From the Chairman File - MIDROC...4 MIDROC Newsletter Volume 14, Issue # 76 March — April 2014...

8
1 Addis Ababa, Ethiopia Volume 14, Issue No. 76 March — April 2014 u¨<eØ Ñ뉋” Inside Pages 4 4 4 4 4 4 A BI-MONTHLY PUBLICATION OF THE OFFICE OF THE CHIEF EXECUTIVE OFFICER This Newsletter provides customers, employees, suppliers, shareholders and the community at large with current information on major performance and other activities of the companies under the leadership of the CEO ወ/ሮ ትርሲት አጐናፍር እኚህ ነበሩ ዶ/ር አረጋ ሽልማቱን ሲቀበሉ While Signing MoU From the Chairman File The MIDROC Ethiopia Investment Group has enormous challenges to endure, therefore, my very simple message to all my companies is “put forth brilliant & continuous effort, and be innovative for real success.” Innovation and creativity both play important role in the success of any business. Unity University Signs Memorandum of Understanding with Addis Ababa University ሚድሮክ ኢትዮጵያ ግሩፕ ከኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አገልግሎት ድርጅት የዕውቅና የምሥክር ወረቀት ተሸለመ ዶ/ር አረጋ ይርዳው የቦርድ ሰብሳቢ ሆነው በድጋሚ ተመረጡ ወ/ሮ ትርሲት አጎናፍር ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ 2 3 3 4 የሲኢኦ ቢሮ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ከኩባንያዎች........5 የሠርቪስ አገልግሎት በአሊያንስ ትራንስፖርት................6 ሬይንቦ ኩባንያ ንግድ ትርዒት ላይ ተሳተፈ....................6 በወልድያ በሁዳ ሪል እስቴት የሚገነባው ስታዲየም........7 Arabic News in Short........................................... መልዕክት½ ከቺፍ ኤግዚኪዩቲቭ ኦፊሰር........................8

Transcript of From the Chairman File - MIDROC...4 MIDROC Newsletter Volume 14, Issue # 76 March — April 2014...

Page 1: From the Chairman File - MIDROC...4 MIDROC Newsletter Volume 14, Issue # 76 March — April 2014 Addis Ababa, Ethiopia ወ/ሮ ትርሲት አጎናፍር ከዚህ ዓለም በሞት

1Addis Ababa, Ethiopia

Volume 14, Issue No. 76 March — April 2014

u¨<eØ Ñ뉋”

Inside Pages

4

4

4

4

4

4

A BI-MONTHLY PUBLICATION OF THE Office Of the chief executive OfficerThis Newsletter provides customers, employees, suppliers, shareholders and the community at large with current information

on major performance and other activities of the companies under the leadership of the CEO

76

ወ/ሮ ትርሲት አጐናፍር እኚህ ነበሩ ዶ/ር አረጋ ሽልማቱን ሲቀበሉ

While Signing MoU

From the Chairman File

The MIDROC Ethiopia Investment Group has enormous challenges to endure, therefore, my very simple message to all my companies is “put forth brilliant & continuous effort, and be innovative for real success.” Innovation and creativity both play important role in the success of any business.

Unity University Signs Memorandum of Understanding with Addis Ababa University•ሚድሮክ ኢትዮጵያ ግሩፕ ከኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አገልግሎት ድርጅት የዕውቅና • የምሥክር ወረቀት ተሸለመዶ/ር አረጋ ይርዳው የቦርድ ሰብሳቢ ሆነው በድጋሚ ተመረጡ• ወ/ሮ ትርሲት አጎናፍር ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ•

2

3

34

የሲኢኦ ቢሮ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ከኩባንያዎች........5 የሠርቪስ አገልግሎት በአሊያንስ ትራንስፖርት................6

ሬይንቦ ኩባንያ ንግድ ትርዒት ላይ ተሳተፈ....................6

በወልድያ በሁዳ ሪል እስቴት የሚገነባው ስታዲየም........7 Arabic News in Short...........................................መልዕክት½ ከቺፍ ኤግዚኪዩቲቭ ኦፊሰር........................8

Page 2: From the Chairman File - MIDROC...4 MIDROC Newsletter Volume 14, Issue # 76 March — April 2014 Addis Ababa, Ethiopia ወ/ሮ ትርሲት አጎናፍር ከዚህ ዓለም በሞት

2

MIDROC NewsletterVolume 14, Issue # 76 March — April 2014

Addis Ababa, Ethiopia

Unity University Signs Memorandum of Understanding with Addis Ababa University

Unity University (UU) signed Memorandum of Understanding

(MoU) with Addis Ababa University (AAU) on May 30, 2014,

at the Senate Hall of Addis Ababa University. The MoU

was signed by Dr. Admassu Tsegaye, President of Addis

Ababa University and Dr. Arega Yirdaw, President of Unity

University and CEO, MIDROC Ethiopia in the presence of

academic and administrative officials of the universities.

Speaking on the occasion, Dr. Admassu Tsegaye expressed

the pleasure in signing the MoU with Unity University,

which he said is, “The renowned and pioneer private higher

education institution”. Dr. Admassu pointed out that AAU

has an enrolment of over 50,000 students, of which the

graduate students number over 14,000. In this connection,

he underlined that AAU has strong desire to work closely

with other institutions of higher learning to meet the

challenges of meeting the needs of all these students.

He said, “Although we are the senior in providing higher

education in the country, we still have some gaps, which

we need to fill by working closely with private institutions of

higher learning.”

Going into areas of cooperation, the President underlined

that student exchange, exchange of academic staffs and

undertaking joint research activities are some among many

areas of cooperation. He further noted, “To this end, we

need to first adequately examine and utilise local resources

before seeking external assistance. Therefore, we are

sincerely grateful to Unity University for the step in this

direction. The idea was in our minds for quite some time;

and we are glad it has now become a reality. The signing

of this MoU is only the first step; and the detailed actions

will follow.”

Speaking on his part, Dr. Arega Yirdaw, President of Unity

University, expressed his pride over and the respect for

the senior Addis Ababa University, which he said, “Is

what made us what we are today. As such, we dare not

compare ourselves with Addis Ababa University. However,

we will humbly learn and gain a lot by working with it.” He

strongly reiterated the need to exhaustively engage locally

before looking outward too. In this regard he said, “We

do not find it appropriate to look for foreign cooperation

before taking advantage of such a renowned University

right at our doorsteps.” Further, Dr. Arega made note of the

advantage Addis Ababa University would draw from Unity.

He underlined that “Unity, being a member of MIDROC

Ethiopia Technology Group Companies, would facilitate for

Addis Ababa University to meet its need to work with the

industrial sectors. Hereby fulfilling its needs for the private-

public relationship.”

Dr. Admassu Tsegaye and Dr. Arega Yirdaw while signing Memorandum of Understanding

Page 3: From the Chairman File - MIDROC...4 MIDROC Newsletter Volume 14, Issue # 76 March — April 2014 Addis Ababa, Ethiopia ወ/ሮ ትርሲት አጎናፍር ከዚህ ዓለም በሞት

3

MIDROC NewsletterVolume 14, Issue # 76 March — April 2014

Addis Ababa, Ethiopia

ሚድሮክ ኢትዮጵያ ግሩፕ ከኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አገልግሎት ድርጅት የዕውቅና የምሥክር ወረቀት ተሸለመ

የሚድሮክ ኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ኩባንያዎች በአገሪቱ የባህር ማጓጓዣ አገልግሎት በላቀ ሁኔታ ተጠቃሚ በመሆናቸው በተገነባው ጠንካራ የሁለትዮሽ የሥራ ግንኙነት ከኢትዮጵያ የባህር ትርንስፖርትና ሎጅስቲክስ አገልግሎት ድርጅት የዕውቅና የምሥክር ወረቀት አግኝተዋል፡፡

የቴክኖሎጂ ግሩፑ ኩባንያዎች የዕውቅና ሽልማቱን ያገኙት የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አገልግሎት ድርጅት 50ኛ የወርቅ እዩቤልዩ በዓሉን ግንቦት 13 ቀን 2006 ዓ.ም. በሸራተን አዲስ በታላቅ ድምቀት ሲያከብር ለረጅም ዓመታት በመርከብ ጥሬ ዕቃዎችንና የምርት

ውጤቶችን ከውጭ አገር በማጓጓዝ ተጠቃሚ መሆናቸውን ከፍተኛ ግምት ውስጥ በማስገባት ነው፡፡

ሽልማቱን ከኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አገልግሎት ድርጅት የቦርድ ሰብሳቢ ከክቡር አቶ መኩሪያ ኃይሌ እጅ የተቀበሉት የሚድሮክ ኢትዮጵያ ቺፍ ኤግዚኪዩቲቭ ኦፊሠር ዶ/ር አረጋ ይርዳው ሲሆኑ፤ በሽልማቱ አሰጣጥ ሥነ-ሥርዓት ላይ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፕሬዚዳንት ክቡር ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ የኢፌዲሪ ፕሬዚዳንት፣ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ የውጭና የአገር ውስጥ ባለሀብቶች፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችና የድርጅቱ ሠራተኞች ተገኝተዋል፡፡

ዶ/ር አረጋ ይርዳው የቦርድ ሰብሳቢ ሆነው በድጋሚ ተመረጡየኢትዮጵያ የግል የከፍተኛ ትምህርት እና የቴክኒክ ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ተቋማት ማኅበር ጠቅላላ ጉባዔ የዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር አረጋ ይርዳውን የቦርድ ሰብሳቢ አድርጐ ለሁለተኛ ጊዜ መረጠ፡፡

ማኅበሩ መጋቢት 27 ቀን 2006 ዓ.ም. ባካሄደው ሁለተኛ ጠቅላላ ጉባዔው ከጥቅምት 2002 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ የካቲት 2006 ዓ.ም. ድረስ ያከናወነውን የሥራ አፈፃፀምና የኦዲት ሪፖርት ካስደመጠ በኋላ በቀጣይ ማኅበሩን የሚመሩ የቦርድ የአመራር አካላትን በመምረጥ ጉባኤውን አጠናቅቋል፡፡

በሪፖርቱ የቀድሞው የአመራር አካላት በማኅበሩ የታቀፉ የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በመመሪያ አፈፃፀም ዙሪያ ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አግባብነትና ጥራት ኤጄንሲ ጋር ተደጋጋሚ ውይይቶች በመካሄዳቸው የነበሩ ችግሮች መፈታታቸው፤ በቴክኒክና ሙያ ትምህርት ሥልጠና፣ በከፍተኛ ትምህርት የተማሪዎች ቅበላ፣ በተቋማት ስያሜ፣ በዕውቅና አሰጣጥ መመሪያ፣ በመምህራን ልማት፣ በትምህርት ጥራት ማስጠበቂያ መመሪያና በሌሎችም በርካታ ጠቃሚ ጉዳዮች ላይ ውይይት መካሄዱ ተገልጿል፡፡

እንደ ሪፖርቱ ገለጻ ቀደም ሲል በሰው ኃይል እጥረት ምክንያት ያልተከናወኑ የውጭ ግንኙነትና ቅርንጫፍ ማኅበራትን የማጠናከር ሥራዎችን በተያዘው በጀት ዓመት በማከናወን፤ በሙከራ ደረጃ ያለውን የማኅበሩን የጥራት

ዩኒት በማጠናከርና አዳዲስ አባል ተቋማትን በማሰባሰብ መመሪያና ደንብን የተከተለ ሥራ በማከናወን በትምህርት ጥራት ላይ የሚፈለገውን ለውጥ ለማምጣት ከፍተኛ ርብርብ ይደረጋል፡፡የማህበሩ የቦርድ ሰብሳቢ ሆነው የተመረጡት የዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር አረጋ ይርዳው በጉባዔው ማጠቃለያ ወቅት በቀጣይ ጊዜ በማኅበሩ የታቀፉና ወደፊት የሚታቀፉ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ራሳቸውን በደንብ ፈትሸው ህግና ደንብን ያከበረ ተግባር ከመፈፀም ባሻገር ሙሉ በሙሉ በትምህርት ጥራት ላይ ለውጥ ማምጣት እንደሚጠበቅባቸውና ለዚህም ማኅበሩ በጽናት እንደሚሠራ ተናግረዋል፡፡

በጉባዔው ከተሳተፉት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ ዘጠኙ በጠቅላላ ጉባዔው በመመረጥ፤ ከዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ ዶ/ር አረጋ ይርዳው በሰብሳቢነት፣ ከአድማስ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ አቶ ሞላ ፀጋይ በምክትል ሰብሳቢነት፣ ከኢትዮጲስ የርቀት ትምህርት ኮሌጅ አቶ አዲል አብደላ በፀሐፊነት ቀሪዎቹ ከቅድስት ማርያም ዩኒቨርሲቲ ረ/ፕሮፌሰር ወንድወሰን ታምራት፣ ከአልፋ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ረ/ፕሮፌሰር ኃ/ሥላሴ ወ/ገሪማ፣ ከሼባ ኮሌጅ አቶ ሱራፌል በርሄ፣ ከአልካን የጤና ሣይንስ ኮሌጅ አቶ አዳሙ ካሤ፣ ከትሮፒካል

የሕክምና ኮሌጅ አቶ አፈወርቅ ጊላይ፣ ከቅድስት ልደታ የጤና ሣይንስ ኮሌጅ

አቶ ኃ/ገብርኤል አቦምሳ በአባልነት ማኅበሩን እንዲመሩ ተመርጠዋል፡፡

ዶ/ር አረጋ ይርዳው ሽልማቱን ሲቀበሉ

ዶ/ር አረጋ ሰብሳቢ ሆነው በተመረጡበት ወቅት

Page 4: From the Chairman File - MIDROC...4 MIDROC Newsletter Volume 14, Issue # 76 March — April 2014 Addis Ababa, Ethiopia ወ/ሮ ትርሲት አጎናፍር ከዚህ ዓለም በሞት

4

MIDROC NewsletterVolume 14, Issue # 76 March — April 2014

Addis Ababa, Ethiopia

ወ/ሮ ትርሲት አጎናፍር ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ1938 – 2006

ወ/ሮ ትርሲት አጎናፍር ከእናታቸው ከወ/ሮ ልክየለሽ አወቀና ከአባታቸው ከአቶ አጎናፍር የምሩ ሚያዝያ 17 ቀን 1938 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ከተማ ተወለዱ፡፡ እድሜያቸው ለትምህርት እንደደረሰም በአዲስ አበባ ናዝሬት ትምህርት ቤት በመግባት እስከ 12ኛ ክፍል ያለውን ትምህርታቸውን በመከታተል ሰኔ 1957 ዓ/ም በጥሩ ውጤት አጠናቀዋል፡፡ በመስከረም 1958 ዓ.ም. የቀድሞው ቀ.ኃ.ሥ. ዩኒቨርሲቲ ቢዝነስ ኮሌጅ በመመደብ፣ በኮሌጁ የሚሰጠውን ትምህርት በማጠናቀቅ በሰኔ 1962 ዓ.ም. በንግድ አመራር ቢ.ኤ. ዲግሪ ተመርቀዋል፡፡

ከቢዝነስ ኮሌጅ እንደተመረቁ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በመግባት ከማኔጅመንት ሰልጣኝ (Trainee) ጀምረው በየወቅቱ በእድገት እየተሾሙ መስከረም 1969 ዓ.ም. በማኔጀርነት፣ ነሐሴ 1975 ዓ.ም. በሠራተኞች አስተዳደር ዳይሬክተርነት እስከ ሰኔ 1981 ዓ.ም. አገልግለዋል፡፡

ከሐምሌ 1981 ዓ.ም. ጀምረው ወደ ማርኬቲንግ መምሪያ በመዘዋወር፣ የሥልጠና አገልግሎት ማኔጀር፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የበርሊን ቢሮ ማኔጀር፣ የኒውዮርክ ቢሮ ማኔጀር በመሆን፤ በማርኬቲንግ ዘርፍ እስከ ሐምሌ 1986 ዓ.ም. ድረስ አገልግለዋል፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ በተሻለ ማኔጅመንት እንዲዋቀር በመንግሥት ሲወሰን ወ/ሮ ትርሲት አጎናፍር በትውስት ወደ ባንኩ እንዲዛወሩና የባንኩን የሰው ኃይል አስተዳደር እንዲያደራጁ በመጠየቁ ከሐምሌ 1986 ዓ.ም. ጀምሮ በምክትል ፕሬዚዳንትነት (Human Resource Mgmt V/P) በማገልገል እንዲሁም በባንኩ ፕሬዚዳንት በሚመራው (Policy Committee) አባልና በልዩ ልዩ ኮሚቴዎች ውስጥ በመሳተፈ በተመደቡበት የሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ ባንኩ አሁን ለደረሰበት የዕድገት ደረጃ ጉልህ አስተዋፅኦ አበርክተዋል።

ከዚያም ወደ ኢትዮጵያ አየር መንገድ ተመልሰው በManpower Planning Expert እና በPersonnel Administration Division ሥራ አስኪያጅ በመሆን ጡረታ እስከወጡበት ግንቦት 1994 ዓ.ም. ድረስ በታማኝነትና በብቃት አገልግለዋል፡፡

እ.ኤ.አ. ማርች 7 2005 ዓ.ም. በትረስት የጥበቃና የሰው ኃይል አገልግሎት ኃ.የተ.የግል ማህበር በዋና ሥራ አስኪያጅነት በመቀጠልም በሚድሮክ ሲኢኦ ማኔጅመንትና አመራር አገልግሎት በከፍተኛ ኤግዚኪዩቲቭ አማካሪነት ደረጃ እስከ ሕልፈተ ሕይወታቸው ድረስ አገልግለዋል፡፡

ወ/ሮ ትርሲት አጎናፍር በጥቅምት 1963 ዓ.ም. ከአቶ ዮሴፍ ወልደ ዮሐንስ ጋር በቫቲካን ቅዱስ ጴጥሮስ ካቴድራል ጋብቻቸውን በመፈጸም፣ በትዳር ሕየወታቸው ሁለት ልጆችን አፍርተዋል፡፡ እንዲሁም ሦስት ብርቅዬ የልጅ ልጆችን ለማየት በቅተዋል፡፡

ወ/ሮ ትርሲት አጎናፍር በማህበራዊ አኗኗራቸው ከሁሉም ሕብረተሰብ ጋር የሚግባቡ እጅግ አዛኝና ሩህሩህ ለጓደኞቻቸውና ለወዳጆቻቸው አለኝታ በሐዘንም ሆነ በደስታ ጊዜ ፈጥነው የሚደርሱ ቀናና በጎ አሳቢ እህት ነበሩ።

ወ/ሮ ትርሲት አጎናፍር ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ታመው በአገር ውስጥና በውጭ አገር በሕክምና ሲረዱ ቆይተው ግንቦት 19 ቀን 2006 ዓ.ም. ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡ የቀብራቸው ሥነ ሥርዓት ሐሙስ ግንቦት 21 ቀን 2006 ዓ.ም. በቅዱስ ጴጥሮስ ወጳውሎስ የካቶሊክ መካነ መቃብር ተፈፅሟል፡፡

ለውድ ልጆቻቸው ለመላው ቤተሰባቸውና ለወዳጆቻቸው እግዚአብሔር መጽናናትን እንዲሰጥልም እንመኛለን፡፡

ወ/ሮ ትርሲት አጐናፍር በሚድሮክ ኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ኩባንያዎች በሥራ ላይ በነበሩበት ወቅት ካደረጓቸው ተሣትፎዎች በከፊል

ከሠራተኞች ማኅደር

Page 5: From the Chairman File - MIDROC...4 MIDROC Newsletter Volume 14, Issue # 76 March — April 2014 Addis Ababa, Ethiopia ወ/ሮ ትርሲት አጎናፍር ከዚህ ዓለም በሞት

5

MIDROC NewsletterVolume 14, Issue # 76 March — April 2014

Addis Ababa, Ethiopia

የሲኢኦ ቢሮ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ከኩባንያዎች ሠራተኞች ጋር ውይይት አካሄዱ

• አመራር አካላቱ በባህር ዳር ከተማ በተካሄደው የስፖርት ውድድር ማጠናቀቂያ በዓል ላይ ተካፋይ ሆነዋል

የሚድሮክ ኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ኩባንያዎች በአዲስ አበባና በክልል የሚገኙ ሠራተኞች በኩባንያዎች አሠራር፣ በአስተዳደርና በልዩ ልዩ ችግሮች ዙሪያ ግልፅ ውይይት አካሄዱ፡፡

በሚድሮክ ኢትዮጵያ ቺፍ ኤግዚኪዩቲቭ ኦፊሰር በዶ/ር አረጋ ይርዳው የተመራ ቡድን ከየካቲት ወር መጀመሪያ ጀምሮ እስከ መጋቢት 10 ቀን 2006 ዓ.ም. በአዲስ አበባና በዱከም ከሚገኙ የቴክኖሎጂ ግሩፑ ኩባንያዎች ሠራተኞች ጋር ግልፅ ውይይት ያካሄደ ሲሆን፤ ከመጋቢት 13 እስከ መጋቢት 23 ቀን 2006 ዓ.ም. ድረስ ደግሞ በክልሎች በሚገኙ የኩባንያዎቹ ቅርንጫፍ መሥሪያ ቤቶች ከሚገኙ ሠራተኞች ጋር ውይይት አድርጓል፡፡

በተለይም በክልሎች ከተካሄደው ውይይት በተጨማሪ የሥራ እንቅስቃሴዎች የተጐበኙ ሲሆን፤ በጨፋ እርሻ ልማት፣ በኮምቦልቻ የኤልፎራ አግሮ ኢንዱስትሪ የምግብ ማቀነባበሪያ ፋብሪካና የኮምቦልቻ ብረታ ብረት ምርቶች ኢንዱስትሪ ፋብሪካ ኮምቦልቻ ቅርንጫፍ፣ በደሴ የሚገኙት ኩዊንስ ሱፐር ማርኬትና ዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ፣ የወይዘሮ ስሂን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ፣ የወልድያ እቴጌ ጣይቱ ብጡል የመጀመሪያ ደረጃ ሙሉ ሣይክል ት/ቤት፣ የወልድያ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት እንዲሁም ግንባታውን ለማጠናቀቅ የመጨረሻ ደረጃ ላይ የሚገኘው የወልድያ ስታዲየም የሥራ ሂደት ተጐብኝቷል፡፡

በጉብኝቱ በሚድሮክ ወርቅ ማዕድን ኃ.የተ.የግ.ማ የ7ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር ዕርዳታ የማስፋፊያ ሥራ የሚከናወንለትና ዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ 1,348 መጽሐፎችን በዕርዳታ የተሰጠው የወልድያ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የፍፃሜ ሥራ ትኩረት ተሰጥቶት እንዲከናወን ሲኢኦ ዶ/ር አረጋ አሳስበዋል፡፡

በወልድያ በሼክ ሙሐመድ ሁሴን አሊ አል አሙዲ ስም እየተገነባ የሚገኘው የወልድያ ስታዲየም የደረሰበት ደረጃና ቀሪ የማጠናቀቂያ ሥራዎቹ በባለሙያዎች ገለፃ ከተደረገ በኋላ ዶ/ር አረጋ ይርዳው ለቀጣዩ ሥራ መመሪያ ሰጥተዋል፡፡

የሲኢኦ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በጐንደር የኤልፎራ አግሮ ኢንዱስትሪ ኃ.የተ.የግ.ማ ቅርንጫፍ መ/ቤት በመገኘት ከሠራተኞች ጋር ውይይት ያካሄዱ ሲሆን፤ በዚያው የሚገኘውን የሞሐ ለስላሣ መጠጦች ኢንዱስትሪ ኃ.የተ.የግ.ማ. የሥራ ሂደት ጐብኝተዋል፡፡

በቺፍ ኤግዚኪዩቲቭ ኦፊሰር ዶ/ር አረጋ ይርዳው የተመራው ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ቡድን ቀደም ሲል ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በቀረበለት ጥሪ መሠረት በባህርዳር አዲሱ ስታዲየም በተካሄደው በ4ኛው የመላው ኢትዮጵያ የስፖርት በዓል ማጠናቀቂያ ደማቅ በዓል ላይ በመገኘት የበዓሉ ተሳታፊ ሆኗል፡፡

በበዓሉ ላይ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. መንግሥት ፕሬዚዳንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመን ጨምሮ ዶ/ር አረጋ ይርዳውና ልዩ ልዩ ጥሪ የተደረገላቸው ታዋቂ ሰዎች ምሁራንና ባለሥልጣናት ተገኝተዋል፡፡

ለ10 ቀናት ከቆየው የሥራ ጉብኝት በተጓዳኝ የአገርን ታሪካዊ ሥፍራዎች የመጐብኘት የአገርህን እወቅ ተግባር ተከናውኗል፡፡ በዚህም የጐንደር ፋሲለደስ ቤተ መንግሥትና ልዩ ልዩ ቦታዎች እንዲሁም የጣና ሐይቅ ገዳማት ተጐብኝተዋል፡፡

Officials hold open house discussion • Dr. Arega Yirdaw attended the 4th all Ethiopian Sport Festival

A delegation comprising higher managerial team of the MIDROC Ethiopia Technology Group companies led by CEO, Dr. Arega Yirdaw held “open house” discussion with employees of the Technology Group Companies in and around Addis Ababa and that of regional state. The discussion was held from February 19 – April 1, 2014.

CEO, MIDROC Ethiopia, Dr. Arega Yirdaw, who chaired the meeting elucidated the purpose of the discussion and initiated employees to forward important issues and problems they have faced so far.

The discussion addressed several issues related to employees and Dr. Arega responded to the questions posed on him from employees.

The field trip has also provided the team with an opportunity to visit ELFORA Agro Industry Chefa Integrated Farm. ELFORA Kombolcha Food Complex, KOSPI-Kombolcha branch, Queen's Supermarket & Unity University Dessie branch, W/ro Shin Polytechnic College, Etege Taytu Bitul Elementary School, Woldya Comprehensive Secondary School and Sheik Mohammed Hussein Ali Al-Amoudi Stadum at Woldya.

During the visit, Unity University donated 1,348 books to Woldya Comprehensive Secondary School.

Mean while a delegation led by Dr, Arega Yirdaw was attended the 4th all Ethiopian sport festival closing ceremony at Bahir Dar Stadium, the newly constructed one.

President Dr. Mulatu Teshome, higher government officials, Dr. Arega Yirdaw and invited guests were present on the event. In a related development a delegation visited Fasiledes palace, Tana Haique Monastry and different historical sites.

ውይይት ከሠራተኞች ጋር Discussion with employees

Page 6: From the Chairman File - MIDROC...4 MIDROC Newsletter Volume 14, Issue # 76 March — April 2014 Addis Ababa, Ethiopia ወ/ሮ ትርሲት አጎናፍር ከዚህ ዓለም በሞት

6

MIDROC NewsletterVolume 14, Issue # 76 March — April 2014

Addis Ababa, Ethiopia

የቴክኖሎጂ ግሩፑ ሠራተኞች የሠርቪስ አገልግሎት በአሊያንስ የትራንስፖርት ሰርቪስ አ.ማ. አማካኝነት እንዲቀጥል ተደረገ

የሚድሮክ ኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ኩባንያዎች ሠራተኞች ወደ ሥራ ቦታ ለመድረስና ወደቤታቸው ለመመለስ የሚያስችላቸው የመጓጓዣ አገልግሎት እንዲያገኙ ከአሊያንስ ትራንስፖርት ሰርቪስ አክሲዮን ማኅበር ጋር ስምምነት በማድረግ አገልግሎቱ እንዲቀጥል ተደረገ፡፡

የቴክኖሎጂ ግሩፑ ኩባንያ ሠራተኞች ቀደም ሲል በአባል ኩባንያው በሬይንቦ የመኪና ኪራይና አስጐብኚ ኃ.የተ.የግ.ማ አማካኝነት አገልግሎት ያገኙ የነበረ ቢሆንም አገልግሎቱ ሳይቋረጥ አስተማማኝ በሆነ ሁኔታ

መጠቀም እንዲቻል ከአሊያንስ ትራንስፖርት ሰርቪስ አክሲዮን ማኅበር ጋር ስምምነት በማድረግ 443 ሠራተኞችን ማጓጓዝ የሚችሉ ስምንት ዘመናዊ አውቶቡሶች እንዲመደቡ ተደርጓል፡፡

አውቶቡሶቹ በስምምነቱ መሠረት ከመጋቢት ወር መጨረሻ ጀምሮ አገልግሎት መስጠት የጀመሩ ሲሆን፤ በሥራ መግቢያ ሠዓት ሠራተኞችን ወደ መቻሬ ኮርፖሬት ሴንተር በማድረስና በሥራ ሰዓት መውጫ በኮርፖሬት ሴንተሩ በመገኘት ወደየቤታቸው የማድረስ ተግባር ያከናውናሉ፡፡

ሬይንቦ ኩባንያ በ3ኛው ዓለም አቀፍ የቱሪዝምና የጉዞ ንግድ ትርዒት ላይ ተሳተፈ

የሚድሮክ ኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ኩባንያዎች አባል ሬይንቦ የመኪና ኪራይና የአስጐብኚ አገልግሎት ኃላ.የተ.የግ.ማ. በ3ኛው ልዩ ዓለም አቀፍ የቱሪዝምና የጉዞ የንግድ ትርዒት ኤግዚቪሽን ላይ ተሳተፈ፡፡

ኩባንያው በኢትዮጵያ ለሚካሄዱ ዓለምአቀፍና አህጉራዊ ስብሰባዎች ባሉት ዘመናዊ መኪናዎች የመኪና ኪራይና ልዩ ልዩ ታሪካዊ ሥፍራዎችን ለሚጐበኙ የተሟላ የአስጐብኚነት አገልግሎት የሚሰጥ በመሆኑ እነዚህኑ አገልግሎቶቹን ለተጠቃሚዎች ለማስተዋወቅ ከሚያዝያ 16 እስከ ሚያዝያ 20 ቀን 2006 ዓ.ም. በሚቆየው በዚሁ ኤግዚቪሽን ላይ ተሳታፊ ሆኗል፡፡

የቱሪዝምና የጉዞ ንግድ ትርዒቱን የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ታደለች ዳለቾ በይፋ የከፈቱ ሲሆን፤ ኤግዚቪሽኑን የአዲስ አበባ ንግድ ምክር ቤትና ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር በጋራ ያዘጋጁት ነው።

በኤግዚቪሽኑ ላይ በአስጐብኚ የጉዞ ወኪልና ተዛማጅ በሆኑ ሥራዎች ላይ የተሰማሩ ከ90 በላይ ድርጅቶች ተካፋይ ሲሆኑ፤ አምባሳደሮችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችም ኤግዚቪሽኑን ጐብኝተዋል፡፡

Rainbow Takes Part at the 3rd Tourism and Travel Fair

Rainbow Exclusive Car Rental and Tour Services Plc, a member of the MIDROC Ethiopia Technology Group Companies participated at the 3rd Tourism and Travel International Fair at Addis Ababa Exhibition Center from April 24 – 28, 2014.

TheExhibitionwasofficiallyopenedbyW/roTadelechDalecho,State Minister of Culture and Tourism, in the presence of senior Governmentofficials,Ambassadors,DiplomaticCommunityandrepresentative of the business community.

Rainbow Exclusive Car Rental and Tour Services Plc. and other companies took part in the exhibition and displayed their services. The exhibition was organized by the Addis Ababa Chamber of Commerce and Sectoral Associations.

ለመጓጓዣ አገልግሎት ከተዘጋጁት አውቶቡሶች በከፊል

አቶ ጥምቀት ወዳጆ ገለፃ ሲያደርጉ / Ato Timket Wodajo explaining the display

Page 7: From the Chairman File - MIDROC...4 MIDROC Newsletter Volume 14, Issue # 76 March — April 2014 Addis Ababa, Ethiopia ወ/ሮ ትርሲት አጎናፍር ከዚህ ዓለም በሞት

7

MIDROC NewsletterVolume 14, Issue # 76 March — April 2014

Addis Ababa, Ethiopia

በወልድያ በሁዳ ሪል እስቴት ኃላ.የተ.የግ.ማ. የሚገነባው የሼህ ሙሐመድ ስታዲየም 60 በመቶ ግንባታው እየተጠናቀቀ ነው

በሰሜን ወሎ ዞን በወልድያ ከተማ በግንባታ ላይ የሚገኘው የወልድያ ሁለገብ ስታዲየም ሥራው ከግማሽ በላይ መገባደዱን ግንባታውን የሚያካሂደው የሁዳ ሪል ስቴት ኃላ.የተ.የግል ማኅበር ዋና ሥራ አስኪያጅ ገለፁ፡፡

የኩባንያው ዋና ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ቴዎድሮስ ሸዋረጋ 25 ሺህ ተመልካቾችን የሚያስተናግደው ይህ ስታዲየም ግንባታ ሥራ 60 ከመቶ የተገባደደና የማጠናቀቂያ ሥራዎች እየተከናወኑ እንደሚገኙ ጠቅሰው፤ ቀሪው በጥራት የሚካሄድ የማሳመር ሥራ እንደሆነ አስረድተዋል፡፡

በወልድያ ከተማ በክብር ዶ/ር ሼህ ሙሐመድ ሁሴን አሊ አል-አሙዲ ስም እየተገነባ ያለው ይህ ስታዲየም በስድስት ብሎኮች የተከፋፈለ ሲሆን፤ ለእንግዳ ማረፊያ፣ ሁለት ተጫዋች ቡድኖችን በአንድ ጊዜ ማስተናገድ የሚችሉ መታጠቢያ ቤቶች፣ የዳኞች ማረፊያና መታጠቢያ ቤቶች፣ የልዩ እንግዶች ማረፊያ ክፍሎች፣ መመገቢያና ማብሰያ ቤቶች፣ ለጋዜጠኞች መግለጫ የሚሰጥበት አዳራሽ፣ ለተጫዋቾች ገለጻና ምክክር የሚደረግባቸው ክፍሎች፣ ጋዜጠኞች የሚዘግቡባቸው ክፍሎች፣ የመጀመሪያ ህክምና ርዳታ የሚደረግባቸው ክፍሎች፣ ሽልማት መስጫ ሥፍራዎችና ልዩ ልዩ ቢሮዎችን የያዘ ሲሆን፤ ቤተመጻሕፍት፣ ጅምናዚየምና የመዋኛ ሥፍራንም ያካተተ ነው።

የስታዲየሙ የግንባታ ሥራ በልዩ ልዩ ግብረ ኃይል የተዋቀረ ሲሆን፤ እያንዳንዱ የየራሱን ሥራ በትጋት በማከናወን በየሳምንቱ የደረሰበትን ደረጃ ሪፖርት በማድረግ የሚያሳውቅና ሥራዎቹ በጥራትና በአግባቡ መከናወናቸውን የሚቆጣጠር አማካሪ ድርጅት መኖሩን ዋና ሥራ አስኪያጁ ገልፀዋል፡፡

ስታዲየሙ ከስፖርት ማዘውተሪያ ሥፍራነት በተጨማሪ ዙሪያውን የንግድ ሥራ ማካሄጃ የሚሆኑ በርካታ ሱቆችን ያካተተ በመሆኑ ግንባታው ሲጠናቀቅ ለበርካታ ዜጐች የሥራ ዕድልን እንደሚፈጥር ተጠቁሟል፡፡

በስታዲየሙ የግንባታ ሥራ እንደየወቅቱና ሥራው ተለዋዋጭነት በቀን ከ400 እስከ 700 ለሚደርሱ ሠራተኞች የሥራ እድል ፈጥሯል፡፡

ስታዲየሙን ለመገንባት በየካቲት 13 ቀን 2003 ዓ.ም. በሸራተን አዲስ ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት፣ የክብር ዶ/ር ሼህ ሙሐመድ ሁሴን አሊ አል-አሙዲና ቦርዱን በበላይነት የሚመሩት የሚድሮክ ኢትዮጵያ ቺፍ ኤግዚኪዩቲቭ ኦፊሰር ዶ/ር አረጋ ይርዳው በተገኙበት የድጋፍ ማሰባሰቢያ ቴሌቶን በማካሄድ በይፋ ሥራው የተጀመረው ይህ ስታዲየም ከአንድ ዓመት በኋላ ተጠናቅቆ ለርክክብ እንደሚበቃ ይጠበቃል፡፡

የስታዲየሙ ገጽታ ከርቀት ሲታይ

የማጠናቀቂያ ሥራ የቀረው የስታዲየሙ የውስጥ ገጽታ

أخبارعربية قصيرة

جامعة يونيتي توقع مذكرة تفاهم مع جامعة أديس أبابا وقع على مذكرة التفاهم كل . في قاعة مجلس الشيوخ لجامعة أديس أبابا2014 مايو عام 30وقعت جامعة يونيتي مذكرة تفاهم مع جامعة أديس أبابا في

إثيوبيا في حضور رئيس جامعة يونيتي والمدير التنفيذي العام لميدروك من الدكتور أدماسو تسجايي، رئيس جامعة أديس أبابا والدكتور أرغا يرداو، .المسؤولين األكاديميين واإلداريين للجامعتين

إثيوبيا تتلقى جائزة من شهادة اإلعتراف من مؤسسة النقل البحري واللوجستية اإلثيوبية مجموعة ميدروكتلقت شركات مجموعة تكنولوجيا لميدروك إثيوبيا جائزة من شهادة اإلعتراف من مؤسسة النقل البحري واللوجستيىة اإلثيوبية لعالقة العمل الثنائية القوية

. مستفيدة بصورة عالية من خدمات النقل البحري للبالدلكونهاالتي بنيت

تلقت شركات مجموعة تكنولوجيا الجائزة من شهادة اإلعتراف بوضع كونها مستفيدة بنقل مواد الخام والمنتجات من الخارج بالسفينة لسنوات طويلة في .عين اإلعتبار بصورة عالية

انتخاب الدكتور أرغا يرداو رئيسا للجنة مرة ثانيةانتخبت الجمعية العامة لجمعية مؤسسات التعليم العالي وتعليم المهنة التقنية والتدريب الخاصة اإلثيوبية رئيس جامعة يونيتي الدكتور أرغا يرداو رئيسا

.للجنة مرة ثانية كبار مسؤولي مكتب المدير التنفيذي أجروا محادثات مع موظفي الشركات

أجرى فريق برئاسة المدير التنفيذي العام، الدكتور أرغا يرداو محادثة صريحة مع موظفي شركات مجموعة تكنولوجيا الموجودين في أديس أبابا ودوكم إ، كما أجرى الفريق محادثة أيضا مع الموظفين الموجودين في مكاتب الشركات الفرعية . م2006 من شهر مجابيت لعام 10بدءا من شهر يكاتيت حتى

.إ. م2006 مجابيت 23 مجابيت حتى 13الموجودة في األقاليم بدءا من

. في المائة60وصول بناء استاد الشيخ محمد الذي يبنى بشركة هدى ريل استيت الخاصة المحدودة في مدينة ولديا إلى أوضح المدير العام لشركة هدى ريل استيت الخاصة المحدودة التي تقوم ببناء استاد ولديا العام في مدينة ولديا بمنطقة شمال وللو الذي هو قيد البناء، أن

.بناءه وصل إلى أكثر من نصف في المائة وأن أعمال 60 ألفا من المشاهدين قد وصل إلى 25وأوضح المدير العام للشركة المهندس توودروس شوارغا، أن بناء هذا اإلستاد الذي يستضيف

.اإلكمال جارية

6الصفحة

Page 8: From the Chairman File - MIDROC...4 MIDROC Newsletter Volume 14, Issue # 76 March — April 2014 Addis Ababa, Ethiopia ወ/ሮ ትርሲት አጎናፍር ከዚህ ዓለም በሞት

8

MIDROC NewsletterVolume 14, Issue # 76 March — April 2014

Addis Ababa, Ethiopia

mL:KT½ kcEF x@Gz!k!†tEV åðsR

ዶ/ር አረጋ ይርዳውDr. Arega Yirdaw

ቺፍ ኤግዚኪዩቲቭ ኦፊሰር፣ ሚድሮክ ኢትዮጵያChief Executive Officer, MIDROC Ethiopia

u’í ¾T>�ÅM (Distributed at no Cost)

Address: Office of the Chief Executive Officer, MIDROC EthiopiaFax: +251-11-371-5988 / 372-4977P.O. Box: 5787, Addis Ababa EthiopiaE-mail: [email protected]: www.midroc-ethiotechgroup.com

ግልፅ ውይይቱ ለሥራችን ውጤታማነት ወሳኝ ነው!የሚድሮክ ኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ኩባንያዎች ከተቋቋሙበት

ወቅት ጀምሮ አሁን እስከደረስንበት ደረጃ ድረስ የምናከናውናቸውን

ሥራዎችና ተጓዳኝ ተግባራት በየደረጃው እየገመገምን ጠንካራ

ጐናችንን እያዳበርን ደከም ያሉትን ደግሞ በጥንካሬ እያጐለበትን

አሁን ላለንበት ደረጃ ደርሰናል፡፡ የቴክኖሎጂ ግሩፑ ኩባንያዎች

ሠራተኞች ከዕለት ተዕለት ሥራዎቻቸው በተጨማሪ በተለያዩ

ጊዜያት ከአመራር አካላቱ ጋር የሚገናኙባቸው የውይይት

መድረኮች ዘርፈ ብዙ ጠቃሚ ጉዳዮችን በማንሳት መፍትሔ

የሚያገኙባቸው ናቸው፡፡

በመቻሬ ኮርፖሬት ሴንተር የሚገኙት የበርካታ ኩባንያዎች

ሠራተኞች ከሚድሮክ ኢትዮጵያ ቺፍ ኤግዚኪዩቲቭ ኦፊሰር ጋር

በተደጋጋሚ ግልፅ ውይይት ማድረጋቸው የተለመደ ቢሆንም

ጊዜውን ጠብቆ በዓመት አንድ ጊዜ ይኸው ግልፅ ውይይት

የሁሉም ኩባንያዎች ሠራተኞች በሚገኙባቸው ቦታዎች ሁሉ

በመድረስ የውይይቱ አካል ማድረግ ጠቀሜታው የጐላ ነው፡፡

ከሌላው የውይይት ልማድ ለየት የሚለው ይህ ግልፅ ውይይት

ሁሉም ሠራተኞች የሚሳተፉበትና ማናቸውንም መጠየቅ

የሚፈልጓቸውን ጉዳዮች የሚያነሱበት መድረክ ሲሆን፤

ሠራተኞች በሥራ አካባቢ የአስተዳደር ግድፈት፣ የሥራ

መጓተት፣ የአሠራር እንዝላልነት ወይም መፈፀም የሚገባቸውና

ያልተፈፀሙ ተግባራት በጥያቄና በአስተያየት መልክ ቀርበው

አፋጣኝ መፍትሔ የሚያገኙበት መድረክ ነው፡፡

በዚህ ዓመትም ከመጋቢት 10 ቀን ጀምሮ እስከ መጋቢት 23

ቀን 2006 ዓ.ም. ድረስ በልዩ ልዩ ቀናት በቅድሚያ በአዲስ አበባ

የሚገኙ ኩባንያዎች ሠራተኞች በሥራ ቦታቸው እየተሰበሰቡ

ከሲኢኦ ዶ/ር አረጋ ይርዳው ጋር ግልፅ ውይይት ሲያካሂዱ

ቆይተዋል፡፡

በአዲስ አበባና በአካባቢዋ ባሉ ኩባንያዎች የተካሄደው ውይይት

ቀጣይ ምዕራፍ በክልል የሚገኙ የቅርንጫፍ የኩባንያዎች

ሠራተኞችንም ያማከለ እንዲሆን ዶ/ር አረጋ ይርዳውና ከፍተኛ

የሥራ ኃላፊዎች የሚገኙበት የኃላፊዎች ቡድን እዚያው ባሉበት

ቦታ በመሄድ ሠራተኞችን በማወያየት መፍትሔ የመስጠትና

የማስተካከል ሥራዎችን ሲያከናውን ቆይቶ ተመልሷል፡፡

በመድረኮቹ ጠቃሚ ሀሳቦች ተነስተው የበሰለ ውይይት

ተካሂዶባቸዋል፡፡ ከእነዚህ የውይይት መድረኮች የምንማረው

ማንኛውም ሠራተኛ ሀሳቡን ካለገደብ በግልፅ በማውጣት

ለአመራሩ በማቅረብ መፍትሔ የሚያገኝበት መሆኑን ነው፡፡

በተለይም በክልል ቅርንጫፍ ኩባንያዎች ከግልፅ ውይይቱ

በተጨማሪ የሥራ የመስክ ምልከታ በማካሄድ ሁለት ተግባራት

ለማከናወን ተችሏል፡፡ በዚህ የመስክ ምልከታ የኩባንያዎች

የሥራ ሂደት የተቃኘ ሲሆን፤ በግንባታ ላይ የሚገኙ ትላልቅ

ሥራዎች አመርቂ ደረጃ ላይ መድረሳቸውን ለማየት አስችሏል።

ይህንኑ መሰል ኩባንያዎቹን ውጤታማ የማድረግ እንቅስቃሴ

ወሳኝ በመሆኑ አጠናክረን የምንቀጥልበት ይሆናል፡፡