በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - zhic.aeኢስላም፣ ኢማን እና...

133

Transcript of በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - zhic.aeኢስላም፣ ኢማን እና...

Page 1: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - zhic.aeኢስላም፣ ኢማን እና ኢሕሳን 3 አጠቃላይ እይታ 4 መግቢያ 6 የጉዞ መመሪያ 6 ለጉዞ
Page 2: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - zhic.aeኢስላም፣ ኢማን እና ኢሕሳን 3 አጠቃላይ እይታ 4 መግቢያ 6 የጉዞ መመሪያ 6 ለጉዞ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ በጣም አዛኝ በሆነው

﴾እነዚያንም የቀኑትን ሰዎች አላህ ቅንነትን ይጨምርላቸዋል፡፡ መልካሞቹ ቀሪዎች

(ሥራዎች) እጌታህ ዘንድ በምንዳ ባለጭ ናቸው፡፡ በመመለሻም የተሻሉ ናቸው፡፡

(መርየም ፡ 76)

Page 3: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - zhic.aeኢስላም፣ ኢማን እና ኢሕሳን 3 አጠቃላይ እይታ 4 መግቢያ 6 የጉዞ መመሪያ 6 ለጉዞ

ዛኢባተ የአዲስ ሙስሊሞች ስርዓተ ትምህርት

መለኮታዊው መንገድየአዲስ ሙስሊሞች መመሪያ መጽሐፍ፡- ሐሰን ላም (ክፍል 1፣ 2 እና 3)፣ ረምዚ አጀም (ክፍል 4)የአምልኮ የመጀመሪያ መመሪያዎች ፡- ረምዚ አጀም (ማሊኪ)፣ ሰማሕ ማሪ (ሐነፊ)፣ ነጃም ኻጃ (ሐንበሊ)፣ ሰኢማ ዲን (ሻፊዒ)የሰላት ምስላዊ መመሪያ (ዲቪዲ)የሰላት ድምጾች (በድምጽ)የመምህሩ መመሪያ ፡- ሰኢማ ዲን የመምህራን ስልጠና ትምህርት፡- ነዲም ሜሞንየመምህራን ማጎልበቻና ማረጋገጫ ፕሮግራም፡- ቀይሰር አሕመድ

Page 4: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - zhic.aeኢስላም፣ ኢማን እና ኢሕሳን 3 አጠቃላይ እይታ 4 መግቢያ 6 የጉዞ መመሪያ 6 ለጉዞ

መለኮታዊውመንገድ

Page 5: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - zhic.aeኢስላም፣ ኢማን እና ኢሕሳን 3 አጠቃላይ እይታ 4 መግቢያ 6 የጉዞ መመሪያ 6 ለጉዞ

© Zayed House for Islamic Culture 2015

Published byZAYED HOUSE FOR ISLAMIC CULTUREP.O. BOX 16090, AL-AIN, UNITED ARAB EMIRATESTEL 800555 FAX +971 3 7810633WWW.ZHIC.AE [email protected]

ISBN 978-9948-22-056-5

Commissioned by Zayed House for Islamic Culture, UAE. Produced by Razi Group, Canada, under the supervision of Tabah Foundation, UAE.

ALL RIGHTS RESERVED. Aside from fair use, meaning a few pages or less for nonprofit educational purposes, review, or scholarly citation, no part of this publication may be reproduced, stored in a retrieval system, or transmitted in any form or by any means, electronic, mechanical, photocopying, recording, or otherwise, without the prior permission of the Copyright owner.

ZHIC has no responsibility for the persistence or accuracy of URLs referred to in this publication, and does not guarantee that any content on such websites is, or will remain, accurate or appropriate. All information is correct as of November 2009, but ZHIC does not guarantee the accuracy of such information thereafter.

Printed in UAE© Zayed House for Islamic Culture 2015

አሳታሚዛይድ የኢስላማዊ ባህል ተቋምፖ.ሳ.ቁ 16090፣ አል ዓይን፣ የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶችስልክ 800555 ፋክስ +971 3 7810633ድረ ገፅ፡ WWW.ZHIC.AE ኢ ሜይል፡ [email protected]

የዚህ መጽሐፍ ህትመት ወጪ የተሸፈነው ተቀማጭነቱ በተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች በሆነው ዛይድ የኢስላማዊ ባህል ተቋም (Zayed House for Islamic Culture) ነው፡፡ የመጽሐፉ ዝግጅት በተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች በሚገኘው ጣባህ ፋውንዴሽን ተጠባባቂነት፣ ካናዳ በሚገኘው

ራዚ ግሩፕ ተካሄደ፡፡

መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡ በህግ በተፈቀደው መሠረት ከትርፍ ጋር ተያያዥነት ለሌላቸው ትምህርታዊ ዓላማዎች፣ ለሒሳዊ ዳሰሳ፣ ወይም ለምሁራዊ ሥራዎች ማጣቀሻነት ካልሆነ በስተቀር፣ ከቅጂው ባለመብት በጽሑፍ የተሰጠ ፈቃድ ሳይገኝ ከዚህ ህትመት ውስጥ አንዲትም አንቀፅ ቢሆን ማባዛት፣ በቤተ መዛግብት ማኖር፣ በኤሌክትሮኒክ፣ በሜካኒካዊ መንገድ፣ በፎቶኮፒ፣ በድምፅ

መሣሪያ በመቅዳት፣ ወይም በሌላ በማንኛውም ቅርፅ ወይም መንገድ ማስተላለፍ አይቻልም፡፡

በዚህ ህትመት ውስጥ የተጠቀሱ ድረ ገፆችን ዘውታሪነት ወይም በውስጣቸው የሚገኙ መረጃዎችን ትክክለኝነት በተመለከተ ዛይድ የኢስላማዊ ባህል ተቋም ምንም ዓይነት ኃላፊነትን አይወስድም፤ እንዲሁም በእነዚህ ድረ ገፆች ስለሚገኙ ማናቸውም ይዘቶች ትክክለኛነት ወይም ተስማሚነት ዋስትና አይሰጥም፡፡ በዚህ ህትመት ውስጥ ያሉ መረጃዎች እስከ ኖቬምበር 2009 ባለው ጊዜ ውስጥ ትክክለኛ ናቸው፤ ያም ሆኖ ከዚህ በኋላ ባለው ጊዜ የመረጃዎቹ ይዘትም ሆነ ትክክለኛነትን

በተመለከተ ዛይድ የኢስላማዊ ባህል ተቋም ዋስትና አይሰጥም፡፡

የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ውስጥ ታተመ

© ዛይድ የኢስላማዊ ባህል ተቋም 2015

Page 6: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - zhic.aeኢስላም፣ ኢማን እና ኢሕሳን 3 አጠቃላይ እይታ 4 መግቢያ 6 የጉዞ መመሪያ 6 ለጉዞ

ሁለተኛ እትም

መለኮታዊው

መንገድለአዲስ ሙሰሊሞች የተዘጋጀ መርጃ መጽሐፍ

ሐሰን ላም ረምዚ አጀም

ዛይድ የኢስላማዊ ባህል ተቋም አል ዓይን፣ የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች

Page 7: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - zhic.aeኢስላም፣ ኢማን እና ኢሕሳን 3 አጠቃላይ እይታ 4 መግቢያ 6 የጉዞ መመሪያ 6 ለጉዞ

ስለ ዛይድ የኢስላማዊ ባህል ተቋም

ዛይድ የኢስላማዊ ባህል ተቋም ለተወሰነ ዓላማ የተቋቋመ፣ ከልዑል አልጋ ወራሹ ሸንጎ ጋር ተቀራርቦ

የሚሠራ ነፃ ተቋም ነው፡፡ ተቋሙ የተመሠረተው በቀድሞው የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ገዢ ሸይኽ ዛይድ

ቢን ሡልጣን አል ናህያን ሲኾን፣ እ.አ.አ በ2005 በክቡርነታቸው ሸይኽ ኸሊፋ ቢን ዛይድ አል ነህያን፣

የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ፕሬዚደንት እና የአቡዳቢ ገዢ በይፋ ተመርቆ ሥራውን ጀምሯል፡፡

ዛይድ የኢስላማዊ ባህል ተቋም ኢስላማዊ ባህልን በማስፋፋት በተለያዩ ብሄሮች መካከል የግንኙነት ድልድይ

በመገንባት ላይ ያተኮሩ ስራዎችን ያከናውናል፡፡ ተቋሙ ስለኢስላም እና ኢስላማዊ ባህል የማወቅ ፍላጎት

ያላቸው አዳዲስ ሙስሊሞችና ግለሰቦችን በደስታ ይቀበላል፡፡ ዛይድ የኢስላማዊ ባህል ተቋም አዳዲስ

ሙስሊሞች ከማኅበረሰብ ጋር ውህደት ለመፍጠር የሚረዳቸውን ርዕይና አቅጣጫ በመስጠት በበርካታ

ቋንቋዎች ለማስተማር ያለመ ልዩ ትምህርታዊ መርኃ ግብር አበልጽጓል፡፡ በተጨማሪም፣ የቁርአን የቃል ጥናት

እና የአረብኛ ቋንቋ፣ የሐጅ አገልግሎቶች፣ የህዝብ ቤተ መጻሕፍት፣ እንዲሁም ባህላዊና በአንድ ጭብጥ

ላይ የተመሠረቱ የጉዞ ሁነቶችና ስፖርቶችን የመሳሰሉ ሌሎች ማኅበራዊ አገልግሎቶችን ያካተቱ ልዩ መርኃ

ግብሮችን ያቀርባል፡፡

ጥቂት ስለ ሸይኽ ዛይድ

ሸይኽ ዛይድ እ.አ.አ በ1918 በአል ዓይን ከተማ ተወልደው አብዛኛውን

የህፃንነት ጊዜያቸውን በዚያው አሳልፈዋል፡፡ የአቡዳቢ ገዢ ሆነው

በርካታ የስኬት ዓመታትን ካሳለፉ በኋላ፣ እ.አ.አ በ1971 በአዲስ

መልክ የተመሠረተውና ዋና ከተማይቱን አቡዳቢን ጨምሮ የሰባት

ኤሚሬቶች ፌደሬሽን የሆነው የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች መሪነትን

ጨብጠዋል፡፡ ሸይኽ ዛይድ የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶችን እጅግ ፈጣን

ለውጥ በሚታይበት ወቅት ላይ በመምራት፣ ለአያሌ አሥርት ዓመታት

ከባድ ችግሮችን ላሳለፈው አካባቢ ሀብት፣ ትምህርትና መልካም

ዕድሎችን አስገኝተዋል፡፡ ሸይኽ ዛይድ በህዝቡ እና በአገሩ ዘንድ ከፍተኛ

ተወዳጅነት የነበራቸውና፣ በተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ውስጥ የአብሮ

መኖር፣ የመቻቻል እና የመከባበር ባህል እንዲዳብር ከፍተኛ ሚና

የተጫወቱ ሰው ነበሩ፡፡ ሸይኽ ዛይድ እ.አ.አ. በ2004 ከዚህች ዓለም

የተለዩ ሲኾን፣ አቡዳቢ ውስጥ ከሚገኘውና በስማቸው ከሚጠራው ታላቅ

መስጂድ አጠገብ ቀብራቸው ተፈጽሟል፡፡ በዙፋናቸውም ላይ የበኩር

ልጃቸው የተከበሩ ሸይኽ ኸሊፋ ቢን ዛይድ አል ናህያን ተተክተዋል፡፡

Page 8: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - zhic.aeኢስላም፣ ኢማን እና ኢሕሳን 3 አጠቃላይ እይታ 4 መግቢያ 6 የጉዞ መመሪያ 6 ለጉዞ

መልዕክት ከዛይድ የኢስላማዊ ባህል ተቋም

ለአላህ (ሱ.ወ) ክብር ይገባውና በተባበሩት ዐረብ ኤመሬቶች ውስጥ ኢስላምን የሚቀበሉ ሰዎች ቁጥር

በእጅጉ እየጨመረ መጥቷል ፡፡ የዛይድ ኢሰላማዊ ባህል ማዕከል ከምስረታው አንስቶ ኢስላምን ለሚቀበሉ

ሰዎች አስፈላጊውን እገዛና ወደ ማህበረሰቡ የሚቀላቀሉበትን ሁኔታዎች እያመቻቸ

ይገኛል፡፡ በዚህም መሰረት ስለ ኢስላም መሰረታዊና ወጥነት ያለው ስርኣተ- ትምህርት ማዘጋጀት አስፈላጊ

ሆኖ ተገኝቷል፡፡

ከዚህ በመነሳት ዛይድ የኢስላማዊ ባህል ተቋም ይህን በማኅበረሰቦችና ባህሎች መካከል የሚታይ የግንዛቤ

ክፍተት ለማጥበብ ወይም ለመዝጋት በሚደረገው ጥረት ላይ መሪ ሚና ለመጫወት የሚጥር ተቋም

ነው፡፡ ዓላማችን ውጤታማ የባህል ልውውጥ ሐሳቦችን በማራመድ፣ ህዝቦች በተሻለ ሁኔታ እርስ በእርስ

እንዲተዋወቁና አንዳቸው የሌላውን እሴት እንዲያደንቁ መርዳት ነው፡፡ የዚህ ጥረት አንዱ ክፍል በልዩ ልዩ

ርዕሰ ጉዳዮች ዐውድ የተሰናዱና ለዚህ ዓላማ ጠቀሜታ ያላቸው ስራዎችን አዘጋጅቶ በማቅረብ ዓለምን

ከኢስላም እና ከአንድ ቢሊዮን ከሚበልጡት ተከታዮቹ ጋር ማስተዋወቅ ነው፡፡

ዛይድ የኢስላማዊ ባህል ተቋም ከኢስላም ጋር ተዋወቁ! የተሰኘውን ይህን ተከታታይ ቅፅ ሲያቀርብ ከፍተኛ

ደስታ ይሰማዋል፡፡ በተከታታይ ቅፆች የሚቀርቡት ስራዎች በዘመናችን እጅግ የተዛባ ግንዛቤ ሰለባ በሆኑት

ህዝቦች ዙርያ ለየት ያሉ እይታዎችን ያቋድሳሉ፡፡ ቅፆቹ የዘመናችንን የተለዩ ተግዳሮቶች ተረድቶ ተገቢ

አፀፋ በመስጠት ዓላማ በመገናኛ ብዙኃን ውጤቶች ላይ የተካሄዱ ዙርያ መለስ ጥናቶችን መሠረት በማድረግ

የተዘጋጁ ናቸው፡፡

በዚህ አጋጣሚ ዛይድ የኢስላማዊ ባህል ተቋም በተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች የሚገኘው ጧባህ ፋውንዴሽን

እና ካናዳ የሚገኘው ራዚ ግሩፕ ይህ ልዩ እና ኪናዊ አቀራረብ የተላበሰ ፕሮጀክት እጅግ ስኬታማ ይሆን

ዘንድ ላደረጉት ያልተቆጠበ ጥረት ምስጋናውን ለማቅረብ ይወዳል፡፡ በዚህ ቅፅ ውስጥ የቀረቡት ሥራዎች

ስለ ኢስላማዊ መርኆች እና ስለ ሙስሊም ህዝቦች አንባቢያንን በማሳወቅ ረገድ በጣም ጠቃሚ እንደሚሆኑ

ተስፋ እናደርጋለን፡፡ ይህ አነስተኛ ጥረት የእርስ በርስ መግባባት፣ መልካም ፈቃድና ፍሬያማ የአብሮ መኖር

ድልድይ ከመገንባት አኳያ የመጀመርያው እርምጃ ነው፡፡

ዛይድ የኢስላማዊ ባህል ተቋም

Page 9: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - zhic.aeኢስላም፣ ኢማን እና ኢሕሳን 3 አጠቃላይ እይታ 4 መግቢያ 6 የጉዞ መመሪያ 6 ለጉዞ
Page 10: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - zhic.aeኢስላም፣ ኢማን እና ኢሕሳን 3 አጠቃላይ እይታ 4 መግቢያ 6 የጉዞ መመሪያ 6 ለጉዞ

ጥቂት ስለ ደራሲዎቹ

ሐሰን ላም

ሐሰን ላም በኦንታሪዮ መምህራን ኮሌጅ እውቅና ያለው አባልና በመጀመሪያ ደረጃ መምህርነት በማገልገል ላይ ያለ ነው ፡፡

በትምህርት የመጀመሪያ ዲግሪውን ከኦንታሪዬ የትምህርት ጥናት ከማግኘቱ አስቀድሞ በእንግሊዘኛ ቋንቋ የመጀመሪያ ዲግሪውን

ከቶሮንቶ ዩኒቨርስቲ ተቀብሏል፡፡

የኢስላማዊ እውቀት ጉዞውን የጀመረው የዐረብኛ ቋንቋን በመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪነቱ በሚማርበት ወቅት

ነው፡፡ ይህም ተጨማሪ እውቀቶችን ለማግኘት ወደ ውጭ እንዲጓዝ አስችሎታል፡፡ በአሁኑ ጊዜ ቶሮንቶ ካናዳ ውስጥ ከባለቤቱ

ጋር በመኖር ላይ ይገኛል፡፡

ረምዚ አጀም

ረምዚ አጀም ራዚ ግሩፕ (www.razigroup.com) ተባባሪ መስራች ከመሆኑ በተጨማሪ የሥርዓተ ትምህርት ማጐልበቻ

ክፍል ኃላፊ ሆኖ እያገለገለ ይገኛል፡፡ ከዚህም በላይ ሪሳላህ የተሰኘ ድርጀት በማቋቋም ድርጅቱን በአስተዳደርነት እየመራ

ይገኛል፡፡ ይህ ሪሳላህ የተሰኘው ድርጅቱ እስልምናን አዲስ ለተቀበሉ ሙስሊሞች ትምህርታዊና ማህበራዊ አገልግሎቶችን

የሚያቀርብ ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት ነው፡፡

ረምዚ እ.ኤ.አ በ1995 ኢስላማዊ ትምህርቱን ደማስቆ ሶሪያ በሚገኘው አቡ ኑር ኢስላማዊ ተቋም በመጀመር ቀስ በቀስ

በ1998 ወደ ቅደመ ኮሌጅ ትምህርት ፕሮግራም አሳድጓል፡፡ ደማስቆ ውስጥ ሳለ እንደ ሸይኽ ረመዳን አል-ቡጢ፣ ሸይኽ

ኑረዲን ዒጥር እና አዲብ ከላስ ባሉ ታላላቅ ሊቃውንት ዘንድ የተለያዩ ኢስላማዊ እውቀቶችን ቀስሟል፡፡

ኢስላማዊ ትምህርቱን በመቀጠልም ወደ ምዕራብ አቅጣጫ በመጓዝ በሞሮኮ የእስልምናና የወቅፍ ጉዳዮች ሚኒስቴር

በተደረገለት ግብዣ መሠረት በመደበኛ ተማሪነት በጥንታዊ የሃይማኖት መምህራን ማስልጠኛ ተመዝግቦ ትምህርቱን

ተከታትሏል፡፡ ረምዚ በዚህ ተቋም የሙሉ ጊዜ ተማሪ ሆኖ ሲመዘገብ የመጀመሪያው ምዕራባዊ ሰልጣኝ ለመሆን ችሏል፡፡

ሞሮኮ ውስጥ ሳለ ፌስ፣ ሳሌ እና ደቡብ ሞሮኮ ውስጥ ከሚገኙ የተለያዩ ሙስሊም ሊቃውንት የብቃት ማረጋገጫና

የመምህርነት ፈቃድ ለማግኘት ችሏል፡፡

ረምዚ እ.ኤ.አ በ2001 ወደ ቶሮንቶ ከተመለሰ በኋላ ሙስሊሙን ማህበረሰብ በስፋት ሲያገለግል የቆየ ሲሆን በአሁኑ

ጊዜም፡፡ በመደበኛነት በሪሳላህ ት/ቤት ውስጥ እያስተማረ ከሚስቱና ከአራት ልጆቹ ጋር ቶሮንቶ ውስጥ ይኖራል፡፡

Page 11: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - zhic.aeኢስላም፣ ኢማን እና ኢሕሳን 3 አጠቃላይ እይታ 4 መግቢያ 6 የጉዞ መመሪያ 6 ለጉዞ

የአነባበብ መፍቻዎች

ی/آ/ا አሊፍ አ

ب ባ በ

ت ታእ ተ

ث ሣ ሠ

ج ጂም ጀ

ح ሐ ሐ

خ ኻ ኸ

د ዳል ደ

ذ ዛል ዘ

ر ራ ረ

ز ዘይን ዘ

س ሲን ሰ

ش ሺን ሸ

ص ሷድ ሷ

ض ዷድ ደ

ط ጧ ጠ

ظ ዟ ዘ /በጥርስና ምላስ/

ع ዓይን ዐ

غ ገይን ገ

ف ፋ ፈ

ق ቃፍ ቀ

ك ካፍ ከ

ل ላም ለ

م ሚም መ

ن ኑን ነ

ه ሃእ ሀ

و ወው ወ

ي ያ የ

Page 12: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - zhic.aeኢስላም፣ ኢማን እና ኢሕሳን 3 አጠቃላይ እይታ 4 መግቢያ 6 የጉዞ መመሪያ 6 ለጉዞ

የዐረብኛ ምሕጻረ ቃላት

(ሱ.ወ)፡- (ሱብሐነሁ ወተዓላ) ከሁሉ ነገሮች የጠራና የልዕልና ባለቤት የሆነው አላህ፡፡

(ሰ.ዐ.ወ)፡- (ስል-ላሁ ዐለይሂ ወሰልለም) የአላህ እዝነትና ሰላም በእሳቸው ላይ ይሁን፡፡

(ረ.ዐ)፡- (ረዲየል-ላሁ ዐንሁ፣ ረዲየል-ላሁ ዐንሃ፣ ረዲየ-ላሁ ዐንሁም) መልካም ስራውን ይቀበለው፣ መልካም ስራዋን ይቀበላት፣ መልካም ስራቸውን ይቀበላቸው፡፡

(ዐ.ሰ)፡- (ዐለይሂ አስ-ሰላም) የአላህ ሰላም በእሳቸው ላይ ይሁን፡፡

Page 13: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - zhic.aeኢስላም፣ ኢማን እና ኢሕሳን 3 አጠቃላይ እይታ 4 መግቢያ 6 የጉዞ መመሪያ 6 ለጉዞ
Page 14: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - zhic.aeኢስላም፣ ኢማን እና ኢሕሳን 3 አጠቃላይ እይታ 4 መግቢያ 6 የጉዞ መመሪያ 6 ለጉዞ

ማውጫ

ሰንጠረዦችና ምስሎች 1

ኢስላም፣ ኢማን እና ኢሕሳን 3

አጠቃላይ እይታ 4

መግቢያ 6

የጉዞ መመሪያ 6ለጉዞ የሚሆን ምክር 6መንገዱን ማቅረብ 7የጅብሪል (ዐ.ሰ) ሐዲስ 8መለኮታዊው መንገድ 9

ክፍል 1 ፡- ኢስላም (እጅ መስጠት)

ምዕራፍ 1

አጠቃላይ እይታ 12የኢስላም መለያዎች 12አምስቱ መሠረቶች 12የእውቀት አስፈላጊነት 13መለኮታዊው ሕግ 14

ምዕራፍ 2

ሸሃዳህ (የእምነት ምስክርነት) 17የመጀመሪያዎቹ እርምጃዎች 17አዲስ ጅማሮ 18የአምላክን አንድነት ማረጋገጥ 18የነብዩን (ሰ.ዐ.ወ) መልዕክት ማረጋገጥ 19

ምዕራፍ 3ሰላት (ስግደት) 20ወደ ፈጣሪ መገናኛ 20

"የዓይኔ ማረፊያ" 21ሰላትን ወደ ሕይወት ማምጣት 22በሌሎች ወቅቶች መስገድ 23

ምዕራፍ 4ዘካት (የምጽዋት ግብር) 25የመስጠት ግዴታ 25የዘካት መስፈርቶች 26

ምዕራፍ 5በረመዳን ወር መጾም 29አዲሲቷ ጨረቃ 29የጾም አስፈላጊነት 29የጾም ደረጃዎች 30ጾምን መፍታት (መፈሰክ) 30ትምህርቶችን መማር 31

ምዕራፍ 6ሐጅ (መንፈሳዊ ጉዞ) 33የፈጣሪ ቤት 33ለጉዞው መዘጋጀት 34የሐጅ መሰረታዊ ስርአቶች 34ታላቁ መስዋዕት 36ነብዩን (ሰ.ዐ.ወ) መጎብኘት 36

ክፍል ሁለት ፡- ኢማን (እምነት)

ምዕራፍ 7አጠቃላይ ዳሰሳ 40የእምነት ዛፍ 40ስድስቱ መሰረቶች 40

ምዕራፍ 8

በአላህ ማመን 41የፈጣሪ መገለጫዎችና እጅግ

ውብ የሆኑ ስሞቹ 41

የፈጣሪን መለኮታዊ ሕልውና ማወቅ 44አምስቱ አሉታዊ ባሀሪያት 44ሰባቱ ማረጋገጫ ባህሪያት 45ከእዝነት ጋር መኖር 46

ምዕራፍ 9

በመላእክት ማመን 48

የፈጣሪ አገልጋዮች 48የተወሰኑ ልዩ መላዕክት 48

Page 15: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - zhic.aeኢስላም፣ ኢማን እና ኢሕሳን 3 አጠቃላይ እይታ 4 መግቢያ 6 የጉዞ መመሪያ 6 ለጉዞ

ምዕራፍ 10በመለኮታዊ መጽሐፍት ማመን 50

መለኮታዊ ራዕይ 50የፈጣሪ ቃል 5 1

ቁር ኣን በሕይወታችን ውስጥ 52

ምዕርፍ 11በመልዕክተኞች ማመን 54

የላቁ መሪዎች 54የነብይነት መቋጫ 55

ነብያዊ መንገድ 56ነብያዊ የሕይወት ታሪክ 56ነብዩን (ሰ.ዐ.ወ) መውደድ 58

ምዕራፍ 12በመጨረሻው ቀን ማመን 60

የቀኑ ፍጻሜ 60ጉዞ ወደ ቀብር 61የመጨረሻው መተሳሰብ 61ካሳ 62ለፍጻሜው ቀን መዘጋጀት 63

ምዕራ 13በፈርዱ፣ በመጥፎና ጥሩ ገድ ማመን 64

የሁኔታዎች ቅደም ተከተል 64የፈጣሪ ውሳኔ 64ለመለኮታዊ ውሳኔ ምላሽ መስጠት 64

ክፍል ሶስት ፡-ኢሕሳን (ቅንነት)

ምዕራፍ 14

አጠቃላይ ዳሰሳ 68የመንፈሳዊ ቅንነት ቅደም ተከተል 68የእውቀትና የፍቅር መንገድ 68

ምዕረፍ 15ልብና የሰውነት ክፍሎች 70

ምዕራፍ 16የልብ ደረጃዎችና ባህሪያት 72ጸጸት 73ፍራቻ (ኸውፍ) ፣ ተስፋ (ረጃእ) ፣

ትዕግስት (ሰብር) 74

ምዕራፍ 17ቤተሰብና በዙሪያ ያሉ ነገሮች 75

ምዕራፍ 18አላህን (ሱ.ወ) ማስታወስ (ዚክር) 76ክፍል አራት ፡- መብቶች እና ሃላፊነቶች 77

ክፍል አራት ፡- መብቶች እና ሃላፊነቶች

ምዕራፍ 19አጠቃሌ ዳሰሳ 82መግቢያ 82የፈጣሪ መብቶች 83የአላህ መልዕከተኛ (ሰ.ዐ.ወ) መብቶች 83

ምዕራፍ 20

ግላዊ መብቶችና ሃላፊነቶች 85

ሚዛናዊነት 85እኩልነት 85ንጹህ ነገሮችን መመገብ 85የአመጋገብ ሥርዓት 86ጎጂ ንጥረ ነገሮች 86አለባበስ እና ትህትና 87

ምዕራፍ 21ቤተሰባዊ ግንኙነት 88የቤተሰብ አስፈላጊነት 88የጋብቻ ሱንና 89የጋብቻ መብቶችና ሃላፊነቶች 89ጋብቻ ለመመስረት የሚያስፈልግ ምክር 90

ልጆች 91

Page 16: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - zhic.aeኢስላም፣ ኢማን እና ኢሕሳን 3 አጠቃላይ እይታ 4 መግቢያ 6 የጉዞ መመሪያ 6 ለጉዞ

ምዕራፍ 22የአማኞች ማህበረሰብ 93የሙሰሊም ክብር 93ከሌሎች ሙሰሊሞች ጋር መግባባት 93በሙሰሊሞች መካካል ያለን ትስስር ማጠናከር 94

ምዕራፍ 23

ማህበራዊና ህዝባዊ ግዴታዎች 95ሙሰሊም ባልሆነ ማህበረሰብ ውስጥ መኖር 95ከሌላ እምነት ተከታዮች ጋር መቀራረብ 96የብዝሃነት ልቅና 97

ምዕራፍ 24ገንዘብ ነክ ግንኙነቶች 98የፈጣሪን ችሮታ መፈለግ 98ሌሎችን መርዳት 98የስራ ልቅና 98አሰሪዎችና ሰራተኞች 99ብድርና ወለድ 99

ምዕራፍ 25

ተፈጥሮና አካባቢ 100የፈጣሪ ተዓምራት 100አስተዳዳሪነት 100ለአካባቢ እንክብካቤ ማድረግ 100

የወደፊቱ ጉዞ 102

የቃላት መፍቻ 105

የመርጃ መጽሐፍ ጥቆማ 110

ሕዳጎች 112

የፎቶዎች እውቅና 114

Page 17: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - zhic.aeኢስላም፣ ኢማን እና ኢሕሳን 3 አጠቃላይ እይታ 4 መግቢያ 6 የጉዞ መመሪያ 6 ለጉዞ
Page 18: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - zhic.aeኢስላም፣ ኢማን እና ኢሕሳን 3 አጠቃላይ እይታ 4 መግቢያ 6 የጉዞ መመሪያ 6 ለጉዞ

1የሰንጠረዥና ስዕላዊ መረጃዎች

የሰንጠረዥና ስዕላዊ መረጃዎች

ክፍል 1፡- እስልምና (እጅ መስጠት)

ምዕራፍ 1አጠቃላይ እይታ

ሰንጠረዥ፡- የመለኮታዊ ሕግ መመሪያዎች

ዝርዝር፡- የመለኮታዊ ሕግ መመሪያዎች ዓላማ

ክፍል 2፡-በአላህ ማመን

ምዕራፍ 8በአላህ ማመን

ስዕላዊ መረጃ፡- ዘጠና ዘጠኙ የአላህ ስሞች

ዝርዝር፡- አምስቱ ተጻራሪ ባህሪያት

ዝርዝር፡- ሰባቱ ማረጋገጪያ ባህሪያት

ምዕራፍ 9

በመላእክት ማመን

ሰንጠረዥ፡- የተወሰኑ መላዕክቶች

ምዕራፍ 10

በመለኮታዊ መጽሐፍት ማመን

ሰንጠረዥ፡- መለኮታዊ መጽሐፍት

ምዕራፍ 11

በመልዕክተኞች ማመን

ዝርዝር፡- የመልዕክተኞች ሥነ-ምግባራት ሰንጠረዥ፡- ነብያትና መልዕክተኞች

ክፍል 3፡-ኢሕሳን (መልካምነት፣ ሥነ-ምግባር)

ምዕራፍ 15ልብና የሰውነት ክፍሎች

ምዕራፍ 16

የልብ ደረጃዎችና ባህሪያት

አራቱ «መ»ዎች ምዕራፍ 18

አላህን ማስታወስ (ዚክር)

ዝርዝር፡- የዚክር ስልቶች

ክፍል 4፡- መብቶችና ግዴታዎች

ምዕራፍ 21ቤተሰባዊ ግንኙነቶች

ሰንጠረዥ፡- ከእነሱ ጋር ጋብቻ አንዳይፈጽሙ ክልክል የሆኑ

የወንድ እና የሴት ዓይነቶች

Page 19: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - zhic.aeኢስላም፣ ኢማን እና ኢሕሳን 3 አጠቃላይ እይታ 4 መግቢያ 6 የጉዞ መመሪያ 6 ለጉዞ
Page 20: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - zhic.aeኢስላም፣ ኢማን እና ኢሕሳን 3 አጠቃላይ እይታ 4 መግቢያ 6 የጉዞ መመሪያ 6 ለጉዞ

3እስልምና ኢማንና ኢሕሳን

የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) የቅርብ ባልደረባ የሆኑት ዑመር ኢብኑል ኸጣብ (ረ.ዐ) እንዲህ ብለዋል፡-

ከዕለታት አንድ ቀን ከአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ጋር ተቀምጠን ሳለ አንድ ልብሱ በጣም ነጭ፣ ፀጉሩ በጣም

ጥቁር፣ የመንገደኛ ምልክት ፈጽሞ የማይታይበት የሆነና ከእኛ መካከል ማንም የማያውቀው የሆነ ሰው ድንገት

መጣና የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ዘንድ ጉልበቱን ከጉልበታቸው ጋር አጠጋግቶ፣ እጆቹንም ታፋው ላይ አድርጎ

ተቀመጠ፡፡

ከዚያም «ሙሐመድ ሆይ! ስለ እስልምና ንገረኝ» አላቸው፡፡ የአላህ መልዕክተኛም (ሰ.ዐ.ወ)«እስልምና

ማለት ከአላህ በሰተቀር በርግጥ አምልኮ የሚገባው ሌላ አምላክ የለም ሙሐመድ የአላህ መልዕክተኛ ነው ብለህ

መመስከርህ፣ ሶላት መስገድህ፣ ምጽዋትን (ዘካን) መስጠትህ፣ ረመዷንንም መፆምህና አቅምህ ከፈቀደ ቤቱን

መጎብኘትህ (ሐጅ ማድረግህ) ነው» አሉት፡፡ ሰውዬውም «እውነት ብለሃል» አለ ፡፡

የአላህን መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ጠይቆ የምላሹን እውነተኛነት ሲያረጋግጥላቸው በሰውዬው ንግግር በጣም

ተገረምን፡፡ ከዚያም «ስለ ኢማን ንገረኝ» አላቸው፡፡ የአላህ መልዕክተኛም (ሰ.ዐ.ወ) «ኢማን ማለት በአላህ፣

በመልዕክቱ፣ በመጽሐፍቱ፣ በመልዕክተኞቹ እና በመጨረሻው ቀን አይቀሬነትና ሁሉም ነገር (መልካሙም ሆነ

መጥፎ) በአላህ ውሳኔ የሚከሰት መሆኑን ማመንህ ነው» አሉት ሰውዬውም «እውነት ብለሃል» አለ፡፡ ቀጥሎም

«ስለ ኢሕሳን ንገረኝ» አለ፡፡ የአላህ መልዕክተኛም (ሰ.ዐ.ወ) «አላህን እንደምታየው ሆነህ ልትገዛው ነው፡፡

አንተ ልታየው ባትችል እንኳ እርሱ ያይሃልና» አሉት፡፡ ከዚያም «ስለትንሳኤ ቀን (ስለየውመል ቂያማህ) ንገረኝ»

አለ፡፡ የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) «ተጠያቂው ከጠያቂው የበለጠ አያውቅም»

አሉት፡፡ እርሱም መልሶ «ስለ ምልክቶቿ ንገረኝ» አለ ፡፡ እርሳቸውም ፣ «ባሪያ እመቤትዋን ትወልዳለች፣ ጫማ

የሌላቸው፣ የታረዙና እረኛ የነበሩ ሰዎች ታላላቅ ሕንፃዎችን ለመገንባት ሲፎካከሩ ታያለህ» አሉት፡፡

ከዚያ በኋላ ሰውዬው ሄደ እኔም እዚያው ለጥቂት ጊዜ ቆየሁ፡፡ የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) «ዑመር ሆይ! ይህ

ሰው ማን እንደሆነ ታውቃለህን?» አሉኝ፡፡ እኔም «አላህና መልዕክተኛው የበለጠ ያውቃሉ» አልኳቸው፡፡ እርሳቸውም

«ይህ ጅብሪል ነው፡፡ እምነታችሁን ሊያስተምራችሁ ነው የመጣው» አሉ፡፡ (ሶሒሕ ሙስሊም)

እስልምና ኢማንና ኢሕሳን

Page 21: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - zhic.aeኢስላም፣ ኢማን እና ኢሕሳን 3 አጠቃላይ እይታ 4 መግቢያ 6 የጉዞ መመሪያ 6 ለጉዞ

መለኮታዊው መንገድ፡-የአዲስ ሙስሊሞች ስርዓተ ትምህርት4

«ነገሮችን ቀላል አድርጉ፡፡ አታክብዱ፡፡» ይህ መጽሐፍ የሚከተለው ታላቅ የትምህርት መሠረት በዚህ የነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ሐዲስ ላይ ጥገኛ ነው፡፡

እጅግ በጣም ተአማኒነት ካላቸው ሙስሊም ምሁራን መካከል አንዱ የሆኑት ኢብኑ ሐጅር አል-ዐስቀላኒይ (አላህ ይዘንላቸውና) ከላይ የተመለከተውን ሐዲስ አስመልክተው ሲናገሩ፣ «ሐሳቡ ለአዳዲስ ሙስሊሞች እጅጉን ተስማሚ ነው» ብለዋል፡፡ በትክክል የዚህ መጽሐፍ አንባቢያን አዳዲስ ሙሰሊሞች በመሆናቸው እኛም ይህን ነብያዊ ሐዲስ በልቦናችን ውስጥ በወጉ አስቀምጠናል፡፡ ኢብኑ ሐጅር አክለው እንዲህ ብለዋል፣ «ስለዚህ እውቀት ደረጃ በደረጃ ሲሆን መልካም ነው፡፡ አንድ ርዕሰ ጉዳይ ከጅማሬው ቀላል ከሆነ ማንኛውም ሰው ጉጉት አድሮበት ወደ ውስጥ እንዲገባ ከማድረጉ ባሻገር ትምህርቱንም በደስታ መንፈስ እንዲማር ያስችለዋል» ብለዋል፡፡

የዚህ መጽሐፍ አብይ ዓላማ ጠቅለል ያሉ የኢስላም ማዕዘናትን፣ የኢማን መሠረቶችንና የኢሕሳን መንገዶችን በሚማርክ እና ሰፋ ባለ ሁኔታ እስልምናን ለተቀበሉ አዳዲስ ሙሰሊሞች ማቅረብ ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪም የተወሰኑ ቁልፍ የሆኑ ሥነ-ምግባሮችንና ማንኛውም አዲስ ሙሰሊም የሚፈልገውን ተግባራዊ ምክሮች ማቅረብ ነው፡፡የሥነ-ትምህርታዊው ይዘታችን ዓላማ ግቡን ይመታ ዘንድ፤ የመጽሐፉ ፍሬ ሃሳቦች ከዚህ በላይ በተቀመጠውና በጣም በሚታወቀው የጅብሪል (ዐ.ሰ) ሐዲስ ነብያዊ ቅደም ተከተሎችን ጠብቀው ተቀምጠዋል፡፡ ወደ ሃይማኖቱ አዲስ ለሚመጡ በእያንዳንዱ ክፍል ሥር ያለው ማብራሪያ በውስጡ መግቢያ፣ ግላዊ ምክር እና አስፋላጊ የሆኑ ትምህርቶች ተካትተውበታል፡፡ የመጽሐፉ ቋንቋ ሆን ተብሎ ግልጽ እና ምሁራዊ ያልሆነ እንዲሆን ተደርጓል፡፡ እንደዚሁም ሰፋ ያሉ ማስረጃዎችና ሃይማኖታዊ ዝርዝር ሃሳቦችም በትንሹ ተቀምጠዋል፡፡

እስልምናን የተቀበሉ ሰዎች በጊዜው ካለው ሕብረተሰብ ጋር እንዲቀላቀሉ ለመርዳትም መጽሐፉ በውስጡ መብትና ኃላፊነቶችን መሠረት ያደረገ በተለይ ሰዎች ከፈጣሪያቸው፣ ከራሳቸው እና በዙሪያቸው ካሉት ጋር የሚኖራቸውን ግንኙነት፣ ተግባራዊ የአኗኗር ዘይቤ ክፍል አካቷል፡፡ እስልምናን የተቀበሉ አዳዲስ ሙሰሊሞችን ለመምራትና ተጨማሪ ጥናትንም ለማረጋገጥ ይረዳ ዘንድ ተአማኒና ደረጃቸውን የጠበቁ ሃይማኖታዊ አስተምህሮዎች በመጽሐፉ በሚመከሩ የንባብ ክፍሎች ውስጥ ተካተዋል፡፡

አብዛኛዎቹ እስልምናን የተቀበሉ ሰዎች ሙስሊም ከሆኑ በኋላ ከሚያጋጥሟቸው ችግሮች መካከል አንዱ በርካታ ቁጥር ካላቸው በዐረብኛ ቋንቋ ከተቀመጡ ሃይማኖታዊ ቃላት ጋር መተዋወቅ ነው፡፡ ይህን መደናገር ለመቀነስና ትምህርቱን የተፋጠነ ለማድረግ ሲባል እነዚህ ሃይማኖታዊ ቃላት በተደጋጋሚ ሲጠቀሱ ትርጉማቸው እጥር ምጥን ባለ ሁኔታ ከጎናቸው የተቀመጠ ሲሆን በተጨማሪም በመጽሐፉ መጨረሻ በቃላት መፍቻ ስር በድጋሚ ፍቺያቸው ተቀምጧል፡፡

በሚቻለው አቅም መጽሐፉ የሚስብና ተቀባይነት ያለው ይሆን ዘንድ መርጃ ሰንጠረዦች፣ ኢስላማዊ ትውፊቶችን የሚያንጸባርቁ ምስሎች እና በአንድ ወቅት ወደ መለኮታዊው መንገድ የመጡ ሰዎች አስፈላጊ ምክሮችና ተሞክሮዎች ተካተው ቀርበዋል፡፡ በመጽሐፉ ውስጥ በጥንቃቄ የተዘጋጁት ፍሬ ሃሳቦች እና የመጽሐፉ ገጽታዎች ተማሪዎች በግል እንዲያነቧቸው የተዘጋጁ ቢሆንም መጽሐፉን ብቃት ካለው ሰው ጋር መማር ይበረታታል፡፡ በንጽሕና፣ ስግደት እና ፆም ላይ ያተኮሩ የተወሰኑ አስተምህሮዎች ከዚህ ጋር ተያያዥነት ካለውና መለኮታዊው መንገድ የመጀመሪያ ትምህርት በአምልኮት ላይ የተሰኘ ርዕስ ባለው መጽሐፍ ቅጽ ውስጥ ይገኛሉ፡፡

መቅድም

Page 22: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - zhic.aeኢስላም፣ ኢማን እና ኢሕሳን 3 አጠቃላይ እይታ 4 መግቢያ 6 የጉዞ መመሪያ 6 ለጉዞ

5መቅድም

ይህ መጽሐፍ መልካም የሆኑ ሃይማኖታዊ ግንዛቤዎችን ያገኙ ዘንድ እስልምናን ለተቀበሉ አዳዲስ ሙስሊሞች ሁኔታዎችን ያመቻቻል የሚል ተስፋ ተጥሎበታል፡፡ ይህን መረዳት ደግሞ አዲስ ያገኙትን እምነት ከንጽጽራዊ፣ ሚዛናዊነትና ምክንያታዊነት ስሜት ጋር እንዲያመቻቹ ያደርጋቸዋል፡፡

ሐሰን ላም

ረምዚ አጀም

Page 23: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - zhic.aeኢስላም፣ ኢማን እና ኢሕሳን 3 አጠቃላይ እይታ 4 መግቢያ 6 የጉዞ መመሪያ 6 ለጉዞ

መለኮታዊው መንገድ፡-የአዲስ ሙስሊሞች ስርዓተ ትምህርት6

መግቢያ የጉዞው የመጀመሪያ እርምጃዎች

እንኳን ወደ እስልምና በደህና መጡ፡፡ በዚህ የተባረከ ጉዞ ለመሳፈር እርሶ የመጀመሪያውም የመጨረሻውም ሰው አይደሉም፡፡ እስልምና ሰፊ እና እየተለጠጠ የሚሄድ መንገድ ነው፡፡ በውስጡ ሰፊ የሆነ ክፍል እንዲሁም ጥሩ ጓደኛ ያገኛሉ፡፡ ይህ መንገድ ልክ እንደ ማንኛውም ጉዞ በልባዊ ጥንካሬና በአንድ እርምጃ ይጀምራል፡፡

ሰዎች በተለያዩና ማለቂያ በሌላቸው ምክንያቶች ወደ እስልምና ይመጣሉ፡፡ የርሶ በዚህ መንገድ ላይ መሳፈርም፤ ክቡር እና አስደሳች ከሆነ ግላዊ ውሳኔ የመነጨ መሆን አለበት፡፡ ይህንን ጉዞ እንደ መጀመርዎ ምናልባት በበርካታ ነገሮች ሊገረሙ ይችሉ ይሆናል፡፡ ግና በትክክል ወዴት እየሄዱ ነው ያሉት?! ምን ዓይነትስ ስንቅ ነው የሚያስፈልግዎት? በመንገድዎ ላይ ምን ያጋጥምዎታል? እንዲሁም በጣም አስፋላጊው ነገር መንገድዎን እንዴት አግኝተው ወደ መዳረሻዎ ሊደርሱ ይችላሉ? እስልምናን የመረጡ ሰዎች እነዚህንና ሌሎች መሰል ጥያቄዎችን ይጠየቃሉ፡፡

የጉዞ መመሪያ

ይህ «መለኮታዊው መንገድ-ለአዲስ ሙሰሊሞች መርጃ መጽሐፍ» የሚለው መጽሐፍ የተዘጋጀው ከላይ ለተዘረዘሩት ጥያቄዎች በቂ ምላሽ ታገኙ ዘንድ ለመርዳትና እግረመንገዱንም ድጋፍንና ማነሳሳትን ለማድረግ ነው፡፡ መጽሐፉ አዲስ ሙስሊም ለሆናችሁት የመንገዱን መግለጫ ከማቅረቡ በተጨማሪ የእስልምናን መረጃዎች ያስተዋውቃል፡፡ ስለዚህ በራስ የመተማመን መንፈስ አዲሱን የሕይወት መንገዳችሁን ተግባራዊ እንድታድረጉ ይረዳችኋል፡፡

ይህ መንገድ የመንፈሳዊ እድገትና የራስ ብልጽግና የእድሜ ልክ ጉዞ ነው፡፡ በዚህ ጉዟችሁ ባልተለመደ ሁኔታ ውስጥ ውጣ ውረዶችንና ተግዳሮቶችን ከጊዜ ወደ ጊዜ ትጋፈጣላችሁ፡፡ እውነታው ይህ ቢሆንም እስልምና በምስጋናና በጥረት የሚገኝ ከፈጣሪ የተሰጠ ውድ መመሪያ ነው፡፡

ፈጣሪ አንድን ሰው ከመራው ለእርሱ ወይም ለእርሷ ሁሉንም ነገሮች ክፍት በማድረግ ወደ እስልምና የሚወስዱትን የመጀመሪያ እርምጃዎች ምቹ ያደርግለታል፡፡ አላህ እንዲህ ብሏል፣

አላህም ሊመራው የሚሻውን ሰው ደረቱን (ልቡን) ለኢስላም ይከፍትለታል... (አል-አንዓም፡ 125)

ስለጉዞው አንዳንድ ምክሮች

ወደማንኛውም ጠቃሚ መዳረሻ በሚደረግ ጉዞ እንደሚሆነው ሁሉ፣ ይህ መንገድም ሥራንና ቆራጥነትን ይጠይቃል፡፡ በሁሉም ጥረቶቹ ተጠቃሚ ይሆን ዘንድ ማንኛውም ሰው የተወሰኑ ነጥቦች አእምሮው ውስጥ ሊቀመጡ ይገባል፡፡ እነርሱም፡-

በመጀመሪያ፣ የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- «ማንኛውም ድርጊት የሚመነዳው በልበ-ውሳኔዎች አንጻር ነው፡፡»3 «የመልካም ሥራዎች ምንዳ በልባዊ እሳቤዎች (ኒያዎች) ልክ ነው፡፡»ወደ አላህ ለመቅረብ በሚል ልባዊ-ውሳኔ (ኒያ) ጉዞህን ጀምር፡፡ በመልካም እሳቤ (ኒያ) ላይ የተመሠረተ ትምህርትም በረከት ያልተለየው አምልኮታዊ ተግባር (ኢባዳ) ይሆናል፡፡

ሁለተኛ፣ የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- «በአላህ ዘንድ እጅግ የተወደዱ መልካም ተግባራት ማለት ጥቂትም ቢሆኑ ዘውትር የሚሠሩ መልካም ሥራዎች ናቸው፡፡»4 ደረጃቹን በሚመጥን መልኩ አንብቡ፣ ተማሩ፡፡ ከዚያም የተማራችሁትን ነገር ወደተግባር ለውጡ፡፡ በመጨረሻም ከምታደርጓቸው ጥረቶቻችሁ ባሻገር ድል ከአላህ ዘንድ እንደሚመጣ አስተውሉ፡፡ ሁላችንም

Page 24: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - zhic.aeኢስላም፣ ኢማን እና ኢሕሳን 3 አጠቃላይ እይታ 4 መግቢያ 6 የጉዞ መመሪያ 6 ለጉዞ

7መግቢያ

ዘውትር ወደ አላህ መመለስ እና ከፊት ለፊታችን የሚያጋጥሙንን እንቅፋቶች ያሰወግድልን ዘንድ እርዳታውን መጠየቅ ይኖርብናል፡፡ ትምክህታችንንም በእሱ ላይ ማድርግ አለብን፡፡ አላህ እንዲህ ብሏል፡፡

አላህ የእነዚያ ያመኑት ሰዎች ረዳት ነው ከጨለማዎች ወደ ብርሃን ያወጣቸዋል…(አል-በቀራህ፡ 257)

ወደ መንገዱ መቃረብ

እስልምና ከአላህ የወረደ የመጨረሻው መለኮታዊው መገለጽ እንደመሆኑ መልከ ብዙና እንደ አካላዊ፣ አእምሯዊ፣ ስሜታዊና መንፈሳዊ ያሉትን ዘርፎች የሚዳስስ የአኗኗር ዘይቤ ነው፡፡

ሃይማኖትን እንዴት መረዳትና መቅረብ ይቻላል? የሚለውን መወሰን በራሱ በጣም የሚከብድ ተግዳሮት ሊሆን ይችላል፡፡ ይሁን እንጂ ለዚህ በጣም የተሻለው መንገድ የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ከመለኮታዊው ርዕዮት ጋር እንዴት ይኖሩ ነበር ብሎ መመርመርና ፈለጋቸውን ማጥናት ነው፡፡ እንደ መጨረሻ የአላህ መልዕክተኛነታቸው ሚናቸው ቁርኣንን ማስተላለፍ ብቻ ሳይሆን በሱንናቸው ተግብረውና ሕይወቱን ኖረው ማሳየት ሲሆን ሁኔታው በቁርኣን እንዲህ ተብሎ ተጽፏል፡- ›LI uU�S“” Là ŸÔd†¨< ¾§’”& u’`c<

Là ›”k뇔 ¾T>Á’w. ¾T>Ö^†¨<U.

SêNõ”“ Øuw” ¾T>Áe}U^†¨<U ¾§’”

SM¡}— u¨<e׆¨< uLŸ Ñ>²?. u�`ÓØ KÑcL

†¨<& �’`c<U Ÿ²=Á uòƒ uÓMê eI}ƒ

¨<eØ ’u\:: (ኣለ-ዒምራን፡ 164)

የነብዩን (ሰ.ዐ.ወ) ሕይወት የተመለከቱ አብይ የእውቀት ምንጮች ሁሉ በነቢያዊው ሐዲስ ማለትም ንግግሮቻቸው፣ ድርጊቶቻቸው፣ ትክክልና ትክክል ያልሆኑ ያሏቸው ሁነቶች ውስጥ በሙሉ ተጽፈው ይገኛሉ፡፡ እነዚህ መልዕክቶች ተጠብቀው የተላለፉት በባልደረቦቻቸውና ከዚያ በኋላ በተከታታይ በመጡ ትውልዶች በኩል ነው፡፡

ሌላኛው የሐዲስ ዓይነት ደግሞ ከአላህ ከራሱ ለነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) የተላለፈላቸው ነብዩም (ሰ.ዐ.ወ) በራሳቸው አባባል ለሌሎች ያስተላለፉት ንግግር ሲሆን ሐዲስ አል- ቁድስ በመባል ይታወቃል፡፡ ሐዲስ አል-ቁድስ ከቁርኣን የሚለየው የቁርኣን ቃላትም ሆኖ መልዕክቱ ከአላህ በቀጥታ ለነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) የወረደ በመሆኑ ነው፡፡

አንድ ከጅብሪል (ዐ.ሰ) ጋር በቀጥታ የተያያዘ ነቢያዊ ሐዲስ ግልጽና ስልታዊ በሆነ አቀራረብ እስልምናን የተለያዩ ገጽታዎች እንድናውቅና አንዱ ከሌላኛው ጋር እንዴት እንደሚዛመድ እንድንረዳ አድርጎናል፡፡ ይህም የሃይማኖቱን መሠረታዊ ነገሮች በማብራራት በተግባራዊ ደረጃ እንድናውቅ ያስችለናል፡፡

እውቀትን ለመፈለግ መንገድ የተጓዘ አላህ ወደ ጀነት የሚያመራውን መንገድ ያገራለታል — ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)“

Page 25: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - zhic.aeኢስላም፣ ኢማን እና ኢሕሳን 3 አጠቃላይ እይታ 4 መግቢያ 6 የጉዞ መመሪያ 6 ለጉዞ

መለኮታዊው መንገድ፡-የአዲስ ሙስሊሞች ስርዓተ ትምህርት8

የጅብሪል (ዐ.ሰ) ሐዲስ

የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) የቅርብ ባልደረባ የሆኑት

ዑመር ኢብኑል ኸጣብ (ረ.ዐ) እንዲህ ብለዋል፡-

ከዕለታት አንድ ቀን ከአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ)

ጋር ተቀምጠን ሳለ አንድ ልብሱ በጣም ነጭ፣ ፀጉሩ

በጣም ጥቁር፣ የመንገደኛ ምልክት ፈጽሞ የማይታይበትና

ከእኛ መካከል ማንም የማያውቀው የሆነ ሰው ድንገት

መጣና የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ዘንድ ጉልበቱን

ከጉልበታቸው ጋር አጠጋግቶ፣ እጆቹንም ታፋው ላይ

አድርጎ ተቀመጠ፡፡

ከዚያም «ሙሐመድ ሆይ! ስለ እስልምና ንገረኝ»

አላቸው፡፡ የአላህ መልዕክተኛም (ሰ.ዐ.ወ)«እስልምና

ማለት ከአላህ በሰተቀር በርግጥ አምልኮ የሚገባው ሌላ

አምላክ የለም ሙሐመድ የአላህ መልዕክተኛ ነው ብለህ

መመስከርህ፣ ሶላት መስገድህ፣ ምጽዋትን (ዘካን)

መስጠትህ፣ ረመዷንንም መፆምህና አቅምህ ከፈቀደ ቤቱን

መጎብኘትህ (ሐጅ ማድረግህ) ነው» አሉት፡፡ ሰውዬውም

«እውነት ብለሃል» አለ፡፡ የአላህን መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ)

ጠይቆ የምላሹን እውነተኛነት ሲያረጋግጥላቸው በሰውዬው

ንግግር በጣም ተገረምን አሉ ዐመር (ረ.ዐ)- ፡፡ ከዚያም

«ስለ ኢማን ንገረኝ» አላቸው፡፡

የአላህ መልዕክተኛም (ሰ.ዐ.ወ) «ኢማን ማለት

በአላህ፣ በመልዕክቱ፣ በመጽሐፍቱ፣ በመልዕክተኞቹ

እና በመጨረሻው ቀን አይቀሬነትና መልካምም ሆነ

መጥፎ ነገር የሚከሰተው በአላህ ውሳኔ (ቀደር)

መሆኑን አምነህ መቀበልህ ነው» አሉት፡፡

ሰውዬውም «እውነት ብለሃል» አለ፡፡ ቀጥሎም

«ስለ ኢሕሳን ንገረኝ» አለ፡፡ የአላህ መልዕክተኛም

(ሰ.ዐ.ወ) «አላህን እንደምታየው ሆነህ ልትገዛው

[ከላይ] ትልቁ የሸይኽ ዛይድ መስጂድ፣ አቡ ዳቢ - የተባበሩት ዐረብ ኤሜሬቶች

Page 26: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - zhic.aeኢስላም፣ ኢማን እና ኢሕሳን 3 አጠቃላይ እይታ 4 መግቢያ 6 የጉዞ መመሪያ 6 ለጉዞ

9መግቢያ

ነው፡፡ አንተ ልታየው ባትችል እንኳ እሱ ያይኻልና» አሉት፡፡

ከዚያም «ስለትንሳኤ ቀን (ስለየውመል ቂያማህ) ንገረኝ»

አለ፡፡ የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) «ተጠያቂው

ከጠያቂው የበለጠ አያውቅም» አሉት፡፡ እርሱም መልሶ

«ስለ ምልክቶቿ ንገረኝ» አለ ፡፡ እርሳቸውም (ሰ.ዐ.ወ)፣

«ባሪያ እመቤትዋን ትወልዳለች፣ መጫሚያ የሌላቸው፣

የታረዙና እረኛ የነበሩ ሰዎች ታላላቅ ሕንፃዎችን ለመገንባት

ሲፎካከሩ ትመለከታለህ» አሉት ፡፡

ከዚያ በኋላ ሰውዬው ሄደ እኔም እዚያው ለጥቂት ጊዜ

ቆየሁ፡፡ የአላህ መልዕክተኛ (ሶ.ዐ.ወ) «ዑመር

ሆይ! ይህን ጠያቂ ሰው ማን እንደሆነ ታውቃለህን?»

አሉኝ፡፡ እኔም «አላህና መልዕክተኛው በተሻለ ያውቃሉ»

አልኳቸው፡፡ እሳቸውም «እሱ በርግጥ ጅብሪል ነው፡፡

እምነታችሁን ሊያስተምራችሁ ነው የመጣው» አሉ፡፡

(ሶሒሕ ሙስሊም)

መለኮታዊው መንገድ

የጅብሪል (ዐ.ሰ) ሐዲስ ይህን ሃይማኖት የሚያብራሩ ሶስት

መሰረታዊና ተዛማጅነት ያላቸውን ገጽታዎች እንረዳ ዘንድ

መሠረታዊ ማዕቀፎችን አስቀምጦሎናል የመጀመሪያው

ገጽታ በአምስት እጅግ በጣም አስፈላጊ በሆኑ የተለያዩ

ውስጣዊና ውጫዊ ስልጠናዎች የተከበበው እስልምና

ራሱ ነው፡፡ ሁለተኛው ገጽታ መለኮታዊውን መገለጽ

እንረዳ ዘንድ የሚያስችለን እውቀትንና እምነትን

አጠቃሎ የያዘው ኢማን (እምነት) ነው፡፡

ሶስተኛው ገጽታ ግለሰቦች ትህትናን የተላበሰ አምልኮትን

በተሟላ ሁኔታ ይፈጽሙ ዘንድና በእያንዳንዷ ተግባራቸው

ፈጣሪ እንደሚመለከታቸው የሚያረጋግጥላቸው ኢሕሳን

የተሰኘው ነው፡፡

በመጨረሻም እነዚህ ሦስት ገጽታዎች ለፍርዱ ቀን

ለመዘጋጀት በዕለት ተዕለት ሕይወታችን ውስጥ

ተግባራዊ የምናደርጋቸው ናቸው፡፡ ይህ መዘጋጀት እኛ

በምንጠቀምባቸው መብቶችና በራሳችን ዙሪያ ባሉ

የአላህና የሌሎች አካላት ሃላፊነቶች የተከበቡ ናቸው፡፡

አላህ ወደ እሰልምና የምታድረገውን ጉዞህን ገርና ቀላል

እንዲያደርግልህ እንጸልይልሃለን፡፡ እያንዳንዱ እርምጃህ

ውጤታማ ሆኖ በጉዞህ መልካም እንዲገጥምህም

እንመኛለን፡፡ አላህ መንገድህን ቀና አድርጎ በቀጣዩ

ዓለም ጀነትን የምትጎናጸፍ ያድርግህ፡፡

Page 27: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - zhic.aeኢስላም፣ ኢማን እና ኢሕሳን 3 አጠቃላይ እይታ 4 መግቢያ 6 የጉዞ መመሪያ 6 ለጉዞ
Page 28: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - zhic.aeኢስላም፣ ኢማን እና ኢሕሳን 3 አጠቃላይ እይታ 4 መግቢያ 6 የጉዞ መመሪያ 6 ለጉዞ

እስልምና (እጅ መስጠት)

«እስልምና ማለት ከአላህ በሰተቀር በርግጥ አምልኮ የሚገባው ሌላ አምላክ የለም ሙሐመድ የአላህ መልዕክተኛ ነው ብለህ መመስከርህ፣ ሶላት መስገድህ፣ ምጽዋትን (ዘካን) መስጠትህ፣ ረመዷንንም መፆምህና አቅምህ ከፈቀደ ቤቱን መጎብኘትህ (ሐጅ ማድረግህ) ነው» የጅብሪል (ዐ.ሰ) ሐዲስ

Page 29: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - zhic.aeኢስላም፣ ኢማን እና ኢሕሳን 3 አጠቃላይ እይታ 4 መግቢያ 6 የጉዞ መመሪያ 6 ለጉዞ

መለኮታዊው መንገድ፡-የአዲስ ሙስሊሞች ስርዓተ ትምህርት12

አጠቃላይ እይታ

የእስልምና መሠረተ ሃሳብበሰው ልጆች ታሪክ አላህ ወደተለያዩ ሕዘቦችና ጎሳዎች በርካታ ቁጥር ያላቸውን ነብያትና መልዕክተኞችን የላከ ሲሆን ተመሳሳይና አስፈላጊ መልዕክትን ይዘው መጥተዋል፡፡ ¨Ñ•Š JÃ! ›LI” }Ѳ<& K“”} Ÿ`c< K?L

U”U ›UL¡ ¾L‹G<U& ...(አል-አዕራፍ፡ 59)

የመጨራሻው መልዕክተኛ የሆኑት ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) የአላህን አንድነትና ብቸኝነት እንደገና ለማጠናከርና ከአላህ በሚቀበሉት መለኮታዊ ርዕይ መሠረት ሰዎች እንደገና እርሱን ወደ መገዛት ይመለሱ ዘንድ ለሰዎች በአጠቃላይ ተልከዋል፡፡

ይህ አምልኮ በፈጣሪ ፊት መተናነስና በቅንነት ለእርሱ ፍላጎት እጅ መስጠትን ይጠይቃል፡፡ ይህ ደግሞ የእስልምና መሠረታዊ ትርጓሜ ነው፡፡ እውነተኛ እጅ መስጠት የሚመጣው ለእርሱ መለኮታዊነት በቅድሚያ እውቅና ከመስጠት እና በውጫዊም ሆነ ውስጣዊ መንፈስ ከመለኮታዊ ትዕዛዛቱ ጋር ከመስማማትና ከመቀበል በኋላ ነው፡፡

በጣም አፍቃሪ የሆነው አላህ መልዕክተኛው (ሰ.ዐ.ወ) ለሰው ልጆች እንዲህ ብለው እንዲናገሩ ነግሯቸዋል፣ "በላቸው፡-

›LI” ¾Uƒ¨Æ �”ŧ“‹G< }Ÿ}K<˜&

›LI èNj%EM“& %Ö=œ„‰‹G<”U K“”}

ÃU^M“& ›LIU SP] ›³˜ ’¨<::(ኣለ-ዒምራን፡ 31)

የሰው ልጅ ልቦና ሰላምና እርጋታን ሊያገኝ የሚችለው ፍላጎቶቹና ዝንባሌዎቹ ከመላኮታዊው ሕግ ጋር ስምምነት ሲያሳዩ ነው፡፡ በአምልኮ መንገድ ላይ ተጨማሪ ጥረት ማድረግ መጽናት ከፈጣሪ ጋር ያለውን ትስስር እንዲንናፍቅ በማድረግ የሚፈጥረውን ደስታና ፍስሐን ያጎናጽፋል፡፡

አምስቱ ምሰሶዎችበጅብሪል (ዐ.ሰ) ሐዲስ ላይ በተጠቀሰው መሠረት ለአላህ እጅ መስጠት የሚጀምረው አላህ አንድ እንደሆነና ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) የእርሱ መልዕክተኛ መሆናቸውን በማወጅ ነው፡፡ ይህ የመጀመሪያና መሠረታዊ የሆነ ምሰሶ ለታላቅ ቁም ነገርና ዓላማ የሚያበቃውን የሕይወት መንገድ ይከፍትልናል፡፡

የዚህ የማዕከላዊ ምሰሶ መሠረት አንዴ በወጉ ከቆመ ቀሪዎቹ ምሶሶዎች ሃይማኖታዊ ሕይወታችንን መዋቅሮች የሚደግፉ ናቸው፡፡ እነርሱም ሶላት መስገድ፣ ምጽዋት (ዘካት) መስጠት፣ የረመዷንን ወር መጾም እና የተቀደሰውን ቤት መጎብኘት (ሐጅ) ናቸው፡፡

1

Page 30: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - zhic.aeኢስላም፣ ኢማን እና ኢሕሳን 3 አጠቃላይ እይታ 4 መግቢያ 6 የጉዞ መመሪያ 6 ለጉዞ

13ክፍል 1 ፡- እስልምና

ለአላህ ታማኝ መሆን በውስጡ እነዚህን አምስት ምሰሶዎች ማሟላትን አካትቶ ይዟል፡፡ ነገር ግን እነዚህን ተግባራት በአግባቡ ለመፈጸም አንድ ሰው አስፈላጊ የሆነ ዕውቀት በመማር መጀመር ግድ ይለዋል፡፡

የእውቀት አስፈላጊነት

በቁርአን ላይ አላህ አማኞች እውቀትን ይፈልጉ ዘንድ

እንዲህ በማለት ያበረታታል፡፡

… አላህ ከናንተ እነዚያን ያመኑትንና እነዚያንም

ዕውቀትን የተሰጡትን በደረጃዎች ከፍ ያደርጋል፤ አላህም

በምትሠሩት ሁሉ ውስጠ ዐዋቂ ነው፡፡ (አል-ሙጃደላህ፡ 11)

ገና በመለኮታዊው መገለጽ ጅማሮ «አንብብ በዚያ

(ሁሉን) በፈጠረው ጌታህ ስም» (አል-ዐለቅ፡ 1)

አላህ መልካም ነገር የሻለትን ሰው በሃይማኖት ላይ ዐዋቂ ያደርገዋል፡፡ —ነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)

በማለት አላህ እስልምናን የእውቀትና የምርምር ሃይማኖት

አድርጎታል፡፡ «እውቀትን መፈለግ በእያንዳንዱ ሙስሊም

ላይ ግዴታ ነው»6 በሚለው የነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ትዕዛዝ

መሠረት ሙስሊሞች ሁሌም እውቀትን ለመፈለግ ረጅም

ርቀት ይጓዛሉ፡፡

እውቀት ፈላጊዎች ለሆኑ ሁሉ መሠረታዊው መነሻ ነጥብ

ትክክለኛ አውቀትን መፈለግ ነው፡፡ አምልኮት እርሱ

ባስቀመጠው መለኮታዊ መንገድ ወደ አላህ መቃረቢያ

ተግባር እንደመሆኑ አላህን እንዴት ማምለክ እንደሚገባ

ማወቅ በጣም አስፈላጊ ነው፡፡

ስለዚህ ቀድሞውኑ የመማር አጋጣሚውን ያላገኙት ምን

ይሁኑ? ከእዝነቱ የተነሳ አላህ ባላወቁት ነገር ተጠያቂ

አያደርጋቸውም፡፡ እውነታው ይህ ቢሆንም ቅሉ መማር

ግዴታቸው መሆኑ ግን እንደጸና ይቆያል፡፡

Page 31: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - zhic.aeኢስላም፣ ኢማን እና ኢሕሳን 3 አጠቃላይ እይታ 4 መግቢያ 6 የጉዞ መመሪያ 6 ለጉዞ

መለኮታዊው መንገድ፡-የአዲስ ሙስሊሞች ስርዓተ ትምህርት14

የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) «የድንቁርና መድኃኒት

መጠየቅ ነው»7 ብለዋል፡፡

እስልምና ታላቅ የሆነ የእውቀት ታሪክና ሰፊ መለኮታዊ

ሥርአት አለው፡፡ በረጅሙ የእስልምና ታሪክ ዛሬም

ድረስ ከተለያዩ የአማኝ ክፍሎች የተነሱ የተለያዩ ከባባድ

ጥያቄዎችን በትክክለኛው መንገድ የተመሩ ሙስሊም

ምሁራን በአግባቡ መልሰዋል፡፡ የአላህ መልዕክተኛ

(ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፣ «ዑለሞች (ምሁራን)

የነቢያት ወራሾች ናቸው»

ሰፊው የእስልምና ዕውቀት አድማስ እውነቱን ለሚፈልጉ

ሁሉ ትክክለኛውንና የስኬቱን መንገድ በተለያዩ ዘርፎች

በሚያመላከቱ ታላላቅ እና ፈሪሃ አላህ ያላቸው በሆኑ

ምሁራን ደማቅ ምክር ያሸበረቀ ነው፡፡ እነዚህ የዕውቀት

ባለቤት የሆኑ ወንዶችና ሴቶች ትምህርታቸውን ያገኙት

በታላቅ ስነ-ምግባር፣ ታጋሽነት በተሞላበት ጥረት ነው፡፡

ይህም ሊሳካ የቻለው እውቀትንና መመሪያን

ከነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) ከተቀበሉ ሰዎች ተያያዥነት

ባለው ሰንሰለታዊ ትስስር በመምህራኖቻቸው በኩል

በተደረገ ጥንቃቄ የታከለበት ጥረት ነው፡፡ እነዚህ ሰዎች

የተጣሉባቸውን ሃላፊነቶች የሚያከብሩ፣ ያወቁትን ነገር

ተግባራዊ የሚያደርጉ እንዲሁም ያሏቸውን የእውቀት

ሀብቶች ለሌሎች የሚያካፍሉ ነበሩ፡፡

የምንቀስማቸው በርካታ እውቀቶች ያሉ ቢሆንም እኛ

ግን መጀመር ያለብን ግዴታዎቻችንን እንድንወጣ

የሚያስችሉንን ለምሳሌ እንዴት ነው የምንሰግደው

የሚለውን የመሳሰሉ እውቀቶችን ነው፡፡

ያወቅነውን ወደ ተግባር ስንቀይር እውቀታችን ቀስ

በቀስ ይጨምራል፡፡ በሐዲስ «የሚያውቀውን ተግባራዊ

የሚያደርግ አላህ የማያውቀውን ነገር ያሳውቀዋል»9

የሚል ተጠቅሷል፡፡ ዕውቀትን መፈለግ በሕይወታችን

ውስጥ ትልቁን ቦታ ሊይዝ ይገባል፡፡

መለኮታዊው ሕግየሙስሊም እውቀት ሲጨምር የእሱ ወይም የእሷ ልብ የጠራና ለእስላማዊ ሕግ (ሸሪዓ) የተመቻቸ ይሆናል፡፡ አላህ በቁርኣን እንዲህ ብሏል

…ከናንተ ለሁሉም ሕግንና መንገድን አደረግን፤ (አል-ማኢዳህ፡ 48)

በረሃ ላይ ያለ መንገድ አቅጣጫ የሳተንና የተጠማን ተጓዥ የውሃ ምንጭ ወዳለበት እንደሚመራውና ሕይወት እንደሚሰጠው ሁሉ እስላማዊው መለኮታዊ ሕግ ሕይወታችንን የምንመራበትን ካርታ በመስጠት ሕይወታችንን እንዴት እንደምንመራና ደስታን እንዴት እንደምናገኝ አቅጣጫውን ያመላክተናል፡፡

መለኮታዊው ሕግ በወጉ በሰነድ የተዘጋጀና በራዕይ የተገለጹ ትዕዛዛትን አቅፎ የያዘ ሲሆን፡፡ ከአራት መሠረታዊ ምንጮች የተውጣጣ ሕግ ነው፡፡ እነርሱም፡-

1 ቁርኣን

2 ሱንና ወይም የነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) የሕይወት ዘይቤ፣ ማለትም ከንግግራቸው፣ ከድርጊታቸው፣ ሲሠሩ ተመልክተው ያጸደቋቸው ወይም ያወገዟቸው ተግባራት ናቸው፡፡

3 ኢጅማዕ ማለትም ብቃት ያላቸው ሙስሊም ምሁራን በአንድ ጉዳይ ላይ የወሰዱት የጋራ አቋም፡፡

4 ቂያስ ወይም ማመሳሰል በአንድ ጉዳይ የተሰጠን ብያኔ ላልተሰጠው ጉዳይ በመስጠት ሕግ ማበጀት

ከነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ዘመን አንስቶ የእርሳቸውንና የተከታዮቻቸውን ትክክለኛ እምነትንና ተግባራትን በመጠበቅና ለትውልድ በማስተላለፍ ሂደት ላይ ያተኮረ የምሁራን ልማድ ነበር፡፡ ብቃት ያላቸው መምህራንና ተማሪዎቻቸው ትክክለኛውን እምነትንና የሕግ ምሁራን

�“”} ÁS“‹G< JÃ! ›LI” }Ѳ<& SM¡}—¨<”“ Ÿ�“”}U ¾eM×” vKu ?„‹” �²²<&... (አን-ኒሳእ፡ 59) “

Page 32: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - zhic.aeኢስላም፣ ኢማን እና ኢሕሳን 3 አጠቃላይ እይታ 4 መግቢያ 6 የጉዞ መመሪያ 6 ለጉዞ

15ክፍል 1 ፡- እስልምና

አላህ የኔን ሕዝቦች በተሳሳተ መንግድ ላይ የተስማሙ አላደረጋቸውም፡፡ —ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ)

ከቁርኣንና ከሱንና አውጣጥተው ያዘጋጇቸውን መለኮታዊ

መመሪያዎች በጥንቃቄ በመመዝገብ አስተላልፈዋል፡፡

ምሁራዊ ጥረቶችንና መሰረታዊ የሆኑትን የእሰላማዊ

ሕግ ምንጮችን የመረዳት ዘዴዎች በመዝሀብ

(መንገድ) ወይም የሕግ ትምህርት ቤቶች ውስጥ

ተካትተዋል፡፡ በእስላማዊው ዓለም ተቀባይነት ያላቸው፣

ተግባራዊ የሚደረጉና እስካሁንም ድረስ ተከታይ ያላቸው

አራት ዋና ዋና መዝሀቦች (የሕግ ትምህርት ቤቶች) አልሉ፡፡

እነዚህ አራት የሕግ ትምህርት ቤቶች የኢማም አቡ ሐኒፋህ፣

የኢማም ማሊክ፣ የኢማም አሽ-ሻፊዒይ እና የኢማም

አሕመድ ኢብኑ ሐንበል የሕግ ትምህርት ቤቶች ናቸው፡፡

በእነዚህ ምሁራዊ ዘዴዎች ኢስላማዊው ሕግ ሊጠበቅና

ለሁሉም የሕይወት ዘርፍ መመሪያ ሆኖ ሊቆይ ችሏል፡፡

ይህም ታላቅ ጠቀሜታን አስገኝቷል፡፡

መሠረታዊዎቹ የመለኮታዊ ሕግ መመሪያዎች የሰው

ልጆችን እንቅስቃሴዎች ከዚህ በታች እንደተመለከተው

በአምስት መደቦች ከፋፍለው አስቀምጠዋቸዋል፡፡ እንደ

አጠቃላይም መለኮታዊው ሕግ ጠቃሚዎቹን ነገሮች

ከጎጂዎቹ ለይቷቸዋል፡፡ ለግለሰቦችም ሆነ ለሕብረተሰቡ

በዚህም ሆነ በቀጣዩ ዓለም የሚበጁትን ነገሮች አንጥሮ

በማውጣት አስቀምጧል፡፡

የመለኮታዊው ሕግ መመሪያዎች አምስት መሰረታዊ ግቦችን ለማሟላት ያገለግላሉ፡፡ እነርሱም፡-

1 ሃይማኖትን መጠበቅ

መለኮታዊው ሕግ በዚህኛውና በመጪው ዓለም ደስታን ለሰዎች ማጎናጸፍ የሚችሉ ለምሳሌ የመማር፣ የመቀናትና የሃይማኖታዊ ተግባራትን የመከወን መብትን የሚያረጋግጡና የሚጠብቁ አስተምህሮዎችን ያበረታታል፣ ያነሳሳል፡፡ «አላህ የኔን ሕዝቦች በጥምመት ላይ አያስማማቸውም፡፡» ነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)

2 የሕይወትን ክቡርነት ማረጋገጥ መለኮታዊው ሕግ የግለሰብን ብቻ ሳይሆን የማህበረሰብንም ሕይወት ይጠብቃል፡፡ እንደምግብ፣ መጠለያና መድኃኒት ያሉትንና ለሕይወት አስፈላጊ ነገሮችን የማግኘት መብትን ከማጠናከርና ከመጠበቅ አልፎ ጅምላ ጭፍጨፋዎችን፣ ግድያን፣ ጭቆናንና ራስን ማጥፋትን ፍጹም ክልክል አድርጓል፡፡

3 አእምሮን መጠበቅ

መለኮታዊ ሕግ አእምሮን መጠበቅንና መንከባከብን ያበረታታል፡፡ የአእምሮን ብቃት የሚያዳክሙ ንጥረ

ድንጋጌ ዐረብኛ መግለጫ

የግዴታ ተግባር ፈርድ/ዋጂብመተግበራቸው ግድ የሆኑ ቢሠሩ ምንዳ የሚገኝባቸው ባይተገበሩ ተጠያቂ የሚያስደርጉ

ተግባራት፡፡

የተወደደ ተግባር ሱንና/መንዱብ በመተግበራቸው ምንዳ የሚገኝባቸው ባይተገበሩ ተጠያቂ የማያስደርጉ ተግባራት፡፡

የተፈቀደ ተግባር ሙባሕምንዳ የማያስገኙ የማያስኮንኑም ሆነው፤ በመልካም እሳቤ ከተተገበሩ ግን ምንዳን

ሊያስገኙ የሚችሉ ተግባራት፡፡

የተጠላ ተግባር መክሩህየማይበረታቱና ቢሠሩ ተጠያቂ የማያስደርጉ ነገር ግን የራቃቸው ሰው ምንዳ

የሚያገኝባቸው ተግባራት፡፡

የተከለከለ ተግባር ሐራምክልክል የሆኑና በመሠራታቸው ተጠያቂ የሚያስደርጉ፤ የራቃቸው ሰው ምንዳ

የሚያገኝባቸው ተግባራት፡፡

Page 33: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - zhic.aeኢስላም፣ ኢማን እና ኢሕሳን 3 አጠቃላይ እይታ 4 መግቢያ 6 የጉዞ መመሪያ 6 ለጉዞ

መለኮታዊው መንገድ፡-የአዲስ ሙስሊሞች ስርዓተ ትምህርት16

ነገሮችን መውሰድ ይከለክላል፡፡ እንዲሁም እውቀትንና ምርምርን የመሣሠሉ ጠቃሚ ነገሮችን ያበረታታል፡፡

4 የቤተሰብ ግንኙነትን መጠበቅ

ሌላው የመለኮታዊው ሕግ ዓላማ በቤተሰብ መካከል ያለው ሰላማዊ ግንኙነት ጤናማ ሆኖ እንዲቀጥል ማስቻል ነው፡፡ የዝምድና ትስስር እንዲጠናከር የቤተሰብ አንድነት እንዲጐለብት ጋብቻ እንዲሰምር የውርስ ሕግንና ሥርዓተ ቀብርን የተመለከቱ ደንቦችን ሳይቀር በመመሪያ አዘጋጅቷል፡፡

5 ለንብረትና ለአካባቢ ጥበቃ ማድረግ

መለኮታዊው ሕግ ሃብትንና የአካባቢ ጥበቃን በተመለከተ ትኩረት ያደርጋል፡፡ የግለሰቦች የባለቤትነት መብት ኢንቨስትመንትን፣ ለተቸገሩ መርዳትን ውሃንና የተፈጥሮ ሃብት ብክነትን ለመከላከል ይጥራል፡፡

ዛሬ ሃይማኖታችሁን ለናንተ ሞላሁላችሁ፡፡ ጸጋዬንም በናንተ ላይ ፈጸምኩ ለእናንተም ኢስላምን ከሃይማኖት በኩል ወደድኩ (አል-ማኢዳህ፡7)

አሁን ከመነሻውና ከመመረያው በመነሳት ከኛ በፊት የኢስላም የመጀመሪያ መሰረት በሆነውና ወደ ጀነት፣ ወደ እጅ መስጠት እና እምነት መንገድ በሆነው መንገድ ላይ ጉዟችንን እንጀምር ፡፡

‹‹ዛሬ ሃይማኖታችሁን ለናንተ ሞላሁላችሁ፡፡ ጸጋዬንም በናንተ ላይ ፈጸምኩ፡፡ ለእናንተም ኢስላምን ከሃይማኖት በኩል ወደድኩ›› —(አል-ማኢዳህ ፡3)“

Page 34: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - zhic.aeኢስላም፣ ኢማን እና ኢሕሳን 3 አጠቃላይ እይታ 4 መግቢያ 6 የጉዞ መመሪያ 6 ለጉዞ

17ክፍል 1 ፡- እስልምና

የምስክርነት ቃል (ሸሃዳ) የመጀመሪያዎቹ እርምጃዎች

በዚህ መንገድ ላይ የሚኖረው ጉዞ የሚጀምረው አንድ

ሰው የምስጋናንና ሲሳይን በሚሰጠው ጌታው ፊት

የመተናነስን ስሜት ማዳመጥ ሲጀምር ነው፡፡

ይህ ስሜት በልብ ውስጥ ሥር እየሰደደ በመሄድ ግለሰቡ

ወይም ግለሰቧ አንድ ከሆነው ፈጣሪ ውጪ አምልኮና

እጅጉን ሊፈቀር የሚገባው ምንም ነገር እንደሌለ

እስከሚያረጋግጡ ድረስ ውስጥ ውስጡን የሚያድግ

ነው፡፡

ጊዜያት ይዘገያሉ፣ ዓለምም ላፍታ የቆመች

ትመስላለች፡፡ አንድ ግለሰብ አላህን በማመስገን

ልቅናውን የሚገልጽባቸውና ለእርሱ እጅ መስጠቱን

ይፋ የሚያወጣባቸው ቃላት ለማግኘት ይታገላል፤

በመጨረሻም ከጥልቅ ልቦናው በእንባ በመታጀብ ይህን

የእምነት ማረጋገጫ በአንደበቱ ይናገራል፡-

«አሸሃዱ አን ላ ኢላሀ ኢል-ለላህ ወአሸሀዱ አንነ

ሙሐመደን ረሱሉላህ» ትርጉሙ

«ከአላህ በስተቀር አምልኮ የሚገባው ጌታ የለም ብዬ

እመሰክራለሁ፤ ሙሐመድ የአላህ መልዕክተኛ ናቸው

ብዬ እናዘዛለሁ» ይላል፡፡

በዚህ ማረጋገጫ ግለሰቡ ሙሰሊም ይሆናል፡፡ የእርሱ

ወይም የእርሷ ልብ እምነቱን ያጸድቃል ለአላህ እጅ

መስጠትንም ይቀበላል፡፡ ውጫዊው እንቅስቀሴም

የውስጣዊውን የእምነት ጥንካሬ ያንጸባርቃል፡፡

2

Page 35: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - zhic.aeኢስላም፣ ኢማን እና ኢሕሳን 3 አጠቃላይ እይታ 4 መግቢያ 6 የጉዞ መመሪያ 6 ለጉዞ

መለኮታዊው መንገድ፡-የአዲስ ሙስሊሞች ስርዓተ ትምህርት18

አንድ ሰው ወደ እምነቱ ደፍ ዘው ብሎ የሚገባው በራሱ

ፍላጐት ብቻ ተነሳስቶ መሆን አለበት፡፡ በምንም ሁኔታ

መገደድ የለበትም፡፡ አላህ በቁርኣኑ እንዲህ ብሏል፡-

«በሃይማኖት ማስገደድ የለም፤ ቅኑ መንገድ ከጠማማው

በእርግጥ ተገለጠ፤ በጣዖትም የሚክድና በአላህ

የሚያምን ሰው፥ ለርሷ መበጠስ የሌላትን ጠንካራ

ዘለበት በእርግጥ ጨበጠ፤ አላህም ሰሚ ዐዋቂ ነው፡፡»

(አል-በቀራህ፡ 256)

አዲስ ጅማሬቁርኣን እያንዳንዱ የሰው ልጅ ቀድሞውኑ ሳይወለድ በፊት ከአላህ ጋር እንዴት ቃል ኪዳን እንደተጋባ በወጉ ይገልጻል፡፡ አላህ እያንዳንዷን ነፍስ እንዴት እንደፈጠራትና ከአንድ ሰው ጀርባ ላይ እንዳደረጋት ከዚያም እንዴት አድርገው የእርሱን ጌትነት እንደመሰከሩ ሲገልጽ እንዲህ ይላል፣

... #Ñ@�‹G< ›ÃÅKG<U”;$ c=M u’õf‰†¨<

Là veScŸ^†¨< Ñ>²? (¾§’¨<” ›e�¨<e)&

#Ñ@�‹” ’I ScŸ`”.$ ›K<:: ... (አል-አዕራፍ፡ 172)የእምነትን የምስክርነት ቃል መስጠት በአላህና በእያንዳንዷ ነፍስ መካካል የነበረውን የቀድሞ ትስስር ዳግም ሲያድስ በሁለቱ መካከል የነበረው የተቀደሰ ቃል ኪዳን እንደገና እንዲቀጥል ያደርጋል፡፡ አላህ እንዲህ ይላል፡-

«በርሱ ላይ አላህን ቃል ኪዳን የተጋባበትን የሞላም ሰው ታላቅ ምንዳን በእርግጥ ይሰጠዋል» (አል-ፈትሕ፡ 10)በዚህ ሂደት ሰውዬው ወደ ፊጥራ ወይም የመጀመሪያው የሰው ልጅ ነፍስ የተፈጥሮ ንጽህና ብሎም ተፈጥሯዊ ሁኔታ ይመለሳል፡፡ መልካም ሥራው ወይም ሥራዋ ለእርሱ (ለእሷ) ጥቅም ሲባል ይቀመጣል፡፡ ሰውየው ከዚህ ቀደም ይሠራው ከነበረ ወንጀል በሙሉ ጸድቶ አዲስ እንደተፈጠረ ሰው ንጹህ ይሆናል፡፡ ይህ አዲስ ሙስሊም ሕይወቱን የሚመራው ዛሬ እንደተወለደ ሕፃን

ምንም ሃጢአት የሌለበት ሆኖ ነው፡፡ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፣ «አንድ ሰው እስልምናን ከልቡ ከተቀበለ አላህ ቀድሞ የሠራውን ወንጀሉን በሙሉ ይምረዋል፡፡ ከዚያ በሚሠራው ነገር በሙሉ ተጠያቂ መሆን ይጀምራል፡፡ በእያንዳንዱ መልካም ተግባሩ ከአስር እስከ ሰባት መቶ ምንዳ እንደሚያገኝ ሁሉ አላህ ወንጀሉን ካልማረው በስተቀር በእያንዳንዱ መጥፎ ተግባሩ አንድ ሃጢአት ብቻ ይመዘግብበታል፡፡»10

የአላህን አንድነትና መለኮታዊነት ማረጋገጥ

የምስክርነት ቃል (ሸሃዳን) በምንይዝበት ጊዜ ከአላህ ጋር የተቀደሰ ቃል ኪዳን መጋባታችን በመሆኑ የሁለቱን የእምነት ቃላት ትርጓሜ ምንነት በቅጡ ልንረዳው ይገባል ምክንያቱም ሁለቱም ለእምነታችን በጣም አስፈላጊ ነገሮች ናቸውና፡፡

የምስክርነቱ የመጀመሪያ ክፍል ‘ላ ኢላሃ’ የሚለው ቃል ሲሆን ቃሉ አምላክ የሚባል ነገር የለም የሚል ትርጉም አዝሏል፡፡ ‹‹አምላክ የለም…..» በማለት መመስከር የጀመረ ሰው በልቡ ውስጥ ያለውን ውሸትና የቆሸሸ ነገር በሙሉ ሙልጭ አድርጎ ሊያወጣ ይገባዋል፡፡

በማስከተል “ኢለሏህ” (ከአላህ በስተቀር) ብሎ በማከል በባዶ ልቡ ውስጥ የተውሂድን (የአላህ አንድነትን) ብርሃን ዳግም ይሞላል፡፡ በዚህ መንገድ ግለሰቡ ከነበረበት የውሸት እምነት ባርነትና አስተሳሰብ ይላቀቃል፡፡

በማከያውም በእውቀት ላይ የተመሠረተ በዚህኛውና በወዲያኛው ዓለም የሚበቃውን በአላህ ላይ ያለውን ፍጹምነት ያጸናል፡፡ በአላህ አንድነት የመሠከረ በአላህ ከማጋራት (ከሽርክ) የነጻ ይሆናል፡፡ ከአላህም ጋር ሌላን አጋር አዳብሎ አያመልክም፡፡ አላህ እንዲህ ብሏል፡- «አላህ በርሱ የማጋራትን (ወንጀል) አይምርም ከዚህም ወዲያ ያለውን ለሚሻው ሰው ይምራል፡፡ በአላህም የሚያጋራ ሰው (ከውነት) የራቀን መሳሳት በእርግጥ ተሳሳተ» (አን-ኒሳእ፡ 116)

ብስራት ይሰማችሁ፡፡ ሰዎችንም አበስሩ ፡፡ በእውነት ላ ኢላሀ ኢልለላህ ‹ከአላህ በስተቀር በርግጥ አምልኮ የሚገባው ሌላ አምላክ የለም አጋርም የለውም› ያለ ጀነት በርግጥ ገብቷል፡፡ —ነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)

Page 36: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - zhic.aeኢስላም፣ ኢማን እና ኢሕሳን 3 አጠቃላይ እይታ 4 መግቢያ 6 የጉዞ መመሪያ 6 ለጉዞ

19ክፍል 1 ፡- እስልምና

በአላህ ላይ ሌላን አካል ማጋራት በተለያየ መንገድ ወደ ልብ ሊገባ ይችላል፡፡ ይህም በሁለት መንገድ ይገለጻል፡፡ አንደኛው ከባድ ሽርክ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ድብቅ ሽርክ የሚባለው ነው፡፡ ከባዱ ሽርክ ከአላህ ጋር ሌላን አካል ደርቦ ማምለክ ሲሆን፡፡ አላህን በምትወድበት ልብ ሌላን አካል መውደድም ነው፡፡ እነዚህ አካላት የተቀረጹ ሃውልቶች፣ በተፈጥሮ የተገኙ ነገሮች፣ ሰዎች፣ መናፍስት ወይም ሌላ ነገር ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ድብቅ ማጋራት (ሽርክ) የሚባለው ደግሞ በአላህ አንድነትና ጌትነት ማምለኩ እንዳለ ሆኖ አንድን የጽድቅ ተግባር ለአላህ ብሎ ሳይሆን ሰዎችን ለማስደሰት ወይም ለታይታ መፈጸም ነው፡፡

የነቢዩ ሙሐመድን (ሰ.ዐ.ወ) መልዕክት ማረጋገጥሁለተኛው የምስክርነት (የሸሃዳ) ክፍል ነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) የሰው ዘር በሙሉ ከተኛበት የእንቅልፍ

ዓለም እንዲነቃና የመለኮትን ፈቃድ ይፈጽም ዘንድ የተላኩ የመጨረሻው ነቢይ መሆናቸውን መመስከር ነው፡፡

ይህም በትክክል ሲብራራ የነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) መልዕክተኝነት በእውነት ላይ የተመሠረተ ነው ብሎ መመስከር፣ ያመጡትን ነገር መቀበል እንዲሁም ፈለጋቸውን መከተል ነው፡፡ አላህ እንዲህ ይላል፡- «ሙሐመድ ከወንዶቻችሁ የአንድም ሰው አባት አይደለም ግን የአላህ መልዕክተኛና የነቢዮች መደምደሚያ ነው፡፡» (አል-አሕዛብ፡ 40)

ሁለቱን የምስክርነት ቃላት በአንደበት መናገር ለአንድ ሰው ወደ ኢስላም ክትት ብሎ የመግባቱ ማረጋገጫ ነው፡፡ የምስክርነት ቃላቱ ለሕይወት መድህን ሲሆኑ በገነት ማለቂያ ለሌለው ጸጋ ያሳጫሉ፡፡

ጌታዬ ሆይ! አውቄ በአንተ ላይ አንዳች ነገር ከማጋራት በአንተ እጠበቃለሁ፡፡ ሳላውቅ በአንተ ላይ አንዳች ነገር ከማጋራት በአንተ እጠበቃለሁ —ነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)

በዚህ አዲስ ጅምር በመነሳትና እምነታችንን በማሳረፍ እምነታችንን ወደ ተግባር ለመለወጥ ቀጣይ ወደሆነው የእስልምና መሰረት ወደ ሰላት እናምራ ፡፡

Page 37: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - zhic.aeኢስላም፣ ኢማን እና ኢሕሳን 3 አጠቃላይ እይታ 4 መግቢያ 6 የጉዞ መመሪያ 6 ለጉዞ

መለኮታዊው መንገድ፡-የአዲስ ሙስሊሞች ስርዓተ ትምህርት20

ሶላት (ስግደት)

ወደ አላህ መገናኛበቀን ውስጥ ለአምስት ጊዜያት ያህል በመላው ዓለም ከጣሪያዎች በላይ ጣፋጭ የሆነ ድምጽ አዘውትሮ ይሰማል፡፡ ይህ ጥሪ አየሩን ሰንጥቆ፣ በረሃውን አቋርጦ፤ ተራሮችን አልፎ ይሰማል፡፡ የአላህን ፍጹም ታላቅነት ያውጃል፡፡ አላህን ማውሳት ፍጹም ታዛዥ ሆኖ እርሱን በማምለክ ላይ መጽናት ወደርሱ እንደሚያቃርብ ያበሥራል፡፡

«ወደ ጸሎት ኑ!» በማለት ይጣራል «ወደ እውነተኛው የስኬት ሕይወት ኑ!» እነዚህ ቃላት በጆሮ ውስጥ ያቃጭላሉ፡፡ በየትም ሥፍራ ያሉ ሙስሊሞችን ነቃ ብለው እንዲያስቡ ያስታውሳሉ፡፡ ወደ ሶላት ይጋብዛሉ፡፡

ለአላህ የምናደርገውን ቃል ኪዳን እንድናድሰው፣ ፊታችንን ወደ መካ (ቂብላ) በማዞር ትሁትና ታዛዥ ሆነን አላህን እንድናመልክ ይጠቁማል፡፡አላህ እንዲህ ብሏል፡-

«እኔ አላህ እኔ ነኝ ያለ እኔ አምላክ የለምና ተገዛኝ ሶላትንም (በርሷ) እኔን ለማውሳት ስገድ» (ጣሃ፡ 14)

በሌላ የቁርኣን አንቀጽ ደግሞ

«ሶላት በምዕመናን ላይ በጊዜያት የተወሰነች ግዴታ ናትና» ብሏል (አል-ኒሳእ፡ 103)

3

Page 38: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - zhic.aeኢስላም፣ ኢማን እና ኢሕሳን 3 አጠቃላይ እይታ 4 መግቢያ 6 የጉዞ መመሪያ 6 ለጉዞ

21ክፍል 1 ፡- እስልምና

እነዚያ በየዕለቱ ጥሪውን በሚሰሙበት ጊዜ ምላሽ የሚሰጡ፣ ለጌታቸው ትዕዛዝ ያደሩ፣ በሕይወታቸው ላደረገላቸው ነገር ሁሉ ምሥጋና የሚያቀርቡ የአላህን በረከት የሚያገኙ ናቸው፡፡ የእነርሱ ነፍስ በሃሴት ትታደሳለች፡፡ ቀናቸው ዘወትር ፈጣሪያቸውን በማስታወስ ሕያውና የደመቀ ሆኖ ያልፋል፡፡

የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንደሰገዱት ይሰግዳሉ፡፡ እጅግ በተመስጦና በሚማርክ እንቅስቃሴ አቋቋማቸው፣ ማጐንበሳቸውና ስግደታቸው፣ የሚያነብቡት ቁርኣንና የሚያደርጉት ጸሎት በአስተውሎትና አላህን በእጅጉ በሚያልቅ መልኩ ይከውናሉ፡፡ ሶላታቸው የተስተካከለ ከመሆኑ የተነሳ የሰውነታቸው እንቅስቃሴ ከነፍሳቸውና ከአዕምሯቸው ጋር የተስማማ ሆኖ ከፈጣሪያቸው ጋር በመንፈስ የሰመረ ግንኙነት ያደርጋሉ፡፡አላህ እንዲህ ብሏል፡-

«አላህን ሃይማኖትን ለርሱ ብቻ አጥሪዎች ቀጥተኞች ኾነው ሊገዙት ሶላትንም አስተካክለው ሊሰግዱ ዘካንም ሊሰጡ እንጅ ያልታዘዙ ሲኾኑ (ተለያዩ) ይህም የቀጥተኛይቱ (ሃይማኖት) ድንጋጌ ነው፡፡" (አል-በይናህ፡ 5)

«የዓይኔ ማረፊያ»

ከአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) በላይ አላህን የሚቀርበው፣ የሚያውቀውና በጥልቀት የሚግገዛው ማንም የለም፡፡ በእርሳቸው ዘንድ ከአምልኮ ተግባራት መካከል እንደ ሰላት (ስግደት) በጣም ተወዳጅ የሆነ ነገር የለም፡፡ እንዲህ ይላሉ፡- «አንድ ሰው ሶላቱን በሚሰግድበት ጊዜ ከአላህ ጋር በቅርበት እየተነጋገረ ነው፡፡ ማናችሁም ጌታውን በምን ሁኔታ እንደሚያናግር ይመልከት፡፡››11

የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ሶላት በሚሰግዱበት ጊዜ ለረጅም ጊዜ ቁርኣንን እያነበቡ ከአላህ ጋር በቅርበት ይነጋገሩ ነበር፡፡ በሶላት ውስጥ ሲሆኑ ደስታን እንደሚያገኙ ሲናገሩ «የዓይኖቼ ማረፊያ በሰላት ውስጥ ተደርጓል፡፡›› ብለዋል፡፡12

ይህም እርጋታንና ምቾትን ያገኙ የነበረው በፈጣሪያቸው ፈት ትሁት ሆነው ሲሰግዱ መሆኑን ያሳያል፡፡ፀሐይ በሰማይ ተጉዛ አንድ የሰላት ወቅት ሲደርስ በቀድምትነት እስልምናን ከተቀበሉት የነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ባልደረባዎች አንዱና በእስልምና ታሪክ የመጀመሪያው የሶላት ጥሪ አድራጊ (ሙአዚን) የሆነውን ቢላልን «ቢላል ሆይ አዛን በማድረግ እርጋታን አጎናጽፈን»13 በማለት ያስታውሱት ነበር፡፡

ሶላት የውስጥ ሰላምንና እርጋታን ያጎናጽፋል፡፡ ዘውትር በሶላታቸው የጠነከሩ ሰዎች የላቀ ምግባርና መረጋጋት ይታይባቸዋል፡፡ ሥርዓቱን ጠብቆ ሶላቱን የሚሰግድ ወይም የምትሰግድ ልቡ አላህን ለመገዛት ታዛዥ ይሆናል፡፡ አላህ በቁርኣኑ እንዲህ ይለናል፡፡

የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ሶላት የመንጽኤ ሰበብ መሆኑን ባበሰሩበት ሐዲሳቸው «ከናንተ መካከል በአንዱ ሰው ቤቱ በራፍ ወንዝ በኖርና በየቀኑ አምስት ጊዜ በሱ ውሃ ቢታጠብ ሰውነቱ ቁሻሻው ይቀራልን?» በማለት አጠገባቸው የነበሩትን ሰሓባዎቻቸውን ጠየቁ፡፡ ሰሓቦቹም፣ «በጭራሽ አይቀርም» አሉ፡፡ እሳቸውም «ያም እንደአምስቱ ወቅት ሶላቶች ነው፡፡ አላህ በአምስቱ ወቅት ሰላቶች ወንጀሎችን ያስወግዳል»14 አሉ፡፡

ሰላትን ወደ ሕይወት ማምጣት

የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) በተጨማሪም እንዲህ ብለዋል፣

«አንድ ባሪያ በፍርዱ ቀን ሲቀሰቀስ መጀመሪያ የሚጠየቀው ስለሶላቱ ነው፡፡ ሶላቱ ያማረና የተስተካከለ ከሆነ ስኬትን ይጐናጸፋል፡፡ ሶላቱ የተበላሸ ከሆነ ግን ይከስራል፡፡»15

በአንድ የሶላት ወቅት የነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) አጎት ልጅና አማች የሆኑት ዐሊ ኢብን አቢጣሊብ (ረ.ዐ) ተንቀጠቀጡ፡፡ ከዚያም ምን እንደሆኑ ሲጠየቁ «መሬት፣ ሰማይና ተራራ እንዲሸከሙ ተገልጾላቸው

ሶላትንም ደንቡን ጠብቀህ ስገድ ሶላት ከመጥፎና ከሚጠላ ነገር ሁሉ ትከላከላለችና —(አል-ዐንከቡት፡- 45)

Page 39: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - zhic.aeኢስላም፣ ኢማን እና ኢሕሳን 3 አጠቃላይ እይታ 4 መግቢያ 6 የጉዞ መመሪያ 6 ለጉዞ

መለኮታዊው መንገድ፡-የአዲስ ሙስሊሞች ስርዓተ ትምህርት22

አልሸክምም ያሉት አደራ አሁን እሸከማለሁ፡፡» አሉ፡፡

ሶላት ውጫዊ እንቅስቃሴና ንግግር አይፈልግም፡፡ ሆኖም

ሕይወት ይኖረው ዘንድ ውስጣዊ ስክነትን ይሻል፡፡ አንድ

ጊዜ ወደ ሶላት የገባ ሰው ግንኙነቱ ቀጥታ ከፈጣሪው

ጋር በመሆኑ አካላዊና አዕምሯአዊ ሁለንተናውን በአላህ

ፈቃድ በማስገዛት ወደርሱ ለመቃረብ ተስፋ መሰነቅ

አልለበት፡፡

ውጫዊ ንጽሕና የምንለው ልብስና የሚሰገድበት

ቦታ ትኩረት ሊያገኝ የሚገባውን ያህል በሰላት

ወቅት የአዕምሮና የልቦና መስተካከልም ወሳኝ

የሆነ ጉዳይ ነው፡፡ የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ)

እንዲህ በማለት አስጠንቅቀዋል፡-

«አንድ ሰው መላው አካላቱ ተሰባስቦ በሶላቱ

ካልተመሰጠ በሥራው ግማሽ አጅርም አያገኝም፡፡ አንድ

ሶስተኛም አያገኝም፡፡ አንድ አራተኛም አያገኝም፡፡ አንድ

አምስተኛ፣ አንድ ስድስተኛ ወይም አንድ አስረኛ ላያገኝ

ይችላል፡፡ በመሆኑም ሰውዬው ሲሰግድ በተመስጦና

አላህን በመፍራት መሆን አለበት፡፡»

የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ባልደረባ የሆኑት አቡ

ደርዳእ (ረ.ዐ) እንዲህ በማለት ይመክራሉ፡-

«አንድ ሰው ወደ ሶላት ከመግባቱ በፊት ጉዳዮቹን

ሁሉ አስተካክሎ ማጠናቀቅ ይኖርበታል፡፡ ከዚያም

አእምሮውን (ጽሞናውን) ወደ ስግደት ማድረግ ነው»

በተጨማሪም ሌላው የነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ባልደረባ

ሙስሊም ኢብኑ የሳር (ረ.ዐ) ሶላት እየሰገዱ

በነበሩበት ወቅት የመስጅዱ አንድ ምሶሶ ይወድቅና

ይፈርሳል፡፡ እርሳቸው በሶላቱ ከመመሰጣቸው የተነሳ

ሰግደው እስኪጨርሱ ድረስ ምን እንደተፈጠረ እንኳ

እንዳላወቁ ተወስቷል፡፡

አንድ ሰው ሶላቱን በፍራቻና በመተናነስ የሚሰግድ

ከሆነ ልቡ ከማን ጋር እየተነጋገረ እንደሆነ በመገንዘብ

ትለዝባለች፡፡

የነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) የልጅ ልጅ ልጅ የሆኑት

ዐሊ ኢብን አልሑሰይን (ረ.ዐ) ለሶላት ዉዱእ

ማድረግ ሲጀምሩ ነበር ፊታቸው መገርጣት

የሚጀምረው፡፡ ስለዚህ ጉዳይ ተጠይቀው ሲመለሱ

«ማን ፊት ለመቆም እየተዘጋጀሁ እንደሆነ ልብ

ብላችኋልን?» ይሉ ነበር፡፡

አንድ ሰው በሶላቱ ውስጥ ዋነኛውና ፈጣሪውን ከልቡ

የሚያልቅበት አጋጣሚ መሬት ላይ ሲደፉ (ሱጁድ)

ነው፡፡ በዚያ ጊዜ የአላህን ታላቅነት ለመመስከር በሚበቃ

ሁኔታ ራሱን በትህትና ዝቅ ያደርጋል፡፡

የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) «አንድ የአላህ

ባሪያ ወደጌታው ይበልጥ የሚቀርበው ሱጁድ

በሚያደርግበት ጊዜ ነው፡፡ (ሱጁድ ላይ) ዱዓ

አብዙ፡፡›› 16 ብለዋል፡፡

አንተ በቅርብ እስልምናን የተቀላቀልክ ከሆንክ

ለመጀመሪያ ጊዜ ሶላት ላይ አስቸጋሪ ሁኔታ ሊያጋጥምህ

ይችላል፡፡ በተለይ ደግሞ በሶላቱ ውስጥ የምትጠቀማቸው

አረብኛ ቃላት ሊፈትኑህ ይችላሉ፡፡

ለዚህ የሚረዳህ የዚህ መጽሐፍ የመጀመሪያ ክፍል

የሆነው «አላህን ለመገዛት የመጀመሪያው መመሪያ»

የሚለው መጽሐፍ ሲሆን ሰፊ ማብራሪያና ጥልቅ መረጃ

ይሰጥሃል፡፡

የሶላት ጊዜዎችንና የአሰጋገድ ሂደቶችን ደረጃ በደረጃ

ያመላክትሃል፡፡ እንዲሁም በድምጽ የታገዘ መረጃን፣

የአረብኛ ቃላትንና ሃረጐችን ጭምር የያዘ ዝርዝር

ያቀርብልሃል፡፡

በአላህ ፊት አንድ ሰው በተደጋጋሚ ስግደት (ሱጁድ) አያደርግም በዚያ ሰበብ አንድ ደረጃ ከፍ የሚያደርገውና ሃጢአቱን የሚፍቅለት ቢሆን እንጂ፡፡ ) —ነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)“

Page 40: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - zhic.aeኢስላም፣ ኢማን እና ኢሕሳን 3 አጠቃላይ እይታ 4 መግቢያ 6 የጉዞ መመሪያ 6 ለጉዞ

23ክፍል 1 ፡- እስልምና

በሌሎች ጊዜያቶችየሚሰገዱ ሶላቶችበቀንና በማታ የምንሰግዳቸው የአምስት ወቅት ስግደቶች (ሶላቶች) የየዕለት ተዕለት ሕይወታችንን ይቆጣጠራሉ፡፡ ይሁን እንጂ ከፈጣሪያቸው ጋር ይበልጥ ለመቀራረብ ለሚሹ ሌሎች ብዙ አማራጭ ስግደቶች አልሉ፡፡

የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) የውዴታ ሶላቶችን ከግዴታ ሶላቶች በፊትና በኋላ ሁሌም ይሰግዱ ነበር፡፡ እነዚህ የውዴታ ሶላቶች የግዴታ ሶላቱን ከማጠናከር ባሻገር ለግዴታ ሶላት እንድንዘጋጅና ለሳትናቸው አንዳንድ ጉድለቶች ማካካሻ የሚሆኑ ናቸው፡፡

በተለያየ ሁኔታ የሚሰገዱ ሌሎች ሶላቶችም አልሉ፡- የዓርብ ዕለት ስግደትን ብንወስድ በምክር (ኹጥባ) የታገዘና በዝሁር ሰላት ምትክ በመስጊድ የሚሰገድ ነው፡፡ ሌላው የሙታን (ጀናዛ) ሶላት ነው፡፡ ይህም አንድ ሰው ከዚህ ዓለም በሞት ሲለይ በሕብረት የሚሰገድ ነው፡፡ ሌላው በጋራ የሚሰገድ የፈቃደኝነት ሶላት የተራዊሕ ማለትም በረመዳን ምሽቶች ከዒሻእ ሶላት በኋላ የሚሰገደው ነው፡፡

ከዚህም በተጨማሪ በሁለቱ ዒዶች ወቅት የሚሰገደው የሕብረት ሶላትም የበዓሎቻችን ማብሰሪያ ነው፡፡ የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ለተከታዮቻቸው ካስተማሩዋቸው ተጨማሪ ሶላቶች እጅግ አስፈላጊ ነው ያሉት ‹የመመራት ሶላትን› ወይም ‹ሶላቱል ኢስቲኻራ› ነው፡፡

በኅብረት የሚሰገድ ሶላት ለብቻ ከምትሰገድ ሶላት በ27 ደረጃ ይበልጣል —ነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)“

Page 41: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - zhic.aeኢስላም፣ ኢማን እና ኢሕሳን 3 አጠቃላይ እይታ 4 መግቢያ 6 የጉዞ መመሪያ 6 ለጉዞ

መለኮታዊው መንገድ፡-የአዲስ ሙስሊሞች ስርዓተ ትምህርት24

ይህ ሶላት አንድን ጉዳይ አስመልክተን ምን መወሰን እንዳለብን ለመምረጥ ስንቸገር አላህ ትክክሉን እንዲመራን የምንሰግደው ነው፡፡ በዚህ ሶላት አማካኝነት አላህ ለእኛ መልካም የሆነውን ነገር እንዲያመላክተንና ከሚጐዳን ነገር ደግሞ እንዲያርቀን ራሳችንን ለእርሱ ፈቃድ በአደራ የምንሰጥበት አጋጣሚም ነው፡፡

በዚህ ሰላት ትላልቅና አነስተኛ የሆኑ እንደ ትዳር፣ አገር መቀየር፣ አዲስ ሥራ መያዝ የመሳሰሉትን ጉዳዮች አስመልክተን ልንሰግድና ምሪት ልናገኝ እንችላለን፡፡ የሌሊት ሰላት (ተሐጁድም) በፈቃደኝነት ከሚሰገዱ ሶላቶች መካከል ነው፡፡ ይህ ሶላት በአብዛኛው የሌሊቱ አንድ ሶስተኛ ካለፈ በኋላ የሚሰገድ ሲሆን ወቅቱ ለሶላት

እጅግ የተመቸና የተባረከ ነው፡፡ ጸጥ ባለው የሌሊት ግርማ ታጅቦ ከአላህ ጋር በተመስጦ ለመነጋገር ጊዜው ተስማሚ ነው፡፡ በሌሊቱ መጨረሻ ለመነሳት ቀደም ብሎ መተኛት ይመከራል፡፡ የሌሊት ወቅት መንፈስን ሰብስቦና ልብን አጥርቶ በተመስጦ ለመስገድ ይረዳል፡፡

ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንደገለጹት «በየቀኑ የሌሊቱ አንድ ሶስተኛ በሚጋመስበት ወቅት አላህ በታላቅ ሞገስና ክብር ወደ አንደኛ ሰማይ በመውረድ ማነው ተቸግሮ የሚለምነኝና ለልመናው ምላሽ የምሰጠው? ማነው የሚጠይቀኝና ጥያቄውን የምመልስለት? ማነው ምህረትን የሚፈልግና የምምረው? 17 በማለት ይጠይቃል»

እስካሁን ድረስ ስለ ሶላት ተምረናል፡፡ ከዚህ በመቀጠል ደግሞ ከኢስላም ማዕዘናት አንዱ ስለሆነው የግዴታ ምጽዋት (ዘካ)

እንማራለን፡፡

አማኞች ሆይ! ሰላምታን አብዙ ፣ ሰዎችን መግቡ ፣ የዘምድና ግንኙነትን አጠንክሩ ፣ ሰዎች በተኙበት ወቅት

ሰላትን ስገዱ ጀነት ተገባላችሁ፡፡ —ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ)

Page 42: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - zhic.aeኢስላም፣ ኢማን እና ኢሕሳን 3 አጠቃላይ እይታ 4 መግቢያ 6 የጉዞ መመሪያ 6 ለጉዞ

25ክፍል 1 ፡- እስልምና

ዘካት (የግዴታ ምጽዋት)

የመስጠቱ ግዴታ

ከመንፈሳዊ ተግባራት አንዱ እያንዳንዳችን ለመጭው

ዓለም ሕይወቱ ይለፋል፣ ሀር ይዘራልም፡፡ ከመንፈሳዊ

አስተምሮቱና ሥርዓቱ ጎን ለጎን ለነፍሳችን ብለን

በምንሰራው ከአላህ ምንዳን የምናገኝበት ነው፡፡

ይህ መንፈሳዊ ሥርዓትና ልምምድ በግዴታነት

የምንፈጽመው ምጽዋትንም ያካተተ ነው፡፡ ይህ ምጽዋት

የሚደረገው በየዓመቱ አስፈላጊ ከሆነው ሃብት ትርፍ

በሆነው ላይ የተወሰነ ነው፡፡ አነስተኛው ፐርሰንት ተሰልቶ

ለተቸገረ የሚሰጥ ነው፡፡ ይህን በመስጠታችን ለሌሎች

የጠቀምን ሊመስለን ይችላል፡፡

እውነታው ግን ለራሳችን ስንል ነው የምናደርገው፡፡ አላህ

እንዲህ ይላል፡- «በአላህና በመልዕክተኛው እመኑ

(በአላህ) በርሱ ተተኪዎች ባደረገችሁም ገንዘብ ለግሱ

እነዚያም ከናንተ ውስጥ ያመኑትና የለገሱት ለነርሱ

ታላቅ ምንዳ አልላቸው» (አል-ሀዲድ፡ 7)

ዘካን በተመለከተ ያሉት የቁርኣን አንቀጾች ሶላትን

በተመለከተ ከተቀመጠው ትዕዛዝ ጋር የተያያዘ ነው

«አላህን ሃይማኖትን ለርሱ ብቻ አጥሪዎች ቀጥተኞች

ኾነው ሊገዙት ሶላትንም አስተካክለው ሊሰግዱ ዘካንም

ሊሰጡ እንጂ ያልታዘዙ ሲኾኑ (ተለያዩ) ይህም

የቀጥተኛይቱ (ሃይማኖት) ድንጋጌ ነው»

(አል-በይናህ፡ 5)

ሶላት ከአላህ ጋር የምንገናኝበት መንገድ ሲሆን ዘካ

ደግም ከአላህ ጋር ያለንን ግንኙነት የምናጠናክርበት ዘዴ

ነው፡፡ ሰውዬው ለፍቶ ካገኘው ጥሪት ቆንጥሮ ለመስጠት

ነፍሱ ትፈታተነዋለች፡፡

በአላህ ትዕዛዝ ካልተገደደች በቀር፡፡ ሆኖም የመስጠትን

ጠቀሜታ ሊያሳውቅ በሚችል አስተምሮት መስጠትን

እንዲወድና ከአላህ ጋር ያለውን ግንኙነት ነፍሱን

በመግታት እንዲያጠናክር ከተደረገ ነፍስ ከዚህች ዓለም

ጋር ያላት ግንኙነት ያነሰ ይሆናል፡፡

4

Page 43: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - zhic.aeኢስላም፣ ኢማን እና ኢሕሳን 3 አጠቃላይ እይታ 4 መግቢያ 6 የጉዞ መመሪያ 6 ለጉዞ

መለኮታዊው መንገድ፡-የአዲስ ሙስሊሞች ስርዓተ ትምህርት26

አላህ በቁርኣኑ እንዲህ ይላል «የምትወዱትን

እስከምትለግሱ ድረስ በጎን ሥራ (ዋጋዋን) አታገኙም

ከምንም ነገር ብትለግሱ አላህ ያውቀዋል» (አል-

ዒምራን፡ 92)

ዘካ ቀልብንም ያጠራል በሰዎች መካከል ለሚኖረንም

ውስጣዊ ግንኙነት ጠቀሜታ አለው ዘካን የሚሰጡ

ሰዎች ከማህበረሰቡ ውስጥ አነስተኛ እድልን

ያገኛሉ፡፡ ዘካ ፍትሐዊ የሆነ የሃብት ክፍፍል እንዲኖርም

ያደርጋል ዘካ ለሚገባቸው ሰዎችም በጊዜው ቢሰጣቸው

የተወደደ ነው፡፡

የዘካ መስፈርቶችያለህ ሃብት ዘካ ለማውጣት የሚያስችል መሆንና አለመሆኑን ለመወሰንና በዓመቱ ውስጥ የምታወጣውን የዘካ መጠን ለማወቅ የኒሳብን ጽንሰ ሃሳብ ማወቅ ይኖርብሃል፡፡ ኒሳብ ማለት አንድ ሰው የያዘው ገንዘብ ዘካ የሚወጣበት አነስተኛው መነሻ መጠን ነው፡፡

ወርቅ ኒሳብ ሞላ የሚባለው ከ87.48 ግራም በልጦ ሲገኝ ሲሆን ብር ደግሞ 612.36 ግራም ሲሞላ ነው፡፡ ከእነዚህ (ክቡር ማዕደናት) ተመጣጣኝ የሆነውን ዘካ ለማውጣት በአገሩ የገንዘብ መጠን የተመሠረተ ስሌት ይሠራል፡፡

ስለሆነም ማንኛውም ኒሳብ የሞላ ሃብት አንድ ዓመት ከሆነው ዘካ ይወጣበታል፡፡ የዚህ ገንዘብ 2.5 ከመቶ በዘካ መልክ ለባለሃቆች ይከፋፈላል፡፡

ባለሃቆች የሚባሉትና ዘካ የሚሰጣቸው የሕብረተሰብ ክፍሎች ድሆች፣ ምስኪኖች ዕዳ ያለባቸው፣ መንገደኞች ወዘተ ናቸው፡፡ ዘካን ለቤተሰብ አባላት መስጠት ይበረታታል፡፡ ይህም ሲባል ሰዎች ዘካ በሚያወጣው ሰው ጥገኝነት ሥር ያልሆኑና ከሚስት፣ ከልጆችና ከወላጆች ውጪ ያሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡ ምክንያቱም እነዚህ ከላይ

የተጠቀሱትን ማስተዳደር የሰውየው ሙሉ ግዴታ ነውና፡፡መልካምን ነገር ለማጨድ የፈለገ ሰው መልካም ነገር መዝራትና አዝመራውንም መንከባከብ እንዳለበት ሁሉ ዘካ የሚሰጥ ሁሉ ሊከተለው የሚገባ ሥነምግባር ይኖራል፡፡

ከሁሉም በላይ ዘካ የሚሰጠው ከልብና በጥሩ እሳቤ (ኒያ) መሆን ይኖርበታል፡፡ ከዚያ በመለስ መልካም ገጽታን ለማግኘት ወይም ከሰዎች ውለታን በመጠበቅ እንዳይሆን መጠንቀቅ ያሻል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ዘካ የሚሰጥ ሰው ማወቅ ያለበት እያንዳንዱ በእጁ የሚገኝ ጸጋ ሁሉ ከአላህ የተሰጠው መሆኑን ነው፡፡

ያ ጸጋ የእርሱ ወይም የእርሷ ሳይሆን ፈጣሪው በእርሱ በኩል የድሆችን መብት ይጠብቅ ዘንድ በአደራነት ያስቀመጠው ነው፡፡

ስለሆነም አንድ ሰው ይህን ሁሉ ተገንዝቦ ዘካ ሲሰጥ ማመናጨቅና ስድብን በማስወገድ በእርጋታና በትሕትና መሆን ይኖርበታል፡፡የምትከፍለውን የዘካ መጠን፣ ለማን እንደምትሰጥና እንዴት ወደ ሰዎቹ እንደምትሄድ ወዘተ ለማወቅ የዕውቀት ባለቤት የሆነ ሰው ምክር እንዲለግስህ አድርግ፡፡

በሌላ ጊዜ ምጽዋት (ሰደቃ) ስለመሰጠት

ግዴታ ከሆነው ዘካ በተጓዳኝ በፈቃደኝነት የሚሰጥ

የአዘቦት ልገሳ ‹ሰደቃ› የሚባል ሲሆን መስጠቱ

በጣም የሚበረታታ ተግባር ነው፡፡ እውነተኛ ምጽዋትን

ዘርተህ ትህትናን ብታጠጣው በቀጣዩ ዓለም ብዙ

ምርት ትሰበስባለህ፡፡

የአላህ መልዕክተኛን (ሰ.ዐ.ወ) ያህል ለጋስነት

የሚያበዛ አልነበረም፡፡ የባለቤታቸው የአክስት ልጅ

የሆነው ሃኪም እስልምናን ሲቀበል ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ)

አንድ መቶ ያህል ግመሎችን ሰጥተውታል፡፡

ከሊፋው ባዘዙኝ መሠረት ዘካ ለመሰብሰብ ወደ ሙስሊም አፍሪካውያን ዘንድ ሄድኩ፡፡ ከሰበሰብኩ በኋላ ዘካ የሚገባው የተቸገረ ሰው እንዳለ ጠየቅሁ፡፡ ሆኖም አንድም ድሃ ሰው አላገኘሁም፡፡ — የህያ ኢብን ሰዓድ (720 አ.ሂ)

Page 44: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - zhic.aeኢስላም፣ ኢማን እና ኢሕሳን 3 አጠቃላይ እይታ 4 መግቢያ 6 የጉዞ መመሪያ 6 ለጉዞ

27ክፍል 1 ፡- እስልምና

ሐኪም ግን በቂ አይደለም በማለት ቅሬታውን በማቅረቡ

ተጨማሪ ሁለት መቶ ግመሎችን ጨመሩለትና

«የሰጪ እጅ ከተቀባይ እጅ ይበልጣል» የሚል ምክር

ለገሱት፡፡ ሐኪም ይሄን ሲሰማ የጨመሩለትን በሙሉ

መልሶላቸው ከዚህ በኋላ ሁሌም «ሰጪ» ለመሆን

ቃል ገባ18

የነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ባልደረቦች የአላህን ውዴታ

ለማግኘትና የተቸገረን ለመርዳት ብዙ ብዙ ይለግሱ

ነበር፡፡ ከነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ቅርብ ወዳጆች አንዱ

የነበሩት ዑመር ኢብኑ አል-ኸጣብ (ረ.ዐ) ለአላህና

መልዕክተኛው (ሰ.ዐ.ወ) ግማሽ ሃብታቸውን

ለግሰዋል፡፡

በሠሩት ሥራ ረክተው ሳለ የአላህ መልዕክተኛ

(ሰ.ዐ.ወ) የቅርብ ወዳጅና የመጀመሪያው ኸሊፋ

አቡበከር (ረ.ዐ) የሠሩትን ሰሙ፡፡ አቡበከር

(ረ.ዐ) ያላቸውን ሃብት በሙሉ ነበር አምጥተው

የሰጡት፡፡ ይህን ሲሰሙ ዑመር (ረ.ዐ)

«እኔና እርሱ በመልካም ሥራ ላይ አንፎካከርም

ሁልጊዜም እርሱ የሚቀድመኝ ቢሆን እንጂ» አሉ፡፡

እነዚያ ቸር ምዕመናን በሚሰጡበት ጊዜ ምርጡን

ነገር ነበር የራሳቸውን ፍላጎት ገትተው ለሌላው

የሚለግሱት፡፡ እነርሱ ዘንድ ተወዳጅ የሆነውን ነገር

በመስጠታቸው በመንፈሳዊነታቸው ላይ የሚኖረው

ተጽዕኖ እጅጉን ከፍ ያለ ነበር፡፡

ከላይ የሚውል (ሰጪ) እጅ ከታች ከሚውል (ተቀባይ) ይበልጣል፡፡ —ነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)

Page 45: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - zhic.aeኢስላም፣ ኢማን እና ኢሕሳን 3 አጠቃላይ እይታ 4 መግቢያ 6 የጉዞ መመሪያ 6 ለጉዞ

መለኮታዊው መንገድ፡-የአዲስ ሙስሊሞች ስርዓተ ትምህርት28

ደጋግ የአላህ ባሪያዎች ማንኛውንም ነገር ቢሰጡ

ወይም ለሌሎች ቢያካፍሉ ከሃብታቸው ላይ ቅንጣት

እንደማይቀንስ እንዲያውም ሃብታቸው እንደሚጸዳና

እጥፍ ድርብ እንደሚጨምር ያምኑ ነበር፡፡

አላህ በቁርኣኑ እንዲህ ይላል፡-

የእነዚያ ገንዘቦቻቸውን በአላህ መንገድ የሚለግሱ

ሰዎች (ልግስና) ምሳሌ በየዘለላው ሁሉ መቶ ቅንጣት

ያለባቸውን ሰባት ዘለላዎች እንዳበቀለች አንዲት

ቅንጣት ብጤ ነው፡፡ አላህም ለሚሻው ሰው (ከዚህ

በላይ) ያነባብራል፡፡ (አል-በቀራህ፡ 261)

ምጽዋት (ሰደቃ) ሲባል ገንዘብን መስጠት ብቻ

አይደለም፡፡ ሰዎችን ለመርዳት ተብሎ የሚፈጸም

ማንኛውም መልካም ነገር እንደ ምጽዋት (ሰደቃ)

ይቆጠራል፡፡ የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ፈገግታ

ምጽዋት (ሰደቃ) እንደሆነ ሲናገሩ እንዲህ

ብለዋል፡- «እያንዳንዱ ሰው ፀሐይ ከወጣችበት

ጀምሮ ለእያንዳንዱ የመገጣጠሚያ አካሉ ምጽዋት

(ሰደቃ) ሊሰጥ ይገባዋል፡፡ በሁለት ሰዎች መካከል

መስማማት ሰደቃ ነው፣ አንድ ሰው መጓጓዣው

ላይ እንዲወጣ ወይም እቃውን እንዲጭን መርዳት

ሰደቃ ነው፡፡ መልካም ንግግር ሰደቃ ነው፡፡ ወደ ሰላት

የምታደርግ እያንዳንዷ እርምጃ ሰደቃ ናት እንዲሁም

ሰዎችን የሚጐዳ ነገር ከመንገድ ላይ ማስወገድ ሰደቃ

ነው፡፡»19

እያንዳንዱ ሰው በነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) መንገድ

ለመጓዝ ራሱን ማለማመድ መቻል ያለበት

ሲሆን ልግስና በማድረግ ማሕበረሰቡን መርዳት

ይኖርበታል፡፡ አላህ በቁርኣኑ እንዲህ ብሏል

እነዚያ ገንዘቦቻቸውን በሌሊትና በቀን በድብቅም

በግልጽም የሚለግሱ ለነርሱ በጌታቸው ዘንድ ምንዳቸው

አላቸው፡፡ በነርሱም ላይ ፍርሃት የለባቸውም እነርሱም

አያዝኑም (አል-በቀራህ፡ 274)

አንድ ሙስሊምን ያለበሰ አላህ የቂያማ ዕለት የጀነት ልብስን ያለብሰዋል —ነቢዩ ሙሐመድ (ሶ.ዐ.ወ)

ነፍሳችንን በሶላት ከፍ ካደረግናትና የማሕበረሰቡን ሐቅ የግዴታ ምጽዋት (ዘካ) በመስጠት ከተወጣን ነፍሳችንን (ፍላጐታችንን)

የሚገታልን ወደሆነው ሌላው የኢስላም ማዕዘን (ጾም) እናመራለን፡፡

Page 46: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - zhic.aeኢስላም፣ ኢማን እና ኢሕሳን 3 አጠቃላይ እይታ 4 መግቢያ 6 የጉዞ መመሪያ 6 ለጉዞ

29ክፍል 1 ፡- እስልምና

የረመዳንን ወር መጾም

አዲስ ጨረቃ

ጉዟችንን ቀጥለናል፡፡ ጨለማው ነግሶ ከሩቁ ኮረብታ ጫፍ

ላይ የተሰበሰቡ ሰዎች ፊታቸውን ወደ ላይ አቅንተዋል፡፡

ሁሉም በጸጥታ የምሽቱን ሰማይ ይመለከታሉ፡፡

ይሄኔ ነው የአዲሱን ወር መምጣት የምታበስረው ጨረቃ

የብር ማጭድ መስላ አድማሱ ላይ የታየችው፡፡

በረመዳን ወር ከጐሕ መውጣት አንስቶ እስከ ፀሐይ

መግባት ሙስሊሞች ከምግብ፣ ከመጠጥና ከወሲባዊ

ተራክቦ ይታቀባሉ፡፡ አላህ በቁርኣኑ እንዲህ ይላል፡-

«እንድትጾሙ የተጻፈባችሁ ያ በርሱ ውስጥ ለሰዎች መሪ

ከቅን መንገድ እውነትን ከውሸት ከሚለዩም ገላጮች

(አንቀጾች) ሲኾን ቁርኣን የተወረደበት የረመዳን ወር

ነው፡፡ ከናንተም ወሩን ያገኘ ሰው ይጹመው፡፡»

(አል-በቀራህ፡ 185)

በረመዳን ውስጥ የጀነት በሮች ወለል ተደርገውና

በመልካም መዓዛ ታውደው ይከፈታሉ፡፡ በተቃራኒው

የጀሃነም በሮች ይዘጋሉ፣ ሰይጣናትም በሠንሰለት

ይታሠራሉ፡፡ በዚህም ምክንያት ሰዎችን ማሣሣት

አይችሉም፡፡ እውነተኛ አማኞችም መልካም ተግባራትን

እንዳይፈጽሙና በዚያም እጥፍ ድርብ ምንዳን

እንዳያገኙ ማቀብ አይሆንላቸውም፡፡

የመጾም ዓላማ

ሰውነታችን የሚፈልገውን እርካታ ማዘግየት ሁሌም

የነፍስ ጥንካሬን እንድናገኝ ይረዳናል፡፡ ዓለማዊ ፍላጎትን

በመገደብ ከነፍስ ተጽእኖ መላቀቅ እንችላለን፡፡ አላህ

በቁርኣንኑ እንዲህ ይለናል፡፡

እናንተ ያመናችሁ ሆይ ጾም በነዚያ ከናንተ በፊት

በነበሩት (ሕዝቦች) ላይ እንደተፃፈ በናንተም ላይ

ተጸፈ(ተደነባ) ልትጠነቀቁ ይከጀላልና

(አል-በቀራህ፡ 183)

ጾም በራስ ላይ ጥብቅ ቁጥጥር በማድረግ ባሪያው ለጌታው

ሲል ድብቅ መስዋዕትነት እንዲከፍል ያደርገዋል፡፡ ቀደም

ሲል ስናነሳቸው የነበሩ የእስልምና ማዕዘናት አካላዊ

ተግባራት ላይ የተመሠረቱ ነበሩ፡፡

ሥራችንንም ምናልባት ሌሎች ሰዎች ያዩት ይሆናል፡፡

ጾም ግን ውስጣዊ በመሆኑ ለሰዎች እይታ አይጋለጥም

በመሆኑም ጾመኛ በአላህ ዘንድ የተለየ ክብር

አለው፡፡ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) አላህ በሐዲስ አል-ቁዱስ

«ጾም ለኔ ነው የምመነዳውም እኔው ነኝ» ማለቱን

ተናግረዋል፡፡20

5

Page 47: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - zhic.aeኢስላም፣ ኢማን እና ኢሕሳን 3 አጠቃላይ እይታ 4 መግቢያ 6 የጉዞ መመሪያ 6 ለጉዞ

መለኮታዊው መንገድ፡-የአዲስ ሙስሊሞች ስርዓተ ትምህርት30

ለመጾም ያሰበ ሰው ጐሕ ከመውጣቱ በፊት ተነስቶ

ቀለል ያለ ምግብ (ስሁር) መመገብ ይኖርበታል፡፡

ይህ የነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ልማድ ሲሆን በማግስቱ ከንጋት

እስከ ፀሐይ መጥለቅ ለመጾም ብርታትን ያጐናጽፋል፡፡

አንድ ባሪያ ፆሟል የሚባለው ራሱን ከምግብ ከመጠጥና

ከወሲባዊ ግንኙነት በቀኑ ክፍለ ጊዜ አቅቦ መዋል ሲችል

ነው፡፡ በዚህም የተነሣ እርሱ ወይም እርሷ የረሃብን

ስቃይ፣ የጥምን ቃጠሎና ፍላጐትን ሁሉ ያምቃሉ፡፡

የምግብና የመጠጥ አስፈልጐትን ችላ በማለት ከዚህ

እርካታ ባሻገር ለሚገኝ ታላቅ ግብ ያልማሉ፡፡

በሂደቱም ደመነፍሳዊ ፍላጐት ይገታና ለፈጣሪ ፍላጐት

ያድራል፡፡ ከዚያም ለአምልኮ መሳነፍ ይወገድና መንፈሳዊ

ብቃት መላበስ ይከተላል፡፡

የጾም ደረጃዎች

በተወዳጁ ነብይ (ሰ.ዐ.ወ) ማስጠንቀቂያ መሠረት

ብዙ ሰዎች በጾማቸው ከመራብና ከመጠማት በቀር

ምንም ሳያተርፉ ይቀራሉ፡፡ እነዚህ ሰዎች በጾማቸው

ምንም ዓይነት ምድራዊ ፋይዳ አልያም ለነገ

የሚያስቀምጡት ምንዳ የሌላቸው ናቸው፡፡

እነዚህ ሰዎች ምንም እንኳን ጨጓራቸው ምግብና

መጠጥ እንዳያገኝ ቢያቅቡት የተለያዩ ስሜቶቻቸውንና

ደመነፍሳቸውን ርሃብ ሲያረኩ የሚውሉ መሆናቸው

እውነት ነው፡፡

በመሆኑም ጾም ማለት ከምግብና ከመጠጥ መታቀብ

ብቻ አለመሆኑንና ከሃጢአትና ካለመታዘዝ መራቅ

የሚያስፈልግ መሆኑን አልተገነዘቡም፡፡ የአላህ

መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል

«ጾም ጋሻ ነው አንድ ሰው የጾመ ከሆነ ጸያፍ ንግግርም

ሆነ ያልተገባ ነገር አይናገር፡፡ አንድ ሰው ቢመታው

ወይም ቢሰድበው ሁለት ጊዜ «እኔ ጾመኛ ነኝ» ይበል፡፡

ለአንድ ጾመኛ ከምግብና ከመጠጥ ከመታቀቡ

ይልቅ የስሜቱን ልጓም መያዝ አለመቻሉ ከአላህ

ያርቀዋል፡፡ በተለይም ዓይኖች ልብን በሚመርዙ

እይታዎች፣ ምላሶችም ከመዋሸት፣ ከሃሜት፣ ስም

ከማጥፋትና ጸያፍ ነገሮች ከመናገር ጆሮዎችም መጥፎ

ከመስማት መታቀብ ይኖርባቸዋል፡፡

ጾመኛ ሰው ምንጊዜም ነፍሱን በሚያነፃት ተግባር

ማተኮርና መለኮታዊው አካል ከርሱ ምን

እንደሚጠበቅበት ማስተንተን አለበት፡፡

ይህን ሁሉ ነገር ትቶና ከምግቡና መጠጡ በመቆጠብ

የአላህን ፍራቻ (ተቅዋ) መሰነቅን ዋነኛው ትኩረቱ

ሊያደርግ ግድ ነው፡፡

ከጾም ሁሉ ትልቅ ደረጃ የሚሰጠው የነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ)

እና ከአላህ ጋር ፍጹም ወዳጅነት ያላቸው ባሮቹ

ጾም ነው፡፡ የእነርሱ ጾም ከዓለማዊ ጉዳይና ከስጋዊ

ስሜት የጸዳ በመሆኑ ወደ ፈጣሪያቸው እንዲቀርቡ

አስችሏቸዋል፡፡

ጾምን መግደፍ (ማፍጠር)

ፀሐይ ወደ ማደሪያዋ ስታቆለቁል በጾም የደከመ

ባሪያ ለሰዓታት ርቋቸው የነበሩትን የምግብና መጠጥ

ጸጋዎች በከፍተኛ አድናቆት ማሰብ ይጀምራል፡፡

ስለሆነም የጾመኛ ልብ ወደ ፈጣሪው በትህትና

በመመለስ እያንዳንዷን ትንሽ ጸጋ ሁሉ በአድናቆትና

በምስጋና ያስባል፡፡ ምክንያቱም በርካታ ሰዎች

ለሁልጊዜውም ሲራቡና ሲጠሙ መኖራቸውንም

ያስተውላል፡፡

በመጨረሻም ፀሐዩዋ ከአድማሱ በታች ስትጠልቅ

የዕለቱ ጾም ይጠናቀቃል፡፡ ስዎችም ጾማቸውን

ለመግደፍ በያቅጣጫው ይሯሯጣሉ፡፡ በቴምርና

ውሃ መግደፍ (ማፍጠር) የነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ)

ሱንና ነው፡፡ እርሳቸው እንዲህ ይላሉ፡-

አላህን አምኖና ምንዳውንም እንደሚሞላለት በመተሳሰብ የረመዳንን ወር የጾመ ያለፉት ሃጢአቶቹ ይሰረዙለታል፡፡ —ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ)“

Page 48: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - zhic.aeኢስላም፣ ኢማን እና ኢሕሳን 3 አጠቃላይ እይታ 4 መግቢያ 6 የጉዞ መመሪያ 6 ለጉዞ

31ክፍል 1 ፡- እስልምና

‹‹አንድን ጾመኛ ያስፈጠረ የጾመኛው ምንዳ ምንም

ሳይቀንስ የጾመኛውን ምንዳ ያገኛል፡፡››

ቤተሰቦችና ማሕበረሰቦች ጾማቸውን ለመግደፍ

ምሽቱን ይሰባሰባሉ፡፡ ይህ የማፍጠሪያ ምግብ ቀለል

ያለና በአካል ላይ ጫና የማያስከትል እንዲሆን

ይመከራል፡፡

ምክንያቱም ከጤንነት አንፃር ብቻ ሳይሆን ምሽቱን

ለሚደረጉ የአምልኮ ተግባራትም ጭምር ጠግቦ

መብላት ስለማያመች ነው፡፡ ከዒሻ ስግደት በኋላ

መስጊዶች የወሩን ትሩፋት በአምልኮ ለማግኘት

ተግባራት በሚፈልጉ ሰዎች ይጨናነቃሉ፡፡

ተራዊህ ሶላትን ይሰግዳሉ ቁርኣንን ያነብባሉ፣ ምጽዋትን

(ሰደቃ) ይሰጣሉ እንዲሁም እጆቻቸውን በማንሳት

አላህን ይለምናሉ፡፡ በእነርሱ የአምልኮ ተግባራት

የረመዳን ቀንና ሌሊቶች በብርሃን ይደምቃሉ፡፡

የምንቀስማቸው አስተምህሮዎች

በረመዷን የመጨረሻዎቹ ቀናት ገደማ ታላቅ

መንፈሳዊ በረከት ያላት፣ ‹ለይለተል ቀድር›

(የመወስኛይቱ ሌሊት) በመባል የምትታወቅ ሌሊት

አልለች፡፡

በዚህች ሌሊት ነበር የሰውን ዘር እጣፋንታ ከሥር

መሠረቱ የቀየረው ታላቁ ቁርኣን ለነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ)

የወረደላቸው፡፡

የመወሰኛይቱን ሌሊት ትክክለኛ ቀን በተመለከተ ምሁራን

የተለያዩ አስተያየቶችን የሰጡ ቢሆንም ጥቅል ስምምነት

ላይ የተደረሰበት ከወሩ የመጨረሻ ጎዶሎ ቀናት መካከል

በአንዱ የምትገኝ መሆኑ ነው፡፡ ቁርኣን ይህችን ሌሊት

ከሺህ ወር በላጭ እንደሆነች ይገልፃል፡፡ ስለሆነም

የሶስት ሰዎችን ጸሎት (ዱዓ) አላህ ውድቅ አያደርግም፡- ጾመኛ ሰው ሲገድፍ (ሲያፈጥር) የሚያደርገውን፣ የፍትሃዊ ዳኛን (ቃዲን) እንዲሁም የተበደለን ሰው ጸሎት (ዱዓ)፡፡ —ነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)

[ከላይ] ሙሰሊሞች ጾማቸውን ለመፍታት (ለመግደፍ) ተሰባስበው

Page 49: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - zhic.aeኢስላም፣ ኢማን እና ኢሕሳን 3 አጠቃላይ እይታ 4 መግቢያ 6 የጉዞ መመሪያ 6 ለጉዞ

መለኮታዊው መንገድ፡-የአዲስ ሙስሊሞች ስርዓተ ትምህርት32

ምዕመናን ከዚህች ሌሊት የሚገኘውን ታላቅ በረከት

ለማግኘት የመጨረሻዎቹን አሥር ሌሊቶች ተግተው

ይጠባበቃሉ፡፡

በመጨረሻም ብርማ አዲስ ጨረቃ በአድማሱ ላይ

ስትታይ ረመዳንን እንሰናበታለን፡፡ የታላቅ መንፈሳዊ

ስልጠናና ተመስጦ ወር የነበረው ረመዳን ሲያበቃ

ሙስሊሞች አንድ ላይ ተሰባስበው የኢድ አል-ፈጥር

በዓላቸውን ያከብራሉ፡፡

ቤቶች ይጸዳሉ፣ ልዩ ልዩ ማድመቂያዎች በየግድግዳውና

ጣሪያው ላይ ይሰቀላሉ፡፡ ጣፋጭ ምግቦችና መጠጦች

ተዘጋጅተው ይደረደራሉ፡፡ ከኢድ አል-ፈጥር በተጨማሪም

በፆም ወራት የተገኙትን መንፈሳዊ ልምዶች የማስታወስና

ፈጣሪ አላህ በሰላም ግዴታውን እንድናጠናቀቅ ስላደረገን

ምስጋና የምናቀርብበት ዕለት ነው፡፡

የዒድ በዓል ከመድረሱ ጥቂት ቀናት ጀምሮ ሶላቱ

እስኪሰገድ ድረስ ‘ዘካት አል-ፈጥር’ የሚባል ምጽዋት

(ሰደቃ) እንሰጣለን፡፡ ድሆች ያንን ተከፋፍለው ልክ

እንደማንኛውም ሙስሊም ተደስተው ይውላሉ፡፡

በዓመቱ ውስጥ መፆም የሚወደድባቸው በርካታ

ቀናት አልሉ፡፡ የረመዳን ጾማችን ተቀባይነት እንዳገኘ

የምናውቅበት ምልክት ሌሎች ተጨማሪ አምልኮቶችና

በጐ ተግባራትን ስንፈጽምና በረመዳን የጀመርናቸውን

መልካም ነገሮች ሁሉ በሌሎቹም ወራት መቀጠል

ስንችል ነው፡፡

ጉዟችንን በእምነት ማረጋገጫ የምስክርነት ቃል ጀምረን ከዚያም የኢሰላም መሰረቶች የሆኑትን ሰላትን፣ ዘካትና ጾምን ተመልከተን የመጨረሻ ወደሆነው የሐጅ ስነ-ስርኣት ደርሰና ፡፡

የመወሰኛይቱን ሌሊት በመጨረሻዎቹ አሥር ቀናት ፈልጓት —ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)“

Page 50: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - zhic.aeኢስላም፣ ኢማን እና ኢሕሳን 3 አጠቃላይ እይታ 4 መግቢያ 6 የጉዞ መመሪያ 6 ለጉዞ

33ክፍል 1 ፡- እስልምና

ሐጅ (ቅዱሱን ስፍራ መጎብኘት)

የፈጣሪ ቤት

በተቀደሰው የመካ መስጊድ ቅጽር ውስጥ ልዩ የሆነውና

ባለ አራት ማዕዘን ቅርጽ ያለው ካዕባ በብቸኝነት ግርማ

ተላብሶ ቆሟል፡፡

ካዕባን በጥንት ጊዜ የገነቡት ነቢዩ ኢብራሂም (ዐ.ሰ)

እና ልጃቸው ኢስማኢል (ዐ.ሰ) ሲሆኑ ካዕባ አንዱን

አምላክ በብቸኝነት ለሚያመልኩ ሁሉ በምድረበዳው

የሚገኝ የእምነት ማዕከል እንዲሆን የወረደላቸውን

መለኮታዊ ትዕዛዝ ተከትለው ነው፡፡ አላህ እንዲህ ይላል፡-

ለኢብራሂምም የቤቱን (የካዕባን) ስፍራ መመለሻ

ባደረግንለት ጊዜ በኔ ምንንም አታጋሩ ቤቴንም ለሚዞሩትና

ለሚቆሙበት ለሚያጎነብሱትና በግንባራቸውም ለሚደፉት

ንጹህ አድርግላቸው (ባልነው ጊዜ አስታውስ)

(አል-ሐጅ 26)

አላህ ካዕባን እንዲያንጹ ነቢዩ ኢብራሂምን (ዐ.ሰ)

ሲያዝ ለሰው ዘር በሙሉ ልክ አንደወደብ ላይ

መብራት ከሩቁ የሚያንጸባርቅ የአምልኮ ሥፍራን ነበር

ያዘጋጀው፡፡ እናም እንዲህ በማለት ወደዚያ ሥፍራ

አማኞች እንዲሰባሰቡ ጥሪ አድርጓል፡-

ነቢዩ ኢብራሂም (ዐ.ሰ) የጀመሩት ይህ ሥርዓት

ፍፃሜውን ያገኘው በነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)

ነበር፡፡ በዛሬው ጊዜ ካዕባ በምድር የተለያዩ ማዕዘናት

ለሚመጡ ምዕመናን ሁሉ የእምነት፣ የተመስጦና

አንዱን ፈጣሪ ብቻ የማምለኪያ ምልክት ሆኖ ቀጥሏል፡፡

በየትም ሥፍራ ያሉ ሙስሊሞች በየዕለቱ ለአምስት

6

[ከላይ] ካዕባ ብቸኛው የእውነተኛ አምልኮት ሥፍራ

Page 51: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - zhic.aeኢስላም፣ ኢማን እና ኢሕሳን 3 አጠቃላይ እይታ 4 መግቢያ 6 የጉዞ መመሪያ 6 ለጉዞ

መለኮታዊው መንገድ፡-የአዲስ ሙስሊሞች ስርዓተ ትምህርት34

ጊዜያት ያህል ፊታቸውን ወደዚህ ቅዱስ ስፍራ የሚያዞሩ

ሲሆኑ ልባቸውን ደግሞ ወደ ቤቱ ጌታ ወደ አላህ

ያዞራሉ፡፡

በየዓመቱ በሐጅ ወቅት አማኞች ከሁሉም የምድር

ማዕዘናት ተሰባስበው ወደዚያ ሥፍራ በመሔድ

የፈጣሪያቸውን ጥሪ በሟሟላትና ቤቱን በእምነታቸው

በማስጌጥ ታዛዥነታቸውን ያሳያሉ፡፡

አላህ እንዲህ ይላል፡-

«ለአላህም በሰዎች ላይ ወደርሱ መኼድን በቻለ ሁሉ

ላይ ቤቱን መጎብኘት ግዴታ አለባቸው»

(አለ-ዒምራን፡ 97)

ለጉዞ መዘጋጀት

የሐጅን ሥርዓተ ጸሎት ለመፈጸም የሚሹ ከዚህች ዓለም

ጋር ያላቸውን ትስስሮሽ ወደ ጐን ብለው፣ ቤተሰባቸውን፣

ንብረታቸውን፣ ቤታቸውንና ምቾታቸውን ጥለው ለጉዞ

ይሰናዳሉ፡፡ ከዚያም በትህትና ተሞልተው ከእርሱ ጋር

የገቡትን ቃል ኪዳን ለመሙላትና እምነታቸውንም

ለማደስ ወደዚያው ያቀናሉ፡፡

ያለፈውን የአኗኗር ዘይቤያቸውን ሁሉ እርግፍ አድርገው

በመተው በተለየ የአለባበስ ሥርዓት (የኢሕራም ልብስ)

ራሳቸውን ይቀይራሉ፡፡ ይህ ልብስ የሚያስታውሳቸው

ዕለተ ሞታቸው ሲደርስና ጌታቸው ጋር ለመገናኘት

ወደ መቃብሮቻቸው ሲወሰዱ የሚጠቀለሉበት የከፈን

ጨርቅ ነው፡፡

ሞት እንደሚታወቀው ሁሉንም በማዋረድ በተመሳሳይ

ሁኔታ ወደ አፈር እንደሚመልሰው ሁሉ የኢህራም ልብስም

የሃብት፣ የክብር፣ የሥልጣንና የዘር ልዩነቶችን አስወግዶ

ሁሉንም አንድ ዓይነት ያደርገዋል፡፡ እነሆ እዚያ የተገኘ

ሁሉ ንጹሕ ባሪያ በመሆን የሐጅ ሥርዓቱን ይፈጽማል፡፡

ይህን በመሰለ የቅድስና ሁኔታ ተጓዡ በዚያ አካባቢ

የሚገኝን ማንኛውም ሕይወት ያለው ፍጡር መጉዳት

እንዲሁም ጥፍርንና ጸጉርን መቁረጥና መነቃቀል

የተከለከለ ነው፡፡ ልክ እንደሌሎቹ የኢስላም ማዕዘናት

ይህ የአምልኮ ተግባር ትዕግስትንና ጽናትን ይጠይቃል፡፡

በተጨማሪም ተጓዡ ክርክርንና ስርዓቱን የሚያስተጓጉል

ማናቸውንም ሁኔታ ማስወገድ ይጠበቅበታል፡፡

የአላህ ነቢይ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ በማለት ቃል

ገብተዋል፡- «ያልተገቡ ንግግር ሳይናገር እና

እኩይ ተግባራትን ሳይፈጽም ሐጅ ያደረገ (የአላህን

ቤት የጎበኘ) ሰው (አላህ ያለፈውን ኃጢአቱን

በሙሉ ሰርዞለት) ልክ እናቱ እንደወለደችው ሆኖ

ይመለሳል፡፡»

አማኞች ሐጅ ለማድረግ ገና የተቀደሰውን ሥፍራ

ሲመለከቱ ልባቸው ከበሮ ይደልቃል፡፡ ይህም

የፈጣሪያቸውን ፈቃድ ለመፈጸምና ባርነታቸውን

ለማረጋገጥ ዝግጁ መሆናቸውን የሚያሳይ ምልክት ነው፡፡

ከዚያም “ለበይክ አላሁመ ለበይክ!” ይላሉ፡፡

ትርጉሙ “አላህ ሆይ! ፈቃድህን ለመፈጸም እዚህ

ነኝ!” ማለት ነው፡፡ እዚያ ሥፍራ የሄዱት የአላህን

ትዕዛዝ ለመፈጸምና ከዓለማዊ ጉዳዮች ይልቅ እርሱን

በመምረጥ ነው፡፡

ይህ ስሜት በቀጣዩ የመልእከተኛው (ሰ.ዐ.ወ)

ንግግር ተጠቃሏል፡- «ለተቀደሰ የሐጅ ተግባር ከጀነት

ውጪ ሌላ ምንዳ የለውም»

ዋና ዋና የሐጅ ሥርዓቶች

ገና የተከበረው መስጊድ ክልሎች ውስጥ እንደገቡ

አማኞች ተከታታይ የሆነውን ዝማሬ (ተልቢያ)

ማሰማታቸውን ይያያዙታል፡፡ ከዚያም በታላቁና ጥንታዊው

የካዕባ ግንብ ክፉኛ ልባቸው ይታመሳል፡፡ ቁጥራቸው

የማይታወቅ ሰዎች ዙሪያውን ሲዞሩ (ጠዋፍ ሲያደርጉ)

(አልነውም) በሰዎችም ውስጥ በሐጅ ትዕዛዝ ጥራ እግረኞች ከየሩቅ መንገድ በሚመጡ ከሲታ ግመሎችም ሁሉ ላይ

ኾነው ይመጡሃልና —(አል-ሐጅ፡ 27)

Page 52: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - zhic.aeኢስላም፣ ኢማን እና ኢሕሳን 3 አጠቃላይ እይታ 4 መግቢያ 6 የጉዞ መመሪያ 6 ለጉዞ

35ክፍል 1 ፡- እስልምና

በማየት ይበልጥ ይደመማሉ፡፡ ከዚያ በኋላ ራሳቸውን

እንደ ግብረ ጉንዳን በሚተምመው አማኝ መካከል

አስገብተው እነርሱም ዙሪያውን መዞር (ጠዋፍ

ማድረግ) ይጀምራሉ፡፡

በዚያ ዑደታቸው ረጋ ብለው ሲፈስሱ ልክ ከሰማየ

ሰማያት በላይ በሚገኘው የፈጣሪያቸው ዙፋን ዙሪያ

የሚዞሩትን መላእክት ይመስላሉ፡፡ ከዚያ በኋላ ደግሞ

ጉዟቸውን ቀጥለው ሶፋና መርዋ በተባሉት ኮረብታዎች

መካከል ወዳለው ሥፍራ ያመራሉ፡፡ በዚያ ሥፍራ ነበር

የኢስማኢል (ዐ.ሰ) እናት ሐጀር ለሕፃኑ ልጇ ውሃ

ፍለጋ ከወዲያ ወዲህ የተንከላወተችው፡፡ አላህም

በመጨረሻ የዘምዘም ውሃ እንዲፈልቅላት አድርጐ

እስካሁን ድረስ ምእመናን ወደዚያ ለሐጅ ሲሄዱ

ይጠጡታል፡፡

ከሐጅ ሥርዓቶች ሁሉ በጣም አስፈላጊው ደግሞ

የሚከናወነው ምዕምናን ሁሉ አንድ ላይ በሚሰባሰቡበት

የአረፋ ሜዳ ነው፡፡ እዚያ በሚገኘው የእዝነት ኮረብታ

ላይ ሆነው ነበር ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) በመሰናበቻው

ሐጅ የመጨረሻውን ንግግራቸውን ያሰሙት፡፡ በጊዜው

አማኞች እርስበርሳቸው እንዲዋደዱና አንዱ ለሌላው

መልካም ነገር እንዲያደርግ ምክራቸውን ለግሰዋል፡፡

ከመሰናበቻ ንግግራቸው በኋላም የመጨረሻውና ቀጣዩ

የቁርኣን አንቀጽ ወርዶላቸዋል፡-

… ³_ HÃT•�‹G<” K“”} VLG<L‹G<::

çÒ”U u“”} Là ðçUŸ<:: K�“”}U

›=eLU” ŸHÃT•ƒ uŸ<M ̈ ÅÉŸ<&...(አል-

ማኢዳህ፡ 3)አረፋት ሜዳ ላይ መቆም የአላህን እዝነት

መጠየቂያ፣ ተግቶ ጸሎት (ዱዓ) ማድረጊያና የራስን

ነፍስ መመርመሪያ አጋጣሚን ይፈጥራል፡፡ አንድ ሰው

ዙሪያውን በተንጣለለው ሜዳ የተሰበሰበውን ከተለያየ ዘር

የተውጣጣ ህልቆ መሣፍርት የሌለው ሕዝብ ሲመለከት

የመጪውን ዓለምና የፍርዱን ቀን ውሎ ማስታወሱ

አይቀርም፡፡

በቀጣዩ ቀን ምዕመናኑ ወደ ሚና ተመልሰው ትናንሽ

ጠጠሮችን በሰይጣን ተመስለው በቆሙ ሶስት አምዶች

(ምሶሶዎች) ላይ ይጥላሉ፡፡ ይህ ሥርዓት ነቢዩ ኢብራሂም

(ዐ.ሰ) በዚያ ሥፍራ ጌታቸውን እንዳይታዘዙ ሰይጣን

ሊጐተጐታቸው ሲሞክር በጠጠሮች የደበደቡትን

ለማስታወስ የሚደረግ ነው፡፡

ታላቁ መስዋእትነት

ቁርኣን ነቢዩ ኢብራሂም (ዐ.ሰ) ልጃቸውን

እስማኢልን (ዐ.ሰ) መስዋእት እንዳያደርጉት አላህ

እንዴት እንደፈተናቸው ይናገራል፡፡ እንዲሁም አባትና

ልጁ የፈጣሪያቸውን ትዕዛዝ ለማክበር ያሳዩትን ጽናትም

ይገልፃል፡፡

ሐጃጆች የአላህ እንግዶች ናቸው ፡፡ ቢጠይቁት የፈለጉትን ይሰጣቸዋል፡፡ ምህረት ቢጥይቁት ምህረቱን ይለግሳቸዋል፡፡ —ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ)“

Page 53: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - zhic.aeኢስላም፣ ኢማን እና ኢሕሳን 3 አጠቃላይ እይታ 4 መግቢያ 6 የጉዞ መመሪያ 6 ለጉዞ

መለኮታዊው መንገድ፡-የአዲስ ሙስሊሞች ስርዓተ ትምህርት36

የነቢዩ ኢብራሂም (ዐ.ሰ) ንጹህ እምነትና እውነተኛነት

በመጨረሻ ክሷቸዋል፡፡ ልጃቸውን መስዋእት ሊያደርጉት

በተዘጋጁበት ቅጽበት አላህ ትልቅ የበግ ሙክት በቤዛነት

ልኮላቸዋል፡፡

ይህ የአላህን ትዕዛዝ ለመፈጸም ማንኛውንም ነገር

ለመሰዋት መዘጋጀታቸው በሐጅ ወቅት በያመቱ

በዕለተ አረፋ (ኢድ አል-አደሃ) እንስሳትን በማረድ

ይታወሳል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ ሐጅ የማያደርጉና በቀረው የዓለም

ክፍል ያሉ ሙስሊሞች የኢድ አል-አደሃን በዓል በያሉበት

ሥፍራ ያከብሩታል፡፡ አቅም ያላቸውና የመስዋእት

እንስሳትን ማረድ የሚችሉ እያረዱ የተወሰነውን ክፍል

ለድሆች ይለግሣሉ፡፡ በዚህ ዓይነት የኢድ-በዓል ሲከበር

ሙስሊሞች አዲስ ልብሶችን ይለብሳሉ ስጦታዎችንም

ይለዋወጣሉ፣ በአምላክ በረከት ቤተሰቦች እርስበርስ

እየተጠያየቁ በደስታ ያሳልፋሉ፡፡

ነቢዩን (ሰ.ዐ.ወ) መጐብኘት

በመጨረሻም ሐጅ የሚያደርጉ ምእመናን ሥርዓተ

ሐጁን የሚያደርጉት ጸጉራቸውን በማሳጠርና ወደ

መካ ተመልሰው የመጨረሻውን ጠዋፍ በማድረግ

(ካዕባን በመዞር) ሲሆን ያደረጉትን ሐጅም አላህ

እንዲቀበላቸው ተስፋ ይሰንቃሉ፡፡

ይሁን እንጂ ለብዙዎቹ ጉዟቸው በዚህ አይገታም፡፡

አንድ ሊጐበኙት የሚገባቸው ሥፍራ አልለ፡፡ እርሱም

ከመካ በስተሰሜን በኩል የምትገኘው ቅድስቷ የመዲና

ከተማ ናት፡፡

መዲና ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) የኖሩባት፣ ወሕይ (ራዕይ)

የተቀበሉባት፣ መስጊድ የገነቡባት ብቻ ሳትሆን ሞተው

የተቀበሩባትም ጭምር ናት፡፡ የመዲና አፈር እስከ

ዓለም ፍጻሜ ብሩክ እንደሆነ ይቆያል፡፡ ምክንያቱም

በውስጡ የታላቁና ብሩኩ ነቢይ (ሰ.ዐ.ወ) አካል

አርፎበታልና፡፡

የሐጅ ተጓዦች ወደ መዲና የሚጓዙት ባላት ሰላም፣

በረከቶችና በነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) መስጊድ በመስገድ

የሚገኘውን ትልቅ ምንዳ በማሰብ ነው፡፡ ከሁሉም

በላይ ግን የሰውን ዘር መድህን ወደሚያገኝበትና

የእርጋታ ሕይወት ወደሰፈነበት ኢስላም የጠሩትን ነቢይ

(ሰ.ዐ.ወ) ሰላም ለማለት ነው፡፡ እርሳቸው በእርግጥም

ከፍጡራን ሁሉ በላጩ ናቸው፡፡ እንዲህ ብለዋል፡-

ከዚህ በፊት በሁሉም ዘንድ አንድ ዓይነት ስሜት እና በቀለም ልዩነት ውስጥ ወንድማማችነትን የማጠናከር እውነታ አላየሁም…. —ማልኮም ኤክስ የሐጅ ልምዱን ሲያካፍል

Page 54: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - zhic.aeኢስላም፣ ኢማን እና ኢሕሳን 3 አጠቃላይ እይታ 4 መግቢያ 6 የጉዞ መመሪያ 6 ለጉዞ

37ክፍል 1 ፡- እስልምና

«ማንም ለኔ ሰላምታ አያቀርብልኝም አላህ ነፍሴን

መልሷት ለሰላምታው ምላሽ የሰጠሁት ቢሆን እንጂ»

ነቢዩን (ሰ.ዐ.ወ) ሰላም ከማለት በፊት ተጓዦች

በመስጊዳቸው ገብተው በመቃብራቸውና ዲስኩር

(ኹጥባ) ያሰሙበት በነበረው ሥፍራ መካከል ባለው

ረውዳ በተባለው ቦታ ላይ ሁለት ዙር (ረከዓ) ሶለት

ቢሰግዱ ይመረጣል፡፡

ይህን ሥፍራ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ከገነት አጸዶች አንዱ

መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በረውዳ ላይ ሶላት ከሰገዱ በኋላ

አማኞች ፍጹም በተረጋጋና ትሕትና በተላበሰ ሁኔታ ወደ

ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) መቃብር በመሄድ ሰላምታ ማቅረብ

ነው፡፡ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡-

«የኔን የቀብር ቦታ ጎብኝቶ በኔ ላይ ሰላምታን ያወረደ እኔ

ዋስ እሆነዋለሁ»

ይህን ከፈጸሙ በኋላ ተጓዦች ‘በቂዕ’ ወደተባለው

መካነ መቃብር መሄድ ይጠበቅባቸዋል፡፡ በዚያ

በምድራችን አቻ ያልተገኘላቸው የሰናይ ምግባር

ተምሳሌቶች የሆኑ የነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ባልደረቦች

ተቀብረዋል፡፡

መዲና ደጋግመው በሚጐበኟትና እዚያው በሚኖሩ

ሕዝቦቿ ላይ የተወሰኑ መብቶች አሏት፡፡ እነዚህን

መብቶችና የሥነ-ምግባር እሴቶች ማንኛውም ሰው

በሚገባ ማወቅና መጠበቅ ይኖርበታል፡፡ ምክንያቱም

ታላቁ ነቢይ (ሰ.ዐ.ወ) ያረፉባትና ክቡሩ አካላቸው

የሚገኝባት የበረከት ከተማ በመሆኗ ነው፡፡

በሐጅ ወቅት ወደ ፈጣሪ የሚቀርቡበትን መንገዶችና ፈለጎች በመመልከት እኛም ይህንንና ሌሎች የእስልምና

መሰረቶችን ፈለጎች ወደቀጣዩ ጉዞ እናመራለን፡፡

መቃብሬን የሚጐበኝ አማላጅነቴ ተረጋገጠለችለት፡፡ —ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)“

Page 55: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - zhic.aeኢስላም፣ ኢማን እና ኢሕሳን 3 አጠቃላይ እይታ 4 መግቢያ 6 የጉዞ መመሪያ 6 ለጉዞ
Page 56: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - zhic.aeኢስላም፣ ኢማን እና ኢሕሳን 3 አጠቃላይ እይታ 4 መግቢያ 6 የጉዞ መመሪያ 6 ለጉዞ

ኢማን(እምነት)

«ኢማን ማለት በአላህ፣ በመልዕክቱ፣ በመጽሐፍቱ፣ በመልዕክተኞቹ እና በመጨረሻው ቀን አይቀሬነት ማመንና መልካምም ሆነ መጥፎ ነገር የሚያጋጥመው በአላህ ፈቃድ እንደሆነ አምኖ መቀበል ነው»

—የጅብሪል (ዐ.ሰ) ሐዲስ

Page 57: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - zhic.aeኢስላም፣ ኢማን እና ኢሕሳን 3 አጠቃላይ እይታ 4 መግቢያ 6 የጉዞ መመሪያ 6 ለጉዞ

መለኮታዊው መንገድ፡-የአዲስ ሙስሊሞች ስርዓተ ትምህርት40

አጠቃላይ እይታ7

የእምነት ዛፍ

አላህ መልካምን ቃል ሥርዋ (በምድር ውስጥ) የተደላደለች ቅርንጫፍዋም ወደ ሰማይ (የረዘመች) እንደሆነች መልካም ዛፍ አድርጎ ምሳሌን እንዴት እንደገለጸ አላየኽምን? ምግቧን (ፍሬዋን) በጌታዋ ፈቃድ በየጊዜው ትሰጣለች፡፡ አላህም ለሰዎች ይገሠጹ ዘንድ ምሳሌዎችን ይገልጻል፡፡

(ኢብራሂም፡ 24-25)

የኢማን ሥር በግምት፣ በጥርጣሬ ወይም በይሆናል ላይ

የተተከለ አይደለም፡፡ የሙስሊም እምነት በእውነተኛ

እውቀት ላይ ሥሩን የሰደደ በመለኮታዊው ሃይል

በመልእክተኛው (ሰ.ዐ.ወ) እና ከእነርሱ በሆነ

የእምነት ዛፍ ግንድ የፈጣሪን እውነት መቀበል ሲሆን

ፍሬው ደግሞ ከእርግጠኝነትና እውነተኝነት የተገኙ

መልካም ቃላት ናቸው፡፡

ስድስቱ ማዕዘናት

በአምስቱ የእስልምና መሠረቶችና ከእነርሱ በሚመነጭ

ተጽዕኖ ነፍስ ከጌታዋ ጋር የሚኖራት ግንኙነት ይሰምራል፡፡

ስድስቱን የእምነት ማዕዘናትን በማወቅ ግለሰቡ ለማመን

ምን ሁኔታዎችን ማሟላት እንደሚያስፈልግ የፈጣሪውን

ታላላቅ ምልክቶች በመገንዘብ በመለኮታዊው ፍላጐት

ሥር ራሱን ለማስማማት ይጥራል፡፡

ከእምነት መሠረታዊ ማዕዘናት የመጀመሪያው በአላህ

ማመን ሲሆን በዚህ እውነታ ዙሪያ ነው እንግዲህ

በመላእክቱ፣ በመጽሐፍቱ፣ በመልእክተኞቹ፣

በመጨረሻው ቀንና ክፉም ሆነ ደግ በፈጣሪ ፈቃድ

የሚፈጸም መሆኑን (ቀደር) ማመን የተባሉት የእምነት

ማዕዘናት የሚሽከረከሩት፡፡

እነዚህን ነገሮች አዘውትሮ በማሰላሰል እንዲሁም

በሰማያትና በምድር ያሉትን ምልክቶች በማስተዋል

አማኝ የሆነ ሰው የመጨረሻው የሕይወቱ ፌርማታ

እስኪደርስ ድረስ በእምነቱ ይመላለሳል፡፡

አሁን በኢማን ብርሃን ላይ ሆነን የሚታዩንን የኢማን ምልክቶች እየመረመርን ከመጀመሪያው የእምነት መሰረት በመጀመር መንገዳችንን እንቀጥል፡፡

Page 58: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - zhic.aeኢስላም፣ ኢማን እና ኢሕሳን 3 አጠቃላይ እይታ 4 መግቢያ 6 የጉዞ መመሪያ 6 ለጉዞ

41ክፍል 2፡- በአላህ ማመን

በአላህ ማመን8

ምልክቶቹና እጅግ ውብ የሆኑት ስሞቹ

በዚህ ጉዟችን ላይ እያለን በሚያጋጥመን ሰላማዊና ጸጥተኛ ቅጽበቶች ቆም ብለን እንድናስተውላቸው የሚገፋፉን ተፈጥሯዊ ክስተቶች በዙሪያችን ሞልተዋል፡፡በሰማያትና በምድር መካከል ያሉት ትዕይንቶች የፈጣሪን መኖር አፍ አውጥተው የሚያውጁ ምልክቶች ናቸው፡፡

እጅግ ሩቅ በሆነው ፈለከ ሰማይ ከሚንተገተጉት ከዋክብት ጀምሮ በምድር አፈር ውስጥ እስከሚሳቡት ትላትሎች፣ ገና ለመፈንዳት ከደረሰው የአበባ እንቡጥ እስከሚያለቅሱት እንቦቃቅላዎች ያሉት ሁሉ ትኩረታችንን እንድንቸራቸው ይጋብዙናል፡፡ ይህ ሁሉ የሚያምር የተፈጥሮ ትዕይንት ያስገኘውን ምሉዕ በኩልሄ ችሎታ ይገልጣል፡፡

በተጨማሪም እያንዳንዱ እንቅስቃሴና ክስተት የመለኮታዊውን ኃይል ስሞችና ባሕሪያት ያንጸባርቃል፡፡ እነዚህ ስሞችና ባሕሪያት እያንዳንዱን ሰው በዕለት ተዕለት ሕይወቱ ያጋጥሙታል፡፡ ከተራሮች ላይ የሚነሳን የእሳተ ገሞራ ፍንዳታና እንቅጥቃጤ ስንመለከት ምን ያህል ታላቅና ግዙፍ መሆኑን እናስተውላለን፡፡

ወቅቶች ሲፈራረቁ ሕይወትን ሰጪ ገዳይና አስነሺ የሆነውን አንዱን ፈጣሪ እናስባለን፡፡ እናት ለልጇ የምታሳየውን አምሳያ የሌለው ፍቅር ስንመለከት እጅግ በጣም ሩህሩህና በጣም አዛኝ የሚለውን የፈጣሪ ስምና ባሕሪ እናስታውሳለን፡፡የታላቅ ግርማና ልግስና ባለቤት የሆነው አላህ እንዲህ ይላል፡-

“እርሱም (ቁርኣን) እውነት መኾኑ ለነርሱ እስከሚገለፅላቸው ድረስ በአጽናፎቹ ውስጥና በነፍሶቻቸውም ውስጥ ያሉትን ተአምራታችንን በእርግጥ እናሳያቸዋለን፤ ጌታህም እርሱ በነገሩ ሁሉ ላይ ዐዋቂ መኾኑ አይበቃቸውምን?” (ሐሚም አስ-ሰጅዳህ፡ 53)

አላህ የሚለው ልዩ ስም ለአንዱና ለብቸኛው መለኮታዊ ኃይል የሚውል መጠሪያ ነው፡፡ ይህ ስም ለእርሱ ብቻ የተሰጠ እንደመሆኑም ማንም አይሻማውም፡፡ እንዲህ ይላል፡-

“… K`c< V¡g?” �¨<nKI”;”(መሪየም፡ 65)ከዚህም በተጨማሪ አላህ ሌሎች ዘጠና ጠዘኝ የሚሆኑ ስሞች አሉት፡፡ እነዚህ ስሞቹ የእርሱን ባሕሪያትና በፍጥረተ ዓለሙ ውስጥ የሚገለጡ ድርጊቶቹንና ሥራዎቹን የሚያንጸባርቁ ናቸው፡፡

ይሁን እንጂ ሁሉንም የሚያጠቃልለው መጠሪያ ግን አላህ የሚለው ሲሆን ይህም መለኮታዊውን ኃይል ለመጥራት በተደጋጋሚ የምንጠቀምበት ነው፡፡ የአላህን ዘጠና ዘጠኝ ስሞችና ትርጉማቸውን ጭምር ማወቅ አስፈላጊ ነው፡፡ አላህ እንዲህ ይላል፡-

Page 59: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - zhic.aeኢስላም፣ ኢማን እና ኢሕሳን 3 አጠቃላይ እይታ 4 መግቢያ 6 የጉዞ መመሪያ 6 ለጉዞ

መለኮታዊው መንገድ፡-የአዲስ ሙስሊሞች ስርዓተ ትምህርት42

አር-ራሕማኑእጅግ በጣም ሩህሩህ

አር-ረሒሙእጅግ በጣም አዛኙ

አል-መሊኩንጉሡ

አል-ቁድዱሱከጉድለት ሁሉ የጠራው

አስ-ሰላሙየሰላም ባለቤት

አል-ሙእሚኑጸጥታን ሰጪው

አል-ሙሀይሚኑጠባቂው

አል-ዓዚዙ አሸናፊው

አል-ጀብባሩ ኃያሉ

አል-ሙተከብቢሩ ኩሩው

አል-ኻሊቁ ፈጣሪው

አል-ባሪኡ አስገኚው

አል-ሙሶውዊሩ መልክን አሳማሪው

አል-ገፍፋሩ መሐሪው

አል-ቀህሃሩ አሸናፊው

አል-ወህሃቡ በጣም ለጋሹ

አር-ረዝዛቁ ሲሳይን ሰጪው

አል-ፈትታሑ ከፋቹ ለድል የሚያበቃው

አል-ዓሊሙ ዐዋቂው

አል-ቃቢዱ ሲሳይን የሚጨብጠው

አል-ባሲጡ ዘርጊው

አል-ኻፊዱ

ዝቅ አድራጊው

አር-ራፊዑ ከፍ አድራጊው

አል-ሙዒዝዙ አክባሪው

አል-ሙዚልሉ አዋራጁ

አስ-ሰሚዑ¢ ሰሚው

አል-በሲሩ መልካቹ

አል-ሐክሙ ፈራጁ

አል-ዐድሉ ፍትሐዊው

አል-ለጢፉ ሩህሩሁ

አል-ኸቢሩ ውስጠ አዋቂው

አል-ሐሊሙ ታጋሹ

አል-ዓዚሙ ታላቁ

አል-ገፋሩ መሐሪው

አሽ-ሸኩሩ አመስጋኙ

አል-ዐሊይዩ የበላዩ

አል-ከቢሩ ታላቁ

አል-ሐፊዙ ጠባቂው

አል-ሙቂቱ ቀላቢው

አል-ሐሲቡ ተቆጣጣሪው

አል-ጀሊሉ የላቀው

አል-ከሪሙ ቸሩ

አር-ረቂቡ ተጠባባቂው

አል-ሙጂቡ ጸሎትን ተቀባዩ

አል-ዋሲዑ ችሮታው ሰፊ የሆነው

አል-ሐኪሙ ዳኛው

አል-ወዱዱ አፍቃሪው

አል-መጂዱ የተላቀው

አል-ባዒሡ ቀስቃሹ

አሽ-ሸሂዱ ተከታታይ

አል-ላሁ

Page 60: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - zhic.aeኢስላም፣ ኢማን እና ኢሕሳን 3 አጠቃላይ እይታ 4 መግቢያ 6 የጉዞ መመሪያ 6 ለጉዞ

43ክፍል 2፡- በአላህ ማመን

በእርግጥ አላህ መቶ ለመሙላት አንድ ሲቀር ዘጠና ዘጠኝ ስሞች አሉት፡፡ አንዷን ያገኘ ጀነት ይገባል፡፡ — ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ)

አል-ሐቅቁ እውነተኛው

አል-ወኪሉ አስተናባሪው

አል-ቀዊይዩ ብርቱው

አል-መቲኑ ብርቱው

አል-ወሊይዩ ረዳቱ

አል-ሐሚዱ ምስጉኑ

አል-ሙሕሲ መልካም ዋዩ

አል-ሙብዱኡ አስገኚው

አል-ሙዒዱ አዘጋጅ

አል-ሙሕዪ ሕይወት ሰጪው

አል-ሙሚቱ ገዳዩ

አል-ሐይዩ ሕያው የሆነው

አል-ቀይዩሙ ራሱን ቻይ

አል-ዋጂዱ ግኙ

አል-ማጂዱ አስገኚው

አል-ዋሒዱ ብቸኛው

አስ-ሶመዱ መጠጊያው

አል-ቃዲሩ ሁሉን ቻዩ

አል-ሙቅተዲሩ ቻዩ

አል-ሙቀድዲሙ አስቀዳሚው

አል-ሙአኽኺሩ አራቂው

አል-አውወሉ የመጀመሪያው

አል-ኣኺሩ የመጨረሻው

አዝ-ዟሂሩ ግልጹ

አል-ባጢኑ ስውሩ

አል-ዋሊ ተከላካይ

አል-ሙተዒሊ የላቀው

አል-በርሩ በጐ ዋዩ

አት-ተውዋቡ ጸጸትን ተቀባዩ

አል-ሙንተቂሙ ተበቃዩ

አል-ዐፉውዉ ይቅር ባዩ

አር-ረኡፉ አዛኙ

ማሊኩል ሙልኩ ንጉሠ-ነገሥቱ

አል-ሙቅሲጡ ተበዳይን ረጂው

አል-ጃሚዑ ሰብሳቢው

አል-ገኒይዩ ተብቃቂው

አል-ሙግኒ አብቃቂው

አል-ማኒዑ ከልካዩ

አድ-ዷርሩ ጐጂው

አን-ናፊዑ ጠቃሚው

አን-ኑሩ ብርሃኑ

አል-ሃዲ መሪው

አል-በዲዑ ያለብጤ ፈጣሪው

አል-ባቂ ብቻውን ቀሪው

አል-ዋሪሡ ዓለማትን ወራሹ

አር-ረሺዱ ቀጥተኛውን መንገድ

አመልካቹ

አስ-ሶቡሩ ታጋሽ

ዙል ጀላሊ ወልኢክራሚ የግርማና የመከበር ባለቤት

Page 61: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - zhic.aeኢስላም፣ ኢማን እና ኢሕሳን 3 አጠቃላይ እይታ 4 መግቢያ 6 የጉዞ መመሪያ 6 ለጉዞ

መለኮታዊው መንገድ፡-የአዲስ ሙስሊሞች ስርዓተ ትምህርት44

“K›LIU SM"U eV‹ ›K<ƒ& (eƒçM¿) u`dDU Ø\ƒ&...” (አል-አዕራፍ፡ 180)

እነዚህ ስሞች ስለአላህ ባሕሪያት የሚናገሩ ሲሆን አማኝ ሰው ስለርሱ ይበልጥ እንዲያውቅ ያስችሉታል፡፡ እነዚህን ዘጠና ዘጠኝ ስሞች መዘርዘር ስሞቹን እንድናጠናቸው ትርጉማቸውን እንድናውቅ ሕይወታችንን በእነርሱ አማካይነት ለመቀየር ያስችላል፡፡

አማኝ የሆነ ሰው በተለይም “እጅግ በጣም ሩህሩህ” የሚለውን ስሙን የተገነዘበ ርህራሄ የሚያንጸባርቅ ሲሆን

“ሁሉን ሰሚ” የሚለውን ስያሜ የተገነዘበ ደግሞ ሞኝነት ከሚንጸባረቅባቸው ንግግሮች ራሱን በማራቅ መልካም ነገሮችን ብቻ ይናገራል፡፡ሁሉም ዓይነት ባሕርያት ብቸኛ በሆነው አንድ አምላክ መታየታቸውን በቅንነት እንረዳ፡፡ ቀደምት ምዕመናን የአላህን ስሞች የምር ነበር የተረዱት በተለይ «ፍጹም ሩሕሩሕነቱን»፡፡

መለኮታዊነቱን ማወቅየዚህ ስም ባለቤት የሆነው በተጨማሪም እንዲህ ይለናል፡፡

“ጋኔንንና ሰውንም. ሊግገዙኝ እንጅ ለሌላ አልፈጠርኳቸውም፡፡” (አዝ-ዛሪያት፡ 56)

ይህን አምልኮት የሚያሳየን እርሱን በሚገባ ማወቅና ማንነቱን በግልጽ በመረዳት የጉዟችን መዳረሻ የሆነው የአንድ አምላክ ሃይማኖት የእምነታችን መሠረት እንዲሆን ያስችለናል፡፡ አንድ ሰው ስለ ኃያሉ ጌታ ለማወቅ ከፈለገ መለኮታዊ ባሕሪያቱን በሚገባ ማወቅ ግዴታው ነው፡፡ ከእነዚህ ባሕሪያት የተወሰኑት ከፍጡራን ባሕሪያት በስም ይመሳሰላሉ፡፡ ይሁን እንጂ ለፈጣሪያችን ሲሆን ግን እነዚህ ባሕሪያት ምሉዕነትን የሚወክሉ ይሆናሉ፡፡

የአላህ ሕልውና

የዚህ ምሉእነት መገለጫ ከሆኑት የአላህ ባሕሪያት

(አሰ-ሲፋ አን-ነፍስያ)

የፈጣሪ መኖር

ፍጹም ታላቅነቱና ራሱን የገለጸባቸው ባህሪያት (አል-

ሲፋ አን-ነፍሲያ) ይባላሉ፡፡ ባሕሪያቱ እሱን ብቻ

ለመግለጽ የሚያገለግሉ ናቸው፡፡ በተለይ የእርሱን መኖር

ማረጋገጫና መግለጫ ፈጣሪ ብቻ ነው፡፡ ሕልውናው

ሊታወቅ የሚገባው፡፡ ምክንያቱም በምድር ላይ ያሉ

ፍጡራን በአጠቃላይ ቀድሞውኑ ያልነበሩና ከተፈጠሩ

በኋላም በመለኮታዊው ኃይል ላይ ሕልውናቸው ጥገኛ

ነው፡፡

የሌሎች መኖር ከአላህ ሕላዌ (መኖር )ጋር ፈጽሞ

አይነጻጸርም፡፡ ምክንያቱም የእርሱ መኖር በጅማሬ፣

በፍጻሜ፣ በጥገኝነትና በለውጥ ፈጽሞ ሊገለጽ

አይችልምና ነው፡፡

አምስቱ የማይነጻጸሩ ባህሪያት

የመለኮታዊውን ኃይል ምሉዕነት የሚያረጋግጡ ሌሎች

ተጨማሪ ባህሪያትም አልሉ፡፡ እነዚህን ባህሪያት

የምናውቃቸው የፍጡራንን ጉድለቶች ነቅሰን በማውጣት

ነው፡፡

እነዚህ ባህሪያት ሲፋት "አት-ተንዚህያ" በመባል

የሚታወቁ ሲሆን ከመለኮታዊ ምሉዕነት ውጪ ካሉ

ባህሪያት ጋር ይፋለሳሉ፡፡ ይህም ሰለእርሱ ማወቅ

የሚገባንን በወጉ እንድንገነዘብ ያግዛል፡፡ እነዚህ

የማይነጻጸሩ ባህሪያት የሚከተሉት ናቸው፡፡

1 ብቸኝነት (ወሕዳኒያህ)

አላህ አንድ እና ብቸኛ ሲሆን የብቸኝነትን ባሕሪም የሚጋራው የለም፡፡ እርሱ (አላህ) የተለያዩ ነገሮች ጥምረት አይደለም፡፡ ነገር ግን ሊገለጽ የማይችልና ቅዱስ የሆነ አካል ነው፡፡

እምነት ማለት መጀቦን ወይም ምኞት ማለት አይደለም፡፡ እምነት ማለት በልቦና ውስጥ ሰፍሮ በተግባር ሲተገበር ነው፡፡ —ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ)

Page 62: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - zhic.aeኢስላም፣ ኢማን እና ኢሕሳን 3 አጠቃላይ እይታ 4 መግቢያ 6 የጉዞ መመሪያ 6 ለጉዞ

45ክፍል 2፡- በአላህ ማመን

ልዩ የሆኑትን ባሕሪያቱን የሚጋራው ወይም በመለኮታዊነቱና በመፍጠር ኃይሉ አምሳያ አይገኝለትም፡፡አላህ እንዲህ ብሏል፣ "አምላካችሁ በእርግጥ አንድ ነው፡፡" (አስ-ሷፍፋት፡ 4)

2 መጀመሪያ የሌለው (አል-ቀዲም) እና

3 መጨረሻም የሌለው (አል-አኺር)

አላህ ለዘመኑ ጅማሬ የሌለውና እስከዘላለሙም ሕያውና

ሁሉን ቻይ ሆኖ ያለ እንከን የሚኖር ጌታ ነው፡፡ አላህ

እንዲህ ብሏል፣

እርሱ ፊትም ያለ ኋላም ቀሪ፣ ግልጽም ስውርም ነው፤

እርሱም ነገሩን ሁሉ ዐዋቂ ነው፡፡ (አል-ሐዲድ ፡3)

4 በራሱ ተብቃቂ (ቂያም ቢን-ነፍስ)

አላህ በራሱ የሚብቃቃና በማንም ላይ ጥገኛ ያልሆነ ጌታ ሲሆን ፍጥረታት ግን በአጠቃላይ የእርሱን እርዳታና ጥገኝነት ይፈልጋሉ፡፡

አላህ እንዲህ ይላል፣ እናንተ ሰዎች ሆይ! እናንተ (ሁል ጊዜ) ወደ አላህ ከጃዮች ናችሁ፤ አላህም እርሱ ተብቃቂው ምስጉኑ ነው፡፡ (ፋጢር ፡ 15)

5 ልቅና (ሙኻለፉ ሊል-ሐዋዲሥ)

አላህ ከማንኛውም ዓይነት ፍጡር ጋር ፈጽሞ

አይመሳሰልም፡፡ ሚስት፣ አጋር፣ አምሳያ እና ልጆች

የሌሉት ሲሆን፡፡ ፆታ የለሽ፣ ልዩና ከእዝነ ህሊናና

ምናባዊ አመለካካት ውጭ የሆነ ጌታ ነው፡፡

አላህ በይዘት፣ በቅርጽ፣ በቀለም ወዘተ ሊመጠን

የማይችልና በጊዜና በቦታ የማይገደብ የልቅና

ባለቤት ነው፡፡

አላህ እንዲህ ብሏል፡- የሚመስለው ምንም ነገር

የለም፤ (አሽ-ሹራ፡ 11) ፡፡

እነዚህ ባህሪያት በአጠቃላይ የአላህ መልዕክተኛ

(ሰ.ዐ.ወ) የቁርኣን አንድ ሶስተኛ ነች ባሏት በአል-

ኢኽላስ ምዕራፍ ውስጥ አንድ ላይ ተጠቃለው ይገኛሉ፡-

በል፡- እርሱ አላህ አንድ ነው፡፡ አላህ (የሁሉ)

መጠጊያ ነው፡፡ አልወለደም፤ አልተወለደምም፡፡

ለርሱም አንድም ብጤ የለውም፡፡

(አል-ኢኽላስ፡ 1-4)

ሰባቱ ማረጋገጫ ባህሪያት

አንድ ጊዜ ስህተት የሆኑ አስተሳሰቦችን ውድቅ ካደረግን በኋላ የአላህን ምሉዕነትና ማንነት የሚገልጹና የሚያረጋግጡ ሰባት ባህሪያትን ጠንቅቀን ማወቅ አለብን፡፡

እነዚህ ባህሪያት "ሲፋት አል-መዓኒ" በመባል የሚታወቁ ሲሆን የሚከተሉት ናቸው፡-

1 ሕይወት (ሐያት)

አላህ ሕያው ነው፡፡ ጅማሬና ፍጻሜ በሌለው ሕልውናውም ይገለጻል፡፡ አላህ እንዲህ ብሏል፣

አላህ ከእርሱ በቀር ሌላ አምላክ የለም፤ ሕያው፣ ራሱን ቻይ ነው፤ (አል-በቀራህ ፡ 255)

በዚያ በማይሞተው ሕያው አምላክ ላይ ተመካ፤ (አል-ፉርቃን ፡ 58)

2 ችሎታ ወይም ኃይል (ቁድራህ)

አላህ የችሎታና የኃይል ባለቤት ሲሆን መግድልና ሕያው

ማድረግ እንዲሁም ማስገኘትና ማጥፋት ይችላል፡፡ አላህ

እንዲህ ይላል፡-

አላህ የነገሩ ሁሉ ፈጣሪ ነው፡፡ እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ

አስተናባሪ ነው፡፡ (አዝ-ዙመር፡ 62)

አላህ በነገሩ ሁሉ ቻይ ነውና፡፡ (አል-በቀራህ ፡ 20)

አርሱም (ቁርኣን) እውነት መኾኑ ለነርሱ እስከሚገለጽላቸው ድረስ በአጽናፎቹ ውስጥና በነፍሶቻቸውም ውስጥ ያሉትን ታምራቶቻችንን በእርግጥ አናሳያቸዋልን ፤ —(እስ-ሳፍፋት ፡- 53)

Page 63: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - zhic.aeኢስላም፣ ኢማን እና ኢሕሳን 3 አጠቃላይ እይታ 4 መግቢያ 6 የጉዞ መመሪያ 6 ለጉዞ

መለኮታዊው መንገድ፡-የአዲስ ሙስሊሞች ስርዓተ ትምህርት46

3 እውቀት (ዒልም)

አላህ ምሉዕ በኩልሄና በዕውቀቱ ሁሉን ከባቢ ነው፡፡

እርሱ ሁሉንም አዋቂ በመሆኑ ከእሱ የሚደበቅም ሆነ

የሚሰወር ነገር የለም፡፡ አላህ እንዲህ ይላል፡-

የሩቅ ነገርም መክፈቻዎች እርሱ ዘንድ ናቸው፤ ከርሱ

በቀር ማንም አያውቃቸውም፡፡ በየብስና በባሕር ያለውንም

ሁሉ ያውቃል፤ ከቅጠልም አንዲትም አትረግፍም

የሚያውቃት ቢኾን እንጅ፤ (አል-አንዓም ፡ 59)

አላህም በነገሩ ሁሉ ዐዋቂ ነው፡፡ (አን-ኒሳእ ፡ 176)

4 ፍላጎት (ኢራዳህ)

አላህ የፍላጎት ባለቤት ነው፡፡ በዚህም የተነሳ የሻውን ሁሉ

ይሠራል፡፡ ማንኛውም ዓይነት ነገር ከእርሱ ፍላጎት ውጭ ፈጽሞ

ሊከሰት አይችልም፡፡ አላህ እንዲህ ይላል፡-

ለማንኛውም ነገር (መኾኑን) በሻነው ጊዜ ቃላችን ለርሱ

ኹን ማለት ብቻ ነው፤ ወዲያውም ይኾናል፡፡ (አን-ነሕል ፡ 40)

5 መስማት

እና

6 ማየት

አላህ የሚሰማ በመሆኑ ያለ ጆሮና ድምጽ ሁሉንም ነገር

ልቅም አድርጐ የመስማት ባህሪ ባለቤት ነው፡፡ በአንጻሩም

ምንም ዓይን የመመልከቻ መሣሪያ ሳያስፈልገው ሁሉንም

ነገር የሚያይ በመሆኑ የማየት ባህሪ ባለቤት ነው፡፡

ከእርሱ እይታና ማዳመጥ የሚሰወር አንዳች ነገር

የለም፡፡ አላህ እንዲህ ይላል፣

የሚመስለው ምንም ነገር የለም፤ እርሱም ሰሚው

ተመልካቹ ነው፡፡ (አሽ-ሹራ፡ 11)

7 ንግግር (ከላም)

አላህ የንግግር ባለቤት ነው፡፡ የእርሱ ንግግር ጅማሬ የለሽና

ዘላለማዊ ነው፡፡ ንግግሩ በድምጽ፣ በፊደልና በቃል ሊገለጽ

የሚችል አይደለም፡፡ ቁርኣን ይህንኑ ሲያረጋግጥ እንዲህ ይላል፡-

ከዛፍም በምድር ያለው ሁሉ ብዕሮች ቢሆኑ ኖሮ ባሕሩም

ከርሱ (ማለቅ) በኋላ ሰባት ባሕሮች የሚጨመሩለት ኾኖ

(ቀለም ቢኾንና ቢጻፍባቸው) የአላህ ቃላት ባላለቀች ነበር፤ (ሉቅማን፡ 27)

እጅግ አዛኝ ከኾነው ፈጣሪ ጋር መኖር

አላህ እንዲህ ብሏል፣

አላህ የሰማያትና ምድር አብሪ ነው፤ (አን-ኑር፡ 35)

አላህ በልዕልናውና በታላቅነት መንበሩ እጅግ የራቀ

ቢመስልም ለፍጡራኑ ቅርብና እነርሱን በእውቀቱ ከባቢ

ነው፡፡ ከርህራሄውና ከእዝነቱ መስፋት የተነሳ ፍጥረታቱን

በሙሉ ይንከባከባል፡፡

የአላህ መልዕከተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል ፣ አላህ

ፍጥረታትን ከፈጠረ በኋላ ከዙፋኑ በላይ ‘አዋጅ!

በርግጥ እዝነቴ ቁጣዬን አሸንፋለች’ የሚል ጽሑፍ

አስፍሯል፡፡29

በእስልምና መንገድ ላይ የሚጓዙ ሁሉ የአላህ ምህረት

በነገሩ ሁሉ ላይ ተንሰራፍቶና ውብ ሆኖ ያዩታል፡፡ ይህን

ስለሚገነዘቡም ብቸኘነት አይሰማቸውም፡፡ አላህ እንዲህ

ይላል፡-

ሰውንም ነፍሱ (በሐሳቡ) የምታጫውተውን የምናውቅ

ስንኾን፣ በእርግጥ ፈጠርነው፤ እኛም ከደም ጋኑ ጅማት

ይበልጥ ወደርሱ ቅርብ ነን፡፡ (ቃፍ፡ 16) እርሱም

የትም ብትኾኑ ከናንተ ጋር ነው፤

በል፡- እርሱ አላህ አንድ ነው፡፡ አላህ (የሁሉ) መጠጊያ ነው፡፡ አልወለደም፤ አልተወለደምም፡፡ ለርሱም አንድም ብጤ የለውም፡፡" —(አል-ኢኽላስ ፡- 1-4)“

Page 64: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - zhic.aeኢስላም፣ ኢማን እና ኢሕሳን 3 አጠቃላይ እይታ 4 መግቢያ 6 የጉዞ መመሪያ 6 ለጉዞ

47ክፍል 2፡- በአላህ ማመን

(አል-ሐዲድ፡ 4)ወደ ፍጡራኑ በመለኮታዊና በርህራሄ እይታ ይመለከታቸዋል ፡፡ እርዳታውንም በቀጥታ ለእያንዳንዱ ግለሰብ እንደርሱ ፍላጎት ያዳርሳል፡፡ አላህም (ሱ.ወ) እንዲህ ብሏል ፣ ‹‹ባሮቼም ከእኔ በጠየቁህ

እምነት ሰባ ቅርንጫፎች አሉት ፡፡ ከነርሱ ውስጥ ትልቁ በእርግጥ ከአላህ በስተቀር አምልኮት የሚገባው አምላክ የለም የሚለው ሲሆን ከነርሱ ውስጥ ትንሹ ደግሞ ጎጂ ነገሮችን ከመንገድ ላይ ማስወገድ ነው፡፡ —ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ)

ጊዜ (እንዲህ በላቸው) እኔ ቅርብ ነኝ፡፡ የለማኝን ጸሎት በለመነኝ ጊዜ እቀበለዋለሁ፡፡›› (አል-በቀራህ ፡ 186) በምላሹም እያንዳንዱ በመንገዱ ላይ የሚጓዝ ተጓዥ አላህን (ሱ.ወ) ሊያመሰግንና እርሱንም በቅንነት ሊያመልክ ይገባዋል ፡፡

Page 65: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - zhic.aeኢስላም፣ ኢማን እና ኢሕሳን 3 አጠቃላይ እይታ 4 መግቢያ 6 የጉዞ መመሪያ 6 ለጉዞ

መለኮታዊው መንገድ፡-የአዲስ ሙስሊሞች ስርዓተ ትምህርት48

በመላእክት ማመን9

የአላህ ባሮች

በእምነት ጐዳና ላይ አብረውን ሲጓዙ ከነበሩ ሰዎች በተጨማሪ አላህን የሚያመልኩ ሌሎች ፍጥረታትአልሉ፡፡ አጽናፈ ዓለሙ የተለያዩ የሕላዌ ቅርጽና ይዘት ባላቸው ፍጡራን የተሞላ መድረክ ነው፡፡ ከእነዚህ ፍጡራን ከፊሎቹ የሚታዩ ሲሆኑ ከፊሎቹን ደግሞ በዓይናችን አናያቸውም፡፡

ከሕዋሳቶቻችን የራቀውን ዓለም አስመልክተው ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ከነገሩን መልእክቶች መካከል ከብርሃን የተፈጠሩ በሰው ልጅ የተለመዱ ዓይኖች የማይታዩ ፍጡራን መኖራቸው ይገኝበታል፡፡ አካሎቹ በተለያዩ ቅርጾች ራሳቸውን የመቀያየር ችሎታ እንዳላቸውም ጭምር ነግረውናል፡፡እነዚህ ፍጡራን መላእክት ሲሆኑ ንጹሕ፣ ፆታ የሌላቸውና ከማንኛውም ዓይነት ቁሳዊ ፍላጐት ነጻ የሆኑ ናቸው፡፡ ለፈጣሪያቸው ፍጹም ታዛዥ በመሆናቸው እንዲፈጽሙ የተነገራቸውን ማንኛውንም ነገር ይፈጽማሉ፡፡ ዋነኛው ሥራቸው በቀንም ሆነ በማታ ፈጣሪያቸውን ማወደስ ነው፡፡

ከመላእክት ውስጥ የተወሰኑት መለኮታዊውን መንበር (ዙፋን) የሚሸከሙ ሲሆን የተወሰኑት ደግሞ በዙፋኑ ዙሪያ እየዞሩ ፈጣሪያቸውን ያሞግሳሉ እንዲሁም ለአማኞች ምህረትን ይለምናሉ፡፡ ሁኔታው በቁርኣን እንደሚከተለው ተገልጿል፡-

… «ጌታችን ሆይ! ነገሩን ሁሉ በእዝነትና በዕውቀት ከበሃል፤ ስለዚህ ለነዚያ ለተጸጸቱት. መንገድህንም ለተከተሉት ምሕረት. አድርግላቸው፤ የእሳትንም ቅጣት ጠብቃቸው.» እያሉ ለነዚያ ላመኑት ምሕረትን ይለምናሉ፡፡ (አል-ሙእሚን፡ 7)

ሌሎች መላእክት ደግሞ ከጌታቸው የሆኑ ልዩመልእክቶችንና ምልክቶችን ለተወሰኑ ሰዎች ያደርሳሉ፡፡ አሁንም ሌሎቹ በምድር ላይ በመጓዝ የአላህ ስም የሚወሳባቸውን ሥፍራዎች በመክበብ ከቆዩ በኋላ ማውሳቱ ሲያበቃ ይበተናሉ፡፡

ልዩ የሆኑ መላእክት

ምንም እንኳን በዓይነ-ሥጋ የማይታዩ መሆናቸውን ሙስሊሞች ቢያምኑም መላእክት በሰው ልጅ ጉዳዮች ላይ በንቃት የሚሳተፉ ሲሆን ለሰው ልጅ ሕይወትም ብዙ ጠቃሚ ነገሮችን ይከውናሉ፡፡

ከመላእክት ሁሉ ዋነኛውና ሊቀ መላእክት በመሆን የሚታወቀው ገብርኤል ጅብሪል (ዐ.ሰ) ነው፡፡ እርሱ በእርግጥም ከፍ ያለ ደረጃ ያለው ሲሆን ራዕይን (ወሕይን) ለነቢያት የሚያደርሰው እርሱ ነው፡፡ ጅብሪል (ዐ.ሰ) ቁርኣንን ለነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) አውርዶላቸዋል፡፡

ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) አንድ ዕለት ወደ ሰማይ ሲመለከቱ ጅብሪል (ዐ.ሰ) አድማሱን ሁሉ ሞልቶት አስተዋሉ፡፡ ከዚያም “ሙሐመድ ሆይ! አንተ የአላህ መልእክተኛ ነህ እኔ ደግሞ ጅብሪል ነኝ” አለ፡፡ ሌላው በቁርኣን ስሙ የተወሳ መልአክ ሚካኤል (ዐ.ሰ) ነው፡፡ እርሱ በአላህ ፈቃድ ዝናብንና ሲሳይን ወደ መሬት ያወርዳል፡፡ የፍርዱ ቀን በሚደርስ ጊዜ ኢስራፊል (ዐ.ሰ) የተባለው መልአክ የሚነፋው መለከት የዚህች ዓለም ፍፃሜና የመጪው ዓለም (የፍርዱ ቀን) መጀመሩን ያውጃል፡፡

ሪድዋን (ዐ.ሰ) ጀነትን የሚቆጣጠር መልአክ ሲሆን ያልተፈቀደላቸው ሰዎች ወደርሷ ውስጥ እንዳይገቡ ይከላከላል፡፡ ሌላው ደግሞ ማሊክ የተባለው የጀሃነም አለቃ ነው፡፡ ማሊክ እጅግ ጠንካራና አስፈሪ መሆኑ ተጠቅሷል፡፡ በምድረ ዓለም ላይ እያለ እያንዳንዱ ሰው ሁለት ተጠባባቂ መላእከት ተመድበው ይከታተሉታል፡፡

እነርሱም ረቂብና አቲድ ናቸው፡፡ የተከበሩና የእያንዳንዱን ሰው ጥሩና መጥፎ ድርጊቶች የሚመዘግቡ ናቸው፡፡እያንዳንዱ ሰው በምድራዊ ሕይወቱ የሚቆይበት ጊዜ ሲጠናቀቅ የማይናወጽ አቋም ያለው የሞት መልአክ

Page 66: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - zhic.aeኢስላም፣ ኢማን እና ኢሕሳን 3 አጠቃላይ እይታ 4 መግቢያ 6 የጉዞ መመሪያ 6 ለጉዞ

49ክፍል 2፡- በአላህ ማመን

አዝራኤል ይመጣና ቢዘጋጅም ባይዘጋጅም ነፍሱን ይወስዳል፡፡ ከዚያም ቀብር ውስጥ ሲገባ ነኪርና ሙንከር

የተባሉት መላእክት ስለጌታው፣ ሃይማኖቱ፣ የሚከተለው ነቢይ ማን እንደሆነ ይጠይቁታል፡፡ ይህ ጥያቄ በፍርዱ ቀን ለሰው ልጅ ለሚቀርብለት ጥያቄ እንደ መጀመሪያ (መተዋወቂያ) ነው፡፡

እነዚህን ሁለ የተለያዩ ሚናዎች የሚጫወቱት መላእክት ውስጣዊና ውጫዊ ጉዳያችንን በቀጥታ የሚነካ ተጽዕኖ በእኛ ላይ ያላቸው ሲሆን ይህም እስከ ሕይወታችን

መጨረሻ የማይቋረጥ ነው፡፡

አላህ የሚጓዙ መላዕከት አሉት ፡፡ በጉዟቸው ውስጥም አላህን የሚያሰታውሱ ሰዎችን ይፈልጋሉ ፡፡ አላህን የሚያስታውሱ ሰዎችን ሲያገኙ እርስ በርሳቸው ይጠራራሉ፡… —ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ)

ከእኛ ምናብ ውጪ ስላለው ዓለም በታላቅ አስተውሎት ስናማትር አላህ ባሮቹን ወደ ዘላለማዊው ሃቅ እንዴት እንደሚመራቸው ይህን

ሶስተኛውን የእምነት ማዕዘን በማጤን እንገናዘባለን፡፡

መልአክ የሚያከናውነው ተግባር

ገብርኤል (ጅብሪል ዐ.ሰ) ወህይ (ራዕይ) አመላላሽ

ሚካኤል (ዐ.ሰ) ዝናብና ሲሳይን (ሪዝቅ) የሚያወርድ (የሚያከፋፍል)

ኢስራፊል (ዐ.ሰ) የፍርዱ ቀን ሲደርስ በመለከቱ (በቀንዱ) የሚነፋ

ሪድዋን (ዐ.ሰ) የገነት ጠባቂ (ዘበኛ)

ማሊክ (ዐ.ሰ) የገሃነም ጠባቂ (ዘበኛ)

ረቂብ (ዐ.ሰ) ጥሩና መጥፎ ድርጊቶችን መዝጋቢ

አቲድ (ዐ.ሰ) ጥሩና መጥፎ ድርጊቶችን መዝጋቢ

አዝራኢል (ዐ.ሰ) የሞት መልአክ

ሙንከር (ዐ.ሰ) በቀብር ውስጥ ሙታንን የሚጠይቅ

ነኪር (ዐ.ሰ) በቀብር ውስጥ ሙታንን የሚጠይቅ

Page 67: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - zhic.aeኢስላም፣ ኢማን እና ኢሕሳን 3 አጠቃላይ እይታ 4 መግቢያ 6 የጉዞ መመሪያ 6 ለጉዞ

መለኮታዊው መንገድ፡-የአዲስ ሙስሊሞች ስርዓተ ትምህርት50

በመለኮታዊ መጽሐፍ ማመን10

መለኮታዊ ራዕይ

በሰው ልጅ ታሪክ የተለያዩ ምዕራፎች አላህ ከአደም

ልጆች ጋር ለመነጋገር የተመረጡ ነቢያትን ሲልክ ኖሯል፡፡

ለተለያዩ ቡድኖች ለጊዜያቸውና ላሉበት ሥፍራ ተስማሚ

የሆኑ መጽሐፍትን በማውረድ ለመጪው ዓለም የተሳካ

ዝግጅት እንዲያደርጉ ሰጥቷቸዋል፡፡

አላህ እንዲህ ይላል፡-

ከአላህ ዘንድ ብርሃንና ገላጭ መጽሐፍ በእርግጥ

መጣላችሁ አላህ ውዴታውን የተከተሉትን ሰዎች

የሰላምን መንገዶች በርሱ ይመራቸዋል፡፡ በፈቃዱም

ከጨለማዎች ወደ ብርሃን ያወጣቸዋል ወደ ቀጥተኛው

መንገድ ይመራቸዋል፡፡ (አል-ማኢዳህ፡ 15-16)

እያንዳንዱ ሕዝብ በራሱ ቋንቋ የተሰጡትን ዝርዝር

ሕግጋት ይፈጽም ዘንድ የጋራ እውነታ ወደሆነው

አንድ ቃል መምጣት ነበረበት፡፡ ይህም ከአላህ በቀር

የሚያመልኩት ጌታ የለም የሚለው ነው፡፡

አላህ እንዲህ ይላል፡-ከመልዕክተኛ ማንኛውንም

ለነርሱ ያብራራላቸው ዘንድ በወገኖቹ ቋንቋ እንጂ በሌላ

አልላክንም፡፡ (ኢብራሂም፡ 4)

እነዚህ ሁሉ መለኮታዊ መጽሐፍት የወረዱት ከተመሳሳይ

ምንጭ እንደሆኑና የያዟቸው መልእክቶች ከአንዱ

ፈጣሪ የተወረዱ መሆናቸውን ሙስሊሞች ይቀበላሉ፡፡

ይሁን እንጂ እንዲህ ሲባል መጽሐፍቱ ጥንት በወረዱበት

አኳኋን ሳይበረዙና ሳይከለሱ ተቀምጠዋል ለማለት

ያስቸግራል፡፡

ከፈጣሪ አላህ ለሰው ልጆች በተለያዩ ጊዜያት በርካታ

መጽሐፍት እንደ ወረዱላቸው ቢታወቅም ከእነርሱ

ውስጥ አራቱ ብቻ ናቸው በስም የተጠቀሱት፡፡

Page 68: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - zhic.aeኢስላም፣ ኢማን እና ኢሕሳን 3 አጠቃላይ እይታ 4 መግቢያ 6 የጉዞ መመሪያ 6 ለጉዞ

51ክፍል 2፡- በአላህ ማመን

እነርሱም ለነቢዩ ሙሣ (ዐ.ሰ) ተውራት (ኦሪት)፣

ለነቢዩ ዳውድ (ዐ.ሰ) ዘቡር (መዝሙር)፣ ለነቢዩ

ዒሣ (ዐ.ሰ) ኢንጅል (ወንጌል) እና ለነቢዩ ሙሐመድ

(ሰ.ዐ.ወ) ቁርኣን (ፉርቃን) ናቸው፡፡ይሁን እንጂ

ከሌሎች መጽሐፍት በተለየ ሁኔታ ቁርኣን ምንም ዓይነት

ለውጥ ሳይደረግበት እስካሁን የቆየ ሲሆን ለወደፊቱም

ይቀጥላል፡፡ አላህ እንደሚከተለው በማለት ቃል

ገብቷልና፡-

እኛ ቁርኣንን እኛው አወረድነው እኛም ለርሱ

ጠባቂዎቹ ነን (አል፡ ሒጅር፡ 9)

የአላህ ቃል

ቁርኣን ለሰው ልጆች እስከ ዓለም ፍፃሜ የሚቆይ

መመሪያ መጽሐፍ እንደመሆኑ ከእርሱ በፊት የወረዱ

መጽሐፍትን የሚያረጋግጥና የያዟቸውን ሕግጋት

ደግሞ የሚያድስ ነው፡፡ በጣም ሩሕሩሕ የሆነው አላህ

እንዲህ ይላል፡-

እናንተ cዎ‹ JÃ! ŸÑ@�‹G< Ódç? uÅ[„‹

¨<eØU LK¨< (¾SÖ^Ö` ui�) SÉ�’>ƒ

KU�S“”U w`H”“ �´’ƒ u�`ÓØ

S׋L‹G<:: (ዩኑስ፡ 57)

የመጀመሪያው ክቡር የሆነ ወሕይ (ራዕይ) በነቢዩ

ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ላይ በመልአኩ ጅብሪል

(ገብርኤል) አማካይነት ሲወርድ የነበረው ብርሃን

ጨለማዎችን ድል የነሣ ነበር፡፡ ያ ራዕይ በመወሰኛይቱ

ሌሊት (ለይለቱል ቀድር) ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) የአርባ

ዓመት ጐልማሳ ሆነው እያሉ ነበር የወረደው፡፡ከዚያ

በኃላ በቀጠሉት ሃያ ሶስት ዓመታት ቁርኣን በጠራ

የዐረብኛ ቋንቋ እየወረደ መለኮታዊው ምሪት ሥርዓት

ባለው መልኩ ቀጥሏል፡፡ አላህ እንዲህ ይላል፡-

�”Ų=G<U ®[w— l`œ” §• ›¨[É’¨<& ›LI”U

Ãð\ ²”É. ¨ÃU K’c< ÓXç?” ÁÉeL†¨< ²”É

Ÿ³‰ ÅÒÓS” u¨<eÖ< ÑKê”:: (ጣሃ፡ 113)

ለነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) የወረደላቸው

አምሳያ የሌለው ቁርኣን አድማጮቹን የሚያስደምም

በትርጓሜውና በቋንቋ ደረጃው አምሳያ የሌለው ነው፡፡

ምዕራፎቹ በትክክል የተሰደሩ አንቀጾቹ ደግሞ የዓለምን

አፈጣጠርና መጨረሻዋን እንዲሁም የሚታየውንና

የማይታየውንም ዓለም የሚዳስሱ ናቸው፡፡

ኃያሉ አላህ እንዲህ ይላል፡-

ÃIU Á¨[É’¨< ¾§’ ¾}v[Ÿ SêNõ ’¨<&

}Ÿ}K<ƒU& Ã�²”L‹G<U ²”É (Ÿ¡IŃ)

}Ö”kl:: (አል-አንዓም፡ 155)

የቁርኣንን ታላቅነትና ቅድስና የተገነዘቡ በነቢዩ

(ሰ.ዐ.ወ) ዙሪያ የነበሩ ሰዎች ራሳቸውን እያነጹ

መለኮታዊ መጽሐፍ የተላኩላቸው ነብያት

ተውራት (ኦሪት) ለነቢዩ ሙሳ (ዐ.ሰ)

ዘቡር (መዝሙር) ለነቢዩ ዳውድ (ዐ.ሰ)

ኢንጅል (ወንጌል) ለነቢዩ ኢሳ (ዐ.ሰ)

ቁርኣን (ፉርቃን) ለነቢዩ መሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)

ይህ ቁርኣን ወደዚያች እርሷ ቀጥተኛ ወደ ኾነችው መንገድ ይመራል ፤ እነዚያንም በጎ የሚሰሩትን ምእመናን ለነሱ ታላቅ ምንዳ ያላቸው መሆኑን ያበስራል፡፡ —(አል -ኢስራእ ፡-9)

Page 69: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - zhic.aeኢስላም፣ ኢማን እና ኢሕሳን 3 አጠቃላይ እይታ 4 መግቢያ 6 የጉዞ መመሪያ 6 ለጉዞ

መለኮታዊው መንገድ፡-የአዲስ ሙስሊሞች ስርዓተ ትምህርት52

(ውዱዕ እያደረጉ) ነበር የሚነኩት፡፡ አንዳንዶቹ

የተወሰኑ ምዕራፎቹን በተለያዩ ቁሳቁሶች ላይ ይጽፉ

የነበሩ ሲሆን ሌሎቹ ደግሞ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ባሉበት

በታላቅ ጥንቃቄ ካዳመጡ በኋላ በአእምሯቸው ይይዙት

ነበር፡፡ አላህ እንዲህ ይላል፡-

ቁርኣንንም ለመገንዘብ በእርግጥ አገራነው፤

ተገንዛቢም አልለን? (አል-ቀመር፡ 17)

ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) በሕይወት በነበሩባቸው ዘመናት

ቁርኣንን በቃላቸው ያጠኑና ያጠኑትም ነገር ትክክለኛ

መሆኑን በሚገባ ያመሳከሩ በርካታ ሰዎች ነበሩ፡፡ ከዚያ

ጊዜ ጀምሮ ያለምንም አነስተኛ ለውጥ ከትውልድ ወደ

ትውልድ ሲተላለፍ ቆይቷል፡፡

ጊዜ እያለፈ ሲሄድ የቁርኣንን ትርጉሞች በስፋት

የሚተነትን የታላላቅ ምሁራን ስብስብ ተፈጠረ፡፡ እነዚያ

ምሁራን ሕይወታቸውን ለፈጣሪያቸው ያስገዙና ሙሉ

ተመስጧቸውን ለቁርኣን የሰጡ ነበሩ፡፡

በውጤቱም በርካታ የቁርኣን ትንታኔዎች የተዘጋጁ

ሲሆን ይህም ለቁጥር የሚያታክቱ ሥነ-ጽሑፋዊ ቅርሶች

እንዲገኙ አስችሏል፡፡

ቁርኣንና የእኛ ሕይወት

ከቁርኣን ጋር ያላቸውን ግንኙነት የሚያሳምሩ በእርሱ

እንዲያስተነትኑና እንዲሠሩበት የሚያስችላቸውን

ጥቅም ያገኛሉ፡፡ እያንዳንዷ አንቀጽ ለእነርሱ

ለራሳቸው የወረደች ያህል በነፍሶቻቸው ላይ ተጽዕኖ

ያድርባቸዋል፡፡ ያወረደውንም ፈጣሪያቸውን ግርማ

ይፈራሉ፡፡ አላህ እንዲህ ይላል፡-

ይህንን ቁርኣን በተራራ ላይ ባወረድነው ኖሮ ከአላህ

ፍራቻ (የተነሳ) ተዋራጅ ተሰንጣቂ ኾኖ ባየኸው

ነበር፤ ይህችንም ምሳሌ ይገመግሙ ዘንድ ለሰዎች

እንገልፃታለን፡፡ (አል-ሐሽር፡ 21)

ቁርኣንን ማንበብ ዓይንን፣ ምላስንና ጆሮን የሚያሳትፍ

የአምልኮት ክፍል ነው፡፡ ዓይኖች ከዚህ አምልኮ

﴾﴾«እንደዚሁም ዐረብኛ ቁርኣን ኾኖ አወረድነው አላህንም ይፈሩ ዘንድ ወይም ለነሱ ግሳፄን ያድስላቸው ዘንድ ከዛቻ ደጋግመን በውስጡ ገለጽን —(ጣሃ፡- 113)“

Page 70: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - zhic.aeኢስላም፣ ኢማን እና ኢሕሳን 3 አጠቃላይ እይታ 4 መግቢያ 6 የጉዞ መመሪያ 6 ለጉዞ

53ክፍል 2፡- በአላህ ማመን

የሚኖራቸው ድርሻ የቁርኣንን ጽሑፎች ማየታቸው

ሲሆን ምላስ ማንበቡ፣ ጆሮዎች ደግሞ ጣፋጭ የሆነውን

ቅላፄ ማዳመጣቸው ነው፡፡

ቁርኣን የወረደበትን የዐረብኛ ቋንቋ መማር

ይመከራል፡፡ ዐረብኛ ቋንቋን በሚገባ ማወቅ የሠራህ

አካል ያወረደልህን መጽሐፍ በጥልቅ አድናቆት

እንድትመረምረው ያግዝሃል፡፡

በተጨማሪም ከቻልክ የአነባበብህንና የድምጽ

አወጣጥህን እንድታስተካክል የሚያግዝህ አስተማሪ

ቢኖርህ መልካም ነው፡፡ ይህን ሁሉ ማሳካት ምናልባትም

ተግዳሮት ያለው ሊሆንብህ ይችላል፡፡

ይሁን እንጂ ማሳካት ከቻልክ ግን ውድ በሆነ ውጤት

ትካሳለህ፡፡ ሁሉን ዓዋቂ የሆነው አላህ እንዲህ ይላል፡-

ÃI l`œ” ̈ Ų=Á‹ �`dD kØ}— ̈ Å §’‹¨<

S”ÑÉ ÃS^M& �’²=Á”U uÔ ¾T>W\ƒ”

U�S“” K’c< �Lp U”Ç ÁL†¨< S§’<”

Áue^M:: (አል-ኢስራእ፡ 9)

ምንም እንኳን በአንጡራው የዐረበኛ ቋንቋ የወረደው

ቁርኣን ለሁሉም ሥፍራና በሁሉም ዘመናት ሊኖሩና

ለሚኖሩ ሰዎች ተስማሚ ቢሆንም ወደሌሎች ቋንቋዎች

ተተርጉሞ መሠራጨቱም እውነት ነው፡፡

እንዲህ መሆኑ ደግሞ ቁርኣንን በሚገባ ለመረዳትና

በትንሹም ቢሆን በመደበኛነት ወደርሱ ለመቅረብ በጣም

ይጠቅማል፡፡ በተለይም ደግሞ ማለዳ ተነስቶ ማንበቡ

ከሁሉም ጊዜ የበለጠ ነው፡፡ ከዚሁ ጋር በሚመሳሰል

ሁኔታ አላህ በንጋት (ሱብሂ) ስግደት ቁርኣንን ማንበብ

ያለውን ፋይዳ ሲያስገነዝብ እንዲህ ይላል፡-

... ¾ÔI fLƒ. (SL�¡ƒ) ¾T>×ƃ ’¨<“::

(ኢስራእ፡ 78)

ባለው የማነሳሳት ብቃቱና በመንፈሳዊ ትሩፋቱ

ቁርኣን በእያንዳንዱ ሙስሊም ሕይወት ላይ

ማዕከላዊ ሥፍራ አለው፡፡ ቁርኣን የሕይወትን ሚዛን

ለመጠበቅ፣ ሰላምንና ደስታን ለማግኘት በመመሪያነት

ያገለግላል፡፡ የአላህ ነቢይ (ሰ.ዐ.ወ) ቁርኣንን

አስመልክተው እንዲህ ብለዋል፡፡

“ግልጽ የሆነ ብርሃን፣ የተዋጣለት መድሃኒት፣ አጥብቆ

ለያዘው መከላከያ (ጋሻ) ለሚከተለው (ለሚሠራበት)

ደግሞ መድህን ነው፡፡”

ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ሕይወታቸውን በቁርኣን በመምራት

ረገድ አርዓያችን ሲሆኑ ይህን ጉልህ ባሕሪያቸውንም

ባለቤታቸው አዒሻ (ረ.ዐ) ስትገልጽ

“ባሕሪያቸው ቁርኣን ነበር” ብላለች፡፡

ማንኛውም ፈላጊ በእውነት ፈላጊ አይደለም በተክክል ቁርኣን የሚፈልገውን ፍላጎቱን እንደሚያሟላለት እስካላወቀ ድረስ፡፡ —ሸይኽ መድየን

በመለኮታዊው መጸሐፍ ቀጥተኛውን መንገድ እየተመራን አሁን ደግሞ አራተኛ ወደሆነው የእምነት ማዕዘን አናመራ ፡፡ ይኸውም መለኮታዊ

መልዕከት ወደኛ ባመጡትና በአላህ (ሰ.ወ) በተላኩት መልዕክተኞች ማመን ነው፡፡

Page 71: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - zhic.aeኢስላም፣ ኢማን እና ኢሕሳን 3 አጠቃላይ እይታ 4 መግቢያ 6 የጉዞ መመሪያ 6 ለጉዞ

መለኮታዊው መንገድ፡-የአዲስ ሙስሊሞች ስርዓተ ትምህርት54

በመልዕክተኞች ማመን 11

የተከበሩ መልእክተኞች

በዚህ መንገድ ከእኛ በፊት ብዙዎች ተጉዘዋል፡፡ ከእነዚህ

ሕዝቦች መካከል ዋነኞቹ በአዛኙ አላህ ወደተለያዩ

ማሕበረሰቦችና ሕዝቦች የተላኩ ነፍሶች ናቸው፡፡ እነዚህ

መልእክተኞች ጉዞው የሚጠይቃቸውን ሁኔታዎች

ጠንቅቀው የሚያውቁና ሕዝቦችን ወደ እውነተኛው

ጐዳና ያመላከቱ ናቸው፡፡

በታሪክ ዘመናት ሁሉ እያንዳንዱ ሕዝብ የየራሱ ነቢያት

ተልከውለታል፡፡ አላህ አዛኝ በመሆኑና በፍትሃዊነቱ

ነቢያትንና መልእክተኞችን ሳይልክ ሕዝቦችን

አይቀጣም፡፡ እነዚያ መለኮታዊውን ምሪት ሳያገኙ የቀሩ

ይቅርታ የሚደረግላቸው ሲሆን መልእክቱን ያጣጣሉና

ያልተቀበሉ ደግሞ ተጠያቂነት ይሰፍርባቸዋል፡፡

አላህ እንዲህ ይላል፡-

KQ´x‹U G<K< SM¡}— ›L†¨<& SM¡}—

¨<U uS× Ñ>²? (c=Áe}vwK<) uS"ŸL†¨<

uƒ¡¡M Ãð[ÇM& �’`c<U ›ÃuÅK<U::

(ዩኑስ፡ 47)

በተጨማሪም እንዲህ ይላል SM°¡}—”U

�eŸU”M¡ É[e ¾U”k× ›ÃÅK”U::

(አል-ኢስራእ፡ 15) መልዕክተኞች ለየሕዝባቸው ሲላኩ

ሕዝቡ በሚናገረው ቋንቋ ነው መልእክቱን የሚያደርሱት፡

፡ እንደዚያም ሆኖ ሁሉም ተመሣሣይ መልዕክትን ነበር

ያደርሱ የነበረው፡፡ አላህ እንዲህ ይላል፡፡

u¾Q´u<U G<K< ¨<eØ #›LI” }Ѳ<&

×±ƒ”U ^l$ uTKƒ SM¡}—” u�`ÓØ

MŸ“M&...(አል-ነሕል፡ 36)

በተጨማሪም እንዲህ ይላል፡-

Ÿ›”} uòƒU �’J Ÿ�’@ K?L ›UL¡ ¾KU“

}Ѳ<˜ uTKƒ ¨Å`c< ¾U“¨`ÉKƒ u=§”

�”Ï ŸSM¡}— ›”É”U ›ML¡”U:: (አል-

አንቢያ�፡ 25)

ምንም እንኳን መልእክቱን ለሰዎች የማድረስ ኃላፊነትን

ቢሸከሙም መልእክተኞችም ያው እንደማንኛውም

ሰው ምግብን የሚበሉ፣ የሚተኙ፣ የሚያገቡ፣ ልጆችን

የሚወልዱ የሚያረጁና የሚሞቱ ናቸው፡፡ ይህ ሁሉ ሃቅ

በቀጣዩ የቁርኣን አንቀጽ እንዲህ ተብሎ ተጽፏል፡-

Ÿ›”} uòƒU ŸSM¡}™‹ �’c< u�`ÓØ

UÓw” ¾T>uK< uÑuÁ ዎ‹U ¾T>¤?Æ §’¨<

ue}k` ›ML¡”U&... (አል-ፉርቃን፡ 20)

ይሁን እንጂ እነዚህ የተመረጡ ሰዎች ታላቅ በሆነው

የመልእክተኛነት ተልዕኳቸው የተለዩ ባሕሪያት ነበሯቸው

እነርሱም

1 እውነተኝነት (ሲድቅ)

2 ታማኝነት (አማና)

3 ብልህነት

4 መልእክት አድራሽነት

እነርሱ በእርግጥም እውነተኞች በመሆናቸው የማይዋሹ፣ ታማኞች፣ ከኃጢአት የተጠበቁና ቃልኪዳናቸውን አክባሪዎች ነበሩ፡፡ ከፍተኛ ማስተዋል (ብልህነት) የነበራቸው ሲሆን ከበቀለኝነት ባሕሪም የጸዱ ነበሩ፡፡ በተጨማሪም የተላኩበትን መልእክት ሙሉ ለሙሉ ነበር ለሕዝባቸው የሚያደርሱት፡፡

በርካታ ነቢያትና መልዕክተኞች በቁርኣን ተጠቅሰዋል፡፡ ነቢይ ማለት ከፈጣሪው ወሕይ (ራዕይ) የሚወርድለት ማለት ሲሆን መልእክተኛ ግን የሚወርድለትን መልእክት ለሰዎች የማድረስ ኃላፊነት ያለበት ነው፡፡ በቁርኣን ሃያ አምስት የሚሆኑ መልዕክተኞች በስም የተጠቀሱ ሲሆን ሌሎች በርካታ መልዕክተኞች ግን በስም ሳይጠቀሱ ቀርተዋል፡፡ አላህ እንዲህ ይላል፡-

Page 72: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - zhic.aeኢስላም፣ ኢማን እና ኢሕሳን 3 አጠቃላይ እይታ 4 መግቢያ 6 የጉዞ መመሪያ 6 ለጉዞ

55ክፍል 2፡- በአላህ ማመን

Ÿ²=IU uòƒ u›”} Là u�`ÓØ ¾}

[¡“†¨<” SM¡}™‹ v”} LÃU ÁM}

[¡“†¨<” SM¡}™‹ (�”ÅL¡” L¡”I)::... (አል-ኒሳእ፡ 164)

እነዚህን ቀጥሎ ባለው ሰንጠረዥ ስማቸው የሠፈረውን ነቢያትና መልእክተኞች ማመንና ከአባታችን አደም (ዐ.ሰ) ጀምሮ እስከመጨረሻው መልእክተኛ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ድረስ በተከታታይ የተላኩ መሆናቸውን መቀበል ከእምነት ማዕዘናት አንዱ ነው፡፡

የነቢያት መደምደሚያ

ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ነብይነት በሚገነባ ቤት እንደሚመሰልና

እርሳቸው ደግሞ የመጨረሻው ጡብ እንደሆኑ ተናግረዋል፡

፡ እርሳቸው የነቢያት ሁሉ መደምደሚያ ናቸውና ኃያሉ

አላህ እንዲህ ይላል፡-

ሙሐመድ ከወንዶቻችሁ የአንድም ሰው አባት

አይደለም፤ ግን የአላህ መልክተኛና የነቢዮች

መደምደሚያ ነው፤… (አል-አሕዛብ፡ 40)

የመጨረሻና የነብያት ሁሉ መደምደሚያ እንደመሆናቸው

ነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) የተላኩት ለተወሰኑ

ሕዝቦች ሳይሆን ለመላው የሰው ዘር ነው፡፡ የአዛኞች ሁሉ

አዛኝ የሆነው አላህ እንዲህ ይላል፡-

አንተንም ለሰዎች ሁሉ በመላ፥ አብሳሪና አስፈራሪ

አድርገን ቢኾን እንጂ አላክንህም፤… (ሰበእ፡ 28)

እርሳቸው ይዘውት የመጡት መልእክት ከበፊታቸው

የነበሩትን እምነቶች በማሟላትና ቀደምት ሕግጋትን

በመሻር እስከ ዓለም ፍጻሜ ይቆያል፡፡የአላህ ነቢይ ቁርኣንን

ለሰዎች ከማስተማርና ወደ ቀናው ጐዳና ከመምራት

በተጨማሪ ከቀደምት የተሳሳቱ እምነቶቻቸውና መጥፎ

ልማዶቻቸው ያነጿቸው ነበር፡፡ ከዚህ በላይ ጥበብን

የነቢያትና የመልዕክተኞች

ስም ዝርዝር

ሙሐመድ(ሰ.ዐ.ወ)

ዒሳ(እየሱስ ዐ.ሰ)

የህያ(ዩሃንስ ዐ.ሰ)

ዘከሪያ(ዘካሪያስ ዐ.ሰ)

አል-የሰዕ(ኤልሳዕ ዐ.ሰ)

ኢሊያስ(ኤሊያስ ዐ.ሰ)

ዩኑስ(ዮናስ ዐ.ሰ)

ዙል ኪፍል(ሕዝቅኤል ዐ.ሰ)

አዩብ(እዮብ ዐ.ሰ)

ሱለይማን(ሰለሞን ዐ.ሰ)

ዳውድ(ዳዊት ዐ.ሰ)

ሙሳ(ሙሴ ዐ.ሰ)

ሀሩን(አሮን ዐ.ሰ)

ሹአይብ(ዐ.ሰ)

ዩሱፍ(ዮሴፍ ዐ.ሰ)

ያዕቁብ(ያዕቆብ ዐ.ሰ)

አስሃቅ(ኢሳቅ ዐ.ሰ)

ኢስማኢል(ኢስሃሜል ዐ.ሰ)

ኢብራሂም(አብረሃም ዐ.ሰ)

ሉጥ(ሎጥ ዐ.ሰ)

ሷሊህ(ዐ.ሰ)

ሁድ(ዐ.ሰ)

ኑህ(ኖሕ ዐ.ሰ)

ኢድሪስ(ሄኖክ ዐ.ሰ)

አደም(አዳም ዐ.ሰ)

Ÿ²=IU uòƒ u›”} Là u�`ÓØ ¾}[¡“†¨<” SM¡}™‹. v”} LÃU ÁM}[¡“†¨<”

SM¡}™‹. (�”ÅL¡” L¡”I)::... —(አል-ኒሳእ፡- 164)“

[ከላይ] በቁረኣን ላይ በስም የተጠቀሱት መልዕከተኞች ስም ዝርዝር

Page 73: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - zhic.aeኢስላም፣ ኢማን እና ኢሕሳን 3 አጠቃላይ እይታ 4 መግቢያ 6 የጉዞ መመሪያ 6 ለጉዞ

መለኮታዊው መንገድ፡-የአዲስ ሙስሊሞች ስርዓተ ትምህርት56

ያመጡ ሲሆን ሥነ-ምግባርን የተሟላ ይሆን ዘንድ

ታላቅ አርአያ በመሆን መንገዳቸውን መከተል ለሚሹ

ሁሉ አሳይተዋል፡፡ አላህ የነቢዩን (ሰ.ዐ.ወ) ያማረና

ለስላሳ ጸባይ በማየት እንዲህ ይላል፡-

ለናንተ፥ አላህንና የመጨረሻውን ቀን የሚከጅል ለኾነ

ሰው፥ አላህንም በብዙ ለሚያወሳ፥ በአላህ መልዕክተኛ

መልካም መከተል አላችሁ፤ (አል-አሕዛብ፡ 21)

ኃያሉ አላህ በተጨማሪም፡-

አንተም በታላቅ ጠባይ ላይ ነህ (አል _ ቀለም)

በማለት አሞግሷቸዋል፡፡

ነብያዊ መንገድ

ከፍጥረቱ ሁሉ አላህ ዘንድ በላጭ የሆኑት ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንደመሆናቸው በእርሳቸው ላይ የእዝነት ሰላምታውን እንዲህ በማለት አውርዶባቸዋል፡-

አላህና መላእክቱ በነቢዩ ላይ የአክብሮት እዝነትን ያወርዳሉ፤ እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በ ርሱ ላይ የአክብሮት እዝነትን አውርዱ፤ የማክበርንም ሰላምታ ሰላም በሉ፡፡ (አል-አሕዛብ፡ 56)

እንግዲህ የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ያመጡትን ሁሉ ከመቀበልና ከማረጋገጥ በተጨማሪ እውነተኛ ሙስሊሞች በእርሳቸው ላይ እዝነትንና ሰላምታን ማውረድ ይጠበቅባቸዋል ማለት ነው፡፡

ሙስሊሞች ነቢዩን (ሰ.ዐ.ወ) ከመውደዳቸው በተጨማሪ አኗኗራቸውንና የሕይወት ፈለጋቸውን ይኮርጃሉ፡፡ የመጀመሪያዎቹ ሙስሊም ትውልዶች ከዚህ አንፃር ከነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ከራሳቸው ብዙ ነገሮችን መቅሰም በመቻላቸው ፈለጋቸውን በመከተል በኩል ብዙ ርቀት ሄደዋል፡፡ የእርሳቸው ባልደረቦች እያንዳንዷን የተናገሯትን ነገርና የፈጸሟትን ድርጊት ያን ያክል ጥቅም የሌላት ብትመስልም እንኳን በጥንቃቄ በማስታወስ ይመዘግቧት ነበር፡፡ እንዲሁም እርሳቸው ያጸደቁትንና

ውድቅ ያደረጉትን ሁሉ ጉዳዩ ቢገለጽላቸውም ባይገለጽላቸውም ይይዙት ነበር፡፡ እነዚህን ሁሉ ነገሮች ነው እንግዲህ ሐዲስ ብለን የምንጠራቸውና የእርሳቸውን ፈለግ መከተል እንችል ዘንድ ከትውልድ ወደ ትውልድ እያስተላለፍን የምንጠብቃቸው፡፡

ከጊዜ በኋላ ደግሞ የእነዚህን ሐዲሶች ትክክለኛነት በማበጠር የሚያረጋግጥ የምሁራን (ኡለማዕ) ክፍል ተነሣ፡፡ በዚህ ጥረት ምክንያትም የነብዩን (ሰ.ዐ.ወ) የሕይወት እንቅስቃሴ የሚመለከቱ በርካታ የሐዲስ ጥራዞች ሊዘጋጁ በቅተዋል፡፡ ከእነዚህ ታዋቂ የሐዲስ መዛግብት መካከል የኢማም ማሊክ፣ የኢማም ቡኻሪ፣ የኢማም ሙስሊምና የኢማም አት-ቲርሚዚ ስብስቦች ይገኙበታል፡፡

ቁርኣን አላህ ለባሮቹ ያወረደው ቀጥተኛ መመሪያ ሲሆን የነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ሱንና ደግሞ እነዚህን መመሪያዎች በዕለት ተዕለት አኗኗራችን ተግባራዊ የምናደርግበት ተምሳሌት ነው፡፡ ለምሳሌ አላህ በቁርኣን እንድንሰግድ አዞናል፡፡ ይሁን እንጂ በነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ሕያው ተምሳሌት ነው የስግደታችንን ዝርዝር ጉዳይ የምናውቀው፡፡ቁርኣን፣ የነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ሱንና ኢጅማዕ ከሚባለው የታላላቅ ባልደረቦቻቸው አቋምና ማነጻጸር (ቂያስ) ከተሰኘው ምሁራዊ ጥረት ጋር በአንድ ላይ ተደምረው ኢሰላማዊውን ሕገ ሸሪዓ ያስገኛሉ፡፡

የነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) የሕይወት ታሪክ (ሲራ)

ሐዲስ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) የተናገሯቸውንና ያደረጓቸውን ነገሮች የሚዘግብልን ቢሆንም ጠቅላላውን የእርሳቸውን የሕይወት ታሪክ በተሟላ መልኩ ለማወቅ ግን አያስችለንም፡፡ ሙሉውን የእርሳቸውን ታሪክ ለማግኘት የሕይወት ገድላቸውን (ሲራቸውን) ማንበብ ግድ ይለናል፡፡ በየዘመናቱ የተነሱ የተለያዩ ጸሐፍት የነቢዩን (ሰ.ዐ.ወ) ታሪክ በተለያዩ ቋንቋዎች አዘጋጅተዋል፡፡ ብዙዎች በአፃፃፍ የተነቃቁበትና ታዋቂ የሆነው ግን የኢብን ሂሻም ታሪክ (ሲራ) ነው፡፡ ይህ መጽሐፍ በነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ውብ ሕይወት ላይ የብርሃን ጸዳል ያፈስበታል፡፡ እንዲሁም ለሙስሊሙ ሕዝብ (ኡማ)

(ሙሐመድ ሆይ!) ለዓለማትም እዝነት አድርገን እንጂ አልላክንህም፡፡ —(አል-አንቢያእ ፡ 47)“

Page 74: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - zhic.aeኢስላም፣ ኢማን እና ኢሕሳን 3 አጠቃላይ እይታ 4 መግቢያ 6 የጉዞ መመሪያ 6 ለጉዞ

57ክፍል 2፡- በአላህ ማመን

የሚጠቅሙ በርካታ ትምህርቶችን ይዟል፡፡

ነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) በመካ ከተማ ከተከበረ የዘር ሃረግ በ570 ድ.ል ተወለዱ፡፡ አባታቸው ገና ሳይወለዱ እናታቸው ደግሞ ገና የስድስት ዓመት ልጅ እያሉ ነበር የሞቱባቸው፡፡ እናም ገና ከልጅነታቸው ጀምሮ ወላጅ አጥ (የቲም) ሆነው በመጀመሪያ ከአያታቸው አብዱል ሙጦሊብ ቀጥለውም ከአጐታቸው አቡ ጣሊብ ጋር አድገዋል፡፡

ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) መካከለኛ ቁመት፣ የሚያምር መልክ፣ ልከኛ ሰውነትና ሰፊ ትከሻ ነበራቸው፡፡ ዓይኖቻቸው ትላልቅና ረዣዥም ሽፋሽት ያላቸው ሲሆን ፀጉራቸውና ጺማቸው ደግሞ ጥቁርና

ጥቅጥቅ ያለ ዞማ ነበር፡፡ በፊታቸው ላይ ቀለል ያለ ብርሃን ይፈስሳል፡፡ ቀጥ ያለው አፍንጫቸው ከተስተካከለው የፊታቸው ቅርጽና ከሚያምሩት ከናፍሮቻቸው ጋር እጅግ ውበትን አላብሷቸዋል፡፡

ሕዝቦቻቸው ቀድሞም በክቡር ባሕሪያቸውና በእውነተኛነታቸው ያውቋቸዋል፡፡ በዚህም የተነሣ ‘አል አሚን’ (ታማኙ) በሚል ስያሜ ነበር ነቢይ ሳይሆኑ በፊት ይጠሩ የነበረው፡፡ እንዲሁም አደራን በመጠበቅ፣ ምክርን በመለገስና በብልህነታቸውም መልካም ሥም ነበራቸው፡፡

ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ሁልጊዜም ሰውን በአክብሮት የሚቀበሉና ፈገግታ የማይለያቸው ነበሩ፡፡ ለቤተሰቦቻቸው ጥሩ፣ እንደአባዋራ ሚስቶቻቸውን በመልካም ሁኔታ የሚይዙ፣ እንዲሁም ቤት ውስጥ በተለያዩ ሥራዎች የሚያግዙ ነበሩ፡፡ ባልደረቦቻቸውን እንዲህ በማለት አስተምረዋቸዋል፡- “ከእናንተ በላጩ ለቤተሰቡ ጥሩ የሆነው ነው እኔ ለቤተሰቤ ጥሩ ነኝ፡፡” እንደ አባት ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ልጆችን የሚወዱና ከእነርሱ ጋር መጫወት የሚያስደስታቸው ሲሆን ኡማማ የተባለችውን የልጃቸውን ልጅ ሲሰግዱ ትከሻቸው ላይ ያስቀምጧት ነበር፡፡ የሰዎች ችግር ያሳስባቸዋል ያሳዝናቸዋልም፡፡ በአንድ ወቅት በመንገድ ላይ አንድ ልጅ የሚጫወትበት ወፍ (በቀቀን) ሞቶበት በጣም ተክዞ ተመልክተውት ከልጁ ጋር አብረው በመቀመጥ አጽናንተውታል፡፡

ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ሰዎችን ወደ ኢስላም መጥራት ሲጀምሩ መልእክታቸውን ካስተባበሉ ሰዎች ስድብ፣ ዘለፋ፣ ድብደባና ሌላም በርካታ ክፉ ነገር ደርሶባቸዋል፡፡ ይሁን እንጂ በዚያ የትግላቸው ወቅት በመታገሥና ጠላቶቻቸውን በጥሩ ሥነ-ምግባር በመቅረብ ነበር መልእክታቸውን ያደርሱ የነበረው፡፡ በመጨረሻም መካን ለቅቀው ወደ መዲና እንዲሰደዱ ከአላህ ፈቃድ አገኙ፡፡ ይሁን እንጂ ከብዙ ዓመት የስደት ሕይወት በኋላ ወደ መካ በድል ሲመለሱ በጠላቶቻቸው ላይ የበቀል ዱላ አላወረዱባቸውም፡፡ ከዚያ ይልቅ ርህራሄና ችሮታ በተሞላበት መንፈስ ያዟቸው እንጂ፡፡መዲና ውስጥ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) በየጊዜው የሚያድገውን

ከፊሉንም ነቢያት በከፊሉ ላይ በእርግጥ አስበልጠናል፤ —(አል-ኢስራእ ፡- 55)“

[ከላይ] መዲና ውስጥ የሚገኘው የነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) መስጂድ

Page 75: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - zhic.aeኢስላም፣ ኢማን እና ኢሕሳን 3 አጠቃላይ እይታ 4 መግቢያ 6 የጉዞ መመሪያ 6 ለጉዞ

መለኮታዊው መንገድ፡-የአዲስ ሙስሊሞች ስርዓተ ትምህርት58

ማሕበረሰብ መምራት ቀጠሉ፡፡ በሂደቱም የመዲና ሙስሊም ማሕበረሰቦች (አንሷር በመባል ይታወቃሉ) ያግዟቸው ነበር፡፡ አንሷሮች ነቢዩን (ሰ.ዐ.ወ) በፍቅር እጆቻቸውን ዘርግተው ነበር የተቀበሏቸው፡፡

ከዚያ በኋላ ስኬት የተሞላባቸው ጊዜያትን አሳልፈው በስልሳ ሶስት ዓመታቸው ይህችን ዓለም ተሰናበቱ፡፡ ከኋላቸው ቁርኣንንና ፈለገ ሕይወታቸውን (ሱናቸውን) እንዲሁም በተከታዮቻቸው ዘንድ ለዝንት ዓለም የማይረሳ የሆነ ፍቅራቸውን ትተው አልፈዋል፡፡

ከዚያ ሁሉ በኋላ ሙስሊሙን ማኅበረሰብ የመምራቱ ኃላፊነት በተወዳጁ ጓደኛቸውና አማታቸው አቡበከር አስ-ሲዲቅ (ረ.ዐ) ትከሻ ላይ አረፈ፡፡ አቡበከር (ረ.ዐ) የነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ባለቤት የአዒሻ (ረ.ዐ) አባት ናቸው፡፡

አቡበከር (ረ.ዐ) በጣም አላህን የሚፈሩና ከመጀመሪያዎቹ ሙስሊሞች አንዱ ነበሩ፡፡ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ከሞቱ በኋላ በነበሩት ጥቂት ዓመታት ሙስሊሙን ማሕበረሰብ ከመሩ በኋላ ኡመር ኢብን አል-ኸጣብ (ረ.ዐ) ተኳቸው፡፡ እርሳቸውን ደግሞ ዑስማን (ረ.ዐ) ከዚያም ዓሊ (ረ.ዐ) የኸሊፋነቱን ቦታ በተከታታይ በመያዝ ሙስሊሞችን መርተዋል፡፡ እነዚህ አራቱ የነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) የረዥም ጊዜ ወዳጆችና አላህን የሚፈሩ እንዲሁም በትክክል የተመሩ ኸሊፋዎች ነበሩ፡፡ እነርሱ አመራር ላይ በነበሩባቸው ዘመናት ሙስሊሙ ማሕበረሰብ ቁጥሩ እጅግ የበዛ ሲሆን በርካታ ሃገራትም ተከፍተዋል፡፡ በሂደቱም ሌሎች ሕዝቦችን ወደ ኢስላም የመጥራቱ ተልዕኮ በስፋት ቀጥሏል፡፡

ነብዩን (ሰ.ዐ.ወ) መውደድ

እምነት (ኢማን) ከሚረጋገጥባቸው ምልክቶች አንዱ ነቢዩን (ሰ.ዐ.ወ) ከልብ መውደድ ነው፡፡ ነቢዩን (ሰ.ዐ.ወ) ማፍቀር ማለት ልባችንን ከርሳቸው ጋር ማስተሳሰርና በመጪው ዓለም ከእርሳቸው ጋር የምንሆንበትን ጊዜ መናፈቅ ነው፡፡ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡-

«ማንም አላመነም እኔን ከራሱ፣ ከቤተሰቡ፣ ከሰው ልጆች በሙሉ አብልጦ ያልወደደ» የነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ባልደረቦች እርሳቸውን ከልባቸው ይወዷቸው የነበሩ ሲሆን ይህንኑ ፍቅራቸውንም ይገልጹላቸው ነበር፡፡ ሰውባን (ረ.ዐ) ነቢዩን (ሰ.ዐ.ወ) በጣም

ከመውደዱ የተነሣ ከርሳቸው መለየት አይሆንለትም ነበር፡፡ አንድ ዕለት ነቢዩን (ሰ.ዐ.ወ) ሲያገኛቸው ፊቱ ለምን እንደገረጣ ሲጠይቁት እንዲህ አለ፡-

“የአላህ መልእክተኛ ሆይ! እኔ ከባድም ሆነ ቀላል ሕመም የለብኝም፡፡ ሆኖም ግን ከእርስዎ ከተለየሁና ሳላይዎት ከቆየሁ መልሼ እስካገኝዎ ድረስ ናፍቆቴ ይበረታል፡፡ ከዚያም የመጪውን ዓለም ሁኔታ አስባለሁ፡፡ እዚያ የማላይዎት ስለሚመስለኝ እፈራለሁ፡፡ ምክንያቱም እርስዎ የሚሆኑት ከታላላቆቹ ነቢያት ጋር ነው፡፡ ተሳክቶልኝ ጀነት ከገባሁ የእኔ ደረጃ ከርስዎ

በአላህም ልታምኑ ፣ በመልዕክተኛውም (ልታምኑ) ፣ ልትረዱትም ፣ ልታከብሩትም ፣ (አላህን) በጧትና ከቀትር በኋላ ልታወድሱትም (ላክነው) ፡፡ —(አል-ፈትሕ ፡- 9 )

[ከላይ] ሐጃጆች ብርሃን ተራራ የሚገኘውንና ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ለመጀመሪያ ጊዜ ከጅብሪል (ዐ.ሰ) ጋር የተገናኙበትንና ቀርኣን የወረደበትን "ሒራእ" የተሰኘ ዋሻ ሲወጡ፡፡

Page 76: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - zhic.aeኢስላም፣ ኢማን እና ኢሕሳን 3 አጠቃላይ እይታ 4 መግቢያ 6 የጉዞ መመሪያ 6 ለጉዞ

59ክፍል 2፡- በአላህ ማመን

ጋር አይስተካከልም፡፡ ጀሃነም የምገባ ከሆነ ደግሞ ጭራሽ ለሁልጊዜም አላይዎትም!”

ሰውባን (ረ.ዐ) ይህን ተናግሮ ብዙም ሳይቆይ ነበር አላህ ቀጣዩን የቁርኣን አንቀጽ ያወረደው፡-አላህንና መልእክተኛውን የሚታዘዝ ሰው እነዚህ ከእነዚያ አላህ በእነርሱ ላይ ከለገሰላቸው ከነቢያት፣ ከፃድቃንም፣ ከሰማእታትም ከመልካሞቹ ጋር ይሆናሉ፡፡ የእነዚያ ጓደኝነት ምንኛ አማረ! (አን-ኒሳእ፡ 69)

ነቢዩን (ሰ.ዐ.ወ) ካወቅካቸው ትወዳቸዋለህ፡፡ እርሳቸውን ለማወቅ ደግሞ የሕይወት ታሪካቸውን (ሲራቸውን) በማንበብ፣ ውብ የሆነውን አኗኗራቸውን አካላዊ ቅርፃቸውን፣ ክቡር ባሕሪያቶቻቸውን በዝርዝር ማጥናት ያስፈልጋል፡፡

ከሁሉም በላይ ደግሞ የእርሳቸውን ባሕሪያት ከሚያንጸባርቁና አላህን ፈሪ ከሆኑ ሰዎች ጋር መወዳጀት ተገቢ ነው፡፡

ከነብያት ድካ በኋላ ደግሞ አሁን ስድስተኛ የእምነት መሰረት ወደሆነው በፍጻሜው ሰአት የሚከሰቱትን ክስተቶች ወደሚያሳየን መሰረት

እናመራለን፡፡

ከጎሳችሁ የሆነ ችግራችሁ በእርሱ ላይ ጽኑ የሆነ ፣ በእናንተ (እምነት) ላይ የሚጓጓ፣ በምእመናን (ላይ) ርኅሩኅ አዛኝ የኾነ መልዕክተኛ በእርግጥ መጣላችሁ ፡፡ —(አት-ተውባህ ፡- 128)

Page 77: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - zhic.aeኢስላም፣ ኢማን እና ኢሕሳን 3 አጠቃላይ እይታ 4 መግቢያ 6 የጉዞ መመሪያ 6 ለጉዞ

መለኮታዊው መንገድ፡-የአዲስ ሙስሊሞች ስርዓተ ትምህርት60

በመጨረሻው ቀን ማመን12

የዓለም ፍጻሜ

በምድር ላይ ያሉ ፍጡራን በአጠቃላይ ከዚህ በፊት

አይተውትና ሰምተውት የማያውቁት አስደንጋጭና አሰቃቂ

የሆነ ተከታታይ መከራ ወደፊት ይከሰታል፡፡ በዚህ ጊዜ

በሰዎች መካከል የነበረው ጥብቅ ትስስር ይቋረጣል፡፡ ብክለት

ይስፋፋል፡፡ ምድር በእንቅጥቃጤ ትርዳለች፡፡ የጊዜውን

መቃረብ ለማመልከትም ፀሐይ ካለወትሮዋ ከምዕራብ በኩል

ትወጣለች፡፡

ልጆችም በወላጆቻቸው ላይ ያምጻሉ፡፡ ባሪያ ሴት እመቤቷን

ትወልዳለች፡፡ እውቀት በሙሉ ከሰው ልጆች አእምሮ

የሚጠፋ ሲሆን ድንቁርና ይበልጥ ያይላል፡፡ ሕገ-ወጥ

ተግባራት በግልጽ ይስፋፋሉ፡፡ ትክክል የሆነው ነገር የተሳሳተ፤

ስህተት የሆነው ነገር ደግሞ ትክክል ሆኖ ይታያል፡፡

በዚህ ጊዜ እነዚያ ትክክለኛውንና ቀጥተኛውን የኢስላም

መንገድ የያዙ ክስተቶች በነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)

ቀድመው የተተነበዩ የመጨረሻው ዘመን የተወሰኑ

ምልክቶች እንደሆኑ ያረጋግጣሉ፡፡

በዚያ ወቅት የጐመን ዘር ፍሬ የምታህል እምነት ያለው

በመለኮታዊው ነፋስ ሲጠፋ ከሃዲያን ብቻ ምድር ላይ

ይቀራሉ፡፡ በዚህ ሁሉ መካከልም ትርምስምሱና ምስቅልቅሉ

ይበልጥ ይበረታል፡፡ ከዚያም ከኢስራፊል (ዐ.ሰ) የቀንድ

እንቢልታ የሚወጣው ጩኸት በምድር ላይ ያሉ በሙሉ

እንዲሞቱ ከማድረጉ ባሻገር የፍርዱ ቀን መቃረቡን

ያውጃል፡፡

Page 78: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - zhic.aeኢስላም፣ ኢማን እና ኢሕሳን 3 አጠቃላይ እይታ 4 መግቢያ 6 የጉዞ መመሪያ 6 ለጉዞ

61ክፍል 2፡- በአላህ ማመን

ወደ መቃብር የሚደረገው ጉዞ

ጊዜው ከመድረሱ በፊት ሁሉም ሰው ይህች ዓለም

የሁልጊዜም መኖሪያ አለመሆኗን በመገንዘብ መዘጋጀት

ይኖርበታል፡፡ ይህች ምድራዊ ሕይወት ሌላ ሳትሆን

ለመጪው ዓለም የሚሆን ስንቅ የሚቋጠርባትና ከሞት

በኋላ ለሚጠብቀን ሕይወት መድህን የሚሆን መልካም

ሥራ የሚሠራባት ናት፡፡

እነዚያ ድቅድቅ በሆነው የቀብር ጨለማ የሚገቡ አስፈሪውን

አጣብቂኝ ይጋፈጡታል፡፡ አፈር በነርሱ ላይ ሲጫንባቸው ያለ

በቂ ስንቅ መጓዛቸውን ይገነዘባሉ፡፡ ክብራቸውና ምድራዊ ሃብት

ንብረታቸው ከእነርሱ ጋር አብረው አይሄዱም፡፡ አብሯቸው

የሚጓዝ ነገር ካለ እምነታቸውና መልካም ሥራቸው ብቻ

ነው፡፡ከዚያ በኋላ ነኪር እና ሙንከር (ዐ.ሰ) የተባሉ

ሁለት መላእክት ወደነርሱ ይቀርቡና ስለ ፈጣሪያቸው፣ ስለ

ሃይማኖታቸውና ስለ ነቢያቸው ይጠይቋቸዋል፡፡

ባሳለፉት የእምነት ሕይወትና በአምልኮታቸው የተነሣ

አማኞች የሆኑት የሚቀርቡላቸውን ጥያቄዎች በአግባቡ

ለመመለስና ፈተናዎቹንም ለማለፍ የሚያበቋቸውን

መልሶች ከወዲሁ ይታጠቃሉ፡፡በዚህም የተነሳ ቀብሮቻቸው

በብርሃን የሚሞሉ ከመሆናቸው ባሻገር ከጀነት

በሚመጣላቸው ማራኪ መዓዛና ጨፌ ላይ ይንፈላሰሳሉ፡፡

ነገር ግን እነዚያ በምድራዊ ሕይወታቸው የማያምኑና

ድንበር አላፊዎች የነበሩ የመቃብር ውስጥ ጥያቄዎችን

ፈጽሞ መመለስ አይችሉም፡፡ በዚህም ሳቢያ ቀብሮቻቸው

የእሳት ጉድጓዶች ይሆናሉ፡፡ የመጨረሻው ሰዓት

እስኪመጣም እዚያው ውስጥ ይቀጣሉ፡፡

የመጨረሻው ምርመራ

ከመጀመሪያው የእንቢልታ ድምፅ በኋላ ኢስራፊል

ለሁለተኛ ጊዜ በእንቢልታው ድምፅ ያሰማል፡፡ በዚያ

ጊዜ ሙታን በሙሉ ዳግም ሕይወት ይዘራሉ፡፡ በጭንቀትና

በፍራቻ ተውጠው ሁሉም በአንድ ላይ ተሰባስበው

የመጨረሻውን ምርመራ ይጠባበቃሉ፡፡ ኃያሉ ፈጣሪ ይህን

ቀን“ልቦች ተሸባሪዎች ናቸው፡፡ ዓይኖቻቸው ተዋራጆች

(አቀርቃሪዎች) ናቸው፡፡” (አን-ናዚዓት፡ 8-9)

በማለት እንዲሁም “ልጆችን ሸበቶዎች የሚያደርገው

ቀን” (አል-ሙዝዘምሚል ፡ 17) በማለት ገልጾታል፡፡

በዚህ ወቅት እያንዳንዱ ሰው በራሱ ጉዳይ የሚያዝበት

ጊዜ በመሆኑ ስለ ወዳጆቹና ስለቤተሰቡ የሚያስብበት

ቅንጣት ጊዜ አይኖርም፡፡ ፀሐይ በጣም ትቀርባለች፡፡

ሙቀቷም እነዚያ በነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) አንደበት

በአላህ ጥላ ሥር ይሆናሉ ተብሎ ከተነገረላቸው ሰባት

ሰዎች (ቡድኖች) በስተቀር በሌሎች ላይ እጅግ የበረታ

ይሆናል፡፡እነዚህ ጥላ በሌለበት ሙቀት በአላህ ጥላ ሥር

የሚሆኑ ሰባት ሰዎች፡-ፍትሃዊ መሪ፣ አላህን በማምለክ

ያደገ ወጣት፣ ልቦናው ከመስጂድ የተቆራኘ ሰው፣

ለአላህ ሲሉ የሚዋደዱ ሁለት ሰዎች፣ አላህን እፈራለሁ

በማለት ከአማላይ ሴት የራቀ ሰው፣ ምጽዋትን በስውር

(በድብቅ) የሚሰጥ ሰው፣ ብቻውን ሲሆን አላህን

በማስታወስ ፊቱ በእንባ የሚታጠብ ሰው ናቸው፡፡

በመጨረሻም እያንዳንዱ ግለሰብ ስለ ሠራው ሥራ

በግል ለመጠየቅ አላህ ፊት ይቀርባል፡፡ በዚያ ቀን ረቂብ

እና ዐቲድ (ዐ.ሰ) በተባሉ መላእክት ሲመዘገብ

የቆየው የሥራ መዝገብ ይፋ ይሆናል፡፡ ምስክሮች

ይጠራሉ፡፡ በዕለቱ ምንም የሚሰወር ነገር የለም፡፡

እውነተኛው ፈራጅ (አላህ) እንዲህ በማለት ይናገራል፡-

በነሱ ላይ ምላሶቻቸው፣ እጆቻቸውና እግሮቻቸውም

ይሠሩት በነበሩት ነገር በሚመሰክሩባቸው ቀን (አን-ኑር፡ 24)

ከዚያም የእያንዳንዱ ሰው መልካምም ይሁን እኩይ

ድርጊት ይመዘናል፡፡ አንድ ሰው በሕይወቱ ውስጥ

የፈጸማቸው ድርጊቶች የደስታው ወይም የሃዘኑ

በዚያ ቀን ልቦች ተሸባሪዊች ናቸው ፡፡ ዓይኖቻቸው ተዋራጆች (አቀርቃሪዎች) ናቸው ፡፡ —(አን-ናዚዓት ፡- 8-9)“

Page 79: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - zhic.aeኢስላም፣ ኢማን እና ኢሕሳን 3 አጠቃላይ እይታ 4 መግቢያ 6 የጉዞ መመሪያ 6 ለጉዞ

መለኮታዊው መንገድ፡-የአዲስ ሙስሊሞች ስርዓተ ትምህርት62

ምንጭ ይሆናሉ፡፡ የምርመራ ባለቤት የሆነው አላህ

እንዲህ ይላል፡-

በመልካም ሥራ የመጣ ሰው ለርሱ ከርስዋ የበለጠ

ምንዳ አለው፡፡ እነርሱም በዚያ ቀን ከድንጋጤ ጸጥተኞች

ናቸው፡፡ በመጥፎም የመጡ ሰዎች ፊቶቻቸው በእሳት

ውስጥ ይደፋሉ፤ ትሠሩት የነበራችሁትን እንጂ

አትመነዱም (ይባላሉ)፡፡ (አን-ነምል፡ 89-90)

ከዚያ በኋላ ሲራጥ የተባለና እንደ ምላጭ የሰላ ድልድይ

በጀሃነም ላይ ይዘረጋል፡፡ እነዚያ የእምነት ባለቤቶችና

የታዘዙትን ሥራ ለመፈጸም ይጣደፉ የነበሩት ሰዎች

ድልድዩን በብርሃን ፍጥነት ያቋርጣሉ፡፡ ሌሎች ሰዎች ግን

በብዙ ትግልና መከራ የሚያልፉ ሲሆን የተወሰኑት ደግሞ

ተንሸራትተው ጀሃነም ላይ ይወድቃሉ፡፡

ምንዳ (ደሞወዝ)

እነዚያ መልካምን የሠሩ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ቃል

የተገባላቸው ምንጭ (ሃውድ) አጠገብ ሆነው ሰላምታ

ያቀርቡላቸዋል፡፡ በተከበሩት እጆቻቸውም ከዚያ እየቀዱ

አማኝ ለሆኑት ተከታዮቻቸው ይሰጧቸዋል፡፡ ይህ በራሱ

ከርሳቸው ጋር ለነበራቸው ልዩ ግንኙነት ምልክት

ነው፡፡ ከዚያ ውሃ የጠጣ ማንኛውም ሰው ፈጽሞ ጥም

አያገኘውም፡፡ከዚያም እጅግ በጣም አዛኝ የሆነው አላህ

ነቢያትና ከአማኞች መካከልም ጻድቃን የሆኑ ሌሎች

ሰዎችን እንዲያማልዱ ይፈቅድላቸዋል፡፡ የማማለድ

ፈቃድ ከሚሰጣቸው መካከል የመጀመሪያው ነቢዩ

ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ይሆናሉ፡፡ የእርሳቸው ምልጃ

በእርግጥም በርካቶችን ከጀሃነም እሳት ያድናቸዋል፡፡

ረጅም ከባድና አስቸጋሪ ከሆነው ጉዞ በኋላ እያንዳንዱ

ሰው የመጨረሻ ማረፊያ ስፍራው ላይ ይደርሳል፡፡

እነዚያ ቀናውን መንገድ የተከተሉት ዘላለማዊ የሆነውን

የጀነት ሕይወት ይታደላሉ፡፡ በአንጻሩ ደግሞ እነዚያ

ሃቁን ያልተቀበሉና እኩይ ድርጊቶችን ሲፈጽሙ የኖሩ

ለዘላለማዊው የጀሃነም ቅጣት ይዳረጋሉ፡፡አላህ (ሱ.ወ)

እነዚህን ሁለት እጣፈንታዎች ሲያነጻጽር እንዲህ

ብሏል፡-

“የዚያች ጥንቁቆቹ ተስፋ የተሰጧት ገነት ምስል

በውስጧ ሺታው ከማይለውጥ ውሃ ወንዞች ጣዕሙ

ከማይለወጥ ወተትም ወንዞች ለጠጪዎች ሁሉ ጣፋጭ

ከኾነች የወይን ጠጅም ወንዞች ከተነጠረ ማርም

ወንዞች አልሉባት፡፡ ለነሱም በውስጧ ከፍሬዎች ሁሉ

(በያይነቱ) ከጌታቸው ምሕረትም አልላቸው (በዚህች

ገነት ውስጥ ዘውታሪ የኾነ ሰው) እርሱ በእሳት ውስጥ

ዘውታሪ እንደኾነ ሰው ሞቃትንም ውሃ እንደተጋቱ

አንጀቶቻቸውንም ወዲያውኑ እንደ ቆራረጠው ነውን?

(አይደለም)፡፡” (ሙሐመድ፡ 15)

ይህም ቢሆን፥ አላህ (ሱ.ወ) በቸርነቱና እጅግ በጣም

አዛኝ በሆነው ባሕሪው ጀሀነም ውስጥ ይቀጡ ከነበሩት

መካከል ጥቂት እምነት በልቦቻቸው ያላቸውን ሰዎች

በማውጣት ከሌሎች ጋር በጸጋይቱ ጀነት እንዲኖሩ

ያደርጋል፡፡

ለመጨረሻው ቀን መዘጋጀትነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) በሕይወት በነበሩበት ጊዜ ተከታዮቻቸው እንዴት አድርገው ለመጨረሻው የምርመራ ቀን እንደሚዘጋጁ ሲያስተምሩ እንዲህ ብለዋል፡-

‹‹በዚህ ዓለም ባይተዋር ወይም መንገደኛ ሁን፡፡ ራስህንም ከቀብር ባለቤቶች አንዱ እንደሆንክ አዳርገህ አስብ››35 ከዚህም በተጨማሪ ተከታዮቻቸው ሁልጊዜ ‘ጥፍጥናን ቆራጭ’ ብለው የጠሩትን ሞትን እንዲያስታውሱ ሂሳብ ሳያገኛቸው በፊት ራሳቸው ሥራቸውን እንዲተሳሰቡ መክረዋል፡፡ እንዲህም ብለዋል፡-

‹‹እጅግ ብልጦች ማለት እነዚያ ከወዲሁ ሞትን የሚያስታውሱና ከሞት በኋላ ላለው ሕይወት ራሳቸውን ከወዲሁ የሚያዘጋጁ ናቸው፡፡ እነርሱም በዚህች ምድር ክብር የሚቀዳጁ ከሞት በኋላ ባለው ዓለም የክብር ስፍራን የሚጐናጸፉ ናቸው፡፡››36

የትንሳኤ ቀን ሲቀርብ አንድ ሰው በእጁ ላይ የተምር ፍሬ ብትኖረው ክስተቱ ሳይከሰት በፊት በእጁ ላይ ያለቸውን ፍሬ ከቻለ ይትከላት —ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ)

Page 80: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - zhic.aeኢስላም፣ ኢማን እና ኢሕሳን 3 አጠቃላይ እይታ 4 መግቢያ 6 የጉዞ መመሪያ 6 ለጉዞ

63ክፍል 2፡- በአላህ ማመን

ሞትን ማስታወስ ሥራዎቻችንን መለስ ብለን እንድንገመግም ከመርዳቱ በተጨማሪ በዚህች ምድር ላይ ያለን ሕይወት አጭር መሆኗን እንድናስብ ያደርገናል፡፡ ሞትን ማሰባችን በንስሃ (ተውባ) ወደ አላህ እንድንመለስ ከሞት በኋላ ላለው ዘላለማዊ ሃገር ስንቅ እንድናዘጋጅ ያበረታታናል፡፡አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ በማለት ያስጠነቅቃል፡-

ለመሰብሰቢያው ቀን የሚሰበስብባችሁን ቀን(አስታውሱ)፤ ይህ የመጎዳዳት (መግለጫ) ቀን ነው፤ በአላህም የሚያምን ሰው መልካምንም የሚሠራ ከርሱ ኃጢአቶቹን ይሰርይለታል፤ (ይፍቅለታል)፤ ከሥሮቻቸውም ወንዞች የሚፈሱባቸውን ገነቶች በውስጣቸው ዘለዓለም ዘውታሪዎች ሲኾኑ

ያገባዋል፤ ይህ ታላቅ ማግኘት ነው፡፡ እነዚያም የካዱና በአንቀጾቻችን ያስተባበሉ እነዚያ በውስጡ ዘውታሪዎች ሲኾኑ የእሳት ጓዶች ናቸው፤ መመለሻቸውም ከፋ! ከመከራም (ማንንም) አይነካም በአላህ ፈቃድ ቢኾን እንጅ፤ በአላህም የሚያምን ሰው ልቡን (ለትዕግስት) ይመራዋል፤ አላህም ነገሩን ሁሉ ዐዋቂ ነው፡፡ (አት-ተጋቡን፡ 9-11)ነቢዩ ሙሐመድም (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡-

‹‹በዚህች ዓለም ምን መሥራት አለብኝ? የኔና የዚህች ምድር ምሳሌ ልክ በበጋ ሙቀት እንደሚጋልብና አንዲት የሚያርፉት ዛፍ እንደሚያገኝ ጋላቢ ነው፡፡ ጋላቢው በዚህች ዛፍ ጥላ ስር ለጥቂት ጊዜ አርፎ ከዚያ በኋላ ዛፏን ትቷት እንደሚሄድ ነው፡፡››37

ለቅን ባሪያዎቼ ዓይን አይቶት ፣ ጆሮ ሰምቶት እንዲሁም በልቦና ውልብ ብሎ የማያውቀውን ነገር አዘጋጅቼላቸዋለሁ፡፡ —ሐዲስ አል-ቁድስ ¬“

ለመጨረሻው ቀን ስንዘጋጅ የምንፈተነው ትዕዛዝ በመጠበቅና ክልከላን በማክበር ብቻ ሳይሆን በመከራና በድሎታችንም ጭምር ነው፡፡ ለእነዚህ

ፈተናዎች የሚኖረን አጸፋ የእምነታችን ክፍል ሲሆን ከእምነት ማዕዘናትም አንዱ ነው፡፡

Page 81: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - zhic.aeኢስላም፣ ኢማን እና ኢሕሳን 3 አጠቃላይ እይታ 4 መግቢያ 6 የጉዞ መመሪያ 6 ለጉዞ

መለኮታዊው መንገድ፡-የአዲስ ሙስሊሞች ስርዓተ ትምህርት64

በእጣፋንታ (ቀዷና ቀደር) ማመን13

በመንገዱ ላይ ያሉ ክስተቶችይህ የምንጓዝበት መንገድ ቀላል ሊሆን ይችላል፡፡ ነገር ግን እያንዳንዳችን በተለያዩ ጊዜያት ለመከራና ችግሮች ልንጋለጥ እንችላለን፡፡ ይህ አጋጣሚ ደግሞ የጥንካሬያችን መሞከሪያ ነው፡፡

የሕይወት ተሞክሮዎች በውጫዊ ገጽታቸው የአጋጣሚ ተግባራት መስለው ሊታዩ ይችላሉ፡፡ ይሁን እንጂ በእምነት ዓይን ስንቃኛቸው እነዚህን ግልጽና ድብቅ የሆኑ ክስተቶች የላካቸው የመለኮታዊ ጥበብ ባለቤት የሆነው አንዱ ጌታ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ አላህ ሁሉን አዋቂና ነገሮቻችንም ባማረ ሁኔታ የሚከውን ነው፡፡አላህ እንዲህ ይላል፡-

በምድርም በነፍሶቻችሁም መከራ (ማንንም) አትነካም ሳንፈጥራት በፊት በመጽሐፉ የተመዘገበች ብትኾን እንጅ፤ ይህ በአላህ ላይ ገር ነው፡፡ (አል-ሐዲድ 22)

የአላህ ውሳኔእነዚያ የመለኮታዊውን ኃይል ምሉእነት ጠንቅቀው የሚረዱ ቁሳዊም ይሁን የማይዳሰስ ክስተት ወደ ሕልውና የሚመጣው በአላህ መሻትና የመፍጠር ኃይል እንዲሁም ፍጹማዊ በሆነው እውቀቱ መሆኑን ያረጋግጣሉ፡፡

አላህ ስለራሱ እንዲህ ይላል፡-

አላህ የሚሻውን ይፈጥራል፤ አንዳችን በሻ ጊዜ ለርሱ ኹን ይለዋል ወዲያውኑም ይኾናል፡፡ (አለ-ዒምራን፡ 47)

ለፈጠራቸው እያንዳንዱ ፍጥረታት ድርሻ ለክቷል፤ ወስኗልም፡፡ ይህም በሕይወት የሚቆዩበትን ጊዜ፣ የሚያስፈልጋቸውን የሲሳይ መጠን እንዲሁም የሚያጋጥሟቸውን ጥሩና መጥፎ ክስተቶች ያጠቃልላል፡፡ አላህ እንዲህ ይላል፡-(እርሱ) ያ... ነገሩንም ሁሉ የፈጠረና በትክክልም ያዘጋጀው ነው፡፡ (አል-ፉርቃን፡ 2)

ስለዚህ ማንኛውም ሰው ላይላዩን ሲታይ ጥሩ ወይም መጥፎ፥ ጠቃሚ ወይም ጎጂ ሁኔታ ሊያጋጥመው ይችላል፡፡ ይሁን እንጂ ውስጡን ግን በሚገባ የሚያውቀው የጥበብ ባለቤት የሆነው አላህ ብቻ ነው፡፡ አላህ በቁርኣኑ እንዲህ ይላል፡-

ከሚሠራው ሁሉ አይጠየቅም፤ እነርሱ (ፍጥረቶቹ) ግን ይጠየቃሉ፡፡ (አል-አንቢያእ፡ 23)

ለመለኮታዊው ውሳኔ የሚኖረን አጸፋ

ምንም እንኳን አማኞች በመንገዱ ላይ ጠንክረው እየታገሉና እየለፉ ቢሆንም እምነታቸውን የሚያኖሩት ግን በፈጣሪያቸው ላይ ነው፡፡ መለኮታዊውን ውሳኔ በራሳቸው ሊቀለብሱ እንዲሁም ከነገራቶች ፍፃሜ ሊያመልጡ እንደማይችሉ ጠንቅቀው ያውቃሉ፡፡

ምክንያቱም ሁሉም ነገር በአላህ ቁጥጥር ሥር ነውና፡፡ አማኞች የመከራ ወጀቦች ከአላህ በኩል ካልሆነ በስተቀር በማንም ኃይልና ችሎታ ሊከሰቱ እንደማይችሉ እያንዳንዱ ግለሰብም በመንገዱ ላይ እንደሚፈተን ያምናሉ፡፡ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡-

‹‹ትልቅ ምንዳ የሚገኘው ከትልቅ ተሞክሮ ጋር ነው፡፡ አላህ አንድን ሕዝብ ሲወደው በአንዳች ነገር ይሞክራቸዋል (ይፈትናቸዋል)፡፡ ማንኛውም ይህን ተሞክሮ በጸጋ የሚቀበሉ ከሆነ በርግጥ ታላቁን ደስታ አሸንፈዋል፡፡ያፈገፈገም ቁጣን ያገኛል››38

አላህ እንዲህ ብሏል፡-ሰዎቹ አምነናል በማለታቸው ብቻ፥ እነሱ ሳይፈተኑ የሚትተዉ መኾናቸውን ጠረጠሩን? (አል-ዐንከቡት፡ 2) እንዲህም ብሏል፡-ከፍርሃትና ከረኃብም በጥቂት ነገር፥ ከገንዘቦችና ከነፍሶችም ከፍራፍሬዎችም በመቀነስ በእርግጥ እንሞክራችኋለን፤ ታጋሾችንም (በገነት) አብስር፡፡ (አል-በቀራህ፡ 155)

Page 82: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - zhic.aeኢስላም፣ ኢማን እና ኢሕሳን 3 አጠቃላይ እይታ 4 መግቢያ 6 የጉዞ መመሪያ 6 ለጉዞ

65ክፍል 2፡- በአላህ ማመን

የመለኮታዊው ውሳኔ (ቀደር) ምስጢር ያለው ማንኛውንም ነገር በጸጋ ከመቀበል ላይ ነው፡፡ ከቀደምት ምሁራን አንዱ እንደተናገሩት፡- መለኮታዊውን ውሳኔ በጸጋ የሚቀበል ሰው ልክ አፍቃሪ በፍቅረኛው ድርጊት እንደሚደሰት ብጤ ነው ይህም ጣፋጭ ወይም መራራ ቢሆን ለውጥ አያመጣም፡፡

አማኝ የሆነ ሰው ምንም ነገር ቢያጋጥመው በሰላትና በዱዓ (ጸሎት) ላይ በመጽናት አላህን ለማስደሰት ይጥራል፡፡ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ሌሎችን ትዕግስትና እርጋታ ይኖራቸው ዘንድ መክረዋል፡፡ በተለይ እርሳቸው ራሳቸው ከባድ በሆኑ መከራዎች ውስጥ ይህን ባሕሪ በተግባር አሳይተዋል፡፡ ውብ የሆነው መልካም ባሕሪያቸው የሚያጋጥሙን መከራዎች ምንም ያህል ቢሆኑ የጽናት ተምሳሌት ሆኖ ያገለግለናል፡፡ ከነቢያት ይበልጥ ማንም አልተፈተነም አልተሞከረም፡፡

የነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ባልደረቦች “የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! ከሕዝቦች መካከል ብዙ ፈተናዎች (ተሞክሮዎችን) የተቀበለ ማነው?” በማለት ጠየቋቸው፡፡ እሳቸውም ሲመልሱ ‹‹ነቢያት ናቸው፡፡ ከዚያ ለነርሱ የቀረቡ ሰዎች ናቸው፡፡ ከዚያም ለእነርሱ የቀረቡት ናቸው፡፡ የአንድ ባሪያ ፈተና በኢማኑ መጠን ነው፡፡ ባሪያው በዚህ ዓለም ምንም ኃጢአት የሌለው ሆኖ ትቶ እስከሚሄድ ድረስ መፈተኑ (መሞከሩ) የሚቀጥል ነው››39 አሉ፡፡

እነዚያ ለአላህ ታዛዦች የሆኑ በምቾታቸው ወቅት አመስጋኝ ሊሆኑ ይገባል፡፡ በአንጻሩ ደግሞ ችግሮች በሚያጋጥሟቸው ጊዜ በትዕግስት በትህትና የሚቀበሉ መሆን አለባቸው፡፡ ይህም የሆነው ጉዳያቸውን ከሚያውቅና ከሚያስወግድላቸው ፈጣሪያቸው የበለጠ ማንም እንደሌለ ስለሚገነዘቡ ነው፡፡

በምድርም በነፍሶቻችሁም መከራ (ማንንም) አትነካም ሳንፈጥራት በፊት በመጽሐፍ የተመዘገበች ብትኾን እንጅ፤

ይህ በአላህ ላይ ገር ነው፡፡ —(አል-ሐዲድ፡- 22)

እምነትን (ኢማንን) እና ማዕዘናቱን እንዲሁም ተግባራዊ የማድረጉን ሂደት ከተገነዘብን ከዚህ ቀጥለን ደግሞ ወደ ቀጣዩ የጉዞ እርከን

በመተላለፍ ከፍተኛ የሆነ መንፈሳዊ ውበትንና ምልአትን የሚያላብስ የሆነውን ማሳመርን (ኢህሳንን) እንዳስሳለን፡፡

Page 83: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - zhic.aeኢስላም፣ ኢማን እና ኢሕሳን 3 አጠቃላይ እይታ 4 መግቢያ 6 የጉዞ መመሪያ 6 ለጉዞ
Page 84: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - zhic.aeኢስላም፣ ኢማን እና ኢሕሳን 3 አጠቃላይ እይታ 4 መግቢያ 6 የጉዞ መመሪያ 6 ለጉዞ

ኢሕሳን(ማሳመር)

‹‹ኢሕሳን ማለት አላህን እንደምትመለከተው አድርገህ ማምለክ ማለት ነው፡፡ አንተ ባታየው እንኳ እርሱ ያይሃልና፡፡›› የጂብሪል (ዐ.ሰ) ሐዲስ

Page 85: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - zhic.aeኢስላም፣ ኢማን እና ኢሕሳን 3 አጠቃላይ እይታ 4 መግቢያ 6 የጉዞ መመሪያ 6 ለጉዞ

መለኮታዊው መንገድ፡-የአዲስ ሙስሊሞች ስርዓተ ትምህርት68

አጠቃላይ እይታ14

መንፈሳዊው የማሳመር (ኢህሳን) መንገድ

እስካሁን እንደተማርነው፥ አንደበት እስኪመሰክርና አካላት እስኪያረጋግጡ ድረስ መንገዱ ረዥም ሲሆን እርሱም ኢስላም መሆኑን አውቀናል፡፡ ወደፊት የሚደረገው ጉዞ የሚሰምረው ውጫዊው ሁኔታ ከውስጣዊው እምነት ጋር ሲጣጣም ብቻ ነው፡፡ ይህም ኢማን ይባላል፡፡ ኢሕሳን ደግሞ ልቦና በብርሃን ሲሞላና ግድየለሽነት ሲወገድ በግልጽ የሚንጸባረቅ እውነታ ነው፡፡

የኛ ታላቅ ተምሳሌት የሆኑት ነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ሁለት የኢሕሳን ደረጃዎችን በጂብሪል (ዐ.ሰ) ሐዲስ አመላክተዋል፡፡ ከሁለቱ ደረጃዎች የላቀው እንደተመልካች ሆኖ በመንገዱ ላይ መጓዝ ነው፡፡

‹‹ልክ አንተ እንደምታየው አድርገህ እንዲል ሐዲሱ፡፡›› አንድ ሰው ይህን ለማግኘት የማይችል ከሆነ ሌላው ቢቀር የትም ቦታ ቢሆን አብሮት የሚሆነውን ሕሊናውን ማዳመጥ ይኖርበታል፡፡ ይኸውም ‹‹አንተ ባታየውም እርሱ ያይሃልና›› የሚለው የኢህሳን ደረጃ ነው፡፡ የዚህ ብርሃናማ መንገድ አቅጣጫ እውቀት፣ ፍቅርና መንፈሳዊ ለውጥ ማድረግ መሆኑን ያጤኗል፡፡

የእውቀትና የፍቅር መንገድ

ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡-‹‹ልዕልና የተገባው

ጌታ እንዲህ ብሏል፡- በእኔ ላይ አጋር በሚያደርግ ላይ

ጦርነት አውጃለሁ፡፡ ባሪያዬ ወደኔ ይበልጥ ተወዳጅ ሆኖ

አይቃረብም እኔ ግዴታ ባደረግኩበት ሥራዎች ቢሆን

እንጂ፡፡ ባሪያዬ እኔ እስክወደው ድረስ በፍላጎት በሚሠሩ

ተግባራት ወደኔ ይቃረባል፡፡ እኔ ከወደድኩት የሚሰማበት

ጆሮዎቹ፣ የሚያይበት ዓይኖቹ፣ የሚዳስስበት መዳፎቹ፣

የሚራመድበት እግሮቹ እሆንለታለሁ፡፡ ከጠየቀኝ

የጠየቀውን በርግጥ እሰጠዋለሁ፡፡ በእኔ መጠበቅን

ከፈለገ በርግጥ እጠብቀዋለሁ፡፡››40

ይህ የእውቀት መንገድ ነው፡፡ ምክንያቱም ማንኛውም

ሰው አላህ ‹‹ግዴታ ያደረገበትን ነገሮች›› ማወቅ

ያለበት በመሆኑ ተግባራዊ ሊያደርገው ይችላል፡፡ ይህም

የፍቅር መንገድ ነው፡፡ ምክንያቱም በፈቃደኝነት የሚሠሩ

ሥራዎች ከግዴታነት መንፈስ ውጪ በፍቅር የሚሠሩ

በመሆናቸው ነው፡፡

እንዲሁም ይህ በራሱ የመንፈሳዊ ለውጥ መንገድ ነው፡፡

ምክንያቱም አላህ እንዲህ ብሏል፡-

‹‹እኔ ከወደድኩት የሚሰማበት ጆሮዎች፣ የሚያይበት

ዓይኖች፣ የሚይዝበት እጆች፣ የሚራመድበት እግሮች

እሆንለታለሁ፡፡›› እነዚህ በአጠቃላይ በቀጥታ

የሚተርጐሙ ሳይሆኑ የአላህን አንድነት (ተውሒድን)

Page 86: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - zhic.aeኢስላም፣ ኢማን እና ኢሕሳን 3 አጠቃላይ እይታ 4 መግቢያ 6 የጉዞ መመሪያ 6 ለጉዞ

ክፍል 3፡- ኢሕሳን 69

የሚያንጸባርቁ ተለዋጭ ዘይቤያዊ አነጋገር (Meta-phor) መገለጫዎች ናቸው፡፡ይህን መሰሉን የመለኮታዊ

አንድነት (ተውሂድ) ደረጃ ለማግኘት ግዴታ የተደረጉ

ተግባራትን ለመከወን የሚደረግ ቋሚ ጥረት እንደ

ቅድመ ሁኔታ ይቆጠራል፡፡ እነዚህ የመታዘዝ ተግባራት

መልካም ሥርዓት (አደብ) እና ልባዊነት (ኢኽላስ)

ከተላበሱ ግለሰቡ ሁነኛ መንፈሳዊ ሥፍራንና ልዩ የሆነ

የፍቅር ደረጃን ሊጐናጸፍ ይችላል፡፡ አላህ እንዲህ ይላል፡-

በላቸው፡- አላህን የምትወዱ እንደኾናችሁ ተከተሉኝ፤

አላህ ይወዳችኋልና፡፡ (አለ-ዒምራን፡ 31)

ልብ (ቀልብ) አላህን እንድትፈራና ልክ እርሱን

እንደምትመለከት ለመሆን መቻሏ ጥገኛ የሆነው

በንጽሕናዋ ላይ ነው፡፡ አላህ እንዲህ ብሏል፡-

እነሆ ዓይኖች አይታወሩም ግን እነዚያ በደረቶች ውስጥ

ያሉት ልቦች ይታወራሉ፡፡ (አል-ሐጅ፡ 46)

ልክ የአንድ ሰው እይታ ባይተዋር የሆነ ነገር ዓይን ውስጥ

በመግባቱ ምክንያት ሊታወክ እንደሚችለው ሁሉ የልብም

መንፈሳዊ እይታም በትንሽ ነገር ይታወካል፡፡ ይህ ትንሽ

ነገር ውጫዊ ወይም ውስጣዊ የሆኑ እኩይ ተግባር ሊሆን

ይችላል፡፡ ነገር ግን መንፈሳዊው ልብ የጠራና እርሱን

ከሚያሳውሩ ነገሮች የተጠበቀ ከሆነ ማሳመር (ኢሕሳን)

በአንድ ሰው መንፈሳዊ ጉዞ እውን ይሆናል፡፡

በሰውነት ውስጥ ቁራጭ ሥጋ አለች፡፡ ይህች ሥጋ ከተስተካከለች ሌላው የሰውነት አካል ይስተካከላል፡፡ ይህች ሥጋ ከተበላሸች ሌላው የሰውነት አካል ይበላሻል፡፡ አዋጅ ይህች ቁራጭ ሥጋ ልብ ነች፡፡ —ነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)

Page 87: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - zhic.aeኢስላም፣ ኢማን እና ኢሕሳን 3 አጠቃላይ እይታ 4 መግቢያ 6 የጉዞ መመሪያ 6 ለጉዞ

መለኮታዊው መንገድ፡-የአዲስ ሙስሊሞች ስርዓተ ትምህርት70

ልብና የሰውነት ክፍሎች15

ውስጣዊ ሁኔታችን ሲስተካከል ውጫዊው ማንነታችን

እንደሚያምር ሁሉ ውጫዊውም ሁኔታችን ውስጣዊውን

ማንነታችንን (ልባችንን) የእርግጠኝነት ብርሃን

ሊያላብሰው ወይም ጨለማን ሊያወርሰው ይችላል፡፡

ዓይኖች፣ ጆሮዎች፣ ምላስ፣ ሆድ፣ መገጣጠሚያ አካላትና

ሐፍረተ ሥጋዎች ባጠቃላይ ከልቦና ጋር ቀጥተኛ የሆነ

ግንኙነት አላቸው፡፡ እነዚህ አካላት በአግባቡ ከተመሩና

ለተፈጠሩበት ዓላማ ብቻ የሚያገለግሉ ከሆኑ የልቦና

ንጽሕናንና መንፈሳዊ ብርሃንን ይጨምራሉ፡፡

ነገር ግን በመለኮታዊው ሕግ የማይመሩና አግባብነት

በሌለው ሁኔታ ግልጋሎት ላይ የሚውሉ ከሆነ በልብ

ውስጥ ጽልመትን ይጥላሉ፡፡ የአንድ ሰው አካላት መጥፎ

ድርጊት ከመፈጸማቸው ውጪ ልብን ለእንዲህ ዓይነቱ

ሁኔታ የሚዳርገው ሌላ ምክንያት የለም፡፡ አላህ እንዲህ

ይላል፡-

በልቦቻቸው ላይ ይሠሩት የነበሩት (ኃጢአት)

ደገደገባቸው፡፡ (አል-ሙጠፊፊን፡ 14)

የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡-

‹‹ አንድ አማኝ ሰው ኃጢአት ሲፈጽም በእርግጥ ልቡ

በጥቁር ነጥብ ያጠላል፡፡››41 አላህ የሰጠን አካላቶቻችን

ልክ እኛ ዘንድ በአደራ መልክ እንደተቀመጡ ንብረቶች

ናቸው፡፡ እነርሱ ወደ መጪው ዓለም ለመመለስ

የምናደርገውን ጉዞ ለማሳለጥ የተሰጡን ስጦታዎች

ናቸው፡፡ አላህ እንዲህ ይላል፡-

ገንዘብም ልጆችም በማይጠቅሙበት ቀን፤ ወደ አላህ

በንጹሕ ልብ የመጣ ሰው ቢኾን እንጅ፡፡

(አሽ-ሹዐራእ፡ 88-89)

እነዚህን ስጦታዎች ሰጪውን ላለመታዘዝ መጠቀም

የምስጋና ቢስነት አብይ መገለጫ ነው፡፡ እንዲሁም

ማንኛውም ምስጋናን ማሳየት የሚፈልግ ሰው የግዴታ

የሰውነት አካላቱን መጠበቅና አላህ ለሚፈልጋቸው

ተግባራት ብቻ የማዋል ግዴታ አልለበት፡፡

1 ዓይኖች

ማንኛውም ሰው በዓይኖቹ የአላህን አስደናቂ ትዕይንቶች፣ ልዕልናውንና ኃያልነቱን የሚገልጹ ምልክቶችን፣ እውቀትንና ሌሎች ግርማውን የሚያሳዩ ባሕሪያቱን ማየት ይችላል፡፡ ዓይኖች ለልብና ለምናብ የመጀመሪያዎቹ መስኮቶች ናቸው፡፡ ስለዚህ በዓይኖች ዝሙትንና የተከለከሉ ነገሮችን ከመመልከት መቆጠብ ግዴታ ነው፡፡

2 ጆሮዎች

በጆሮዎች አንድ ተጓዥ መንገደኛ የአላህን ንግግሮችና የአላህን ነቢይ (ሰ.ዐ.ወ) ሐዲሶች እንዲሁም የልሂቃንን ጥበብና እውቀት ያዳምጣል፡፡ ጆሮዎችም እንዲሁ ሌሎቹ ወደ ልብ የሚያደርሱ መስኮቶች ናቸው፡፡ ስለዚህ ጆሮዎች ጸያፍ ነገሮችን፣ ሐሜትን፣ አሉባልታ ወሬዎችንና ሌሎች የተከለከሉ ነገሮችን እንዳያዳምጡ መከላከል ግዴታ ነው፡፡

3 ምላስ

በምላስ የአላህ ስም ይወሳበታል፡፡ በርሱም ከርሱ ጋር እንነጋገርበታለን፡፡ ምላስ መልካም ምክሮችን፣ እውቀትንና መመሪያዎችን ያስተላልፋል፡፡ ስለዚህ ምላስን ከሃሰት፣ ከሐሜት፣ ከስድብና ዘለፋ፣ ከማጭበርበር ከመራገም፣ ከክርክር፣ ከጉራ፣ ቃል ኪዳን ከማፍረስ መጠበቅ ግዴታ ነው፡፡

4 ሆድ

በሆድ በኩል ማናቸውም የተወሰዱ ነገሮች ወደ ሰውነት ገብተው ልቦናን ያበላሻሉ፡፡ አላህ በርግጥ ንጹህና መልካም ምግቦችን በመመገብ አካላችንን እንድንገነባ ጸጋውን ለግሶናል፡፡ ይህን ካደረግን ጉዟችን ቀላል ይሆንልናል፡፡ ሆድን ካልተፈቀዱና ክልክል ከሆኑ ምግቦችና መጠጦች መጠበቅ ግዴታ ነው፡፡ ማሳመርን

Page 88: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - zhic.aeኢስላም፣ ኢማን እና ኢሕሳን 3 አጠቃላይ እይታ 4 መግቢያ 6 የጉዞ መመሪያ 6 ለጉዞ

ክፍል 3፡- ኢሕሳን 71

(ኢሕሳን) የሚፈልግ ሰው በመጠኑ መመገብ አለበት፡፡ ጥጋብ ልብን ያደርቃል፤ አእምሮን ያላሽቃል፤ አካላትን ያደክማል፣ እንዲሁም ለጤናማ እንቅስቃሴዎች እንቅፋት ይሆናል፡፡

5 እጅ

በእጆች ማንኛውም ሰው ይሠራል፣ ይቀበላል፣ ይጽፋል፣ ይረዳል፣ የሰው ልጆችን ያገለግላል፡፡ የእጆች ተግባራት ልቦና ላይ ተጽዕኖ ይፈጥራሉ፡፡ ስለዚህ እጆች ሰዎችን እንዳይጨቁኑ፣ ያልተፈቀዱ የገቢ ምንጮችን እንዳይወስዱ በአጠቃላይ ክልክል የሆኑ ነገሮችን እንዳይነኩ በተለይ በብዕር ስም እንዳያጠፉና የሃሰት ወሬን እንዳያሰራጩ መጠበቅ ግዴታ ነው፡፡

6 እግሮች

እግሮች እንቅስቃሴዎችን ቀላል ያደርጋሉ፡፡ ወደ በጐ ሥፍራዎች፣ ሥራ፣ መስጊድ ለመጓዝ ሶላት ላይ ለመቆምና ትልቁን የሐጅ ሥነ ሥርአት ለመፈጸም ይረዱናል፡፡ እግሮቻችን የሚያደርጉት ጉዞ በልባችን ላይ

ተጽዕኖ ያሳድራል፡፡ ስለሆነም እግሮቻችን ክልክል ወደሆኑ ሥፍራዎች እንዳይወስዱን መጠንቀቅ ያስፈልጋል፡፡

7 ሐፍረት ስጋዎች

ሐፍረተ ስጋዎች ጋብቻን ቅዱስ በማድረግ ለጋራ ውህደት ትልቅ ሚና ይጫወታሉ፡፡ እነዚህን የአካል ክፍሎቻችንን የምንጠቀምባቸው ሁኔታዎችና ምክንያቶች በልባችን ላይ ተጽዕኖ ያሳድራሉ፡፡ ስለሆነም ሃፍረተ ስጋዎቻችንን በመጠበቅ በሕጋዊ (ሃላል) ሁኔታ ብቻ መጠቀም ግዴታችን ነው፡፡

አላህ እንዲህ ይላል፡-

ለምእመናን ንገራቸው፡- ዓይናቸውን (ያልተፈቀደን ከማየት) ይከልከሉ፣ ብልቶቻቸውንም ይጠብቁ፤ ይህ ለነሱ የተሻለ ነው፤ አላህ በሚሠሩት ሁሉ ውስጥ ዐዋቂ ነው፡፡ ለምእመናትም ንገራቸው ዓይናቸውን ይከልክሉ፤ ብልቶቻቸውንም ይጠብቁ፣ ጌጣቸውንም ከርሷ ግልጽ ከኾነው በስተቀር አይግለጡ (አን-ኑር፡ 30-31)

እይታ ከዲያቢሎስ ቀስቶች መካከል መርዛማው ቀስት ነው፡፡ አላህን በመፍራት የተወ ሰው አላህ በልቦናው የሚያጣጥመው የሆነን የኢማን ጥፍጥና ይተካለታል፡፡ —ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ)

Page 89: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - zhic.aeኢስላም፣ ኢማን እና ኢሕሳን 3 አጠቃላይ እይታ 4 መግቢያ 6 የጉዞ መመሪያ 6 ለጉዞ

መለኮታዊው መንገድ፡-የአዲስ ሙስሊሞች ስርዓተ ትምህርት72

የልብ ባሕሪያት16

አላህ እንዲህ ይላል፡-

የኃጢአትንም ግልጹንም ድብቁንም ተውዉ፤

(አል-አንዓም፡120)

በኢስላማዊው መንገድ ስንጓዝ በመለኮታዊው ሕግ

አካላትን ብቻ ሳይሆን ልብንም መቆጣጠር አለብን፡፡

ግባችን ወደሆነው ማሳመር (ኢህሳን) ላይ ለመድረስ

ቀላል የሚሆነው ልቦና ከሚያስጠይቁ ባሕሪያት ተጠብቆ

በሚያስመሰግኑ ባህሪያት የታጀበ እንደሆነ ብቻ ነው፡፡

ጉዞው በስኬት እንዲደመደም የልብ ሁኔታ መስተካከል

አለበት፡፡

መሪያችንና አርአያችን የሆኑት የአላህ መልዕክተኛ

(ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፤

«በሰውነት ውስጥ አንዲት ቁራጭ ስጋ አለች፡፡ ይህች

ቁራጭ ስጋ ከተስተካከለች ሰውነትም ይስተካከላል ይህች

ቁራጭ ስጋ ከተበላሸች ሰውነትም ይበላሻል፡፡ አዋጅ ይህች

ቁራጭ ስጋ ልብ ነች፡፡» 42

ልብ በተፈጥሮ ከምንም ነገር የጸዳ ቢሆንም ቅሉ

የሚከተሉት የቆሸሹ ባህሪያት ሲበክሉት ቀስ በቀስና

በሂደት እየቆሸሸ ይመጣል፡፡ በመጨረሻም ስስት፣

ንዴት፣ ሃሰት፣ ቅናት፣ ተንኮል፣ ንፉግነት፣ ልታይ ባይነት፣

ግብዝነት፣ ኩራት፣ ምቀኝነት፣ ራስ ወዳድነትና አፍቅሮተ

ንዋይ ይወርሩታል፡፡

በዚህ ምክንያት ማሳመር (ኢሕሳን) የሚፈልጉ

ራሳቸውን ለመጠበቅ እነዚህን አሳፋሪ ባሕሪያት ማወቅ

ግድ ይላቸዋል፡፡ በዚህ መሠረታዊ እውቀት መገኘት ሳቢያ

Page 90: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - zhic.aeኢስላም፣ ኢማን እና ኢሕሳን 3 አጠቃላይ እይታ 4 መግቢያ 6 የጉዞ መመሪያ 6 ለጉዞ

ክፍል 3፡- ኢሕሳን 73

እነዚህ ጸያፍ ባህሪያት በቀላሉ ተለይተው ይወጣሉ፡፡

በምትካቸው መልካም ከሆኑት ባሕሪያት ለምሳሌ የአላህን

አንድነት ማወቅ (ተውሂድ)፣ ቅንነት፣ ጸጸት፣ የአላህ

ፍቅርና ናፍቆት፣ ፍራቻ፣ ተስፋ፣ ቁጥብነት፣ መመካት፣

ቻይነት፣ ትዕግስት፣ አመስጋኝነት፣ እውነተኛነትና

መብቃቃት ይተካሉ፡፡ ልብ በእነዚህ ባሕሪያት ደጋግሞ

መጐብኘት አለበት፤ በውስጡ ለሁሌም እስኪቀመጡ

ድረስ፡፡ እንዲህ ዓይነቱ ልብ ነው እንግዲህ በመልካም

ባሕሪያት ያሸበረቀና የምንፈጽማቸው ተግባራት ትርጉም

ያላቸው እንዲሆኑ የሚያስችል ጠንካራ ልብ፡፡

የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡-

«አላህ አካላችሁን ወይም ገጽታችሁን አይመለከትም

ነገር ግን ልቦቻችሁን ያያል፡፡"43

መመለስ (ተውባህ)

ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- «በእርግጥ አላህ

በሁሉም ነገር ላይ መልካምነትን አስቀምጧል፡፡»44

በልቦናው ውስጥ ዘወትር እምነቱ ከፍ ከፍ የሚልና

የሚሻሻል የሆነ ሙስሊም ትግሉ ተጠናቋል የሚል ስሜት

ፈጽሞ የለውም፡፡ ምክንያቱም ማሳመር (ኢህሳን)

በሁሉም ነገር ውስጥ ያስፈልጋልና፡፡

ለለውጥ የሚነሳሳ ጸጸት ልቦና ውስጥ ሲሰርጽ

መንገደኛውን በማነቃቃት የመንፈሳዊውን ትግል ጅማሬ

ወለል አድርጐ ያሳየዋል፡፡

አላህ እንዲህ ይላል፡-

እነዚያም በኛ መንገድ የታገሉ መንገዳችንን በእርግጥ

እንመራቸዋለን፤ አላህም በእርግጥ ከበጎ ሠሪዎች ጋር

ነው (አል-ዐንከቡት፡ 69)

እነዚህ መንገዶች ሁሉ ወደ ማሳመር (ኢሕሳን)

የሚያቃርቡ ሁኔታዎች ሲሆኑ መንገደኛው አላህን

እንዲታዘዝ ይመሩታል፡፡ መንፈሳዊው ጉዞም የሚጀምረው

ተጓዡ በእውነተኛነትና በጽናት ወደፈጣሪው ፊቱን

ሲመልስ ነው፡፡ ይህ መመለስ ተውባህ (ጸጸት)ተብሎ

ይጠራል፡፡ ይህ መንገድ ርቆ የነበረ ልቦና ወደ አላህ

ይበልጥ የሚቃረብበት ጐዳና ነው፡፡አላህ (ሱ.ወ)

እንዲህ ይላል፡-

ምእመናኖች ሆይ! ትድኑ ዘንድ ሁላችሁም ወደ አላህ

(በመመለስ) ተጸጸቱ፡፡ (አን-ኑር ፡31)

ከድብቁም ሆነ ከግልጹም ኃጢአት በመጸጸት ወደ አላህ

መቃረብ ግዴታ ነው፡፡

መመለስ (ተውባህ) ተቀባይነት ያለው ይሆን ዘንድ

አራት መስፈርቶች አሉ፡- እነዚህ መስፈርቶች አራቱ

«መ»ዎች በመባል ይታወቃሉ፡፡ እነርሱም

1 መጸጸት

2 መቆጠብ

3 መወሰን

4 መመለስ ናቸው፡፡

የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፤ «ጸጸት ተውባህ ነው፡፡»45

ይህ ማለት አንዳች ዓይነት ስሕተት ከፈፀሙ በኋላ በእውነት ተጸጽቶ መመለስ ዳግመኛ ወደ መሰል ተግባር ላለመመለስ ለመወሰን ይረዳል፡፡ ኃጢአቱ የሌላን ሰው መብት አብሮ ያቀላቀለ ከሆነ ንስሃው ተቀባይነት ያገኝ ዘንድ መብቱ የግዴታ ለባለቤቱ መመለስ አለበት፡፡

እነዚህ አራቱ «መ»ዎች ከተሟሉ ማንኛውም ተጓዥ ወደ ፊት መቀጠልና መጓዝ አለበት፡፡ የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል

«ከኃጢአቱ በመጸጸት የተመለሰ ሰው ልክ ሃጢአት እንደሌለበት ሰው ነው፡፡»46

በተሳሳተው መንገድ ላይ ከሄዳችሁ ተመለሱ፡፡ ከተጸጸታችሁ ትንሽ ጠብቁ፡፡ ካላወቃችሁ ጠይቁ ፡፡ከተናደዳችሁ ንዴታችሁን ተቆጣጠሩ ፡፡ —ሐሰን አል-በስሪይ

Page 91: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - zhic.aeኢስላም፣ ኢማን እና ኢሕሳን 3 አጠቃላይ እይታ 4 መግቢያ 6 የጉዞ መመሪያ 6 ለጉዞ

መለኮታዊው መንገድ፡-የአዲስ ሙስሊሞች ስርዓተ ትምህርት74

በተደጋጋሚ ድንበር ማለፍና ኃጢአት ውስጥ መውደቅ ግለሰቡ ራሱን በኃጢአት ሙሉ ለሙሉ የተዘፈቀ አድርጎ እንዲቆጥርና በማንኛውም ነገር ላይ ተስፋ የለሽ እንዲሆን ያደርገዋል፡፡ አላህ ከዚህ መሰሉ ምግባር እንርቅ ዘንድ ሲያስጠነቅቀን እንዲህ ብሏል፡-

እናንተ በነፍሶቻችሁ ላይ ድንበር ያለፋችሁ ባሮቼ ሆይ! ከአላህ እዝነት ተስፋ አትቁረጡ፤ አላህ ኃጢኣቶችን በመላ ይምራልና፡፡ እነሆ እርሱ መሓሪው አዛኙ ነውና፡፡(አዝ-ዙመር፡ 54)

ፍራቻና ተስፋ

ፍራቻ እና ተስፋ ወደ ማሳመር (ኢህሳን) ለሚደረገው

ጉዞ እንደ ቅድመ ሁኔታ ይቆጠራሉ፡፡ ምክንያቱም

ሁለቱም በልቦና ውስጥ ተቀምጠው በተለያየ ደረጃ

መሥራት ይኖርባቸዋልና፡፡

ፍራቻ ማለት ማንኛውም ሰው ለሰራው ኃጢአት በዚህ

ወይም በቀጣዩ ዓለም ተጠያቂ እሆናለሁ ብሎ በማሰቡ

ልቦናው የሚያሳድረው ጭንቀት ነው፡፡

ፍራቻ በማንኛውም ኃጢአት እንደምንቀጣ አውቀን

በጥንቃቄ እንድንቀሳቀስ የሚያደርገን ነገር ነው፡፡ ይህ

ባህሪ በተለይም አላህን በማመጽ ላይ የሚገኝ ማንኛውም

ሙስሊም ሥነ-ምግባር ሊሆን ይገባል፡፡ ያለዚያ ተስፋ

ያለአግባብ ይለመልማል (ያይላል)፡፡

የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ

ብለዋል፡- “መንገድን የሚፈራ ሰው በሌሊት ይጓዛል፡፡

በሌሊት የተጓዘም ያሰበበት ይደርሳል፡፡ አዋጅ የአላህ ዕቃ

ውድ ናት አዋጅ የአላህ ዕቃ ጀነት ናት፡፡”

ተስፋ ማለት ልብ (ቀልብ) ከአላህ እዝነት ጋር

የሚቆራኝበት ሁኔታ ነው፡፡ ተስፋ ነገሮች ከአላህ እዝነትና

እርዳታ ጋር እንዲገናኙ የሚያደርግ ሲሆን አላህን

የሚያስደስቱ ተግባራትን እንሠራ ዘንድ የሚያነሳሳ

ግፊት ነው፡፡ የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ

ብለዋል፤- «አንድ በአላህ አማኝ ያልሆነ ሰው

የአላህን እዝነት ምን ያህል እንደሆነ ቢያውቅ ኖሮ ጀነት

የመግባትን ተስፋ ፈጽሞ አያጣም ነበር፡፡»48 ተስፋ

የሕሊና እረፍትንና ደስታን ከማምጣቱ በተጨማሪ

ጉዞውን ቀላልና ብርሃናማ ያደርገዋል፡፡

ትዕግስት (ሶብር)

ወደ ግባችን እንደርስ ዘንድ ትዕግስት ትልቅ ድጋፍ

ይሆነናል፡፡ ትዕግስት ወደፊት ለሚከሰቱ ችግሮች ራሳችንን

እንድናዘጋጅ ይረዳናል፡፡

የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፤-

«የአማኝ ነገር ሁሉ ይገርማል፡፡ ነገሩ በሙሉ መልካም

ነው፡፡ ጥሩ ነገር ሲያጋጥመው አላህን ያመሰግናል፡፡ ይህ

ለርሱ መልካም ነው፡፡ መጥፎ ነገር ሲያጋጥመው ትዕግስት

ያደርጋል ፡፡ ይህም ለርሱ መልካም ነገር ይሆንለታል፡፡»49

ያለትዕግስት ያሰብነው ቦታ አንደርስም፡፡ የአላህ

መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) «ጀነት በአስቸጋሪ ነገሮች

የተከበበች ናት፡፡ ጀሃነም ደግሞ በሚፈታተኑ (አማላይ)

ነገሮች የተከበበች ናት፡፡» ብለዋል፡፡

የትዕግስት አስፈላጊው ነገር ፍላጎትን ለአላህ ትዕዛዝ

መግራትና የአመጽን ስሜት ማዳፈን ነው፡፡ ስለሆነም

ትዕግስት የአላህን ትዕዛዝ ለመጠበቅና ከከለከላቸው

ነገሮች ለመራቅ የግድ ያስፈልጋል ማለት ነው፡፡

ባሪያዬ ምንጊዜም ባስታወሰኝና ከናፍሮቹ እኔን ለማውሳት በተንቀሳቀሱ ቁጥር ከርሱ ጋር እሆናለሁ፡፡ —ሐዲስ አል-ቁድስ“

Page 92: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - zhic.aeኢስላም፣ ኢማን እና ኢሕሳን 3 አጠቃላይ እይታ 4 መግቢያ 6 የጉዞ መመሪያ 6 ለጉዞ

ክፍል 3፡- ኢሕሳን 75

ጓደኞችና አከባቢያችን17

ማንኛውም ጉዞ ከመልካም ወዳጅ (ጓደኛ) ውጭ ሊፈፀም አይችልም፡፡ መልካም ጓደኛ መያዝ በአቅጣጫና ፍጥነታችን ላይ አዎንታዊ ተጽዕኖ ያሳድራል፡፡ ከጓደኞች ሁሉ ምርጦቹ አላህን አዘውትረው የሚያስታውሱ አዛኝና ደጐች የሆኑት ናቸው፡፡

የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ከሰዎች በላጮቹ “ስታያቸው አላህን የሚያስታውሱ ናቸው” ብለዋል፡፡51

ማሳመርን (ኢሕሳንን) የሚፈልግ ሰው ከመልካምና ክቡር ዓላማዎች የሚያዘናጉ ጓደኞችን መቀነስ ብሎም መተው ይጠበቅበታል፡፡ የአላህ መልዕክተኛ (ሶ.ዐ.ወ) መልካም ጓደኛን ጥሩ መአዛ ያለውን ሽቶ በሚሸጥ የሽቶ ነጋዴ መስለውታል፡፡ እንዲህ ብለዋል፣ «መልካም ጓደኛ ማለት ልክ ሚስክ የተባለውን ግሩም መአዛ ያለው ሽቶ እንደሚሸጥ ነጋዴ ነው፡፡ ይህ ሰው ምናልባት

ከሽቶው ይሰጥሃል ወይም ይህን ሽቶ አንተ ከርሱ ትገዘዋለህ፡፡ ወይም ከርሱ ጥሩ ሽታ ታገኛለህ፡፡ ነገር ግን መጥፎ ጓደኛ ማለት ልክ ወናፍ እንደሚነፋ ነው፡፡ ምናልባት ልብስህን ያቃጥልብሃል ወይም ከርሱ መጥፎ ሽታ ልታገኝ ትችላለህ፡፡»

አንድ ሰው እንደሙስሊም የሕይወት ዘይቤውን መለወጥ ካለበት መጥፎ ልማዶቹን አስወግዶ ቀስ በቀስ በአዲሶቹ መተካት ይኖርበታል፡፡ በሂደቱም በጐ ተጽዕኖ የሚያሳድሩ፣ ንግግራቸው፣ ድርጊታቸውና መንፈሳዊ ጐናቸው ጠቃሚ የሆነ ጓደኞችን መምረጥና ከነርሱ ጋር መሆን ይበጀዋል፡፡ አላህ እንዲህ ብሏል፡-

በጊዜያቱ እምላለሁ፤ ሰው ሁሉ በእርግጥ በኪሳራ ውስጥ ነው፡፡ እነዚያ ያመኑትና መልካሞችን የሠሩት፥ በውነትም አደራ የተባባሉት በመታገስም አደራ የተባባሉት ብቻ ሲቀሩ፡፡ (አል-ዐስር፡ 1-3)

Page 93: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - zhic.aeኢስላም፣ ኢማን እና ኢሕሳን 3 አጠቃላይ እይታ 4 መግቢያ 6 የጉዞ መመሪያ 6 ለጉዞ

መለኮታዊው መንገድ፡-የአዲስ ሙስሊሞች ስርዓተ ትምህርት76

አላህን ማስታወስ (ዚክር)18

በጉዞ ወቅት መልካም ወዳጅ ማለት አላህ ብቻ ሲሆን እንዲህ ብሏል፡-

«እኔ ባሪያዬ እስካስታወሰኝ ድረስ ከርሱ ጋር ነኝ፡፡"52

ቁርኣን ወይስ ሐዲሰል ቁድስ? የሚሳመር (ኢሕሳን) ምሁራን በአጠቃላይ:- አንድ ሙስሊም በአምልኮቱና በመልካም ተግባሩ ምንዳ ያገኛል በሚለው ተስማምተዋል፡፡ በተጨማሪም ይህ መንፈሳዊ ደረጃ የሚገኘው የአላህን ስም በመልካም ሥነ-ምግባር (አደብ)ና ንቃት በመጥራት ነው በሚለው ሀሳብም ላይ እንዲሁ ስምምነት አሳይተዋል፡፡

በዚህ መሰሉ አላህን የማስታወስ ተግባር (ዚክር) ነው ልብ የሚለወጠው፡፡የማንኛውም በተነሳሽነት የሚፈፀም ተግባር ዋነኛ መሠረት አላህን ማስታወስ (ዚክር) ነው፡፡ ማንኛውም ሰው አላህን የማስታወስ ብቃቱን ሊጨምር የሚችለው ደግሞ በምላሱ በሚያደርገው (ዚክር) ሲሆን ይህንንም «አላህን እንደምታየው አድርገህ ተገዛው» እስከሚለው ሊያደርሰው ይችላል፡፡

አላህን ማስታወስ (ዚክር) ለመንፈስ ምግብ ነው፡፡ ዚክር ከሌለ መንፈስ ይሞታል፡፡ የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- «አላህን የሚያስታውስና የማያስታውስ ሰው ምሳሌ ልክ ሕይወት እንዳለውና እንደ ሞተ ሰው ነው፡፡»53

አላህን ለማስታወስ (ለዚክር) ገደብ አልተበጀለትም፡፡ ስለሆነም አንድ ሰው አላህን በፈለገበት ግዜና ሁኔታ በብዛት ሊያስታውሰው ይችላል፡፡ አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ብሏል፡-

እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ብዙ ማውሳትን አውሱት፡፡ (አል አሕዛብ፡ 41)ኢብን አባስ (ረ.ዐ) የተባሉት የነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ባልደረባና ከታወቁት የቁርኣን ተንታኞች አንዱ «ብዙ ማውሳትን አውሱ» የሚለውን ሀረግ ትርጓሜ

«ሁልጊዜም አላህን አስታውሱት ማለት ነው» ብለዋል፡፡ ይህ ደግሞ በሌላ የቁርኣን አንቀጽ የተጠቀሰ ሲሆን አማኞችን እንዲህ ሲል ይገልጻቸዋል፡

-«(እነርሱም) እነዚያ ቆመው ተቀምጠውም በጎኖቻቸው ተጋድመውም አላህን የሚያወሱ በሰማያትና በምድር አፈጣጠርም የሚያስተነትኑ... ናቸው፡፡» (አለ ዒምራን፡ 195)

ይህ የቁርአን አንቀጽ በማንኛውም ሁኔታ አላህን ማስታወስ (ዚክር ማድረግን) ያበረታታል፡፡በአጠቃላይ ዚክር አላህን የማስታወስ ተግባር ስለሆነ በማንኛውም ዓይነት ቋንቋ ሊተገበር ይችላል፡፡

ያም ቢሆን ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ያስተማሯቸው ዚክሮች በዐረብኛ ቋንቋ መባል አለባቸው፡፡ ዚክርን ድምፅን በማጉላት ወይም ባለማጉላት ማከናወን ይቻላል፡፡ ማንኛውም ሙስሊም ሊያውቃቸው የሚገቡ በርካታ የዚክር ዓይነቶች አሉ፡፡ ከእነርሱ መካከል በላጩ «ላ ኢላሀ ኢልለላህ» የሚለው ነው፡፡

የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፤- «ኢማን ከሰባ በላይ ቅርንጫፎች አሉት ከእነርሱ መካከል ትልቁ «ላ ኢላሀ ኢልለላህ» ማለት ሲሆን ትንሹ ደግሞ ጎጂ ነገሮች ከመንገድ ላይ ማስወገድ ነው፡፡»54 በተጨማሪም ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ለባልደረቦቻቸው “ኢማናችሁን

አድሱ” አሏቸው፡፡ እነርሱም «የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! እንዴት አድርገን ነው ኢማናችንን ማደስ የምንችለው?» በማለት ጠየቋቸው፡፡ እርሳቸውም «ላ ኢላሀ ኢልለላህ የሚለውን ንግግር አብዙ» አሏቸው፡፡55አላህ እንዲህ ብሏል፡-

(እነርሱም) እነዚያ ያመኑ ልቦቻቸውም አላህን በማውሳት የሚረኩ ናቸው፤ ንቁ አላህን በማውሳት ልቦች ይረካሉ፡፡ (አር-ረዕድ፡ 28) የሚከተሉት የዚክር ዓይነቶች በተደጋጋሚ መባል ያለባቸው ሲሆን በተወሰኑ ክፍሎች ተሸንሽነዋል፡-

Page 94: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - zhic.aeኢስላም፣ ኢማን እና ኢሕሳን 3 አጠቃላይ እይታ 4 መግቢያ 6 የጉዞ መመሪያ 6 ለጉዞ

ክፍል 3፡- ኢሕሳን 77

ከአላህ ጥበቃን መፈለግ

«አዑዙ ቢልላሂ ሚነሸ- ሸይጧኒር- ረጂም»

(ከተረገመው ሰይጣን በአላህ እጠበቃለሁ፡፡)

በስመላህ (በአላህ ስም)

ቢስሚላሂ አር-ረሕማኒ አር-ረሒም

(በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ በጣም አዛኝ በኾነው፡፡)

በነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ላይ የአላህን ሰላምና በረከት ማውረድ

ሰልላሁ ዐለይሂ ወሰለልም

(የአላህ ሰላምና በረከት በርሳቸው ላይ ይሁን)

ምህረትን መጠየቅ

አስተግፊሩላህ

(ከአላህ ምህረት እጠይቃለሁ)

አላህን ማላቅ

ሱብሐነልላህ

(ለአላህ ጥራት ይገባው)

ምስጋና

አልሐምዱሊላህ

(ለአላህ ምስጋና ይገባው)

ተክቢር

አላሁ አክበር

(አላህ ትልቅ ነው)

የአላህን ብቸኝነት ማረጋገጥ

ላ ኢላሀ ኢልለላህ

(ከአላህ በስተቀር አምልኮ የሚገባው ሌላ አምላክ የለም)

የአላህን ኃይል ማረጋገጥ

ላ ሐውል ወላ ቁወተ ኢልላ ቢልላህ

(ከአላህ በስተቀር ብልሃትም ሆነ ኃይል ያለው ማንም የለም)

በነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ላይ ሰላምና በረከትን ማውረድ አላህ እንዲህ ይላል፡-

አላህና መላእክቱ በነቢዩ ላይ የአክብሮት እዝነትን ያወርዳሉ፤ እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በ ርሱ ላይ የአክብሮት እዝነትን አውርዱ፤ የማክበርንም ሰላምታ ሰላም በሉ፡፡ (አል-አሕዛብ፡ 56)

አላህ ነቢዩን (ሰ.ዐ.ወ) ለማክበር፣ ለማላቅና ደረጃቸውን ከፍ ለማድረግ ሰላምና በረከቱን በርሳቸው ላይ አውርዷል፡፡ መላዕክትም እንዲሁ ሰላምታቸውን እርሳቸውን ለማክበር አውርደዋል፡፡ እኛም በርሳቸው ላይ ሰላምታና በረከት ስናወርድ አላህ ለእርሳቸው ቃል የገባላቸውን ደረጃ እንዲያጎናጽፋቸው በማሰብ መሆን

አላህን የሚያስተውስና የማያስተውስ ሰው ምሳሌ ልክ ሕያው እንደሆነና እንደሞተ ሰው ነው፡፡ —ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ)“

Page 95: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - zhic.aeኢስላም፣ ኢማን እና ኢሕሳን 3 አጠቃላይ እይታ 4 መግቢያ 6 የጉዞ መመሪያ 6 ለጉዞ

መለኮታዊው መንገድ፡-የአዲስ ሙስሊሞች ስርዓተ ትምህርት78

ይኖርበታል፡፡ ተወዳጁ ነብያችን (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡፡ «ማንኛውም ሰው በእኔ ላይ አንድ ሰላምታና በረከት አያወርድብኝም አላህ ለርሱ አስር ሰላምታና በረከት የሚያወርድበት ቢሆን እንጂ፡፡»56

በተወዳጁ ነቢይ ላይ ሰላምታና በረከት ማውረድ የአምስቱ ግዴታ ሶላቶች አካል ከመሆኑ ባሻገር በፍርዱ ቀን ወደእርሳቸው ለመቅረብም ምክንያት ይሆናል፡፡ የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- «በፍርዱ ቀን ወደኔ ይበልጥ የሚቀርቡት እነዚያ በእኔ ላይ ሰላምታና በረከት በብዛት የሚያወርዱ ናቸው፡፡»57 እንዲህም ብለዋል፡- «በእኔ ላይ ሰላምታና በረከት በማውረድ ስብስባችሁን አስጊጡ፡፡ በእኔ ላይ የምታወርዱት ሰላምታ በፍርዱ ቀን ብርሃን ይሆናችኋል፡፡»58

ለነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ያለንን ፍቅርና ቅርበት በርሳቸው ላይ በብዛት ሰላምታና በረከት በማውረድ ከፍ ማድረግ አለብን፡፡ ከዚህ ሌላ በርካታ በነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ላይ ሰላምታና በረከት የማውረጃ ዘዴዎች አሉ፡፡ የተወሰኑትን በቃል ያዙና እለታዊ ውዳሴዎቻችሁ አድርጓቸው፡፡ ሁልጊዜ በተለይ በዕለተ ዐርብ (ጁሙዓ) ደጋግሟቸው፡፡

የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡-«በጁሙዐህ ቀን ለእኔ ሰላምና በረከትን ለምኑልኝ፡፡ ምክንያቱም ይህ እለት የሚመሰከርበትና መላእክትም የሚመሰክሩበት እለት ነው፡፡ ማንኛውም ሰው ለእኔ ሲጸልይ ጸሎቱን እስኪያጠናቅቅ ድረስ ጸሎቱ ይደርሰኛል፡፡»59

በትንሳኤ ቀን እኔ ዘንድ የቀረበ ስፍራ ያላው ሰው ማለት በእኔ ላይ በብዛት ሰላምታ ያበዛ ነው፡፡ — ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ)“

Page 96: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - zhic.aeኢስላም፣ ኢማን እና ኢሕሳን 3 አጠቃላይ እይታ 4 መግቢያ 6 የጉዞ መመሪያ 6 ለጉዞ
Page 97: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - zhic.aeኢስላም፣ ኢማን እና ኢሕሳን 3 አጠቃላይ እይታ 4 መግቢያ 6 የጉዞ መመሪያ 6 ለጉዞ
Page 98: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - zhic.aeኢስላም፣ ኢማን እና ኢሕሳን 3 አጠቃላይ እይታ 4 መግቢያ 6 የጉዞ መመሪያ 6 ለጉዞ

መብቶች እና ኃላፊነቶች

«በርግጥ ፈጣሪያችሁ በእናንተ ላይ መብት አለው፡፡ ነፍሳችሁ በናንተ ላይ መብት አልላት፡፡ ቤተሰቦቻችሁ በናንተ ላይ መብት አላቸው፡፡ ስለዚህ ለባለ መብቱ ሁሉ መብቱን ስጡ፡፡» ነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)

Page 99: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - zhic.aeኢስላም፣ ኢማን እና ኢሕሳን 3 አጠቃላይ እይታ 4 መግቢያ 6 የጉዞ መመሪያ 6 ለጉዞ

መለኮታዊው መንገድ፡-የአዲስ ሙስሊሞች ስርዓተ ትምህርት82

አጠቃላይ እይታ19

መግቢያ

ኢስላም በተከታዩ በነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ንግግር ሊጠቃለል ይችላል «…ስለዚህ ለባለመብቱ ሁሉ መብቱን ስጡ፡፡»60

ከፍትሐዊነቱና ከእዝነቱ ባሻገር አላህ የፍጡራኑ ሕይወት እንዲያምር መብቶችን ሰጥቷቸዋል፡፡ እርሱን የማምለክ ዋነኛው መገለጫም እነዚያን መብቶች ማሟላት ነው፡፡

የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) አንድ የአላህ ባሪያ ሊጫወተው የሚገባውን ሚና ራሳቸው ምሳሌ በመሆን አሳይተዋል፡፡ እርሳቸው በእርግጥም በአላህ የተሰጣቸውን ኃላፊነቶችና አደራዎች ሁሉ በሚገባ ተወጥተዋል፡፡ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) አጋዥ ባል፣ አስተዋይ አባት፣ የሚያነቃቃ መሪ፣ ጽኑ ጓደኛ፣ መልካም ጐረቤት፣ ትሁት

አገልጋይና የአላህ መልዕክተኛ ነበሩ፡፡ በእነዚህ ሁሉ ሚናዎች የአላህ ነቢይ (ሰ.ዐ.ወ) ምርጥነታቸውን ማሳየት ብቻ ሳይሆን ባልደረቦቻቸውም እንዴት የሌሎችን መብት መጠበቅና ሚዛናቸውን ጠብቀው መኖር እንዳለባቸው አስተምረዋል፡፡

የነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ታላቅ ስብዕና የተከበሩ በነበሩት ባለቤቶቻቸውና ባልደረቦቻቸው ጭምር ተንጸባርቋል፡፡ እነዚያ ሰዎች የመጀመሪያዎቹ ሙስሊሞች እንደመሆናቸው ማንም አዲስ ኢስላምን የተቀበለ ሰው የሚገጥሙ ተግባራቶች ነበር የገጠማቸው፡፡

አኗኗራቸውና ልምዳቸው በሁሉም የሕይወት ዘርፎች የሚኖሩንን ግንኙነቶች ማለትም ከፈጣሪያችን፣ ከራሳችን ቤተሰቦች፣ ከወላጆቻችን፣ ከማህበረሰባችን እንዲሁም ከዓለም ጋር ያሉንን ግንኙነቶች በተሳካ ሁኔታ እንድናስኬዳቸው ያስችለናል፡፡

Page 100: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - zhic.aeኢስላም፣ ኢማን እና ኢሕሳን 3 አጠቃላይ እይታ 4 መግቢያ 6 የጉዞ መመሪያ 6 ለጉዞ

83ክፍል 4፡- መብቶች እና ኃላፊነቶች

ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል «ሃይማኖት መመካከር ነው»61

ስለሆነም ልባዊ በሆነ የምክክር (ነሲሃ) መንፈስ ይህ ምዕራፍ ተግባራዊ የሚሆኑ ጉዳዮችን በዝርዝር አስዳስሶናል፡፡ ሌሎች ሰዎች በእኛ ላይ ያላቸውን ሃቅ ማወቅና ያንንም በሟሟላት ጉዟችንን የተሳካ ለማድረግ ወሳኝና አስፈላጊ ነገር ነው፡፡

የአላህ መብቶች

አላህ በእኛ ላይ ያለው መብት እጅግ አንገብጋቢ ሲሆን ይኸውም እርሡን በብቸኝነት ማምለካችን ነው፡፡ የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ወጣት የሆነውን ባልደረባቸውን «ሙዓዝ ሆይ! አላህ በባሪያዎቹ ላይ ያለውንና ባሪያዎቹ ደግሞ በርሱ ላይ ያላቸውን መብት ታውቃለህን?» በማለት ጠየቁት፡፡

እርሱም «አላህና መልዕክተኛው ይበልጥ ያውቃሉ» በማለት መለሰላቸው፡፡ እርሳቸውም «አላህ ባሪያዎቹ ላይ ያለው መብት ከርሱ ጋር ማንንም ሳያጋሩ እርሱን ብቻ መገዛታቸው ነው፡፡ ባሮቹ በእርሱ ላይ ያላቸው መብት ደግሞ እስካላጋሩበት ድረስ እነርሱን አለመቅጣቱ ነው" አሉት፡፡62

በዚህም የተነሳ አላህ በባሪያዎቹ ላይ ያለው መብት ሦስት የኢስላም መሠረቶችን ያጠቃለለ ነው፡፡ እነርሱም ኢስላም፣ ኢማንና ኢሕሳን ናቸው፡፡ አላህ በእኛ ላይ ያለው መብት ጥርት ባለ እውቀትና በርግጠኝነት በእርሱ እንድናምንና መሠረተ ቢስ ከሆኑ አስተሳሰቦች እንድንርቅ ያደርገናል፡፡

ይህ የእምነት (ኢማን) ዓለም ነው፡፡ አላህ በሰውነታችን ላይ መብት አለው፡፡ መብቱም እርሱን ለማምለክና ግዴታ ያደረገብንን ተግባራት ለመፈጸም እንድንጠቀምባቸው ያስገድደናል፡፡ ይህ የኢስላም እውነታ መገለጫ

ነው፡፡ አላህ በልባችን ላይ መብት አለው፡፡ መብቱም በርሱ ላይ መመካታችን፣ እርሱን ብቻ ማፍቀራችን፣ በርሱ ላይ ብቻ ተስፋ ማድረጋችን ነው፡፡ ይህ የኢሕሳን እውነታ መገለጫ ነው፡፡ ይህ የኢስላም ዓለም ነው፡፡ እንዲሁም በልባችን ላይ መብት አለው፡፡ በእርሱ ብቻ እንድንመካ፣ እርሱን ብቻ እንድናፈቅር፣ በእርሱ ላይ ብቻ ተስፋ እንድናደርግና እርሱን በሚገባ እንድናውቀው መፈለጉ ነው፡፡ ይህ የኢህሣን ዓለም ነው፡፡

የአላህን መብቶች ማሟላታችን ብቻ የሌሎችንም መብቶች እንድናሟላና እንድንጠብቅ ያደርገናል፡፡ እንደ እውነቱ ከሆነ የሌሎችን መብቶች ማሟላት ማለት በርግጥ የአላህን መብት እንደማሟላት ነውና፡፡

ምክር (ነሲሃ)

አላህን በብዛት በማውሳትና ውብ ስሞቹን በማወቅ ወደርሱ

ተቃረብ፡፡ ማንኛውም ነገር ሲያጋጥምህ በአላህ ፍላጎት

እንደተከሰተ በማወቅ በትዕግስት ተቀበል፡፡ ለብቻህ ስትሆን

ጊዜ ወስደህ ለእርሡ ስገድ፣ ከልብህም የምትፈልገውን

ጠይቀው፡፡

የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) መብቶች

የመጨረሻው የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ከፍጥረታት መካከል ምርጥና የነቢያት ሁሉ መደምደሚያ ናቸው፡፡ ባላቸው የላቀ ደረጃና ስፍራ በኛ ላይ በርካታ መብቶች አሏቸው፡፡

በእርሳቸው ማመን

ከሁሉም በላይ የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) በእኛ ላይ ያላቸው መብት እርሳቸው የመጨረሻው የአላህ መልዕክተኛ መሆናቸውንና ለሰው ዘር በሙሉ መላካቸውን በእርግጠኝነት ማመን ነው፡፡ አላህ እንዲህ ይላል፡-

በአላህና በመልዕክተኛውም በዚያም ባወረድነው ብርሃን እመኑ (አት-ተጋቡን፡ 8)

አላህ ባሪያዎቹ ላይ ያለው መብት ከርሱ ጋር ማንንም ሳያጋሩ እርሱን ብቻ መገዛታቸውን ነው፡፡ በእርሱ ላይ ያሉት የባሪያዎቹ መብቶች ደግሞ አጋርተው እስካልተገዙ (እስካልመለኩ) ድረስ እነርሱን አለመቅጣቱ ነው፡፡ —ነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)

Page 101: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - zhic.aeኢስላም፣ ኢማን እና ኢሕሳን 3 አጠቃላይ እይታ 4 መግቢያ 6 የጉዞ መመሪያ 6 ለጉዞ

መለኮታዊው መንገድ፡-የአዲስ ሙስሊሞች ስርዓተ ትምህርት84

እርሳቸውን መከተል

በኢስላማዊ መንገድ እርሳቸው የኛ ታላቅ መሪያችንና አርአያችን እስከሆኑ ድረስ የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) በእኛ ላይ ካሏቸው መብቶች መካከል ዋነኛው ያዘዙትን መቀበል፣ የከለከሉትን መከልከል ነው፡፡ አላህ እንዲህ ብሏል፡-

እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህንና መልዕክተኛውን ታዘዙ፤ (አል- አንፋል፡ 20)

እንዲህም ብሏል፡፡ መልዕክተኛውን የሚታዘዝ በእርግጥ አላህን ታዘዘ (አን-ኒሳእ፡ 80)

እርሳቸውን መውደድ

የእርሳቸውን ተምሳሌትነት በግልጽ መከተል ብቻ አይደለም፡፡ የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) በእኛ ላይ

ያላቸው መብት እርሳቸውን ከማንም በላይ መውደድም መብታቸው ነው ፡፡ ከእለታት አንድ ቀን አንድ ሰው ወደ አላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) መጣና «የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! የሰዓቷ (የዕለተ ትንሳኤ) መምጪያ መቼ ነው?» በማለት ጠየቃቸው፡፡ እርሳቸውም ለእርሷ ምን አዘጋጅተሃል?» አሉት፡፡

እርሱም «ለርሷ በርካታ ሰላቶችን፣ አጽዋማትንና ምጽዋትን (ሰደቃን) አላዘጋጀሁም፡፡ ነገር ግን አላህንና መልዕክተኛውን እወዳለሁ» አላቸው፡፡ እርሳቸውም «አንተ ከወደድከው ጋር ትሆናለህ»63 አሉት፡፡

ምክር (ነሲሃ)

ስለ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ስነ-ምግባርና አካላዊ ገጽታ የእርሳቸውን የሕይወት ታሪክ (ሲራ) በማንበብ በደንብ እወቅ፡፡ በተግባርም ፈለጋቸውን ለመከተል ሞክር፡፡ የእርሳቸውን አርዓያ የሚከተሉ ሰዎችን ተጎዳኝ፡፡ ሰላምና እዝነት በርሳቸው ላይ በብዛት አውርድ፡፡

በአላህ መልዕክተኛ መልካም መከተል አልላችሁ፡፡ —(አል-አሕዛብ፡-21)“

[ከላይ] መዲና የሚገኘው የነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) መስጂድ ውስጠኛ ክፍል

Page 102: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - zhic.aeኢስላም፣ ኢማን እና ኢሕሳን 3 አጠቃላይ እይታ 4 መግቢያ 6 የጉዞ መመሪያ 6 ለጉዞ

85ክፍል 4፡- መብቶች እና ኃላፊነቶች

የራስ መብቶችና ኃላፊነቶች20

ሚዛናዊነት

በተለይ አንድ ሰው ወደ ኢስላም ሲመጣ (ኢስላምን ሲቀበል) የሚኖረው ሃይማኖት መነቃቃት በርካታ የአምልኮት ተግባራትን በፍጥነትና በብዛት እንዲሠራና በሂደቱም እንዲዋጥ ያደርገዋል፡፡

ይህ በብዙ ሰዎች ዘንድ የሚከሰት መሆኑ እውነት ነው፡፡ ይሁን እንጂ ረዥም ርቀት ለመጓዝ ሚዛንን መጠበቅ አስፈላጊ ነው፡፡

የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- «ሃይማኖት ገር ነው፡፡ ማናችሁም ሃይማኖቱን አያጠብቅም ሃይማኖቱ የሚያሸንፈው ቢሆን እንጂ ፡፡ ስለዚህ ጽኑ ሁኑ፣ መልካምን አብስሩ፣ በመልካምም ተኗኗሩ፡፡"64

መካከለኛነት

በአንድ ወቅት የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) አምልኮታዊ ተግባራቶቻቸውን ለማሻሻል በሚል፤ አንደኛው ሌሊቱን ሳይተኛ በሶላት ለማሳለፍ፣ ሁለተኛው ዓመቱን በሙሉ ለመጾም፣ ሦስተኛው ደግሞ ከጋብቻ መራቅ ለውሰኑ ሰዎች መክረዋል፡፡ ትክክልለኛውንም መንገድ አመላክተዋል፡፡

ይኸውም እሳቸው (ነብዩ) (ሰ.ዐ.ወ) ወደ እርሱ በመሄድ እንዲህ በማለት መከሯቸው «በአላህ እምላሉሁ! እኔ ከናንተ እጅግ አላህን ፈሪያችሁና ባላጫችሁ ነኝ፡፡ ነገር ግን እጾማለሁ፣ ፆሜንም እገድፋለሁ፡፡ እተኛለሁ፣ እሰግዳለሁም፡፡ ሴቶችን አገባለሁም፡፡ የእኔን ሱንና (ፈለግ) ያልተከተለ ከእኔ ተከታዮች አይደለም፡፡»65

በአምልኮት ተግባራት ድንበር ማለፍ የነቢዩን (ሰ.ዐ.ወ) ሱንና የሚቃረን ተግባር ብቻ ሳይሆን የሌሎች ሰዎችን መብትም ይጋፋል፡፡ እውነተኛ አምልኮታዊ ተግባር የሚገኘው ከነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ጋር ስምምነት በማሳየትና ሌሎች ሰዎችን በማክበር ነው፡፡ አላህ እንዲህ ብሏል፡- ምርጥ ሕዝቦች አደረግናችሁ፡፡ (አል በቀራህ፡ 143)አላህ ልንፈራው (ተቅዋ ሊኖረን) ዘንድ ዓለማዊ ሕይወትንና

መልካም ነገሮችን እንድንተው አይፈልግም፡፡ ግልጽ በሆነው መለኮታዊ ትዕዛዝና ክልከላ መካከል በርካታ የተፈቀዱ ነገሮች አሉ፡፡ ነገር ግን በመካከለኛነት እንድንተገብራቸው ተነግሮናል፡፡አላህ እንዲህ ብሏል፡-

…አላህ በናንተ ገሩን (ነገር) ይሻል፤ በናንተም ችግሩን አይሻም (አል በቀራህ፡ 185)

ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ራሳቸው እንኳ ጊዜያቸውን ለሦስት ይከፍሉ ነበር፡፡ እያንዳንዱን የጊዜ ክፍልም ለተገቢው ጉዳይ ያውሉት ነበር፡፡ አንዱን ክፍል ለአምልኮ ተግባር የመደቡት ሲሆን ሁለተኛውን ለቤተሰባቸው፤ ቀሪውን ደግሞ የሰዎችን ችግር ለማዳመጥና ጉዳያቸውን ለመፈጸም

ምክር (ነሲሃ)

ግዴታ የሆኑ ተግባራትን በጊዜያቸውና በአግባቡ የመፈፀምን

ልማድ አዳብር፡፡ የእለት ተዕለት ተግባራትህን ጥሩ እሳቤ

(ኒያ) በማሳደር ወደ አምልኮታዊ ተግባር ለውጥ፡፡

የሌሎችን መብት መጠበቅና ማሟላትም አላህን የማምለክ

ክፍል መሆኑን ጠንቅቀህ እወቅ፡፡

ንጹሕ ምግብን መመገብአላህ እንዲህ ይላል፡-

እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ከነዚያ ከሰጠናችሁ ጣፋጮች ብሉ፥ ለአላህም እርሱን ብቻ የምትገዙ እንደኾናችሁ አመስግኑ፤ (አል በቀራህ፡ 172)

የማንኛውም ሰው ውስጣዊ አካልና መንፈስ ከፈጣሪ የተሰጡ የአደራ ንብረቶች ናቸውና ተገቢው እንክብካቤ ይደረግላቸው ዘንድ መብት አላቸው፡፡ ምድራዊውን ፍላጎት ለማሟላት አካላት አስፈላጊውን ነገር መካከለኛ በሆነ ሁኔታ ሊሟላላቸው ይገባል፡፡

ንጹሕና የተመጣጠኑ ምግቦችን መመገብ ሰውነትን ከመገንባቱ በተጨማሪ የአካልን መብቶች መወጣት ጭምር ነው፡፡ መለኮታዊው ሕግ ከባህል ባህል፣

Page 103: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - zhic.aeኢስላም፣ ኢማን እና ኢሕሳን 3 አጠቃላይ እይታ 4 መግቢያ 6 የጉዞ መመሪያ 6 ለጉዞ

መለኮታዊው መንገድ፡-የአዲስ ሙስሊሞች ስርዓተ ትምህርት86

ከአካባቢ አካባቢ ለሚለያዩ ምግቦች ምንም ዓይነት አሳሪ መመሪያዎችን አላስቀመጠም፡፡ እንዲያውም መመሪያዎቹ ለውጥን የሚያስተናግዱ ናቸው፡፡

አብዛኛዎቹ ምግቦች ለመመገብ የተፈቀዱ (ሐላል) ተደርገው ይወሰዳሉ፡፡ ለምሳሌ ፍራፍሬዎች፣ አትክልቶች፣ ጥራጥሬዎች አሳና የወተት ተዋጽኦዎች፣ እንዲሁም የስጋ ተዋጽኦዎች፣ ለምሳሌ የከብት፣ የበግ ስጋ የእንስሳው እርድ በኢስላማዊው ሕግ በአግባቡ የተፈፀመ ከሆነ የተፈቀደ ነው፡፡

ንጹሕ ያልሆኑና ክልክል (ሐራም) የሆኑ ምግቦችን መመገብ የተከለከለ መሆኑን አስመልክቶ አላህ እንዲህ ይላል-በናንተ ላይ እርም ያደረገው፥ በክትንና ደምን፥ የእሪያ ሥጋንም በርሱም (ማረድ) ከአላህ ስምሌላ የተነሳበትን ነገር ብቻ ነው፤ ሽፍታና ወሰን አላፊ ሳይኾን፥ (ለመብላት) የተገደደ ሰውም፥ በርሱ ላይ ኃጢኣት የለበትም፤ አላህ መሓሪ አዛኝ ነውና፡፡ (አል በቀራህ፡ 173)

የአመጋገብ ሥርዓት

ምግብ ስንመገብ አስፈላጊ የሆኑ ሥነ-ሥርዓቶችን መከተል ግድ ይለናል፡፡ ምግቡን ቢስሚልላህ (በአላህ ስም) ብሎ መጀመር ያስፈልጋል፡፡ ተመግበን ስንጨርስ ደግሞ «አል- ሐምዱሊልላህ» (ለአላህ ምስጋና ይገባው) እንላለን፡፡ ነቢዩ(ሰ.ዐ.ወ) ተቀምጠው የሚመገቡ ሲሆን ቀኝ እጃቸውን ይጠቀሙ ነበር፡፡ እንዲሁም ሰዎች ከፊት ለፊታቸው ብቻ እንዲመገቡና ከሰው ፊት ምግብ እንዳያነሱ መክረዋል፡፡ የማይፈልጉት ወይም የማይስማማቸው ምግብ ቢቀርብላቸው እንኳ ወደ ጎን ይተውታል እንጂ በምግቡ ላይ ሒስ (ትችት) አይሰነዝሩም ነበር፡፡

ምክር (ነሲሃ)

በአቅራቢያህ የሚገኝና የተፈቀደ (ሐላል) ምግብ

የሚገኘበትን ቦታ ምረጥ፡፡ በተቻለህ ያክል ለጤንነት

ጠቃሚ የሆኑትን ምግቦች ብቻ ተመገብ፡፡ በመልካም ሁኔታ

ያልተዘጋጁትን ደግሞ አስወግድ፡፡ ከቻልክ ከሰዎች ጋር

በመመገብ የአላህን በረከት አግኝ፡፡

ጎጂ ንጥረ ነገሮችካልተፈቀዱት የምግብ ዓይነቶች ጎን ለጎን ፍጹም ክልክል የሆኑ የምግብ ዓይነቶችም አልሉ፡፡ ይኸውም በተፈጥሯቸው በሚያስከትሉት ጉዳትና በአካልና በአእምሮ ላይ በሚያመጡት አሉታዊ ተጽዕኖ ነው፡፡ በኢስላማዊ ሕግ መሠረት ራስን ወይም ሌሎች ሰዎችን የሚጎዱ ነገሮችን እያወቁ መጠቀም ፍጹም ክልክል ነው፡፡ ለምሳሌ አልኮልና መሰል አስካሪ መጠጦች የሰውን ልጅ አእምሮ ስለሚጎዱና ከቁጥጥር ውጭ ስለሚያደርጉ ለግለሰቦችም ሆነ ለማህበረሰቡ ጠንቅ በመሆናቸው ክልክል ተደርገዋል፡፡

አላህ ጎጂ ነገሮችን እንዳንጠቀም እንዲህ በማለት አስጠንቅቋል፡-

ሰይጣን የሚፈልገው በሚያሰክር መጠጥና በቁማር፥ በመካከላችሁ ጠብንና ጥላቻን ሊጥል፥ አላህን ከማውሳትና ከስግደትም ሊያግዳችሁ ብቻ ነው፡፡ ታዲያ እናንተ (ከነዚህ) ተከልካዮች ናችሁን? (ተከልከሉ)፡፡ (አል- ማኢዳህ፡ 91)

አደንዛዥ እፆችም ቢሆኑ ክልክል ተደርገዋል፡፡ ምክንያቱም ለረዥም ጊዜ ለሚቆይ ሱሰኝነት ስለሚያጋልጡ፣ መጥፎ ስነ-ምግባር ስለሚያላብሱና አላህን ከማስታወስ እንቅፋት ስለሚሆኑ ነው፡፡ የትንባሆ (ሲጋራ) ምርቶችን በተመለከተ ለጤና ጠንቅ መሆናቸው በሳይንስ የተረጋገጠና የታወቀ በመሆኑ ከእኛ ሊርቁ ይገባል፡፡

አለባበስ እና ትህትና

የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡-«የሃያእ (ዓይን አፋርነት) ሁሉም ነገሩ መልካም ነው፡፡»66

ሃያእ የአማኞችን ሕይወት በቀጥታ የሚነካሲሆን በአነጋገራቸው፣ በስነ- ምግባራቸው በአትኩሮቶቻቸው፣በእንቅስቃሴዎቻቸውና በአለባበሳቸው ላይ ይንፀባረቃል በአለባበስ ረገድ «ኢስላማዊ አለባበስ»

ልቦች ሐላል በሆኑ መንገዶች የተገኙ ሲሳዮችን በመመገብ ይለሰልሳሉ፡፡ — ኢማም አሕመድ ኢብን ሐንበል“

Page 104: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - zhic.aeኢስላም፣ ኢማን እና ኢሕሳን 3 አጠቃላይ እይታ 4 መግቢያ 6 የጉዞ መመሪያ 6 ለጉዞ

87ክፍል 4፡- መብቶች እና ኃላፊነቶች

ተብሎ የተገለጸ ሕግ የለም፡፡ ይህ የሆነበት ምክንያት የሰዎች አልባሳት ከባህል ባህል፣ ከልማድ ልማድ፣ ከቦታ ቦታና ከሀገር ሀገር ስለሚለያዩ ነው፡፡ በአግባቡ የሰውነት ክፍልን እስከሸፈነ ድረስ ማንኛውም ሰው የሀገሩንና የማሕበረሰቡን አልባሳት መልበስ ይችላል፡፡አላህ እንዲህ ይላል፡-

የአደም ልጆች ሆይ! ሃፍረት ገላችሁን የሚሸሽግን ልብስ ጌጥንም በእርግጥ በናንተ ላይ አወረድን፤ አላህን የመፍራትም ልብስ ይህ የተሻለ ነው፡፡ (አል አዕራፍ፡ 26)

ይህ ለወንዶችም ሆነ ለሴቶች የሚያመለክተው ማንኛውም የጋብቻ ወይም የደም ትስስር (ግንኙነት) የሌላቸው ባይተዋር ሰዎች ባሉበት አጋጣሚና ስፍራ ሐፍረተ ገላቸውንና መታየት የሌለባቸውን የአካል

ክፍሎች በአጠቃላይ የመሸፈን ግዴታ እንዳለባቸው ነው፡፡ የወንድ ልጅ ሐፍረተ ገላ የሚባለው ከእንብርቱ እስከ ጉልበቶቹ ያለው የሰውነቱ ክፍል ሲሆን የሴት ልጅ ሐፍረተ ገላ ደግሞ ከእጆቿና ከፊቷ በስተቀር ያለው የአካል ክፍል ሁሉ ነው፡፡

ምክር (ነሲሃ)

ለአላህ ስትል ጨዋነትን የሚያሳዩ አልባሳትን ልበስ (ልበሺ)፡፡

ወደ ውጭ ስትወጣ የማያንጸባርቁ እና የሰውነትን ቅርጽ የማያሳዩ ልብሶችን ልበስ(ልበሺ)፡፡

ንጽሕናው የተጠበቀ ልብስ ዘውትር ልበስ፡፡ ልብስህ ንጹሕ

(ጡሃራ) መሆኑንም አረጋግጥ (አረጋግጪ)፡፡

የዚህችና የመጪው ዓለም ስኬት በአምስት ባህሪያት ይገለጻል፡፡ እነርሱም፡- ባለ ነገር መብቃቃት፣ ሃራም (ያልተፈቀዱ) ከሆኑ ነገሮች ራስንና ሌሎችን መጠበቅ፣ ከተፈቀደ የገቢ ምንጭ ብቻ ሲሳይን ማግኘት፣ አላህን የሚያስደስቱ አልባሳትን መልበስና በማንኛውም ሁኔታ በአላህ ላይ እምነትን መጣል፡፡ —ኢማም መሐመድ ኢብን ኢድሪስ አሽ-ሻፊዒ

Page 105: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - zhic.aeኢስላም፣ ኢማን እና ኢሕሳን 3 አጠቃላይ እይታ 4 መግቢያ 6 የጉዞ መመሪያ 6 ለጉዞ

መለኮታዊው መንገድ፡-የአዲስ ሙስሊሞች ስርዓተ ትምህርት88

ቤተሰባዊ ግንኙነት21

የቤተሰብ ጠቀሜታ

በኢስላም ቤተሰባዊ ትስስርን ጠብቆ ማቆየት ግዴታ ከመሆኑ ባሻገር የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ትስስሩን የሚቆርጡትን ሰዎች ኮንነዋል፡፡የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡-

“በዚህኛውም ዓለምም ሆነ በመጪው ዓለም በአላህ ዘንድ ከበደልና ቤተሰባዊ ትስስርን ከመቁረጥ የበለጠ ታላቅ ቅጣትን የሚያስከትል ትልቅ ሃጢአት የለም፡፡»67አዲስ እስልምናን የተቀበልክ ሙስሊም ከሆንክ ቤተሰቦችህ ባንተ ላይ ያላቸው መብት ጽኑ ነው፡፡ ስለሆነም እነርሱን በትህትናና በአክብሮት መያዝ ግዴታህ ነው፡፡አላህ እንዲህ ይላል፡-

ሰውንም በወላጆቹ (በጎ እንዲያደርግ) በጥብቅ አዘዝነው፡፡ እናቱ ከድካም በላይ በኾነ ድካም አረገዘችው፤ ጡት መጣያውም በሁለት ዓመት

ውስጥ ነው፡፡ ለኔም ለወላጆችህም አመስግን በማለት (አዘዝነው)፤ መመለሻው ወደኔ ነው፡፡ (ሉቅማን፡ 14) በአንድ አጋጣሚ አንድ ሰው ወደ አላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ዘንድ መጣና «በእኔ ዘንድ መልካም ጉድኝት የሚፈልገው ሰው ማን ነው?» በማለት ጠየቃቸው፡፡ እሳቸውም «እናትህ ነች በማለት መለሱለት፡፡ አሁንም ከርሷ በኃላ መልካም ጉድኝት የሚያስፈልገው ሰው ማን ነው?» በማለት ጠየቃቸው፡፡ እሳቸውም አሁንም በድጋሚ «እናትህ ነች» አሉት፡፡ ሰውዬውም ለሦስተኛ ጊዜ «ከርሷ በኋላ መልካም ጉድኝት የሚያስፈልገው ሰው ማን ነው?» በማለት ጠየቃቸው አሁንም « እናትህ ነች» በማለት መለሱለት፡፡

ለአራተኛ ጊዜ ሰውዬው «ከርሷ በኋላ መልካም ጉድኝት የሚያስፈልገው ሰው ማን ነው?» በማለት ጠየቃቸው፡፡ እሳቸውም በአራተኛው መልሳቸው ላይ «አባትህ ነው» በማለት መለሱለት፡፡»68 ምንም እንኳን አንዳንድ ቤተሰቦች

Page 106: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - zhic.aeኢስላም፣ ኢማን እና ኢሕሳን 3 አጠቃላይ እይታ 4 መግቢያ 6 የጉዞ መመሪያ 6 ለጉዞ

89ክፍል 4፡- መብቶች እና ኃላፊነቶች

የቤተሰባቸው አባል ወደ ኢስላም የመግባቱን ውሳኔ መጀመሪያ ላይ ቢቀበሉም የሚያስከትለውን የአኗኗር ዘይቤ ለውጥ ሲመለከቱ ግን ሁኔታውን መቀበል ያዳግታቸዋል፡፡

ስለሆነም ኢስላምን የተቀበለው ሰው መገለል፣ ጠብና ጥላቻን ሊያስተናግድ ይችላል፡፡እነዚህን ችግሮች ችሎ ለማለፍ በእርግጥ ትዕግስትንና ችሎታን ይጠይቃል፡፡

የነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ባልደረቦች (ሰሐባዎች) እስልምናን በመቀበላቸው ሳቢያ በወቅቱ ከቤተሰቦቻቸውና ከማህበረሰባቸው ከባድ ችግሮችና መከራዎች ደርሰውባቸው እንደነበረ በአዕምሯችን ውስጥ ማስቀመጥ አለብን፡፡ ለምሳሌ ሙሰዐብ ኢብኑ ዑመይር (ረ.ዐ)አዲሱን እምነቱን ባልወደደችው እናቱ ታስሮ ነበር፡፡ ቢላል ኢብን ረባሕን (ረ.ዐ) የመሰሉት ደግሞ እስልምናን በመቀበላቸው ከእምነታቸው እንዲመለሱ ተገርፈዋል፡፡ ነገር ግን ሁሉም የደረሰባቸውን መከራና ስቃይ አላህ መንገድ እስኪያደርግላቸው ድረስ በትዕግስት አሳልፈዋል፡፡ ኢስላምን የተቀበለው ሰው በሕይወቱ ያሳየውን ለውጥ ቤተሰቦቹ እንዲያስተውሉ ጊዜ ከተሰጣቸው በአብዛኛው ሁኔታዎችን በቅጡ ይገነዘባሉ፡፡

ምክር (ነሲሃ)

በሃይማኖት ጉዳይ ክርክርን አስወግድ፡፡ ለወላጆችህ

ጥሩነትህን ለማሳየት የተለየ ጥረት አድርግ፡፡ በኢስላማዊ

ሕይወትህ ውስጥ ያገኘሃቸውን መልካም ለውጦች

አሳያቸው፡፡ አላህን እንድታምጽ እስካላዘዙህ ድረስ ወላጆችህን

ታዘዛቸው፡፡

የጋብቻ ሱንና

የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ጋብቻ ያለውን

ጠቀሜታ የኢማን ግማሽ መሆኑን ከገለጹ በኋላ

እንዲህ ብለዋል፡- «ጋብቻ ፈለጌ (ሱንናዬ) ነው፡፡

ፈለጌን (ሱንናዬን) የሚወድ ሰው የእኔን ተምሳሌትነት

ይከተል፡፡»69አላህ እንዲህ ብሏል፡-

ለናንተም ከነፍሶቻችሁ (ከጎሶቻችሁ) ሚስቶችን

ወደነርሱ ትረኩ ዘንድ መፍጠሩ፤ በመካከላችሁም

ፍቅርንና እዝነትን ማድረጉ ከአስደናቂ ምልክቶቹ

ነው፤ በዚህ ውስጥ ለሚያስተውሉ ሕዝቦች ተአምራት

አልሉ፡፡(አር ሩም፡ 21)

አላህ ወንዶችና ሴቶች አንዳችው ለሌኛቸው ልክ

እንደልብስ እንደሆኑ ገልጿል፡፡ ስለዚህ ባልና ሚስት

አንዱ የሌላውን ድክመትና ጥፋት በተቻላቸው አቅም

መደበቅ (መሸፈን) ይኖርባቸዋል፡፡ እርስበርሳቸው

በመከባበርና በመልካም ጸባይ መኗኗርም አለባቸው፡፡

ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- "መልካም አማኝ

ማለት ለቤተሰቦቹ መልካምና ቅን የሆነ ሰው ነው፡፡"70

የጋብቻ መብቶችና ግዴታዎች

ባሎች የቤተሰባቸውን ገንዘብ ነክ ጉዳዮች የመሸፈንና

የመርዳት፤ በአንፃሩ ሚስቶች ባሎቻቸው ያመጡትን

ገንዘብና ንብረት በአግባቡ የመጠበቅና የመንከባከብ

ግዴታ አለባቸው፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለም ሁለቱም

ወገኖች (ባልና ሚስት) የቤተሰባቸውን ፍላጎቶች

ዘወትር ግንዛቤ ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡

ባሎች በተለይ ቤት ውስጥ ያሉትን ሰዎች በሙሉ

መርዳትና በአደራ የወሰዷቸውን ሚስቶቻቸውን

በሚገባ ሊንከባከቧቸው ግዴታ አለባቸው፡፡

ምንም እንኳን በመለኮታዊው ሕግ ፊት ወንዶችና

ሴቶች እኩል ቢሆኑም ጋብቻ ከዚያም ርቆ ፍቅር

የተሞላበትና ዘላቂ ይሆን ዘንድ ባልና ሚስት ሃይማኖታዊ

ኃላፊነቶቻቸውን ሊወጡ ይገባል፡፡ የአላህ መልዕክተኛ

(ሰ.ዐ.ወ) ቤታቸው ውስጥ ባሉ እንቅስቃሴዎች

ተሳታፊ ነበሩ፡፡ በቤት ውስጥ ቤተሰቦቻቸውን ይረዱ

ሚስቶቻቸውንም ያግዙ ነበር፡፡ የመጀመሪያ ሚስታቸው

በአስራ አምስት ዓመታት የሚበልጧቸው ኸዲጃ

(ረ.ዐ) ነበሩ፡፡ ከእሳቸው ጋር በቆዩባቸው ጊዜያት ብዙ

ከአማኞች መካከል ምሉእ የሆነ እምነት ያለው ማለት መልካም ሥነ-ምግባር ያለውና ጥሩ የሆነ ነው፡፡ —ነቢዩ ሙሐመድ(ሰ.ዐ.ወ) “

Page 107: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - zhic.aeኢስላም፣ ኢማን እና ኢሕሳን 3 አጠቃላይ እይታ 4 መግቢያ 6 የጉዞ መመሪያ 6 ለጉዞ

መለኮታዊው መንገድ፡-የአዲስ ሙስሊሞች ስርዓተ ትምህርት90

ምክራቸውን ይለግሷቸው ዘንድ ይጠይቋቸው ነበር፡፡ ኸዲጃ

(ረ.ዐ) የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) መልዕክታቸውን

ለማድረስ በሚንቀሳቀሱበት ወቅት ከመካ ጣኦታዊያን

ይደርሱባቸው የነበሩትን ጥቃቶች ይከላከሉላቸው ነበር፡፡

ጋብቻ ለመመስረት የሚያስፈልግ ምክር

እስልምናን የተቀበሉ ሰዎች ጋብቻ ከመመስረታቸው

በፊት ትንሽ ጊዜ ቢቆዩ ይመረጣል፡፡ ጋብቻ ውስጥ ገብተው

የጋብቻን ግዴታና የተወሳሰቡ ኃላፊነቶች ከመሸከማቸው

በፊት እንደሙስሊም የጀመሩትን አዲስ ሕይወት በቅጡ

ሊለማመዱት ይገባል፡፡ እስልምናን የተቀበሉ ሴቶች ደግሞ

በተለይ ወደ ጋብቻ ከማምራታቸው በፊት አስፈላጊውን

ጥንቃቄ ሊወስዱ ይገባል፡፡

የቀረበላቸውን የጋብቻ ጥያቄ ካለምንም ቅድመ ግንዛቤ

በችኮላ መቀበል የለባቸውም፡፡ ምክንያቱም ኢስላማዊ

ማህበረሰብ እንደማንኛውም ማህበረሰብ በውስጡ

የሃይማኖት ግንዛቤ ደረጃቸው የተለያየ ግለሰቦችን

ያቀፈ ነውና፡፡

በተወሰኑ አጋጣሚዎች ኢስላምን የተቀበሉ ሰዎች

ቀደም ሲል ጋብቻ የመሠረቱና ተጓዳኞቻቸው እስልምናን

ያልተቀበሉ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ይህ መሰሉ ሁኔታና አጋጣሚ

እጅግ አሳሳቢ በመሆኑ ጥበብ የተላበሰ አያያዝና ተገቢ

ጥንቃቄ ሊሰጠው ይገባል፡፡

የሁሉም ሰዎች ሁኔታዎች እንደየሰዎቹ ይለያያሉ፡፡ (በተለይ

በጋብቻው ውስጥ ልጆች የተወለዱ ከሆነ) ለተጨማሪ

ምክር በዘርፉ ባለሙያ የሆኑትንና እውቀት ያላቸውን

ሰዎች መቅረቡ አስፈላጊ ነው፡፡እንደ አጠቃላይ በወንዶች

እና በሴቶች መካከል የሚኖረውን ግንኙነት በተመለከተ

ኢስላም መካከለኛ የሆነ እይታ አለው፡፡

መለኮታዊው ሕግ የሰዎችን ሃይማኖትና ክብር በጋብቻ

ተቀዳሚ ሕይወትና በቤተሰብ ምስረታ የመጠበቅ ዓላማ

አለው፡፡ ስለዚህ በሰዎች መካከል የሚኖረው ግንኙነት

በጋብቻና በቤተሰባዊ ትስስር የተማከለ እንዲሆን ይሻል፡፡

ተቃራኒ ፆታ ሆኖ ጋብቻ መፈፀም የማይችል ሰው

‘መሕረም’ ሲባል ጋብቻ ሊፈጽም የሚችል ሰው ደግሞ

‘መሕረም ያልሆነ’ በመባል ይታወቃል፡፡

ከእናንተ መካከል ምሉእ የሆነ ኢማን ያለው ማለት መልካም ስነ- ምግባር ያለው ሰው ነው፡፡ እንዲሁም ከእናንተ መካከል መልካም ማለት ለቤተሰቦቹ መልካም የሆነ ነው፡፡ —ነቢዩ ሙሐመድ(ሶ.ዐ.ወ)

Page 108: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - zhic.aeኢስላም፣ ኢማን እና ኢሕሳን 3 አጠቃላይ እይታ 4 መግቢያ 6 የጉዞ መመሪያ 6 ለጉዞ

91ክፍል 4፡- መብቶች እና ኃላፊነቶች

ከእነርሱ ጋር ጋብቻ እንዳይፈጽም በወንዱ ላይ ክልክል የሆኑ ሴቶች

ከእነርሱጋር ጋብቻእንዳትፈጽም በሴቷ ላይ ክልክል የሆኑ ወንዶች

﴾እናት﴾አያትና ከዚያ በላይ ﴾ሴት ልጅ﴾የሴት ልጅ ልጅና ከዚያ በታች﴾እህት ﴾የእህት ወይም የወንድም ሴት ልጆች﴾አክስት ﴾አማት (የሚስት እናት)﴾የአማት እናት ﴾የአባት ሚስት(የእንጀራ እናት)﴾የወንድ ልጅ ሚስት

አባት አያትና ከዚያ በላይወንድ ልጅየወንድ ልጅ ልጅና ከዚያ በታች ወንድምየእህት ወይም የወንድም ወንድ ልጆችአጎት አማት (የባል አባት) የአማት አባት የእናት ባል (የእንጀራ አባት)የሴት ልጅ ባል

መሕረም የሚባሉት ልጅና ወላጆች እንዲሁም ቅርበት

ያለው የስጋ ግንኑነት ያላቸው ሰዎች ናቸው፡፡ ‘መሕረም

ካልሆነ’ ሰው ጋር የሚኖር ግንኙነትን በተመለከተ

ጨዋነት የተላበሰና መልካም ሥነ ምግባር የሚንፀባረቅበት

መሆን አለበት፡፡

ከጋብቻ ውጭ የሚኖር ማንኛውም ዓይነት ቅርርብ

ለምሳሌ መቀጣጠር፣ አካላዊ ንክኪ ከሰው ተገልሎ

ለብቻ መቀመጥ ፈጽሞ የማይፈቀድ ጉዳይ ነው፡፡

የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) "አንድ ወንድና ሴት

ብቻቸውን አይሆኑም ሦስተኛው ሰይጣን ቢሆን እንጂ»

ብለዋል፡፡ አላህ እንዲህ ይላል፡-

ለምእመናን ንገራቸው፡- ዓይኖቻቸውን (ያልተፈቀደን

ከማየት) ይከልክሉ፤ ብልቶቻቸውንም ይጠብቁ፤

ይህ ለነሱ የተሻለ ነው አላህ በሚሠሩት ሁሉ ውስጠ

ዐዋቂ ነው፡፡ ለምእመናትም ንገራቸው፡- ዓይኖቻቸውን

ይከልክሉ፤ ብልቶቻቸውንም ይጠብቁ፤ ጌጣቸውንም

ከርሷ ግልጽ ከሆነው በስተቀር አይግለጡ፤

(አን ኑር፡ 31-32)

ምክር (ነሲሃ)

የጋብቻን ኃላፊነቶችና ግዴታዎች በደንብ እውቅ፡፡ አዲስ ወደ

እስልምና የገባሽ ከሆንሽ ለጋብቻ የምትመርጪው ወንድ

ምን ዓይነት መሆን እንዳለበት ለመወሰን እውቀት ያላቸው

አማካሪዎች ይኑሩሽ፡፡ አዲስ ወደ እስልምና የገባህ ከሆንክ

ለጋብቻ የምትመርጣትን ሴት ወኪሎች በሚገባ ቅረባቸው፡፡

ልጆች

ልጆች የማፍራት ዕድል ያገኙ ሁሉ በወላጅነታቸው

የተጣሉባቸውን ኃላፊነቶች ጠንቅቀው ሊያውቁ

ይገባል፡፡ ወንድም ሆኑ ሴት ሕፃናት የመማርና ግዴታ የሆኑ

ሃይማኖታዊ እውቀቶችን የማግኘት መብቶች አሏቸው፡፡

እነዚህን መብቶች በማሟላት ጤናማ ግንኙነት ያለው

ማህበረሰብ ሊያስገኙ የሚችሉ ሲሆን ለዚህ ድርጊታቸው

ምንዳ ያገኛሉ፡፡

የአላህ ነቢይ (ሰ.ዐ.ወ) ሰዎች ከሚጠብቋቸው ነገሮች

እንደሚጠየቁ ሲናገሩ እንዲህ ብለዋል፡- «ሁላችሁም

እረኞች ናችሁ፤ ከምትጠብቁት ነገር ትጠየቃላችሁ፡፡»72

የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) የልጆችን ፍላጎት በጣም

ለናንተም ከነፍሶቻችሁ (ከጎሶቻችሁ) ሚስቶችን ወደነርሱ ትረኩ ዘንድ መፍጠሩ፤ በመካከላችሁም ፍቅርንና እዝነ ትን ማድረጉ ከአስደናቂ ምልክቶቹ ነው፤ በዚህ ውስጥ ለሚያስተውሉ ሕዝቦች ተአምራት አልሉ፡፡

—(አር ሩም፡- 21) “

Page 109: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - zhic.aeኢስላም፣ ኢማን እና ኢሕሳን 3 አጠቃላይ እይታ 4 መግቢያ 6 የጉዞ መመሪያ 6 ለጉዞ

መለኮታዊው መንገድ፡-የአዲስ ሙስሊሞች ስርዓተ ትምህርት92

ይገነዘቡ ነበር፡፡ ስለሆነም በሕብረት የሚሰገድ ሶላትን

በመምራት ላይ እያሉ የሕፃን ልጅ ለቅሶ ከሰሙ እናትዬዋ

ሕፃኑን ታባብለው ዘንድ ሶላቱን ያሳጥሩት (ያፋጥኑት)

ነበር፡፡በአንድ ወቅት አንድ ሰው ወደ አላህ መልዕክተኛ

(ሰ.ዐ.ወ) ዘንድ መጣና «እኔ አስር ልጆች አሉኝ፤

ከአስሩ መካከል አንዱንም ስሜ አላውቅም»

አላቸው፡፡ እርሳቸውም «የማያዝን አላህ አያዝንለትም»

አሉት፡፡73

ምክር (ነሲሃ)

ለሚስትህ አዛኝ ትሁትና ደግ ሁንላት፡፡ ልጆችህ

አንተን እንደሚመለከቱህ አስተውል፡፡ ስለዚህ ጥሩ፣

እርጋታ የሰፈነብህና አፍቃሪ አባት ሁን፡፡ እነርሱ አንተ

የምትወክለውን ማንኛውንም ነገር (ሃይማኖትህን ጭምር)

ይወዳሉና፡፡ ለልጆችህ ደህንነት አሳቢነትን አሳይ፡፡ ያኔ

ልጆችህ ያንተን ትኩረት ለማግኘት ሲጥሩ ታስተውላለህ፡፡

ትህትና በአንዳች ነገር ላይ መልካምነት እንጂ ሌላ አያመጣም፡፡ ከርሱ ከጠፋ ደግሞ መጥፎነትን ቢያመጣ እንጂ ሌላ አያመጣም፡፡ —ነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)“

Page 110: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - zhic.aeኢስላም፣ ኢማን እና ኢሕሳን 3 አጠቃላይ እይታ 4 መግቢያ 6 የጉዞ መመሪያ 6 ለጉዞ

93ክፍል 4፡- መብቶች እና ኃላፊነቶች

የአማኞች ማሕበረሰብ 22

የሙስሊም ክብር

በእምነት የመተሳሰር ገመድ ውስጥ እስካሉ ድረስ

አማኝ የሆነ ሰው ሁሉ በሌሎች ላይ የተወሰኑ መብቶች

ያሉት ሲሆን እንዲሁም የሌሎችን መብቶች የማክበር

ኃላፊነትም አለበት፡፡

የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) አንድ ሙስሊም

በወንድሙ ላይ ስድስት መሠረታዊ መብቶች እንዳሉት

ሲናገሩ እንዲህ ብለዋል «አንድ ሙስሊም በሌላው

ሙስሊም ላይ ስድስት መብቶች አሉት፡፡

እነርሱም፡- ሲታመም ሊጠይቀው፣ ከሞተ አስከሬኑን

ሊሸኝ፣ ከጋበዘው ግብዣውን ሊቀበለው፣ ባገኘው ጊዜ

ሰላምታ ሊያቀርብለት፣ ካስነጠሰና አላህን ካመሰገነ

በኋላ የአላህን እዝነት ሊጠይቅለትና እርሱ ባለበትም ሆነ

በሌለበት ቦታ ስለርሡ እውነተኛ ነገር ሊናገርለት፡፡74

የአላህ ነቢይ (ሰ.ዐ.ወ) የሙስሊም ክብር ምን ያህል

ትልቅ እንደሆነ ሲገልጹ እንዲህ ብለዋል፡- “አንድ

ሙስሊም በሌላው ሙስሊም ወንድሙ ላይ፤ ደሙ፣

ንብረቱና ክብሩ ፍጹም ክልክል ነው፡፡” «አንድ

ሙስሊም የሌላው ሙስሊም ወንድሙን ደም ንብረትና

ክብሩን አይድፈር፡፡»75 በተጨማሪም ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ)

«ሙስሊም ማለት ሰዎች ከእጁና ከምላሱ የተጠበቁለት

ሰው ነው»76 ብለዋል፡፡

የአላህ ነብይ (ሰ.ዐ.ወ) ሙስሊሞች አንዱ ሌላውን

እንዳይጎዳና የጥላቻን ዘር በመካከላቸው እንዳይዘሩ

ሲያስጠነቅቁ እንዲህ ብለዋል፡

“የስለላ ተግባር አንዳችሁ በሌላችሁ ላይ አትፈጽሙ፡፡ አንደኛው

በሌለበት ሌላኛው አንዳችሁ አንዳችሁን አይማ፣

አትጨራረቱ፣ እናንተ አማኞች ሆይ! ሙስሊሞች

ወንድማማቾች ናቸው፡፡ስለዚህ አይበድለው፣ አሳንሶም አይመልከተው፣ አይዋሸው፣ አያታለውም፡፡ ፍራቻ እዚህ ላይ ነው (አሉና ወደ ልባቸው ሦስት ጊዜ

አመላከቱ) ከዚያም አንድ ሙስሊም ወንድሙን ማዋረድ ለወንጀል በቂው ነው፡፡” 77 አሉ፡፡

የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ወደ መዲና ከተሰደዱ በኋላ ሙስሊሞች አንድ እንዲሆኑ ይመኙ ነበር፡፡ በዚህም የተነሳ በቅድሚያ ተግባራዊ ያደረጉት ነገር በመካ ሙስሊሞችና በመዲና ነዋሪ ሙስሊሞች መካከል የወንድማማችነትን ትስስር መፍጠር ነበር፡፡

ከሌሎች ሙስሊሞች ጋር መወያየት

በመጀመሪያ ቀድሞውኑ ከማታውቀው ኢስላማዊ

ማኅበረሰብ ጋር ተቀላቅሎ መኖር በእጅጉ ሊከብድህ

ይችላል፡፡ ነገር ግን በአእምሮህ መቀመጥ ያለበት ነጥብ

ሙስሊሙ ማኅበረሰብ ከተለያዩ ባሕሎችና ማእዘናት

በመውጣጣት የተመሠረተ መሆኑን ነው፡፡

በኢስላም የዘርም ሆነ የባሕል መድልኦና ልዩነት የለም፡፡

ስለሆነም በውስጡ እስካለህ ድረስ አንተም እንደሌላው

ሙስሊም የማሕበረሰቡ (ኡማው) አባል ነህ፡፡

የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) በርግጥ የተላኩት

ለሰው ልጆች በአጠቃላይ ነው፡፡ ስለዚህ የራስህን የባሕል

ውርስ ቋንቋ እና የዘር ሐረግህን ወደኋላ መተው

አይጠበቅብህም፡፡አላህ እንዲህ ይላል፡-

እናንተ ሰዎች ሆይ! እኛ ከወንድና ከሴት ፈጠርናችሁ፤

እንድትተዋወቁም ጎሳዎችና ነገዶች አደረግናችሁ፤

አላህ ዘንድ በላጫችሁ፥ በጣም አላህን ፈሪያችሁ ነው፤

አላህ ግልጽን ዐዋቂ፥ ውስጥንም ዐዋቂ ነው፡፡ (አል-

ሑጁራት፡ 13)

እነዚህን ቀላልና የተለመዱ የሥነ ምግባር መገለጫዎች

በመደንገግ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ማንኛውም ሙስሊም

በሌላው ወንድሙ ላይ ስህተት እንዳይፈጽም

አስተምረዋል፡፡

Page 111: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - zhic.aeኢስላም፣ ኢማን እና ኢሕሳን 3 አጠቃላይ እይታ 4 መግቢያ 6 የጉዞ መመሪያ 6 ለጉዞ

መለኮታዊው መንገድ፡-የአዲስ ሙስሊሞች ስርዓተ ትምህርት94

የተለያዩ ባሕሎችና ልማዶች መልካም እስከሆኑና

የኢስላምን መሠረታዊ ሃሳቦች እስካልተቃረኑ ድረስ

ኢስላም ፈጽሞ አያጠፋቸውም፤ አያወግዛቸውምም፡፡

ኢስላማዊ መነቃቃት ያላቸውን ሰዎች ልታገኝና ያንተ

ኢስላምን መቀበል የፈጠረባቸውን ጉጉት ልታስተውል

ትችላለህ፡፡ እነዚህ ሰዎችም ካላቸው ፍላጎት የተነሳ

የማይገባ ምክር ይሰጡህ ይሆናል፡፡ ምናልባትም ይህ

ምክራቸውም አንተ ካለህበት የተለየ ሁኔታ ጋር ፈጽሞ

የማይጣጣም ሊሆንም ይችላል፡፡

በተጨማሪም የምክር ጋጋታ ምናልባት ግርታንና ፍርሃትን

ሊፈጥር ይችላል፡፡ አንተ ግን በዘዴና በሚያምር አኳኋን

ይህን ሁኔታ ለመጋፈጥ ራስህን አዘጋጅ፡፡

በሙስሊሞች መካከል ያለውን ትስስር ማጠናከር

የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡-

“ማናችሁም በርግጥ አላመነም ለራሱ የሚወደውን ነገር

ለወንድሙ እስካልወደደ ድረስ፡፡”78 ለሌሎች እገዛዎችን

ማድረግና በችሮታ መንፈስ መቀራረብ በመካከላችን

ያለውን የወንድማማችነትና የእህትማማችነት ትስስር

ይበልጥ ያጠናክራል፡፡የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ)

ምንም የዘር፣ የቀለምና የባሕል ልዩነት ሳይፈጠር አማኞች

ሰላምታ እንዲለዋወጡ አስተምረዋል፡፡ እንዲሁም ስጦታ

እንዲሰጣጡ መክረዋል፡፡ እነዚህ እንቅስቃሴዎች በሙሉ

በሰዎች መካከል ያለውን ፍቅር ይበልጥ ያጠናክራሉ፡፡

ከዚህ ሌላ አንዳችን ሌላኛችንን ለአላህ ስንል

እንድንጠይቅ ጉብኝቱም ቀላል እንዲሆንና ብዙ

በመቀመጥ ለአስተናጋጃችን የሚከብድ መሆን

እንደሌለበት ተነግሮናል፡፡ በሌላ በኩል የሚጎበኙ

ሰዎች የእንግዳቸውን ፍላጎት እንዲያዳምጡና ቆይታው

መልካምና የሚያስደስት እንዲሆን የቻሉትን ሁሉ

እንዲያደርጉ ይመከራሉ፡፡

ምክር (ነሲሃ)

‘አስ-ሰላሙ ዐለይኩም’ በሚለው ሰላምታ ለመጀመር

ሁልጊዜ ቀዳሚ ሁን፡፡

ማንንም ቢሆን በጥርጣሬ አትመልከት፡፡ ከዚያ ይልቅ ነገሮች

ግልጽ እስኪሆኑ ድረስ ተጠባበቅ፡፡ ለአላህ ብለህና ከአላህ

መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ጋር ባላቸው ግንኙነት ምክንያት

ብቻ ሰዎችን ውደድ፡፡

እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በትክክል (ፍትሕ) ቀዋሚዎች በነፍሶቻችሁ ወይም በወላጆች ወይም በቅርብ ዘመዶች ላይ ቢኾንም እንኳ ለአላህ መስካሪዎች ኹኑ፡፡ — አን-ኒሳእ፡- 135

Page 112: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - zhic.aeኢስላም፣ ኢማን እና ኢሕሳን 3 አጠቃላይ እይታ 4 መግቢያ 6 የጉዞ መመሪያ 6 ለጉዞ

95ክፍል 4፡- መብቶች እና ኃላፊነቶች

ማሕበራዊና ሕዝባዊ ግዴታዎች23

ሙስሊም ባልሆነ ማኅበረሰብ መካከል መኖር

የሙስሊሙ ማኅበረሰብ አባል ከመሆን በተጨማሪ አዲስ ወደ እስልምና የገቡ ሰዎች በሚኖሩበት ሰፊ ማኅበረሰብ ውስጥ ያላቸውን ተሳትፎ መቀጠል አለባቸው፡፡ ምንም እንኳን መጀመሪያ ላይ ሙስሊም ባልሆኑ ወገኖች መካከል መኖር ግርታን ሊፈጥር ቢችልም እንኳ አላህ ከማኅበረሰቡ እንዲርቁ ወይም እንዲገለሉ አይፈልግም፡፡

እንዲያውም ሙስሊሞች ከዚህ በተቃራኒ ገለልተኛነትን ማስወገድና ማሕበራዊ መስተጋብራቸውን ማጠናከር አለባቸው፡፡ የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ነቢያዊ መልዕክትን ማስተላለፍ ከመጀመራቸው በፊት ከመካዊያን ማኅበረሰቦች ጋር ማለፊያ ግንኙነት ነበራቸው፡፡ በአንድ አጋጣሚ ለተጨቋኞች ፍትሕ ይኖር ዘንድ በተደረገ ንቅናቄ ተሳትፈዋል፡፡ በሌላ አጋጣሚ ደግሞ ከዕባን እንደገና በመገንባቱ እንቅስቃሴና ጥቁሩን ድንጋይ በተገቢው ስፍራ ላይ በማስቀመጡ ሂደት ላይ ጉልህ ሚና ተጫውተዋል፡፡

የኢስላምን ጥሪ ማሰራጨት ከጀመሩ በኋላ እንኳ የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እና ባልደረቦቻቸው ሙስሊም ካልሆኑ ወገኖች ጋር በንግድና ማኅበራዊ ጉዳዮች ይገናኙ ነበር፡፡ የነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ሚስት የነበሩት ኸዲጃ (ረ.ዐ) የታወቁ ነጋዴ ነበሩ፡፡ አቡበክርም (ረ.ዐ) ሆኑ ራሳቸው የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ነጋዴዎች ነበሩ፡፡ በዚህም ተግባራቸው ሙስሊም ካልሆኑ ወገኖች ጋር የንግድ ትስስር ነበራቸው፡፡

የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) በተከታዮቻቸው ላይ ችግርና ስቃይ ሲደርስባቸው የተወሰኑ ባልደረባዎቻቸውን ወደ ክርስቲያኗ አቢሲኒያ(የአሁኗ ኢትዮጵያ) ልከዋቸዋል፡፡ በዚያ ክርስቲያን ንጉሥ በሚያስተዳድረው መንግሥት መጠጊያና ፍትህን አግኝተውም ነበር፡፡ በጊዜው እንዲያውም ንጉሡ በውስጣዊ ሽኩቻ ላይ በነበረበት ጊዜ በጠላቶቹ ላይ ድል እንዲቀዳጅ ሙስሊሞቹ ጸልየዋል፡፡79 ለእነርሡ ሃይማኖታቸውን

በመጠበቅና ከሌሎች ሃይማኖት ተከታዮች ጋር በመስማማት መካከል ተቃርኖ አልነበረም፡፡

እንደዜጋ ማናችንም በርካታ መብቶችንና ጥቅሞችን እናገኛለን፡፡ ጤናና ትምህርትን ጨምሮ የተለያዩ የተፈጥሮ ሃብቶችንና የሕዝብ መሠረተ ልማቶችን በብዙ መልኩ እንገለገልባቸዋለን፡፡

አንድ ሰው ከማኅበረሰቡ ብዙ ነገሮችን እያገኘ ከራሱ ምንም የማይሰጥ ከሆነ የራስ ወዳድነትና የምስጋና ቢስነት መገለጫ ምልክት ነው፡፡ የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡-

“ሰዎችን የማያመሰግን አላህን ፈጽሞ አያመሰግንም፡፡”80

በእርግጥ አንድ ግለሰብ ከማኅበረሰቡ ጋር የማይስማማባቸው ሁኔታዎች ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ ይህም ቢሆን ሁላችንም እንደ ሙስሊም ለማኀበረሰባችንና ለዜጎቻችን ያሉብንን ኃላፊነቶች የሃይማኖት ልዩነት ሳያግደን መወጣት ይኖርብናል፡፡

የመተናነስና የትህትና በሕሪያቶችን በማጎልበት ኩራትንና ጥላቻን ማስወገድም ይጠበቅብናል፡፡ እናም በእርጋታና በማሳመር (ኢህሳን) ሌሎችን መጥቀም የእኛ ድርሻ ነው፡፡ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) «ከሰዎች ሁሉ በላጩ ሌሎች የሚጠቃቀሙበት ነው» ብለዋል፡፡”81

ከሌላ እምነት ተከታዮች ጋር የሚኖረን መስተጋብር

በኢስላም ሕይወት ውስጥ ያሉ ሁሉ ከሁሉም እምነት ተከታዮች ጋር ጥሩ ግንኙነት ይኖራቸው ዘንድ ይበረታታሉ፡፡ እነዚህ ሰዎች ዘመዶቻቸው፣ ጎረቤቶቻቸው፣ የሥራ ባልደረቦቻቸው፣ የቀድሞ ጓደኞቻቸውና ሌሎች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡-

“በአላህና በመጨረሻው ቀን የሚያምን መልካም ነገርን ይናገር ወይም ዝም ይበል፡፡ በአላህና በመጨረሻው ቀን የሚያምን ለጎረቤቱ መልካምን ይዋል፡፡ በአላህና በመጨረሻዋ ቀን የሚያምን እንግዳውን ያክብር፡፡”82

Page 113: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - zhic.aeኢስላም፣ ኢማን እና ኢሕሳን 3 አጠቃላይ እይታ 4 መግቢያ 6 የጉዞ መመሪያ 6 ለጉዞ

መለኮታዊው መንገድ፡-የአዲስ ሙስሊሞች ስርዓተ ትምህርት96

“ከመካከላችሁ አንዳችሁም አላመነም ለራሱ የሚወደውን ለወንድሙ እስካልወደደ ድረስ” የሚለውን የነቢዩን (ሰ.ዐ.ወ) ንግግር በተመለከተ ኢማም አን-ነወዊይን የመሳሰሉ በርካታ ምሁራን “ወንድሙ” የሚለው ቃል ሰፊ የሆነውን ሰብአዊ ወንድማማችነት ያጠቃልላል ብለዋል፡፡

ለሌሎች ሃይማኖት ተከታዮች መልካምን መመኘት፣ በትህትናና በአክብሮት መቅረብ፣ በዚህም አስታክከን የኢስላምን ሥነ ምግባር ውበት ማንጸባረቅ አስፈላጊ ነው፡፡ከሌላ እምነት ተከታዮች ጋር በምናደርገው መቀራረብ፣ እነርሱን ወደቤታችን መጋበዝና እኛም የእነርሱንም ግብዣ መቀበል ተቀባይነት ያለው ተግባር ነው፡፡ የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) የሚኗኗሯቸውን የሌላ እምነት ተከታዮች ከመጎብኘት አልፈው ለጥቂት ጊዜያት (ቀናት) ካላዩዋቸው የጤንነት ሁኔታቸውን ይጠይቁ ነበር፡፡ መዲና ውስጥ ሳሉ ከአይሁዳውያን ጋር በጉርብትና ይኖሩ የነበረ ሲሆን አንድ ቀን አንድ ወጣት ልጅ ታሞ ሄደው በመጠየቅ አጽናንተውታል፡፡

ኢስላምን ከመቀበልህ በፊት ጓደኞችህ የነበሩና ሙስሊም ያልሆኑ ሰዎች ጋር የነበረህ ግንኙነት በአዲሱ እምነትህና የሕይወት ዘይቤህ ምክንያት ተለውጦ ይሆናል፡፡ ይሁን እንጂ እነዚያ ጓደኞችህ ባንተ ላይ የተወሰነ መብት ያላቸው እንደመሆኑ ጨርሶ ልታርቃቸው አይገባም፡፡

ከዚያ ይልቅ በአዲሱ እምነትህ ምክንያት ልትቀጥላቸው የማትችላቸው አንዳንድ የተከለከሉ ድርጊቶች ሊኖሩ ስለሚችሉ በርጋታና ብልህነት በተሞላበት ሁኔታ ቀስ በቀስ ግንኙነትህን ማላላት ነው የሚኖርብህ፡፡

የብዘሃነት ጥበብ የተለያዩ እምነቶችን የሚከተሉ ሕዝቦች ባሉበት ማሕበረሰብ ስንኖር ልዩነቶችን ማስተናገዳችን ግድ ነው፡፡ በዕለት ተዕለት መስተጋብር የተለያየ ዘር፣ ቋንቋ ሃይማኖትና ማሕበራዊ ደረጃ ካላቸው ሰዎች ጋር እንገናኛለን፡፡ ይህን ልዩነት የግጭትና የክፍፍል መነሻ ከማድረግ ይልቅ የአላህ መገለጫ ውበት አድርገን መቀበል ይኖርብናል፡፡ አላህ እንዲህ ይላል፡-

ሰማያትና ምድርንም መፍጠሩ፣ የቋንቋዎቻችሁ የመልኮቻችሁም መለያየት ከአስደናቂ ምልክቶቹ ነው፡፡ በዚህ ውስጥ ለዐዋቂዎች ተዓምራቶች አሉበት፡፡(አር ሩም፡22)

አላህን የሚፈሩ ሰዎች በሰብዓዊ ፍጡራን ላይ ምንም ዓይነት ጥላቻ የላቸውም፡፡ በእምነታቸው እርግጠኞች ከመሆናቸውም በላይ የፈጣሪያቸውን ውለታ ለመግለጽ ለሁሉም የሰው ዘር ችሮታቸውን ያሳያሉ፡፡

ምክር (ነሲሃ)

ለምድራዊ ሕግጋት (ደንቦች) ታዛዣ ሁን፡፡ ምክንያቱም

አንተ የኢስላም አምባሳደር መሆንህን አስታውስ፡፡

ሁልጊዜም ክብርህን ጠብቅ፡፡ ራስን ማክበርህ ከመልካም

ፀባይ መካከል አንዱ ነውና፡፡ ፍሬ ቢስ ለሆኑ ክርክሮች ቦታ

አትስጥ፡፡ ማሕበረሰብህን የተበተቡትን ማሕበራዊና ምጣኔ

ሃብታዊ ችግሮች ለመለወጥ ትጋ፡፡

ከእነዚያ በሃይማኖት ካልተጋደሏችሁ. ከአገሮቻችሁም ካላወጡዋችሁ (ከሓዲዎች)መልካም ብትውሉላቸውና ወደነርሱ ብታስተካክሉ አላህ አይከለክላችሁም፤ አላህ ትክክለኞችን ይወዳልና፡፡ —(አል-ሙምተሒናህ፡- 8)“

Page 114: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - zhic.aeኢስላም፣ ኢማን እና ኢሕሳን 3 አጠቃላይ እይታ 4 መግቢያ 6 የጉዞ መመሪያ 6 ለጉዞ

97

Page 115: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - zhic.aeኢስላም፣ ኢማን እና ኢሕሳን 3 አጠቃላይ እይታ 4 መግቢያ 6 የጉዞ መመሪያ 6 ለጉዞ

መለኮታዊው መንገድ፡-የአዲስ ሙስሊሞች ስርዓተ ትምህርት98

ገንዘብ ነክ ግንኙነቶች24

የአላህን ችሮታ መፈለግየማህበረሰቡ ልማድ እንደመሆናቸው ሙስሊሞች ሲሳያቸውን ለመፈለግ ይንቀሳቀሳሉ፡፡ ይህንንም የሚያደርጉት በፈጣሪያቸው ያላቸውን መመካት እንደያዙ ከትሩፋቱ በመፈለግና ምጣኔ ሃብታቸውን ለማደላደል ነው፡፡አላህ እንዲህ ይላል፡-

ከችሮታውም ሌሊትንና ቀንን በውስጡ ልታርፉበት ከትሩፋቱም ልትፈልጉበት አመስጋኞችም ልትሆኑ አደረገላችሁ፡፡ (አል ቀሰስ፡ 73)

ሌሎችን ማገዝትክክለኛ የሆነ እሳቤ (ኒያ) በልባችን ይዘን በመንቀሳቀስና ሲሳያችንን በመፈለግ ራሳችንንና ቤተሰባችንን መደገፍ ከቻልን ይህ በራሱ እንደ አምልኮት ተግባር (ኢባዳ) ይቆጠርልናል፡፡ምንም እንኳን ቤተሰቡን የማስተዳደር ሙሉ ኃላፊነት የሚወድቀው በአባዋራው ጫንቃ ላይ ቢሆንም ሁለቱም ተጓዳኞች ቤተሰባቸውን ለመደገፍ ባላቸው እሳቤ (ኒያ) ልክ ምንዳ ያገኛሉ፡፡

ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ይላሉ፡-«ማንኛውንም ወጪ አታወጣም ባወጣኸው ወጪ የተመነዳህ ካልሆነ በስተቀር፡፡ በሚስትህ አፍ ውስጥ የምታስገባው ጉርሻ እንኳ ሳይቀር፡፡» 83

ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) በተጨማሪ እንዲህ ብለዋል፡- «ራስህን የምትመግበው ነገር ሁሉ ላንተ ምጽዋት ነው፡፡ ልጅህን የምትመግበው ነገር ሁሉ ላንተ ምጽዋት ነው፡፡ እንዲሁም ሚስትን የምትመግባት ማንኛውም ነገር ሁሉ ላንተ ምጽዋት ነው፡፡»84

የሥራ ክቡርነት

ተገቢውን ተግባር አከናውኖ ገንዘብ በማግኘት ሕይወትን መምራት ክቡርና የታዘዝንበት ተግባር ነው፡፡ ይህም ሰውየው የሚያገኘው ገንዘብ በተፈቀደ (ሃላል) መንገድ እስከሆነ ድረስ የገንዘቡ መጠን ሰውየው በማሕበረሰቡ ውስጥ ያለው ደረጃ ግምት ውስጥ አይገባም፡፡ በኢስላም

በአላህ መመካት ትልቁ ሃብት ሲሆን ምስጋና ቢስ መሆን ደግሞ አሳፋሪ ተግባር ነው፡፡

ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡- «እስልምናን የተቀበለ ጥቂት የሚጠቃቀምበትን ሲሳይና ምጽዋት የሚሰጥና አላህ በለገሰው የማመስገንን ጸጋ አላህ የለገሰው የሆነ ሰው ነው፡፡" 85

ሃብት የተሰጣቸው ሰዎች አላህን ማመስገን ያለባቸው ሲሆን ከሰጣቸው ፀጋ የተወሰነውን ቆርሰው ለመለገስ ለውለታው እውቅና መስጠት አለባቸው፡፡ አላህ እንዲህ ይላል፡-

የመጸወቱ ወንዶችና የመጸወቱ ሴቶች ለአላህም መልካም ብድርን ያበደሩ ለእነርሡም መልካም ምንዳ አላቸው፡፡ (አል ሐዲድ፡ 18)

አላህ በሰጠው መብቃቃት ማለት አንድ ሰው ገቢ ለማግኘት ከመስረቅ፣ ከማጭበርበር፣ከምዝበራ እንዲሁም በመለኮታዊው ሕግ ክልክል ከሆኑ ነገሮች ሲሳዩን ከማግኘት መታቀብ ማለት ነው፡፡

አሠሪዎች እና ሠራተኛ

አሠሪዎችና ሠራተኞች ሊከተሏቸው የሚገቡ መብቶችና ኃላፊነቶች አሏቸው፡፡ ሠራተኞች ሥራቸውን በትጋት በመሥራት ግዴታቸውን መወጣት ያለባቸው ሲሆን ጥንቃቄና ማሳመር (ኢህሳን) ማንጸባረቅ አለባቸው፡፡ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፤ «ልዕልና የተገባው ጌታ አንዳች ተግባርን የፈጸመንና ተግባሩ ላይም ምሉዕነትን ያስከተለን ሰው ይወዳል፡፡» 86

አሠሪዎች ለሠራተኞቻቸው በሚያደርጉት አያያዝ ተጠያቂዎች ናቸው፡፡ እነርሡን በፍትሐዊነት የመያዝና ደሞዛቸውን ከማጭበርበር እንዲታቀቡም ታዘዋል፡፡ የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋ፡- «ለሠራተኛህ ላቡ ሳይደርቅ በፊት የሠራበትን ምንዳ ስጠው፡፡»87

Page 116: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - zhic.aeኢስላም፣ ኢማን እና ኢሕሳን 3 አጠቃላይ እይታ 4 መግቢያ 6 የጉዞ መመሪያ 6 ለጉዞ

99ክፍል 4፡- መብቶች እና ኃላፊነቶች

ብድር እና ወለድ

የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) አደራን በመጠበቅና የተበደሩትን ነገር በመመለስ ተግባር ላይ እጅግ በጣም ጥንቁቅ ነበሩ፡፡ በተለይ ከመካ ወደ መዲና ከመሰደዳቸው በፊት መካ ውስጥ ሰዎች እርሳቸው ዘንድ ይቀመጥላቸው ዘንድ በአደራ የሰጧቸውን ንብረቶች ሁሉንም ለባለቤቶቻቸው መልሰውላቸዋል፡፡ ከዚህም ሌላ የሕይወታቸው ፍጻሜ በተቃረበ ጊዜ እንኳ እዳዎቻቸው ሙሉ ለሙሉ መከፈላቸውን አረጋግጠው ነበር፡፡

ሌላው እጅግ በጣም ልዩ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባው ገንዘብ ነክ ጉዳይ ወለድ (አራጣ) ነው፡፡ ይኸውም ብድር ለማግኘት የሚከፈል የሆነ ተጨማሪ ክፍያ ነው፡፡ ወለድን መሠረት ያደረገ የገንዘብ ልውውጥ ብድር እንዲስፋፋ ከማበረታቱም በላይ ችግረኛ የሆኑ ሰዎችን መጠቀሚያ ያደርጋል፡፡

በኢስላም ገንዘብ ነክ ልውውጦች በጥንቃቄ ሊያዙና ለአበዳሪዎች፤ ለተበዳሪውና ለማህበረሰቡ በአጠቃላይ ጠቀሜታን ሊያስገኙ የሚችሉ መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡ አንድ ሰው የራሱን የገንዘብ አወጣጥ በመገምገምና የጊዜውን የፈጂነት (Consumerism) ዝንባሌንና ቁሳዊነትን በመቋቋም በወለድ መበደርን

ሊያቆም ይችላል፡፡ በኢስላማዊው መንገድ ላይ ያሉ ሁሉ ለኑሯቸው አቅማቸው በሚፈቅደው ሁኔታ የሚያወጡ ቢሆኑም ከሚያገኙት በላይ ለመክፈል ግን ፈጽሞ ወደ ብድር አያመሩም፡፡

በባለወለድ ባንኮች ውስጥ ሂሳብ ቁጥር ያላቸው ሰዎች ከባንክ የሚያገኙት ወለድ የራሳቸው ገንዘብ ወይም ሕጋዊ ንብረታቸው አይደለም፡፡ ስለሆነም ከዚህ የተወገዘ ተግባር ለመላቀቅ በአቅራቢያቸው ወለድ አልባ ባንኮች የሚገኙ ከሆነ ወደነርሡ በመሄድ አገልግሎት ማግኘት ይኖርባቸዋል፡፡

አላህ ወለድን ከማስጠንቀቁ በተጨማሪ በብርቱ አውግዟል፡፡ እንዲህ ይላል፡- እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አራጣን የተነባበሩ እጥፎች ሲሆኑ አትብሉ፡፡ ትድኑም ዘንድ አላህን ፍሩ፡፡ (አለ ዒምራን፡ 130)

ምክር፡- (ነሲሃ)

ራስን ለመደገፍ ስትል ትምህርትህን ወይም ሙያህን

ተከታተል፡፡ ምስኪን ለሆኑት በየጊዜው ምጽዋት (ሰደቃ)

በመስጠት ለሀብትህ በረከትን አምጣ፡፡

አቅምህ በፈቀደው መጠን ያለብህን ብድር ቶሎ ለመክፈል

እቅድ አውጣ፡፡ እነዚህ ብድሮች ሙስሊም ከመሆንህ በፊት

የወሰድካቸው ቢሆን እንኳን ከመክፈል ወደ ኋላ አትበል፡፡

የአላህ መልዕክተኛን (ሶ.ዐ.ወ) ለአስር ዓመታት አገልግያለሁ፡፡ አንድ ቀንም እኔ የሚያስከፋ ቃል ተናግረውኝ አያውቁም፡፡ እንዲሁም ይህን ለምን ስራህ ወይም ይህን ለምን አልሰራህም በማለት ጠይቀውኝ አያውቁም፡፡ — ሰሐቢዩ አነስ (ረ.ዐ)

Page 117: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - zhic.aeኢስላም፣ ኢማን እና ኢሕሳን 3 አጠቃላይ እይታ 4 መግቢያ 6 የጉዞ መመሪያ 6 ለጉዞ

መለኮታዊው መንገድ፡-የአዲስ ሙስሊሞች ስርዓተ ትምህርት100

ተፈጥሮ እና አከባቢያችን 25

የአላህ ምልክት

የሰው ልጅ የተፈጥሮና የቁርኣን ግንኙነት የኢስላም

ተፈጥሮ ባሕሪ መሠረት ነው፡፡ የቁርኣን አንቀጽ

«አያት» ወይም ምልክቶች ሲባሉ የተፈጥሮ መስህቦችና

ውበቶችም እንዲሁ «አያት» ይባላሉ፡፡

ወደዚያ በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ የርሱ ወደ

ኾነው አላህ መንገድ (ትመራለህ)፤ ንቁ! ነገሮቹ ሁሉ

ወደ አላህ ይመለሳሉ፡፡ (አሽ-ሹራ፡ 53)

አንድ ሰው በፍጥረተ-ዓለሙ የአላህን ተአምራት

በጥልቀት ሲያሰላስል ከተፈጥሮ ጋር ያለው ግንኙነት

ይበልጥ ሥር እየሰደደ ይሄዳል፡፡ አብዛኛዎቹ ይህን መሰሉ

ምልክቶቹን ከማንበብ ጋር በተዛመደ ተፈጥሮን ማድነቅ

ከአላህ ጋር ያለንን ግንኙነት ለማሳደግ እንደመነሻ

ይሆናል፡፡

የምድር ተተኪዎች (ኸሊፋዎች)

እንደ ተተኪነታችን እኛ ሰዎች የምድር ጠባቂዎች እና

ተንከባካቢዎች ነን፡፡ ምንም እንኳን ሁኔታ ስፍራና ከባድ

ኃላፊነቶችን የጨመረልን ቢሆንም እኛ የምድሪቷ ኃላፊዎችና

ጌቶች አይደለንም፡፡ የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ)

«ዓለም ጣፋጭና አረንጓዴ ነች፡፡ በርግጥ አላህ እናንተን

ምትክ (ኸሊፋ) በማድረግ ምን እንደምትሠሩ

ይመለከታችኋል ብለዋል፡፡»88

እንደ ምድር ጠባቂነታችንና ተንከባካቢነታችን የተፈጥሮ

ሃብቷን በአስተዋይነት መጠቀምና ስነ- ምህዳራዊ

ሚዛኗን በመጠበቅ ለቀጣዩ ትውልድ እንድናስተላልፍ

ኃላፊነት ተጥሎብናል፡፡

አላህ እንዲህ ብሏል፡-

አር-ረሕማን፤ ቁርኣንን አስተማረ፡፡ ሰውን

ፈጠረ፡፡ መናገርን አስተማረው፡፡ ፀሐይና ጨረቃ

በተወሰነ ልክ (ይኼዳሉ)፤ ሐረግና ዛፍም (ለርሱ)

ይሰግዳሉ፡፡ ሰማይንም አጓናት፤ ትክክለኛነትንም

ደነገገ፡፡ በሚዛን (ስትመዝኑ) እንዳትበድሉ፡፡ (አር-

ራሕማን፡ 1-8)

አካባቢን መንከባከብ

አላህ እንዲህ ብሏል፤

ከተንቀሳቃሽም በምድር (የሚኼድ)፤ በሁለት

ክንፎቹ የሚበርም በራሪ መሰሎቻችሁ ሕዝቦች እንጅ

ሌላ አይደሉም፤ (አል አንዓም፡ 38)

የምድር ምትክነታችንን ኃላፊነቶች ለመወጣት

በአካባቢያዊ ሕግ አነሳሽነት ላይ መመካት የለብንም

በአንፃሩ በመለኮታዊው ደንብ በተጠቀሡ ሕጎችና

በነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ነብያዊ አስተምህሮዎች ላይ

መመርኮዝ አለብን፡፡ ከመጠን ያለፈ አጠቃቀምንና

ስግብግብነት አስጠንቅቆናል፡፡

ምክንያቱም ሁኔታው ወደ አካባቢያዊና መንፈሳዊ

መቆርቆዝ ስለሚያመራ ነው፡፡ አላህ እንዲህ ይላል፡-

«የሰዎች እጆች በሠሩት ኀጢኣት ምክንያት የዚያን

የሠሩትን ከፊሉን ያቀምሳቸው ዘንድ መከራው

በየብስና በባሕር ተገለጠ፤ (ተሰራጨ)፤ እነርሱ

ሊመለሱ ይከጀላልና፡፡» (አር-ሩም፡ 41)

በምድራችን ላይ የሚኖሩ ሕይወት ያላቸው ፍጥረታትም

መብቶች አሏቸው፡፡ የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ)

«ለእንስሳት መልካም መዋል ምንዳ ያስገኛልን?»

ተብለው ሲጠየቁ «ሕይወት ላለው ማንኛውም ፍጡር

መልካም መዋል ምንዳ ያስገኛል» 89 በማለት መልሰዋል፡፡

የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) በሞቃት ወቅት በውሃ

ጥም ወንዝ ዳር ቆሞ ሲያለከልክ ለነበረ ውሻ ምንጭ

ውስጥ ወርዶ በጫማው ውሃ በመቅዳት ያጠጣውንና

በዚህም ሳቢያ አላህ ኃጢአቶቹን የማረለትን ሰው ታሪክ

Page 118: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - zhic.aeኢስላም፣ ኢማን እና ኢሕሳን 3 አጠቃላይ እይታ 4 መግቢያ 6 የጉዞ መመሪያ 6 ለጉዞ

101ክፍል 4፡- መብቶች እና ኃላፊነቶች

ለሰሐቦቻቸው (ባልደረባዎቻቸው) ነግረዋቸዋል፡፡

እንዲሁም ድመቷን አስራ ምግብን የከለከለቻትን ሴት

በዚህ ድርጊቷ ምክንያት አላህ እንደቀጣት ነግረዋቸዋል፡፡፡

ምክር (ነሲሃ)

የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፤ «ንጽሕና

የእምነት አጋማሽ ነው»90 ስለዚህ ንጽሕና በአለባበሳችን

በገጽታችን በመኖሪያችንና በተፈጥሯዊ አካባቢያችን ሊገለጽ

ይገባል፡፡

ሥነ- ሕይወትን የሚያዛቡ ዘዴዎችን አጠቃቀም በመቀነስ

አካባቢህን ጠብቅ፡፡ አስፈላጊ ከሆነ ከአካባቢህ የሚገኝን

ምግብ ግዛ ፡፡

ወደ ተፈጥሮ አካባቢዎችና መናፈሻዎች በመሄድ ከተፈጥሮ

ጋር ያለህን ግንኙነት አጠናክር፡፡

የሰዎች እጆች በሠሩት ኀጢኣት ምክንያት የዚያን የሠሩትን ከፊሉን ያቀምሳቸው ዘንድ መከራው በየብስና በባሕር

ተገለጠ፤ (ተሰራጨ)፤ እነርሱ ሊመለሱ ይከጀላልና፡፡ —(አር-ሩም፡- 41)“

Page 119: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - zhic.aeኢስላም፣ ኢማን እና ኢሕሳን 3 አጠቃላይ እይታ 4 መግቢያ 6 የጉዞ መመሪያ 6 ለጉዞ

መለኮታዊው መንገድ፡-የአዲስ ሙስሊሞች ስርዓተ ትምህርት102

የወደፊቱ ጉዞ በመንገዱ ላይ መቀጠል

ይህ መጽሐፍ እስልምናን ሰፋ ባለ ሁኔታ አቅርቧል፡፡ የመንገዱንም አጠቃላይ ካርታ እንዲሁ ምንም እንኳን አንተ የመጀመሪያውን እርምጃ የተራመድክ ቢሆንም ይህ ጉዞህ ወደ ዘላለማዊው ሕይወት የሚያደርስህ መሆኑን አስተውል፡፡

አዲስ ሙስሊም እንደመሆንህ አሁንም መማርና መተግበር ያለብህ በርካታ ነገሮች አሉ፡፡ ይህ ደግሞ ታታሪነትን፣ ትዕግስትን ስነ-ምግባርንና፣ ሳይታክቱ መከታተልን በተለይም አላህን ለማግኘት መጓጓትን ይጠይቃል፡፡እውቀት መፈለጋችሁን ስትቀጥሉና በእምነታችሁ ስትጎለብቱ በመለኮታዊው ሕግ ውስጥ ጥልቀት ያላቸው ደረጃዎች እንዳሉ ትረዳላችሁ፡፡የሃይማኖቱ ምሶሶዎች፣ የእምነት ማዕዘናት፣ የአምልኮታዊ ተግባራት ደረጃ፣ ሞራላዊና ስነ- ምግባራዊ እሴቶች ማንኛውም ሙስሊም

ሊያውቃቸው የሚገባ ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ናቸው፡፡ ከዚህ ሌላ ሙስሊም ምሁራን በጋራ ያልተስማሙባቸው በርካታ ጥልቅ ጉዳዮች አሉ፡፡ እነዚህ አለመስማማቶች (አለመግባባቶች) አስፈላጊ የሆኑ የሃሳብ ነጻነቶችና እዝነቶች ናቸው፡፡

ስለሆነም ጉዳት የሌላቸው እስከሆኑ ድረስ ልናከብራቸው ይገባናል፡፡ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡-«አንድ ምሁራዊ ጥረት የሚያደርግ (ሙጅተሂድ) ሰው በአንድ ነገር ዙሪያ ብያኔ (ፈትዋ) አስተላልፎ ትክክለኛ ከሆነ ሁለት ምንዳዎች አሉት፡፡ ብያኔው ስህተት ከሆነ አንድ ምንዳ አለው፡፡»91ቀጥላችሁ ደግሞ የምትማሩትን የዕውቀት ዘርፍ ስትመርጡ በቀጥታ በእናንተ ላይ ግዴታ የሚሆኑ ተግባራት ላይ አተኩሩ፡፡ ለምሳሌ የእምነትን (ኢማንን) መሠረቶች ጠንቅቃችሁ ማወቃችሁንና

Page 120: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - zhic.aeኢስላም፣ ኢማን እና ኢሕሳን 3 አጠቃላይ እይታ 4 መግቢያ 6 የጉዞ መመሪያ 6 ለጉዞ

103በመንገዱ ላይ መቀጠል

አምልኮታዊ ተግባራት የሆኑትን አምስቱን ግዴታዎች ጨምሮ ውዱእ ማድረግ፣ ሶላትና ፆምን በተመለከተ በቂ ዕውቀት መያዛችሁን እርግጠኛ መሆን ይጠበቅባችኋል፡፡

አንዴ በእነዚህ የአምልኮ ተግባራት ዙሪያ ጥንካሬ ካላችሁ ከዚህ በኋላ ሌሎቹን ግዴታ የሆኑ የአምልኮ ተግባራትን መማር ለምሳሌ ሐጅንና እምነታችሁን (ኢማናችሁን) የሚያጠናክሩላችሁን ትምህርቶች የቁርኣን ንባብ ሐዲስና የነቢዩን (ሰ.ዐ.ወ) የሕይወት ታሪክ ሲራ እንዲሁም ዐረብኛ ቋንቋን ማወቅ ትችላላችሁ፡፡የሚቀጥለውን ደረጃ ቀላል ለማድረግ ተጨማሪ የማጠቀሻ መጽሐፍት ዝርዝር በዚህ መጽሐፍ መጨረሻ ላይ ተካትቷል፡፡ እንደ አዲስ ሙስሊም በማህበረሰባችሁ

ውስጥ የሚገኙ ኢስላማዊ ትምህርቶችን፣ ምክሮችን ሃይማኖታዊ የቡድን ጥናቶችን መከታተል ለጥያቄዎቻችሁ አጥጋቢ ምላሽ ሊሰጧችሁ የሚችሉ ብቃት ያላቸውን ሙስሊም ምሁራን መቅረብ ይጠበቅባችኋል፡፡

በስተመጨረሻ የዚህ መጽሐፍ አዘጋጆችና አርታኢያን በቀሰማችሁት ትምህርት ትጠቀሙ ዘንድ ዘወትር ዱአ ያደርጉላችኋል፡፡

(ለአመነች ነፍስም) አንቺ የረካሺው ነፍስ ሆይ! ወዳጅ ተወዳጅ ሆነሽ ወደ ጌታሽ ተመለሺ ፡፡ በባሮቼም ውስጥ ግቢ ገነቴንም ግቢ (ትባላለች) (አል- ፈጅር፡ 27-30)

የሰው ልጅ ሆይ! እኔን ብቻ እስከጠራኸኝና እስከጠየከኝ ድረስ የሰራኸውን ሃጢአት በሙሉ እምርልሃለሁ…፡፡ —ሐዲስ አል-ቁድስ“

Page 121: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - zhic.aeኢስላም፣ ኢማን እና ኢሕሳን 3 አጠቃላይ እይታ 4 መግቢያ 6 የጉዞ መመሪያ 6 ለጉዞ

መለኮታዊው መንገድ፡-የአዲስ ሙስሊሞች ስርዓተ ትምህርት104

ለይለቱል ቀድር፣ እድል ሁሉ የሚወሰንባትና ቁርኣን ለመጀመሪያ ጊዜ የወረደባት የተከበረች ሌሊት፡፡ እንደ ብዙሃኑ

ምሁራን ሃሳብ ይህች ቀን ከረመዳን የመጨረሻ አሥር ቀናት መካከል ትገኛለች፡፡

ሐዲስ፡- በትክክለኛ ሁኔታ የተዘገበ የሆነ የነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ንግግር ወይም ተግባር ሲሆን ሁለተኛው

የኢስላማዊ ሕግ ምንጭ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡

ሐዲሰል አል ቁድሲ፡- በትክክል የተዘገበና በነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) አንደበት የተገለጸ የአላህ (ሱ.ወ) ንግግር፡፡ ሲሆን

ከቁርዓን የተለየ መለኮታዊ ራዕይ መሆኑም ይታወቃል፡፡

ሐጅ፡- መካ ውስጥ የሚገኘውን የአላህ ቤት (ካዕባ) የመጎብኘት ሥርዓት፡፡

ሐላል፡- በኢስላማዊው ሕግ ፍጹም የተፈቀደ ነገር ወይም ተግባር፡፡

ሐራም፡- በኢስላማዊው ሕግ ፍጹም የተከለከለ ነገር ወይም ተግባር፡፡

ሐያእ፡- ትህትና (አይን አፋርነት)፡፡

ሐያት፡- መለኮታዊ ሕይወት፡፡

መዝሃብ፡- በኢስላማዊው የፊቅህ እናት ተቀባይነት ያለው የሕግ ትምህርት ቤት፡፡

መዲና፡- ከመካ በስተ ሰሜን በኩል የምትገኝና ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) የተሰደዱበት የዐረቢያ ከተማ፡፡

መሕረም፡- ተቃራኒ ፆታ ሆኖ ከርሱ ጋር ጋብቻ ልንፈጽም የማንችል የሆነ ሰው ለምሳሌ ወላጆች ለልጆች ወንድምና

እህት ወዘተ..

መንዱብ፡- በኢስላማዊው ሕግ የሚበረታታ ተግባር፡፡

መርዋ፡- በሐጅ ወቅት ሰዎች ከሚሮጡባቸው ሁለት ኮረብታዎች አንዱ፡፡

ሚና፡- ሐጅ የሚፈጽሙ ሰዎች ጠጠሮችን የሚወረውሩበት ስፍራ፡፡

መስጂድ፡- የሙስሊሞች አምልኮ ስፍራ ፡፡

መካ፡- ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) የተወለዱባት ዐረቢያ ውስጥ የምትገኝ ከተማ፡፡

ሙባሕ፡- በኢስላማዊው ሕግ የተፈቀዱ ተግባራት፡፡

ሙአዚን፡- ወደ ሶላት ጥሪ የሚያደርግ ሰው፡፡

ሙጅተሂድ፡-በጣም ጥልቅ እውቀት የተላበሰና ከኢስላማዊ የሕግ ምንጮች የሕግ ጽንሰ ሃሳቦችን የማውጣት ብቃት

ያለው ሰው፡፡

ሙከልለፍ፡-ግዴታ የሆኑ ሃይማኖታዊ ተግባራትን የመፈፀም ግዴታ ያለበትና ባይፈጽም በኃላፊነት ተጠያቂ የሚሆን

(ለአቅመ አዳም) ሔዋን የደረሰ ግለሰብ፡፡

የቃላት መፍቻ

Page 122: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - zhic.aeኢስላም፣ ኢማን እና ኢሕሳን 3 አጠቃላይ እይታ 4 መግቢያ 6 የጉዞ መመሪያ 6 ለጉዞ

105የቃላት መፍቻ

ረጃእ፡- መለኮታዊውን ምህረት የማግኘት ተስፋ፡፡

ረመዳን፡-በኢስላማዊ የዘመን አቆጣጠር ቀመር የተከበረ፣ ነብዩ ሙሐመድ( ሰ.ዐ.ወ) ለመጀመሪያ ጊዜ

መለኮታዊ ራዕይ የተቀበሉበትና ሙስሊሞች ከንጋት እስከ ፀሐይ መጥለቅ ጊዜ ድረስ ከምግብ፣ ከመጠጥና ከስጋዊ

ፍላጎት ተቆጥበው የሚፆሙት ወር፡፡

ረውዳ፡- በነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) መስጂድ ውስጥ በእርሳቸው መካነ- መቃብርና በመስበኪያ ሰገነታቸው

(ሚንበራቸው) መካከል የሚገኝ ስፍራ፡፡

ሰብር፡- ትዕግስት፡፡

ሰደቃ፡- በፍላጎት የሚሰጥ ምጽዋት፡፡

ሰፋ፡- በሐጅ ወቅት ሰዎች ከሚሮጡባቸው ኮረብታዎች አንዱ፡፡

ሶላህ፡- ሃይማኖታዊ ስግደት ከአምስቱ የኢስላም ማዕዘናት መካከል አንዱና በሁለተኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ የአምልኮ

ተግባር፡፡

ሰሚዕ፡- የመለኮታዊው ሃይል የመስማት ችሎታ መገለጫ ሲሆን ትርጉሙ የሚሰማ ማለት ነው፡፡

ፆም፡- ከንጋት እስከ ፀሐይ ግባት መፆም፡፡ በረመዳን ወር መፆም ከአምስቱ የኢስላም ምሶሶዎች አንዱ ነው፡፡

ሸሀዳህ፡- ከአላህ በስተቀር አምልኮ የሚገባው አምላክ የለም ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) የአላህ መልዕክተኛው

ናቸው ብሎ የምስክርነት ቃል መስጠት፡፡

ሸሪዓ፡- ኢስላማዊ ሕግ፡፡

ሸይኽ፡- ለኢስላም ምሁር የሚሰጥ አጠቃላይ የሆነ የማዕረግ ስም፡፡

ሲድቅ፡- እውነት

ሺርክ፡- በአላህ (ሱ.ወ) ላይ የማጋራት ተግባር፡፡

አስ-ሲፋህ አን ነፍሲያህ፡- አላህ (ሱ.ወ) መኖሩን የሚያረጋግጡ የግሉ መገለጫዎች፡፡

ሲራ፡- የነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) የሕይወት ታሪክ፡፡

ሱንና፡- የነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ፈለግ፣ አስተምህሮ፣ ተግባር ቢሠራ ለሠራው ምንዳ የሚያስገኘ ባይፈጸም

የማያስጠይቅ ንግግርና ድርጊት፡፡

ሱራ፡- የቁርኣን ምዕራፍ፡፡

Page 123: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - zhic.aeኢስላም፣ ኢማን እና ኢሕሳን 3 አጠቃላይ እይታ 4 መግቢያ 6 የጉዞ መመሪያ 6 ለጉዞ

መለኮታዊው መንገድ፡-የአዲስ ሙስሊሞች ስርዓተ ትምህርት106

ቀደር፡- መለኮታዊ እጣ ፋንታ፡፡

ቂብላ፡- ሶላት በሚሰገድበት ወቅት ወደርሱ መዞሩ ግድ የሆነ የካዕባ አቅጣጫ፡፡

ቀዲም፡- ከአላህ ባሕሪያት አንዱ ሲሆን ለዘመኑ መጀመሪያ የሌለው ማለት ነው፡፡

ቂያም ቢን ነፍስ፡- ከአላህ ባሕሪያት አንዱ ሲሆን በራሱ የተብቃቃ ማለት ነው፡፡

ቂያስ፡- በቀጥታ ሃይማኖታዊ ብይን ለማይሰጥበት ጉዳይ ከርሱ ጋር በይዘትና በባህሪ ከተመሳሰለና የሁለተኛው

ብይን ከሁለቱ የሕግ ምንጮች በአንዳቸው ከተጠቀሰ የዚህን ብይን ከሌላው ጋር በማጣመር አንድ ዓይነት ብይን

መስጠት፡፡

ቁድራ፡- የመለኮታዊው ሃይል ችሎታ መገለጫ ባሕሪ፡፡

ቁርኣን፡- የኢስላም ቅዱስ መጽሐፍ፡፡ የአላህ (ሱ.ወ) ንግግርና፣ በጅብሪል (ዐ.ሰ) አማካይነት ወደ ነብዩ

ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) የወረደ፡፡

አል በቂዕ፡- የነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ቤተሰቦችና ከባልደረቦቻቸው ብዙዎቹ (ረ.ዐ) የተቀበሩበት መዲና ከተማ

ውስጥ የሚገኝ መካነ መቃብር፡፡

በስመላህ፡- ሙስሊሞች ማንኛውንም እንቅስቃሴዎቻቸውን የሚጀምሩበት ሐረግ «በአላህ ስም እጅግ በጣም

ሩሕሩህ በጣም አዛኝ በኾነው» እንዲል ቁርዓን፡፡

በሲር፡- የመለኮታዊውን ኃይል የማየት ባሕሪ የሚገልጽ ስያሜ

ተብሊግ ፡- ማስተላለፍ (መልዕክት ማድረስ)፡፡

ተሐጁድ፡- ከእኩለ ሌሊት ጀምሮ ጎሕ እስኪወጣ ድረስ በፍላጎት የሚሰገድ ሶላት፡፡

ተክቢር፡- «አላህ እጅግ በጣም ትልቅ ነው» ብሎ ማወጅ

ተቅዋ ፡- የአላህ ፍራቻ፡፡

ተራዊሕ፡- በረመዷን ከዒሻ ሶላት በኋላ በሕብረት የሚሰገድ ሱና ሶላት፡፡

ጠዋፍ፡- በሐጅ ሥነ- ሥርዓት ወቅት ካዕባን መዞር፡፡

ተውባህ፡- ከኃጢአት ለመጽዳት (ንሰሃ) መግባት፡፡

ተውሒድ፡- የአላህ (ሱ.ወ)ን ብቸኛነትና አንድነት ማረጋገጥ፡፡

ነሲሐ፡- ምክር፡፡

ኒሳብ፡- ድርሻ (መጠን)፡፡

Page 124: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - zhic.aeኢስላም፣ ኢማን እና ኢሕሳን 3 አጠቃላይ እይታ 4 መግቢያ 6 የጉዞ መመሪያ 6 ለጉዞ

107የቃላት መፍቻ

አዳብ፡- ሥነ- ሥርዓት፡፡

አዛን፡- ወደ ሶላት የሚደረግ ጥሪ፡፡

አ.ሂ፡- እንደ ሂጅሪያ ዘመን አቆጣጠር፡፡

አማና፡- አደራ፡፡

አንሷር፡- ረዳቶች ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ወደ መዲና በስደት በሄዱ ጊዜ የረዷቸው የመዲና ሰዎች መጠሪያ፡፡

አረፋት፡- መካ ውስጥ የሚገኝ ተራራ፡፡

ዐውራህ፡- ሐፍረት ገላ፡፡

አያት፡- የቁርኣን አንቀጽ አላህ መኖሩን የምናውቅበት ማንኛውም ነገርና ክስተት፡፡

ኸሊፋ፡- ከነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ሞት በኋላ የነበረ የሙስሊሞች መሪ እንዲሁም በምድር ላይ ተተኪ፡፡

ወሕደኒይያህ፡- የአላህ (ሱ.ወ) ፍጹም የብቸኝነት ባህሪ፡፡

ዘካት፡- ግዴታ የሆነ ምጽዋት፡፡ በዓመት ከአጠቃላይ ሀብት መካከል ዓመት ከደፈነው 2.5 ከመቶ የሚሆነው

ተሰልቶ ለድሆች የሚሰጥ የሆነና ከኢስላም ምሶሶዎች አንዱ፡፡

ዘካቱ-ል-ፊጥር፡- በረመዳን ወር በመጨረሻ አካባቢ ጀምሮ የኢድ ሶላት እስኪሰገድ ድረስ ለድሆች የሚሰጥ

ምጽዋት፡፡

ዘምዘም፡-መካ ውስጥ የሚገኝ ተአምራዊ ምንጭ፡፡

ዚክር፡- አላህን ማስታወስ፡፡

ዱዓ፡- ጸሎት ወይም ስግደት፡፡

ጀናዛ፡- የሞተ ሰው አካል (አስክሬን)፡፡

ጂን፡- በአብዛኛው ለሰዎች በዓይን የማይታዩ እንደ ሰው ልጅ ሁሉ ለሥሯቸው ሥራዎች ተጠያቂዎች የሆኑ

ሙስሊምና ሙስሊም ያልሆኑ ወገኖች የሚገኙባቸው ከእሳት የተፈጠሩ ፍጡራን፡፡

ጀሙዐህ፡- በእለተ ዐርብ በሕብረት የሚፈጸም ስግደት

Page 125: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - zhic.aeኢስላም፣ ኢማን እና ኢሕሳን 3 አጠቃላይ እይታ 4 መግቢያ 6 የጉዞ መመሪያ 6 ለጉዞ

መለኮታዊው መንገድ፡-የአዲስ ሙስሊሞች ስርዓተ ትምህርት108

ፈርድ፡- ግዴታ፡፡

ፈጣናህ፡- አእምሯዊ ክህሎት፡፡

ፊጥራ፡- ሁሉም የሰው ልጅ የሚወለድበት ተፈጥሯዊ ንጽህና፡፡

ኢፍጣር፡- ፆምን መግደፍ (መፈሰክ)፡፡

ኢሕራም፡- ስፌት የሌለውን ጨርቅ በሐጅ ጸሎት ሥነ-ሥርዓት ወቅት መልበስና ከሐጅ ሥርዓቶች አንዱ የሆነ፡፡

ኢሕሳን፡- ማሳመር፡፡

ኢጅማዕ፡- ብቃትና ጥልቅ እውቀት ያላቸው ሙስሊም ሊቃውንት በአንድ ጉዳይ ላይ የሚያሳዩት የጋራ ስምምነት

ሲሆን ከኢስላማዊ ሕግ ምንጮች አንዱ፡፡

ኢኽላስ፡- የጠራ እሳቤ (ኒያ)፡፡

ዒልም፡- እውቀት፡፡

ኢማም፡- በሕብረት የሚፈፀምን ሶላት የሚመራ ሰው፡፡

ኢማን፡- እምነት ወይም አላህና መልዕክተኛው (ሰ.ዐ.ወ) ባመጡት ነገር ማመን፡፡

ኢራዳህ፡- መለኮታዊ ፍላጎት (መሻት)፡፡

ኢስላም፡- አላህ ለነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ያወረደውና ለሰው ዘር በሙሉ እስከ ዓለም ፍፃሜ የሚያገለግል

ሃይማኖት ፡፡

ኢስቲኻራህ፡- አንድ ሰው በሁለት ጉዳዮች መካከል መወሰን አቅቶት በሚያወላውልበት ጊዜ መለኮታዊ ምሪት

ለማግኘት የሚሰገድ ሶላት፡፡

Page 126: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - zhic.aeኢስላም፣ ኢማን እና ኢሕሳን 3 አጠቃላይ እይታ 4 መግቢያ 6 የጉዞ መመሪያ 6 ለጉዞ

109

Page 127: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - zhic.aeኢስላም፣ ኢማን እና ኢሕሳን 3 አጠቃላይ እይታ 4 መግቢያ 6 የጉዞ መመሪያ 6 ለጉዞ

መለኮታዊው መንገድ፡-የአዲስ ሙስሊሞች ስርዓተ ትምህርት110

የቁርኣን ትርጉሞች

The Holy Qurʾan: Text, Translation and Commentary. Abdullah Yusuf Ali. Tahrike Tarsile Quran Inc., 1987.

The Qurʾan: A New Translation. Thomas Cleary. Starlatch Press, 2004.

The Noble Qurʾan: A New Rendering of its Meaning in English. Abdalhaqq and Aisha Bewley. Bookwork, 2006.

Tafsir al-Jalalayn: Complete English Translation. Aisha Bewley. Dar al Taqwa Ltd., 2008.

የሐዲስ ትርጉሞች

Forty Hadith. Yahya Ibn Sharaf al-Din al-Nawawi, Translated by Ezzeddin Ibrahim and Denys Johnson-Davies. Dar El-Shorouk, 2002.

Al-Muwatta of Imam Malik ibn Anas. Aisha Bewley. Medina Press, 1989.

The Content of Character: Ethical Sayings of the Prophet Muhammad s. Shaykh Al-Amin Ali Mazrui, Hamza Yusuf. Sandala LLC, 2005.

Provision for the Seekers, a Manual of Prophetic Hadiths with Commentary. Abdur-Rahman Ibn Yusuf. White Thread Press, 2005

The Book of Hadith: Sayings of the Prophet Muhammad from the Mishkat al Masabih. Charles Le Gai Eaton & Jeremy Henzell-Thomas. The Book Foundation, 2008.

The Seventy-Seven Branches of Faith. Imam al-Bayhaqi, translated by Abdal-Hakim Murad. The Quilliam Press, 1990.

በነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ዙሪያ የተዘጋጁ መጸሐፍት

Muhammad: His Life Based on the Earliest Sources. Martin Lings (Abu Bakr Siraj ad-Din). Inner Traditions International, 1983.

Muhammad Messenger of Allah, Ash-Shifa of Qadi ‘Iytd. Aisha Bewley. Madinah Press, 1991.

Our Master Mu^ammad s. Abdallah Sirajuddin al-Husayni. Sunni Publications, 2008.

A Day With the Prophet s. Ahmad Von Denffer. The Islamic Foundation, 1979.

እንዲያነቡ የሚመከሩ መጽሃፎች

Page 128: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - zhic.aeኢስላም፣ ኢማን እና ኢሕሳን 3 አጠቃላይ እይታ 4 መግቢያ 6 የጉዞ መመሪያ 6 ለጉዞ

111እንዲያነቡ የሚመከሩ መጽሃፎች

በአምስቱ የእስልምና መሠረቶች ላይ የተዘጋጁ መጽሐፎች

Inner Dimensions of Islamic Worship. Abu Hamid al-Ghazali, translated by Muhtar Holland. The Islamic Foundation, 1992.

Al-Maqasid: Nawawi’s Manual of Islam. Nuh Ha Mim Keller. Amana Publications, 2002.

Understanding the Four Madhhabs: The Facts About Ijtihad and Taqlid. Abdal-Hakim Murad. Islamic Publications International, 1999.

The Absolute Essentials of Islam. Faraz Fareed Rabbani. White Thread Press, 2008.

One Thousand Roads to Mecca. Michael Wolfe. Grove Press, 1997.

Instruction of the Student: The Method of Learning. Burhan al-Din al-Zarnuji. The Starlatch Press, 2001.

Submission: Faith and Beauty. Dr. Joseph Lumbard. Zaytuna Institute, 2008.

Islam and the Destiny of Man. Charles Le Gai Eaton. The Islamic Texts Society, 1985.

The Heirs of the Prophet. Ibn Rajab al-Hanbali, translated by Zaid Shakir. Starlatch Press, 2001.

Principles of Islamic Jurisprudence. Mohammad Hashim Kamali. The Islamic Foundation, 2005.

በኢማን ዙሪያ የተዘጋጁ መጽሐፍት

The Lives of Man. Imam ʿAbdallah ibn ʿAlawi al-Haddad, translated by Mostafa al-Badawi. The Quilliam Press Limited, 1991.

Key to the Garden. Ahmad Mashhur al-Haddad, translated by Mostafa al-Badawi. Starlatch Press, 2003.

The Creed of Imam Al-TahtwÏ.. Abu Jaʿfar al-Tahawi, translated by Hamza Yusuf. Zaytuna Institute, 2007.

Al-Ghazali On the Ninety-Nine Beautiful Names of God. Abu Hamid al-Ghazali, translated by David Burell. The Islamic Texts Society, 1992.

በኢሕሳን ዙሪያ የተዘጋጁ መጽሐፍት

Two Treatises On Mutual Reminding & Good Manners. Imam ʿAbdallah ibn ʿAlawi al-Haddad, translated by Mostafa al-Badawi. Starlatch Press, 2002.

The Book of Assistance. Imam ʿAbdullah ibn ʿAlawi al-Haddad, translated by Mostafa al-Badawi. The Quilliam Press Limited, 1998.

Purification of the Heart. Hamza Yusuf. Starlatch Press, 2004.

Wayfarers to God. Habib ʿAli Zain Al ʿAbideen Al Jifri, translated by Shaykh Mohamed Mlamali Adam. Guidance Media, 2006.

Page 129: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - zhic.aeኢስላም፣ ኢማን እና ኢሕሳን 3 አጠቃላይ እይታ 4 መግቢያ 6 የጉዞ መመሪያ 6 ለጉዞ

መለኮታዊው መንገድ፡-የአዲስ ሙስሊሞች ስርዓተ ትምህርት112

Treatise for the Seekers of Guidance. Abu al-Harith al-Muhasibi, translated by Zaid Shakir. NID Publishers, 2008.

Al-Ghazali On the Remembrance of Death & Afterlife. Abu Hamid al-Ghazali, translated by T.J. Winters. The Islamic Texts Society, 1989.

Al-Ghazali on Invocations and Supplications. Abu Hamid al-Ghazali, translated by Kojiro Nakamura. The Islamic Texts Society, 1990.

በግንኙነቶች ዙሪያ የተዘጋጁ መጽሐፍት

Islam Our Choice: Portraits of Modern American Muslim Women. Debra L. Dirks. Amana Publications, 2003.

On the Duties of Brotherhood. Abu Hamid al-Ghazali, translated by Muhtar Holland. The Overlook Press, 1993.

The Proper Conduct of Marriage in Islam. Abu Hamid al-Ghazali, translated by Muhtar Holland. Al-Baz Publishing Inc., 1998.

The Sun Is Rising In the West: New Muslims Tell About Their Journey to Islam. Muzaffar Haleem. Amana Publications, 2007.

Initiating and Upholding an Islamic Marriage. Hedaya Hartfort. Dar Al-Fath, 2007.

Your Islamic Marriage Contract. Hedaya Hartfort. Dar Al-Fath, 2007.

Motherhood in Islam. Aliah Schliefer. The Islamic Texts Society-USA, 1996.

Financial Transactions in Islamic Jurisprudence. Dr. Wahba al-Zuhayli. Dar al-Fikr, 2008.

Page 130: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - zhic.aeኢስላም፣ ኢማን እና ኢሕሳን 3 አጠቃላይ እይታ 4 መግቢያ 6 የጉዞ መመሪያ 6 ለጉዞ

113እንዲያነቡ የሚመከሩ መጽሃፎች

የድረ-ገጽ ምንጮች

ድረ-ገጾች ለአዲስ ሙስሊሞች

The Muslim Converts’ Association of Singapore: http://www.darul-arqam.org.sg

Easy Guide For New Muslims: http://www.dawanet.com/newmuslim

International Association For New Muslims: http://www.4newmuslims.org

Guide to Islam For New Muslims: http://www.islamicedfoundation.com/guide1.htm

Prayer Times: http://www.islamicfinder.org/

ጥያቄና መልስ ድረ-ገጾች ለሙስሊሞች

SunniPath: http://www.sunnipath.com/

Reading Islam: http://www.readingislam.com

IslamOnline.net: http://www.islamonline.net

Page 131: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - zhic.aeኢስላም፣ ኢማን እና ኢሕሳን 3 አጠቃላይ እይታ 4 መግቢያ 6 የጉዞ መመሪያ 6 ለጉዞ

መለኮታዊው መንገድ፡-የአዲስ ሙስሊሞች ስርዓተ ትምህርት114

1. ኢማም አል-ቡኻሪ፣ ሰሒሕ አል-ቡኻሪ2. አል-ዐስቀላኒይ ኢብን ሐጀር፣ ፈትሑ አል-ባሪ፡፡ በይት አል-አፍካር አድ-ደውሊያ፣ ቅጽ ፡ 1 ገጽ፡ 3243. ኢማም አል-ቡኻሪ፣ ሰሒሕ አል-ቡኻሪ4. ኢማም አሕመድ፣ ሙስነድ5. ኢማም ሙስሊም፣ ሰሒሕ ሙስሊም6. ኢብን ማጀህ፣ ሱነን7. ዝኒ ከማሁ8. ኢማም አት-ቲርሚዚይ፣ ሱነን9. አቡ ኑዐይም፣ ሂልያ አል-አውሊያእ10.ኢማም አል-ቡኻሪ፣ ሰሒሕ አል-ቡኻሪ11.ኢማም አሕመድ፣ ሙስነድ12.ዝኒ ከማሁ13.አቡ ዳዉድ፣ ሱነን14.ኢማም ሙስሊም፣ ሰሒሕ ሙስሊም15.ኢማም አት-ቲርሚዚይ፣ ሱነን16.አቡ ዳዉድ፣ ሱነን17.ኢማም አል-ቡኻሪ፣ ሰሒሕ አል-ቡኻሪ18.ዝኒ ከማሁ19.ዝኒ ከማሁ20.ኢማም ሙስሊም፣ ሰሒሕ ሙስሊም21.ዝኒ ከማሁ22.ኢማም አሕመድ፣ ሙስነድ23.ኢብን ማጀህ፣ ሱነን24.ኢማም ሙስሊም፣ ሰሒሕ ሙስሊም25.ኢማም አሕመድ፣ ሙስነድ26.ኢማም ዳረ አል-ቁጥኒይ፣ ሱነን27.ኢማም ሙስሊም፣ ሰሒሕ ሙስሊም28.ኢማም አል-ቡኻሪ፣ ሰሒሕ አል-ቡኻሪ29.ዝኒ ከማሁ30.ኢማም አድ-ዳረሚይ፣ ሱነን31.ኢማም አሕመድ፣ ሙስነድ32.ኢማም አት-ቲርሚዚይ፣ ሱነን33.ኢማም አል-ቡኻሪ፣ ሰሒሕ አል-ቡኻሪ

34.ኢማም አል-በገዊይ፣ መዓሊም አት-ተንዚል35.ኢብን ማጀህ፣ ሱነን36.ዝኒ ከማሁ37.ኢማም አሕመድ፣ ሙስነድ38.ኢማም አት-ቲርሚዚይ፣ ሱነን39.ኢብን ሒብባን፣ ሰሒሕ ኢብን ሒብባን40.ኢማም አል-ቡኻሪ፣ ሰሒሕ አል-ቡኻሪ41.ኢማም አት-ቲርሚዚይ፣ ሱነን42.ኢማም አሕመድ፣ ሙስነድ43.ኢማም ሙስሊም፣ ሰሒሕ ሙስሊም44.ዝኒ ከማሁ45.ኢማም አሕመድ፣ ሙስነድ46.ኢብን ማጀህ፣ ሱነን47.ኢማም አት-ቲርሚዚይ፣ ሱነን48.ኢማም አል-ቡኻሪ፣ ሰሒሕ አል-ቡኻሪ49.ኢማም ሙስሊም፣ ሰሒሕ ሙስሊም50.ኢማም አል-ቡኻሪ፣ ሰሒሕ አል-ቡኻሪ51.ኢብን ማጀህ፣ ሱነን52.ኢማም አል-ቡኻሪ፣ ሰሒሕ አል-ቡኻሪ53.ዝኒ ከማሁ54.ኢማም ሙስሊም፣ ሰሒሕ ሙስሊም55.ኢማም አሕመድ፣ ሙስነድ56.ኢማም በይሀቂይ፣ ሱነን57.ኢማም አት-ቲርሚዚይ፣ ሱነን58.ዝኒ ከማሁ59.ኢብን ማጀህ፣ ሱነን60.ኢማም አል-ቡኻሪ፣ ሰሒሕ አል-ቡኻሪ61.ኢማም ሙስሊም፣ ሰሒሕ ሙስሊም62.ኢማም አል-ቡኻሪ፣ ሰሒሕ አል-ቡኻሪ63.ዝኒ ከማሁ64.ዝኒ ከማሁ65.ኢማም አት-ቲርሚዚይ፣ ሱነን66.ኢማም አል-ቡኻሪ፣ ሰሒሕ አል-ቡኻሪ

ህዳጎቸ

Page 132: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - zhic.aeኢስላም፣ ኢማን እና ኢሕሳን 3 አጠቃላይ እይታ 4 መግቢያ 6 የጉዞ መመሪያ 6 ለጉዞ

115ሕዳጎች

67.ኢማም አት-ቲርሚዚይ፣ ሱነን68.ኢማም አል-ቡኻሪ፣ ሰሒሕ አል-ቡኻሪ69.ኢብን ማጀህ፣ ሱነን70.ኢማም አት-ቲርሚዚይ፣ ሱነን71.ዝኒ ከማሁ72.ኢማም አል-ቡኻሪ፣ ሰሒሕ አል-ቡኻሪ73.ዝኒ ከማሁ74.ኢማም አት-ቲርሚዚይ፣ ሱነን75.ኢማም ሙስሊም፣ ሰሒሕ ሙስሊም76.ኢማም አል-ቡኻሪ፣ ሰሒሕ አል-ቡኻሪ77.ኢማም ሙስሊም፣ ሰሒሕ ሙስሊም78.ኢማም አል-ቡኻሪ፣ ሰሒሕ አል-ቡኻሪ79.ኢማም አሕመድ፣ ሙስነድ80.ኢማም አት-ቲርሚዚይ፣ ሱነን81.ኢማም አጥ-ጠበራኒይ፣ አል-ሙዕጀም82.ኢማም አል-ቡኻሪ፣ ሰሒሕ አል-ቡኻሪ83.ዝኒ ከማሁ84.ዝኒ ከማሁ85.ኢማም ሙስሊም፣ ሰሒሕ ሙስሊም86.ኢማም አል-በይሀቂይ፣ ሱነን87.ኢብን ማጀህ፣ ሱነን88.ኢማም ሙስሊም፣ ሰሒሕ ሙስሊም89.ኢማም አል-ቡኻሪ፣ ሰሒሕ አል-ቡኻሪ90.ኢማም ሙስሊም፣ ሰሒሕ ሙስሊም91.ዝኒ ከማሁ

Page 133: በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ - zhic.aeኢስላም፣ ኢማን እና ኢሕሳን 3 አጠቃላይ እይታ 4 መግቢያ 6 የጉዞ መመሪያ 6 ለጉዞ