ዲሞክራት ይሁን

ሶሻሊስት፣ ወታደር ይሁን፣…ቄስ ወይም ኢማም….) እንዳይረገጥ፣

እንዳይደፈር፣ የፈለግነውን ፣ ማድረግና መተው፣….መጻፍና መናገር፣

መመራመርና መጠየቅ…መተቸትና መቃወም፣ በሕግ ለተረጋገጠብት

የፓርላማ ሥርዓት፣ እጅ ለእጅ ተያይዘን ፣ ብድግ ብለን ተነስተን

አለመታገላችን፣ የሚያሳዝን ስለሆነ መጠቀስ ያለበት፣ ይቅርታ አድርጉልኝ፣ጉዳይ ነው። ይህም ስለሆነ፣ ይህቺን ነገር አነሳለሁ።

የእያነዳንዱ ኢትዮጵያዊ ዜጋ ሙሉ ነጻነት ጉዳይ፣ ደግሞ፣ በቀጠሮ ገና

ሃምሳና መቶ አመት የሚሰጠው፣ የአራዳ፥ልጆች ጨዋታ አይደለም። ይህ

መብት፣ ከእግዚአብሔር የተሰጠ ነው። ከፍጡሮች ሁሉ፣ ከእንስሶችና

ከአራዊቶች ሁሉ፣ ለእኛ በአምሳሉ የሰጠን መብት፣በምላሳችን

እነድንናገርበት፣ በአእምሮአችን እንድናስብበት፣ በእጃችንን እንድነጽፍበት

ለ አእምሮ – Le'Aimero © | መንፈሳዊ ሐሳብ የአእምሮ ምግብ ነው !

ለ አእምሮ – Le'Aimero © | መንፈሳዊ ሐሳብ የአእምሮ ምግብ ነው !16

Page 18: ለ አእምሮ መጽሔት ቅጽ 1 ቁጥር 2 - LeAimero Vol 1 No 2

7/16/2019 1 2 - LeAimero Vol 1 No 2

http://slidepdf.com/reader/full/-1-2-leaimero-vol-1-no-2 18/61

ነው።…. መናገር መጻፍ፣ ማመዛዘን፣ ክፉን ደጉን ለይቶ፣ መመልከት፣

ዱሮም የነበረ፣ አሁንም ያለ መብት ነው።

ይህን መብት ከጨበጥን፣ የኢትዮጵያ ባህልና ሥልጣኔና እንደሌሎቹ፣ ኃያላን

መንግሥታት፣ አድጎ አብቦ ደርቶ የማይታይበት ምንም ምክንየት የለም።

ቁም ነገሩ፣ ያለው፣ የነጻነት አዋጁን፣ ሁሉም ሰው በአለበትና በቆመበት ቦታ፣

በቤቱም፣ በደጁም በየሜዳው ማወጅ ላይ ነው።

ለምንድነው አሁን እንደዚህ ዓይነቱን አስተሳሰብ ወደ መ ጨ ረሻው ላይ

ያነሳሁት?

አሁን፣ ጌጥ ስለሆ ነና አላፊው አግዳሚ ው በየአለበት ስለሚ ያነሳው

አይደለም ።አይም ሰላችሁ።

ስንት ሰው „ዲሞ ክራሲ እኔ ሥ ልጣ ኑ ላይ ብ ወ ጣ አመ ጣ ላችሁ ዋለሁ!“

ብሎ እንደቀለደብን ሁላችንም እናውቃለን። ስንት ሰው በነጻነት ስም አሳቦ

ሥልጣኑ ላይ ጉብ ብሎ እነደቀለደብንና እንዳሾፈብን ሚሥጢር አይደለም።

ያልዋሹንም ሰዎችና ድርጅቶች አሉ። በጊዜው „ የላብ አደሩን እና የገበሬውን

ወይም የወዝአደሩን ….አምባ ገነን መንግሥት እናመጣላችሁዋለን „ ብለው፣

በአወጡት ፕሮግራማቸው ላይ፣ በይፋ፣ እነሱ ነግረውናል። ግን እኛ፣ ስንት

ሰው እነደሆን ባላውቅም፣ ሞኝ ሁነን፣ ሳይገባን ይህን ሐሳባቸውን

ተቀብለናል።

እንግዲህ ኢትዮጵያን ለማ ዳን እንደዚህ ዓይነቱን ቀልድ ቆሞ ወደ ቁም

ነገሩ፣ እላይ ወደ አልኩት ወደ ነጻ ዜጋ መ ብ ት ጉዳይ መ መ ለስ ሁላችንም

ይኖርብ ናል። ደግሞ ም አለብ ን።

የሚ ቀጥለው ጽሑ ፌ በም ሁርና በፖ ለቲካ፣ ትርጉም ላይ ያተኩ ራል።

ሰለ ትሩፋት፣… ሰለ ምግባረ ሰናይ ፣ ….ስለ መልካም ሥራ፣ …ስለ

ተግሣጽና ምክር ፣ ስለ የኢትዮጵያ የትምህርት አሰሳጥ፣…ስለ ሥልጣን

ለ አእምሮ – Le'Aimero © | መንፈሳዊ ሐሳብ የአእምሮ ምግብ ነው !

ለ አእምሮ – Le'Aimero © | መንፈሳዊ ሐሳብ የአእምሮ ምግብ ነው !17

Page 19: ለ አእምሮ መጽሔት ቅጽ 1 ቁጥር 2 - LeAimero Vol 1 No 2

7/16/2019 1 2 - LeAimero Vol 1 No 2

http://slidepdf.com/reader/full/-1-2-leaimero-vol-1-no-2 19/61

ተዋረድ፣ወይም …ስለ ኤቲክና ሞራል፣ ወይም፣… ሰለ ኢትዮጵያ እሴቶች ፣

…. ስለነዚህ ሁሉ፣ አላነሳሁም።

አልፌም ሄጄ፣ ስለ የሰው ልጆች ባህሪ ( ኮንዲስዮ ፣ ሁማና ) በሰፊው፣

ለመናገር፣ እኔ አልሞከረኩም።

ምንም የሚያጣድፈን ነገር የለም። ተመልሰን፣ ተራ በተራ፣ እንመጣበታለን።

ግን አንድ አስምሬበት ለማለፍ የምፈልገው ነገር ቢኖር፣ ውድ አገራችን

ኢትዮጵያ፣ ትላንት፣ እንደ እንግሊዝና አሜሪካ፣… ፈረንሣይና ጀርመን ፣…

ሩሲያና ጃፓን፣ የተፈጠረች አይደለችም።

አርግጥ እነሱ ግሩም ፖለቲካ ተከትለው፣ ምን የመሰለች አገር፣ ከእኛ በሁዋላ

መሥርተዋል። „ግሩም ፖለቲካ“!… አልኩ?… ምን ማለቴ ነው?

ለመሆኑ፣“…ግሩም ፖለቲካ“ የሚለውን ነገር ለጊዜው እንተውና በጅምላ

ለመሆኑ፣ „ፖለቲካ“… ምንድነው?ብለን እንጠይቅ።

ፖለቲካ!… ሰውን ማጋጭት፣ አገር ማናጋት፣ ቀዶ እና ሰነጣጥቆ እንደ ገና

መልሶ መስፋት? ….ወይስ ፖለቲካ ማለት …የመደብ ትግል ማወጅ፣

የነበረና የቆን ነገር ደምስሶ በአዲስ ( ከአለፈጣሪውና አድራጊው በስተቀር)

ማንም ሰው በማያውቀው መተካት? ለመሆኑ ፣ ከብሔርና ከመደብ ትግል

ሌላ ለየት ያለ ፖለቲካ በኢትዮጵያ አለ ወይ?

ከአለስ እሱ ምን ይባላል?

ዕውነትም፣ „ፖለቲካ“ የጀርመኑ ኦቶ ቮን ቢስማርክ እንደሚለው „ ቆሻሻ “

ነገር ነው? ወይስ ፖለቲካ „ዕጹብ ድንቅ ዕንቁ“ የሆነ ነገር ነው?

ፖለቲካ ! ሕዝብን አሰባስቦ ለዚያ ሕዝብና ለዚያች አገር ጥሩ ነገር መሥራት

ነው? ወይስ፣ የእራስን ጥቅም ብቻ አሳዶ የተቀረውን መርሣት?….

ፖለቲካ ፣ ለመሆኑ ምንድ ነው?

ለ አእምሮ – Le'Aimero © | መንፈሳዊ ሐሳብ የአእምሮ ምግብ ነው !

ለ አእምሮ – Le'Aimero © | መንፈሳዊ ሐሳብ የአእምሮ ምግብ ነው !18

Page 20: ለ አእምሮ መጽሔት ቅጽ 1 ቁጥር 2 - LeAimero Vol 1 No 2

7/16/2019 1 2 - LeAimero Vol 1 No 2

http://slidepdf.com/reader/full/-1-2-leaimero-vol-1-no-2 20/61

ማነው አሁን ፖለቲከኛ ከእኛ መካከል? ምን ዓይነት ፖለቲከኛ …ለመሆኑ፣

ፖለቲከኞች ከየት መጡ?…እነሱ ማን ናቸው ? የፖለቲከኛ መመዘኛ ሚዛኑ

ምንድነው? ፖለቲከኞች ለጠብና ለነገር ነው ፣ የተፈጠሩት? ወይስ ጥሩ

አማራጭ መንገድ ለአገሩቱም ለሕዝቡም ለማቅረብ? ለመሆኑ ፖለቲከኛ ያስፈልጋልናል ወይ?…. ምን ያህል ዘመን በሥልጣን ላይ መቆየት

አለባቸው? ዕድሜ ልካቸውን? ወይስ አራት አመት?… እንክርዳዱን

ከስንዴ እንዴት መለየት ይቻላል?

ስለፖለቲከኞች እና ስለ ምሁሮች ፣ በአጠቃላይ ረብሻ ስለአነሱ ረብሻ፣

ከእናካቴው ስለ ማንም ሳይጠይቃቸውና ሳይለምናቸው ፣„ልምራ

“ስለሚሉት „ፍጡሮች“ የሚቀጥለው ጽሑፍ፣ ያተኩራል።

አዚህ ውሰጥ ስለ መንግሥት አመሰራረትም አነሳለሁ። ከእሱም ጋር ሌሎቹን

ጉዳዮች ሁሉ ወደፊት እጠቅሳለሁ።

አንድ የረሣሁት ነገር ቢኖር ይህ ነው። እሱም:- ” የክርስቲያን ሃይማኖት፣

በገባበት አገር ሁሉ ( ይህ ትልቅ ቁም ነገር ነው) እያንዳንዱን ሕዝብ የአኗኗር

ባህልና ዘዴ ሳቀይር እንደፈለጉት (በዚህ ከሌሎቹ ሃይማኖቶች ይለያል)

ኢንዲኖሩ የሚፈቅድ ሃይማኖት ነው።” በዚህ ምክንያት፣ “የደቡቡ፣ ሕዝቦች

አኗኗር ከሰሜኑ የተለየ ” የሚመስለ። ይህ ስለሆነ ግን እነዚህም ሆኑ እነዚያ

የሰሜኑም ሆነ የደቡቡ፣ የምስራቁም ሆነ የምዕራቡ፣ የመሃል ሃገሩም ሆነ

የዳርዮሹና የጠረፉ ፤ አንዱ ከሌላው ያነሰ ወይንም የላቀ “ኢትዮጵያዊ”

አይደለም፣ አይደሉም። ለመሆኑ የሰውልጅስ የተፈጠረው ከየትስ ሆነና!

ይልማ ኃይለ ሚካኤል

© ለ አእምሮ 2005 / © Le’Aimero Copyright 2013

Posted in ሌሎችሌሎችሌሎችሌሎች / others, ማህበራዊናማህበራዊናማህበራዊናማህበራዊና ፖለቲካፖለቲካፖለቲካፖለቲካ /Social & political, ባህላዊናባህላዊናባህላዊናባህላዊና ማህበራዊማህበራዊማህበራዊማህበራዊ /Cultural & social,

ታሪክናታሪክናታሪክናታሪክና ባህልባህልባህልባህል | Leave a reply

ለ አእምሮ – Le'Aimero © | መንፈሳዊ ሐሳብ የአእምሮ ምግብ ነው !

ለ አእምሮ – Le'Aimero © | መንፈሳዊ ሐሳብ የአእምሮ ምግብ ነው !19

Page 21: ለ አእምሮ መጽሔት ቅጽ 1 ቁጥር 2 - LeAimero Vol 1 No 2

7/16/2019 1 2 - LeAimero Vol 1 No 2

http://slidepdf.com/reader/full/-1-2-leaimero-vol-1-no-2 21/61

የኢትዮጵያናየኢትዮጵያናየኢትዮጵያናየኢትዮጵያና ኤርትራኤርትራኤርትራኤርትራ ሕብረትሕብረትሕብረትሕብረት – የውይይትየውይይትየውይይትየውይይት

ሃሳብናሃሳብናሃሳብናሃሳብና ግንዛቤግንዛቤግንዛቤግንዛቤ

Posted on May 16, 2013

የኢትዮጵያናየኢትዮጵያናየኢትዮጵያናየኢትዮጵያና ኤርትራኤርትራኤርትራኤርትራ ሕብረትሕብረትሕብረትሕብረት – የውይይትየውይይትየውይይትየውይይት ሃሳብናሃሳብናሃሳብናሃሳብና ግንዛቤግንዛቤግንዛቤግንዛቤ

የኢትዮጵያና  የኢትዮጵያና  የኢትዮጵያና  የኢትዮጵያና የኤርትራ የኤርትራ የኤርትራ የኤርትራ ዝምድናና  ዝምድናና  ዝምድናና  ዝምድናና የምሁራኑ የምሁራኑ የምሁራኑ የምሁራኑ ሚና  ሚና  ሚና  ሚና፡፡ ፡፡ ፡፡ ፡፡ 

እንዴት እንዴት እንዴት እንዴት ነበር ነበር ነበር ነበር ? አሁንስ አሁንስ አሁንስ አሁንስ ምን ምን ምን ምን መሆን መሆን መሆን መሆን አለበት አለበት አለበት አለበት ? (PDF)

Tesfatsion-Berlin-lecture-2011

በፕሮፈሰር በፕሮፈሰር በፕሮፈሰር በፕሮፈሰር ተስፋ ተስፋ ተስፋ ተስፋ ጽጽጽጽዮን ዮን ዮን ዮን መድሃኔ መድሃኔ መድሃኔ መድሃኔ የቀረበ የቀረበ የቀረበ የቀረበ ፅሁፍ ፅሁፍ ፅሁፍ ፅሁፍ 

መግቢያ 

 ይህ በፕሮፈሰር ተስፋ ጽዮን መድሃኔ የቀረበው ፅሁፍ በመጀመርያ 

የተደመጠው በጀርመን አገር፡ በበርሊን ከተማ፡  “ አገርህንና ታሪክህን ዕወቅ ” 

በሚለው መድረክ ላይ በጁን 13፡ 2011 ዓ . ም . ወርሀዊ ስብሰባ ነው። 

እዚያ ከንግግሩ ተያይዞ በተካሄደው ውይይት ላይም ኢትዮጵያውያንንና  

ኤርትራውያንን የሚያገናኝ ህዝብ -ለህዝብ፣ የውይይት መድረክ በአውሮጳ 

ለ አእምሮ – Le'Aimero © | መንፈሳዊ ሐሳብ የአእምሮ ምግብ ነው !

ለ አእምሮ – Le'Aimero © | መንፈሳዊ ሐሳብ የአእምሮ ምግብ ነው !20

Page 22: ለ አእምሮ መጽሔት ቅጽ 1 ቁጥር 2 - LeAimero Vol 1 No 2

7/16/2019 1 2 - LeAimero Vol 1 No 2

http://slidepdf.com/reader/full/-1-2-leaimero-vol-1-no-2 22/61

 ይቋቋም የሚል ውሳኔ ተደርሰዋል። ይህ መድረክ በመጀመርያ የሚቋቋመው 

በበርሊን ከተማ ሲሆን ፡ በሌሎች የጀርመን ከተሞችና የአውሮጳ አገሮች  

የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያንም አርአያውን እንዲከተሉ 

እንማጸናለን። 

 ይህ ፅሁፍ፡ ወደፊት ምሁራኑ በዚህና በሌሎች የአከባቢው ጉዳዮች ላይ 

የሚወያዩበት፣ የተለያዩ ሀሳቦችን የሚያራምዱበት፣ እንዲሁም ትችትና  

ምርምር የሚያካሂዱበት አልፎ -አልፎ በሚታተም መፅሄት ላይ ከሌሎች  

ፅሁፎች ጋር አብሮ ይወጣል። እስከዚያ ድረስ ሃሳቡን ሰው እንዲመለከተው 

በማለት በዛሬው አዲሱ ለ አእምሮ ድረ፥ገጻችን ላይ እንዲወጣ አድርገናል። 

ስለ “ አገርህንና ታሪክህን ዕወቅ ” 

 ይልማ ኃ ይለሚካኤል፤ 

( ሰብሳቢ )

*********************

የኢትዮጵያና የኤርትራ ዝምድናና የምሁራኑ ሚና፡፡ 

እንዴት ነበር ? አሁንስ ምን መሆን አለበት ?

ተስፋጽዮን መድሃኔ

ብረመን ዩኒቨርሲቲ፣ ጀርመን

አገርህንና ታሪክህን ዕወቅ፣ ወርሀዊ መድረክ

በርሊን፡ ጁን 13፡ 2011

የሚከተለው ፅሁፍና በበርሊን ከተማ በጁን  13 2011 ስብሰባ የተሰጠው ንግግር፡ በይዘቱም በቋንቋውም ሙሉ በሙሉ አንድ ነው፡፡ ነገር ግን፡ 

ለ አእምሮ – Le'Aimero © | መንፈሳዊ ሐሳብ የአእምሮ ምግብ ነው !

ለ አእምሮ – Le'Aimero © | መንፈሳዊ ሐሳብ የአእምሮ ምግብ ነው !21

Page 23: ለ አእምሮ መጽሔት ቅጽ 1 ቁጥር 2 - LeAimero Vol 1 No 2

7/16/2019 1 2 - LeAimero Vol 1 No 2

http://slidepdf.com/reader/full/-1-2-leaimero-vol-1-no-2 23/61

ንግግሩ ለህትመት በሚዘጋጅበት ጊዜ፡ በስብሰባው ውይይት የተነሱትን 

ነጥቦች ከግምት በማስገባት፡ ይዘታቸው ምንም ሳይለወጥ በበለጠ 

እንዲብራሩ በማለት ጥቂት ሃሳቦች ትንሽ ሰፋ ብለዋል፡፡ ንግግሩ በዚሁ 

መልክ ታትሞ እንዲወጣ ለኢትዮጵያና ለኤርትራ በጎ ምኞት ያላቸው ወዳጆቼ ተባብረውኛል፡፡ በጣም አመሰግናቸዋለሁ፡፡ 

ተስፋ ጽዮን መድሃኔ፡፡ 

የኢትዮጵያና የኤርትራ ዝምድናና የምሁራኑ ሚና፡፡

እንዴት ነበር? አሁንስ ምን መሆን አለበት?

ተስፋጽዮን መድሃኔ (ፕሮፈሰር)

ብረመን ዩኒቨርሲቲ፣ ጀርመን

ይህ ጥያቄ ከተነሳ በጣም ቆይተዋል፡፡ በተለይ ኤርትራ ከኢትዮጵያ

ከተገነጠለች በሁዋላ፡ በተለያየ መልኩ ሲነሳ ነበር፤ አሁንም እየተነሳ ነው፡፡በሁለቱ ኣገሮች መካከል የነበረው ግኑኝነት ችግር ውስጥ ሲገባና፡ በሁዋላም

እየተበላሸ ሄዶ እስከመለያየት ሲደርስ ምሁራን ምን ያደርጉ ነበር? ኣሁንስ

ምን እያደረጉ ነው? ለተፈጠረው ችግር ኣስተዋጽኦ ያደረጉና፡ ኣሁንም

በማድረግ ላይ ያሉ ምሁራን ቢኖሩስ ድክመቶቻቸው ምን ይመስሉ ነበር?

አሁንስ ምን ይመስላሉ? እነዚህንና ሌሎችንም ተመሳሳይ ጥያቄዎች በተለያዩ

መድረኮች በመጠኑም ቢሆን ተወያይተንባቸዋል፡፡

እነዚህ ጥያቄዎች የሚነሱት በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል የነበረው

ወንድማማችነት እንዲታደስና ለሁለቱ ሀገሮች ገንቢ የሆነ ትስስር ይኖር

ዘንድ ምን ማድረግ እንደሚቻል በምንመረምርበት ጊዜ ነው፡፡

በዚሁ ንግግሬ ምሁራን ስል በተለያዩ ዓውደ ጥናቶች ሊቀ-ሊቃውንት ያሰኙ፡

ሞያቸው ሃሳብ ማፍራትና ማቀበል ወይም ማሰራጨት የሁኑ ሰዎችን ማለቴ

አይደለም፡፡ እነዚህን ሊጨምር የሚችል ቢሆንም፡ ምሁራን ስል

ለ አእምሮ – Le'Aimero © | መንፈሳዊ ሐሳብ የአእምሮ ምግብ ነው !

ለ አእምሮ – Le'Aimero © | መንፈሳዊ ሐሳብ የአእምሮ ምግብ ነው !22

Page 24: ለ አእምሮ መጽሔት ቅጽ 1 ቁጥር 2 - LeAimero Vol 1 No 2

7/16/2019 1 2 - LeAimero Vol 1 No 2

http://slidepdf.com/reader/full/-1-2-leaimero-vol-1-no-2 24/61

በህብረተሰቦቻችን ውስጥ ከዘመናዊው ትምህርት ጋር የተዋወቁ፡ በአገር

ፖለቲካና አስተዳደር አስተያየት ያላቸው፡ አቋም መውሰድ የሚችሉ፡

ሚናዎችም የሚኖሩዋቸው ማለቴ ነው፡፡ ቃሉን በዚሁ ትርጉም ለመጠቀም

ፕሮፈሰር ባሀሩ ዘውዴ በ1994 ባሳተመው አንድ ፅሁፍ የገለጸውን ሃሳብመሰረት በማድረግ ነው፡፡

ምሁራን፡ ወሳኝ ናቸው ባይባልም፡ ትልቅ ሚና አላቸው፤ በተለይ በታዳጊ

አገሮች ሚናቸው ከፍ ያለ ነው፡፡ ነገር ግን ምሁራን ብቻ ሳይሆኑ ሁሉም

የሲቪል ህብረተሰብ ክፍሎች ሚናዎች ነበሩዋቸው፣ አሉዋቸውም፡፡ ይህንን

ሳንረሳ ነው በምሁራን ሚና የምናተኩረው፡፡

በኤርትራና በኢትዮጵያ ምሁራን የተለያዩ ሚና ተጫውተዋል፣ ገንቢም

አፍራሽም፡፡ የኢትዮጵያውያን ምሁራን ሚና፡ በተለይ ከአፄ ኃይለሥላሤ

ዘመን አንስቶን በተመለከተ ብዙ ተፅፈዋል፤ ፕሮፈሰር ጳውሎስ ሚልኪያስ

“ ኃይለ ሥላሤ፣ ዘመናዊ ትምህርትና አብዮት በኢትዮጵያ ” በሚል ርእስ

በእንግሊዝኛ የደረሰው መፅሀፍ ከአንጋፋዎቹ ስራዎች አንዱ ነው፡፡

ዛሬ ከምሁራኑ ምንድነው የሚጠበቀው? ወይም ምሁራኑ ምን ማድረግ

አለባቸው? የሚለውን ጥያቄ ለመመለስ ያለፈው አፍራሽ ሚናቸው ምን

እንደነበረ፡ ወይም በአፍራሹ ሂደት ምን ሚና እንደነበራቸው እና አሁን

ደግሞ እንዴት እንደሚታረም መወያየት ያስፈልጋል፡፡ ይህ ግን ገንቢ

ሚናቸውን መካድ አይደለም፤ እርማትና እድገት ስለምንፈልግ ግን

ስህተቶቻችንንና ጥፋቶቻችንን በቀዳሚነት እንመረምራለን፡፡ በሌላ አነጋገር

እርማትና እድገት በሚሻ መንፈስ ነው በድክመቶቻችንና በስህተቶቻችን ላይ

የምናተኩረው፡፡

ይህንን ዓይነት ምርምር ስናደርግ በቅድሚያ የኢትዮጵያና ኤርትራ ግንኙነትምን ወይም እንዴት መሆን እንዳለበት ማየት ይኖርብናል፡፡ ያለንበት ዘመን

ለ አእምሮ – Le'Aimero © | መንፈሳዊ ሐሳብ የአእምሮ ምግብ ነው !

ለ አእምሮ – Le'Aimero © | መንፈሳዊ ሐሳብ የአእምሮ ምግብ ነው !23

Page 25: ለ አእምሮ መጽሔት ቅጽ 1 ቁጥር 2 - LeAimero Vol 1 No 2

7/16/2019 1 2 - LeAimero Vol 1 No 2

http://slidepdf.com/reader/full/-1-2-leaimero-vol-1-no-2 25/61

ዘመነ-ገሎባላይዘሸን ነው፤ አገሮች ወይም ዓለም በሙሉ በተለያዩ ዘርፎች

ተዛምደዋል፡ ተሳስረዋል፡፡ ማንኛውም አገር ያላትን ለሌሎች እያቀበለች፡

የሌላትን ደግሞ ከሌሎች እየተረከበች ነው የምትኖረው፡፡ ከሌሎች አገሮች

በብዙ ዘርፎች ሳትተሳሰር ትርጉም ባለው ሁኔታ የምትኖር አገር የለችም፡፡

በተለይ ድሃ ወይም ታዳጊ ኣገሮች በበለጠ መተሳሰር አለባቸው፡፡

ኢትዮጵያና ኤርትራ ሁለት ድሃ የሆኑ ታዳጊ አገሮች ናቸው፡፡ አሁን ባለው

የዓለም ሁኔታ በሁሉም ዘርፍ መዛመድ እንዳለባቸው ሁለቱን አገሮች

ለሚያውቅ ሁሉ ምንም ጥርጥር የለውም፡፡ ካልተዛመዱና ካልተሳሰሩ

የህዝቦቻቸውን ኑሮና መብቶች ሊያሟሉ አይችሉም፡፡ በሌላ አነጋገር፡ተለያይተን – ማለት አንድ ዓይነት ትስስር ሳናደርግ – የዓለምን ሁኔታ

ልንቋቋመው አንችልም፡፡

አሁን ባለው የዓለም ሁኔታ ኢትዮጵያና ኤርትራ የኢኮኖሚ ብቻ ሳይሆን

የፖለቲካ ዝምድናም ያስፈልጋቸዋል፡፡ የፖለቲካ ዝምድናውም ካሁን በፊት

በተደጋጋሚ እንደገለጽኩት ኮንፈደረሽን የሚባለው ነው፡፡ ኮንፈደረሽን

በኢትዮጵያና ኤርትራ መሀከል ብቻ ሳይሆን ሁሉንም የአፍሪቃ ቀንድ አገሮች

ያቀፈ እንዲሆን የሚፈለግ ነው፡፡ በዚሁ ጊዜ ግን ተግባራዊነት ሊኖረው

የሚችል፡ ያውም አንዳንድ ቅድመሁኔታዎች ከተሟሉ በሁዋላ፡ በኢትዮጵያና

በኤርትራ መሀከል ነው፡፡ የዚህ ሁለት አገሮች ትስስር ለወደፊቱ

የሚቋቋመው የአፍሪቃ ቀንድ ኮንፈደረሽን መሰረት ይሆናል፡፡

ኮንፈደረሽን ማለት ምን እንደሆነ፤ ከፈደረሽን እንዴት እንደሚለይ ካሁን

በፊት በሳን ሆዘ ስብሰባዎች ገልጬዋለሁ፡፡ በይዘቱ የሚለያይ ቢሆንም፡

ኮንፈደረሽን ሲባል፡ በጠቅላላ አነጋገር፡ አገሮች ልዓላውነታቸው

እንደተጠበቀ ሆኖ የሚያደርጉት ትስስር እና የሚያቆሙት መንግስት ነው፤

አብነት በመስጠት ነገሩን ባጭሩ ለመግለጽ፡ አሁን ያለው የአውሮፓ ህብረት

ዓይነት ዝምድናና መንግሥት ማለት ነው፡፡ የፖለቲካው ትሰስር–

እንዲያውም የኢኮኖሚውም ቢሆን – ለምን ያስፈልገናል? ጤናማ የሆነ

መልካም – ማለት ኖርማል – ጉርብትና ብቻ ለምን ኣይበቃም? የሚል

ለ አእምሮ – Le'Aimero © | መንፈሳዊ ሐሳብ የአእምሮ ምግብ ነው !

ለ አእምሮ – Le'Aimero © | መንፈሳዊ ሐሳብ የአእምሮ ምግብ ነው !24

Page 26: ለ አእምሮ መጽሔት ቅጽ 1 ቁጥር 2 - LeAimero Vol 1 No 2

7/16/2019 1 2 - LeAimero Vol 1 No 2

http://slidepdf.com/reader/full/-1-2-leaimero-vol-1-no-2 26/61

ፈታኝ ጥያቄ በአንዳንድ ስብሰባዎች ኣጋጥሞኛል፡፡ እኔን በተመለከተም፡

“ፈደረሽን፡ ኮንፈደረሽን እያለ ባያደነቁረን መልካም ነበር” የሚሉ

ኤርትራውያን እንዳሉ አውቃለሁ፡፡

ይህ ፈታኝ ጥያቄም ሆነ ነቀፌታ የዓለምንና የሁለቱ አገሮቻችንን ሁኔታ

በደንብ ካላጤነ አመለካከት የሚነሳ ነው፡፡እንዲያውም “ጤናማ የሆነ

መልካም” (ኖርማል) ጉርብትና ሲባል በይዘቱ የተለያየ መሆኑን ያልተገነዘበ

አስተሳሰብ የሚያንጸባርቅ ነው፡፡ የሁለት (ወይም በቁጥር ከዚያ በላይ የሆኑ)

አገሮች ዝምድና ይዘት እንደየሁኔታቸው ይለያያል፡፡ የኢትዮጵያ ጉርብትና

ከከኒያ ጋር እና ከጂቡቲ ጋር በይዘቱ አንድ ሊሆን አይችልም፤ የኤርትራጉርብትና ከኢትዮጵያና ከጂቡቲ ጋር ወይም ከየመን ጋር በይዘቱ አንድ

ሊሆን አይችልም፡፡

ኢትዮጵያና ኤርትራ በጂዮግራፊያዊ አቀማመጣቸው፡ በታሪካዊና ባህላዊ

ዝምድናዎቻቸው፡ በኢኮኖሚያዊ እርስ-በርስ ተፈላላጊነታቸው ወይም

ተጠቃቃሚነታቸው (ወይም በጋራ ጥቅሞቻቸው) ምክንያት የጤናማ

ጉርብትናቸው ይዘት ጥብቅ የሆነ ቅርበት ብቻ ነው ሊሆን የሚችለው፡፡ ይህ

በይዘቱ ጥብቅ ቅርበት የሆነ ጉርብትና የኢኮኖሚም የፖለቲካም ገጽታዎች

አሉት፡፡ የኢኮኖሚው ገጽታው መወሃሃድን የሚፈቅድና የሚያስችል መዋቅር

ነው፤ የፖለቲካ ገጽታው ደግሞ፡ ኮንፈደረሽን ወይም እሱን የሚመስል ነው፡፡

ለኔ እንደሚመስለኝ እንዲህ ዓይነት ዝምድና አለማቋቋም ወይም አለማበጀት

ምክንያታዊ (ራሽናል) ወይም ብልህ ውሳኔ አይደለም፤ እንዲያውም

ከዕውነታ ወይም ከገሃድ ዓለም የራቀ (ወይም አንሪያሊስቲክ) ነው፡፡ይህን

ዓይነት ዝምድናን መቃወም ዕውነታን መካድ ነው፤ ኮንፈደረሽን መሳይ

ትስስር አልፈልግም ማለት ቢያንስ በሁለቱ አገሮች መካከል ሊኖር

የሚገባውን ጤናማና በሰላም አብሮ የመኖርን (የመበልጸግን) መርሆ ወይም

ዓላማ አለመቀበል ነው፡፡

ለ አእምሮ – Le'Aimero © | መንፈሳዊ ሐሳብ የአእምሮ ምግብ ነው !

ለ አእምሮ – Le'Aimero © | መንፈሳዊ ሐሳብ የአእምሮ ምግብ ነው !25

Page 27: ለ አእምሮ መጽሔት ቅጽ 1 ቁጥር 2 - LeAimero Vol 1 No 2

7/16/2019 1 2 - LeAimero Vol 1 No 2

http://slidepdf.com/reader/full/-1-2-leaimero-vol-1-no-2 27/61

አሁን ያለው የኢትዮጵያና ኤርትራ ግኑኝነት፡ ዝምድና ሊሆንስ ይቅር፡

ሰላማዊ ጉርብትና ነው ብሎ ለማለት እንኳን አያስደፍርም፡፡ የዚህ ሁኔታ

አመጣጥና ታሪክ ሁላችን የምናውቀው ነውና ጊዜ ልናጠፋበት

አያስፈልግም፡፡ ይልቁንስ መመርመር ያለብን ይህ አሳዛኝ ወይም የማይገባሁኔታ እንዲደርስ እና አሁንም እንዲቀጥል ምሁራኖቹ ምን ሚና ተጫወቱ?

ምን አሰተዋጽኦ አደረጉ? ይህንን አስተዋጽኦ ለማድረግ ያበቁዋቸው

ድክመቶችስ ምን ናቸው? የሚሉትን ጥያቄዎች ነው፡፡ ነገሩን በግልጽ

ለማስቀመጥ፡ በኤርትራ ለነጻነት ወይም ለመገንጠል ጦርነት ይካሄድ

በነበረበት ጊዜ ምሁራኖቹ ምን ሚና ነበራቸው? ኤርትራ ከተገነጠለች

በሁዋላስ ሁኔታው ሲባባስ ምን ሚና ነበራቸው?

ይህንን ጥያቄ ለመመለስ በመጀመርያ የትኞቹ ምሁራን ማለቴ እንደሆነ

ባጭሩ መግለጽ እወዳለሁ፡፡ እነዚህ ምሁራን በ60ዎቹ፡ 70ዎቹ እና

በ80ዎቹ በኢትዮጵያም በኤርትራም ትልቅ ሚና የነበራቸው፤ አሁንም

እያረጁና እየተተኩ ቢሆኑም ገና መጠነኛና እያነሰ የሚሄድ ያለ ሚና ያላቸው

ናቸው፡፡ ከነዚህ ምሁራን አብዛኛዎቹ “ጥላሁን ታከለ” ተብሎ ከሚታወቀውባህሩ ዘውዴ አስቀድሜ በጠቀስኩት መጣጥፍ ሶስተኛው የአዲስ ምሁራን

ትውልድ ብሎ ከሚገልጸው ክፍል ናቸው፡፡

ይህንን የምሁራን ትውልድ አውቀዋለሁ፤ የኔም ትውልድ ነውና፡፡ ብዙው

ከዚህ ትውልድ፡ በተማሪነት ጊዜ፡ በጠቅላላው አነጋገር፡ ተምረው ዕውቀት

የማዳበርን ዓላማ በተግባር የሚገባውን ያህል ቀደምትነት የሰጠአይመስልም፡፡ ታሪክንና ጽንሰ-ሃሳቦችን – የፖለቲካ ጽንሰ-ሃሳቦችን ጨምሮ

– በትጋት ለማንበብ፡ ለማጥናትና በጥልቀት ለማወቅ የጓጓ ነበር ቢባልም፡

አዝማሚያውንና ብቃቱን ግን በተግባር አላስመሰከረም፡፡ ይልቁንስ ለገቢራዊ

ንቅናቄ እና ለአብዮት መዘጋጀት የሚለው መንፈስ ያየለበት ነበር፡፡ ይህ ግን

ለብዙው ወይም ለአብዛኛው ብቻ የሚመለከት ሃቅ ነው፤ ካለበለዚያ

ትምህርታቸውን በደንብ የሚከታተሉና በቂ ንባብ ያደረጉ፡ በፖለቲካ

ንቅናቄም የተሰማሩ ጥቂቶች ነበሩ፡፡ በብዙ የአውሮጳና ሌሎች የምዕራቡ

ለ አእምሮ – Le'Aimero © | መንፈሳዊ ሐሳብ የአእምሮ ምግብ ነው !

ለ አእምሮ – Le'Aimero © | መንፈሳዊ ሐሳብ የአእምሮ ምግብ ነው !26

Page 28: ለ አእምሮ መጽሔት ቅጽ 1 ቁጥር 2 - LeAimero Vol 1 No 2

7/16/2019 1 2 - LeAimero Vol 1 No 2

http://slidepdf.com/reader/full/-1-2-leaimero-vol-1-no-2 28/61

ዓለም አገሮችም፡ ወቅቱ – በተለይ ከ1968 አንስቶ – ተማሪው እንደዚሁ

ከመደበኛ የትምህርት ተቋማትና የህብረተሰቡ ዕሴቶች በመንፈስ እየራቀ

የሄደበት ነበር፡፡

ይህ ትውልድ ለኢትዮጵያም ለኤርትራም ቀና ምኞትና ውብ የሆነ ራዕይ

ነበረው፡፡ ለህዝቦቹ አሳቢ፡ ለሃገሩም ተቆርቋሪ ሆኖ፡ ለማስዋእትነትም ዝግጁ

ነበር፡፡ ከራዕዩ ውበትና ከዓላማው ክብደት ጋር የሚጣጣምና የሚመጣጠን

ዕውቀትና አሰተዋይነት ግን አልነበረውም፡፡ ይህ ትልቅ ድክመት ነበር፤ ከዚህ

ድክመት የተነሳም ይህ ትውልድ፡ በኢትዮጵያም በኤርትራም፡ በህሊናው

ብሄርተኛ፡ አገር-ወዳድ፡ ባለ-ጀብዱና ተራማጅ እያለ፡ አመርቂ የሆነስትራተጂና ስልት ቀይሶ ሁኔታውን ሊቋቋም አልቻለም፡፡ ስለዚህም

ከንጉሳዊው ሥርዓት ህልፈት በሁዋላ በሁለቱም አገሮች ሥልጣን ላይ

በወጡትና አሁንም ገና ሥልጣን ላይ ባሉት ቡድኖች ክፉኛ ተመታ፡፡

መሰረታዊ ከሆኑት ድክመቶች አንዳንዱን አጠር አጠር አድርጌ ልጥቀስ፡፡

- ከድክመቶቹ አንዱ አስቀድሞ ከተጠቀሰው ዕውቀትና በጥልቀት የመረዳት

ችሎታ ካለመኖር ጋር የተያያዘ ነው፡፡ ኢትዮጵያንና ኤርትራን በተመለከተ

ምሁራኖቹ በቂ ዕውቀት አልነበራቸውም፡፡ የኤርትራ ምሁራን ስለ ኢትዮጵያ

ታሪክ ሆነ ፖለቲካ ዕውቀቱ አልነበራቸውም፤ ስለ ኤርትራም ቢሆን

ዕውቀታቸው ጥለቀት ያለው አልነበረም፡፡ ኢትዮጵያውያን ምሁራንምእንደዚሁ ስለ ኤርትራ በመጠኑ ትርጉም ያዘለ ዕውቀት አልነበራቸውም፡፡

- ብዙው ከዚህ የምሁራን ትውልድ ታሪክንና ባህልን በተመለከተ የፍፁም

ተቃውሞ (ንሂሊሰት) የሆነ መንፈስ ነበረው፤ ታሪክንም ሆነ የባህል እሴቶችን

ከቁጥር ውስጥ አላስገባም፡፡ ታሪኩና ባህሉ በጎና የሚያገለግል ገፅታ

እንዳለው ዘንግቶ፡ ሁሉንም ከፊውዳሉ ስርዓት ጋር በማዛመድ ችላ አለ፡፡ታሪክንና ባህልን ችላ ማለት ስህተት ብቻ ሳይሆን እጅግ አደገኛም ነበር፡፡

ለ አእምሮ – Le'Aimero © | መንፈሳዊ ሐሳብ የአእምሮ ምግብ ነው !

ለ አእምሮ – Le'Aimero © | መንፈሳዊ ሐሳብ የአእምሮ ምግብ ነው !27

Page 29: ለ አእምሮ መጽሔት ቅጽ 1 ቁጥር 2 - LeAimero Vol 1 No 2

7/16/2019 1 2 - LeAimero Vol 1 No 2

http://slidepdf.com/reader/full/-1-2-leaimero-vol-1-no-2 29/61

በዚህ ቸልተኝነት ምክንያት፡ በኢትዮጵያም ሆነ በኤርትራ ምሁሩ በምን

ዓይነት ማህበራዊ ሁኔታ ይንቀሳቀስ እንደነበረ አላወቀም፤ በኢትዮጵያ ይሁን

በኤርትራ ምን ያህል ለውጥ ማምጣት እንደሚቻል፣ ለውጡን ለማሳካት

ሊተባበሩ የሚችሉ የህብረተ-ሰቡ ወገኖች የትኞቹ እንደነበሩ፣ በሌላ አነጋገር፡በዚያ ወቅት ዒላማዎቹ ወይም ጠላቶቹ እና ተባባሪዎቹ ወይም ወዳጆቹ

የትኞች እንደነበሩ ብቁ ጥናት በማድረግ አልተረዳም፡፡ ስለዚህም በትግል

ጉዞው ብዙ አላስፈላጊ ጠላቶች አፍርቶ ከሰረ፡፡

- ከዚህ ድክመት ጋር በተያያዘ፡ በፖለቲካው መስክ የአገሮቻችን ወይም

የህብረተ-ሰቦቻችን ባህሎች የጉልበት ወይም ጭካኔ (ቫየለንስ) ባህሪምያለባቸው መሆኑ የምሁራኑ ትውልድ በሚገባ አላጤነም፡፡

በህብረተሰቦቻችን ሰላምና ፍቅር መሰረታዊ እሴቶች ቢሆኑም ፖለቲካዊ

ታሪካችን ግን ታላቅ የጭካኔ ገፅታ ያለበት ነው፡፡ በታሪካችን ብዙውን ጊዜ

ንጉስ በሌላ – ማለት፡ በአዲስ – ንጉስ ሲተካ ህጋዊና ሰላማዊ በሆነ የሽግግር

ሂደት አልነበረም፤ በማንኛውም መልኩ አንዱ – ቡድን ይሁን ግለሰብ –

ሌላውን በኃይል አሸንፎ እንጂ፡፡ ይህንን ነጥብ አንጋፋው ኢትዮጵያዊ ምሁርፕሮፈሰር ንጉሴ አየለ በዚሁ ዓመት በታተመው አንድ መጣጥፍ

አብራርቶታል፡፡ እንዲሁም ደራሲና የፖለቲካ ተንቀሳቃሽ ጌታቸው ረዳ

“ሓይካማ ” በተሰኘው መፅሃፉ ትግራይ ውስጥ ከፖለቲካ ጋር በተያያዘ

የተፈጸመውን፡ በእሳት መለብለብን የጨመረ፡ አረሜናዊ የሰብአዊ መብቶች

ረገጣ ዘርዝሮ በማጋለጥ ባህላችን በፖለቲካዊ ገፅታው ምን ያህል ጭካኔ

እንዳለው ያስረዳል፡፡ የፖለቲካ ባህላችን ይህ ባህርይ እንዳለው በሚገባ

ባለመረዳታቸው አንዳንድ የምሁራን ቡድኖች ተመልሰው የጐዱዋቸውን

የትግል ስልቶች ተጠቀሙ፡፡ በጭካኔ እምብዛም ለተካኑ፡ የጭካኔ ባህላቸው

በምሁራውነት ላልለሰለሰ፡ ርህራሄ ለሌላቸው ቡድኖች ሰለባ ሆኑ፡፡

- ይህ ሲባል ግን ምሁራኖቹም በህብረተ-ሰቡ ባህል ያልተነኩና የህብረተ-

ሰቡ ጠባይ ፈፅሞ የሌላቸው ነበሩ ማለት አይደለም፡፡ በህብረተ-ሰቡ

ተወልደው ያደጉ በመሆናቸው እነርሱም፡ በዘመናዊው ትምህርት ሂደት

ለ አእምሮ – Le'Aimero © | መንፈሳዊ ሐሳብ የአእምሮ ምግብ ነው !

ለ አእምሮ – Le'Aimero © | መንፈሳዊ ሐሳብ የአእምሮ ምግብ ነው !28

Page 30: ለ አእምሮ መጽሔት ቅጽ 1 ቁጥር 2 - LeAimero Vol 1 No 2

7/16/2019 1 2 - LeAimero Vol 1 No 2

http://slidepdf.com/reader/full/-1-2-leaimero-vol-1-no-2 30/61

ባንዳንድ ረገድ ቀየጥ ያሉ ቢሆንም፡ የህብረተ-ሰቡ ዕሴቶች ነበሩዋቸውም

አሉዋቸውም፡፡ አንዳንድ የባህላችን አስከፊ ገፅታዎች – ጭካኔውን ጨምሮ

– ከሌሎቹ ባነሰ መጠን ይሁን እንጂ በምሁራኖቹም ታይቷል፡፡

የሚያሳዝነው ግን ምሁራኖቹ ከህብረተ-ሰቡ ጋር መሰረታዊ ዕሴቶችእንደሚጋሩ በሚገባ መጠን አለማወቃቸው ወይም አለማመናቸው ነው፡፡

ይህ ጉደለት ከባድ ጉዳት እንዳደረሰ አንዳርጋቸው ፅጌ ነፃነትን የማያውቅ ነፃ 

አውጪ በሚለው መፅሃፉ ያመለክታል፡፡

- ይህ የምሁራን ትውልድ በኤርትራም ሆነ በኢትዮጵያ የፊተኞቹ የምሁራን

ትውልዶች ያህል ጨዋነት ወይም ትህትና (ሲቪሊቲ) አልነበረውም፡፡ የሃሳብአገላለፁ ዘይቤ ብዙውን ጊዜ የተረጋጋና ክፍት ሳይሆን፡ የአክራሪነትና የጠብ

ቃና ያዘለ (ፖለሚካል) ነበር፡፡ መደማመጥ፡ መግባባት፡ እና መቻቻል

በሚፈለገው መጠን አልነበሩም፡፡ ( ባህሩ ዘውዴ፡ ገፅ  486 ፤ ገላውዴዎስ 

አርአያ፣ ገፆች   69- 71) ፡፡ በነዚህና በሌሎች ምክንያቶች የዚህ ትውልድ

ምሁራን በተፈለገው መጠን ተግባብተውና ተባብረው መስራት አልቻሉም፡፡

- አስቀድሜ ከጠቀስኳቸው ድክመቶች ጋር የተያያዘ ሌላ ጉድለትም ነበር፤

እሱም ዕውነታው ከሚፈቅደው በላይ ማቀድ ወይም ዕቅድን ለመተግበር

መሞከር (አልትራዪዝም) ነው፤ ይህ ማለት ሁኔታው የሚፈቅደውና

የሚያስችለው ምን እንደሆነ መርምሮ ሳይሆን፡ የተመኙት ግብ ወይም ዓላማ

መደረስ አለበት ብሎ በጭፍን መንቀሳቀስ ማለት ነው፡፡ እንዲህ የመሰለ

ሁኔታን ያላጠናና ያልጠበቀ አካሄድ ብዙውን ጊዜ ጠላትን ይጠቅማል፡፡በቅርቡ ታሪካችን – በኢትዮጵያም በኤርትራም – አይተነዋል፡፡ አሁንም

ይህንን የሚመስል ጉድለት እየታየ ነው፡፡

- ብዙውን ጊዜ ከዚህ ጉድለት ጋር ተያይዞ የሚከሰት ሌላ ድክመትም ነበር፡

አሁንም አለ፤ እሱም ከተባሉት ምሁራን ብዙዎቹ፡ እንደግለሰቦች

ለመስዋእትነት ዝግጁ ቢሆኑና ቢሰዉም፡ የመጨረሻው ዓላማ ወይም ግብበትውልዳቸው ጊዜ እንዲረጋገጥ መሻታቸውና መሞከራቸው ነው፡፡ በሌላ

አነጋገር በውነቱ በሂደት እስከዚህም አያምኑም ነበር ማለት ይቻላል፡፡

ለ አእምሮ – Le'Aimero © | መንፈሳዊ ሐሳብ የአእምሮ ምግብ ነው !

ለ አእምሮ – Le'Aimero © | መንፈሳዊ ሐሳብ የአእምሮ ምግብ ነው !29

Page 31: ለ አእምሮ መጽሔት ቅጽ 1 ቁጥር 2 - LeAimero Vol 1 No 2

7/16/2019 1 2 - LeAimero Vol 1 No 2

http://slidepdf.com/reader/full/-1-2-leaimero-vol-1-no-2 31/61

ዕድገት ሲባል ሂደት ነውና፡ ፈጻሚ ትውልድ ብቻ ሳይሆን ጀማሪ ትውልድ

መሆንም ጀግንነት ነው፤ እንዲያውም ጀማሪ መሆን የበለጠ ጀግንነት ነው

ማለት ይቻላል ምክንያቱም ያልተጀመረ አያልቅምና፡፡ በለውጥ ሂደት

መነሳትና መጠናከር መድረክን ወይም ሁኔታን በጥንቃቄ እያገናዘቡበመሳተፍ ፋንታ የመጨረሻውን ግብ እውን ለማድረግና ለማረጋገጥ በመሻት

የተባሉት ምሁራን ትልቅ ችግር ላይ ወደቁ፡፡

ኤርትራውያንና ኢትዮጵያውያን ምሁራን አሁን ያለው ችግር እንዲከሰት

ባለፉት ዓመታት፡ በተለይ በደርግ ዘመን፡ የየራሳቸው አስተዋፅኦ አድርገዋል፤

አሁንም እያደረጉ ናቸው፡፡ አስተዋጽኦውን ያደረጉት መንግስታቱናድርጅቶቹ ይተገብሩዋቸው ከነበሩት፡ አሁንም ገና እየተከተሉዋቸው ካሉት

የተሳሳቱ ወይም ጐጂ የሆኑ ፖሊሲዎች ጋር በተያያዘ ነው፡፡ የሚከተሉት ዋና

-ዋናዎቹ ናቸው፡፡

ኤርትራውያን ምሁራን በተለይ የኢ.ፒ.ኤል.ኤፍ. ደጋፊዎች የነበሩት፡ ትልቅ

ድክመት አሳይተዋል፡፡ በመሰረቱ እነዚህ ምሁራን አውቶኖሚ – ማለት

የአእምሮ ነጻነት – አልነበራቸውም፡፡ ሊኖራቸውም አይችልም ነበር፤ ያ

ኢሳያስ አፈወርቅ የተቈጣጠረው ድርጅት እምብዛም ጥብቅ በሆነ

ማእከላዊነት ነበር የሚተዳደረው፤ የዲሞክራሲ ጭላንጭል አልነበረውም፡፡

ምሁራኖቹ ታዲያ ለድርጅቱ መሪ አካል ሙሉ-በሙሉ ተገዢ ነበሩ፡፡

የሚጽፏቸው አንቀጾችና የሚደርሷቸው መጻህፍት የኢ.ፒ.ኤል.ኤፍን

አቋሞች የሚያንጸባርቁና፡ የ.ኢፒ.ኤል.ኤፍን ፕሮፓጋንዳ እንዳለው

የሚያሰራጩ ነበሩ። በዚህ ረገድ ኢ.ኤል.ኤፍ. (ጀብሃ) የነበረው ሁኔታ

የተለየ ነበር፤ ከጀብሃ ጋር ተዛምደው የነበሩት ምሁራን በመጠኑ የማይናቅ

አውቶኖሚ ነበራቸው፡፡

- ከአውቶኖሚ ጋር በአንዳንድ ረገድ የሚመሳሰል ሌላ ችግርም ነበር፡፡

አሁንም በመጠኑ አለ፡፡ የኢትዮ-ኤርትራ ጥያቄ በቀዝቃዛው ጦርነት ጊዜ

ለ አእምሮ – Le'Aimero © | መንፈሳዊ ሐሳብ የአእምሮ ምግብ ነው !

ለ አእምሮ – Le'Aimero © | መንፈሳዊ ሐሳብ የአእምሮ ምግብ ነው !30

Page 32: ለ አእምሮ መጽሔት ቅጽ 1 ቁጥር 2 - LeAimero Vol 1 No 2

7/16/2019 1 2 - LeAimero Vol 1 No 2

http://slidepdf.com/reader/full/-1-2-leaimero-vol-1-no-2 32/61

ከርእሰ-ኃያላኑ ፉክክር ጋር ተሳስሮ ነበር፡፡ በአመሪካ የሚመራው የምዕራቡ

ዓለም አፍቃሬ ሶቭየት የነበረውን የአዲስ አበባው መንግስት ይቃወሙ

የነበሩትን ንቅናቄዎች፡ ኢፒ ኤል ኤፍን ጨምሮ፡ ይደግፍ ነበር፡፡ ደርግን

ለማዳከም የኤርትራ ነፃነት ደጋፊዎች ሆነው የቀረቡ የምዕራቡ ስትራተጂአራማጆችም ነበሩ፡፡ አንዳንድ የኢፒ ኤል ኤፍ አባሎችና ደጋፊዎች የሆኑ

ኤርትራውያን ምሁራን ታዲያ የኤርትራን ነገር ለምዕራቡ ስትራተጂ

በሚያገለግል መልኩ እያቀረቡ ቅስቀሳ ሲያካሂዱ ነበር፡፡ አንዳንዱንማ

እንዲህ የመሰለ ዘመቻ ማካሄድ በምዕራቡ ዓለም ኑሮ ለማበጀት የረዳው

ይመስላል፡፡ እነዚህ ምሁራን በዚህ ሁኔታ ስለኤርትራ ሲፅፉና ሲንቀሳቀሱ

እውነተኛ የሆነ አውቶኖሚ ሊኖራቸው ይችል እንዳልነበረ መገመት

ይቻላል፡፡

- ታሪክን በተመለከተ ኤርትራውያን ምሁራን ትልቅ ስህተት ፈፅመው ጉዳት

አድርሰዋል፡፡ ኤርትራ ድሮም ቢሆን ከኢትዮጵያ ጋር ፖለቲካዊና

አስተዳደራዊ ዝምድና አልነበራትም ለማለት ታሪክን ጠምዝዘው አቀረቡ፤

እንዲያውም የውሸት ታሪክ ፈለሰፉ፡፡ እንዲህ በማድረግ ወጣቱንአደነቈሩት፤ ማንነቱን በተመለከተም ግራ አጋቡት፡፡ ይህ ተግባር

የተፈጸመው ኤርትራ የተለየች ሉዓላዊት አገር ለመሆን መብት አላት ለማለት

እንዲመች ነበር፡፡ እጅግ የሚያሳዝነው ኤርትራ ይህ መብት አላት ብሎ

ለመከራከር ታሪክን መጠምዘዝ ወይም የፈጠራ ታሪክ መሸቅሸቅ አስፈላጊ

አለመኖሩ ነው፡፡

- ይህንን የሚመሳሰል ምሁራኑ ያስተጋቡት ኤርትራ የኢትዮጵያ ቅኝ-ግዛት

ናት የሚለው አቋም ነበር፤ ይህም መርዘኛ ውሸት ነበር፡፡ ኤርትራ የነበራት

አውቶኖሚ (ራሰ ገዝነት) በሀይል ተወስዶባት ያለፍላጐትዋ እንደ ጠቅላይ

ግዛት ተቀላቀለች፤ ይህ ግፍም ጭቆናም ነበር፤ የቅኝ ግዛት ሁኔታ ግን

አልነበረም፡፡ ይህ ውሸትም የተፈለገው ለነፃነት ወይም ለመገንጠል ጥያቄ

ደገፍ እንዲሆን በማለት ነበር፡፡ ዳሩ ግን ይህ ውሸትም ኤርትራ ለነፃነት

ለ አእምሮ – Le'Aimero © | መንፈሳዊ ሐሳብ የአእምሮ ምግብ ነው !

ለ አእምሮ – Le'Aimero © | መንፈሳዊ ሐሳብ የአእምሮ ምግብ ነው !31

Page 33: ለ አእምሮ መጽሔት ቅጽ 1 ቁጥር 2 - LeAimero Vol 1 No 2

7/16/2019 1 2 - LeAimero Vol 1 No 2

http://slidepdf.com/reader/full/-1-2-leaimero-vol-1-no-2 33/61

ወይም ለመገንጠል መብት አላት ለማለት አስፈላጊ አልነበረም፡፡ ህዝቡን፡

በተለይ ወጣቱን ግራ ለማጋባት ብቻ አገለገለ፡፡

- አንዳንድ ኤርትራውያን ምሁራን ኢትዮጵያውያንንና ባህላቸውን –

የትግራይ ህዝብን ጨምሮ – ያሳነሰና ያቋሸሸን ፕሮፓጋንዳ በማራመድ ሚና

ተጫውተዋል፡፡ ይህ ሚና አሁንም በተለይ የትግራይ ህዝብን በሚመለከት

እየቀጠለ ነው፡፡

- ኢትዮጵያውያንንና ሌሎችን የቀጠናው ህዝቦች ያሳነሰ መንፈስ ስለ ኤርትራ

ዓቅምና ብቃት የተጋነነ እምነት ማሰማቱ የማይቀር ነበር፡፡ በተግባር

የኢ.ፒ.ኤል.ኤፍ. ድምፅ-ማጉሊያ ናቸው ተብለው ይተቹ የነበሩ ምሁራን

ኤርትራ ንቁና ታታሪ የሆነ ህዝብ ያላት፡ ራሷን በደንብ የምትችል የተአምር

አገር ናት፤ ለወደፊቱም በፍጥነት እነዳደጉትና እንደበለጸጉት አንዳንድ የእስያ

ሃገሮች ልትሆን ነው የሚለውን ጉራ በማራመድ ተሳትፈዋል፡፡ ይህ ብዙ

ኤርትራውያንን ግራ አጋብቶ ከኢትዮጵያውያን ጋር የሚያደርጉት ግኑኝነት

ተቀባይነትና ተግባራዊነት ባለው ሥርዓት እንዲሆን አልረዳም፡፡ ስለዚህም

በሁለቱ ህዝቦች መካከል የነበረውን የወንድማማችነት ዝምድና ትክክለኛውን

ገፅታ እንዳያሳይ አስፈላጊ ያልሆኑ ችግሮችን ሳያስከትል አልቀረም፡፡

- በዚሁ ጊዜም ኤርትራውያን ምሁራን ህዝባቸውን የማሰተማር

ሃላፊነታቸውን እየተወጡ አይደሉም፡፡ ለምሳሌ አሁንም ገና በኤርትራው

መንግስት ፕሮፓጋንዳ ተደጋግሞ የሚለፈፈው በአፄ ኃይለሥላሤ ዘመን

ይሁን በደርግ ጊዜ በህዝቡ ላይ የተፈጸመው ግፍ ነው፡፡ በትግሉ ጊዜ ኢፒ

ኤል ኤፍ በኢትዮጵያውያን ላይ ያደረሰው ግፍ እንደነበረም ምሁራኖቹ

አይገልፁትም ያሉት፤ ምናልባት ለራሳቸውም አያውቁትም ይሆናል፡፡

ለምሳሌ ኮሎኔል አምሳሉ ገብረዝጊ በደረሱት የኤርትራ መዘዝ  በሚል

መፅሃፍ ኢ.ፒ.ኤል.ኤፍ. በኢትዮጵያ ወታደሮች ላይ የወሰዳቸው አንዳንድ

ኢሰብአዊ እርምጃዎች ተገልጸዋል፤ ኤርትራውያን ይህንን ማወቅ አለባቸው፤ማሳወቅ ያለባቸው ደግሞ ምሁራኑ ናቸው፤ እያደረጉት ግን አይደለም፡፡

ለ አእምሮ – Le'Aimero © | መንፈሳዊ ሐሳብ የአእምሮ ምግብ ነው !

ለ አእምሮ – Le'Aimero © | መንፈሳዊ ሐሳብ የአእምሮ ምግብ ነው !32

Page 34: ለ አእምሮ መጽሔት ቅጽ 1 ቁጥር 2 - LeAimero Vol 1 No 2

7/16/2019 1 2 - LeAimero Vol 1 No 2

http://slidepdf.com/reader/full/-1-2-leaimero-vol-1-no-2 34/61

- ኤርትራውያን ምሁራን በኢትዮጵያ መንግስታትና ህዝብ መሃከል አስፈላጊ

በሆነ መጠን ልዩነት አላደረጉም፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ ኤርትራውያንን

በወንድምነት እንደተቀበላቸውና፡ በሁሉም ዘርፍ ከኤርትራውያን ጋር

ለመዛመድ እንዳላመነታ ምሁራኖቹ ባለፈው ጊዜያት በሚገባአልመሰከሩም፡፡ አሁን ግን የኢትዮጵያ ህዝብ የሚመሰገን መሆኑ

የሚመሰክሩ ኤርትራውያን ምሁራን በቁጥር እያደጉ ናቸው፡ ይህም ደስ

የሚያሰኝ ነው፡፡

- የአሁኑን የኢትዮጵያ ሁኔታ በተመለከተ ኤርትራውያን ምሁራን ሁለት

ዓይነት ሆነዋል፡፡ እነርሱም በአስመራው መንግስት ጐን የተሰለፉት እናበተቃዋሚው ጐራ የሚገኙ ናቸው፡፡ የአስመራው መንግሥት ደጋፊዎች

አሁንም እንደበፊቱ የመንግስታቸውን አቋም በማራመድ ኢህአዲግን

የሚያስከፋ ሂስ ያዘለ መልእክት ያስተላልፋሉ፤ ይህንን የሚያደርጉት

ያሉትም መንግሥታቸው ከኢህአዲግ መንግስት ጋር፡ የዕውነት ይሁን

የማስመሰል፡ ቅራኔ ስላለው ነው፡፡ ለዚህ ዓላማ እንግዲህ ኢትዮጵያ ውስጥ

ያለውን አንዳንድ ችግርና ግፍ ይገልፃሉ፡፡ እነዚህ ምሁራን ሁለቱመንግሥታት በታረቁ ወይም ታርቀናል ለማለት በወሰኑ ጊዜ አሁን

በኢህአዲግ መንግስት ላይ የሚያሰሙት ያሉት ሂስና ወቀሳ እንደማያሰሙት

እርግጠኛ ሆኖ መናገር ይቻላል፡፡

በተቃዋሚው ጐራ ካሉት ምሁራን ደግሞ ብዙዎቹ የኢትዮጵያን ሁኔታ

የሚፈርዱት የኢህአዲግ መንግሥት በኤርትራ ነፃነትና ሉዓላውነት ጉዳይ ላይባለው ፖሊሲ መሰረት ነው፡፡ ኢህአዲግ የኤርትራ ነፃነትንና ሉዓላዊነትን

በይፋ ስለሚደግፍ፡ ኢትዮጵያውያን ተቃዋሚዎቹ ደግሞ ስለማይደግፉ ብቻ

በአቶ መለስ ዜናዊ የሚመራው መንግሥት ኢትዮጵያ ውስጥ ለሚፈፅመው

ግፍ ትኩረት አይሰጡትም፡፡ ዲሞክራሲን፡ የሀገሪቱ ሉዓላዊነትንና አንድነትን፡

ሰብዓዊ መብቶችን፡ ኢኮኖሚን፡ ሙስናን ወዘተ… በተመለከተ በውጭ አገር

ታዛቢዎች ሳይቀር በተደጋጋሚ የተዘገበውን ሁሉ ጨርሰው ችላ ይላሉ፤

የኢህአዲግ መንግሥት በተለያዩ ዘርፎች በደል ሲፈፅም እየታየ እኚህ

ለ አእምሮ – Le'Aimero © | መንፈሳዊ ሐሳብ የአእምሮ ምግብ ነው !

ለ አእምሮ – Le'Aimero © | መንፈሳዊ ሐሳብ የአእምሮ ምግብ ነው !33

Page 35: ለ አእምሮ መጽሔት ቅጽ 1 ቁጥር 2 - LeAimero Vol 1 No 2

7/16/2019 1 2 - LeAimero Vol 1 No 2

http://slidepdf.com/reader/full/-1-2-leaimero-vol-1-no-2 35/61

ኤርትራውያን የደግፉታል፡፡ ይህ ትልቅ ድክመት ብቻ ሳይሆን ለሁለቱ

ህዝቦች መቀራረብና መተባበር ዕንቅፋት የሚሆን ነው፡፡

- ኤርትራውያን ምሁራን የኤርትራን መገንጠል አስመልክቶ ኢትዮጵያውያን

ለምን የኢህአዲግ መንግስትን እንደሚወቅሱ አልተረዱም ወይም ለመረዳት

አልመረጡም፡፡ ለምሳሌ በ1993 የተካሄደውን ረፈረንደም እንውሰድ፡፡

ረፈረንደሙ ትክክለኛ ሂደት አልነበረም ብቻ ሳይሆን የዕብሪት መልክም

ነበረው፡፡ ሂደቱ ቢያንስ ኢትዮጵያውያን ምሁራንን በሃሳብና በውይይት

ደረጃ ማሳተፍ ነበረበት፡ ወሳኙን ድምጽ የሚሰጥ የኤርትራ ህዝብ ቢሆንም፡፡

ሂደቱ እንኳንስ ኢትዮጵያውያን ምሁራንን፡ የተለያዩ አቋሞች የነበሯቸውንኤርትራውያን ተቃዋሚዎችንም አላሳተፈም፡፡ ስለዚህ የረፈረንደሙን ሂደት

በተመለከተ ኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይሆኑ አንዳንድ ኤርትራውያንም

የኢህአዲግን መንግስት ይወቅሳሉ፡፡ በአሁኑ ጊዜ ኤርትራውያን ምሁራን

ይህንን ነጥብ በደንብ ማጤን ይኖርባቸዋል፡፡ ይህንን ነጥብ አለመረዳታቸው

በዙ አለመግባባት እንዳስከተለ መገመት አያዳግትም፡፡

- ብዙዎች ኢትዮጵያውያን ምሁራን፡ ድሮም ሆነ አሁን፡ ኤርትራና ኢትዮጵያ

አንድ አገር መሆን አለባቸው ለማለት በታሪክ ላይ ያተኩራሉ፡፡ ኤርትራ

የኢትዮጵያ አካል ነበረች፡ ስለዚህም በፈደረሽን ይሁን በሌላ መልክ

ከኢትዮጵያ ጋር መቀላቀል አለባት ይላሉ፡፡ የሚያነሱት የታሪካዊ ዝምድና

ነጥብ በአብዛኛው ትክክል ነው፡፡ አንዳንድ ኤርትራውያን ምሁራን ሳይቀሩ

ከአክሱም ሥልጣኔ ዘመን አንስቶ ሰፊ አሁን ኤርትራ ከሚባለው ቦታ

የኢትዮጵያ አካል እንደነበረ ይቀበላሉ፡፡

በኢትዮጵያውያን ምሁራን አቋም ያለው ችግር ከዚህ ታሪካዊ ሀቅ ብቻ

ተነስቶ ኤርትራ ለመገንጠል መብት የላትም ለማለት አዳጋች መሆኑ ነው፡፡

ታሪክ የተፈጸመውን ድርጊት ሁሉ ያቀፈ መዝገብ ነው፤ የተለያዩ ዓላማዎች

ወይም አቋሞች ለማራመድ ወይም ለመደገፍ የምንገለገልባቸው፡ ውጤት

ለ አእምሮ – Le'Aimero © | መንፈሳዊ ሐሳብ የአእምሮ ምግብ ነው !

ለ አእምሮ – Le'Aimero © | መንፈሳዊ ሐሳብ የአእምሮ ምግብ ነው !34

Page 36: ለ አእምሮ መጽሔት ቅጽ 1 ቁጥር 2 - LeAimero Vol 1 No 2

7/16/2019 1 2 - LeAimero Vol 1 No 2

http://slidepdf.com/reader/full/-1-2-leaimero-vol-1-no-2 36/61

ያስከተሉና ተፅዕኖ ያዘሉ ድርጊቶች አሉት፡፡ አንዳንዱ ድርጊቶች የረዱንና እና

በኩራት የምናስታውሳቸው ሲሆኑ፡ አንዳንዱ ደግሞ የማንወዳቸው፡ በሃዘንና

በህፍረት የምናስባቸው ናቸው፡፡

ኢትዮጵያንና ኤርትራን በተመለከተ ይህ ችግር አለ፡፡ እርግጥ ነው፡ በረጅሙ

ታሪካቸው ኢትዮጵያና ሰፊ የኤርትራ ክፍል አንድ ነበሩ፡፡ ነገር ግን

ባንወደውና ባንኰራበትም፡ ኤርትራ ከ19ኛው ክፍለ-ዘመን መጨረሻ 

አንስቶ ለ50 ዐመታት ያህል የኢጣልያ ቅኝ ግዛት እንደነበረችም ታሪክ

ነው፡፡ የጣልያን ዘመን ካበቃ በሁዋላ ፈደራሲዮን የተባለው አውታር

መቋቋምና መፍረስም ለራሱ ታሪክ ነበር፡፡ እነዚህ ድርጊቶች ታዲያየየራሳቸው ሚና ኖሮዋቸው፡ መፈታት ያለባቸው ጥያቄዎችና ችግሮች

አስከተለው ፈትነዉናል፤ ገናም እየፈተኑን ነው፡፡

የታሪክ ጥያቄ እንግዲህ ቀላል እንዳልሆነ መረዳት ያስፈልጋል፡፡ አስቀድሞ

እንደተጠቀሰው ኤርትራውያን የሁለቱን አገሮች ታሪካዊ ዝምድና ማወቅና

ማመን ሲገባቸው፡ ኢትዮጵያውያኑ ደግሞ ይህ የታሪክ ዝምድና ሁሉን

ጥያቄዎች የሚገዛ፡ የሁለቱን አገሮች አንድነት የሚያስገድድ አድርገው

ከማቅረብ መቆጠብ አለባቸው፡፡ አንዳንድ በታሪካዊ ጉዞአችን የደረሱትን

ድርጊቶች፡ የማንወዳቸውና የማንኮራባቸው ቢሆኑም፡ ችላ ልንላቸው

ትክክል አይደለም፡፡ ችላ በማለትም ችግሮችን አንፈታም፡፡ በተጨማሪም

ኤርትራ የተለያዩ ብሄረሰቦች ያቀፈች አገር ሆና፡ ትግርኛ ከሚናገረው

በስተቀር የተቀሩት – በተለይ ምዕራባዊው ወገን – ከታሪካዊት ኢትዮጵያጋራ የነበራቸው ዝምድና ላላ ያለና የተቆራረጠ (ኢንተርሚተንት) እንደነበረ

ማስታወስ ይገባል፡፡

- አንዳንድ ምሁራን አሁንም የችግሩ መፍትሄ የኢትዮጵያና ኤርትራ

ፈደራላዊ ውህደት ነው ይላሉ፡፡ በዚህ አቋማቸው ከታወቁት አንዱ የሆነው

ፕሮፈሰር ዳኒኤል ክንዴ፡ ከ2009 ዓ. ም. አንስቶ በሳን ሆዘ ዓመታዊስብሰባዎች ባቀረባቸው ፅሁፎችና በ2005 ዓ.ም. ባሳተመው መፅሀፍ

ይህንን ሃሳብ በሰፊው አብራርቶታል፡፡ የነዚህ ምሁራን አባባል ቅን በሆነ

ለ አእምሮ – Le'Aimero © | መንፈሳዊ ሐሳብ የአእምሮ ምግብ ነው !

ለ አእምሮ – Le'Aimero © | መንፈሳዊ ሐሳብ የአእምሮ ምግብ ነው !35

Page 37: ለ አእምሮ መጽሔት ቅጽ 1 ቁጥር 2 - LeAimero Vol 1 No 2

7/16/2019 1 2 - LeAimero Vol 1 No 2

http://slidepdf.com/reader/full/-1-2-leaimero-vol-1-no-2 37/61

መንፈስ የቀረበ ቢሆንም የኤርትራ ችግር አመጣጥን የዘነጋ ይመስላል፡፡

ምሁራኖቹ የችግሩ መንስዔዎች በአጼ ኃይለሥላሤ ጊዜ የተወሰዱት፡

በኤርትራ ላይ የህዝቡንና የአገሪቱን ክብር የደፈረ ሁኔታ የጫኑ፣

በመጨረሻም ፈደራሲዮኑን ያፈረሱ ኢዲሞክራስያዊ እርምጃዎችመሆናቸውን መርሳት የለባቸውም፡፡ ይህንን ለመረዳት “ የኤርትራ ጉዳይ ” 

የተሰኘውን የአምባሳደር ዘውዴ ረታ አንጋፋ ስራ መመልከት እጅግ

ይጠቅማል፡፡ አሁን ታዲያ ምሁራኖቹ የሁለቱን አገሮች ዝምድና አስመልክቶ

በሚያቀርቡት ሃሳብ ዲሞክራስያዊ የሆነ መንፈስና ዘይቤ መጠቀም

አለባቸው፡፡ አንድ ሉዓላዊነትን የሚሰርዝ ዕቅድ አማራጭ የሌለው መፍትሄ

ነው ብለው ድርቅ ማለት የለባቸውም፤ እንዲህ የመሰለ አቀራረብ አስፈሪ

ነው፤ ለመተማመንና ለትብብር አይረዳም፡፡ አሁን ባለው ሁኔታ ተግባራዊነት

ሊኖረው የሚችል ዝምድና በአንድ ኮንፈረንስ ክፍት ኮንፈደረሽን ብዬ

የገለጽኩት ነው፡፡ ይህ ማለት ሁለቱ ሉዓላዊ አገሮች በኮንፈደረሽን

ይዛመዱና፡ ከዚያ በሁዋላ ህዝቦቻቸው በሙሉ ፍላጎትና በሙሉ ነጻነት

ዝምድናቸውን በተመለከተ የፈለጉትን ለውጥ ሊያደርጉ ይችላሉ ማለት

ነው፡፡ ኮንፈደረሽኑ በጥንቃቄና ለሁለቱ ህዝቦች በሚጠቅም አኳሃን በተግባር

ሲውል ደግሞ ህዝቡን በበለጠ ሊያቀራርብ ብቻ ነው የሚችለው፡፡

ኮንፈደረሽኑ ክፍት የሚባልበት ሌላ ትርጉምም አለ፡፡ ኮንፈደረሽኑ

በኤርትራና በኢትዮጵያ ብቻ ተቋቁሞ የሚቀር አይደለም፡፡ ለሌሎች

የአፍሪቃ ቀንድ አገሮችም በሩ ክፍት ይሆናል፡፡ ሁኔታው በፈቀደ ጊዜ

ጂቡቲ፡ ሱዳን፡ ሶማሊያ ወዘተ… የዲሞክራሲ መርሆዎችን በተከተለ ሂደት

ኮንፈደረሽኑን ሊቀላቀሉ ይችላሉ፡፡ የኤርትራና የኢትዮጵያ ኮንፈደረሽን

ለአፍሪቃ ቀንድ ኮንፈደረሽን መነሾ ብቻ ይሆናል፡፡

- አንዳንድ ኢትዮጵያውያን ምሁራን የኢህአዲግን መንግስት ከመጥላትና

ለማስወገዱ ካላቸው ጉጉት የተነሳ፡ ኤርትራንና የኢሳያስን መንግስት

በሚመለከት የዋህ ወይም ገራገር የሆነ አቋም ይወስዳሉ፡፡ ለምሳሌ

የአስመራው መንግስት የመለስን መንግስት ለመጣል የሚረዳቸው

ለ አእምሮ – Le'Aimero © | መንፈሳዊ ሐሳብ የአእምሮ ምግብ ነው !

ለ አእምሮ – Le'Aimero © | መንፈሳዊ ሐሳብ የአእምሮ ምግብ ነው !36

Page 38: ለ አእምሮ መጽሔት ቅጽ 1 ቁጥር 2 - LeAimero Vol 1 No 2

7/16/2019 1 2 - LeAimero Vol 1 No 2

http://slidepdf.com/reader/full/-1-2-leaimero-vol-1-no-2 38/61

ይመስላቸዋል፤ ከዚያም አልፎ የአስመራው መንግስት በኢትዮጵያ አንድነት

የሚቈረቈር – እንዲያውም አንዳንዴስ የሁለቱን አገሮች ፌደራላዊ አንድነትን

የሚፈልግ – ሆኖ ሲቀርብ ይታለሉለታል፡፡ ከመሀከላቸው ኢሳያስ

አፈወርቅን በይፋ የሚመርቁም በአንድ ወቅት ብቅ ብለው ነበር፡፡ እነዚህምሁራን የነዚያ የኢህአዲግን መንግስት የሚወድሱ ኤርትራውያን

ተቃዋሚዎች ኢትዮጵያዊ ቅጂ ናቸው፡፡ የኤርትራውያኖቹ ውዳሴ-ኢህአዲግ

ለሁለቱ አገሮች ትብብር እንደማያገለግል ሁሉ፡ የኢትዮጵያውያኑ ሻዕቢያን

ማሞገስም አይረዳም፤ እንዲያውም ዕንቅፋት ይሆናል፡፡

- አንዳንድ ኢትዮጵያውያን ምሁራን ኢህአዲግን – በተለይ ህ.ወ.ሓ.ትን –የኤርትራ መሳርያ ወይም ለኤርትራ ጥቅም የቆመ አድርገው ያቀርቡታል፡፡

ይህ አባባል ሃቅነት የለውም፡፡ እርግጥ ነው በአቶ መለስ የሚመራው

ህወሐት (ኢህአዲግ) ኤርትራ እንድትገነጠል ሙሉ በሙሉ ተባበረ፣

እንዲያውም መገንጠሉን በማራመድ ላይ ተሳተፈ፡፡ ይህንን ያደረገው ግን

ለራሱ ጥቅም ብሎ ነው እንጂ ለኤርትራ ህዝብ አስቦ አይደለም፡፡ የኤርትራ

መገንጠል ኢትዮጵያ ውስጥ የብሄር ፖለቲካ ለማሰተጋባትና ለማጠናከር፣እንዲሁም ላንዳንድ የሩቅ ዓላማዎቹን መንገድ ለመጥረግ ለህወሓት አስፈላጊ

ነበር፡፡ ይህንን ጉዳይ ለመረዳት አቶ አብርሃም ያየህ “ የኤርትራ ረፈረንደምና  

ነፃነት አፈፃጸም ሲገመገም “ በሚል አርእስት በህዳር 1994 ወይም

ዲሰምበር 2001 የፃፈው አንቀፅ ያግዛል፡፡ ኤርትራ ውስጥ ከዚሁ

የተጠቀመና ገናም የሚጠቀም አካል ቢኖር አገሪቱን በኃይል ጨቁኖ እየገዛ

ያለ በኢሳያስ አፈወርቅ የሚመራው ቡድን ብቻ ነው፡፡ ስለዚህ የኤርትራን

ህዝብ ከኢህአዲግ ተጠቃሚ አድርጎ ማቅረብ ስህተት ብቻ ሳይሆን ጐጂም

ነው፤ ሁለቱን ህዝቦች ለማቀራረብ ለሚደረገው ጥረት ዕንቅፋት ይፈጥራል፡፡

- አንዳንድ ኢትዮጵያውያን ምሁራን በደርግ ዘመን እንደነበረው ሁሉ

በተግባር የኤርትራን አንድነት የሚፈታተን አቋም ያሰማሉ፡፡ የደርግ

መንግስት በ1987 ባወጣው ፖሊሲ ኤርትራን ወደ ሁለት ራስገዞች ከፋፍሎ

አንድነቷን ለማፍረስ ቃጣ፡፡ ይህ በፖለቲካ እንቅስቃሴ ተሰማርቶ የነበረውን

ለ አእምሮ – Le'Aimero © | መንፈሳዊ ሐሳብ የአእምሮ ምግብ ነው !

ለ አእምሮ – Le'Aimero © | መንፈሳዊ ሐሳብ የአእምሮ ምግብ ነው !37

Page 39: ለ አእምሮ መጽሔት ቅጽ 1 ቁጥር 2 - LeAimero Vol 1 No 2

7/16/2019 1 2 - LeAimero Vol 1 No 2

http://slidepdf.com/reader/full/-1-2-leaimero-vol-1-no-2 39/61

ኤርትራዊ አሳዘነ፤ ተቃውሞዉንም አጠነከረ፡፡ በአሁኑ ጊዜ አንዳንዴ

የምንሰማው ዓሰብና አከባቢዋ ለኢትዮጵያ ይሰጥ የሚል ክርክር የኤርትራን

አንድነት የሚፈታተን ነው፡፡ በፖለቲካ ተሳትፎ ያላቸው ኤርትራውያን

በኤርትራ አንድነት ቀናኢ ናቸው፤ በዚህ ከኢትዮጵያውያን አይለዩም፡፡ ከዚህጋር በተያያዘ አንድ ነገር ማስታወስ እወዳለሁ፡፡ በአንድ ወቅት በ40ዎቹ

ኤርትራን ወደ ሁለት የመክፈል ዕቅድ ነበር፤ በዚያን ጊዜ የተለያዩና፡ ተፃራሪ

አቋሞች የነበሯቸው የኤርትራ የፖለቲካ ፓርቲዎች በሙሉ ዕቅዱን

ተቃወሙት፡፡ እንዲያውም ፈደረሽን የሚለውን ነገር እንደ መሃከለኛ 

መፍትሄ ፓርቲዎቹ በሙሉ የተቀበሉት ኤርትራ እንዳትበታተን በማለት

ነበር፡፡ የኢትዮጵያ አንድነት በኤርትራውያን መከበር እንዳለበት ሁሉ፡

የኤርትራ አንድነትም በኢትዮጵያውያን መከበር አለበት፡፡

የኮንፈደረሽን ሃሳብ ቀርቦ እያለ ዓሰብ ለኢትዮጵያ ይሰጥ ብሎ መጠየቅ

የማያስፈልግ ብቻ ሳይሆን ከኤርትራ ጋር ዝምድና አለመፈለግን

የሚያመለክት ይመስላል፡፡ የሁለቱ አገሮች ኮንፈደረሽን ኢትዮጵያም

ኤርትራም ምፅዋን፡ ዓሰብን እና ሌሎች በቀይ ባህር ዳርቻ ያሉትን ወደቦችበሙሉ በእኩልነት ሊጠቀሙባቸው ያስችላል፡፡ ይህ ሲታወስ እንግዲህ

ዓሰብና አከባቢው ለኢትዮጵያ ይሰጥ ማለት ለብዙ ኤርትራውያን፡ ከኤርትራ

ጋር ምንም ዝምድና አንፈልግም፤ ዓሰብ ብቻ እጃችን ትግባ እንጂ

የተቀረችው ኤርትራ ገደል ብትገባም ግድ የለንም የሚል መልእክት

የሚያስተላልፍ መስሎ ይታያል፡፡ እውነቱን ለመናገር ይህ አባባል በጣም

አስቸጋሪ ነው፤ ምሁራኖቹ ራሳቸው አጥብቀው የሚከራከሩለት ታሪካዊ

ዝምድናን ሳይቀር የሚክድ ይመስላል!! ይህ ከባድ ዕንቅፋት መሆኑ

ኢትዮጵያውያን ምሁራን እነዲገነዘቡት ያስፈልጋል፡፡

- ብዙ ኢትዮጵያውያን፡ ምሁራንን ጨምሮ፡ ኤርትራን እንደ ሉዓላዊት ሃገር

የሚያውቁ መሆናቸውን ለመግለፅ ወይም ለማመልከት የቸገራሉ፤ ፈቃደኞች

ያለመሆናቸው በተለያየ መልክ ይመሰከራል፡፡ የዚሁ ችግራቸው መሰረት

የረፈረንደሙ ሂደት ትክክል አለመኖሩ ነው፡፡ አስቀድሞ እንደተጠቀሰው፡

ለ አእምሮ – Le'Aimero © | መንፈሳዊ ሐሳብ የአእምሮ ምግብ ነው !

ለ አእምሮ – Le'Aimero © | መንፈሳዊ ሐሳብ የአእምሮ ምግብ ነው !38

Page 40: ለ አእምሮ መጽሔት ቅጽ 1 ቁጥር 2 - LeAimero Vol 1 No 2

7/16/2019 1 2 - LeAimero Vol 1 No 2

http://slidepdf.com/reader/full/-1-2-leaimero-vol-1-no-2 40/61

ረፈረንደሙ በትክክል እንዳልተካሄደ ሀቅ ነው፡፡ እኔም ሂደቱ ልክ

እንዳልነበረ በወቅቱ በተለያዩ ፀሁፎች ገልጫለሁ፡፡ ረፈረንደሙ ትክክል

አይሁን እንጂ፡ አሁን የኤርትራ ከኢትዮጵያ መለየትና ሉዓላዊት ሃገር መሆን

ዕውነታ ሆኗል፡፡ ይህንን ዕውነታ አለመቀበል ተግባራዊነት የሌለው ብቻሳይሆን ለወደፊቱም ጦርነት ሊቀሰቅስ የሚችል አደገኛ አቋም ነው፡፡

ኢትዮጵያውያን ምሁራን፡ ምንም እንኳን ስለ ረፈረንደሙ ያላቸው ሂስና

ቅሬታ ትከክል ቢሆን፡ ይህንን ዕውነታ መቀበል አለባቸው፤ ከዚህ ዕውነታ

ሲነሱ ነው ከኤርትራውያን ጋር መግባባትና መተሳሰር እያበጁ ለሁለቱ

አገሮች ዝምድና ገንቢ አስተዋፅኦ ሊያደርጉ የሚችሉ፡፡

- ይህ የረፈረንደም ጉዳይ አንድ መሰረታዊ የሆነ አስተሳሰባችንን የሚመለከት

ነጥብ ያስታውሰኛል፡፡ በአንድ ስብሰባ ላይ ያጋጠመኝን ልንገራችሁ፡፡ ስለ

አገሮቻችን ዝምድና፡ ስለ ኮንፈደረሽን አስፈላጊነት ጨምሮ፡ ንግግር ካደረግሁ

በሁዋላ አንድ ኢትዮጵያዊ ወንድሜ ተነስተው ኮንፈደረሽን የሚባለው ነገር

አይጥመኝም፣ ምክንያቱም ኮንፈደረሽን ከኤርትራ ጋር መቀበል ማለት

የተካሄደውን ረፈረንደም ትከክል ነበር ብሎ ማፅደቅ ነውና ብለውተቃወሙኝ፡፡ ረፈረንደሙ ትክክል ባይኖርም የኤርትራ ሉዓላዊ ህላዌ

ዕውነታ ሆኗል፡ ከሚል ተነስቼ አስቀድሜ ከጠቀስኳት ነጥብ ጋር

የምትመሳሰል መልስ ሰጠሁ፡፡

ኮንፈደረሽን ከተቀበልን በ1993 ዓ. ም – ማለት ከ18 ዓመታት በፊት –

ያለአግባብ የተካሄደው ረፈረንደም ትክክል ነበር እያልን ነው ብሎኮንፈደረሽንን መቃወም ቱክረቱ ወደ ፊት ሳይሆን ወደ ሁዋላ የሆነ

አመለካከትን ያንጸባርቃል፡፡ የኮንፈደረሽን ሃሳብ ወደ ፊት ከሚያይ መንፈስ

መመዘንና መስተናገድ አለበት፡፡ በሌላ አነጋገር፡ ሁለቱ አገሮች ለወደፊቱ

እንዲጠነክሩና እንዲያድጉ፡ ህብረተሰቦቻቸውም እንዲበለፅጉ በማለት ነው

ኮንፈደረሽንን የምንደግፈው፡፡ ረፈረንደሙ ትክክል አለመኖሩን እያመንን

ቱክረቱ ወደ ፊት በሆነ መንፈስ ኮንፈደረሽንን እንቀበላለን፡፡ ብዙ ጊዜ

ያለፈውን ማወቅ አስፈላጊ የሚሆነው እኮ ችግሩንና የችግሩን አመጣጥ

ለ አእምሮ – Le'Aimero © | መንፈሳዊ ሐሳብ የአእምሮ ምግብ ነው !

ለ አእምሮ – Le'Aimero © | መንፈሳዊ ሐሳብ የአእምሮ ምግብ ነው !39

Page 41: ለ አእምሮ መጽሔት ቅጽ 1 ቁጥር 2 - LeAimero Vol 1 No 2

7/16/2019 1 2 - LeAimero Vol 1 No 2

http://slidepdf.com/reader/full/-1-2-leaimero-vol-1-no-2 41/61

ለመረዳት፡ ከተደረገው ጥፋት ለመማር እና የተፈጸመው አለአግባብነት

እንዳይደገም ለማረጋገጥ ነው እንጂ ስለ አንድ የአሁኑ ወይም የወደፊት

ጉዳይ አቋም ለመወሰን አይደለም፡፡

ኤርትራውያንና ኢትዮጵያውያን ምሁራን ባለፉት ዓመታት አሉታዊ

አስተዋጽኦ ለማድረግ ያስገደዱዋቸው ድክመቶች – ሞራላዊና ኣእምሮአዊ –

ማጤን ይገባቸዋል፡፡ድክመቶቻቸውን ሲያጤኑ ባሁኑ ወቅት አጋጥመዉን

ስላሉት ጥያቄዎች በእውነተኛነት፡ በቅንነትና በትህትና ተመራምረው

ችግሮቹን ለመፍታት በሚደረገው ጥረት አስተዋጽኦዋቸውን ሊያሳድጉ

ይችላሉ፡፡ በሁለቱ አገሮቻችን መሀከል የአሁኑ የዓለም ሁኔታ አስፈላጊ

የሚያደርገው፡ እንዲያውም የሚያስገድደው፡ ዝምድና እንዲዋቀር ዘዴዉን

በማፈላለግ ሃላፊነታቸውን በብቃት ሊወጡ ይችላሉ፡፡

ይህንን ለማድረግ እጅግ ሊያግዙ ከሚችሉት ነገሮች አንዱ የኢትዮጵያና

ኤርትራ የውይይት መድረኮች መቋቋም ነው፡፡ በዚህ መድረኮች ሃሳብ

ለሃሳብ ኤየተለዋወጡ ከርስ በርስ መማር ይቻላል፤ እንዲሁም በየጊዜው

እየተገናኙ በበለጠ ሲተዋወቁ መተማመኑ ያድጋል፤ ይህ መተማመንም

ለሁለቱ ህዝቦች መቀራረብ እጅግ ይረዳል፡፡

ይህንን ንግግር ወይም ሀተታ ከመደምደሜ በፊት አንድ ነጥብ ልጥቀስ፡፡

የኢትዮጵያና ኤርትራ የውይይት መድረኮች ዓላማን በተመለከተ ይዘቱፖለቲካ የሌለው ይሁን የሚሉ አንዳንድ ተንቀሳቃሶች – ምሁራን ጨምሮ –

አጋጥመውኛል፡፡ አንዳንዱማ ፈደረሽን፡ ኮንፈደረሽን የሚለው ክርክር

አይኑር፤ ግኑኝነቱ ባህላዊና ማህበራዊ ብቻ ይሁን ይላል፡፡ ይህ በመሰረቱ

የተሳሳተ አመለካከት ይመስለኛል፡፡ የችግሮቻችን ዋና መሰረት እኮ ፖለቲካ

ነው፡፡ ይህንን መረዳት ያስፈልጋል፡፡ ዋናው ችግራችን ወይም የችግራችን

መንስዔ ፖለቲካ በመሆኑ ሁለቱ አገሮች እንዴት ይቀራረቡ? እንዴት

ይዛመዱ? የሚለው ጥያቄ መሰረታዊ አስፈላጊነት አለው፡፡ ለምሳሌ እኔ

ለ አእምሮ – Le'Aimero © | መንፈሳዊ ሐሳብ የአእምሮ ምግብ ነው !

ለ አእምሮ – Le'Aimero © | መንፈሳዊ ሐሳብ የአእምሮ ምግብ ነው !40

Page 42: ለ አእምሮ መጽሔት ቅጽ 1 ቁጥር 2 - LeAimero Vol 1 No 2

7/16/2019 1 2 - LeAimero Vol 1 No 2

http://slidepdf.com/reader/full/-1-2-leaimero-vol-1-no-2 42/61

በበኩሌ፡ ብዙዎቻችሁ እንደምታውቁት፡ አስቀድሜም እንደጠቀስኩት፡

በአሁኑ ታሪካዊ ወቅት ለሁለቱ አገሮች ተገቢ (ኖርማል) የሆነ የሰላም

ጉርብትና በፖለቲካዊ ይዘቱ በሁለቱ አገሮች አንዳንድ አስተዳደርን

የሚመለከቱ ለውጦች ከተደረጉ በሁዋላ የሚዋቀር ኮንፈደረሽን ነው የሚልአቋም አለኝ፡፡ ዝምድናው ይህ ወይስ ሌላ ይሁን? ኮንፈደረሽንስ እንዴት

ይምጣ? ለዚሁ መሟላት ያለባቸው ቅድመ-ሁኔታዎችስ ምንና ምን ናቸው?

በሚሉትና በሌሎች ጥያቄዎች ልንለያይ እንችላለን፡፡ ፖለቲካ የሌለው

የኤርትራና ኢትዮጵያ የወዳጅነት ወይም የውይይት መድረክ የሚለው ሃሳብ

ግን አጉል ነው፤ ቅንነት ያለውም አይመስለኝም፡፡

ለህዝቦቻችን ጥቅም የማያስቡ፡ የህዝቦቻችን ትስስር የማይፈልጉ የውስጥና

የውጭ ኃይሎች አሉ፤ እነዚህ ኃይሎች ባለፉት ዓመታት በሁሉም ደረጃ 

ተባብረዋል፤ አሁንም እየተባበሩ ናቸው፡፡ ኃይልና ገንዘብ ስላላቸው ለህዝቦቹ

ሃቀኛ ትብብር ለሚጥሩት ምሁራን ዕንቅፋት ሊፈጥሩባቸው ይችላሉ፤ በዚህ

ረገድ የማይናቅ አቅም በሚያንጸባርቅ የድርሰትና የቅስቀሳ ስራ

የሚተባበሩዋቸው ምሁራንም አላጡም፡፡ ስለዚህም የሁለቱን ህዝቦች ትስስርለማጠናከር የሚሹ አትዮጵያውያንና ኤርትራውያን ምሁራን መተባበር

አለባቸው፡፡ ይህንን ለማድረግም በተለያየ መስክ መዛመድ፡ በተለያዩ

መድረኮች መገናኘትና መወያየት አለባቸው፡፡ ሃሳብ መለዋወጥ፡ ዕውቀት

ለማዳበር መተጋገዝ እና ገንቢ በሆነ ሂስ እየተራረሙ በአእምሮም በህሊናም

አብረው እንዲጐለብቱና እንዲያድጉ ያስፈልጋል፡፡

አንዳንዱ ምሁር፡ ኢትዮጵያዊም ኤርትራዊም፡ በሞራል ሲቀዘቅዝ፡

አንዳንዱም ሲወድቅ አስተውያለሁ፡፡ ለኔ እንደሚመስለኝ የሞራል ውድቀት

የሚመጣው ብዙውን ጊዜ ችግሮቹን – ታሪካቸውን ጭምር – ካለመረዳትና

ስለመፍትሄው በጥናት ላይ የተመሰረተ ራዕይ ካለመኖር ነው፡፡ ስለዚህ

አስቀድመው የተጠቀሱትንና ሌሎችን ድክመቶች አርመውና አስወግደው፡

ከላይ የተነሱትን ጥያቄዎችና ጉዳዮች በሚገባ አጥንተው፡ መፍትሄን

በተመለከተ ብሩህ ራዕይ ገንብተው፡ ያንን ራዕይ ለመተግበር ደግሞ

ለ አእምሮ – Le'Aimero © | መንፈሳዊ ሐሳብ የአእምሮ ምግብ ነው !

ለ አእምሮ – Le'Aimero © | መንፈሳዊ ሐሳብ የአእምሮ ምግብ ነው !41

Page 43: ለ አእምሮ መጽሔት ቅጽ 1 ቁጥር 2 - LeAimero Vol 1 No 2

7/16/2019 1 2 - LeAimero Vol 1 No 2

http://slidepdf.com/reader/full/-1-2-leaimero-vol-1-no-2 43/61

ሰትራተጂና ስልት በንቃትና በጥንቃቄ ሲቀይሱ መተማመኑ – ኦፕቲሚዝም

– ያጋግማል፤ እያደረም ይጠነክራል፣ ያድጋል፡፡ ብዙዎቻችን ታሪካችን

በብዙ ጐኖቹ ትብብራችንን ይፈቅዳል፣ የዓለም ሁኔታ ይህንኑ ያስገድዳል፣

ህዝቦቻችን ደግሞ ወንድማማችነታቸውን በተግባር አስመስክረዋል ብለንእናምናለን፡፡ እንዲህ ከሆነ ታዲያ የሁለቱ ሃገሮች ሁለ-ገብ ዝምድና

ተግባራዊነት ያለው ራዕይ መሆኑ ልንጠራጠር ይገባል?

የኢትዮጵያና የኤርትራ ምሁራን፡ ይህ ራዕይ እውን ይሆን ዘንድ፡ መተባበር

እንዲጀምሩ ወቅቱ ሃላፊነት እያሸከማቸው መሆኑ መገንዘብ አለባቸው፡፡

ዋቢ ጽሁፎች

- ጌታቸው ረዳ፤ ሓይካማ (ሳን-ሆዘ፡ ካሊፎርኒያ፤ ሃምሌ 2002 ዓ.ም በኢት.

አቈጣጠር)

- ዘውዴ ረታ፣ የኤርትራ ጉዳይ 1941 – 1963 ( አዲሰ አበባ፡ 1998 )

- አምሳሉ ገብረዝጊ ገብሩ፤ የኤርትራ መዘዝ (አዲስ አበባ፤ ጥር 2002 በ

ኢት. አቈ.)

- አንዳርጋቸው ጽጌ፤ ነጻነትን የማያውቅ “ ነጻ አውጭ ” (አዲስ አበባ፤ ጥር

1997)

- አብርሃም ያየህ፤ “ የኤርትራ ረፈረንደምና ነፃነት አፈፃ ጸም ሲገመገም “ ፤

(ህዳር 1994) ዲሰምበር 2001)

- ዳኒኤል ክንዴ፣ “ የኢትዮጵያና ኤርትራ ፌደረሽን አስፈላጊነት“ ፣ (ሳን ሆዘ

2009)

- Bahru Zewde, “The Intellectual and the State in

Twentieth Century Ethiopia”, in Harold G. Marcus

(ed.), New Trends in Ethiopian Studies (Papers of the

ለ አእምሮ – Le'Aimero © | መንፈሳዊ ሐሳብ የአእምሮ ምግብ ነው !

ለ አእምሮ – Le'Aimero © | መንፈሳዊ ሐሳብ የአእምሮ ምግብ ነው !42

Page 44: ለ አእምሮ መጽሔት ቅጽ 1 ቁጥር 2 - LeAimero Vol 1 No 2

7/16/2019 1 2 - LeAimero Vol 1 No 2

http://slidepdf.com/reader/full/-1-2-leaimero-vol-1-no-2 44/61

12 International Conference of Ethiopian Studies)

(Lawrenceville, NJ: The Red Sea Press, 1994).

- Daniel Kendie, The Five Dimensions of the Eritrean

Conflict 1941-2004: Deciphering the Geo-Political 

Puzzle (Gaithersburg, MD: Signature Book Printing,

Inc. 2005).

- Ghelawdewos Araia, Ethiopia: The Political 

Economy of Transition, (Lanham, Maryland:

University Press of America, 1995)

- Negussay Ayele, “Legitimacy, culture of political

violence and violence of culture in Ethiopia”, in Jean

E. Rosenfeld (ed.), Terrorism, Identity and 

Legitimacy: The Four Waves theory and political 

violence, (New York: Routledge, 2011)

- Paulos Milkias, Haile Selassie, Western Education

and Political Revolution in Ethiopia, (Youngstown,

New York: Cambria Press, 2006)

 _______________________________________________ 

- _ 

***  ይህ ፅሁፍ ለማንኛውም ውይይትና ተችት ክፍት ነው ::

————————————————————————————

ሕግ፥ነክ ማስታወሻዎች / Disclaimer & Legal Statements > Le’Aimero’s Disclaimer 

th

ለ አእምሮ – Le'Aimero © | መንፈሳዊ ሐሳብ የአእምሮ ምግብ ነው !

ለ አእምሮ – Le'Aimero © | መንፈሳዊ ሐሳብ የአእምሮ ምግብ ነው !43

Page 45: ለ አእምሮ መጽሔት ቅጽ 1 ቁጥር 2 - LeAimero Vol 1 No 2

7/16/2019 1 2 - LeAimero Vol 1 No 2

http://slidepdf.com/reader/full/-1-2-leaimero-vol-1-no-2 45/61

********

**********************************

Posted in ማህበራዊናማህበራዊናማህበራዊናማህበራዊና ፖለቲካፖለቲካፖለቲካፖለቲካ /Social & political, ባህላዊናባህላዊናባህላዊናባህላዊና ማህበራዊማህበራዊማህበራዊማህበራዊ /Cultural & social, ታሪክናታሪክናታሪክናታሪክና ባህልባህልባህልባህል, ነፃነፃነፃነፃ

አስተያየትአስተያየትአስተያየትአስተያየት/Free Opinions | Leave a reply

ተዋጊተዋጊተዋጊተዋጊ ሮቦታሮቦታሮቦታሮቦታ / Robot

Posted on May 16, 2013

ተዋጊ ሮቦታ

በጋሻና በጦር ፣ በፈረስና በበቅሎ፣ አባቶቻችን የጦር ሜዳ ወጥተው ድልአድርገው ይገቡ ነበር። ጫማ እንኳን ለእግራቸው አልነበራቸውም። ባርኔጣ

ለእራስ ቅላቸው፣ የብረት ሰደሪያ ለደረታቸው፣ ትጥቅና ስንቅ እንኳን

አባቶቻችን፣ ከበሶና ከጭብጥ ቆሎ ሌላ በድንብ የተዘጋጀ፣ ጎተራም

በየቦታው አልነበራቸውም። ያላቸውና የነበራቸው ጠንካራ ወኔ ብቻ ነበር።

አሁን ዘመኑ ለጦረኞች እና ለጦር መሪዎች፣ መሣሪያዎቹ ሁሉ ተቀይረዋል።እንዲያውም አዲስ የተከፈተውን ውይይት በደንብ ከአዳመጥን፣ የቴክኒኩ

ጉዞ ሌላ ደረጃ ላይ ደርሶአል።

የሮበተር ወታደሮችና እነሱ የሚያዙአቸው የሮበተር አጋሰሶች፣ ወደፊት

ለዓለም ጸጥታ የእንግለዙ መምህር፣ ፕሮፌሰር ኑኤል ሻርኪ፣ እንደሚሉት፣

አደገኛ ናቸው።

„ሒውማን ራይትስ ወች“ የሚባለው ለሰው ልጆች መብት፣ መከበር በዓለም

ዙሪያ የሚሟገተውም ድርጅትም፣ ከምሁሩ ጋር አብሮ ሁኖ ፣ አደጋውን

ተመልክቶ፣ ይህ ጉዞ ፣ ዝም ተብሎ መታየት የለበትም፣ ብሎ የትግል

ጥሪውን፣ ለሕዝብ፣ ማሰማት ጀምሮአል።

ለ አእምሮ – Le'Aimero © | መንፈሳዊ ሐሳብ የአእምሮ ምግብ ነው !

ለ አእምሮ – Le'Aimero © | መንፈሳዊ ሐሳብ የአእምሮ ምግብ ነው !44

Page 46: ለ አእምሮ መጽሔት ቅጽ 1 ቁጥር 2 - LeAimero Vol 1 No 2

7/16/2019 1 2 - LeAimero Vol 1 No 2

http://slidepdf.com/reader/full/-1-2-leaimero-vol-1-no-2 46/61

„ደር ሽፒግል“ የሚባለው የጀርመኑ ሳምንታዊ መጽሔት፣ እንደዘገበው፣

ወይዘሮ ጁዲ ዊሊያምስ፣ የሰላም ኖቤል ሽልማት አሸናፊ፣ ትግሉ ወስጥ

ዘለው አብረው፣ ገብተዋል።

አለአብራሪ በአየር ላይ እየከነፈ፣ የጠላትን፣ ምንደርና ምሽግ፣ በቦንብ

የሚደበድበውን አይሮፕላን፣ ቢያንስ፣—ተቃዋሚዎቹ እንደሚሉት፣ አንድ፣

እሱን ቢሮ ውስጥ ተቀምጦ ትዕዛዝ የሚሰጠውና የሚመራው ፣ ሰው

ከጀርባው፣ ቢያንስ አለ።

እራሱን ችሎ ግን፣ ድንበር አቋርጦ፣ የጠላት መንደር፣ በኮምቲውተሩ

መነጽሩ፣ እየተመራ፣ በጥይት፣ ሆነ …በመርዝ ሜዳውን እያጸዳ፣ ወደፊት

የሚሄደውን ፣ “ ዘመናው የሮበተር ወታደር ወይም አጋሰስ“፣ እሱን

የሚያዘው የሚቆጣጠረው፣ ሰው፣ ከጀርባው የለም። እንዲያውም ይህን

በማድረጉ፣—እነሱ እንደሚሉት፣ ለሮበተሩ ሥራ፣ እንበል ደም በማፍስስ

ወንጄሉ፣ ተጠያቂ ክፍልም ወደፊት የለም።

ተሳስቶ ነው፣ ተበላሽቶ ነው፣ ሊሉም ይችላሉ። አናውቀውም ብለውም

የሮበተሩን ባለቤትነታቸውን ሊክዱም፣ ይችላሉ። አንድ አገር ወታደር ከሕግ

ውጭ የሆነ ፍጅት፣ በአንድ ሕዝብ ላይ ቢያደርስ፣ ያን ወታደር የላከው

መንግሥት በዓለም አቀፍ ሕግ ና ደንብ መሰረት፣ ተከሶ፣ ፍርዱን ይቀበላል።

አንድ ሮቦታን በሰራው ሥራ ማን ፍርድ አቅርቦት እሱን ይፋረደዋል?

እንደተነበበው አሜሪካኖቹ፣ አካባቢዉን በመነጽሩ እየቃኘ፣ በጥይትም፣የጠላትን መንደር እየጠረገ ወደፊት፣ የሚጓዝ ሮበትር ሰርተው አውጥተዋል።

ችግሩ ይህ ሮበተር ፊት ለፊቱ የቆመው ጠላት፣ ይሁን ወዳጅ፣ ያ ሰው በእጁ

መዶሻ ይያዝ ወይም ሽጉጥ፣ ሁለቱን አመዛዝኖ መለየት ስለማይችል፣ ቀደም

ብሎ ተኩሶ ደረቱን ብሎ፣ እነሱ እንደሚሉት ሰውዬውን ሊገለው ፣ ይችላል።

ከዚሁ ጉድ፣ ከሮቦተሩ ጋር የሚዛመደው፣ ድሮን የሚባለው አይሮፕላንናጣቢያውም በገራችን ባርባ ምንጭ አካባቢ ተተክሎ፣ የሚሠራውንና

ለ አእምሮ – Le'Aimero © | መንፈሳዊ ሐሳብ የአእምሮ ምግብ ነው !

ለ አእምሮ – Le'Aimero © | መንፈሳዊ ሐሳብ የአእምሮ ምግብ ነው !45

Page 47: ለ አእምሮ መጽሔት ቅጽ 1 ቁጥር 2 - LeAimero Vol 1 No 2

7/16/2019 1 2 - LeAimero Vol 1 No 2

http://slidepdf.com/reader/full/-1-2-leaimero-vol-1-no-2 47/61

የሚያስሰውን፣ የሚያውቅ የኢትዮጵያም ባለሥልጣን የለም! ሮቦቱም አንድ

ቀን ይከተል ይሆናል። ባለ ስልጣኑም ዛሬውኑ ሮቦት ሆኗል ካልተባልን!

የታሪኩ ሞራል ምኑ ላይ ነው? …ጊዜው ተቀይሮአል…ጊዜው አእምሮ

ይጠይቃል!

© ለ አእምሮ 2005 / © Le’Aimero Copyright 2013

Posted in ማህበራዊናማህበራዊናማህበራዊናማህበራዊና ፖለቲካፖለቲካፖለቲካፖለቲካ /Social & political | Leave a reply

በሥልጣንበሥልጣንበሥልጣንበሥልጣን መባለግመባለግመባለግመባለግ! ለምሳሌለምሳሌለምሳሌለምሳሌ በቱርክበቱርክበቱርክበቱርክ አገርአገርአገርአገርPosted on May 16, 2013

በሥልጣን መባለግ! ለምሳሌ በቱርክ አገር

ጠግበው ማለት እንችላለን ፣ የሚቆጣቸው ሰው ምን ያድርጉ ጠፍቶ፣ የቱርክ

ሸንጎ አባሎች፣ ከዚያ የደረሰን ዜና እንደሚለው፣ „ ዕድሜ ልክ ድረስ

የሚቆይ መብትና ጥቅም ለእነሱ ብቻ ለማስከበር“ የተለያዩ የፖለቲካ

ድርጅት አባሎች፣ በጋራ ተነስተዋል።

በቀይ መብራት ላይ መኪናቸው፣ እንደማንኛውም ተራ ሰው፣ሕጉን አክብሮ

እንዳይቆም፣ አነሱ፣ አንካራ ላይ ጠይቀዋል። ግን እንዴት አድርገው?

ቀይ የዲፕሎማቲክ መታወቂያ ወረቀት (ፓስፖርት) ያላቸው፣ የሸንጎአባሎች፣ “ሱድ ፣ ዶቸ ሳይቱንግ „ የተባለው የጀርመኑ ዕለታዊ ጋዜጣ እዚህ

እነደጻፈው፣ እነሱ „እያውለበለቡ ከቀረቡ፣ በቀይ መብራት ላይ ሌሎቹ፣

ሲያቆሙ የእነሱ መኪና ትራፊኩን አቋርጦ፣ መሄድ፣ እንዲፈቀድላቸው „

ጠይቀዋል።

ሌላስ የሚመኙት ነገር አለ?

ለ አእምሮ – Le'Aimero © | መንፈሳዊ ሐሳብ የአእምሮ ምግብ ነው !

ለ አእምሮ – Le'Aimero © | መንፈሳዊ ሐሳብ የአእምሮ ምግብ ነው !46

Page 48: ለ አእምሮ መጽሔት ቅጽ 1 ቁጥር 2 - LeAimero Vol 1 No 2

7/16/2019 1 2 - LeAimero Vol 1 No 2

http://slidepdf.com/reader/full/-1-2-leaimero-vol-1-no-2 48/61

ሽጉጥ፣ ጠበንጃ፣ እና ከባድ መሣሪያ ለመያዝ ከፈለጉ ደግሞ፣ የቱርክ አገር

ጋዜጣዎች እንደጻፉት፣ „ዕድሜ ልካቸው ድረስ ይህን እንደፈለጉት፣

እንዲሰበስቡና እንዲያከማቹ የሚፈቅድላቸው፣ አንድ ልዩ ፈቃድ፣ ለሁሉም

የሸንጎ አባሎች“ ቀጥለው፣ ጠይቀዋል።“

ይህንን እና ሌሎች ምኞታቸውን የሚያረካላቸውን የሕግ አርቃቂ ቡድን

ከመካከላቸው ከመረጡ ወዲህና ፣ ተራው ሕዝብ ጆሮ ውስጥ ነገሩ ከገባ ጊዜ

ጀምሮ ደግሞ፣ አሁንስ አበዙት የሚሉ ሰዎች ቁጥር፣ በቱርክ እየተበራከተ

መጥቶአል። እንዲያውም፣ መሳቂያ ና መቀለጃ፣ አሻንጉሊቶች፣ ጋዜጣዎች

እንደአሉት፣ እነሱ በገዛ እጃቸው፣ አሁን ሁነዋል።

„በሚቀጥለው ሕይወቴ፣ እንደገና ከተወለድኩ“—አንዲት የቤት እመቤት

ለሚመለከተው ሰው ሁሉ ብላ በአናፈሰቺው ትዊተር፣ ላይ፣ እሷ—

„….አለጥርጥር የሸንጎ ኣባል፣ የሕዝብ እንደራሴ ለመሆን እፈልጋለሁ!…

እሆናለሁ!“ ብላም፣ እኛ እዚህ እንዳነበብነው፣ ይህች ሴትዮ ፎክራለች።

አኛም መሆን እንፈልጋልን ብለው፣ አንዳዶቹ፣ ድርጅት መፍጥር ጀምረዋል።

የአንድ ጋዜጣ ሐተታ ጸሓፊ፣ ይህማ፣ አሁን ፖለተከኞቹ የሚያነሱት ጥያቄ፣

ዱሮ ጥለነው የሄድነው „የአንድ የጠገበ ሱልጣን ሕግ ነው“ ብሎ ተቆጥቶ፣ ያ

ጸሓፊ፣ እዚያው ላይ አከታትሎ ፣ ጀርመኖች ተርጉመው እዚህ ለእኛ 

እንደአስቀመጡት፣ „ምንአለበት እግረመንገዳችሁን፣ ኃጢአታችሁን ከላያችሁ

ላይ አጥባችሁ የምታራግፉበት፣ አንድ የሐማም፣ የሙቀት ጢስ፣ መታጠብያ

ቤት፣ በመንግሥት ገንዘብ እንዲሰራላችሁ አብራችሁ ማመልከቻችሁን፣

አሰገቡ፣ ብታስገቡም ይጠቅማችሁዋል“ ብሎ፣ ይኸው ፣ጸሐፍ

ቀልዶባቸዋል።

የሕዝብ እንደራሴዎቹ የጠየቁት ጥያቄ፣ ለእራሳቸው ብቻ ሳይሆን ምን

አለበት ፣ ዘመዶቻቸውን ፣ ቤተሰቦቻቸውንም ቢጨምር፣ መልካም ነው። ያ

ቢሆን እንዴት ጥሩ ነበር ብሎ አንዱ፣ ተንኮለኛ ጋዜጠኛ፣ በሌላ ቦታ

በአምዱ ላይ እነሱን መክሮአቸዋል።።

ለ አእምሮ – Le'Aimero © | መንፈሳዊ ሐሳብ የአእምሮ ምግብ ነው !

ለ አእምሮ – Le'Aimero © | መንፈሳዊ ሐሳብ የአእምሮ ምግብ ነው !47

Page 49: ለ አእምሮ መጽሔት ቅጽ 1 ቁጥር 2 - LeAimero Vol 1 No 2

7/16/2019 1 2 - LeAimero Vol 1 No 2

http://slidepdf.com/reader/full/-1-2-leaimero-vol-1-no-2 49/61

እንደ አነበብነው፣ እነሱም አስበውበት „በእርግጥ ለክፉም ለደጉም „ብለው፣

በተለይ በቀዩ የዲፕሎማቲክ ፓስፖርት፣ ቤተሰቦቻቸው፣ በሙሉ በዚያ

መታወቂያ ወረቀት፣ ቀይ፣የትራፊክ መብራቱን ጥሰው እንዲንቀሳቀሱ፣

„የቤተሰብ፣ ልዩ ፈቃድ „ ጠይቀዋል። ብልጦች ስለሆኑም የቱርክ የሸንጎአባሎች፣ ይኸው „ሱድ ዶቸ ሳይቱንግ“ የተባለው ጋዜጣ፣ ሰሞኑን እዚህ

እንደጻፈው፣ ያንን ልዩ ቀይ ፓስፖርት ለዕድሜ ልክ፣ እንደገና ፓርላማም፣

ውስጥ ተመልስው፣ በሕዝቡም ተመርጠው ባይገቡም፣ እንዲሰጣቸው

ጥይቀዋል።

መቀለጃ እየሆኑ የመጡትን የሸንጎ አባሎች ጥያቄ፣ አስተካክላለሁ ብለው፣

የፓርላመው ፕሬዚዳንት፣ የሰነዘሩት ቃል፣ የባሰ ነገሩን አተረማምሶ፣ ሌላ

ቦታ፣ እነሱን አሁን፣ ከቶአቸዋል።

ሚስተር ቸሚል ቺቼክ፣ የፓርላማው ፕሬዚዳንት፣ „ ይህ አሁን የታሰበው

አዲስ ሕግ“ በእሳቸው ዓይን “ … በተለያዩ ቦታዎችና አንቀጾች ሥር፣

ተበታትነው የሚገኙትን ደንቦች ሰብሰብ አድርጎ አንድ ላይ ለማስቀመጥ ነው

„ ብለው የተቆጣውን ሰው ለማረጋጋት የወረወሩት አነጋገር፣ ሌሎቹን፣

ተራውን ሰው፣ የባሰ ነገር ውስጥ ከቶአል።

እነሱን ብቻ ሳይሆን በተለይ የተለያዩ የቱርክን ጋዜጣ አዘጋጆችና

ጸሓፊዎችን፣ ነገሩ ዕብድ እዚህ እንደጻፈው፣ አድርጎታል። ጎልጉለው

አንዳዶቹ፣ በየሦስት ወሩ ፣ ማለት በአመት አራት ጊዜ፣ የአመት

ደመወዛቸውን፣ በአንዴ የሚቀበሉትን የሸንጎ አባሎች፣ የሒሳብ አከፋፈል

ብዙዎቹ አንስተው፣ ተገቢ አይደለም ብለው፣ በቅጠሎቻቸው ላይ፣

ተችተዋል።

እንደዚህ ከሆነማ „ ጸሓይ ስትወጣ ፣ በጥሩ አየር፣ ምግባቸውን በመሶብ፣

ከብር ስልቻ ጋር፣ ደጃፋቸው ላይ አሰቀምጠን ፖለቲከኞቻችንን „ አንድ

ተንኮለኛ ሠዓሊ“፣ እናስደስታቸው „ የሚለውን ሐሳቡን፣ ቱርክ ውስጥ

አሰራጭቶአል።

ለ አእምሮ – Le'Aimero © | መንፈሳዊ ሐሳብ የአእምሮ ምግብ ነው !

ለ አእምሮ – Le'Aimero © | መንፈሳዊ ሐሳብ የአእምሮ ምግብ ነው !48

Page 50: ለ አእምሮ መጽሔት ቅጽ 1 ቁጥር 2 - LeAimero Vol 1 No 2

7/16/2019 1 2 - LeAimero Vol 1 No 2

http://slidepdf.com/reader/full/-1-2-leaimero-vol-1-no-2 50/61

„የቁንጅና ቀዶ-ጥገናም፣ አብሮ“ ነጻ የሕክምና ወጪ በመንግሥት ሒሳብ ፣

የሚሰጣቸው ከሆነ፣ „…አብሮ እንዲሰጣቸው“ አንድ ፣ የተቃዋሚ ጋዜጣ

ጠይቆአል።

አንድ የብሔራዊ ፓረቲ አባል ሚስተር ኡቻን ይንቸሪ፣ ሳይቸግራቸው

የተናገሩት ቃል ፣ ጀርመኖች እንድጻፉት፣ ቱርኮችን አበሳጭቶአል። „ …

ፖለሶች አቁመውን በፍጥነት ትከንፋላችሁ ብለው እኔንና ሹፌሬን፣ መንጃ 

ፈቃዳችሁን አሳዩን ብለው የስጨነቁንን ነገር እኔ፣ ምንም ጊዜ፣

አልረሣውም። ቀይ ፓስፖርት ቢኖረን ይህ ሁሉ ነገር አይድርስብንም ነበር።“

ሰውዬው ያሉት አሁንም ድረስ ሰውን አስቆጥቶአል።

አሁን በመኪና አደጋ የሚሞቱ ሰዎችን ጉዳይ የሚከታተል አንድ ድርጅት

ተጠሪ እንደአሉት፣ „ የሸንጎ አባሎቹ እንደፈለጉት በቀይ መብራት መክነፍ

ወደፊት የመያመጣው አደጋ ቀላል አይሆንም ብለው፣ „ ሰውዬው

አስጠንቅቀዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚንስተሩን፣ ሽንጎው፣ ውስጥ የተቀመጡ ፣ ተቃዋሚዎቹም

ሆኑ ሥልጣኑን ፣ አሁን የጨበጡት ድርጅቶች ተጠሪ፣ ሁሉም በጋራ በአዲሱ

ሕግ ላይ መስማማታቸው፣ ነገር ግን ፣ ሕጉ በአስቸኳይ እንዳይተላለፍ ፣

ማዝገማቸው፣ ሰውዬውን፣በጣም አድረጎ አስገርሞአቸዋል።

አሁን ሁሉም ይንጫጫል እንጂ፣ ነገ ዞር ብሎ ሕጉን፣ ቢተላለፍ የሚቃወም

የለም የሚሉ አንድንድ ፖለቲከኞች፣ አልጠፉም የሚሉም ሰዎች እዚህ አሉ።ባጠቃላይ ሲታይ ግን ብዙዎቹ የሕዝብ እንደራሴዎቹ፣ ኃይለኛ ስጋት ውስጥ

–ጀርመኖቹ እንደጻፉት፣ እነሱ አሁን ስጋት ውስጥ ገብተዋል።

አንድ የግራው ክንፍ ድርጅት ተጠሪ፣“…እኔ ስለ አዲሱ ሕግ፣ ይዘትና

መልዕክት ምን እንደሆነ ምንም የማውቀው ነገር የለም።… እኔ አብዛኛውን

ጊዜ ከፓርላማው ውጭ፣ ከሕዝቡ ጋር በገጠር ጊዜዬን አጠፋለሁ“ ያለውን

ለ አእምሮ – Le'Aimero © | መንፈሳዊ ሐሳብ የአእምሮ ምግብ ነው !

ለ አእምሮ – Le'Aimero © | መንፈሳዊ ሐሳብ የአእምሮ ምግብ ነው !49

Page 51: ለ አእምሮ መጽሔት ቅጽ 1 ቁጥር 2 - LeAimero Vol 1 No 2

7/16/2019 1 2 - LeAimero Vol 1 No 2

http://slidepdf.com/reader/full/-1-2-leaimero-vol-1-no-2 51/61

አነጋገር፣ ዘጋቢው፣ ለእኛ እንደጻፈው እሱንም ቢሆን የሚያምነው፣ ሰው

የለም።

„የእኛን መብት እንደፈለጉት፣ ፖለቲከኞቹ እንደፈለጉት፣ ይሽሩታል ፣

ይቀይሩታል። ለእራሳቸው ሲሆን ግን፣ ለእነሱ እነደሚያመች አድርገው፣

እንደ ግልቤታቸው የሕዝብና የመንግሥት ሀብትን እንደፈለጉት“፣ አንድ

የሠራተኛው ማህበር ተጠሪ እንዳለው፣ ሕግ አውጥተው፣ „ይዘርፉታል።“

አንዱ ቀልደኛ እኔ ጥሩ መፍትሔ አለኝ ብሎ፣ ብቅ ብሎአል። በእሱ እምነት 

መድሓኒቱ፣ ቱርክ ለገባችበት ችግር መፍትሔው፣ አንድ ነገር ብቻ ነው። 

 „የሕዝብ እንደራሴዎቹ ቁጥር በሸንጎ ውስጥ ከፍ ይበል“  ይላል።  „አሁን 

 ፓርላማ ውስጥ ከአሉት 550 አባሎች ፋንታ፣ ቁጥራቸው፣ ትንሽ ስለሆነ፣ 

ከፍ ብሎ፣ 75 ሚሊዮን እንዲሆኑም  „  ይጠይቃል።  „ችግራችን ያኔ 

 ይፈታል“ ብሎም ግምቱን ሰንዝሮአል። 

———————

© ለ አእምሮ 2005 / © Le’Aimero Copyright 2013

Posted in ሌሎችሌሎችሌሎችሌሎች / others | Leave a reply

የባንክየባንክየባንክየባንክ ዘረፋዘረፋዘረፋዘረፋ በበበበ21ኛውኛውኛውኛው ክፍለክፍለክፍለክፍለ-ዘመንዘመንዘመንዘመን!

Posted on May 16, 2013

የባንክ ዘረፋ በ21ኛው ክፍለ-ዘመን!

ወንበዴዎቹ የመጡት፣ ፖሊስ እነዳለው፣ እንደተለመደው፣ ጨለማን ተገን

አድርገው አይደለም። … በጠራራ ጸሓይ በቀን ነው። እንደዱሮ፣ ፊታቸውን

ተሸፋፍነው „በሽጉጥ እጅ ወደላይ፣ ብለው አስፈራርተው …ገንዘቡን፣

አንዲት ኮሮጆ ውስጥ እንዲጨምሩ የባንክ ሠራተኞቹን አላስጨነቁም።

እንገላለን ብለውም፣ እነሱን አላስፈራሩም። “እነደ ሃያኛው ክፍለ-ዘመን

ሌቦች እንደ ፍልፈል ግማሽ አመት የፈጀ ረጅም ቱቦ ውስጥ ውስጡን

ለ አእምሮ – Le'Aimero © | መንፈሳዊ ሐሳብ የአእምሮ ምግብ ነው !

ለ አእምሮ – Le'Aimero © | መንፈሳዊ ሐሳብ የአእምሮ ምግብ ነው !50

Page 52: ለ አእምሮ መጽሔት ቅጽ 1 ቁጥር 2 - LeAimero Vol 1 No 2

7/16/2019 1 2 - LeAimero Vol 1 No 2

http://slidepdf.com/reader/full/-1-2-leaimero-vol-1-no-2 52/61

ቆፍረው፣ ከታች የባንኩን ካዝና ስብረው ገብተው በጥቁር መኪና

አላመለጡም።

እነዚህ እሳት የላሱ ሌቦች፣ (ቁጥራቸው በደንብ አይታወቅም) የሰሩት ሥራ

ቀላል ነው። እንደ የሆቴል ቤት በር መክፈቻ ፣ ዘመናዊ ካርድ፣ የማግኔት

መስመር ካርዳቸው ላይ፣ ለጥፈው፣ በየባንኩ መግቢያ በር ግድግዳ ላይ፣

ተገትረው ፣ የተሰጣቸውን ትዕዛዝ ተቀብለው፣ ብር የሚተፉትን ቁም

ሳጥኖች፣ ፖሊስ እንዳለው፣ ጠቅጠቅ እያደረጉ፣ እንደ ከረሜላ ጎርፍ፣ አንድ

በእንድ፣ ያስነጥሱአቸው ጀመር።

ከአንዱ የባንክ ግድግዳ ወደ ሌላው እየተሳሳቁ፣ የጀርባ ሻንጣቸውን

እየከፈቱና እየዘጉ የሚሄዱትን ጎረምሳዎች የተማለከቱ ሰዎች እንዳሉት ከሆነ፣

በኒዮርክ ከተማ ብቻ፣ ወደ ሦስት ሺህ ከሚጠጉ የገንዘብ አውቶማቶች፣

ወረበሎቹ፣ ሁለት ሚሊዮን አራት መቶ ሺህ ዶላር ፣ እየቆጠሩ፣ ኪሳቸው

ውስጥ አስገብተዋል።

አሁን እንደተደረሰበት፣ እነሱ ብቻቸውን አልነበሩም። በሃያ ስድስት የተለያዩ

አገሮችና ከተማዎች ፣ ግብረ አበሮቻቸው ተሰማርተው፣ በአደረጉት

ተመሳሳይ የባንክ አዉቶማት ዘረፋ፣ አርባ አምስት ሚሊዮን ዶላር፣

ጠራርገው፣ ሊሰወሩ ችለዋል። ይህም፣ዝርፊያ „ትልቁ የሳይብር ባንክ ዘረፋ

በ21ኛው ክፍለ-ዘመን „ የሚባለውን ስም አትርፎአል። በጠቅላላው

እየተዝናኑ፣ ወደ 36 ሺህ የሚጠጉ ካዝናዎችን ለመጠራረግ፣ አሥር ሰዓት

ብቻ እንደፈጀባቸው፣ ፖሊሶች ተናግረዋል። የጥጋባቸው ብዛት፣ አንድ

ካርድ፣ በቀን ማውጣት የሚፈቀድለትን ገደብ ሰብረው፣ ጭንቅላቱን

አዙረው፣ እንደፈለጉት እንዲታዘዝ፣ አድርገዋል።

ታሪኩ ረጅም ነው። የታሪኩ ሞራል ምኑ ላይ ነው?

እኛ መልሰን እንደገና የምንተርክበት፣ ምክንያት፣ እንኳን ፖለተከኛ፣ሌባውም የስርቆት ብልሃቱን ቀይሮአል ለማለት ነው። ጊዜው አ እምሮ 

ለ አእምሮ – Le'Aimero © | መንፈሳዊ ሐሳብ የአእምሮ ምግብ ነው !

ለ አእምሮ – Le'Aimero © | መንፈሳዊ ሐሳብ የአእምሮ ምግብ ነው !51

Page 53: ለ አእምሮ መጽሔት ቅጽ 1 ቁጥር 2 - LeAimero Vol 1 No 2

7/16/2019 1 2 - LeAimero Vol 1 No 2

http://slidepdf.com/reader/full/-1-2-leaimero-vol-1-no-2 53/61

 ይጠይቃል! እንዳው ለማስታወስ ያህል፣ አጤ ምንልክና አባቶቻችንም

የጣልያን ጦርን ያሸነፉት ጦር ሜዳ ላይ፣ በጋሻና ጦር ብቻም አለነበረም።

ዘመናዊ አውሮፓ ውስጥ ዓይነተኛ ሚና መጫወት የጀመረውን፣

የሚዲያ /Medial power/ ሃይልንና የህዝብ ግንኙነትንም በመገልገልነበር።

አዎ ! ጊዜው ለአ እምሮ ነው ! ጊዜው እንዳው ሃይ በለው ሳይሆን፣ ጥበብን

ብልህነትን፣ አዙሮና አገለባብጦ ማስተዋልን፤ አዎ! የሚያገናዝብ አእምሮን

ይጠይቃል። ካንባ ባሻገር፣ አንባ ገነን እስካልሆኑ ድረስ!

————

© ለ አእምሮ 2005 / © Le’Aimero Copyright 2013

Posted in ሌሎችሌሎችሌሎችሌሎች / others, ማህበራዊናማህበራዊናማህበራዊናማህበራዊና ፖለቲካፖለቲካፖለቲካፖለቲካ /Social & political, ሳይንስናሳይንስናሳይንስናሳይንስና ቴክኖሎጂቴክኖሎጂቴክኖሎጂቴክኖሎጂ/Science &

Technology | Leave a reply

“በኢንቨስትመንትበኢንቨስትመንትበኢንቨስትመንትበኢንቨስትመንት ስምስምስምስም የሚፈጸምየሚፈጸምየሚፈጸምየሚፈጸም የመሬትየመሬትየመሬትየመሬት ነጠቃ፤ነጠቃ፤ነጠቃ፤ነጠቃ፤በኢትዮጵያበኢትዮጵያበኢትዮጵያበኢትዮጵያ” ጥናትጥናትጥናትጥናት

Posted on May 16, 2013

ከአዱሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን) የተገኘ 

ሰነድ፥

ለባለቤቶቹ  ለባለቤቶቹ  ለባለቤቶቹ  ለባለቤቶቹ ከ ከከ ከ አክብሮት አክብሮት አክብሮት አክብሮት ምስጋና  ምስጋና  ምስጋና  ምስጋና ጋር፣  ጋር፣  ጋር፣  ጋር፣ ጥናቱን ጥናቱን ጥናቱን ጥናቱን አንባቢዎች  አንባቢዎች  አንባቢዎች  አንባቢዎች በጽሞና  በጽሞና  በጽሞና  በጽሞና ያገናዝቡ ያገናዝቡ ያገናዝቡ ያገናዝቡ ዘንድ ዘንድ ዘንድ ዘንድ - ለ ለለ ለ አእምሮ አእምሮ አእምሮ አእምሮ መጽሔት መጽሔት መጽሔት መጽሔት -  ላይ ላይ ላይ ላይ ታትሟል ታትሟል ታትሟል ታትሟል! 

***

“በኢንቨስትመንት ስም የሚፈጸም የመሬት ነጠቃ፤ በኢትዮጵያ”

ጥናት ትርጉም ይፋ ሆነ!!

ሰነዱን ለማውጣት፣ ፈቃድን በሚመለከት ከአዱሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ

(አኢጋን) የተገኘ ማሳሰቢያ ፥

ለ አእምሮ – Le'Aimero © | መንፈሳዊ ሐሳብ የአእምሮ ምግብ ነው !

ለ አእምሮ – Le'Aimero © | መንፈሳዊ ሐሳብ የአእምሮ ምግብ ነው !52

Page 54: ለ አእምሮ መጽሔት ቅጽ 1 ቁጥር 2 - LeAimero Vol 1 No 2

7/16/2019 1 2 - LeAimero Vol 1 No 2

http://slidepdf.com/reader/full/-1-2-leaimero-vol-1-no-2 54/61

“… የጋራ ንቅናቄያችን ጽሁፉን የማሰራጨቱ ስራ በጨዋነት፣ ለጽሁፉ ባለቤቶች (ለእንግሊዝኛው

የኦክላንድ ተቋም ለአማርኛው ደግሞ አኢጋን) አስፈላጊውን እውቅና በመስጠት እንዲሆን በዚህ

አጋጣሚ አበክረን እንሳስባለን። ከመሬት ነጠቃ በላይ የከፋ ወንጀል የለም። ዜጎችን በምድራቸው ወደ

ባርነት የሚያሸጋግረው የመሬት ነጠቃ የአገሪቱን ሃብትና ንብረት እየበላ ነው። ይህንን ወደር የሌለው

ወንጀል ለማጋለጥ፣ ለመታገል፣ ለመቃወምም ሆነ ተዛማጅነት ያላቸው ተግባራት ለማከናወን

ለሚፈልጉ ተቋማት፣ ግለሰቦችና ሚዲያዎች ይረዳ ዘንድ (Land Grab –

http://landgrabsmne.wordpress.com/) የሚባል ብሎግ እንዲሁም በፌስቡክ Land

Grab/መሬት ነጠቃ መከፈቱን ለማሳወቅ እንወዳለን። በቅርቡ የሚሻሻለው ይህ ብሎግና የፌስቡክ

ገጽ ከመሬት ወረራ ጋር በተያያዘ ሁሉም ዓይነት ማስረጃዎች የሚታተሙበት ስለሚሆን መረጃ 

ለሚፈልጉ ወገኖች ሁሉ መልካም አጋጣሚ ይሆናል። ጥናታዊ ዘገባውን ከድረገጻችን ላይ ለማግኘት

እዚህ ላይ ይጫኑ፡፡ በኢሜይል ለማግኘት የሚፈልጉ በሙሉ በሚከተለው አድራሻ 

([email protected]  ) ቢጠይቁን በቀጥታ የምንልክ መሆናችንን

እናሳውቃለን፡፡”

ሙሉውን ለማንበብ የሚከተለውን ይጫኑ፥

Land-Grab-smne press release

“በኢንቨስትመንት ስም የሚፈጸም የመሬት ነጠቃ፤ በኢትዮጵያ” ጥናት

ትርጉም “ ፥

Understanding Land Investment Deals in Africa (Ethiopia)

———————————————————

———————————————————

ሕግ፥ነክ ማስታወሻዎች / Disclaimer & Legal Statements > Le’Aimero’s Disclaimer 

Posted in ሌሎችሌሎችሌሎችሌሎች / others, ማህበራዊናማህበራዊናማህበራዊናማህበራዊና ፖለቲካፖለቲካፖለቲካፖለቲካ /Social & political, ባህላዊናባህላዊናባህላዊናባህላዊና ማህበራዊማህበራዊማህበራዊማህበራዊ /Cultural & social, ነፃነፃነፃነፃ

አስተያየትአስተያየትአስተያየትአስተያየት/Free Opinions, አዳዲስአዳዲስአዳዲስአዳዲስ ሰነዶችሰነዶችሰነዶችሰነዶች/የጥናትየጥናትየጥናትየጥናት ወረቀቶችወረቀቶችወረቀቶችወረቀቶች/Documents | Leave a reply

እኛምእኛምእኛምእኛም አለንአለንአለንአለን ሙዚቀኛ፣ሙዚቀኛ፣ሙዚቀኛ፣ሙዚቀኛ፣ ልብንልብንልብንልብን የሚያቃናየሚያቃናየሚያቃናየሚያቃና / ዶክተርዶክተርዶክተርዶክተር

አሸናፊአሸናፊአሸናፊአሸናፊ ከበደከበደከበደከበደ

Posted on May 15, 2013

ዶክተርዶክተርዶክተርዶክተር አሸናፊአሸናፊአሸናፊአሸናፊ ከበደ፣ከበደ፣ከበደ፣ከበደ፣

ለ አእምሮ – Le'Aimero © | መንፈሳዊ ሐሳብ የአእምሮ ምግብ ነው !

ለ አእምሮ  Le'Aimero © | መንፈሳዊ ሐሳብ የአእምሮ ምግብ ነው !53

Page 55: ለ አእምሮ መጽሔት ቅጽ 1 ቁጥር 2 - LeAimero Vol 1 No 2

7/16/2019 1 2 - LeAimero Vol 1 No 2

http://slidepdf.com/reader/full/-1-2-leaimero-vol-1-no-2 55/61

በኢትዮጵያበኢትዮጵያበኢትዮጵያበኢትዮጵያ ካሉትናካሉትናካሉትናካሉትና ከነበሩትከነበሩትከነበሩትከነበሩት የሙዚቃየሙዚቃየሙዚቃየሙዚቃ አዋቂዎችአዋቂዎችአዋቂዎችአዋቂዎች ውስጥ፣ውስጥ፣ውስጥ፣ውስጥ፣ ከፍከፍከፍከፍ ብለውብለውብለውብለው የሚታዩየሚታዩየሚታዩየሚታዩ ናቸው።ናቸው።ናቸው።ናቸው።

http://en.wikipedia.org/wiki/Ashenafi_Kebede

*

የሚከተሉትየሚከተሉትየሚከተሉትየሚከተሉት ዶኩመንታሪዶኩመንታሪዶኩመንታሪዶኩመንታሪ ተንቀሳቃሽተንቀሳቃሽተንቀሳቃሽተንቀሳቃሽ ስዕሎችስዕሎችስዕሎችስዕሎች ያስተዋውቁናል።ያስተዋውቁናል።ያስተዋውቁናል።ያስተዋውቁናል።

ከከከከ ኢቲቪኢቲቪኢቲቪኢቲቪ / ETV፣፣፣፣ ዩዩዩዩ ትዩብትዩብትዩብትዩብ ድረ፣ድረ፣ድረ፣ድረ፣ ገጽገጽገጽገጽ ላይላይላይላይ የተገኘ፣የተገኘ፣የተገኘ፣የተገኘ፣ ለደራሲዎቹለደራሲዎቹለደራሲዎቹለደራሲዎቹ ከመስጋናከመስጋናከመስጋናከመስጋና ጋር፤ጋር፤ጋር፤ጋር፤ 1)

****************

Ethiopia – Dr. Ashenafi Kebede – Ethiopian

Conductor & ethnomusicologist : Part 1/4

Dr. Ashenafi Kebede – Ethiopian conductor &

ethnomusicologist : Part 2/4

http://www.youtube.com/watch?v=U-cN-QQc4Ss

Dr. Ashenafi Kebede – Ethiopian conductor &

ethnomusicologist : Part 3/4

http://www.youtube.com/watch?v=JSKrTxuvmJI

Dr. Ashenafi Kebede – Ethiopian conductor &

ethnomusicologist : Part 4/4

http://www.youtube.com/watch?v=wq6Sg-KSDno

***************************************

ለለለለ አእምሮአእምሮአእምሮአእምሮ መጽሔት፣መጽሔት፣መጽሔት፣መጽሔት፣ ወደወደወደወደ ዋናውዋናውዋናውዋናው ገጽገጽገጽገጽ ለመመለስለመመለስለመመለስለመመለስ…………………..

ለ አእምሮ – Le'Aimero © | መንፈሳዊ ሐሳብ የአእምሮ ምግብ ነው !

ለ አእምሮ – Le'Aimero © | መንፈሳዊ ሐሳብ የአእምሮ ምግብ ነው !54

Page 56: ለ አእምሮ መጽሔት ቅጽ 1 ቁጥር 2 - LeAimero Vol 1 No 2

7/16/2019 1 2 - LeAimero Vol 1 No 2

http://slidepdf.com/reader/full/-1-2-leaimero-vol-1-no-2 56/61

***

አድራሻችን ፥ Public Email

አስተያየት እንዲሁም ለአእምሮ መጽሔት ጥናቶችና ጽሁፎች ለማበርከት ፥ የሚከተለውን አድራሻ ይገልገሉ፥

Public Email

[email protected]

Verified Services

leaimero.com

—————————————————————————————————————————

ሕግ፥ነክ ማስታወሻዎች / Disclaimer & Legal Statements:- Le’Aimero’s Disclaimer 

1) እነዚህን ስዕሎች እዚህ በመውጣታችን የባለቤትነት መብታችሁን ከተላለፍን፣ እንድናነሳው እንዳስታወቃችሁን እንሰርዘዋለን!

***************************************

*

Posted in ሌሎችሌሎችሌሎችሌሎች / others, ኪነ፥ጥበብኪነ፥ጥበብኪነ፥ጥበብኪነ፥ጥበብ | Leave a reply

ILLICIT FINANCIAL FLOWS

FROM AFRICA

Posted on May 12, 2013

ILLICIT FINANCIAL

FLOWS FROM AFRICA:

ለ አእምሮ – Le'Aimero © | መንፈሳዊ ሐሳብ የአእምሮ ምግብ ነው !

ለ አእምሮ – Le'Aimero © | መንፈሳዊ ሐሳብ የአእምሮ ምግብ ነው !55

Page 57: ለ አእምሮ መጽሔት ቅጽ 1 ቁጥር 2 - LeAimero Vol 1 No 2

7/16/2019 1 2 - LeAimero Vol 1 No 2

http://slidepdf.com/reader/full/-1-2-leaimero-vol-1-no-2 57/61

Share this:

 About ለለለለ አእምሮአእምሮአእምሮአእምሮ / Le'Aimeroአሳታሚው፥ ይልማ ኃይለ ሚካኤል - Publisher:- Yilma Haile Michael, Journalist

 View all posts by ለ አእምሮ / Le'Aimero →

ILLICIT FINANCIAL FLOWS FROM AFRICA: HIDDEN RESOURCE FOR DEVELOPMENT

Posted on May 12, 2013

ILLICIT FINANCIAL

FLOWS FROM AFRICA:

HIDDEN RESOURCE FOR DEVELOPMENT

illicit-capital-flow 

ሕግ፥ነክ ማስታወሻዎች / Disclaimer & Legal Statements > Le’Aimero’s Disclaimer

This entry was posted in ሌሎች / others, ኢኮኖሚና ማህበራዊ. Bookmark the permalink.

ለለለለ አእምሮአእምሮአእምሮአእምሮ – Le'Aimero © 

ለለለለ አእምሮአእምሮአእምሮአእምሮ – Le'Aimero © 

Theme: Twenty Ten Blog at WordPress.com.

ILLICIT FINANCIAL FLOWS FROM AFRICA: HIDDEN RESOURCE FOR DEVELOPMENT | ለ አእምሮ – Le'Aimero ©

ILLICIT FINANCIAL FLOWS FROM AFRICA: HIDDEN RESOU...

Page 58: ለ አእምሮ መጽሔት ቅጽ 1 ቁጥር 2 - LeAimero Vol 1 No 2

7/16/2019 1 2 - LeAimero Vol 1 No 2

http://slidepdf.com/reader/full/-1-2-leaimero-vol-1-no-2 58/61

የክንፎቹን ምስል፣ 

ለመታያችን - ለመለያችን፣ ለምን ይሆን የመረጥነው! 

መቃ - ብዕር  ወይም  የአሞራ ወይም ደግሞ  የአውራ ዶሮ ይሁን የ እርግብ ላ ባ፣ ከቀለም 

ብልቃጥ  ጋር  አንድ  ላይ፣  እነዚህ  ሁለቱም፤  ሶስቱም  ነገሮች፣  የቀለም  ሰዎች  ሙያ… 

የጸሓፊዎችና  የደራሲዎች፣  ወይም  ደግሞ፣  ሁላችንም   እንደምናውቀው፣  የጋዜጠኛ 

ምልክቶች 

ናቸው። 

እኛም  አሳታሚዎቹ መርጠን የወሰድነው  ምልክት፣ በአንድ በከል ሲታይ ከዚሁ ጋር፣ 

በትክክል ለመናገር  በጥብቅ የተያያዘም ነው። 

* እንደ ምልክት ፣ ሳያውቁም ሆነ አውቁው እንደስቀመጡት አርማ ቁልጭ ያለች ማብራሪያ ለዚያች ጉዳይ፣ በአሀኑ ሰዓት፣ የሚሰጥ ነገር የለም። 

መቼም አንድ አርማ  ፣ ለአንድ አሳታሚ የግል ድርጅት  ሆነ፣  ወይም ደግሞ አንድ አላማ 

ለአለውና ለሚከተል፣  ለዚያ የፖለቲካ ፓርቲ፣…ነጋዴም ሊሆን ይችላል፣….እሱ መርጦ፣ እንደ ተሸከመው፣ ግንባሩ ላይ እንደ ለጠፈው አርማ ፣ ያ ድርጅት ማን መሆኑን በትክክል የሚያሳይና የሚገልጽ ወይም አለቃላት የሚያብራራ፣ ሌላ ነገር ፣ በዚህ ዓለም ላይ የለም። 

የጀርመኑ  ማርቼዲስ  ፣…  ወይም  አውዲ፣  ቢኤም  ደብሊው፣ወይም  …ቮልክስ  ቫገን፣ 

የእንግሊዙ፣  ወይም  የጀርመኑ  ሮልስ  ሮይስ፣  ….የጃፓኑ  ቶዮታ፣  የፈረንሳዩ  ስትሮዋን፣ 

ወይም  ፔጆ….እነዚህ  ሁሉ  መርጠው  የያዙት  ምልክቶች፣…  ለመኪናዎቹ  ጥራት፣ 

ለጥንካሬአቸው፣…ለክብራቸው፣ ብዙም ማውራት  የማያስፈልጋቸው፣ ማንነታቸው፣ ማን መሆኑን የሚገልጹበት አርማዎች ናቸው። 

„ማጭድና መዶሻ  „ ምንም እንኳን እንደምናውቀው፣ የላብ አደሩና የገበሬው አንድነትን፣ 

ሕብረትን  የሚገልጹ ቢሆንም፣ ዞሮ ዞሮ ከአለፉት ታሪኮች እንደተማርነው፣  የጥቂት „እኛ  ለእናንተ  የምትፈልጉትን፣  የሚስማማችሁን  ነገር ሁሉ፣  እኛ  ብቻ፣  እናውቃላችሁዋለን  „ 

የሚሉ ፣ „ጤናማ ይሁኑ ወይም ዕብዶች፣… ምሁሮች፣ ወይም ወታደሮች“  ምልክት ሁኖ 

Page 59: ለ አእምሮ መጽሔት ቅጽ 1 ቁጥር 2 - LeAimero Vol 1 No 2

7/16/2019 1 2 - LeAimero Vol 1 No 2

http://slidepdf.com/reader/full/-1-2-leaimero-vol-1-no-2 59/61

እንደቀረ  ፣ ሁላችንም ከዚህ ሁሉ አመት በሁዋላ፣ ከቀመስናቸው ግንዛቤዎች፣ ልምዶች፣ 

በደንብ አድርገን፣ ዛሬ  እናውቃለን። 

እንዲያውም ይህ ምልክት በሰሜን ኮሪያና በቻይና ብቅ ያሉ ብልጦች እንደሚያስተምሩን 

ከሆነ  ደግሞ፣  የዘርግንዱ  ሳይነካ  እንደ  ዘውድ  አገዛዝ  ሥልጣኑ  ከልጅ  ልጅ  ወደታች መስመሩን ጠብቆ በቀጥታ በ21ኛው ክፍለ ዘመን የሚተላለፍበት „የዙፋን ምልክት ነው።“ ስለ ዘውድና ዙፋን ከአነሳን አይቀር፣ እነሱ እንኳን ሳይቀሩ ከጊዜውጋር ተራምደው፣ ቢያንስ 

በጃፓን፣… በስዊዲን ፣ በዴንማርክ፣ በኒዘርላነድና በእስፔን…ከሥልጣን ርቀው ለሰብዓዊ መብቶች መከበርና  ፣ ለዲሞክራሲ ሥርዓት ያላቸው አመለካከት፣ አስተያየትና አክብሮት፣ 

„አብዮተኛ   ነኝ ብሎ  ከሚፎክረው  የአፍሪካ ተራማጅ፣  ኮሚኒሰት“  በስንትና  ስንት ኪሎ ሜትር፣  እነሱ  አጣፍተውት፣  እንደሚሄዱ  አሁን  መናገሩና  ማውራቱ፣  ለእኛ   ከንቱ 

ነው።  የእንግሊዞቹማ፣ ነገሥታት ነገሩ ገብቶአቸው፣ ሥልጣኑን ከአስረከቡ፣ ጊዜው በጣም 

ረጅም ነው። 

„ዘውድ“ ሆነ „ማጭድና መዶሻ  „ጊዜው አልፎባቸል። የሚከተላቸውም ሰው አሁን የለም። 

ግን ! ጠበንጃና  ዘንባባ፣  የስንዴ  ነዶና  ዝናር፣  ቀለሃና ድግን መትረየስ፣  እነሱ ምልክቶች 

ደግሞ ምንድናቸው?

አትታለሉ! እነሱም፣ ሌላ ነገር ይምሰሉ እንጂ፣ የጥቂት አምባገነን፣ ምልክቶች ናቸው። 

ታዲያ እኛ  የመረጥነው የአሞራ ክንፍ፣ ወይም የዶሮ ይሁን የዕርግብ ላባ፣ የለም፣ እንዳውም 

የአማልክት  ክንፍ፤  ወይም  ደግሞ፣  መቃ  ብዕር፣  እሱ  ምንድነው? ምን  ለማለት? ምን 

ለማሳየት ተፈልጎ ነው?

ይህ መርጠን  እኛ   የወስደነው  አርማ፣  በሁለት መንገድ፣  በሁለት  አቅጣጫ፣  „የመንፈስ 

ቅዱስ“ ምልክት ነው። 

በአንድ በኩል ከእኛ  ከሰው ልጆች በላይ የሆነ (የሰው ልጅ ዕውቀት ውስን  ነው) አንድ -

እናንተ  የፈለጋችሁትን  ስም ልትሰጡት ትችላላችሁ- ከእኛ   አእምሮ  በላይ  የሆነ፣  የበለጠ 

ጥልቅ ያለው፣  ዕውቀት ያለው፣ ቅዱስ አምላክ፣…. መንፈስ ቅዱስ ከእኛ  በላይ አለ ለማለት ነው። 

ሁለተኛው  ትርጉም፣  የተለያዩ  አስተሳሰቦችና  አመለካከቶች፣  እምነቶችና  አቋሞች፣ የሚቀያየሩ  ዝንባሌዎችና  ግምቶች  ፣  የሚፎካከሩ  እኔ  እሻላለሁ  የሚሉ  አማራጭ መፍትሔዎች፣  አንዱ  ተነስቶ  ሌላውን  በሰይፍና  በብረት  አሳዶ  ሳያጠፋውና  ሳያንቀው፣ 

ተቻችለው፣ ተከባብረው፣ ተደማማጠው፣ ተወቃቅሰው፣ ተማምረው፣….አብረው ሊኖሩ 

ይችላሉ፣ የሚለውን „ቅዱስ ሐሳብ፣ ቅዱስ ተመክክሮ…ቅዱስ መንፈስ፣…“ በእኛ  መካከል ለማራመድም ነው። 

Page 60: ለ አእምሮ መጽሔት ቅጽ 1 ቁጥር 2 - LeAimero Vol 1 No 2

7/16/2019 1 2 - LeAimero Vol 1 No 2

http://slidepdf.com/reader/full/-1-2-leaimero-vol-1-no-2 60/61

በሌላ  ቋንቋ፣  የማንንም  ሰው  ነጻ፣  የሆነውን…  የመናገር፣…  የመቃወም፣…የመተቸት፣ 

የመመራመር፣ የመጠየቅ፣ የመምረጥና የመመረጥ፣ የመጻፍ፣…. ሐሳቡን የመቀየርና ሐሳቡን 

የማስተማር ሆነ  የማስራጨት ሙሉ መብቱን፣  ነጻነቱን  - ማንንም  ሳይፈራና  ሳያጎበድድ፣ 

ኮርቶ፣ በዚህ በያዝነው በ21ኛው ክፍለ-ዘመን፣ ሊተነፍስ ይችላል የሚለውን ሐሳብ፣ በዚህ 

አእምሮ በሚባለው መጽሔት፣ ለማብሰር ነው። 

ኢትዮጵያ  እራሱዋ  ወዳና  ተስማምታ፣  አንዳዶቻችን  ሳንፈጠር፣  ገና  ዱሮ  የፈረመችው 

የሰብዓዊ መብት አዋጅ ግሩም የሆነ ነገር አሰቀምጦልናል። እሱም:- ባርነትን ይከለክላል። “ 

„…ማንም ሰው፣ በባርንት ወይም …በግዴታ አገልጋይነት አይያዝም!“ ይላል። „ በሕግ 

ፊት ማንም ሰው፣ መብቱ የታወቀ  ነው..“ ቀጥሎ ይላል። ወረድ ብሎ  „….ማንም ሰው 

አስተያየት  የመስጠትና  ሐሳቡን  የመግለጽ  ነጻነትና  መብት  አለው፤“  ይላል።  „የሕሊናና 

የሃይማኖት  ነጻነቱን፣  ….የንብረት  ባለቤትነት  መብቱን፣….የመሰብሰብ፣  የመማርና 

የመመራመር መብቱን ፣ይኸው መግለጫ ጠቅሶ፣ በአንቀጽ አንዱ ላይ፣“ የሰው ልጆች ሁሉ በነጻነታቸው፣ በክብራቸውና በመብቶቻቸው እኩል ሆነው የተፈጠሩ ናቸው።“ ይላል። 

እኛ  በዚህ መጽሔት ሙሉ ሰብዓዊ መብታችንን ፣ ሙሉ ሰብዓዊ ነጻነታችንን፣ ከዛሬ ጀምሮ እንደማንኛውም ነጻ ሰው አውጀናል። 

Page 61: ለ አእምሮ መጽሔት ቅጽ 1 ቁጥር 2 - LeAimero Vol 1 No 2

7/16/2019 1 2 - LeAimero Vol 1 No 2

http://slidepdf.com/reader/full/-1-2-leaimero-vol-1-no-2 61/61